ፈቃዱ ተክለማርያም ፲፱፻፵፰—ሐምሌ ፳፬ ቀን ፳፻፲

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ፈቃዱ ተክለማርያም ፲፱፻፵፰—ሐምሌ ፳፬ ቀን ፳፻፲

Postby ዘርዐይ ደረስ » Wed Aug 01, 2018 8:37 pm

ዝነኛውና ተወዳጁ የመድረክና የፊልም ተዋናይ ፈቃዱ ተክለማርያም በትላንትናው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1096
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ፈቃዱ ተክለማርያም ፲፱፻፵፰—ሐምሌ ፳፬ ቀን ፳፻፲

Postby ዘርዐይ ደረስ » Thu Aug 02, 2018 7:29 pm

ከአባቱ ከአቶ ተክለማርያም ኪዳኔና ከእናቱ ከወይዘሮ እልፍነሽ ወንድሙ በአዲስ አበባ ከተማ አራት ኪሎ አካባቢ ተወለደ።የመጀመርያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በአፄ ናዖድና ት/ቤቶች የተከታተለ ሲሆን በ፲፱፻፷፯ዓ∙ል∙ አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የቴያትርና የባህል አዳራሽ በተዋናይነት ተቀጠረ።እስከ ፲፱፻፹፭ ድረስ በዚሁ ቴያትር ቤት ሲሠራ ከቆየ በኋላ ወደ ብሔራዊ ቴያትር ተዛውሮ በህመም ምክንያት እስካቆመበት ጊዜ ድረስ ሠርቷል።በትምህርቱም በኩል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኪነጥበባት ወቴያትር ክፍል ለሁለት ዓመታት ያህል የቴያትር ኮርስ ተከታትሏል።ፈቃዱ ከተወዳጅ ባሕሪው ባሻገር በኢትዮጵያ ብዙም ያልተለመደውን ቀጠሮ አክባሪነትና የሥራ ዲሲፕሊን የተላበሰ ነበር።ከያኒው ባለትዳርና የአንድ ወንድ ልጅ አባት ነበር።
ፈቃዱ ሁለቱም ኩላሊቶቹ ሥራ በማቆማቸው ምክንያት ወደ ውጪ ሄዶ መታከም እንዳለበት ስለተነገረው የሚቀርቡት አርቲስቶች ባካሄዱት ቅስቀሳ በአጭር ጊዜ ውስጥ በመቶ ሺህ የሚቆጠር ብር ለመሰብሰብ ተችሏል።በአጋጣሚ በወቅቱ አንዲት የ፲፰ ዓመት ወጣት ተመሳሳይ የኩላሊት ችግር ስለነበረባት ዕርዳታ ለመጠየቅ ወደ ሚዲያ ወጥታ ስለነበር ፈቃዱ ህዝብን ያስደነቀ ውሳኔ አድርጓል።ይኸውም ለእርሱ ከተዋጣው ገንዘብ ላይ ፸፰ሺህ ብር ለልጅቷ እንዲሰጥ ማድረጉ ነበር።ምክንያቱ ግልጽ ባይሆንልኝም ፈቃዱ በተዋጣለት ገንዘብ ወደ ውጪ ከመሔድ ይልቅ ወደ ጸበል ነበር ያመራው።
ፈቃዱ በሙያው ላይ በቆየባቸው ፵፫ ዓመታት ወደ ፻፶ የሚሆኑ የመድረክ የቴሌቪዥን የሬዲዮና የፊልም ቴያትሮችና ድራማዎች ላይ ተሳትፏል። ከነዚህም ውስጥ
የመድረክ ቴያትሮች
ባለካባና ባለዳባ፣መቃብር ቆፋሪውና የሬሳ ሳጥን ሻጩ፣እሳት ሲነድ፣ኦቴሎ፣ቴዎድሮስ፣ንጉሥ አርማህ፣ኦዲፐስ ንጉሥ
የቴሌቪዥን ድራማዎች
ያልተከፈለ ዕዳ፣የአቤቀለሽ ኑዛዜ፣ባለጉዳይ
ፈቃዱ ከተዋናይነቱ ባሻገር መጽሐፍትን በመተረክም ይታወቃል።ሳቤላ፣የነበረው እንዳልነበረ፣ሞገደኛው ነውጤ እና ግራጫ ቃጭሎች በፈቃዱ ድምፅ በኢትዮጵያ ሬድዮ የተተረኩ መጻሕፍት ነበሩ።
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1096
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ፈቃዱ ተክለማርያም ፲፱፻፵፰—ሐምሌ ፳፬ ቀን ፳፻፲

Postby ቆራሌ » Sun Aug 05, 2018 2:46 pm

ፈቃዱ ታላቅ አርቲስት ነበር ፤ ለትውስታ ያክል

https://www.youtube.com/watch?v=RFPuO5M31NE
ቆራሌ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 49
Joined: Wed Oct 05, 2016 12:58 am

Re: ፈቃዱ ተክለማርያም ፲፱፻፵፰—ሐምሌ ፳፬ ቀን ፳፻፲

Postby ትርንጎ* » Fri Aug 10, 2018 4:31 pm

ነፍስ ይማር! ትልቅ የኪነጥበብ ሰው ነው ያጣነው፡፡
ትርንጎ*
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 715
Joined: Mon Oct 06, 2008 7:43 am


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 7 guests