በደቡብ ኢትዮጵያ አጥማቂው ፓስተር ዶጮ እሸቴ በአዞ ተገደሉ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

በደቡብ ኢትዮጵያ አጥማቂው ፓስተር ዶጮ እሸቴ በአዞ ተገደሉ

Postby ኳስሜዳ » Tue Jun 05, 2018 8:58 pm

Tweet
በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ በላንቴ ቀበሌ ልዩ ስሙ “መርከብ ጣቢያ” በተባለ ስፍራ ከሀይቅ ዳር ቆመው መንፈሳዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ የነበሩ ፓስተር በአዞ በደረሰባቸው ድንገተኛ ጥቃት ህይወታቸው ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የወረዳው ፖሊስ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

(BBC Amahric) — ፓስተር ዶጮ እሸቴ የተባሉት የሃይማኖት አባት እሁድ ጠዋት 2 ሠዓት ተኩል አካባቢ ቁጥራቸው በግምት ሰማኒያ አካባቢ የሆኑ ተከታዮቻቸውን በሃይቁ ውሃ እያጠመቁ በነበረበት ሰዓት አደጋው እንደደረሰባቸው አቶ ከተማ ካይሮ የተባሉ የከተማው ነዋሪ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

አቶ ከተማ ስለ ክስተቱ ሲያስረዱ ”አጥማቂው የመጀመሪያውን ሰው አጥምቀው ሁለተኛውን ማጥመቅ ሲጀምሩ አዞው በድንገት በመውጣት የሚጠመቀውን ሰው ገፍትሮ ሲጥለው አጥማቂውን ግን ጎትቶ ወደ ውሃው ይዞት ሄዷል” ብለዋል።

የወረዳው ፖሊስ ባልደረባ የሆኑት ዋና ሳጅን እውነቱ ካንኮ በበኩላቸው ክስቱት መፈጠሩን አረጋግጠው፤ በወቅቱ በአካባቢው የነበሩ ዓሳ አስጋሪዎችና ወጣቶች በአዞው ጥቃት የተፈፀመባቸውን ግለሰብ ከአዞው ለማስጣል ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ እንደቀረ ተናግረዋል።

ዋና ሳጅን እውነቱ ምንም እንኳን የፓስተሩን ህይወት ማዳን ባይቻልም የአካባቢው ማህበረሰብ የሟች አስከሬን ከአዞው ለማስጠል እንደተቻለ ጨምረው አስረድተዋል።

የሟቹ ፓስተር ዶጮ እሸቴ የቀብር ሥነ-ሥርዓትም ሰኞ እለት ተፈፅሟል።
Image
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2155
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Re: በደቡብ ኢትዮጵያ አጥማቂው ፓስተር ዶጮ እሸቴ በአዞ ተገደሉ

Postby ዘርዐይ ደረስ » Wed Jun 06, 2018 4:01 am

የዋርካ መስራቾች የተለያዩ መድረኮች ያዘጋጁልን የምናቀርባቸውን ፅሑፎች በተገቢው ቦታ እንድናደርጋቸው ነው።ታዲያ ይህ ዜና ከፖለቲካ ጋር ምን አገናኝቶት ነው እዚህ ያመጣኸው?
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1096
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: በደቡብ ኢትዮጵያ አጥማቂው ፓስተር ዶጮ እሸቴ በአዞ ተገደሉ

Postby ኳስሜዳ » Wed Jun 06, 2018 12:52 pm

ምነው ወንድም! አንዳንዴ እስደናቂ ነገር ምንቃኝ ከፖለቲካው እለም ወጥተን!!! ሁኔታው እኮ በጣም እስገራሚ ነው፡፡
ዘርዐይ ደረስ wrote:የዋርካ መስራቾች የተለያዩ መድረኮች ያዘጋጁልን የምናቀርባቸውን ፅሑፎች በተገቢው ቦታ እንድናደርጋቸው ነው።ታዲያ ይህ ዜና ከፖለቲካ ጋር ምን አገናኝቶት ነው እዚህ ያመጣኸው?
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2155
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Re: በደቡብ ኢትዮጵያ አጥማቂው ፓስተር ዶጮ እሸቴ በአዞ ተገደሉ

Postby ዘርዐይ ደረስ » Wed Jun 06, 2018 6:51 pm

ኳስሜዳ፦
የተግባባን አልመሰለኝም።ይህንን ዜና ለምን ዋርካ ላይ አመጣኸው ለማለት ፈልጌ አይደለም።እኔም እኮ ከፖለቲካ ውጭ የሆኑ ነገሮችን አቀርባለሁ።ግን በተቻለኝ መጠን በቦታው እንዲሆን እሞክራለሁ።ለምሳሌ ያንተ ዜና ዋርካ ጄኔራል ላይ የሚቀርብ ዓይነት ነው።
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1096
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Bing [Bot], Google [Bot] and 7 guests