ህጋዊው ሲኖዶስ ለዶ/ር አብይ አመራር ድጋፍና አድናቆት ሰጠ

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

ህጋዊው ሲኖዶስ ለዶ/ር አብይ አመራር ድጋፍና አድናቆት ሰጠ

Postby እሰፋ ማሩ » Sun Jun 24, 2018 4:19 am

https://www.satenaw.com/amharic/wp-cont ... -1-1-2.pdf
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ከሚመራው በስደት ላይ ከሚገኘው ከሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ
ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ሰኔ 16/2010 የተሰጠ መግለጫ
በዛሬው ዕለት በሀገራችን ኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ እየታየ ያለው ደስታ መቸውንም
ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ፤ ወደፊትም ይሆናል ተብሎ የማይገመት ነገር ግን
በእውነት እግዚአብሔር ሕዝቡን የጎበኘበት ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ቀን ነው።
መሪው የሚመራውን ሕዝብ ወዶና አፍቅሮ ልቡን ለሕዝቡ ያስረከበበት ፤ ተመሪው
ሕዝብም መሪውን እንደ ገዥ ሳይሆን እንደ ወላጅ አባት ያየበት ታላቅ ቀን ዕለተ
ቀዳሚት ሰኔ 16 /2010።
በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይና በመላው አገራችን ክፍለ ከተማዎች እየታየ ያለው
የሕዝብ አንድነትና ፍቅር፤ እንዲሁም ለመሪያቸው የሚያቀርቡት ድጋፍ ጠቅላይ
ምኒስተር ዶክተር አቢይ አህመድንና ለዚህ ለውጥ ተግተው ለሚሠሩ
ባልደረቦቻቸውን የበለጠ ከሚመሩት ሕዝብ ጋር ልብ ለልብ የሚአስተሳስራቸው
ይሆናል።
እንዲሁም እግዚአብሔር አምላክ ጠቅላይ ምኒስተር ዶክተር አቢይ አህመድን
መሣሪያ አድርጎ ሀገራችን ኢትዮጵያን ለዘመናት ከኖረችበት የግድያና የምቀኝነት
ጨለማ አውጥቶ የፍቅርና የአብሮነት ሸማ አልብሷታል።ለዚህም እግዚአብሔርን
እማመሰግናለን።በመቀጠልም ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ጠቅላይ ኒስተር አቢይ
አህመድንና መንግስታቸውን ከልብ ይደግፋል ።የሚሠሩት ሥራ ሁሉ የተቃና
እንዲሆን ከልብ ይጸልያል።በመስቀል አደባባይና በተለያዩ ከተማዎች ለጠቅላይ
ምኒስተር ዶክተር አቢይ አክብሮቱንና አጋርነቱ ከለገሠው የኢትዮጵያ ሕዝብ
በመጨረሻም በሀገራችን ሕዝብ ዘንድ እየታየ ያለው ፍቅርና አንድነት
የማያስደስታቸውና እኩይ ተግባር የተጠናወታቸው ክፉዎች የዚህን ታላቅ ሕዝብና
ታላቅ መሪ አላማና የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማደናቀፍ በመስቀል አደባባይ ያደረሱትን
የቦብ ማፈንዳት ጥቃት ቅዱስ ሲኖዶስ በጽኑዕ ያወግዛል።በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ
የተለያዩ የእምነት ተቅዋማት መሪዎችም ይህን እኩይ ተግባር ሊያወግዙት ይገባል
እንላለን ። የኢትዮጵያ ሕዝብም ክፉዎችን ከመካከሉ ለይቶ በማውጣት ለፍርድ
እንዲያቀርባቸው ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል።
በዚህ ዕለት በጥቃቱ ለሞቱ ወገኖቻችን ከልብ እያዘን እግዚአብሔር እረፍተ ነፍስ
እንዲሰጣቸው፣በአካል ለተጎዱት እግዚአብሔር እንዲያድንልን እንጸልያለን። ለተጎዱ
ቤተ ሰቦችም መጽናናቱን እንዲሰጥልን የአምላካችን ፈቃድ ይሁን።
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያን ይጠብቅልን !!!
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1516
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 7 guests