ለካ አላት

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ለካ አላት

Postby እቴጌይት » Sun Aug 12, 2018 3:44 am

ለካ አላት 

የባርነት ዘመኗ - ስቃይዋ ያለቅጥ ረዝሞ
የሰቆቃ ለቅሶዋ - ከትውልድ ትውልድ ከርሞ 
የጥላቻ ባህሩን - በፍቅር በትር  ከፋይ
ዘጸአቷን ፈጻሚ - ከንዓኗን የሚያሳይ  
እምባዋን ከጉንጯ 'ሚያብስ - ልጆቿን የሚያሳማማ
ፈጣሪ የላትም ስንል - ኤሎሄዋን 'ሚሰማ

ከእባብ እንቁላል እርግብ -   ከተኩላ ሆድ በግ ሰርቶ
ለፈ'ሮን ቀንበር ፍዳ - ሁሌ የማይተዋት ትቶ
ታምራቱን የሚያሳይ - ዛሬም የሚታደጋት
ኢትዮጵያ ለካ አምላክ አላት!
እቴጌይት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 656
Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm

Re: ለካ አላት

Postby ዲጎኔ ሞረቴ » Sun Aug 12, 2018 4:50 am

እቴጌይት
የሰው ፊት አይቶ የማያዳላ አምላክ ይህን ለኢትዮጲያ ስላደረገ ምስጋና ይድረሰው!
ዲጎኔ ሞረቴው ከቅኖቹ እቴጌ ተዋበች እቴጌ ጣይቱ እቴጌ ዘውዲቱ እቴጌ መነን እልፍኝ


እቴጌይት wrote:ለካ አላት 
የባርነት ዘመኗ - ስቃይዋ ያለቅጥ ረዝሞ
የሰቆቃ ለቅሶዋ - ከትውልድ ትውልድ ከርሞ 
የጥላቻ ባህሩን - በፍቅር በትር  ከፋይ
ዘጸአቷን ፈጻሚ - ከንዓኗን የሚያሳይ  
እምባዋን ከጉንጯ 'ሚያብስ - ልጆቿን የሚያሳማማ
ፈጣሪ የላትም ስንል - ኤሎሄዋን 'ሚሰማ

ከእባብ እንቁላል እርግብ -   ከተኩላ ሆድ በግ ሰርቶ
ለፈ'ሮን ቀንበር ፍዳ - ሁሌ የማይተዋት ትቶ
ታምራቱን የሚያሳይ - ዛሬም የሚታደጋት
ኢትዮጵያ ለካ አምላክ አላት!
ዲጎኔ ሞረቴ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 24
Joined: Thu Oct 06, 2016 3:59 pm

Re: ለካ አላት

Postby ኮኮቴ » Thu Aug 16, 2018 2:16 pm

ከዋርካ ፈርጦች ውስጥ አንዷ የነበርሽው እህታችን እቴጌይት ... ዋርካ ላይ ዳግም ስላየሁሽ ደስብሎኛል ... ስለ ውብ ግጥምሽም ብእርሽ (ኪቦርድሽ) ይባረክ ብለናል!

ኮኮቴ
o-o-o-o-o-o-o-o-o-o-o-o
".... Indeed, we Ethiopians are a beautiful multi-lingual and multi-cultural people who in a flower vase called Ethiopia decorate the great continent of Africa", Professor Ephraim Isaac
ኮኮቴ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1289
Joined: Wed Nov 04, 2009 2:07 am


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 7 guests