የወያኔ ቅጥረኞች ሽፈራው ሽጉጤና አሽከሮቹ ደባ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የወያኔ ቅጥረኞች ሽፈራው ሽጉጤና አሽከሮቹ ደባ

Postby እሰፋ ማሩ » Thu Jun 14, 2018 11:55 pm

በሀዋሳ ውጥረቱ ቀጥሏል – ጸጥታ አስከባሪዎች ዝም እንዲሉ ተደርጓል።
June 14, 2018 – ምንሊክ ሳልሳዊ
በሀዋሳ ውጥረቱ ቀጥሏል። ጨንበላላን ለማክበር በወጣው ሕዝብ ላይ ሕወሓት ቅጥረኞቹን ሽፈራው ሽጉጤንና አሽከሮቹን አሰማርቶ በፈጠረው አምባጓሮ በርካታ ዜጎች ተጎድተዋል።
በሲዳማና በወላይታ መካከል ግጭት እንዲከሰት በሕወሃት ትእዛዝ የታጠቁ ሽፈራው ሽጉጤ ያሰማራቸው ካድሬዎች በፈጠሩት ችግር ምክንያት ግጭቱ ቀጥሎ ሰላማዊዋ ሀዋሳ በጥይት ስትናጥ ውላለች።
ጸጥታ አስከባሪዎች ዝም እንዲሉ ተደርጓል። ጸጥታ አስከባሪዎች የተሰማሩት ግጭቱ ካለበት ቦታ ይልቅ ባሌለበት ቦታ መሆኑን ታዛቢዎች ይናገራሉ። እነ ሽፈራው ሽጉጤ የህወሃት የእንጀራ ልጆች የዘሩት የዘረኝነት ውጤት ነው።በተለይም በወላይታውና ሲዳማው መካከል ግጭቱ ቀጥሏል።
በጉራጌ ክልልም ወልቂጤ ላይ በቀቤናና በጉራጌ መካከል ግጭት እንዲነሳ እሳቱን የለኮሱት ሽፈራው ሽጉጤ የላካቸው የታጠቁ ሐይሎች መሆናቸው ተረጋግጧል።
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1550
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests

cron