አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው ?

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው ?

Postby ቆቁ » Sun Feb 10, 2019 6:20 pm

ምንድነው ጥቅማ ጥቅሙ ? እሴቱ ?
መሬት በሲግናል ?
ወይስ የስራ እድል በለገሐር ?
ወይስ ነዋሪው ሕዝብ ?

ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4017
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Sun Feb 10, 2019 6:38 pm

London has a diverse range of people and cultures, and more than 300 languages are spoken in the region.[54] Its estimated mid-2016 municipal population (corresponding to Greater London) was 8,787,892,[4] the most populous of any city in the European Union[55] and accounting for 13.4% of the UK population.[56] London's urban area is the second most populous in the EU, after Paris, with 9,787,426 inhabitants at the 2011 census.[57] The population within the London commuter belt is the most populous in the EU with 14,040,163 inhabitants in 2016.[note 4][3][58] London was the world's most populous city from c. 1831 to 1925.[59]
300 ቁዋንቁዋ ?
ለየትኛው ቁዋንቁዋ ነው የለንደን እሴት ? ጥቅማ ጥቅሙ
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4017
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sun Feb 10, 2019 7:01 pm

እንደ አመለካከትህ ነው፡፡
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1053
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Tue Feb 12, 2019 6:22 pm

አመለካከቴ እንደ ጣይቱ ብጡል ነው
የአንተስ አመለካከት እንዴት ነው ?

ያኔ አዲስ አበባ በፍልውሃ ( ፊንፊኔ) ፡ በአዋሬ፡ በየካ ፡ በጉለሌ ፡ በገፈረሳ ፡ ተከፋፍላ መንደራ መንደር በነበረችበት ዘመን ክረምት አልፎ የበጋው ወራት ሊመጣ ሲል ክእንጦጦ ተራራ ወደ ታች ለተመለከታት እጅግ ውበት ያላት በአደይ አበባ ያሸበረቀች የመንደሮች ጥርቅም ነበረች
ይህንን ተመልክታ ነው ጣይቱ ብጡል አደይ አባባ በማለት አዲስ አበባን የገለጸቻት

አዲስ አበባ ከአደይ አበባ የፈነደቀ ነው ፡፡
ፈላስፋው ቆቁ ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች አንዱ
ለኢትዮጵያ ሕዝቦች ፍቅርና ሰላም
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4017
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ዘርዐይ ደረስ » Tue Feb 12, 2019 8:21 pm

የእቴጌ ጣይቱን አዲስ አበባ አንተ አታውቃትም።የአሁኗን አዲስ አበባ እቴጌ ጣይቱ አያውቋትም።እንዴት ነው ተመሳሳይ አመለካከት የሚኖራችሁ?
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1053
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Thu Feb 14, 2019 6:05 pm

ከእንጦጦ ተራራ ሆነህ ወደ ታች ስትመለከት ልክ ጣይቱ ብጡል እንደተመለከተችው ነው አዲስ አበባን የምትመለከታት
ከምኒሊክ ቤተ መንግስት እናት ላይ ሆነህ ዙሪያውን ብትመለከት የእዲስ አበባን ራዲየስ በትክክል እንደ ጣይቱ ብጡል ልትመለከት ትችላለህ

ምናልባት ልዩነታችን
ዛሬ ህንጻ ፡ ያኔ አደይ አበባ
ያኔ ኢትዮጵያ ዛሬ ክልል
እኔም እንደ ጣይቱ ኢትዮጵያ ስል
እኔም እንደ ጣይቱ አዲስ አበባ ስል
አንተም እንደ ጣይቱ አዲስ አበባ ስትል
እንተም እንደ ጣይቱ ኢትዮጵያ ስትል
አመለካከታችን እንደ ጣይቱ ብጡል ይሆናል ማለት ነው
አይደለም ?
ጃዋርና በቀለ ገርባ ፊንፊኔ ሲሉስ ?

ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4017
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Sat Feb 16, 2019 6:08 pm

ያኔ ፡_ጥንት፡ አዲስ አባባ ፡ልዩ፡ መልክ፡ ነበራት ፡፡
እንደ፡ ዛሬው፡ ፈርሰው፡የማይታደሱ፡ ሕንጻዎች፡ ቢቆለሉባት፣ኢንቨስተር፡ የሚባሉ፡ ድንጋይ ፡ራሶች ፡ድንጋይ፡ በድንጋይ ፡ሳይክቡባት፤
መንደሮቹዋ ፡ሁላ፡ በእንጨት፡ ምሰሶና፡ በጭቃ ፡ተመርገው ፡የተሰሩ፡ ቢፈርሱም፡ ለመስራት፡ ቀናት፡ የማይፈጁ ፡ ክብ፡ ቤቶች ፤እርጭ እምጭ ያለች ፡አበባ ፡የሆነች፡ ከተማ ፡ነበረች፡፡
የገፈርሳ፡የቀበና፡ የቡልቡላ ፡ወንዞችና፡ ገባሪ፡ እና፡ ትናንሽ ፡ወንዞች ፡እዚህም ፡እዛም ፡ብቅ፡ ብቅ፡.የሚሉባት፡ ውብ፡. አዲስ ፣ውብ ፡አደይ፡ አበባ፡ ነበረች ፡፡
በአደይ፡ አዲስ አበባ ፡የሚኖሩት ፡ፍጡራን ፡እንደ ፡ዳርዊን፡ የጋላፓጎስ፡ ደሴት ፡ ፍጡራን፡ በብዛት፡ ተመሳሳይ ፡ናቸው ፡ብንል ፡ምንም፡ ስህተት ፡አይኖርም ፡፡
ያን፡ ጊዜ ፡አዲስ፡ አበባን፡ እንደ ፡ጋላፓጎስ ፡የሚያጠናት፡ የሚመራመርባት፡ ሐገራዊ፡ ፍጡር፡ ባለመኖሩ ፡ብዙም፡ ባንበሳጭም፤ ዛሬ ፡ግን ፡በመኪና፡ ለዛውም ፡በተሰባበረ ፡መኪና፡ ጭስና ፡ የሰይጣኖች፡ መዳቀሊያ ፡በሚመስሉ፡ የተዘጉ ፡ቪላ ፡ቤቶች ፡እና ፡እንደ፡ ባቢሎን ፡ግምብ ፡ከኪሎሜትር፡ በላይ፡ በሚርቁ ፡የሰይጣኖች፡ መደነሻ፡ በሚመስሉ፡ ፎቆች፡ መልኩዋ፡ እጅጉን፡ ተቀይሮ፡ እንመለከታለን ፡፡
ስልጣኔ ፡እንበለው ?
ስልጣኔን.፡ እኛ ፡ኢትዮጵያውያን ፡ከውጭ፡ እንማር ?
ምናለን ፡ደሳሳው፡ ክቡ ፡ጎጆእችን ፡ ?
ምናለን ፡ ብርጩማ ?
ምን ፡አለን፡ የመደብ ፡መቀመጫው?

ዛሬ ፡ከየት፡ ላግኘው፡ የሚያስብል፡ ባህላዊ ፡እቃችን፡ የቤት፡ አሰራር፡ ስልታችን፡ ሁላ ፡የትም፡ ተወርውሮ ፡ፎቅ፡ በፎቅ ፡እንደ ፡ኒዎርክ፡ ከተማ!
ዋ ፡አዲስ አበባ !!
ለዚህም፡ ነው ፡ጥቅሙ፡ ጥቅማ፡ ጥቅሙ ፡ እሴቱ ፡የሚባለው፡፡
ሕዝብን ፡የማይጠቅም፡ ነገር ፡ግን ፡ግለሰቦችን፡ በከንቱ፡ የሚያሳብጥ፡፡
ዋ፡ አዲስ አበባ !

የታሉ የአዲስ አበባ ሸረሪቶች?
የታሉ የአዲስ አበባ ጉንዳኖች?
የታሉ እነዛ ድንቅዬ የአዲስ አበባ ቢራቢሮውች ?
የታሉ እነዛ የአዲስ አበባ ብርቅዬ ወፎች ?
የታሉ እነዛ የአዲስ አበባ ርግቦች ፡ ያ ቃና ያለው ዜማቸው ?
የታሉ እነዛ የአዲስ አበባ ትክንትኮች?
እረ ስንቱ?
ከየት እናምጣቸው ከየት እንውለዳቸው ?
ዋ አዲስ አበባ
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4017
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Sun Feb 17, 2019 3:51 pm

እስቲ እንጠያየቅ

የሎንዶን ከተማ እንዴት ተመሰረተች ? የፕራግ ከተማ እንዴት ተመሰረተች ? የሞስኮ ከተማ እንዴት ተመሰረተች?
ይህንን እንድጽፍ ያስገደደኝ የሆነ ግለሰብ በሆነ ካናል የልቡን ሲናገር ሰምቼው ነው፡፡
አሌክሳንዲርያ እንዴት ተመሰረተች?
እነዚህ ከላይ የጠቀስኩዋቸው ከተሞች እንደ አደይ አበባ እዛም እዚህም ብቅ ብቅ ያሉ ከተሞች አልነበሩም፡፡
ለነዚህ ከተሞች ከተማቸው እንዴትም ትመስረት ታሪካቸው ነው ቱሪስት መሳቢያም ነው፡፡
የኛዎች ግን የሚገርሙ ናቸው
አዲስ አበባ እሴቱዋም ጥቅሙዋም በመላው የኢትዮጵያ ልጆች ስራ የተከማቸው ነው ስለሆነም የምንመኘው እንደ ነገር ብቻ ይሆናል
መልካም አስተዳደር ፡፡
ምናልባት ለዚህ ግለሰብ ከልቡ እና በልጅነት ስሜት ሆኖ አዲስ አበባን ከመግለጽ የከተሞች አመሰራረት እንዴት እንደሆነ ቢያነብና ቢያጠና አዲስ አበባ እንዴት እንደተመሰረተች ሊገባው ይችላል ብዬ ስለማምን ነው፡፡
አዲስ አበባ በኢትዮጵያ ልጆች ነው የተመሰረተችው ፡፡ ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች ተካፍለውባታል ፡፡
የአዲስ አበባ ምስረታ ከዓለም ታላላቅ ከተሞች የሚለያት በቅርብ ጊዜ መመስረቱዋ ሲሆን የሚያስደንቃት ደግሞ በዚህ በአጭር ዘመን ውስጥ ከለንደንና ከሞስኮ የምትወዳደር ከተማ መሆንዋ ነው ፡፡
አዲስ አበባ እንደዚህ እንድትሆን ያደረጉዋት የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው ፡፡ መፈናቀል መስፈር የመሳሰሉት ነገሮች ከከተማ ምስረታ ጋር የተያያዙ ለመሆናቸው ይህ ግለሰብ ሳይረዳው ቀርቶ አይደለም ፡፡
ገባርነት የሰለቸው የፊውዳል ኢትዮጵያ ገበሬ ወደ አዲስ አበባ መፍለሱ የሚያስደንቅ ነገር አልነበረም፡፡
ለመሆኑ ገባር ( ገባሮ) የሚለው ቃል ከየት መጣ?
ለመሆኑ ጅማ እንዴት ተመሰረተች ? ጎንደርስ፡ እክሱምስ ?
ጅማ በቅኝ አገዛዝ ነው የተመሰረተችው ?
ጎንደር በቅኝ አገዛዝ ነው የተመሰረተችው?
የጅማ አመሰራረትና የአዲስ አበባ አመሰራረት ልዩነቱ ምንድነው ?
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4017
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቢተወደድ1 » Mon Feb 18, 2019 1:44 pm

በስሜት የሚነዱና ጊዜ ስልጣን የሰጣቸው እንደፈለጉት ይለፈልፉብናል፡፡
የኢትዮጵያዊነት ስሜት እንጂ ሊመራን የሚገባው ያካባቢ ዘረኝነት መሆን አልነበረበትም፡፡
መቆየት ደጉ ብዙ ያሳየናል፡፡
እኛ እንኳን ስደት ላይ ሆነን በማናቀው አገር የሕዝባቸውን ጥቅም ከነሱ እኩል እየተካልፈልን፤
ወደ አገራችን ፖለጢቃ ስንመጣ ይሄን ዘር አስወጣው የሱ መሬት እይደለም ገለመሌ እንላለን
ዘር እኮ ለእህል እንጂ ለሰው ልጅ የተሰጠ መለያ አልነበረም፡፡
ከተማን ለመቆርቆርማ አስመራንም ራስ አሉላ አባ ነጋ ነበሩ የቆረቆሩዋት፤ እሁን እንዲህ ........
ቢተወደድ1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 214
Joined: Thu Sep 01, 2016 8:48 am
Location: Bisheftu

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Mon Feb 18, 2019 7:15 pm

የተማሩ ናቸው የምንላቸው፡ የተማንርን ነን የሚሉት ፡ግለሰቦች በዚህ በዓለማችን ከተሞች እንዴት እንደተመሰረቱ ሳይገባቸው ቀርቶ አይደለም፡፡
ነገሩን ያነሳሁት እንደው ለጨዋታ ያህል ነው ፡፡
ታሪክን መመራመር እና የሰው ዘር መጥላት የተለያዩ ነገሮች ናቸው
ሎንዶን ስትመሰረት ሺ አልቆ ሺ ተገፍቶ ነው ፡፡ሞስኮ ስትመሰረት ሺ አልቆ ሺ ተገፍቶ ነው
ጅማ አይናችን ላይ ያላቸው ከተማ ስትመሰረት ሺ አልቆ ሺ ተገፍቶ ነው
እነ ጃዋር ይህንን ሳያውቁ ነው ለማለት አያስደፍርም ነገር ግን የተጠናወታቸው የሰው ዘር ጥላቻ ነው ለማለት ግን ያስደፍራል፡፡

የቀጠለ ፡
የኦርቶዶክስ እምነት
መጀመሪያ የኦርቶዶክስ ክርስትና ከፕሮቴስታንት የሚለየው በአንድ ትልቅ ጉዳይ ነው፡፡
ፕሮቴስታንቲዝም በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ላይ የተመረኮዘ ስብከትና ጸሎት ሲያደርግ
ኦርቶዶክስና ካቶሊዝም ግን የራሳቸው የቤተ ክርስቲያን መገልገያ ቁዋንቁዋ አላቸው ፡ ግእዝና ላቲን ፡፡ በካቶሊዝም ላቲን እምብዛም እንደ ኢትዮጵያ ርቶዶክስ አይደለም ቢሆንም ቫቲካን ፓፓሱ ሲሰብኩ መስማች ይቻላል ፡፡
በተለይ የኦርቶዶክስ ክርስትና በኢትዮጵያ ፡ ከኢስተርን ኦርቶዶክስ ማለትም ከራሺያና ከሰርቢያ እንዲሁም ከግሪክ ኦርቶዶክስ ክርስትና በመለየት የራሱ የሆነ እና ራሱን የቻለ፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ሌላ በተጨማሪ ፈጣሪን ማገልገያ ቁዋንቁዋ አለው ይህም የግእዝ ቁዋንቁዋ ከዛም የቅዱስ ያሬድ መዝሙር ነው

ኩራ ኢትዮጵያዊ ሁላ፡ ኩራ ወገኔ ሁላ፡ ዛሬ በጎሳ እና በሰው ዘር ጥላቻ የሚነፋው አሉባልታን እዛ ወርውረህ ደረትህን ንፋ፡፡
እኔ ፈላስፋውበቅዱስ ያሬድ እኮራለሁ ይህንን ስል ግን ከወያኔ ጋር ምንም ጉዳይ የለኝም ከትግራይ ሕዝብ ጋር ግን የአንድ ሳንቲም ግልባጭ ነኝ፡፡ ፡፡
ምክንያቱም ያሬድ ከሞዛርት የማይተናነስ ኮምፖኒስት በመሆኑ ፡፡
አቦይ ስብሃት ነጋ ግን ኦርቶዶክስን ሰባበርነው ሲል ቅዱስ ያሬድን የት ረስቶት እንደሆነ ጊዜ ይጠይቀዋል ፡፡

እነ ጃዋር የኦርቶድክስን ክርስትና የመገልገያ ቁዋንቁዋ ለመተርጎም ብቃት ይኖራቸው ይሆን ?

ታዲያ ታሪክን ሳይመረምሩ እንደው ዘራፍ ማለቱ የሰው ዘር ጥላቻ !!
መጽሓፍ ቅዱስን ማርቲን ሉተር በጀርመን ፡ ከዛም ኦነሲሞስ ነሲብ በኢትዮጵያ ወደ ኦሮምኛ ለመተርጎም በቅተዋል
መጽሐፍ ቅዱስን በተፈለገው ቁዋንቁዋ መተርጎም ይቻላል ነገር ግን የያሬድን ፡የቅዱስ ያሬድን ዜማ እንዴት አድርጎ ወደ የትኛው ቁዋንቁዋ መተርጎም ይቻላል?
እነ ጃዋር .....ለዚህ መላ ምት ካላቸው ፡
ሕዝቡን ከእምነቱ በጦርና በእዳፍኔ ማላቀቅ ወይም
ታሪክን አጥንቶ የሚሆን መፍትሄ መፈለግ

ፈላስፋው ይህንን ሲል እነ ጃዋርና ... ይህንን ኢትዮጵያዊነት እንደ ኢትዮጵያዊነት ቆጥረውት ነው ወይስ እንደ ጥላቻ የሚለው ጥያቄ ስለመጣበት ነው
እነ ጃዋር ስለዚህ ጉዳይ ምን ማለት ይችሉ ይሆን ?
ጃዋር ለመሆኑ ስምህ ከየት ነው የመጣ ነው?
ዳውድ ከየት የመጣ ስም ነው?
ቁርዓን የሚቀራው በየትኛው ቁዋንቁዋ ነው ?

ይቀጥላል አዲስ አበቦች መጤ ናቸው የሚለው ቃል
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4017
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ዘርዐይ ደረስ » Mon Feb 18, 2019 8:01 pm

ዘረኛ የሚለውን ቃል ብሄርተኛ በሚለው ብንቀይረው አይሻልም?
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1053
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests