ማዶላ በአደባባይ ተቃጠለ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ማዶላ በአደባባይ ተቃጠለ

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sat Jul 07, 2018 7:37 pm

ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ገደቡ ምንድነው??በዚህ ጉዳይ ላይ በዲሞክራሲ የበለፀጉ የሚባሉትም አገሮች እንኳ አስታራቂ መስመር ለማስመር የሚቸገሩበትነው። በኛም አገር ባለፋት ፳፯ ዓመታት የነበረውን ሁኔታ ብንቃኝ መስፈርቱ ባልታወቀ መመዘኛ አንዱ የህብረተሰብ ክፍል ያለገደብ ሲለቀቅ ብዙኃኑ ደግሞ ታፍኖ ኖሯል።በተለይም በአማራው የኅብረተሰብ ክፍል ላይ መጠነ ሰፊ ፕሮፓጋንዳ ይደረግ እንደ ነበር ሁላችንምየምናስታውሰውነው።በተለይም የቡርቃ ዝምታ በሚል ርእስ በኤርትራዊው ተስፋዬ ገብረአብ የማይዘነጋነው።በግለሰቡ ላይ ግን ምንም ዓይነት እርምጃ አልተወሰደበትም።በሌሎችም ላይ እንደዚሁ።ይህንን ጉዳይ ለማንሳት የፈለግሁት ማዶላ በሚል ርእስ በታተመው መጽሐፍ ምክንያት ነው።የጋሞ ሕዝብ ማንነት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል የተባለው የዚህ መጽሐፍ ከ፩ሺህ በላይ ኮፒዎች ህዝብ በተሰበሰበበት በዛሬው ዕለት ተቃጥለዋል። ታትሞ ለገበያ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ተቃውሞ የቀረበበት ይህ መጽሐፍ ጉዳዩ በፍርድ ቤት ሲታይ ቆይቶ ውሳኔው መሰጠቱ ታውቋል።
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1092
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ማዶላ በአደባባይ ተቃጠለ

Postby ኮኮቴ » Mon Jul 09, 2018 12:19 am

እንደ ተስፋየ ገብረ፟እባብ አይነቶቹን የጭካ ውስጥ እሾሆች ... መግታት የሚቻለው የሚያሳትሟቸውን በተንኮል የተሞሉ መጣጥፎች ባለማንበብ እና እኩይ ተግባራቸውን በአደባባይ በማጋለጥ ነው፡፡ አጅሬው የድሮው አልበቃ ብሎት "የቡርቃ ዝምታ ሲሰበር" የሚል ሌላ መርዝ እያዘጋጀ ነው አሉ፡፡
ኮኮቴ
o-o-o-o-o-o-o-o-o-o-o-o
".... Indeed, we Ethiopians are a beautiful multi-lingual and multi-cultural people who in a flower vase called Ethiopia decorate the great continent of Africa", Professor Ephraim Isaac
ኮኮቴ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1289
Joined: Wed Nov 04, 2009 2:07 am


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests