ጠይና ይስጥልኝ በዘመኑ የመደመር ሂሳብ ተፈታሁ፡፡

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ጠይና ይስጥልኝ በዘመኑ የመደመር ሂሳብ ተፈታሁ፡፡

Postby ክቡራን » Thu Aug 02, 2018 6:09 pm

በመደመር ወይም ይሁን በመቀነስ በማካፈል ይሁን በማባዛት ምክንያቱን በማላውቀው ሁኔታ በዚህ ፎረም ላይ እንዳልሳተፍ ታግጄ ነበር፡፡ ዲሞክራሲ የእንድ ወገን ሙዚቃ የሚሰማበት የሙዚቃ ምርጫ ክፍለ ጊዜ አይደለም፡፡ ያንድ ወገን አስተሳሰብ ብቻ ያስተጋባ ለየት ያለ አመለካከት ያለን ኢትዮጵያውያን ያመለካከት ልዩነታችን ከማክብርና ዲሞክራሲን በተግባር ከመግለጥ ይልቅ የዋርካ እስተዳዳሪዎች ማባረርን መመርጣቸው ያሳዝናል፡፡ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ሃሳብን የምንግለጥበት ቡዙ መድረኮች ተከፈተዋል፡፡ ቡዙ ኢትዮጵያውያን ሃሳቤን ሊሰሙበት ና ሊያነቡበት በሚችሉበት መንገድ ዛሬም ስለ ኢትዮጵያዊነት ማዘሜን እላቆምኩም፡፡ የቡዙዎችን ድጋፍ እድናቆት እንዲሁም ተቃውሞም ( በተወሰነ ደረጃ) አግኝቻለሁ፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን ዛሬም በዚህ መድረክ ይህን ከስር የጣፍኩትን እላለሁ....ይሄ የማልተወው፣ የማይለወጥ፣ ትንቢታዊ ቃሌ ነው፡፡ ይሄ የሚያመው አድሚን ራሱን ለካህን ያሳይ ኢትዮጵያውነቱንም ይጠይቅ፡፡

ወደዳችሁም ጠላችሁም እኛ ኢትዮጵያውያን ነን:: ሌላ ምድር.. ሌላ ኣገር የለንም:: ወላይታነት ኢትዮጵያዊነት ነው… በኦሮሞነት ውስጥ ኢትዮጵያዊነት ኣለ… ትግራዋይነት ኢትዪጵያዊነት ነው.. ባማራነት ውስጥ ኢትዮጵያዊነት ኣለ :: ኣገውና ሽናሻ ቅማንትነትና ፈላሻ ጉራጌነትና ሃመር ኣጋሜነትና ሽዋ በር የኢትዮጵያውነት ውበት.. የኢትዮጵያዊነት ፈርጦች ናቸው ::
እነዚህ ሁሉ የኢትዮጵያ ዘምባቦች ናቸው:: በባህር ዳር የተተተከለች ዘምባባ ንፋስ እንደሚያወዛውዛት ሁሉ ንፋስ ሲመጣ እነዚህ ሁሉ ኣብረው ይወዛወዛሉ.. ከንፋሱ ጋር ያዘማሉ.. ንፋሱ ሲያልፍ ደሞ ኣብረው ቀና ይላሉ:: ወደዳችሁም ጠላችሁም እኛ ሁላችን ኢትዮጵያውያን ነን:: ሌላ ኣገር ሌላ ምድር የለንም:: ኣበባ ኣንድ ኣይነት ቀለም ቢኖረው ኖሮ ኣያምርም ነበር የኣበባ ውበት ነጭ ሮዝ ወይን ጠጅ ቀይ ቢጫ ውሃ ሰማያዊ በመሆኑ ኣበባን ኣይቶ የሚያልፍ የለም:: ስራ ቡዙ የሚባሉት ንቦች እንኴን ለማረፊያነት የሚመርጡት ኣበቦችን ነው:: እንደ ኣበቦች ለማማር እንደ ኣበቦች ማረፊያ እንድንሆን እጅ -ለእጅ መያያዝ ኣለብን:: ኢትዮጵያዊነት በዚህ ይገለጻል:: ኢትዮጵያዊነት በዚህ ይታያል:፡፡
እመለሳለሁ ጊዜ ካገኘሁ፡፡ የዲሞክራሲ መንፈስ ለገባችሁ አድሚኖች ምስጋናዬ ይድረስ ፡፡ እሁን የተደመራችሁ ይመስላል፡፡ ሌሎችንም ፍቱ፡፡ የሙሴ ድምጥ ለፈርኦን ይህን ይላል ..."ህዝቤን ልቀቅ!!"
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7972
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: ጠይና ይስጥልኝ በዘመኑ የመደመር ሂሳብ ተፈታሁ፡፡

Postby ፋኖፋኖ » Thu Aug 02, 2018 7:07 pm

ትምክተኛው/ከፋፋዩ የወያኔ ጋዜጠኛ (fake news) እኔ አድሚን ብሆን ቡዙ የምትለውን አስተካክለህ ብዙ እስከምትል ድረስ እንደገና አግድህ ነበር
ኢትዮጵያውነት በመወለድ በዜግነትና በጸጋ የወረስኩት ህያው ሀብት ንብረት ቅርስ ማንነት ነው : ሰጭም ቀሚም የለብኝ
ፋኖፋኖ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 936
Joined: Wed Nov 08, 2006 10:39 am

Re: ጠይና ይስጥልኝ በዘመኑ የመደመር ሂሳብ ተፈታሁ፡፡

Postby ቆቁ » Thu Aug 02, 2018 7:31 pm

እንኩዋን ተደመርክ ክቡዬ ነፍሱ
እኔስ የት ገባህ ብዬ ሳስብ ሳስብ እንድ ስሙ የሚከብደኝ ሰው መጥቶ አንተ መስለኽኝ ነበር
መቸም ተደመርኩ ስትል 1 + 2 = ክቡዬ ሳይሆን 1+1 = ክቡዬ መሆን ይገባዋል
በሁለት ምላስ መብላትም መናገርም አይቻልምና

ስትደመር ደግሞ ፌክ አርቲክል እያመጣህ እንደ ቀድሞህ አትለጥፍ
ፌክ አርቲክል መለጠፍ ደግሞ መደ'መር አይደለምና
ፌክ ኒውስ አትለጥፍ የራስህን ሐሳብ ለመጻፍ ሞክር
እንደዛ ብቻ ሲሆን መደ'መር የሚቻለውና
ፈላስፋው ወንድምህ


ስማ ዳግማዊ ዋለልኝም ና ተደመር እንበለው

ለሾተልም ንገረው ና ተደመር ብለህ

እናውራ ካልክ ስለ ኢትዮጵያ እናውራ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4016
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ጠይና ይስጥልኝ በዘመኑ የመደመር ሂሳብ ተፈታሁ፡፡

Postby ፉኚዶ ተራራ » Fri Aug 03, 2018 11:54 pm

እንዴ ከቡራን ታላቅ ሰው፡ እንኳን ደህና መጣህ። ኣዎን በመሰረቱ መደመር ጥሩ ነው ፡ ቢሆንም ግን ኔጋቲቭ ቁጥሮቸን ለብቻ ሳይለዩ ሁሉንም ኣንድ ላይ መደመር በመርህ ደረጃ የሚያዛልቅ ኣይመስልም።
ከሰላምታ ጋር፡
ድፋባቸው ቶሌራ ኣስገዶም
የኢህኣዴግ የመደመር ሂደት የበላይ ተቆጣጣሪ
ፉኚዶ ተራራ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 95
Joined: Wed Jul 17, 2013 6:34 pm
Location: americas

Re: ጠይና ይስጥልኝ በዘመኑ የመደመር ሂሳብ ተፈታሁ፡፡

Postby ደጉ » Sun Aug 05, 2018 10:26 am

:-) :-) :-) 3 ጊዜ ብቻ ሳቄ መጣ !!
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4413
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Re: ጠይና ይስጥልኝ በዘመኑ የመደመር ሂሳብ ተፈታሁ፡፡

Postby ዲጎኔ ሞረቴ » Tue Aug 07, 2018 3:49 am

ክቡ
ባልታወቀ ምክንያት ዛፎቼ ተወስደው ተመልሼ ገብቻለሁ፡፡እንኳን ለመደመር አበቃህ መከፋፈል ከወያኔ ጋር ግብአተ መሬቱ በሂደት ላይ ሲሆን በጅጅጋ በመቀሌ ሊንሰራራ ቢቃጣውም ሳሞራ ያኔ ባለው ዘይቤ መልሰን እንቀብረዋለን፡፡ እይዞን አጆሃ ሃወይ ከጄነራል ጀቤና ከአምባሳደር ትርፉ ጋር በመደመር ያጸናህ ዘንድ ምልጃ አቀርባለሁ፡፡ዋለልኝንም ሌሎቹምን ብቅ በሉ የመደመር መንፈስ ይግባባችሁ በልልኝ፡፡
ዲጎኔ ሞረቴው ከአክቲቪስት ጃዋር ጋር ከቄሮ ትግል መነሻ- ጊንጬ

ክቡራን wrote:በመደመር ወይም ይሁን በመቀነስ በማካፈል ይሁን በማባዛት ምክንያቱን በማላውቀው ሁኔታ በዚህ ፎረም ላይ እንዳልሳተፍ ታግጄ ነበር፡፡ ዲሞክራሲ የእንድ ወገን ሙዚቃ የሚሰማበት የሙዚቃ ምርጫ ክፍለ ጊዜ አይደለም፡፡ ያንድ ወገን አስተሳሰብ ብቻ ያስተጋባ ለየት ያለ አመለካከት ያለን ኢትዮጵያውያን ያመለካከት ልዩነታችን ከማክብርና ዲሞክራሲን በተግባር ከመግለጥ ይልቅ የዋርካ እስተዳዳሪዎች ማባረርን መመርጣቸው ያሳዝናል፡፡ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ሃሳብን የምንግለጥበት ቡዙ መድረኮች ተከፈተዋል፡፡ ቡዙ ኢትዮጵያውያን ሃሳቤን ሊሰሙበት ና ሊያነቡበት በሚችሉበት መንገድ ዛሬም ስለ ኢትዮጵያዊነት ማዘሜን እላቆምኩም፡፡ የቡዙዎችን ድጋፍ እድናቆት እንዲሁም ተቃውሞም ( በተወሰነ ደረጃ) አግኝቻለሁ፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን ዛሬም በዚህ መድረክ ይህን ከስር የጣፍኩትን እላለሁ....ይሄ የማልተወው፣ የማይለወጥ፣ ትንቢታዊ ቃሌ ነው፡፡ ይሄ የሚያመው አድሚን ራሱን ለካህን ያሳይ ኢትዮጵያውነቱንም ይጠይቅ፡፡

ወደዳችሁም ጠላችሁም እኛ ኢትዮጵያውያን ነን:: ሌላ ምድር.. ሌላ ኣገር የለንም:: ወላይታነት ኢትዮጵያዊነት ነው… በኦሮሞነት ውስጥ ኢትዮጵያዊነት ኣለ… ትግራዋይነት ኢትዪጵያዊነት ነው.. ባማራነት ውስጥ ኢትዮጵያዊነት ኣለ :: ኣገውና ሽናሻ ቅማንትነትና ፈላሻ ጉራጌነትና ሃመር ኣጋሜነትና ሽዋ በር የኢትዮጵያውነት ውበት.. የኢትዮጵያዊነት ፈርጦች ናቸው ::
እነዚህ ሁሉ የኢትዮጵያ ዘምባቦች ናቸው:: በባህር ዳር የተተተከለች ዘምባባ ንፋስ እንደሚያወዛውዛት ሁሉ ንፋስ ሲመጣ እነዚህ ሁሉ ኣብረው ይወዛወዛሉ.. ከንፋሱ ጋር ያዘማሉ.. ንፋሱ ሲያልፍ ደሞ ኣብረው ቀና ይላሉ:: ወደዳችሁም ጠላችሁም እኛ ሁላችን ኢትዮጵያውያን ነን:: ሌላ ኣገር ሌላ ምድር የለንም:: ኣበባ ኣንድ ኣይነት ቀለም ቢኖረው ኖሮ ኣያምርም ነበር የኣበባ ውበት ነጭ ሮዝ ወይን ጠጅ ቀይ ቢጫ ውሃ ሰማያዊ በመሆኑ ኣበባን ኣይቶ የሚያልፍ የለም:: ስራ ቡዙ የሚባሉት ንቦች እንኴን ለማረፊያነት የሚመርጡት ኣበቦችን ነው:: እንደ ኣበቦች ለማማር እንደ ኣበቦች ማረፊያ እንድንሆን እጅ -ለእጅ መያያዝ ኣለብን:: ኢትዮጵያዊነት በዚህ ይገለጻል:: ኢትዮጵያዊነት በዚህ ይታያል:፡፡
እመለሳለሁ ጊዜ ካገኘሁ፡፡ የዲሞክራሲ መንፈስ ለገባችሁ አድሚኖች ምስጋናዬ ይድረስ ፡፡ እሁን የተደመራችሁ ይመስላል፡፡ ሌሎችንም ፍቱ፡፡ የሙሴ ድምጥ ለፈርኦን ይህን ይላል ..."ህዝቤን ልቀቅ!!"
ዲጎኔ ሞረቴ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 24
Joined: Thu Oct 06, 2016 3:59 pm

Re: ጠይና ይስጥልኝ በዘመኑ የመደመር ሂሳብ ተፈታሁ፡፡

Postby ክቡራን » Wed Aug 08, 2018 6:07 pm

ታላቁ ፈላስፋ ቆቅ ፣ ፉኚዶ ተራራ፣ ዲጎኔ ሞረቴ ሰላምታዬ በያላችሁበት ይድረስ፡፡ የኢትዮጵያ አምላክ ረጅም እድሜና ጤና ይስጣችሁ፡፡ ሌላ ሰው አላየሁም፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7972
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: ጠይና ይስጥልኝ በዘመኑ የመደመር ሂሳብ ተፈታሁ፡፡

Postby ኮኮቴ » Thu Aug 09, 2018 1:22 am

ክቡ ... ክቡነት እንኳን ደህና መጣህ፡፡ እኛ "ተስፈኛ ክድሬዎች (ተካ)" ሆነን ... ያዙኝ ልቀቁኝ ስንል ... እንዳንተ ያለ ... አንድ እንኳን የ"ቀደሞውን ስራርአት" እየናፈቀ የሚቃወምን ሰው በማጣታችም ከፍቶን ነበር ፡)

እንዴት ነው ጩጬዎቹ አደጉ? ተጨማሪ ልጅ ደመርክ ... ወይስ ... የመንግስት ተቆራጭ በመቋረጡ ... አንተም ማስወለድ አቋረጥክ ፡)

ለማንኛውም እንኳን ከዋርካ እስር ነጻ ወጣህ!

ለገ ኮኮቴ
o-o-o-o-o-o-o-o-o-o-o-o
".... Indeed, we Ethiopians are a beautiful multi-lingual and multi-cultural people who in a flower vase called Ethiopia decorate the great continent of Africa", Professor Ephraim Isaac
ኮኮቴ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1289
Joined: Wed Nov 04, 2009 2:07 am

Re: ጠይና ይስጥልኝ በዘመኑ የመደመር ሂሳብ ተፈታሁ፡፡

Postby ክቡራን » Fri Aug 17, 2018 12:17 pm

ጠይና ይስጥልኝ ወገን ኮኮቴ እንደምነህ ልጆቼ ደህና ናቸው፡፡አፍ ፈተወልኛል፣ ባቢም ይሉኛል፣ ግንባሬንም በፍቅር ይስሙታል፡፡ እኔም የናታቸውን ከንፈር በፍቅር እስማለሁ፡፡ እነሆ የሰማይ አምላክ አልተወኝም፣ ደስታንም አልፈነገኝም ፣ የሱ ፍቃድ ቢሆን እናታቸው ሴት ልጅ ትፈልጋለች፡፡ አንተስ ወንድም አለም ደህና ነህ?? እንደ ድሮው እሁንም እጥር ትዘላለህ? ወይስ ቡና አፍልታ ቤትህን አሙቃ የምትጠብቅህን ወይዘሮ አግኝተሃል ? ካልሆነ ንገረኝ፣ ላፈላላግ ፣ ሽምግልናም ብላክ አላስፍርህም፡፡ ሎል፡፡ ሰላም ሁንልኝ፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7972
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: ጠይና ይስጥልኝ በዘመኑ የመደመር ሂሳብ ተፈታሁ፡፡

Postby ዞብል2 » Fri Aug 17, 2018 8:23 pm

ክቡራን(ሜሹ) ጠ/ሚ አቢይ ወያኔዎች ከለላ አድርገው ህዝብን ሲያሰቃዩበት ና ሲገድሉበት፤ ሀገር ሲዘርፉበት፤ የነበረውን፡ ህገ መንግስት፡ እውን ለማድረግ ነው የሚጥረው፡ታዲያ አጎትህ ደበሳይ(ደበረ ሲኦል) ምን ተነካ ብሎ ነው ህገ መንግስቱ ይከበር እያለ የሚያላዝነው? አሁንም እኮ ጠ/ሚሩ ኢህአድግ ነው.......ወይስ እንደ ቀድሞው ካልዘረፍን ነው?
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2006
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ጠይና ይስጥልኝ በዘመኑ የመደመር ሂሳብ ተፈታሁ፡፡

Postby ክቡራን » Sat Aug 18, 2018 5:58 am

ዞብል ( መረባ ጠጅ ቤት) እኔ እኮ የተደመርክ መስሎኝ ነበር፡፡ ግባና ፖሊሲ ይዘህ ታገል.... if you have one..lol በ 2020 ወይ ፓርላማ ወይ 22 አሹ ቤት እናይሃልን፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7972
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests