አንተው ነህ መሪዬ ሊቀጠበብት ዶ/ር አብዬ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

አንተው ነህ መሪዬ ሊቀጠበብት ዶ/ር አብዬ

Postby እሰፋ ማሩ » Fri Jul 13, 2018 3:55 am

“አንተው ነህ መሪዬ!”
(ለክቡር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ዕለተ-መቶኛ የጠ/ሚኒስትርነት ‘ዘመን‘ መታሰቢያ ትሁን!)
በሃቅ የታነጸ - እሚያድር በቃሉ፣
ባለግርማ-ሞገስ - ትህትና ሙሉ፣
አለኝታ፣ መከታ..፣ ለዜጎች መመኪያ፣
ስም ያለው፣ ክብር ያለው - ላገሬ መጠሪያ፤
ስፈልገው የኖርኩ - በሃሳብ በምናቤ፣
አንተው ነህ መሪዬ! የገባህ ከልቤ።
ኢትዮጵያ ለጸሎት - እጆቿን ዘርግታ፣
በእንባዋ ርሳ - ዘመናትን ፈጅታ፣
ያገኘችህ ዕንቁ - የእግዚአብሔር በረከት፣
የአገር ምሰሶ - የሕዝብ ጌጥና ሃብት፤
ባንተ ደስ ይበላት - ስለቷ ሰመረ፣
ወደ ፍቅር ጉዞ አዝማች ተዘመረ፤
ከፍ ብሎ ይውጣ - ይውለብለብ ሰንደቋ፣
አንድነቷም ይመር - በመደመር ቋንቋ።
ዐብይ ኢትዮጵያዊ - ረቂቅ፣ ምጡቅ..ጀግና፣
በሃሳብ ልዕልና - በመሪነት ፋና፣
ዘመን ውስጥ ተቀምጠህ - ዘመን የተሻገርክ፣
አንድነትን፣ ፍቅርን፣.. - ሰላምን የሰበክ፣
ባለራዕይ ዕሴት - ባለፍቅር ጸጋ፣
አንተው ነህ መሪዬ! ደምረኝ ካንተጋ።
ተምዘግዛጊ ጮራ፣ በብርሃን ፍጥነት፣
ተወርዋሪ ኮከብ፣ - ባራቱም ማዕዘናት፣
የላቀ ተምሳሌት - ለስኬት እመርታ፣
የሰፊው ሕዝብ ‘ሎሌ’ - ያገር ባለውለታ፣
ጎንበስ እምልልህ - “ምን ልታዘዝ?” ብዬ፣
የናት አገሬ ልጅ! - አንተው ነህ መሪዬ!
ጌታቸው አበራ
ሐምሌ 2010 ዓ/
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1530
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 5 guests