የኢትዮጲያ ኦሮሞ ትግል ከየት ወዴት?

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የኢትዮጲያ ኦሮሞ ትግል ከየት ወዴት?

Postby እሰፋ ማሩ » Tue Apr 16, 2019 1:34 pm

የኦሮሞ ዘር ወይም ብሄር ከጥንቱ በሰሜን ምስራቅ አፍሪካ ከሚኖሩ ጥንታዊያን ኩሽቲክ ነገዶች ከአፋርና መሰሎቹ አንዱ መሆኑንን የቅርብ ጊዜ ጥናቶች በማረጋገጥ ላይ ናቸው ፡፡የአፋር ህዝብ ከማንም በላይ ቀዳሚው የኢትዮጲያ ብሄር ወይም ዘር ለመሆኑ አርኬዎሎጂና ታሪክ የመሰክሩትን ያህል የኦሮሞም ታሪክ እንደዚሁ ጥንታዊ ሲሆን ከሌላ ስፍራ ከማደጋስካር ወዘተ መጣ የሚለው አፈታሪክና በጥላቻ አራማጆች የሚነገር ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል የሚሉ ተስፈኞች ትርክት ነው፡፡
በሃገራችን ብዙሃን የሆነውና ከሌሎቹ ብሄሮች ወይም ዘሮች ጋር እጅግ የተደባለቀው ኦሮሞ ባለፉት መንግስታት ማንነቱ ባህሉ ቋንቋው እንዳያድግ በጥላቻ ቃልGala "ኦሮሞ" "ኦሮሞ" በሚል ስም ሲጥላላ የኖረ ተገቢ ትግል በተገቢ መንገድ ባለመሄዱ ዋናውና ግንድ ተብሎ የሚጠራው የህዝብ ክፍል ያላስፈላጊ የመገንጠል ጥያቄ በሚያራምዱና ኢትዮጲያን በሚጠሉ መሪዎች ላለፉት ሰላሳ አመታት ሲመራ ቆይቶ ነበር፡፡ በወያኔ ከተደራጀው ኦህዲድ ስር በነበሩ በኦሮሞ ስም ከተደራጀ ፓርቲ ኢትዮጲያዊነትን ለመጀመሪያ ጊዜ በማሰማት የብዙዎችን በተለይም በቁጥር ከማንም ዘር ብሄር በላይ የሆኑትን ድብልቆቹንና ኢትዮጲያዊነትን በሚያራምዱ ልብ ውስጥ በመግባት ትግሉን ለአንድ አመት ያህል በመምራት አያሌ ድንቅ ድሎች ተገኘተዋል ብዙ አፋኝ የወያኔ መውቅሮች ተሰባብረዋል የመናገርና የመጻፍ መብቶች ተገኝተዋል ለዚህም የለማና አብይ ቲም ወይም ቡድን ሊመሰገን ይገባዋል፡፡
ሆኖም ግን ከጥንቱም ከወያኔና ከሻቢያ ጋር ኢትዮጲያዊነትን የማጥፋት ሴራ ያቀናብር የነበረው ኦነግ መስሪ ድርጊት ድሮም ሲፋቅ ኦነግ ነው የሚባለው ኦህዲድ አክራሪ አንጃዎቹ በነአዲሱ አረጋና መሰሎቹ የድብልቅ ህዝቦች ከተማ የሆነችውን የጥንቷን ፊንፊኔ አዲስ አበባ ከተማን የኦሮሞ ብሄር ወይም ዘር ንብረት ነች የሚለውን ኢ ፍ ት ሃዊ ጥያቄ በማራገብ በዲሞግራፊ ስም ለማ መገርሳ ባደረገው ስብሰባ ላይ ታከለ ኡማ በሚዲያ የማይነገር ብዙ እየተባበርን ነው የሚለውን ሚስጥር ከዘረገፈ ወዲህ በተጨማሪም ለማ መግረሳ ያንን ንግግሩን ለማስተባባል በጠራው ስብሰባ ላይ ሿሿ አናድርግም በማለት በፌዝ መልክ ንግግሩ የኦፕዲኦም ስውር አላማ በማሳየት ላይ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ህዝብ ያለው የፌደራል ህግና አለምአቅፍ ሜትሮፖሊታን ትልልቅ ከተሞች አሰራርን ባልተከተለ የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብን የራሱን ማስተዳደር መብቱን ኦፒዲዎች በመርገጥ ላይ ሲሆኑ ለዚህ የሚታገለውን እስክንድር ነጋና ባልደረቦቹን በማዋከብ በማጥላላት ዘመቻ ላይ ናቸው፡፡ ከዚህ ቀድም ብሎ በቡራዩ የተደረገውን የኦነግ አክራሪዎች ጭፍፍጨፋ የተቃወሙ የአዲስ አባባ ወጦችና የህግ ባለሙያዎች በአብይ እህመድ መንግስት ሲታሰሩ በሃይማኖት ጉዳይ የሚናገረንን በሜንጫ ሰይፍ እንመታዋላን ያለእ ጃዋር መሃመድ ብሶበት ለፍተው ኮንደሚኖ ቤት የሰሩ የሁሉም ዘር ተወላጆች እንዳይረከቡ ደም ይፈሳል አይገቡም ብሎ ከነጀሌዎቹ የዛተውን ከማገ ለህግ ከማቅረብ ይልቅ በሰላም የሚታገልውን እስክንድርን በጦርነት ቅስቀሳ የወነጀለውይአብይ አህመድና የዲሞግራፊው ባለቀመር ለማ መገርሳ የትዮጲያዊነት እወጃ ልፈፋ ብቻ መሆኑ ጥያቄ ውስጥ ሲገባ ይህን የተቃወሙ በሳል የአሜሪካ ምሁራንና ታላቆች ለእዶር አብይ የማሳሰቢያ ደብዳቤ መላካቸው ይታወሳል፡፡

ይህ ሁሉ የሚያመለክተው የኢትዮጲያ ኦሮሞ በሃገሪቱ ብዙሃን ብሄር ወይም ዘር ሆኖ በኬንያ አናሳ ቁጥር ካለው ተመሳሳይ የኦሮሞ ብሄር ወይም ዘር ያነሰ የመብትና ስልጣን ክፍፍሉን በተግቢ መንገድ ማስፈጸም ሲገባ በዚህ በኦፕዲኦ ጽንፈኞች በኦነግ የውስጥ አርበኞች ጫና የሚካሄደው እኩይ ሴራ ለኦሮሞም ሆነ ለሌላው ብሄርና ዘር የማይጠቅም ይሆናል ይህንን የተሳሳተ የትግል አካሄድ ሁሉም ዜጋ በተለይ የኦሮሞ ምሁራንና ወጣቶች ሃርሞሳ ኦሮሚያ የኦሮሞ ተሃድሶ በሚሉት ትግል ሊፋለሙት የሚገባ መሆኑን መክራለሁ፡፡
ከዚህ በተረፈ በመካከለኛው ዘመን ከሶማሌ የመጣው ሃገራችን ኢትዮጲያን ከከፍታ ያወረደ የፈረሰው የአህመድ ግራኝን ወራር መሪ ኑርን በምስራቁ የሃገራችን ክፍል ድል ያደረገው የኦሮሞ ጀግና ሰራዊት ተመሳሳዩን ድል በአድዋ ለአፍሪካና ለመላው ጥቁር ህዝብ ኩራት የሆነውን ሰራዊቱን ያዋጣ በሁለተኛው የአልም ጦርነትም አብዲሳ አጋን የመስለ ድንቅ ጀግና ያፈራ ህዝብ ያልተነገረ ታሪኩን በታሪክ ዋቢነት ሊጠቀስ የሚገባ ታሪኩን ከይልማደሬሳ የመካከለኛው ዘመን የኢትዮጲያ ታሪክ ላይ መመልከት ይቻላል
(ይቀጥላል ሌሎችም ታሪካዊ ማስረጃ ያላቸው ይሳተፉ)
Last edited by እሰፋ ማሩ on Fri Apr 19, 2019 3:53 pm, edited 9 times in total.
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1550
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: የኢትዮጲያ ኦሮሞ ትግል ከየት ወዴት?

Postby እሰፋ ማሩ » Fri Apr 19, 2019 1:07 pm

የኢትዮጲያ ህዝቦች ትግል በተቀጣጠለበት የስድሳ ስድስቱ ትግል የገባር ህዝቦችን ትግል ይመራ የነበረው ኢጫአትን ከመሩት አንዱ ባሮ ቱምሳ የመንግስቱ ሃይለማርያም ደጋፊ የነበረውና በመንግስቱ የግል ታሪክ ላይ የተሞገሰው የጀመረው ኦነግ በኦሮሞዎች ልብ ውስጥ ምንጊዜም የማይጠፋ ነው፡፡ሆኖም ግን በትግል ስህተት ኦነግ ለኦሮሞ ብቻ በመቆሙና ኢትዮጵያ የአማራው ፈጠራ ናት በሚል ትርክት በአማራ ጥላቻ መሳቱን የቀድሞው መስራች መሪዎቹ ሌንጮ ለታ በከፊል ሌንጮ ባቲ ሙሉ በሙሉ በቅርቡ የዘከሩት ይገኛል፡፡በዚያ የትግል ወቅት የወለጋው ባሮ ቱምሳ ኢጭአትን ለአሰፋ ጫቦ ትቶ ኦነግን ሲመስረት ወንድሙ ፓስተር ጉዲና በመካነኢይሱስ ቤክ መሪ ሆኖ ብዙ ሲተባበር የመካነኢየሱስ መሪዎች የንጉሱ አማቾች እንደተቃወሙት የጫቱ ፕሮፌሰር ህዝቅኤል ጋቢሳ በቅርቡ የተናገረው ማስረጃ ሲሆን የቀድሞ ደራሲያን ማህበር መሪ አቶ አማረ ማሞ ከጉራጌ ብሄር የሆኑን ይህንን ለደራሲያን ጉብኤ ዘግበው ነበር፡፡ፓስተር ጉዲና ትግሉን ያቆም ዘንድ በደርግ በአውሮፓ ሚሲዮን ተጠሪዎች ፊት ሲጠየቅ እምቢ በማለቱ በራስ ካሳ ግቢ በተመሳሳይ መልኩ የጎጃም ሰዎችን ብቻ መሰቀል በማሳለም በርቱ ብለዋል በሚል ደርግ ከከሰሳቸው ቴዎፍሎስ ጋር ተገድለዋል፡፡
ደርግ ሲወድቅ ሃገር ቤት የገባው የኦነግ አመራር ከወያኔ ጋር ሃገሪቱን የሚያፍረስ የጎሳ ፌደራል ያዋቀሩ ሲሆን ከዚያ ስርአት ያልተጠበቁ ለማ መገርሳና እበይ አህመድ የጀመሩት ያልተጠበቀ የኢትዮጲያዊነት ትግል በልዩ ሁኔታ ቀጥሎ የብዙሃኑን ድጋፍ አግኝቶ ለዚህ ቢደርስም በዚህ ጠማማ ህገመንግስትና በክፋት በተዋቀረው የአዲስ ፊንፊኔ ባለቤትነት የተነሳ የዶር አበይ ለውጥ መስቀለኛ መንገድ ላይ ሲሆን የሃገሪቱ ብዙሃን ሆኖ ብዙ ድሎችን ከሌልቾ ጋር ከአድዋ ጀምሮ ያስመዘገበው የኦሮሞ አመራርም ጥያቄ ውስጥ ነው ፈጣሪ ይህንን ወደበጎ በመለወጥ ሃገራችን በፊውዳል መሳፍንትና በጨካኝ ወራሪ የኦቶማን ኢምፓየትር ሎሌ ሶማሌው ግራኝ አህመድ ከነበረችበት የታላላቅ ጥናታዊ ሃገሮች ከፍታ ኢትዮጲያን ይመልሳት ዘንድ ምኞቴ ነው፡፡
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1550
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: የኢትዮጲያ ኦሮሞ ትግል ከየት ወዴት?

Postby ቢተወደድ1 » Fri Apr 26, 2019 12:12 pm

መቀባጠር አይሰለችህ፤፤
ለዚህ ቤት አርእስት የሚሆንህን መልስ አሁን ኢትዮጵያ ዉስጥ የምታየው ነገር በቂ መልስ ይሆንሃል፡፡ ነገር ማድበስበስና ማሞሻሸር አያሻም፡፡
ከሰባተኛው ንጉስ ጋር ወደፊት!!!
ቢተወደድ1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 360
Joined: Thu Sep 01, 2016 8:48 am
Location: Bisheftu


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot], Majestic-12 [Bot] and 1 guest