WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home | About us | Advertise with us | Contact us
ዑራ ኪዳነምህረት !

 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General


 
View previous topic :: View next topic  
Author Message
አደቆርሳ

ዋና ኮትኳች


Joined: 03 Aug 2005
Posts: 754
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Oct 18, 2005 12:23 pm    Post subject: ዑራ ኪዳነምህረት ! Reply with quote

/ሰላም ወገኖቼ ይህ ጽሁፍ የወንድማችን የደብረ ዲማ ነው እዚህ ያመጣሁት ትልቅ የመማሪያ ርዕስ እንደሆነ በማመን እና በቀላሉ እንድናገኘውና እንድንማማርበት ነው ::ደብረዲማ ቃለህይወት ያሰማልን !!/

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ::
ሰላም ውድ ክርስቲያን ወገኖቼ እንደምን ሰነበታችሁ እኔ በጣም ደህናነኝ ላልተወሰነ ጊዜ አልነበርሁም አሁን ግን ክርሄድሁበት ተመልሻላሁ አብረን እንወያይ :: ለዛረው ይዥ የቀረብሁት >. የሐመረኖሕ ዘጌ ኡራ ኪዳነ ምሕረት ገዳም አጭር ታሪክን ነው ::

በሐገራችን ከሚገኙት ታላላቅ መካነ ቅዱሳት መካከል ይህ ገዳም አንዱ ነው ::

ጣና ሃይቅ 3ሺህ 6መቶ ስኩዬር ኪሎ ሜትር የቆዳ ስፋት ሲኖረው በውስጡም 37 ደሴቶች እና 29 ገዳማት ይገኙበታል ; እነዚህም ገዳማት 11ኛው እስከ 16ትኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንደ ተስፋፉ ይነገራል :: በጣና ሃይቅ አካባቢ ከሚገኙት ገዳማት መካከል ኡራ ኪዳነ ምሕረት ገዳም አንዱ ነው :: የኡራ ኪዳነ ምሕረት ገዳም ዘጌ ከሚባል ደሴት አካል ቦታ ላይ የተቆረቀረ ሲሆን ከባህር ዳር ከተማ በአማካኝ በጀልባ የአንድ ሰአት ጎዞ ወይም በየብስ ደግሞ ወደ 35ኪሎ ሜትር ያህል ይርቃል ::
> ገዳመዘጌ ኡራ ኪዳነምሕረት በክብ ደርብ የግንብ ሕንፃ ጥበብ የተሰራ ሲሆን በአራት ማዕዘን በተሰሩ የእንጨት ግማዶች እና በጥንታዊ የሰዕል ጥበብ የጌጠ ታላቅና ጥንታዊ ቤተክርስቲያን ነው :: በተጨማሪም የዕቃ ግምጃቤት እና አባ ዮሐንስ ቤተክርስቲያኗ ከመታነጿ በፊት ያነጹት ቤተ ዮሐንስ ወይም ቤተ ማዕድ { ቤተ ምርፋቅ } በዙርያው ይገኛል :: የኡራ ኪዳነ ምሕረት የደብረ ሥላሴ እና የአዝዋ ምርያም ገዳማት ከአባ ዮሐንስ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ሥረዐተ ዮሐንስ ተጠብቆ በአንድ መምህር እና በአንድ አበ ምኔት ይተዳደራሉ ::

> አባ ናሆም ;

ገዳመ ዘጌ የጸናችው በአባ ናሆም መሆኑ በታሪክ ይነገራል የአባ ናሆም ታሪክ በአብርሃ ወአጽብሃ በኃላ አንደኛ ረድፍ ሁለተኛ አሞሲን እና ሶስተኛ ሣልሣይ የተባሉ ነገሥታት ከነገሱ በኃላ እንደ ሆነ ይነገራል :; ከዚህ ጊዜ በኃላ አባታችን አባ ናሆም በኢየሩሳሌም ደሴት ዝጋግ በተባለች ደሴት በጸሎት እንዳሉ የልኡል እግዚአብሔር መልአክ ወደ ኢትዮጵያ እንዲሄዱ አዘዛቸው :; ከመጡም ጊዜ የነበሩበት ቦታ በእግዚአብሔር ኃይል ከእሳቸው ጋር መጥቶ በጣና ሐይቅ እንደ ተቀመጠ ይነገራል : ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ይህን ቦታ { ዝጋግን } ለማስታወስ ሲባል ደሴቱ ዘጌ እንደተባለ ይነገራል :: አባታችን አባ ናሆም ከበአታቸው በጸሎት እንዳሉ { የዋልድባው አባ ሳሚኤል ከመወለዳቸው በፊት ] ለዋልድባ ገዳም ሰባት አክሊላት ከሰማይ ሲወርድ አይተው ; መንፈሳዊ ቅናት አድሮባቸው ; ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ሰዕል ፊት ወድቀው እያለቀሱ ይለምኗት ጀመር ;; በዚህ ጊዜ የእመቤታችን ስዕል ድምጽ አእጥታ አባ ኖሆም አትዘን አታልቅስ ; እንሆ ምድርህ ዘጌ እንደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ትሆንልሐለች መነኮሳቷ ልጆችህም እንደ መላዕክት ይሁኑልህ አለቻቸው :: ያን ጊዜ ለገዳመ ዘጌ አስራሁለት አክሊላት ከሰማይ ወረደላት ; አባታችንም አባ ናሆም የሰጠሽኝን ቃል ኪዳን ያጽናልሽ ልጅሽን ኢየሱስ ክርስቶስን አስመጭልኝ ብለው ለመኗት እመቤታችንም ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ አባ ናሆም አስመጣችው :: ይህችም ቢታ ዛሬ አስመጭ በመባል ስትጠራ ትኖራለች ::

የአባ ዮሐንስ ታሪክ ይቀጥላል ::

ደበረ ዲማ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ::

እመቤታችን ለአባቶቻችን የተለመንች እኛንም ትለመነን ታማልደን ታስታርቀን አሜን :

{ ቅኔ }

ዝምዝም ወርቅ መንገድ { መወድስ }

ማርያም ግዮን ፈለገ ኅሊብ
ማርያም ጳዝዮን ማርያም እንቁ ሶፎር
ማርያም ዓለም ዘይስሕብኪ ፍቅር
ማርያም ፈለገ ደም ላባዕድ ዘኢይትትከሰት ማርያም ምሥጢር
ማርያም ጸሐየ ክብር እንተ ፈጠረኪ ወልድ ማዕከለ ተሰዶ ጠፈር ::
_________________

kibremengist
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አደቆርሳ

ዋና ኮትኳች


Joined: 03 Aug 2005
Posts: 754
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Oct 18, 2005 12:40 pm    Post subject: ለወንድሜ ደብረዲማ Reply with quote

የእግዚአብሄር ሰላም ካንተጋር ይሁን !!
በምታቀርባቸው ጽሁፎች ዘወትር የምናገኘው ትምህርት ቀላል አይደለም :የብዙ ጥያቄዎችን መልስ እየመለስክ እንደሆነ እና እኛም ካንተ ጽሁፍ እየተማርን ስለሆነ ቀጣይ ታሪካዊና ሀይማኖታዊ እይታዎችህን በዚሁ ገጽ ሥር እንድናገኝህ
አደራ እንልሀለን ::
ወዳጅህ አደቆርሳ ዘሀገረ አዶላ :
_________________

kibremengist
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

 
Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum


Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia