በእጅ የሚሰጥ ደብዳቤ፡፡

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

በእጅ የሚሰጥ ደብዳቤ፡፡

Postby ቢተወደድ1 » Fri Nov 02, 2018 1:50 pm

ወንድም አለም
ሰሞኑን ሳስብህ ከረምኩ፡፡ ይገርምሃል እክስትህን በዚያ እለት ገበያ ተገናኝተን ጤንነትህን አበሰረችኝ፡፡ እሰየው አኳልኩ፤ እንዳውም ሰሞኑን ሳስበው ነው የከረምኩት ብላት፤ ዲየብዳቤ ጣፍለት አለችንኝ፡፡ አገሩ ቀዬው እንዴት ነው? ሰው በላው አገር ገብታቹህ እልም አላቹህ አይደል? ይሁን እስቲ፤
ባለፈችው ልደታ ማሪያም ግድም ጥጃዬ ገመድ በጥሳ ከሰው ማሳ ገብታ ተገኘች፡፡ ወቅቱ የመኸር ጊዜም አይደል? ማሳውን የሚጠብቀው ልጅ የወ/ሮ አሰለፍን ልጅ ውሃ ልታመጣ ወንዝ ስትወርድ ተከትሎዋት ሄዶ ኖሮ ቁልቁል በነአቶ ይበጃል አጥር በኩል ያለውን የጤፍ ማሳ ወረደችበት፡፡ ወይ የዘንድሮ ልጆች ገና ከመሬት ብቅ ሳይሉ ጎረመሱብን ኮ፡፡ ሲጀምረው አብሬሽ ካልመጣሁ እንስራሽን እሰብራለሁ እያለ ቢያስፈራራት እሷም ቤተሰብ ለቤተሰብ እንዳይቀያየሙ ብላ ፈቀዲየችለት፡፡ አንድ ፈሬ ልጅኮ ኒየበረች፤ አጎጠጎጤዎችዋ ቆመው ዲየግፉኝ የሚሉ ይመስላሉ፡፡ ያንን ረጅም ቀሚስ እየለበስች ዳሌዋን ትደብቀዋለች እንዪ ከተማሪቤት ስትሄድ ብታያት አይንህ አይቶም አይጠግበው፡፡ ይሄን የማዳበሪያ እህል እየበሉ ካለእድሜያቸው አደጉብን፡፡
ወንድም ዐለም
የሰኔ ክረምት ሳይጠባ ብቅ ብትል መልካም ነው፤ አለለዚያ የግሸን ወንዝ ይሞላና ጊዜህን ከተማ ነው የምታሳልፈው፡ ለከተማ ከተማ ያለህበት ይበቃል፡፡

ወንድምህ ደባልቄ ማንያዘዋል፡፡
ቢተወደድ1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 225
Joined: Thu Sep 01, 2016 8:48 am
Location: Bisheftu

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest