አይ የቄሮዎች ነገር......

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

አይ የቄሮዎች ነገር......

Postby ቆራሌ » Wed Jul 25, 2018 7:45 pm

የቄሮ ቦዘኔ ወጣቶች የሀረርን የውሃ መስመር ተቆጣጠሩ.

https://www.youtube.com/watch?v=auLVJ6Wm4PU
ቆራሌ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 44
Joined: Wed Oct 05, 2016 12:58 am

Re: አይ የቄሮዎች ነገር......

Postby እሰፋ ማሩ » Wed Jul 25, 2018 10:00 pm

የቀን ጅቡ ዜናውን የሚሰማ ጆሮ የለህም እንጂ የተዘገበው በቄሮ ስም ጥፋት የሚሰሩትን ለማጋለጥ ነው፡፡በአንዳንድ ቦታዎች በባሌ በወለጋ በሲዳማ የተሰሩት እኩይ ስራዎች የቀን ጅቦቹ መሰሪ ድርጊትና በሃያሰባት አምታት ወያኔ የጅቦቹ አለቃ ያስፋፋው የጥፋት ፍሬ ነው፡፡
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1514
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: አይ የቄሮዎች ነገር......

Postby ቆራሌ » Thu Jul 26, 2018 12:01 am

የሌሊት ጅቡ -አሰፋ ማሩ፡ እስኪ ይቺን ደግሞ ልመርቅልህ..

https://www.youtube.com/watch?v=34uhNpcuyQA
ቆራሌ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 44
Joined: Wed Oct 05, 2016 12:58 am

Re: አይ የቄሮዎች ነገር......

Postby ቆራሌ » Sun Aug 05, 2018 3:37 am

ታላቁ የደርባ ሲሚንቶ ፋብሪካ- በግድ ቅጠሩን በሚሉ ወጣቶች ምክንያት ስራ እቆመ፡፡
https://www.ethiopianreporter.com/article/12312
ቆራሌ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 44
Joined: Wed Oct 05, 2016 12:58 am

Re: አይ የቄሮዎች ነገር......

Postby ደጉ » Sun Aug 05, 2018 10:20 am

ቆራሌው የመጣው ለውጥ ምንም የተመቸህ አትመስልም ... ቅቅቅቅቅቅ እንዳንተ ያለተመቻቸው ናቸው በቄሮም ስም ይሁን በምንም እሚሞክሩት .. :-) ስለ ኢሳያስ ማነንት እኮ ገና ከድሮው እምናውቀው ነው እንዲሁ ደከምክ ... ጽናቱን ይስጥህ እኛ ግን እምንፈለገው ከዚህ በላይ ነው ... ተግባር!! አንተም ስትደግፈው የነበረው የ ወንበዴም ቡድን ለፍርድ ስትቀርቡ ነው፡፡
ተደምረህ እንኩዋን ለሳይበር ኢትዮጵያ አበቃህ .. :-)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4413
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Re: አይ የቄሮዎች ነገር......

Postby ቢተወደድ1 » Mon Aug 06, 2018 2:31 pm

እውነት አልዋጥልህ ያለህ ትመስላለህ፡፡

እሰፋ ማሩ wrote:የቀን ጅቡ ዜናውን የሚሰማ ጆሮ የለህም እንጂ የተዘገበው በቄሮ ስም ጥፋት የሚሰሩትን ለማጋለጥ ነው፡፡በአንዳንድ ቦታዎች በባሌ በወለጋ በሲዳማ የተሰሩት እኩይ ስራዎች የቀን ጅቦቹ መሰሪ ድርጊትና በሃያሰባት አምታት ወያኔ የጅቦቹ አለቃ ያስፋፋው የጥፋት ፍሬ ነው፡፡
ቢተወደድ1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 210
Joined: Thu Sep 01, 2016 8:48 am
Location: Bisheftu

Re: አይ የቄሮዎች ነገር......

Postby ቆራሌ » Sun Aug 12, 2018 10:27 pm

ጎጠኛው ጃዋር የንጹሃን ዜጎች ደም ተገበረለት.....
https://www.youtube.com/watch?v=jA9Q5kSw6Z0
ቆራሌ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 44
Joined: Wed Oct 05, 2016 12:58 am

Re: አይ የቄሮዎች ነገር......

Postby ለማ12 » Mon Aug 13, 2018 4:04 pm

1
ድምጽ አልባው መፈንቅለ መንግስት በኢትዮጵያ
05/12/2010
ከራሚደስ
ባሳለፍናቸው ጥቂት ወራቶች በኢትዮጵያችን እየተመለከትን የምንገኘው የፖለቲካ ጡዘት በገዥው የኢህአዴግ መንደር የተጠበቀው የሪፎርም ሂደት ሳይሆን ያልተጠበቀው የድምጽ የለሽ መፈንቅለ መንግስት ቅርፅና ይዘትን እየተላበሰ መምጣቱ ፍንትው ብለው መታየት ከጀመረ ሳምንታትን መቁጠር ጀምሯል፡፡ ህወሃትንም ሆነ መላውን የትግራይ ህዝብ በማያስደነብርና በማያገል፣ ባልተንቀራፈፈና በጣሙንም ባልተጣደፈ መልኩ ይከናወናል ተብሎ የተጠበቀው ሪፎርም በብርሃን ፍጥነት እየተምዘገዘገ ብቻም ሳይሆን አግላይነቱ እየሰፋ መምጣቱ ገሀድ ሆኗል፡፡ በዚህ አፍላ ጊዜ ውስጥ ወደ ትንታኔ ዘው ብሎ መግባቱ እጅግ አዳጋች መሆኑ ባይካድም ለውይይት ይጋብዝ ዘንድ ትንሽ ማለቱ ክፋት አይኖረውም፡፡ በእርግጥ እንደኛ ባሉ ሀገራት ህዝብ በምክንያትም ሆነ በስሜት ከፍተኛ ድጋፍ የሚቸሩትን ቡድንም ሆነ ግለሰብ በለሆሳስ መተቸትም ሆነ መሞገት "ውግዝ ከመ አሪዮስ" እንደሚያስከትል ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ዳሩ ግን ውግዛቱንም፣ እርግማኑንም አለፍ ሲል ፍረጃውንና ዛቻውንም ከወዲሁ ከግምት አስገብቶ "እረ ጎበዝ እንዴት ነው ነገሩ?" ብሎ መሞገቱ ለአመራሩም፣ ለህዝቡም ሆነ ለኢትዮጵያችን ይጠቅማልና እስቲ ትንሽ እንጠያይቅ፡፡ መቼም በዚህ ነገሮች ፍጥንጥን ባሉበት ወቅት የሚነሱት ጥያቄዎች ማቆሚያ የሚኖራቸው አይመስለኝም፡፡
ኢህአዴግ አለ ወይንስ ሞቷል የሚለው የብዙዎች አእምሮ ውስጥ ከሚብላሉት ጥያቄዎች አንዱ ነው፡፡ "አዲሱ" አመራር የኢህአዴግ ፖሊሲዎችን አስቀጣይ ወይንስ ከላሽ ወይንስ ለዋጭ የሚለው ሌላ ወጣሪ ጥያቄ ነው፡፡ የፖለቲካ ምህዳሩ በአሁኑ ወቅት ሀገር ቤት እየተሸቀዳደሙ እየገቡ የሚገኙትን በተቃራኒ ጫፎች የተወጠሩት የፖለቲካ ስብስቦችን ለማስተናገድ ስፋቱና አቅሙ ከምን ድረስ ይሆን የሚለው መልስ የሚሻ ጥያቄ ይመስላል፡፡ በአጭሩ ከስሜታዊነትቱም፣ ከሀሴቱም ትንሽ በረድ ብሎ አእምሮውን ማድመጥ የጀመረ ጭንቅላት ዛሬም አገራችን የ1966ቱና የ1983ቱ አይነት "ወዴት አየሄድን ይሆን" የሚያሰኝ ጭንቀት ውስጥ መዘፈቁ አይቀሬ ነው፡፡ ይህንን መንገድ ለመገመት ደግሞ አስቀድመን ምንድነው በኢትዮጵያችን የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ የተከሰተው የሚለውን ማጠንጠን የግድ ይላል፡፡ በተለይም ከቀድሞ ጠ/ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ ያለውን የፖለቲካ ሂደት በወፍ በረር መቃኘቱ መሠረታዊ ነው፡፡
የድህረ መለስ ኢህአዴግ
የህወሃትም ሆነ የኢህአዴግ የስጋም የነብስም አባት የነበሩት አቶ መለስ ዜናዊ ህልፈት በገዥው ግንባርም ሆነ በሀገሪቱ የፖለቲካ ሂደት አይነተኛ ተፅዕኖ ፈጥሯል፡፡ የመጀመሪያዎቹ የአቶ ኃ/ ማርያም ደሳለኝ ሁለት የስልጣን ዓመታት ታጋይ መለስን ከመዘከር ያለፈ ስራ ተሰርቷል ብሎ መከራከር
2
የሚከብድ ይመስላል፡፡ በቀጣይ አመታት ውስጥ ግን የአቶ መለስን ሌጋሲ እናስቀጥላለን ከሚለው
መፈክር ጀርባ የኢህአዴግ መንደር እየተተራመሰ መክረሙ የአደባባይ ምስጢር እንደነበር አይካዴ ነው፡፡
በድብቅ ተቀድተው የወጡ በተባሉ የድምፅ ማስረጃዎች እንዳመላከቱት የኢህአዴግ "እህትማማች"
ድርጅቶች ጥርስ ያልነበራቸው ጥርስ እያበቀሉ፣ ባለክራንቻዎቹ ደግሞ ክራንቻቸው እየዶለደመ
መምጣቱ ፍንትው ብሎ መታየት መጀመሩን መገንዘብ አያዳግትም ነበር፡፡ "እህት" ድርጅቶቹ
ሰፍሮባቸው ከነበረው የፍርሃት ቆፈን በተላቀቀ መልኩ መከራከር፣ መተቻቸት፣ መደፋፈር እውን
መሆን ከጀመረ ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ የዚህ ትከሻ ለትከሻ መነጋገሩ በሂደት ለተፈጠረው ሕዝባዊ
እምቢተኝነትና ተቃውሞ በእርሾነት እንዳገለገለ አያጠራጥርም፡፡
ከቄሮ እስከ ፋኖ
ለአመታት በአማራ ክልል ቦግ እልም እያለ የሰነባበተው ተቃውሞ ከፌደራል አወቃቀር፣ ከሰንደቅ
አላማ፣ ከታሪክ አረዳድ ወዘተ አንጻር የነበሩ ክፍተቶች እንደተጠበቁ ሆነው የወልቃይት ጉዳይ ጡዘቱን
እጅግ ከፍተኛ ወደ ሆነ ደረጃ ቢያሸጋግረውም ቅሉ የሀገሪቷ የፖለቲካ ምህዳር ዝዋሮውን ማርሽ
ለማስቀየር የሚያስችል አቅሙ ከኦሮሚያው እንቅስቃሴ ጋር ሲነጻጸር አምብዛም እንዳልነበረ ታዘበናል፡፡
በተቃራኒው የኦሮሚያ ህዝብም ሆነ ገዥ ድርጅቱ ኦህዴድ ከኢህአዴግ መሠረታዊ መስመር እጅግ
የተጣጣመ ርዕዮት አንግበው፣ ይበል ብሎም በዘመነ ኢህአዴግ የፖለቲካ ለውጥ ሂደት ውልደቶች
የሆኑት ቄሮዎች በድርጅቱም ሆነ በሀገሪቷ የፖለቲካ ጎዞ ከፍተኛ የሆነ ጫና ማሳረፍ ችለዋል፡፡
የኦህዴድ አመራሮች በተለያዩ ምክንያቶች ህወሃት ላይ የነበራቸውን ቅሬታ ቀስ በቀስ ከከፍተኛ እስከ
ዝቅተኛ አመራሮች በማዋረድ፣ በሂደትም ወጣቱ እንዲነቃቃና ትግሉን እንዲቀላቀል በእጅጉ በተጠናና
በተቀናጀ መልኩ ከወረዳ ካድሬዎች፣ ከክልል የጸጥታ አስከባሪዎች አንስቶ ከመንግስት መዋቅር ውጭ
የሚገኙ ተቃዋሚዎችና አክቲቪስቶች መስመርን ሁሉ በመጠቀም በይበልጥም የክልሉን ጂኦ
እስትራቴጂያዊ አቀማመጥ ባገናዘበ መልኩ የኢትዮጵያና የአፍሪካ መዲና የሆነችውን የአዲስ አበባ
ማንቁርት በማነቅ ህውሃት ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትን እዲያከብርና ተገዶ የፖለቲካ መዋቅራዊ
ሃይሉን ቁጥጥር እንዲያጣ ተደርጓል፡፡ ባለፉት ሁለት አስርተ አመታት በለመድነው አፈራረጅ ተነስተን
ከአገሪቷ ርዕሰ ብሔር፣ ርዕሰ መንግስት፣ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አፈጉባኤም ጭምር፣ አቃቤ ሕግ፣
መከላከያ ሚኒስቴር፣ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የአየር ሀይል አዛዥ፣ የዋና ከተማዋ ከንቲባ፣ የጠቅላይ
ሚኒስቴር ጸ/ቤት፣የቤተ መንግስት ጥበቃ ዕዝ እና ሌሎችም ወሳኝ የሀገሪቷ መዋቅሮች በአብዛኛው
በኦህዴድ አባላት ለመያዝ በቅተዋል፡፡ ብአዴኖች ወቅታዊና ታክቲካል ድጋፍ ለኦህዴድ ቢያደርጉም
በተቸራቸው የስልጣን ድርሻም ሆነ ወደ ሀገሪቷ የፖለቲካ መድረክ በግብዣና በምልጃ ኦህዴድ
አግተልትሎ እያስገባቸው በሚገኙት ጠርዘኛ የኦሮሞ ፖለቲካ ድርጅቶች ቅሬት፣ ስጋትና ጥርጣሬ
ሳይነግስባቸው እንዳልቀረ ሹክሹክታ እየሰማን እንገኛለን፡፡ በተጨማሪም የወጣቱ ጠ/ሚኒስቴር ግለ
3
ባህሪም የብአዴን አመራሮችን በቀጣይ ስጋታቸውን እየጨመረ በሂደትም የቄሮና የፋኖ ታክቲካል
ወዳጅነት እድሜ አጠር ያደርገው ይሆን ብለው ጭንቅ የገቡ ታዛቢዎች ማቆጥቆጣቸውን መታዘብ
እየጀመርን ነው፡፡
"ሰባተኛው ንጉስ"
ወጣቱ ጠ/ሚኒስትር በልጅነታቸው ከእናታቸው ይሁን ከጅማ ሼካዎች የተተነበየላቸው ንግስና ሲያወጉን
እንደው ለቀልድ ለጨዋታ ይሆን ብለው የወሰዱ ብዙ ሰዎች አሁን አሁን የጠ/ሚኒስትሩ ያለፉት
ሁለትና ሶስት ወራት ጉዞና ንግግሮች ሲከታተሉ፣ ሰውየው የንግስና ትርክት ከምራቸው ወስደውታል
እንዴ ብለው ማፌዝ ጀምረዋል፡፡ ነገሩ ከፌዝ በላይ ነውና ህዝቡም ሆነ ድርጅታቸው ከወዲሁ
ሊያጤኑት ይገባል ባዩችም አልጠፉም፡፡ "ብዙ ታላላቅ አጋጣሚች፣ በትናንሽ ሰዎች እንዲያመልጡን
ተደርጓል" እንደሚባለው ከጭፍን ድጋፍ፣ ወደ ሞጋች ድጋፍ ሰጭነት መዘዋወሩ ሳይበጅ አይቀርም፡፡
የስልጣን መንበሩን ሲቆጣጠሩ በእድሜያቸው ከዶ/ር አብይ ያንሱ የነበሩት ጓድ ሊቀመንበር መንግስቱም
ሆነ ጓድ ታጋይ መለስ ከመንግስት ምክር ቤትና ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ እንጂ
ደፍረው ከጠ/ሚኒስትሩ የተሰጠ መግለጫ ብለው በመገናኛ ብዙሃን አስነግረው አያውቁም፡፡ በተለይም
ከኢህአዴግ መስመር በጣሙኑ በተጋነነ መልኩ ግለ-ሰብዕና ግንባታው ይሁነኝ ተብሎ እየተሰራበት
እንደሚገኝ ግልጽ እየሆነ መጥቷል፡፡
የጠ/ሚኒስትሩ ጠቅላይ እውቀትም የሳቸውን እድሜ ያክል በተግባር በውትድርና የቆዩትን
ከፍተኛ የመከላከያ አመራሮች ስለ ውትድርና ስልጠና ሲሰጡ ሰምተን ተደንቀናል፡፡ የአመራር
ዕውቀታቸውንም ምንም እንኳ የእንግሊዝኛ ቃላቶች ቢበዙበትም ላለፉት ሁለት አስርተ አመታት
በከፍተኛ አመራርነት ላይ ለቆዩት ባለስልጣኖቻቸው በሰጡት የአመራር ስልጠና ለመታዘብ በቅተናል፡፡
ጠ/ሚኒስትሩ ለአንጋፋና ለወጣት የጥበብ ሰዎችም የኪነ ጥበብ ህልዩትን ሲተነትኑ ተመልክተን
ተደምመን አልፈናል፡፡ ስልጠናው ቀጥሏል "ምሁራን" ተወያይተው፣ "ፑሽ አፕ" ሰርተው ሰልጥነዋል፡፡
ጠቅላዩ በሀገረ ዲሲ፣ ሜኖሶታና ሎስ አንጀለስ ተጉዘው ዲያስፖራውንም የእውቀት ጠበል ረጭተው
ተመልስዋል፡፡ ወስን አቋራጭ ለተባሉት በጎ ፈቃደኞች አቅጣጫ አመላክትዋል፡፡ እያለ እያለ እስከ
ጥቃቅንና አነስተኛ ወረድ ብሎም የጎዳና ተዳዳሪዎች ስልጠና እንደርስ ይሆናል፡፡ እንደአያያዛቸው፡፡
በጠ/ሚኒስትሩ ድካም የለሽ ጉዞም ብዙዎች ተደምመዋል፡፡ በየአካባቢው እየገነፈሉ የሚገኙትን
ግጭቶች ለማብረድ በየክልሎቹ መኳተናቸው ሳያንስ በየጎረቤቱ ሀገራት ያከናወኗቸው የማራቶን ጉዞዎች
ሰውየው ደጋፊዎቻቸውን ከጎናቸው ለማሰለፍ ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ገላጭ ነው፡፡
በስሜት እንደጎርፍ የሚከተላቸው ህዝብና በየሄዱበት መድፍ ተኩሰው በክብር የተቀበሏቸው የጎረቤት
ሀገራት ድጋፍ እውን ከጫጉላ ሽርጉድ በኋላም ይቀጥል ይሆን ብለው በስጋት እየጠበቁ የሚገኙ
4
ታዛቢዎች የጋራ ስጋት መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ ሁሉን ማስደሰቱ ይከብዳልና ከሽርሽሩ መልስ ወደ
ተግባራዊ ስራ በጥልቀት ሲገባ ከህዝቡ ጎርፍ መስመር ለቀው የሚፈሱ እንደማይጠፉ ሁሉ ጎረቤትና
የአካባቢ ሀገራትም ጥቅምና አሰላለፍ ተለዋዋጭ እንደሚሆን መገመቱ አይከብድም፡፡ በተለይም እንደኛ
ባለ የቀንዱ አካባቢ ከሀያላኑ ሀገራት የሚሰነዘሩ ያልተቋረጡ ታሪካዊ ጣልቃ ገብነትን ከግምት ስናስገባ፡፡
የውክልና (Proxy) ሽኩቻ
አሁን በኢህአዴግ ውስጥ የገባው ንፋስ እንዲሁ በእህት ድርጅቶች መካከል ያለ የስልጣንና የጥቅም
የበላይነትን የማስጠበቃ ሽኩቻ በዘለለ መልኩ የሀያላን ሀገራት የእጅ አዙር ትንቅንቅ እንደሆነ የሚገመቱ
አልጠፉም፡፡ ሀያላኑ በኢትዮጵያችን ምናልባትም አብደላ ነገሰ ወይንስ ገ/ማርያም ሊያሳስባቸው ይችል
እንደሆን እንጂ ኪሮስ ሄዶ ጫላ መምጣቱ ያን ያክል ከቁብ የሚቆጥሩት ጉዳይ አይሆንም፡፡ ለእነርሱ
ማን ጥቅማችንን በተገቢው መንገድ ያስፈጽማል ነው ቁም ነገሩ፡፡ በዚህ ስሌት ህወሃት መሩ ኢህአዴግ
ላለፉት ሀያ ሰባት አመታት የተጓዘበት ልማታዊ መንግስት ርዕዮት ለምዕራባውያኑ እጅግ ተመራጭ
የማያስብል እንደነበር አይዘነጋም፡፡ በተለይም በኢኮኖሚው መስክ ቻይና በኢትዮጵያም ብቻም ሳይሆን
በአፍሪካ አጆቿን እንድትዘረጋ በር የከፈተ ተብሎ ህወሃት መወቀስ ከጀመረ ሰንበትበት ብሏል፡፡ ከአንድ
ክ/ዘመን በላይ ከዘለቀው የምዕራባዊያን ግንኙነት ውጤት ያልታዩ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች
በጥቂት አመታት የቻይና ግንኙነት ትሩፋቱን ማየት የጀመረ ህዝብም ሆሊውድ ለዘመናት የጠረነፋውን
ልብ ወደ ቻይና ማሽፈቱ አይቀሬ መሆኑ ለአሜሪካዎቹ ግልጽ እየሆነ መጥቷል፡፡
ዛሬ የአፍሪካ ባለስልጣናትና ሀብታሞች ልጆቻቸውን ለትምህርት ወደ ቻይን መላክ
መጀመራቸውን ላስተዋለ አፍሪካ "አድዮስ ምዕራብ" እያለች መሆኑን ማስተዋል አይከብደውም፡፡
በመሆኑም አሜሪካም ሆነች የአውሮፓና የአረብ ጀሌዎቿ አፍሪካን ከቻይና መንጋጋ ለማላቀቅ ያላሰለሰ
ጥረት እንደሚያደርጉ ጥርጥር የለውም፡፡ በሰኔ አስራ ስድስቱ የአብዬት አደባባይ የቦንብ ጥቃት በብርሃን
ፍጥነት የምዕራባውያኑ የደህንነት ተቋማት ዘው ብለው መግባታቸው ለውጡን እንደግፋለን ብቻም
ሳይሆን ጠ/ሚኒስትሩም ጀርባቸው ስስ አንዳልሆነ ለጠላትም ለወዳጅም በሾኬ የነገሩበት እንደሆነ
ገምተናል፡፡ ግትሩን ህወሃት "Game over" ብለው ከሰድሳ በላይ የትላልቅ ካምፓኒዎች ሥራ
አስኪያጆችን አግተልትለው የመጡት ከፍተኛ የአሜሪካ የንግድ ሚኒስቴር ባለስልጣናትና አንዳንድ
ሴናተሮች አዲሱን ጠ/ሚኒስትር እንደሚደግፉና ከዚህ በፊትም ሰለአለም ሰላም አብረው እንደጸለዩ
ሲያበስሩን "ነገሩ እንዴት ነው" ብለን ታዝበን አልፈነዋል፡፡ ከሳኡዲና ከኢምሬት ገዥዎች ጋር
ያስተዋልነው ብን ያለ ፍቅር ግንኙነት ከጠቅላያችን የአባትና የአያት ስም መመሰጥ ባለፈ የሀያላኗ
አሜሪካ ይሁንታም ትዕዛዝም ያለበት ለመሆኑ መጠራጠሩ አይከፋም፡፡ ትናንት የህወሃትን እጅ
ለመጠምዘዝ በተከናወኑ እርምጃዎች ገደል የገባውን የሀገሪቱን ኢኮኖሚ መልሶ ለማንሰራራት ያግዝ
ዘንድ በአይነትም ሆነ በጥሬው ወደ ሀገሪቱ ካዝና እንዲገባ የተደረገው እርዳታ "አዲሱን" ኃይል በእግሩ
5
እንዲቆም የሚያደርገው ርብርብ አካል መሆኑ ነው፡፡ በአጠቃላይ የሀገሪቷን ኢኮኖሚ በቀላሉ ከቻይና
ማላቀቅ አይታሰቤ ቢሆንም ከቻይና ጋር ቅልጥ ያለ ፍቅር ውስጥ የተዘፈቁትን ኃይሎች ከአካባቢው
ማጽዳት የምዕራባውያኖች ቀዳሚ እርምጃ ሳይሆን እንዳልቀረ መጠርጠሩ አይከፋም፡፡ ህወሃት ብቻም
ሳይሆን የጅቡቲው አቻውም ከቻይና ፍቅር አልላቀቀ በማለቱ እያረፈበት የሚገኘው ቡጢ የዋዛ
እንዳይደለ እየታዘብን እንገኛለን፡፡ ከወራት በፊት ጅቡቲ የሚገኘው የቻይና የጦር ሰፈር እዛው ባለው
የአሜሪካን የጦር ሰፈር ላይ ሰለላ እያካሄደ ነው ብላ አሜሪካን መወንጀሏ እንደተጠበቀ ሆኖ ጅቡቲ
ውስጥ እነ ፈረንሳይ ይዘውት የነበረውን ሚና ቻይና በመንገዱም፣ በባቡር መስመር ዝርጋታውም አልፎ
ተርፎም free zone የመገንባቱን ወዘተ ሚና መተካቷ ምዕራባውያኑን ማስከፋቱ አይቀሬ ሆኖ ሳለ
የጅቡቲ ወደብን ያስተዳድር የነበረው የዱባይ ፖርት ኮንትራት መሰረዟና ማባረሯም የአካባቢው የአረብ
ሀያላኑን አይን ማቅላቱ አያጠራጥርም፡፡ የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች የጅቡቲን መንግስት በለንደን ፍርድ
ችሎት ከመሞገት አልፎ የበርበራ ወደብን ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ ለማልማት መስማማቱ ጅቡቲን ታፋ
ሰር ገብቶ መቆንጠጥ ጋር የሚያመሳስሉት አልጠፉም፡፡ ይባስ ብሎ ቀደም ሲል የየመን ሁቲዎችን
ለመደብደብ የሚጠቀሙባቸውን የኤርትራ ወደቦች ለኢትዮጵያ በራቸውን እንዲከፍቱ ሁለቱን ሀገራት
በማሸማገል የተጫወቱት ሚና ከዚህ ቀደም የጅቡቲው አየር ኃይል አዛዥ የኤሜሬቱን ካውንስለር አሪፍ
አሊ አልታቡርን ያጮሏቸው ጥፊ ግብረ መልስ ብቻም ሳይሆን የትንሾ ጅቡቲ ኢኮኖሚ ላይ ያረፈ
አደገኛ በትር እንደሚሆን ጥርጥር የለውም፡፡
ተዛወሪ መኪና ካብ አዲስ አስመራ
የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ውሳኔ እየተገበሩ መሆኑን ደጋግመው የሚገልፁት ጠ/ሚኒስትር አብይ
የኤርትራን የእርቅ ጉዞ የተያያዙበት ሁናቴ ከድርጅታቻው ቡራኬ የዘለለና የሃያላኑንና የአረብ ገልፍ
አገራትን ትዕዛዝ በፍጥነት የመተግበር ትልም ያነገበ እንደሚመስል ለታዛቢ ግልጽ እየሆነ መጥቷል፡፡
ተራ የዲፕሎማሲ ፕሮቶኮሎችን በሙሉ በደረመስ መልኩ ጠ/ሚኒስትሩ ኤርትራን በተመለከተ
ያደረጓቸው ንግግሮች በአዲስ አበባ ሆነ በአስመራ የተከናወኑ ትርዒቶች በፍጥነትም በይዘትም
ብዙዎችን ግር ማሰኘቱ አይቀሬ ነው፡፡ እርግጥ ነው ህወሃትን ከማብሸቅ ባለፈም ለጠ/ሚኒስትሩ ከፍተኛ
የህዝብ ድጋፍ ማስቆጠሩ አይካዴ ነው፡፡ ህዝብ መቼስ ጎርፍ ነውና ትናንት "የእናት ጡት ነካሽ"
የተባሉትን አቶ ኢሳያስ አፈወርቂን አንቅሮ በተፋበት እንደበቱ ዛሬ ላይ ጠ/ሚኒስትሩ በስሜታዊነት
ጎርፍ እየነዱት "ኢሱ"፣ "ኢሱ" አስብለው አሰቦርቀውታል፡፡ ቁም ነገሩ ይህ ሁሉ ሽርጉድ ለኢትዮጵያ
ምን ጥቀም ይኖረዋል ነው፡፡ አጎራባች ለሆኑት ለትግራይና ለአፋር ማህበረሰብ እርቁ እፎይታን ብቻም
ሳይሆን ከደንበር ዘለል ካሉ ዘመዶቻቸው ጋር በነጻነት የመገናኘት፣ የመገበያየት ወዘተ .. ማህበራዊና
ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎች እንዳሉት እሙን ቢሆንም ቅሉ ሀገራዊ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው
ወደ ኤርትራ ማድላቱ ግልጽ ይመስላል፡፡ የገልፍ አረብ አገራት ካውንስል በነብስ አባታቸው አሜሪካ
6
እየተመሩ በየመን ሁቲዎች ላይ በሰነዘሩት የጥቃት ዘመቻ ከተቃራኒው የዶሀ ካምፕ (ቱርክንና ኢራንን
ጨምሮ) በፍጥነት እራሳቸው እርቀው ወደ ሀያላኑ ጉያ የተሸጎጡት አቶ ኢሳያስ በጉርሻ መልክ ካገኙት
ከአረቦቹ እርጥባን ባለፈ ከአለም ፖለቲካ መድረክ ግርዶሽ እየተገፈፈላቸው በሂደትም ከጎረቤት ኢትዮጵያ
ጋር ወደ እርቅ መንገድ እንዲገቡ (ያውም ተለምነው) እድል ተመቻችቶላቸዋል፡፡ እነ አሜሪካ
ምናልባትም ቻይና አፍቃሪ ተብሎ የሚታማውን ህወሃትን ከመበቀል የዘለለ በኢህአዴግ የውስጥ ሽኩቻ
እጅን በማስገባት የኃይል ሚዛኑ ወደ ወጣቶቹ የኦህዴድ አመራሮች እንዲያዘነብልና እነርሱም በተራቸው
ኤርትራን ወደ አለም አቀፍ የፖለቲካ መድረክ የመመለሱ ሂደት ላይ የራሳቸውን ያላሰለሰ ጥረት
ይጫወቱ ዘንድ ተደርገዋል፡፡ ይህ ባህር ተሻጋሪና ድንበር ዘለል፣ አለምአቀፋዊ እና ክልላዊ የፖለቲካ
ቁማር ለወጣት መሪዎቻችን የህውሃትን ጡንቻ አዝሎ የእነርሱን ለማጠንከር ከመርዳቱ ባሻገር
እንደሀገር የሚኖረው ጠቀሜታ ሰከን ባለና በኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ታሪክ የምንታወቅበትን አድሏዊ
ያልሆነ የመካከለኛይቱን መስመር በጥንቃቄ ጠብቆ የመጓዝ ባህል ዘለቄታዊነትን ያገናዘበ ይሆን ብለው
ጥርጣሬና ስጋት የገባቸው ወገኖች በርከትክት ማለት ጀምረዋል፡፡ የወዲ ዜናዊና የወዲ አፎምን ፍቅር
ከየት ወደየት እንዳላጋን ተመልክቶ ያለፈ አእምሮ ያለው ዜጋ የኦቦ አብይንና የኢሱን ፍቅር ላይ
መተማመን እንደሚያስቸግረው ጥርጥር የለውም፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ መቀሌ መሽገዋል ያሏቸው ሰዎች
መቼስ "ፍቅር ያዘኝ ብለሽ አታበይ ደንበር ደንበር" እያሉ እንደሆነ ጥርጥር የለውም፡፡
የዶላር ያለህ
የ"አዲሱ" አመራር ሌላው አጣብቂኝ የዶላር እጥረት ነው፡፡ ኢህአዴግ በሚያካሂዳቸው መጠነ ሰፊ
ፕሮጀክቶች ምክንያት የውጭ ምንዛሬ እጥረት ከሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ጋር አብሮ የነበረ ችግር
ቢሆንም ቅሉ ሙስኝነትና ላለፉት ሶስት ዓመታት በሀገሪቱ ገንፍሎ የነበረው ህዝባዊ አመፅ ኢኮኖሚው
ላይ ያሳረፉት ተፅዕኖ ቀላል የሚባል እንዳልሆነ እሙን ነው፡፡ ሀገር በቀልና የውጭ ባለኃብቶችን እምነት
መልሶ መገንባት፣ ቀደም ሲል ሲጠቀሙባቸው የነበሩትን ቄሮንና መሰል ወጣት የአመፅ አቀጣጣዮችን
በህግና በስርዓተ-ትድድር ማስገባት፣ በደርጉ ዘመን አባባል ስግብግብና አሻጥረኛ ነጋዴዎችን ወደ
መስመር መመለሱ፣ የኢኮኖሚ ግለቱን ቀንስ አድርጎ የውጭ ምንዛሬ ፍላጎትን መግታት ወዘተ…
ጊዜያዊ እፎይታን ቢያመጡም ለኢኮኖሚ መረጋጋቱና ፈጣን የኢኮኖሚ እድገትን ለማስቀጠል ዘለቄታዊ
መፍትሄዎች አይደሉም፡፡ በዘመቻ መልክ ብርንም ሆነ ዶላርን መስብስቡ አሁንም ጊዜያዊ ችግር መፍቻ
እንጂ ዘላቂ መፍትሄነቱ እምብዛም ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ብዙ የተዘመረለት የዲያስፖራ ትረስት ፈንድም
ቢሆን ከጥቂት ዙሮች በላይ መቀጠሉ አጠራጣሪ ነው፡፡ መቼም ለጊዜው ጠ/ሚኒስትሩ "ጅቦቹ መጡብኝ"
አይነት ማስፈራሪያ የጠላቴ ጠላት በሚለው ቀመር መሠረት ትንሽ ዙሮች ዶላር መስብስቡ ባይቀርም
በሂደት የ"አዲሱ" አመራር አንኳር የፖለቲካና የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ሲተነተኑ ብሎም ወደ ተግባራዊ
7
ክንዋኔዎች ሲገባ አኩራፊ ኃይል አይጠፋምና የዶላር ስብስባው እንቅፋት እንደሚገጥመው ጥርጥር
የለውም፡፡ የጠላት ጆሮ አይስማውና፡፡
የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት በዘለቄታው አስተማማኝ ደረጃ ሊደርስ የሚችለው የሰው ኪስ ያለውን ምንዛሬ
በዛቻ ብቻ በመሰብሰብ፣ ከሃያላኑና ከአጎራባች አረብ አገራት በሚገኝ እርጥባን እንዲሁም ዲያስፖራውን
በአማላይ ቃላትና ተስፋ በመሸንገል ሳይሆን ሀገሪቷ ወደ ውጭ የምትልከው ምርትን ወደ ሀገር ውስጥ
ከምታስገባው ጋር ማመጣጠን ሲቻል ብቻ ነው፡፡ ወደ ውጭ ጥሬ ሀብት ተልኮ ዶላር መሰብሰብ እጅግ
አዳጋች በመሆኑ የኢህአዴግ አመራር ፊቱን ወደ ኤክስፖርት መር የኢንዱስትሪ ልማት በማዞር
በየቦታው የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ የኢንዱስትሪ ምርቶችን አምርቶ ወደ ገበያ
ለማቅረብም በአለም አቅፍ ገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን የብር አቅምን ቀነስ (devalue) ማድረጉ የግድ
ይላል፡፡ የዋሽንግተን ኮንሰንስስ ተቋማት (የአለም ባንክና የአለም የገንዘብ ድርጅት) የብር አቅምን ቀንሱ
ጉትጎታ የ"ቀድሞው" የህውሃት መር ኢህአዴግ ከቻይና ጋር በመጣመር ትንሽም ቢሆን ጫናውን
ተቋቁሞ ቆይቷል፡፡ "አዲሱ" ኦህዴድ መር ኢህአዴግ አመራር "የቅደሞዎቹን" አካሄድ ካወገዘ ዘንዳ
የዋሽንግተን ኮንሰንስስ ተቋማትን ትእዛዝ አዘል ምክር መቀበሉ አይቀሬ መሆኑ ነው፡፡ ይህ ደግሞ
የዶላር ምንዛሬን ከፍ ያደረግ እንደሆነ እንጂ ሊቀንሰው አይቻለውም፡፡ ጥቁር ገበያን በተመለከተም
ከገበያው የሚያስወጣው የፖለቲካ አዋጅ ሳይሆን የኢኮኖሚ ፍላጎትንና አቅርቦትን ህግ ብቻ ነው፡፡
ባንኮች አስመጪዎች የሚጠይቁትን የውጭ ምንዛሬ መጠን ማቅረብ ከቻሉ ነጋዴው ወደ ጥቁር ገበያው
የሚያስኬደው ገፊ ሀይል ተወግደ ማለት ነው፡፡ በተቃራኒው አስመጪው የሚጠይቀውን የውጭ ምንዛሬ
ባንኮች ማቅረብ ካልቻሉ ወይ ከአስመጭነት ንግድ መውጣት ይኖርባቸዋል፡፡ አልያም መንግስት ዳግም
ከዋጋ በታች (under invoice) አሰራርን መፍቀድ ይኖርበታል፡፡ ይህ ደግሞ ለጥቁር ገበያው
መንሰራፋት ሰፊ እድል ተፈጠረለት ማለት ነው፡፡ በአጭሩ ህዝቡ በስሜታዊነት "እሳቸው የማይቻላቸው
የለምና" ከሚለው ቀቢፀ ተስፋ ወጣ ብሎ ለክቡር ጠ/ሚኒስትርና "አዲሱ" አመራራቸው ምክርም
ሙግትም ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
የ"ቀድሞ" አመራሮች ትችት በልክ ቢሆንስ
የ"ቀን ጅቦች"፣ "ጠጉረ ልውጦች" ወዘተ የሚስኙ የጠላት ምስል ቀረጻ ፕሮጀክት ተለጥጦ ከድጋፍ
ማሳባሰቢያ መሳሪያነቱ ገዝፎ ነገ ልንመልሰው ወደማንችለው አዝቅት ይዞን ሳይንደረደር ቢገታ የተሻለ
ነው፡፡ ፍረጃውና ክሱ በግልጽ ሊጠቀስ ይገባዋል፡፡ ግለሰቦችም ሆነ ቡድን አሻሚ ባልሆኑ አገላለጾች
ሊገለጹም አስፈላጊ ከሆነ በህግ ሊጠየቁም ይገባቸዋል፡፡ የ"ቀድሞ" የተባሉት አመራሮች ያደረጉትን በጎ
ነገሮች እውቅና መሰጠቱም ለአብሮነት መፍትሄ እንጂ የበታችነት ስሜት እንዲሰማን ሊያደርጉ
አይገባም፡፡ "ደርግን የጣለው እራሱ ደርግ ነው" የሚለው አባባል ከህወሃት መንደርም ተደጋግሞ
8
የሚሰማ የአነጋገር ፈሊጥ መሆኑ ቢታወቅም የጠ/ሚኒስትሩ ለአፋር ሽማግሌ በሰመራ የመለሱበት
አግባብ ግን የመናናቅና የመበሻሸቅ ፖሊቲካ ውስጥ መነከራቸውን አሳባቂ ነበር፡፡
"ሽብርተኛው መንግስት ነበር" የሚለውም አገላለጽ በየማረሚያ ቤቱ ስቃይ የደረሰባቸውን እስረኞች
በቴሌቪዥን መስኮት በማቅረብ ይፋዊ የማጥላላትና የተጠያቂነት ዘመቻ እየከፈቱ በተቃራኒው በይቅርታ
እንደመር ዓይነቱ ንግግር ጉንጭ አልፈ ከመሆኑም ባሻገር ግብዝነትን ገላጭም ይመስላል፡፡ ከሰሞኑ
ለ"ምሁራን" ሹክ ያሏቸው "አባይ ፖለቲካ ነው" አይነቱ ጨዋታ ህዝብ መንግስት ላይ ሊኖረው
የሚገባውን እምነት ከመሸርሸርም ባለፈ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን ህልውና ጥያቄ ውስጥ ሊከት የሚችል
አካሄድ ነው፡፡ ለግብፅ መሪ አል-ሲሲ ሶስት ጊዜ "ወላሂ ወላሂ ወላሂ ግብፅን ላንጎዳ ቃል እንገባለን"
ካሉት ጋር ሲጣመር ደግሞ እውነት አባይ ፖለቲካ ሆኖ ነው ወይንስ የግብፅ ረጅም እጅ የሀገራችንን
ሉአላዊነት በስመ የኢህአዴግ ክፍፍል መዳፈሯን ቀጥላለች ሊያሰኝ ይችላልና ጥንቃቄ ያሻዋል፡፡ በጥቅሉ
በኢህአዴግ መንደር ቅጥ አጥቶ የነበረውን የህወሃት የበላይነት ማስወገዱ ይበል የሚያሰኝ ተግባር ሆኖ
እያለ በዘመነ ህወሃት የተደረገው ሁሉ እርኩስ ነበር ማለቱ ለቀጣይ የአብሮነት ጉዟችን አደናቃፊ
ድንጋዮች ከመደርደር ብዙም አይለይምና ይታረም ነው ቁምነገሩ፡፡
ከግለ-ሰብዕና ግንባታ ወደ ድርጅታዊ ቅርጽ ብንመለስስ
"አዲሱ" አመራር ድርጅታዊ ቅርጽን እየለቀቀ የጠ/ሚኒስትሩን ግለ-ስብዕና መገንባት ላይ ተጠምዶ
ይገኛል፡፡ ምናልባት ይህ ጉዞ አገሪቱን ከፓርላሜንታዊ ወደ ፕሬዚዳንታዊ አመራር ለማሸጋገር ታልሞ
ካልሆነ በስተቀር አንድን ግለሰብ ከመሪነት ባለፈ መለኮታዊ ኃይል እየላበሱ መሄዱ እጅግ አደገኛ አካሄድ
ነውና ለከት ሊበጅለት ይገባዋል፡፡ ኢህአዴግ ያስፈፀማቸውንም ሆነ በእቅድ ነድፎ ይዟቸው የነበሩትን
ራዕዮች ሁሉ እየጠለፉ የራስ ብቻ ማድረጉ ነገ ማጣፊያውን ያሳጣልና ሊታረም ይገባዋል፡፡ ህብረ-
ብሄራዊ አህዳዊነት ላይ መስራት፣ ኢትዮጵያዊነትን ከህጻናት እስከ ኪነጥበብ ዘርፎች ድረስ ማቀንቀን፣
አጋር ድርጅቶችን ወደ ግንባሩ መቀላቀል አልፎ ተርፎም ግንባሩን ወደ ህብረ-ብሔራዊነት እና ርዕዮት
አለምን የተመረኮዘ ፓርቲንት መለወጥ፣ የፌደራሊዝም ተግዳሮቶችን ማጥናትና መከለስ፣ ትላልቅና
አትራፊ መንግስታዊ ድርጅቶችን በከፊል ወደ ግል ይዞታ ማዛዋወር፣ መድበለ ፓርቲ ስርዓትን
ከወረቀት በዘለለ መልኩ በመጠኑም ቢሆን ተግባራዊ ለማድረግ የም/ቤት ወንበርን እስከመጨመርና
የምርጫ ህግን አስከ ማሻሻል የሚደረስ የህገ-መንግስት ማሻሻያዎች የማድረግ ወዘተ… ትልሞችን
የጠ/ሚኒስትሩ አዳዲስ ተግባራት አድርጎ ማቅረቡ ጊዜያዊ የህዝብ ድጋፍ ቢያጎርፍም ቅሉ በሂደት
በህዝብም ዘንድ ያስገምታልና ሊታረም ይገባዋል፡፡ በተለያዮ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና የደኅንነት ስጋቶችን
ለማብረድም ሆነ ለማስወገድ ታሳቢ ተደርገው ወደ ህዝብ ጆሮ ጊዜውን ጠብቆ ሊንቆረቆሩ የሚገቡ
ጉዳዮች በችኮላ ይፋ ማድረጉ አደጋ ሊኖረው ይችላልና ሰከን ብሎ ቢታሰብበት አይከፋም፡፡
9
ከስብከተ-ምኞት ወደ መግለጸ-አውነታ
ኢትዮጵያ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ እድገቷ እንድትሆን የምንመኘውን ሳይሆን አሁን ባለንበት
ዘመንና አቅም ልንደርስ በምንችለው እውነታ ዙሪያ ህዝቡን ማሳባሰቡና ማነቃቃቱ አማራጭ የለውም፡፡
"ከንጋቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ ሀገራችን ድፍድፍ ነዳጅ ማውጣት ትጀምራለች" አይነቱ የሚዲያ ሽፋን
በየዕለቱ በአዳዲስ ብስራቶች ቀልቡን ለሳተው ኢትዮጵያዊ ከሰመመን ሳይወጣ ለ"ነብዮ" መሪያችን
ድጋፍን እንዲለግስ ቢገፈውም ቅሉ በሰፊው የተከፈተውን የህዝብ ጉጉት ማሟላቱ ሊያስቸግር ይችላልና
ቃል መግባቱም በልኩ ቢሆን ይመረጣል፡፡ በቀጣይ ጥቂት ወራት የውጭ ምንዛሬ ተመን ቁልቁል
ይጓዛል፣ ሀገሪቷም ሁሉ በእጄ ሁሉ በደጄ ትሆናለች በሚለው አቅጣጫ የተሰበሰበ ድጋፍ ሙልጭ ብሎ
ለመጥፋት ብዙም ጊዜና ጉልበት እንደማይጠይቅ ሊታሰብ ይገባል፡፡ የዴሞክራሲ ስርዓቱም ገና ተወልዶ
በቅጡ መዳህ ሳይጀምር ዘሎ የምዕራባውያን አይነቱ ሁሉም ከነአስተሳሰቡ የተጋበዘበት አካሄድ
ሀገሪቷንም ሆነ ህዝቧን ወደየት ይዟቸው እንደሚሄድ መገመት አስቸጋሪ አይሆንም፡፡ ዛሬ ላይ
መገንጠል አለብን የሚል የፖለቲካ ድርጅትና ሁሉን ጠቅላይና አዋሀጅ የሆነ አስተሳሰብ ያነገበ ድርጅት
በእኩልነት ሀሳባቸውን ገልጸውና ደጋፊዋቻቸውን ቀስቅሰው፣ ተወዳድረው የተሸነፈው በአሸናፊው ሃሳብ
ተገዝቶ በሰለጠነ መልኩ ይጓዛል ብሎ ማሰብ ኢትዮጵያን አለማወቅ ወይንም የፖለቲካ የዋህነት እንጂ
ሌላ ሊሆን አይችልም፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ እንደምሳሌ የገለፁት የእስራኤል ክኔሴት የሚያስተናግድው
የአስተሳሰብ ስብጥር ለእኛም እንደምኞትና ግብ ተመዝግቦ ይቆየንና ትኩረታችን ፅንፍ የረገጠ
አስተሳሰቦች የጨዋታ ሜዳ ውስጥ በሰፊው ከመነከራቸው አሰቀድሞ በአነስተኛ ደረጃ ላይ መግባባት
ፈጥረው እንዲመጡ ማድረጉ በተገባ ነበር፡፡
የአመጻ ፖለቲካ ይገታ
በእርግጥ የአመጻ ፖለቲካ በቀላሉ አይገረሰሴ ናቸው ተብለው ታስበው የነበሩ መንግስታትን አሽቀንጥሮ
ሲጥል የሰሜን አፍሪካ አረብ ሀገራት ጥሩ ማሳያዎች ሆነውን አልፈዋል፡፡ ይህ የአመጻ ፖለቲካ
በኢትዮጵያችንም ውጤታማ መሆን እንደቻለ በቅርቡ መታዘብ ችለናል፡፡ የህወሃት መር ኢህአዴግ
ከውጭ ሊከሰቱ ከሚችሉ አመጻዎች እራሱን ሲከላከል ቢቆይም ቅሉ ከድርጅቱ ውስጣዊ ከሆነው የአመጻ
ፖለቲካ ማምለጥ አለመቻሉ እሙን ሆኗል፡፡ የህወሃትን የበላይነት ከዚህ በላይ መሽከም አቅቶናል ያሉ
የኢህአዴግ "እህት" ድርጅቶች በራስ ተነሳሽነት፣ በህወሃት ለተወስነ ሪፎርም በጎ ፈቃደኝነት፣
በተቃዋሚው ጉትጎታ እንዲሁም በውጭ ኃይሎች አይዞን ባይነት ታጅበው ሊሆን በሚችል ሁናቴ
ህወሃትን በድርጅታዊ መስመርም ሆነ ከድርጅት መስመር ውጭ ባሉ የቄሮ፣ የፋኖ፣ የዘርማ ወዘተ
የአመጻ እንቅስቃሴዎች ተጠቅመውና በማህበራዊ ሚዲያዎች አቀጣጣይነት የአመጻ ፖለቲካን በተገቢው
ሁኔታ ተጠቅመው ለድል በቅተዋል፡፡ ይህ በኦህዴድ የሚመራው እራሱን "የለውጥ ኃይል" ብሎ
የሚጠራው የኢህአዴጋውያን ስብስብ መንግሰት የመምራቱንም ኃላፊነት ከተቆጣጠረ በኃላም የአመጻ
10
ፖለቲካን ሲጠቀም ተስተውሏል፡፡ በአዲሱ አማርኛ ለአልደመር ባዬች አደፍርሶ ማጥራትን እንደ
አቋራጭ ወደ መፍትሄ መዳረሻ ስልት እየተጠቀሙበት ይገኛል፡፡ በሀዋሳና አካባቢው የተነሳው ድፍርስ
ከህወሃት ጋር ቁርኝት አላቸው የተባሉት አመራሮች ጎርፍ ጠራርጓቸው ሄዱል፡፡ በተመሳሳይ የማደፍረስ
ዘመቻ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልልንም "የማይደመሩትን" የማጥራት ዘመቻው ብዙ ዋጋ ቢያስከፍለንም
እየተተገበረ ይገኛል፡፡ ይህ ስልት ውጤታማ ባይሆንም በቤንሻጉል ጉሙዝና በአፋር ክልልም
ተሞክሯል፡፡ ለወደፊት እንደሚደገምም ጥርጥር የለውም፡፡ አፍቃሪ ህወሀት አመራሮችን እስከሚጸዱ
ድረስ፡፡ ይህ በየክልሉ አመጽ አስነስቶ አመራሩን የመቀየር ስልት በእርግጥ ፈጣን የሆነ ውጤት
እንደሚያመጣ እሙን ቢሆንም በህብረተስቡ መካከል ጭሮት የሚያልፈው እሳት ለዘለቄታው ማርገቡ
ቀላል ላይሆን ይችላል፡፡ ያደፈረስው ቤት እሳት ባይጠፋ ተጠያቂውስ ማን ሊሆን ነው ብሎ መሞገት
ያስፈልጋል፡፡ ዛሬ "አይደመርም" ተብሎ የሚታሰብን ቡድንና ግለስብ ጠርጎ ለማውጣት የምንጠቀምበት
የአመጻ ፖለቲካ ብሄርን ከብሄር፣ ጎሳን ከጎሳ፣ ሀይማኖትን ከሀይማኖት አናክሶ ጊዜያዊ ውጤት
ቢያመጣም ለነገ የሀገር ህልውና ላይ ለሚደነቀረው አደጋ ከወዲሁ ሊታሰብ በተገባ፡፡ በመሆኑም
"የለውጥ" አካል ሊሆኑ አይችሉም የተባሉ ግለስቦችም ሆኑ ቡድኖች ከቀጥተኛ የማስወገድ፣ የመጥረግ
ወዘተ አካሄድ ተላቅን በሰከነ ፖለቲካዊና ድርጅታዊ አሰራር መስመር ተከትሎ ቢከናወን ውጤቱ ብቻም
ሳይሆን የሚያመጣው የወደፊት አደጋ መቀነስ ይቻላልና የአመጻ ፖለቲካን "እዚህ አድርሰህናልና
እናመሰግንሀለን" ተብሎ ከፖለቲካው መድረክ በጡረታ አልያም በረጅም እረፍት ቢገለል የተሻለ
ይሆናል፡፡
ሽርሽር ይብቃ፣ ሃብት አይባክን
ጠ/ሚኒስትሩ ለማመን በሚከብድ ጥንካሬ ስልጣነ መንበሩን ከተረከቡ ቀን አንስተው እስካሁን ድረስ
አላረፉም ብሎ ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ እንደዚህ አይነት ትኩስ ኃይል ያለው መሪ መገኘቱ እሰየው
የሚያስብል ቢሆንም ቅሉ ከዙረቱ ምን አተረፍን ብሎ መጠየቁም አይከፋም፡፡ ትናንትና ጠ/ሚኒስትሩ
በፍቅር እየተቃቀፍ ከጎበኛቸው ጎረቤት ሀገራት መካከል እነ ጅቡቲ ይፋዊ ተቃውሞ ማሰማት እየጀመሩ
ነው፡፡ ኬንያም በሰሞኑ የጠ/ሚኒስትሩ ከኤርትራ ጋር ባሳዩት የፍቅር አወዳደቅ ትልቁ የLAPSSET
ኮሪደር ልማት እንከን ያጋጠመው ይሆን በሚል ስጋት ውስጥ መግባታቸውን ከመግለጽ አልቦዘኑም፡፡
ግብፅ ለጊዜው "ስለቴ ስመረ፣ ሀሳቤ ተሣካ" እያለች ቢሆንም አል-ሲሲ የኦቦ አብይን "ወላሂ" ተማምነው
አርፈው ይቀመጣሉ ብሎ ማስቡ የዋህነት ነው፡፡ ለኢትዮጵያ አየቆፈሩ የሚገኙትን ጉድጓድ ጥልቀት
ከማስፋት መቼም እንደማይቦዝኑ እርግጥ ነው፡፡ የአቡዳቢና የሳኡዲን ኒሻንና ዶላር በተዘዋዋሪ በሱዳንም
በሱማሊያም ረጃጅም እጅ ባላቸው ኢራን፣ ቱርክና ቃጣር የእጥፍ ዋጋ ያስከፍለን ይሆን ብሎ
መጠርጠሩ አይከፋም፡፡ ወንድም የሆነው የየመን ህዝብስ እንዴት ይታዘበን ይሆን ብሎ በሀፍረት
የሚሸማቀቅ አይጠፋም፡፡ ከሀገር ቤት ዙረቱም ምን እንዳተረፍን ስሌት ብንሰራ አይከፋም፡፡ ዛሬ
11
በቤንሻንጉል፣ ሶማሌ፣ ኦሮሚያ፣ ትግራይ፣ ሀዋሳ ወዘተ ያሉትን ሽኩቻና ውጥረቶች ለተመለከተ ያ
ሁሉ ዙረትና ውብ ቃላት ድርደራ ፍሬ አለማፍራቱን ብሎም ጊዜና የሀገር ሀብት ብክነት መሆኑን
እያሳየን ይገኛል፡፡ በመሆኑም ሽርሽር ይገታ፣ ህዝበኛ ንግግሮች ይለዘቡ፣ ጥልቀት ያላቸው፣ ፍሬያቸው
በሂደት የሚጎመራ ተግባራት ላይ ትኩረት ይደረግ፡፡ ድምርህ "ከጅቦቹ" ወይንስ "ከለውጡ" ጋር የሚባሉ
አጓጉል ፍረጃዎች ይቁሙና ፖሊሲ መር፣ አቅጣጫ መር፣ አይዲዮሎጂ መር ድመራ ይፋ ይሁን፡፡
"ጅቦቹ ሊበሉኝ መጡ" ከሚለው ማስፈራሪያ እንውጣና የኢትዮጵያን ህዝብ የፖለቲካና የኢኮኖሚ
አቅጣጫዎች ላይ ተወያይተንና ተግባብተን እንደመር፡፡ አሁን በተያያዝነው ህዝበኛና ጥራዝ ነጠቅ በሆነ
ሰበካና የመልካም ዘመን ብስራት ብዙ መጓዝ የምንችል አይመስልም፡፡ የአሜሪካና የህዝብ ድጋፍ እንደ
ጎርፍ ነውና በጥንቃቄ እንጠቀምበት እንጂ በሙሉ ኃይላችን አንዘፍዘፍበት፡፡ አሸዋ ላይ መቋሚያ
ተደግፎ መዘባነን ትርፉ ዋይታ ነው፡፡ ኢትዮጵያችንም የሚያስፍልጋት ህዝቡን ወደ ክፍታ የሚያሸጋግር
መሪ እንጂ ተመሪ አይደለምና፡፡ በመሆኑም ቆም ተብሎ ከግለሰብና ከንኡስ ቡድን ውሳኔ ወጥተን
ድርጅታዊ ጥልቅ ውይይት ማድረግ ካልተቻለ ኢትዮጵያን መልሰን ወደ እርስ በእርስ ጦርነት
ልንጨምራት እንችላለንና በረጋ መንፈስ ይህንን ትልቅ የታሪክ ኃላፊነት አንወጣ፡፡ የራስን ታሪክ
አጠፍቶ ሀገርንም ከመበተን እንዲያድን ጠ/ሚኒስትሩ በራዕይም በመንፈስም ይታገዙ ዘንድ ሀሌሉያ
ብለን መፀለይ ግድ ሳይለን አልቀረም፡፡ "ሰባተኛው ንጉስ" በአጭር እንዲቀጭ ጌታም ፍቃዱ
አይደለምና፡፡ አሜን!!
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1107
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Re: አይ የቄሮዎች ነገር......

Postby ቆራሌ » Sun Aug 26, 2018 9:34 pm

አብዲ ኢሌ ከርቸሌ እንደወረደው -ኦቦ ለማ መገርሳስ ለዚህ በደል ተጠያቂ አይደለምን?
https://www.youtube.com/watch?v=ufWxNTWNKZo
ቆራሌ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 44
Joined: Wed Oct 05, 2016 12:58 am

Re: አይ የቄሮዎች ነገር......

Postby ክቡራን » Mon Aug 27, 2018 3:57 am

ትክክል ነው ቆራሌው "አንድ ቦታ ላይ ፍትህ ሲጠፋ ሌላም ቦታ ላይ ፍትህ እንደጠፋ ይቆጠራል" ይባላል፡፡ የህግ የበላይነት ካልሰፈነና የዲሞክራትክ ኢንስትቱይሽኖች በተግባር ካልዋሉ እውነተኛ ፍትህ ኢትዮጵያ ውስጥ አለ ብሎ መናገር እይቻልም፡፡ አብዲ ኢሌን ባመራር ድክመት የያዙ እጆች ጥፋት ያለባቸውን የኦሮሞ አመራሮችን ሊዘላቸው አይገባም፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7972
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: አይ የቄሮዎች ነገር......

Postby ቆራሌ » Sun Sep 16, 2018 9:09 pm

ቆራሌ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 44
Joined: Wed Oct 05, 2016 12:58 am

Re: አይ የቄሮዎች ነገር......

Postby ቢተወደድ1 » Mon Sep 17, 2018 11:39 am

የቀን ጅቦች ስትሉ የቀን ጅሎች አ.አ ቀለም ሲቀቡ ሰንብተዋል፡፡
ለነገሩማ ዛፍም ቂቤ ይቀቡ የለም፡፡
ቢተወደድ1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 210
Joined: Thu Sep 01, 2016 8:48 am
Location: Bisheftu

Re: አይ የቄሮዎች ነገር......

Postby ቆራሌ » Sat Sep 22, 2018 7:51 pm

የኦሮሚያ ፖሊሶች በፊሽካ እየተጠራሩ ከቄሮ ጋር ተባብረው አስፈጁን፡፡ ባንጻሩ ደግሞ- የፌደራል ፖሊሶችና ሰፊው የአዲስ አበባ ህዝቦች ያደረጉልንን ውለታ መቼም ቢሆን አንረሳውም - ይላሉ እነዚህ ብርቱ ወጣቶች
https://www.youtube.com/watch?v=U0yKcUuV4zg
ቆራሌ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 44
Joined: Wed Oct 05, 2016 12:58 am

Re: አይ የቄሮዎች ነገር......

Postby ቆራሌ » Fri Oct 05, 2018 4:11 am

ለመሆኑ እነዚህ ቄሮ - ሰው ናቸው ወይስ የዱር እንስሳ?
እንዴት ለሰላም ጉዳይ ለመደራደር ተወክለው የመጡ ሰዎችን ይገድላሉ፡፡ዘገባው የሪፖርተር ነው

መስከረም 15 ቀን 2011 ዓ.ም. አራት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የካማሺ ዞን አመራሮች በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በመገደላቸው ሳቢያ ግጭቱ ተቀስቅሷል፡፡

በተጠቀሰው ቀን የምዕራብ ወለጋ፣ የካማሺና የመተከል ዞኖች አመራሮች በሁለቱ ክልሎች አጎራባች ወረዳዎች ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ያጋጠመውን የሰላም መደፍረስና በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች እየፈጠሩት ያለውን ችግር ለመፍታት በማሰብ ለውይይት ተቀምጠው እንደነበር፣ አመራሮቹም በጋራ የተለያዩ ውሳኔዎችን ማሳለፋቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

የካማሺ ዞን አመራሮች በአሶሳ የተደረገውን ስብሰባ ጨርሰው ሲመለሱ፣ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ልዩ ስሙ መቀቢላ በተባለ ሥፍራ በታጣቂዎች ተገድለዋል፡፡

በግድያው ወቅት ጥቃቱን የፈጸሙት የታጠቁ ኃይሎች አመራሮቹ የነበሩባቸውን ሁለት ተሽከርካሪዎችም አቃጥለዋል፡፡
ቆራሌ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 44
Joined: Wed Oct 05, 2016 12:58 am


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests