የሁለት ቁርስ ግብዣዎች ወግ ... በትግራይ ህዝብ እና በወያኔ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የሁለት ቁርስ ግብዣዎች ወግ ... በትግራይ ህዝብ እና በወያኔ

Postby ኮኮቴ » Fri Sep 14, 2018 8:53 pm

ያው የቀን እንጂ የሰው ጀግኛ የለውም እንዲሉ ... ወያኔና ሻቢያን ... በ1983 ... ጊዜ አጀግኗቸው በስልጣን መሰላል ወደላይ ሲፈነጠሩ የታየ አንድ በጎ ክስተት ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ወታደሮች ስብእናቸውን ተገፈው ... ከኤርትራ ተባረው ወደ ሃገራቸው ሲመለሱ ... የትግራይን ምድር ባቋረጡበት ግዜ ... ደጋጎቹ የትግራይ እናቶች እና አባቶች ... የተራቡትን አብልተው ... የታረዙትን አልብሰው በፍቅር ተቀብለው እንደሸኟቸው ሰምተን ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ከ40አመት በላይ ኦሮሚያን ከኢትዮጵያ ካልገነጠልኩ እንዳለ ጎልምሶ ያረጀው ኦነግ ... የመጨረሻ የጡረታ ግዜውን ካሳለፈበት ከአስመራ ወደ ኢትዮጵያ በዛላንበሳ በኩል ሲገባ ... ወያኔዎች ... ተቀብለው "ቁርስ" አብልተው ወደ መሃል አገር ሊሽኙት ነው ሲባል ሰማን፡፡ እረ እንደውም የነ ክቡ ዘመዶች የሶሻል ሚዲያ ፕሮፋይላቸውን በኦነግ ባንዲራ ቀይረዋል፡፡ የኦሮሞን ወጣት በኦነግ ስም አስረው ... የእስር ቤቱን ቋንቋ ኦሮሚኛ እስኪሆን እንዳላደረጉት ሁሉ .. ድንገት ወያኔዎች ... ከኦነግ ጋር ፎንቃል የጠለፋቸው ለምን ይሆን?? መቼም ... ግም ለግም አብረህ አዝግም እንደሚባለው ... የአሁኑ ፍቅር የጥፋት ተልኮን እንደያዘ ለማወቅ ... እንደ ታምራት ገለታ ጠንቋይ መሆን አያስፈልግም፡፡

ለማንኛውም ... ቄሮዎች "ኢትዮጵያ እናታችን" ሲሉ ተስምተው ... ወያኔን ክው አድርገውታል ... የውያኔ/ኦነግ ፍቅርም ሳይከርም ባጭሩ መቀጨቱ ነው፡፡
ለገ፟ ኮኮቴ
o-o-o-o-o-o-o-o-o-o-o-o
".... Indeed, we Ethiopians are a beautiful multi-lingual and multi-cultural people who in a flower vase called Ethiopia decorate the great continent of Africa", Professor Ephraim Isaac
ኮኮቴ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1290
Joined: Wed Nov 04, 2009 2:07 am

Re: የሁለት ቁርስ ግብዣዎች ወግ ... በትግራይ ህዝብ እና በወያኔ

Postby ቆቁ » Mon Sep 17, 2018 3:53 pm

ኮኮቴ አንድ ጥያቄ
ፈላስፋው የመጠየቅ መብት አለው ያልገባው ነገር ካለ መሰለኝ
ሌላውም እንደዚሁ
በዜናው ብዛት ፡በፌክ ኒውሱ ብዛት፡ በፌክ ቪዲዮው ፡ብዛት ፈላስፋው የዘለለኩት ነገር ያለ ስለመሰለኝ ነው
መቀሌ የገባው የኦነግ ሰራዊት ብቻ ነበር ?
ሌላ ሰራዊት በመቀሌ በኩል አላላፈም ?
የምናነበው የቁርሱ ወይም የምሳው ዝግጅት ስለኦነግ ሰራዊት ብቻ ነው

ምን ትላለህ ?
ከአክብሮት ሰላምታ ጋር

አንድነታችንና ልዩነታችን ለዘላለም ይኖራል

የሰላም መጨረሻው ደስታና ፍቅር ነው
የጦርነት መጨረሻው ሐዘንና እልቂት ነው

ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4067
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 11 guests

cron