ሰበር መረጃ: የኦነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ዳውድ ኢብሳን ከሀላፊነቱ አነሱት!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ሰበር መረጃ: የኦነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ዳውድ ኢብሳን ከሀላፊነቱ አነሱት!

Postby ኳስሜዳ » Mon Jul 27, 2020 3:35 pm

የአነግ ሸኔ ማዕከላዊ ኮሚቴ የግንባሩን ሊቀመንበር ጃል ዳዉድ ኢብሳን ከስልጣን በማዉረድ በምክትላቸዉ ጃል አራርሶ ቢቂላ እንዲተኩ አድርጓል፡፡ ጃል ዳዉድ ኢብሳ ከስልጣን እንዲወርዱ የግንባሩ ማዕከላዊ ኮሚቴ የወሰነበት ምክንያቶች

1ኛ. ከማዕከላዊ ኮሚቴዉ እዉቅና ዉጭ ከወያኔ ጋር አጋርነት ፈጥረዉ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸዉ ታሪካዊ ስህተት በመሆኑ

2ኛ. በአንድ በኩል ሰላማዊ ይትግል ስልትን በሌላ በኩል ደግሞ የትጥቅ ትግልን እንዳማራጭ ወስደዉ መንቀሳቀሳቸዉ እና ጫካ ላለዉ ኦነግ ሰራዊት አሁንም አመራር መስጠት መቀጠላቸዉ ትክክል አለመሆኑ

3ኛ. አባ ቶርቤ በመባል የሚታወቅ እና በከተሞች የጸጥታ ሃይሎችን፣ የመንግስት አመራሮችን፣ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ግድያን የሚፈጽመዉን የሽብር ቡድን አሰልጥነዉ እና አስታጥቀዉ የሚያሰማሩት ጃል ዳዉድ ኢብሳ መሆናቸዉ በመረጋገጡ እና ከዚህ ድርጊታቸዉ እንዲቆጠቡ በተደጋጋሚ ተግሳጽ ቢሰጣቸዉም መታራም ባለመቻላዉ ከስልጣን እንደወርዱ የኦነግ ማዕከላዊ ኮሚቴዉ ዛሬ ሃምሌ 20/2012 ዓ.ም ወስኗል፡፡
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2245
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot], Google Adsense [Bot] and 3 guests