WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
በልሳን መናገር ማጎራት መቀበጣጠር ነውን ?
Goto page 1, 2, 3 ... 12, 13, 14  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General

View previous topic :: View next topic  
Author Message
NATHRATHE

ኮትኳች

Joined: 18 Apr 2005
Posts: 298
Location: united states

PostPosted: Wed Oct 26, 2005 3:58 pm    Post subject: በልሳን መናገር ማጎራት መቀበጣጠር ነውን ? Reply with quote

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን

ሰላም ክርስቲያኖች

ዲያብሎስ በተለያዩ ወቅት የተለያዩ ዘዴዎችን እየተጠቀመ የሰው ልጆችን ክርስቶስ በደሙ ከመሰረታት ቅድስ ቤተ ክርስቲያን ለመንጠቅ ሲራራጥ ይታያል ::ከሚጠቀምባቸው የተለያዩ ዘዴዎች መካከል ሰይጣን የያዘው ሰው /የአህምሮ ህመም ያለበት ሰው / እንደሚያደርገው መንፈራገጥ አረፋ መድፈቅ መለፍለፍ መንቀጥቀጥ የመሳሰሉት ነው ::ይህንን የሴጣን መለይስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በማጣመም የማይሆን ትርጉም ሲሰጡት ያታያሉ ::

እኔ የሚገርመኝ ይህ በማይታወቅ ቋንቋ መቀበጣጠር ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ (ወይም ኢትዮጵያውያን የሆኑ ) Protestants ብቻ የሚገለጥላቸው ሳይሆን አይቀርም ::እዚህ እኔ ባለሁበት በሰሜን አሜሪካ TV and Radio እንዲሁም በተለያዩ መንገዶች Protestants አዳራሽ ስብከት ሆነ ፕሮግራም ተከታትያለሁ ህዝቡ በስነስርዐት ቁጭ ብሎ ከመማር የዘፈን እና የጸሎት ሰዐት ሲሆንም ስርዐት ባለው መንገድ ሌላ ቋንቋ ሳይጨምሩ በእንግሊዘኛ ብቻ መረሀግብራቸውን ይጨርሳሉ ::በመዝሙር ሰአት ቀውጢ የሚሆነው የጥቁሮች ቸርች እንኳን የሚንዘፈዘፍ የሚወድቅ በማይታወቅ ቋንቋ የሚቀበጣጥር የለም ::አንዱ ከኢትዮጵያ የመጣ ጴንጤ ኢትዮጵያ እንደለመደው እንዘፈዘፋለሁ ቢል አጋንት ይዞታል ብለው ተጋግዘው ተሸክመው እንደሚወስዱት አጠያያቂ አይደለም ::

እኔ የተከታተልካቸው አብዣኛው በጣም ትላልቅ የሚባሉ ቸርቾች ውስጥ አላጋጠመኝም ይሆናል እንጂ ምን አልባት ኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ መንዘፍዘፍና መቀበጣጠር ያስተማሩ ሊኖሩ ይችሉ ይሆናል ::እኔ ግን ከአብዣኛው Protestants ተለይተው ኢትዮጵያ ያሉ አጋንት እንደያዛቸው የሚንዘፈዘፉ ሰዎች ከየትኛው Protestants ቸርች ተምረው እንደሆነ ቢነግሩኝ ደስ ይለኛል ::

ለመግቢያ ያህል በአለማችን ያለውን እውነታ እንዲህ ካላኩ የኛዎቹ ሰዎች እነሱ "በልሳን መናገር " ስለሚሉት መቀበጣጠር እና አጋንት እንደያዘው ሰው መውደቅ መንፈራገጥ እነዱ ከሚጠቅሳቸው ጥቅሶች እና መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረንን በተከታታይ እናያለን ::የእውቀት ባለቤት እውቀቱንና ማስተዋሉን ይግለጽልን ::

ይቆየን ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
NATHRATHE

ኮትኳች

Joined: 18 Apr 2005
Posts: 298
Location: united states

PostPosted: Wed Oct 26, 2005 4:53 pm    Post subject: Reply with quote

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ::

ሰላም ክርስቲያኖች

ስለ ልሳን ትርጉም ከማየታችን በፊት ከመጽሐፍ ቅዱስ የተወሰነ እንመልከት ::

በዓለ አምሳ የተባለው ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ንፋስ ከሰማይ ድምጽ መጣ ተቀምጠው የነበሩበትን ቤት ሁሉ ሞላው ::እንደ እሳት የተከፋፈሉ ልሳኖች ታያቸው ::በእያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው :መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር ::
ከሰማያት በታች ካሉ ሕዝብ ሁሉ በጸሎት የተጉ አይሁድ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር ::ይህም ድምጽ በሆነ ጊዜ ሕዝብ ሁሉ ተሰበሰቡ :
እያንዳንዱ በገዛ ቋንቋው ሲናገሩ ይሰማ ስለነበር የሚሉትን አጡ ::ተገርመውም ተደንቀውም እንዲህ አሉ እነሆ እነዚህ የሚናገሩ ሁሉ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን ?እኛም እያንዳንዳችን የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋችንን እንዴት እንሰማለን ?የጳርቴና የሜዴ የኢላሜጤም ሰዎች ...የእግዚያብሔርን ድንቅ ስራ በልሳኖቻችን ሲናገሩ እንሰማለን ::ሐዋ 2:1-12

ከዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የሚከተሉትን በቀላሉ እንረዳለን

  1. መንፈስ ቅዱስ የልሳን የመናገር ጸጋ ለሐዋርያት እንደሰጠ
  2. ሐዋርያት በተሰጣቸው ሌላ (በፊት ይናገሩት ከነበረው ) ልሳን ሲናገሩ ህዝብ ተወልዶ ባደገበት አካባቢ የሚነገረውን ቋንቋ በመናገራቸው መደነቁን
  3. ህዝብ ምንም እንኳን በወቅቱ በክርስቶስ የባህሪ አምላክነት አምኖ ባይጠመቅም (ክርስቲያን ባይሆንም ) ሐዋርያቱ በገዛ ልሳኑ (በአፍ መፍቻ ቋንቋው ) ሲናገሩ የሚናገሩትን ተረድቶ (understand ስላደረጋቸው ) የሚናገሩት የእግዚያብሔርን ታላቅ ስራ ነው ብሎ መመስከሩን እና ሌሎችንም እንረዳለን ::

ከዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ተነስተን ስለ ልሳን መናገር የሚከተሉትን እናያለን

  • በልሳን መናገር ማለት ሳያድጉበት ወይም ሳይማሩት እንዲሁ በእግዚያብሔር መንፈስ ቅዱስ የሚሰጥ በሌላ (ባልተማሩትና ባላደጉበት ) ቋንቋ መናገር ማለት መሆኑን ::
  • በልሳን መናገር ሐዋርያት በተሰጣቸው 72 ቋንቋ ሲናገሩ ከተለይ የአለማችን ክፍል ኢየሩሳሌም ለበኃል ተሰብስበው የነበሩ አይሁድ እንደመሰከሩላቸው ቋንቋው የሚሰማ በአለም ላይ ያለ ቋንቋ መሆኑን እንረዳለን ::

ዛሬ ኢትዮጵያውያን Protestants እንናገራለን የሚሉት ልሳን በመጀመርያ የሚሰማው ሰው (የኔ ቋንቋ ነው የሚል አለ ::ከተለያቱ አለማት የመጡ አይሁዶች ለሐዋርያት እንደመሰከሩላቸው :Smileየየትኛው ሀገር ወይም ህዝብ ቋንቋ ነው ??ተናጋሪውም ሰሚውም የማያውቀው ስድብ ይሁን እርግማን ይሁን ለይቶ የሚመሰክርለት የሌለው ነው ::

በሚቀጥለው ሌሎች ጥቅሶችን እስክናይ እግዚያብሔር ማስተዋሉን ይስጠን እያልክ እሰናበታለሁ ::

ይቆየን ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ግሸንማርያም

ኮትኳች

Joined: 15 Aug 2005
Posts: 349
Location: ethiopia

PostPosted: Wed Oct 26, 2005 6:02 pm    Post subject: ድንቅ ትምህርት :: Reply with quote

በስመ አብ በስመ ወልድ በስመ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ::

የተከበርክ ውድ ወንድሜ ናዝሬት ለጤናክ እንደምን ላለክ ? እኔ ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይመስገን ደህና ነኝ ::

የመምህር ዘበነ ጉባኤ እንዴት ነበር በድንቨር ኮሎራዶ ? ጻፍልን እንጂ ::

ይህንን ስለ ልሳን የሚገርምህ እኔ ከዚህ ትምህርት ቡሀላ ስለ ልሳንና መናፍቃን ዛሬ በየመጋዘናቸው የሚቀባጥሩትን የእውሸት ልሳን ዋርካ ላይ ለማውጣት አስቤ ሁሉንም ነገር ጨርሼ ነበር :: ነገር ግን እግዚአብሔር ስለ ፈቀደልክ አውጥተከዋል :: ባንተ በቀረ ደግሞ እኔ እጨምርበታልሁኝ :: ዲያቢሎስ ግን እየተነቃበት ስለሆነ ዋርካን ለቅቆ ቢሄድ የሚሻለው አይመስልክም ናዝሬት ?

በል ቀጥልበት እኔም ስለ ቅዱሳን መላእክት የጀመርኩትን ትምህርት እንድ እግዚአብሔር ፈቃድ ከጨረስኩኝ ቡሀላ ወደዚህ አምድ እመጣለሁኝ ::

በተረፈ ቅድስት ድንግል ማርያም እና ቅዱሳን መላእክት ይጠብቁህ :: የመናፍቃንን አንደበት አሁንም በተሰጠህ ጸጋ አንደበታቸውን በእግዚአብሔር ቃል ዝጋው ::

አክባሪህ ግሸንማርያም / ሐይለሚካኤል
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባምላኩ

ኮትኳች

Joined: 30 Jun 2005
Posts: 126
Location: ethiopia

PostPosted: Wed Oct 26, 2005 8:53 pm    Post subject: መልስ በልሳን መናገር መጽሀፍ ቅዱሳዊ አይደለም ለሚሉ Reply with quote

Nathrathe የማሪያም አምልኮ መጽሃፉን እንድትክድና የደብተራዎችን ትምህርት እያስመረጠህ ነው።
Nathrathe
Quote:
ዛሬ ኢትዮጵያውያን Protestants እንናገራለን የሚሉት ልሳን በመጀመርያ የሚሰማው ሰው (የኔ ቋንቋ ነው የሚል አለ ::ከተለያቱ አለማት የመጡ አይሁዶች ለሐዋርያት እንደመሰከሩላቸው : የየትኛው ሀገር ወይም ህዝብ ቋንቋ ነው ??ተናጋሪውም ሰሚውም የማያውቀው ስድብ ይሁን እርግማን ይሁን ለይቶ የሚመሰክርለት የሌለው ነው ::

1ቆሮ .14:2 በልሳን የሚናገርስ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርም፤ የሚያስተውለው የለምና፥ በመንፈስ ግን ምሥጢርን ይናገራል፤

1ቆሮ .14:4 በልሳን የሚናገር ራሱን ያንጻል፤ ትንቢትን የሚናገር ግን ማኅበሩን ያንጻል።
1ቆሮ .14:5 ሁላችሁ በልሳኖች ልትናገሩ እወድ ነበር፥ ትንቢትን ልትናገሩ ግን ከዚህ ይልቅ እወዳለሁ፤ ማኅበሩ ይታነጽ ዘንድ ንግግሩን ባይተረጐም በልሳኖች ከሚናገር ትንቢትን የሚናገር ይበልጣል።
ከተጻፈው ቀንሰህ ብታምን ወይም ጨምረህ ብታምን በሌላ መንፈስ የተሞላህ ትሆናለህ ስለዚህ ከሰማይ ላንተ ብሎ የወረደው የሚፈልጉትን አጥቶ ባለም ሙላት ያለው መንፈስ ቅዱስን ዓይንህን ከፍተህ ብትጠራው መጥቶ ይገባል ወደእውነትም ይመራሃል ጌታንም ያለጉድለት እንድታመሰግንና እንድትጋለግል ያስችልሃል።ስለዚህ አንተ ብቻ መንፈስ ቅዱስ ተሞላና በልሳን ካልተናገርክ ታያለህ።እንግዲህ በልሳን መናገር የለም የምትሉ ከሆነ መጽሃፍ ቅዱስን አለማመንና ደብተራዎችን ማመን ነው።በጥላቻ ተሞልቶ እግዚአብሄርን አመልካለሁ ማለት አይቻልም።
ልሳን በመንፈስ ቅዱስ ለመሞላት ምልክቱ ነው።ሐዋ 2 3-4፣ሐዋ 191-6፤ሐዋ 1045-48 አንብብ።
ስለልሳን እንዳንተ ያሉ የማያምኑ ምን እንደሚሉና እንዴት እንደሚያስቡ ጳውሎስ እንዲህ ይላል።
1ቆሮ .14:22 እንግዲያስ በልሳኖች መናገር ለማያምኑ ምልክት ነው እንጂ ለሚያምኑ አይደለም፥ ትንቢት ግን ለሚያምኑ እንጂ ለማያምኑ አይደለም።
1ቆሮ .14:23 እንግዲህ ማኅበር ሁሉ አብረው ቢሰበሰቡ ሁሉም በልሳኖች ቢናገሩና ያልተማሩ ወይም የማያምኑ ሰዎች ቢገቡ። አብደዋል አይሉምን ?
1ቆሮ .14:24 ሁሉ ትንቢት ቢናገሩ ግን የማያምን ወይም ያልተማረ ሰው ቢገባ በሁሉ ይወቀሳል፥ በሁሉም ይመረመራል፤
ልክ እንደ Nathrathe ማለት ነው ::
ስለዚህ ልሳን ማለት የግድ የዚህ አለም ቋንቋ ሊሆን አይችልም።ስለዚህ አቶ Nathrathe ያን የሚሰግዱለትንና የሚያመልኩትን የወይዘሮ ማሪያምን ፎቶ ቀደድ ቀደድ አድርገው ቅዱስ ቃሉን ገልበጥ ገልበጥ ያድርጉ።
መንፈስ ቅዱስ ሳይሞሉ መንግስተ ሰማየት እገባለሁ ማለት ዘበት ነው።ዮሐ 35።ሰው ከውሃና ከመንፈስ መወለድ አለበት።ካልሆነስ ?ካልሆነማ በምድር ዘመንህ ደረቅ የክርስትና ህይወትና ከአለማውያን የማይሻል ኑሮ እየኖርክ የምትከብርበትን እንኳ ሳታገኝ በሰላም እጦት ተጨንቀህ ትሞታለህ።በዚህ አለም ሰላም የለህም ለመንግስተ ሰማየት ደግም የርስት መያዣ የለህም።መንፈስ ቅዱስ የመንግስተ ሰማየት የርስት መያዣ ነው።አይከፈልበትም አምላክን በሙሉ ልብ መጠየቅ እንጂ።ልሳንም ቢሆን ስጦታ ነው።
ማር 1617-18 ያመኑት በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ ይላል።አዲስ ቋንቋ ማለት ከኢትዮጵያ ቋንቋዎች አንዱ ማለት ነው ?ካልሆነ አያውቁምና ከመቀደድ አፍ መያዝ ይሻላል።ዝም ባለ አፍ ዝምብ አይገባም አይደል የሚባለው።አለማወቅህን ከምትዘራ ዝም ብትል አዋቂ በመሰልክ ነበር።
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
NATHRATHE

ኮትኳች

Joined: 18 Apr 2005
Posts: 298
Location: united states

PostPosted: Thu Oct 27, 2005 1:34 am    Post subject: Reply with quote

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ::

ሰላም ክርስቲያኖች

በልሳን የሚናገር ለእግዚያብሔር እንጂ ለሰው አይናገርምና የሚያስተውለው የለምና መንፈስ ግን ሚስጥርን ይናገራል ::

አሁን ይህ ጥቅስ በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፉትን ስለ ልሳን የሚናገሩትን ሽሮ በልሳም መናገር ማለት እንደ አጋንት (ጠንቃዮች እንደሚሆኑት ) ለማጎራት መረጃ ሊሆን እንዴት ይችላል ::የእግዚያብሔር ቃል እንደፈለግን ለማጣመም ካልፈለግን በስተቀር ::

ይህን ጥቅስ በደንብ ለመረዳት ከላይ በመጠኑ ያብራራውትን የሐዋ 29-12 ያለውን ደግሞ ማየት ይጠቅማል ::ከላይ እንደተገለጸው ሐዋርያት በተሰጣቸው የልሳን መናገር ጸጋ (ያለ ትምህርት እንዲሁ በአንድ ጊዜ በተሰጣቸው 72 ቋንቋ የመናገር ጸጋ ) በአዳዲስ ቋንቋዎች ሲናገሩ በአካባቢው ተሰብስበው የነበሩ ከአለም ዙሪያ እንደ ሀይሁድ ስርዓት ኢየሩስሌም ለመስገድ መተው የነበሩ አይሁድ ሐዋርያት በአለም ላይ ባለ ቋንቋ ሁሉ የእግዚያብሔር ድንቅ ስራ መናገራቸውን መስክረዋል ::ነገር ግን ሐዋርያት የሚናገሩት የእግዚያብሔር ድንቅ ስራ (ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚያብሔር ልጅ እንደሆነና የበሀሪም አምላክ መሆኑ ) ስለረቀቀባቸው የአምላክ ሰው መሆን በቀላሉ ሊገባቸው ስላልቻለ ሐዋርያት ሰክረው የእርዚያብሔር ልጅ ሰው የመሆንና ሰዎችን ለማዳን ተሰቅሎ ሞቶ በሶስተኛው ቀን የመነሳቱ ነገር ስለረቀቀባቸው (እነሱ በፍልስፍና ከሚያውቁት በጣም አዲስና እንግዳ ትምህርት ስለሆነባቸው ) ጎሽ የወይን ጠጅ ጠጥተዋል ብላቸዋል ::ይህ ያሉት ምክንያት ከላይ እንዳልኩት የሚያወሩት ስላልሰማቸው ሳይሆን ስለ እግዚያብሔር የሚያወራቸው ፈጽሞ ሊገባቸው ስላልቻለ ነው ::

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ስለ ልሳን መናገር በተናገረበት አንቀጹ 1ቆሮ 14:2 ላይ የሚናገርስ ለእግዚያብሔር እንጂ ለሰው አይናገርም የሚያስተውለው የለምና ብሎ አስተምራል ::ሐዋርያት ሲናገሩ ከተለያዩ የአለም ክፍሎች የመጡ ሀይሁድ ቢሰማቸውም (ምን እንደሚሉ ቢሰሙም ) የሚናገሩት የእግዚያብሔር ቃል እነሱ ከዚያ በፊት ከሚያውቁት ትምህርት ጋር ስለተለየባቸው ስለረቀቀባቸው ማስተዋል አልቻሉም ::እዚህ ጋር መናፍቃን የማይጣመመውን ለምን በግድ ለማጣመም እንደፈለጉ አልገባኝም ::መስማትና ማስተዋ የሰማይና የምድር ያህል ይራራቃሉ ::ለምሳሌ በሐ . 8:26 ጀምረን ብናይ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ የሚያነበውን የትንቢተ ኦሳያስ ቃሉ ምን እንደሚል አንብቦታል ነገር ግን ስለምን እንደሚናገር ማስተዋል ስልቻለ እግዚያብሔር መንፈስ ቅዱስ በቅዱስ ፊሊጶስ አድሮ እንዲያስተውል አድርጎታል ::በአጠቃላይ ጥቅሱ የሚሰማው የለም ሳይሆን የሚያስተውለው የለም ነው የሚለው ::ይህም የሚገባው የሚረዳው የለም አለ እንጂ ቋንቋውን ምን የማን እንደሆነ የሚሰማው የለም አላለም ::

ወንድሞች ሆይ በአህምሮ ሕፃናት አትሁኑ እንጂ በአህምሮ ሽማግሌዎች ሁኑ ::ሌሎችን ልሳናት በሚናገሩ ሰዎችና በሌላ አንደበት ለዚህ ህዝብ እናገራለሁ እንዲህም ቢሆን አይሰሙኝም ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፋል ::[b]እንግዲህ በልሳኖች መናገር ለማያምኑ ምልክት ነው እንጂ ለሚያምኑ አይደለም ትንቢት ግን ለሚያምኑ እንጂ ለማናምኑ አይደለም ::...

ይህ ቃል የሚያስተምረን በልሳን መናገር ለአህዛብ ምልክት እንዲሆናቸውና የእግዚያብሔርን ቃል የሚያስተምሩ ሐዋርያት በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ሲሄዱ ከህዝብ ጋር መግባቢያ የቋንቋ ችግር እንዳትገጥማቸው እግዚያብሔር መንፈስ ቅዱስ ከሰጣቸው የተለያዩ ጸጋዎች መካከል አንዱ ይህ ነው ::

ባምላኩ እንደጻፈ(ች)ው:
ስለዚህ ልሳን ማለት የግድ የዚህ አለም ቋንቋ ሊሆን አይችልም

ልሳን በዚህ አለም በሌለ በማይታወቅ ቋንቋ መለፍለፍ ነው ተብሎ አንድም ቦታ በመጽሐፍ ቅዱስ አልተጻፈም ::እግዚያብሔር የሰላም አምላክ ነው እንጂ የሁከት አምላክ አይደለምና :: ስለሆነም ባልተጻፈ ቃል እያጎራህ እራስህን ሰላም አታሳጣ ::እግዚያብሄር ማስተዋሉን ይስጠን ::

ይቀጥላል

ይቆየን
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ፎግር

ኮትኳች

Joined: 20 Feb 2005
Posts: 147
Location: united states

PostPosted: Thu Oct 27, 2005 2:27 am    Post subject: ልሳን Reply with quote

ልሳን የግድ የሚተረጎም መሆን የለበትም :: 1ቆሮ 13:1 ክርስቲያን በመላእክት ልሳን ሊናገር ይችላልና :: የሚናገረውም ለአምላክ ነው 14:2:: ልሳን የለም እያሉ የሚያስተምሩ ከቃሉና ከአምላክ መንፈስ የራቁ መናፍቃን ናቸው ::
_________________
love
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Report post
NATHRATHE

ኮትኳች

Joined: 18 Apr 2005
Posts: 298
Location: united states

PostPosted: Thu Oct 27, 2005 2:56 am    Post subject: Re: ልሳን Reply with quote

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ::

ሰላም ክርስቲያኖች

ፎግር እንደጻፈ(ች)ው:
ልሳን የግድ የሚተረጎም መሆን የለበትም :: 1ቆሮ 13:1 ክርስቲያን በመላእክት ልሳን ሊናገር ይችላልና :: የሚናገረውም ለአምላክ ነው 14:2::

በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮህ ናስ ወይም እንደሚሻንሻ ጸናጽን ሆኛለሁ ::

ይህ እኮ የሚለው በአለም ላይ ባሉ በሰዎች ቋንቋ ሁሉ ብናገር የመላእክትም ቋንቋ ምናገር ብችል ፍቅር ከሌለኝ ከንቱ ነኝ እንጂ ባለቤት በሌለው በማይታወቅ ከአጋንት በስተቀር እኔነኝ የሚል አካል በሌለው ማጎራት ልሳን ነው አይልም ::ይህ ጥቅስ የሚያሳየን ልሳን የሰዎች ወይም የመላእክት ቋንቋ እንደሆነ ነው ::1ቆሮ 13:1-2

ይቆየን ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዘላለማዊ

ዋና ኮትኳች

Joined: 16 Aug 2004
Posts: 680
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Oct 27, 2005 11:41 pm    Post subject: Reply with quote

ወገኖቸ ሰላም በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም

ልሳንን በተመለከተ በዓለማችን በጣም ብዙ ዝብርቅርቃቸው የወጡ ነገሮች ይስተዋላሉ፡ ከጥንታውያን ተብዬ ተመጻዳቂዎቹ እስከዘመነኛ የእምነት እንቅስቃሴ ኃይማኖቶች ድረስ እውነተኛውን የእግዚአብሔር መንገድ የሚያሰድብ ብዙ ነገር ሳትታዘቡ አልቀራችሁም። የእኛዎቹ “ጥንታውያን” ርግማን ይሁን በረከት በማያውቁት በግዕዝ ልሳን ሲንበለበሉ ክርስትና የሆልዊድ አክሽን ፊልም የሆነባቸው ደግሞ ከአስተማሪያቸው እንዲህ በል ተብለው የተማሩትን በየአደባባዩ መፎከሪያ አድርገውት እንደነበር የሩቅ ዘመን ትዝታ አይደለም።

መስመር የሳተ ምግባር በመታየቱ በልሳን መናገር የለም ወደሚል መደምደሚያ መድረስ የካልኩለስ ፎርሙላ ትንተናን ያልተማረ ወይንም ኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ ያላጠና የዋህ ሰው ይህ ምን የሚሉት ጅልነት ነው፣ ለምን ወረቀትና ጊዜያችሁን ታባክናላችሁ ወደሚል መደምደሚያ እንደመድረስ ይሆናል። ወይንም የእኔዋ አያት የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ሳለሁ የልብስ ቅድ ዲዛይን በወረቀት ሰርታችሁ አምጡ ተብለን ያወጣነውን ፓተርን የምን ቤት ማቆሸሽ ነው ብላ አውጥታ እንደጣለችው አይነት ያለማወቅ ይሆናል ::

ያልገባቸውና ያልተገለጠላቸው ሰዎች ከመስመር የወጣ ስራ ስለሰሩ በልሳን መናገር መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነን ትምህርት እንደርካሽ ነገር የሚቆጥር መደምደሚያ ተጽፎ በማየቴ ገረመኝ። እውን በልሳን መናገር በክርስትና የሌለ ነገር ነውን ? አንድ የእግዚአብሔር ሰው ይህን ተጠይቆ ሲመልስ የሰማሁትን እዚህ ብጽፈው ጠቃሚ ይመስለኛል፦ ስለልሳን ከመነጋገር በፊት ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት መንፈስ ቅዱስ መሞላት አለበት የሚለው ከሁሉ ቀዳሚ ነው። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ ወንጌል 35 “እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም”። ይህ ቃል የማይሻር የኃያሉ አምላክ ቃል ነው ብሎ የሚያምን ሰው ሁሉ መንፈስ ቅዱስ ሊሞላ ያስፈልገዋል። ሰው መንፈስ ቅዱስ መሞላቱን መለያ ያስቀመጠው ምልክት ልሳን ነው፤ በቀጣይነት ፍሬው ይመስክራል።
==> ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ መሞላታቸው የተገለጠው በልሳን ነበር - ሐዋርያት ሥራ 24
==> ቆርኔሌዎስና ቤተሰቡ መንፈስ ቅዱስ መሞላታቸውን ሐዋርያት የመሰከሩት በልሳን ሲናገሩ ስለተመለከቱዋቸው መሆኑን ሐዋርያት ሥራ 1044-47 ምሥክር ነው።
==> የኤፌሶን ሰዎች መንፈስ ቅዱስ ተሞሉ በልሳንም ተናገሩ ተብሎ በሐዋርያት ሥራ 196-7 ተጽፏል።

የልሳን አይነቶችን ከመነጋገር በፊት በዚህ መተማመን ፍሬ ያለው ውይይት ለማድረግ መስመር ይቀዳል እንማማርበታለን ብዬ ነው።

ሰላም ይብዛላችሁ።
_________________
በነፍስህ ለቍጣ ችኩል አትሁን ቍጣ በሰነፍ ብብት ያርፋልና
መጽሐፈ መክብብ 7፡9
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ፎግር

ኮትኳች

Joined: 20 Feb 2005
Posts: 147
Location: united states

PostPosted: Fri Oct 28, 2005 1:57 am    Post subject: Re: ልሳን Reply with quote

NATHRATHE እንደጻፈ(ች)ው:
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ::
Very Happy Very Happy Very Happy Very Happy Very Happy Very Happy Very Happy
ምን ልትል ፈልገህ እንደሆነ አብራራልን Question የመልላእክት ልሳን ምን እንደሆነ ታውቃለህ /የሚያውቅስ ሰው ታውቃለህን ? ዝም ብለህ ለመከራከር ስትል የማይሆን ነገር አታምጣ :: በልሳን የሚናገርስ ለአምላክ እንጂ ለሰው አይናገርም ;; በመንፈስ ግን ሚስጥርን ይናገራል :: ከመካከላችሁ የሚተረጉም ከሌለ ...እያለ ልሳን ሊተረጎምም ላይተረጎምም እንደሚችል ይናገራል :: በተጨማሪም በልሳን ከመናገርም አትከልከሉ ይላል ቃሉ :: በርግጥ መንፈስ ቅዱስን የማያውቅ ሰው ሀዋሪያቱ ሲናገሩ በነበሩ ግዜ እንደነበሩት አይነት ሰዎች ናቸው :: የአምላክ መንፈስ ለዩሴፍ ሚስት (ለማሪያም ), አቦ ለሚባለው ግብጻዊ ሰውዬና ለመሳሰሉት ለሚሰግዱ የተሰጠ ሳይሆን በሰማይና በምድር ያሉ ሁሉ ሊሰግዱለት ለሚገባው ለኢየሱስ ለሚሰግዱ የተሰጠ ስለሆነ ክርክርህ ሀይማኖተኛ መሆንህን ብቻ እንጂ ቃሉ ቁልጭ አድርጎ አስቀምጦታል ::

ሰላም ክርስቲያኖች

ፎግር እንደጻፈ(ች)ው:
ልሳን የግድ የሚተረጎም መሆን የለበትም :: 1ቆሮ 13:1 ክርስቲያን በመላእክት ልሳን ሊናገር ይችላልና :: የሚናገረውም ለአምላክ ነው 14:2::

በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮህ ናስ ወይም እንደሚሻንሻ ጸናጽን ሆኛለሁ ::

ይህ እኮ የሚለው በአለም ላይ ባሉ በሰዎች ቋንቋ ሁሉ ብናገር የመላእክትም ቋንቋ ምናገር ብችል ፍቅር ከሌለኝ ከንቱ ነኝ እንጂ ባለቤት በሌለው በማይታወቅ ከአጋንት በስተቀር እኔነኝ የሚል አካል በሌለው ማጎራት ልሳን ነው አይልም ::ይህ ጥቅስ የሚያሳየን ልሳን የሰዎች ወይም የመላእክት ቋንቋ እንደሆነ ነው ::1ቆሮ 13:1-2

ይቆየን ::
Very Happy
_________________
love
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Report post
NATHRATHE

ኮትኳች

Joined: 18 Apr 2005
Posts: 298
Location: united states

PostPosted: Fri Oct 28, 2005 6:02 am    Post subject: Reply with quote

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ::

ሰላም ክርስቲያኖች

ዘላለማዊ እንደጻፈ(ች)ው:
የእኛዎቹ “ጥንታውያን” ርግማን ይሁን በረከት በማያውቁት በግዕዝ ልሳን ሲንበለበሉ

ምነው ጭፍን ትሆናለህ ::የትኛው ካህን ነው የሚናገረውን የግህዝ ቃል ትርጉም የማያውቀው ::እኛም ምህመናን ብንሆን በቤተ ክርስቲያን በግህዝ የተጻፉትን አብዛኛዎቹ የቅዳሴና ሌሎች የጸሎት መጽሐፍ በሌሎች ቋንቋዎች ስለተተረጎሙ ምንም ማለት እንደሆኑ አብዛኛው ሰው ይረዳዋል ::ይህ ግን ከዘመናችን የወፍ ቋንቋ ይሁን ኬት የመጣ የማይታወቅ ትርጉሙን ማንም የማያውቀው ሰዎች እንደሚቀበጣጥሩት አይደለም ::

በቤተ ክርስቲያናችን ስለ ልሳን ያለው ትምህርት በአጭሩ እኔ የተማርኩት እንደሚከተለው ነው ::

በልሳን መናገር የመንፈስ ቅዱስ አጦታ ከሆኑት መካከል አንዱ ሲሆን ልሳን ማለት ሰው ሳያድግበት ወይም ሳይማር እግዚያብሔር መንፈስ ቅዱስ ለአገልግሎት ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች የሚሰጥ የቋንቋ ጸጋ ነው ::

እኔ ኢትዮጵያ ያሉ Protestants እንናገራለን የሚሉት ነገር አንደኛ ቋንቋ ስለመሆኑ ምንም የቋንቋ መመዘኛዎችን ያማያማላ (እንደ እንስሳት ድምጽ ብቻ እንጂ ቋንቋ ለመሰኘት የሚያስፈልጉ መሰረታዊ ነገሮችን የማያማላ ብቻ ሳይሆን አንዱም የሌሉት ) ዝም ብሎ ጩኸት ብቻ የሆነ እና ዋናው ምክንያት ሐዋርያት የተሰጣቸውን የቋንቋ ጸጋ የማያማላ ነው ::በቤተ ክርስቲያችን አንድ ሰው የልሳን ጸጋ ተሰጠው የሚባለው (እንዳንረሳ ልሳን ለአህዛብ ምልክት እንደሆነ እና አገልጋይ ለዚህ አግልግሎት የተመረጠ ከሆነ ) ለሐዋርያት እንደተሰጣቸው አይነት የሚከተሉትን መኖር ያለባቸው

  • የተሰጠው አዲስ ቋንቋ በትምህርት ወይም በማደግ ያላገኘው
  • ቋንቋው ባለቤት ካለው (የእኔ ነው የሚለው የሚሰማው ካለ ለምሣሌ ሐዋርያት ለተሰጣቸው ቋንቋ ከአለም ላይ ኢየሩሳሌም የተሰበሰቡ አይሁድ ቋንቋው በየአደጉበት አካባቢ የሚነገር እንደሆነ እንደመሰከሩት )
  • የቋንቋው ጸጋ የተሰጠውም በተሰጠው የቋንቋ ጸጋ ወንጌል ሰምተው ለማያውቁ ህዝቦች በሚናገሩት ቋንቋ ማስተማሪያነት እንዲጠቀምበት እና በሌሎችም ምክንያቶች ነው ::

ከዚህ ውጭ ቋንቋ ይሁን ጩሆት በማይታወቅና ሁሉም ሰው የተጠና በሚመስል ተመሳሳይ ድምጽ የሚጭኽው የቋንቋ ጸጋ ነው ለማለት በጣም ይከብዳል ::ይህ ዲያብሎስ ቃለ እግዚያብሔርን ለማያውቁ ሰዎች መጫወጫ ማሳቻ ያዘጋጅው ወጥመድ ነው ::እኔ የሚገርመኝ እዚህ አሜሪካ አንድም ቀን እንዲህ በማይታወቅ ቋንቋ የሚያጎራ ሰው አጋጥሞኝ አያውቅም ::ታዲያ እዚህ በምዕራቡ አለም ያሉ አብዛኛው Protetsants የማያውቁት ኢትዮጵያ ያሉ Protestants Big deal ያደረጉት ለምንድን ነው ? እዚህ ያሉት ለምን ተለዩ ?ይህ አፍሪካ ያለን ህዝብ ለማሳት የተዘጋጀ ወጥመድ እንጂ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል ? እራሳቸው የማይፈጽሙትን በሰው ሲጫወቱ ይገርማል ::እሚያሳዝነው ምንም በማያውቀው እያጎራ ጊዜውን የሚጫወትበት ወገኔ ነው ::

እስቲ አንተ በልሳን መናገር ማለት እንዲት እንደሆነ ንገረንና ከዚያን እንቀጥልበታለን ::እኔ ስለተናገርኩት ከላይ (ከዚህ Naw በፊት Post ባደረኩት ) አብዛኛውን ጥቅስ ያስቀመጥኩ ስለሆነ አሁን መድገም ስላልፈለኩ ጣላስቀመጥኩም ::ቤተ ክርስቲያን ከምታስተምረው ከመጽሐፍ ቅዱስ ይለያል የሚል ካለ የሚቃረነውን ጥቅስ ቢያሳየን ደስተኞች ነው ::እግዚያብሔር ለሁላችንም ልቦና ይስጠን

ይቆየን ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ግሸንማርያም

ኮትኳች

Joined: 15 Aug 2005
Posts: 349
Location: ethiopia

PostPosted: Fri Oct 28, 2005 7:36 pm    Post subject: ፕሮቴስታኖትች የመንፈስቅዱስ ሙላት አላቸው ??? Reply with quote

በስመ አብ በስመ ወልድ በስመ ወመንፈስቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን :: የተከበርክ ውድ ወንድሜ ናዝሬት ለጤናክ እንደምን አለክ ? እኔ ቸርነቱ የባህርይው የሆነ ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይግባው ደህና ነኝ :: ይህ አሁን የጀመርከው ርእስ በጣም አስተማሪ ነው :: ብዙ ሰዎች መንፈስቅዱስን ያገኙ እየመሰላቸው መንፈሰ እርኩ እላይ እያደረሰ የሚያፈርጣቸው ሰዎች አሉ :: ለምሳሌ አንድ ኢትዮጵያ ውስጥ የመናፍቃን መጋዘን አለ :: በዚያ ውስጥ አንዴ መንፈስቅዱስ ወረደ ብሎ ፓስተሩ ሲጮህ ሰው ሁሉ ጣሪያ እየነካ ተዘረረ :: የሚገርምክ አንድ ዘብ ነገር ነበር :: ሰው ሁሉ ሲወድቅ እኔ አልወደቅኩም ነበር :: ከዚያ እውነቴን ነው የምልክ በጠረባ ጣለኝ በዝኅን ግዜ ተነስቼ ምነው መታህኝ እለዋልሁኝ መንፈስቅዱስ ነው አለኝ :: ሳስበው በጣም ያስቀኛል :: የመንፈስቅዱስን ማንነት ገና አላወቁም መጸሀፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል ሰውን ብትሰድበው ሐጢያትህ ይቅር ይባልልካል መንፈስቅዱን የሚሳደብ ግን ሐጢያቱ አይስተሰርይለትም ይላል :: ትመልከቱ ሰይጣን የመናፍቅን ሐጢያት እንዳይፋቅ ስለሚፈልግ መንፈስቅዱስን ያሰድባቸውል :: ሰውን በካራቴ እየጣሉ በመንፈስቅዱስ ቢያላክኩ ምን ይባላል :: አይ አለማወቅ :: መንፈስቅዱስ እኮ በሀዋርያት ላይ ሲወርድ ዝም ብሎ አልወረደም :: አለምን ሄዳችሁ አስተምሩ ብሎ በማርቆስ ምህራፍ 16 ቁጥር 15-17 ስትመለከቱ አለምን አስተምሩ የሚል ትእዛዝ እግዚአብሔር ለቅዱሳን ሐዋርያት ሰጥቷቸዋል :: አለምን አስተምሩ ስለተባሉ አለም ደግሞ የተለያየ ቍዋንቅዋ ስለሚናገር የግድ የአለምን ቁዋንቅዋ መናገር መቻል ነበረባቸው ለማስተማር :: ስለዚህ ነው ልሳን የተሰጣቸው እንጂ ዛሬ መናፍቃን ጎሬ ውስጥ እንድሚታየው ለፓስተሩም ለሴቱም ለወንዱም አይሰጥም :: ይህ የሚሰጠው ለጥቂት ሰዎች ነው :: እነሱም እግዚአብሔር ሲመርጣቸው ነው :: እኔ ግን አንድ በየለያዩ ቁውንቁዋዎች (ልሳኖች ) መናገር የሚችል ወጣት ባህታዊ አውቃለሁኝ ::ይህ ባህታዊ ሲዳሞ ሲሄድ በሲዳሞኛ ወደ ትግራይ ሲሄድ በትግርኛ ወደ ኦሮምያ ሲሄድ በኦርምኛ አዲስ አበባ ሲመጣ በአማርኛ ወንጌልን ያስተምራል :: ብዙ ጊዜ እንደውም እንጦጦ ኪዳነምህርት ያስተምራል :: ልሳን ማለት እኮ ይሄ ነው :: መናፍቃን የሚያወሩት ከመጸሀፍቅዱስ ጋር ምንም ግኑኝነት የሌለው ተረት ነው :: እስቲ ለማንኛውም መናፍቃን መንፈስቅዱስ አለብን ብለው ያወራሉ :: ይህ ዲሞክራሲ ነው :: ማለት ይችላሉ :: አይከለከሉም :: ነገር ግን በመጸሀፍቅድስ ውስጥ መንፈስቅዱስ የወረደባቸው ሰዎች ምን ይመስሉ ነበር እያልን :: መናፍቃን ዛሬ መንፈስቅዱስ ወረደብን እያሉ ከሚቀባጥሩ ጋር እስቲ በንጽጽር እንመልከተው ::ፕሮቴስታንቶች የመንፈስቅዱስ ሙላት አላቸው ? ? [u]

"" መንፈስን ሁሉ አትመኑ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር እንደሆኑ መርምሩ 1ኛዮሐንስምህራፍ 4 ቁጥር 1:: ተመልከቱ ወገኖቼ መንፈስን ሁሉ ማመን አይገባም :: ምክንያቱም ሰይጣን ራሱ አስመስሎ መምጣት ይችላልና :: 2ኛቆሮንጦስ ምህራፍ 11 ቁጥር 15 ስይጣን ቅዱስ መልአክ እስከ መድረስ ያስመስላል ይላል :: ስለዚህ የእርኩስ መንፈስንና የቅዱስ መንፈስን ባህርይ መለየት ከሁላችን ይጠበቃል ::

ዛሬ በፕሮቴስታኑ አለም የምናያቸው ነገሮች ከእግዚአብሔር መንፈስ እንዳልሆነ ያገጋግጡልናል ::
እስቲ በመጸሀፍቅድስ ውስጥ የመንፈስቅዱስ ሙላት የነበረባቸው ሰዎች ምን ይመስላሉ ምን ይናገራሉ ??

ለምሳሌ ቅድስት ኤልሳቤጥ የቅዱስ ዮሐንስ እናት መንፈስቅዱስ ሞላባት ይላል :: ልክ መንፈስቅዱስ እንደሞላባት ቅድስት ድንግል ማርያምን በታላቅ ቃል ጮሀ አመሰግነቻት :: ቃሉ እንንዲህ ይላል "" ኤልሳቤጥ የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ጽንሱ በማህጸኑዋ ውስጥ ዘለለ በኤልሳቤጥም መንፈስቅዱስ ሞላባት በታላቅ ድምጽ ጮሀ እንዲህ አለች :- አንቺ ከሴቶች መካከል የተለሽ ነሽ የማህጸንሽም ፍሬ የተባረከ ነው :: የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል የሰላምታሽ ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ጽንሱ በማህጸን ዘለለ ሉቃስ ምህራፍ 1 ቁጥር 39-45 "" አለቻት :: ተመልከቱ ! መንፈስቅዱስ ያለበት ሰው እንደዝህ ቅድስት ድንግል ማርያምን ያመሰግናል :: ዛሬ ግን መናፍቃኑ ቅድስት ድንግል ማርያምን እየሰደቡዋት መንፈስቅዱ አለብን ሲሉ ሼም አይቆነጥጣቸውም :: አያፍሩም :: መንፈስቅዱስ አንድ ነው :: በኤልሳቤጥ ላይ መንፈስቅዱስ አድሮ ቅድስት ድንግል ማርያም አስመስግኗታል :: የዘመናችን መንፈስቅዱስ ቅድስት ድንግል ማርያም ያሰድባልን ? ይቅር ይበላቸው :: ስለዚህ አንዱ የመንፈስቅድስ እና የመንፈስእርኩስ መለያ ይህ ነው :: መንፈስቅዱስ ሰዎች ላይ ሲያድር ቅዱሳንን እመቤታችን ቅድስት ንጽህትይ ማርያምንን እንድትመሰገን ያደርጋታል :: እግጠኛ ነኝ ከዚህ ትምህት ቡሀላ ቅድስት ድንግል ማርያምንም ሆነ ቅዱሳንኑን አይሳደቡም :: ከእግዚአብሔር የሆነ መንፈስ ቅዱሳንን እንዲሳደቡ አይፈቅድም :: እንደውም መጸሀፍቅዱስ ቅዱሳንን የሚሰድብ የተረገመ ይሁን ይላል :: በመዝሙር ምህራፍ 30 ቁጥር 18 ስትመለከቱ በሽንገላ በትህቢት በቅዱሳን ላይ የሚናገሩ አንደበቶች ድዳ ይሁኑ ይላል :: ሰለዚህ አንድ ሰው ተነስቶ ቁዳኑን ወይም የእግዚአብሔር እናት ይህች ምንድናት ወይዘሮ እያለ ቢሳደብ በቀላሉ የእርኩሳን መናፍት ሐይል እንዳለበት በዚሁ ማወቅ እንችላለን :: እስቲ በየተኛው የመጸሀፍቅዱስ ጥቅስ ላይ ነው ቅዱሳኑን ተሳደቡ የሚለው ? አንድም ቦታ አታገኙም :: ቅዱሳኑን አክብሩ የአክብሮ ስግደት ስገዱላቸው የሚል ግን ታገኛላችሁ ::

ስለዚህ ፕሮቴስታንቶቹ (ማቲንሉተር የመሰረተው እምነት ) ከእግዚአብሔር ቢሆኑ ኖሮ ቅዱሳንን አይሳደቡም የቅዱሳንን ክብር ይጠብቁ ነበር :: ቅዱሳንን የሚቃወም መንፈስ ከአጋንንት ነው ራእይ ምህራፍ 12 ቁጥር 1-7 ::

ቅዱስ ጳውሎስ ሲመክረን ""መንፈስን አታጥፉ ትንቢትን አትናቁ ሁሉን ፈትኑ ከማናቸውም አይነት ክፉ ነገ ራቁ 1ኛተሰሎንቄ ምህራፍ 5 ቁጥር 19 :: በዚህ መሰረት የእግዚአብሔር መንፈስን ስራ አለማጥፋት የሚገባ ነው :: የሚበልጠውን ትንቢት ንቆ ወደ ልሳን መሮጡ ጥሩ አይደለም :: ከእግዚአብሔር መንፈስ ጋር መጣላት ነው :: ሁሉን ፈትኑ እንደተባለ ሰይጣን ባፈረበት በቅዱስ መስቀሉ የእግዚአብሔርንና የሰይጣንን መንፈስ መለየት እንችላለን :: ስለዚህ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ የመስቀሉ ሐይል ያስፈል 1ኛቆሮንጦስ ምህራፍ 1 ቁጥር 18 ::

ልሳን ደግሞ የመጨረሻ ትንሽ ስጦታ ነው :: ፕሮጠስታንቶች በጣም ይስገበገባሉ ለልሳን ልሳን ግን ትንሹ የመጨረሻው ስጦታ ነው :: ከእውቀት : ከእምነት : ከመፈወስ : ትንቢትን ከመናገር ከነዚህ ሁሉ ስጦታዎች ልሳን የመጨረሻው ነው 1ኛቆሮንጦስ ምህራፍ 12 ቁጥር 9-11 ::

እንግዲህ እናንተ ደግሞ መንፈሳዊ ስጦታን በብርቱ የምትፈልጉ ከሆናችሁ ቤተክርስትያንን ለማነጽ እንዲበዛላችሁ ፈልቁ 1ኛቆሮንጦስ ምህራፍ 14 ቁጥር 12 :: ቤት ክርስያንን የሚያንጻት ደግሞ ትልቁ ስጦታ ፍቅር ነው :: እንጂ ልሳን አይደልም አይደለም ::

እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሶስቱ ጸንተው ይኖራሉ ከነዚህም ፍቅር ይበልጣል 1ኛቆሮንጦስ ምህራፍ 13 ቁጥር 13 ::

በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ከሌለኝ እንደሚጮህ ናስ ወይም እንደሚሸዋሽዋ ጽናጽል እሆናለውሁ 1ኛቆሮንጦስ ምህራፍ 13 ቁጥር 1 ::

ለዚህም ይመስላል ልሳንን ብቻ ሲያስቡ ፍቅርን ረስተው በአሁኑ ሰአት በፕሮቴስታንቶች መካከል የሰይጣን ሰራ የሆነው መለያየት እያበዛ የመጣው :: ምክንያቱም ፕሮቴስታንት በጀመሪያ እምነት አልነበረም :: ማርቲን ሉተር ጀርመናዊያንን ለመታደግ አሁን ባለንበት ጊዜ የእገሌ አገር ዲሞክራሳዊ ታጋይ እየተባለ ስም እንደሚሰጠው ሁሉ :: ማርቲን ሉተርም ከካቶሊክ ለመለየት ሲያስብ ካቶሊክን የሚቃወም ደርጅት ለማቆም አሰበ :: አስቦም ተቃዋሚ ድርጅት ሲል ፕሮቴስታንት ብሎ የድርጅቱን ስም ሰየመው :: ከዚያ ቡሀላ ሰዎች ለምን የጀርመን እምነት አናእርገውም ብዙ ተከታዮች አሉን ድርጅታችንን ክርስትያን እያልን እንጥራ አሉ :: ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እራሳቸውን በራሳቸው ክርስትያን ይላሉ :: በወቅቱ ይህ እምነት 1 ነበር :: አሁን ግን በቁጥር በሚያዳግት ሁኔታይገኛል ፍቅር ስለሌላቸው በየጊዜው እንደ ትል ይበጣጠሳሉ ይለያያሉ በአሜሪካ ብቻ 1 የነበረው እምነት አሁን 1700 ከአንድ ሰባት መቶ በላይ ሆኑዋል :: በጣም የሚያስቅ ነው :: ይህ ሁሉ የሆነው አንደኛው ምክንያት ፍቅር ስሌላቸው ነው ::

መጸሀፍቅዱስ እንዲህ ይላል "" ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም ትንቢትም ቢሆን ይሻራል ልሳኖችም ቢሆን ይቀራሉ 1ኛቆሮንጦስ ምህራፍ 13 ቁጥር 8 :: ስለዚህ ለሚቀር ነገር ያን ያህል ከመድከም ሊወድቅ የማይችለውን ፍቅር መያዝ በበለጠባቸው ነበር :: ፍቅር ስለሌላቸው እኮ ነው ምስኪን ኢትዮጵያዊ የኔ ቢጤ እርቦት መንገድ ላይ ውድቅ ዳቦ ሲለምን ለዚህ ሚስኪን ኢትዮጵያዊ ማርቲን ሉተር የመሰረተውን የጀርመን እምነት ካልተቀበል አልሰጥህም የሚሉት :: አማላካችን ኢየሱስ ክርስቶ ግን ለሚለምናችሁ ለተቸገተ ሁሉ ስጡ ብሏል ሉቃስ ምህራፍ 6 ቁጥር 29 :: ፍቅር ለባልንጀራው ክፉ አያደርግም ይራራል ችግረኛን ይረዳል ስለዚህም ጌታችን ፍቅር የህግ ፍጻሜ ነው አለ ሮሜ ምህራፍ 13 ቁጥር 8-10 ::ያውም ተገለጸልን የሚሉት እኮ እውነት ቢሆን እሺ :: ይህ የእውሸት ዝም ብለው ብቻ እንዲህ ይላሉ ቂቂቂቂቅ ጫጫጫ አሌሌል ጢሬስስስስስ ሞሲኝኝኝኝኝኝኝ ቡርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርር ወገኖቼ ይህንን ነው የሚሉት መንፈስቅዱ ወረደ ብለው ይሄ መቼም አስቂኝ ድራማ በእመት ስም እለሀለሁኝ ::
አቤት ማስተዋል ከሰው ስትወሰድ እንዲህ ያውራል ለካ ? ለዚህ ነው 12 አመቱ ብላቴና እግዚአብሔርን ማስተዋልን ስጠኝ ብሎ የለመነው :: እግዚአብሄርም ጥበብን ሰጠው :: ለሁላችንም ጥበቡን ያድለን አሜን ::

መጸሀፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል "" እግዚአብሔር ፍቅር ነው "" 1ኛዮሐንስ ምህራፍ 4 ቁጥር 8"" እግዚአብሔር ይሚከብረው በልሳን ሳይሆን በፍቅር ነው ::ስለዚህ የበለጠውን ስጦታ አናሳ ትንሽ ለተባለ የልሳን ስጦታ ሰዎችን ማሩዋሩዋጥ ለዚያውም ላልተጣራ ልሳን :: ከመጸህፍቅዱስ ጋር ምንም መመሳሰል ለሌልው ለማርቲንሉተር ቲዎሪ እርሳችንን ባሪያ አናድርግ :: ከልሳን ይልቅ የሚበልጠውን ፍቅርን መፈለጉ ይሻላል ::

ይቀጥላል ::

ውድ ወንድሜ ናዝሬት በዚሁ ቀጥል የአጋንንትን አፍ አሁንም ዝጋው !!! ቅድስት ድንግል ማርያም ትባርክህ ትቀድስህ ልጄ ወዳጄ ትበልክ ቃለ ሕይወት ያሰማልን መንግሰተ ሰማያትን ታዋርስልን :: ::

የእግዚአብሔር ቸርነት የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት የጻድቃን የሰማእታት ጸሎትና ምልጃ የቅዱሳን መላእክት አማልጅነትና ተራዳይነት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን ::

ኢየሱስ ፈራጅ ወይስ አማላጅ ከሚለው መጸሀፍ ላይ የተወሰደ :: በመምህር ዲያቆን አሐዱ አስረስ :: ውንድማችንን ቃለ ህይወት ያስማልን ::

ወስብሀት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለ መስቀሉ ክቡር ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ፎግር

ኮትኳች

Joined: 20 Feb 2005
Posts: 147
Location: united states

PostPosted: Sat Oct 29, 2005 5:40 am    Post subject: ቂቂቂ ...የአይጥ ምስክር ...ነው አሉ Reply with quote

ለግሰን ማሪያም

እንዴት ያለ ፕሮፖጋንዳ ነው ባክህ :: የናንተ መለኪያ ሰው ሆኖ መቅረቱ ያሳዝናል ይልቅ ዝም ብለህ የማይሆን ነገር ከምትቀባጥር ወደ ጌታ ኢየሱስ ዞር በል :: ዛሬ እነ ወይዘሮ ማሪያምን አቶ ተክለህይማኖትን ; የጦር መሪውን ጊዩርጊስን ከማምለክ ዳን :: የአምላክ ቃልን በግልጽ እየተቃወምክ መሆኑን አትዘንጋ :: ስለእናንተ ህይማኖትማ ቤት ይቁጠረው :: ስንቱን በቁሙ ገደላችሁት ድንጋይ እያሳለምችሁ : በቅዱሳን ስም ለአጋንንት እያሰገዳችሁ እረ ስንቱ ...ቤት ይቁጠረው Evil or Very Mad Evil or Very Mad Evil or Very Mad Evil or Very Mad :: ገድል ነው ገደል እያላችሁ ባባቶቻችን የተጫወታችሁት ይበቃል ጌታ መጣባችሁ ከነዝባዝንኬያችሁ ከምድሪታ እንድትወጡ :: የሚያሳዝነኝ የኔ ዘመዶች (በተለይ ገጠር ያሉት የናንንተ ገድል (ገደል ) መጫወቻ መሆናቸው ነው ) አምላክ ይታደጋቸው ::

ሲወርድ ሲዋረድ እያላችሁ የተዋረደውን ዝባዝንኬ ታጠጡታላችሁ ለየዋሁ የኢትዩጵያ ህዝብ :: Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing

ጌታ ነገሩን ሁሉ እየገለባበጠው ነው :: ምን ይታወቃል በቅርብ የጌታ ልጆች ገዳም ውስጥ ለጌታ የሚዘምሩት (የሚሰግዱበት ) ጊዜ ይመጣ ይሆናል :: Very Happy Very Happy Very Happy ያኔ ደሰታ ; ሰላም ; ምስጋና ; እርካታ በገዳም ውስጥ ይሆናል :: ጌታን የሚወዱ ሲደሰቱ የአጋንንት ተከታዩች አንጀታቸው እያረረ ከሰይጣን ጋር ወደ ውጭ :: አንተም በዚህ ትስማማለህ አደል ::
_________________
love
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Report post
አፈ -ጉባኤ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Mar 2005
Posts: 566
Location: united states

PostPosted: Sat Oct 29, 2005 7:14 am    Post subject: ሳይንሱ ምን ይላል ? Reply with quote

ጥቂት በልሳን ስለ መናገር ከሳይንሱና ከከሀዲያን አምባ ::

አንዳንድ ሳይኮሎጂስቶች በልሳን ተናጋሪዎችን (እንናገራለን ባዮችን ) የአእምሮ ጉድለት ያለባቸው ናቸው ሲሉ እንደ ጆን ኪልዳብል ያሉ ሳይካትሪስቶች ደግሞ በህይወታቸው ብዙ ቀውስ ያጋጠማቸው ናቸው ይላሉ ::
የስነ ቋንቋ ጠበብት (ሊንግዊስት ) ደግሞ ተናጋሪዎቹ እሚናገሩት ምንም አይነት ስልት የሌለው : ስሜት የለሽ : ልፍለፋ ነው ባይ ናቸው ::

ተጠራጣሪዎች ደግሞ ልሳንን ግላዊ ቅዠት : (Self-hypnotism) ሀይማኖታዊ ትፍስህት : ስሜትን መቆጣጠር አለመቻል ይሉታል :: እኔም ከነኚህ ጎራ እመደባለሁ :: በተለያዩ ጉባኤዎች ላይ ያጋጠሙኝ ልሳን ተናጋሪዎች በጥልቅ ስሜት ተውጠው ጥቂት ስልት አልባ ቃላትን ካነበነቡ በኾላ በሚታወቅ የእብራይስጥ ቃል ሲቋጩ አድምጫለሁ ::

አንድ የተረዳሁት ነገር ቢኖር ብዙዎቹ ለማጭበርበር ብለው አይደለም እሚናገሩት መንፈሱ በማይገባቸው ቋንቋ በነሱ አድሮ የተናገረ ስለሚመስላቸው ነው :: የዋሆች !
ባጠቃላይ ልሳን ብሎ ልፍለፋ አስቂኝ ድራማ ነው ::

ከጠርጣሮች መንደር
አፈ -ጉባኤ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ፎግር

ኮትኳች

Joined: 20 Feb 2005
Posts: 147
Location: united states

PostPosted: Sat Oct 29, 2005 3:49 pm    Post subject: ለፈላስፋው አፈ -ጉባኤ Reply with quote

አይ አንተ የማትገባበት የለም መቼም :: አንተና መሰሎችህ ስለልሳን ለመናገር ብቃት የላችሁም ምክንያቱም በራሳችሁ ጠባብ አመለካከት እንጂ በአምላክ ቃል የማታምኑ ተስፋ ቢሶች ናችሁ :: ከዚህ በፊት የብሉይ ኪዳኑ አምላክ አረመኔ እንደሆነ ተርከህልን ነበር ዛሬ ደግሞ ስለልሳን ልታስተምር ብቅ አልክ :: እንዳንተ አይነቱን ሰው /ቅዱስ ፍጥረታዊ (በጠባብ አእምሮው የሚመራ ) ሰው ይለዋል ስለዚህም ለፍጥረታዊ ሰው የአምላክ ነገር ሞኝነት ነው :: በጣም የገረምከኝ ደግሞ ሰለ አምላክ ቸርነትም ተናግረህ እንደነበር አስታውሳለሁ በዚያም ነበር የብሉይ ኪዳኑን አምላክ ወንጀለኛ ያደረግከው :: አምላክ አፍቃሪ መሆኑን ማን እንዳስተማረህ ብትገልጽልን ? ምክንያቱም አንዳንድ አንተን መሳዩች አምላክ አረመኔ ነው ሲሉ ይሰማሉና :: እንደኔ እንደኔ የሁላችሁም ተራ ፍልስፍና መሆኑ አንዳች አልጠራጠርም :: ዛሬ በአለማችን ያሉት ክርስትያኖች አንተ እንዳልከው የዋሆች ቢሆኑም ካንተና ከመሰሎችህ የተሳሉ ጠቢባን ናቸው :: ከየት እንደመጡ ምን እንደሚሰሩና ወዴት እንደሚሄዱ የሚያውቁ የምሁር ምሁር ናቸው ::
_________________
love
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Report post
አፈ -ጉባኤ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Mar 2005
Posts: 566
Location: united states

PostPosted: Sat Oct 29, 2005 6:48 pm    Post subject: Re: ለፈላስፋው አፈ -ጉባኤ Reply with quote

ፎግር እንደጻፈ(ች)ው:

አንተና መሰሎችህ ስለልሳን ለመናገር ብቃት የላችሁም ምክንያቱም በራሳችሁ ጠባብ አመለካከት እንጂ በአምላክ ቃል የማታምኑ ተስፋ ቢሶች ናችሁ ::

እኛን ከሀዲያኑን ተወንና ለምን ክርስቲያኖቹ ራሳችሁ መኖሩን አትተማመኑም ? እንደ ስምህ አሪፍ ፎጋሪ ነህ :: በየዋህነት በምሻው ወቅትም ለናንተ የተገጠመላችሁ መንፈሳዊ ሪሲቨር ስላልተገጠመልኝ እንደሆነ አላውቅም ከጫጫታ በቀር የሰማሁት አልነበረም :: አንተም ሆንክ ቢጤዎችህ አንድም ቀን ትርጉም ያለው ነገር ሰምታችሁ እንደማታውቁ ፍጹም እርግጠኛ ነኝ :: አትፎግሩ ! አትደናቆሩ !

ይህ ልማድ በክርስቲያኑ ይጉላ እንጂ በሎሎችም እምነቶች የተለመደ ጉዳይ ነው ለምሳሌ በሄይቲ ቩዱ አምልኮ :: እነሱስ እሚያጫጭሷት ነገርም ነች እንዲያ እምታስረግዳቸው ::

Quote:
ከዚህ በፊት የብሉይ ኪዳኑ አምላክ አረመኔ እንደሆነ ተርከህልን ነበር ::

ብሉይ ኪዳን ባብዛኛው ግደል ጨፍጭፍ ነው እሚለው :: እሰው አገር ድረስ ሄደው "አዋቂውን ህጻናቱን ከብቱን እስትንፋስ ያለውን ፍጡር ሁሉ ጨፍጭፉ " ብሎ እሚያስጨፈጭፍ አምላክን መሀሪ ልበለው ? ሳኦል ጮሌው ሰውን ጨርሶ ከብቱን ይዞ ስለተመለሰ ስልጣኑን እንደተቀማ አላነበብክም ? በየወቅቱ አምላካችሁ መላእክቱን እየላከ እልፍ አእላፉን ደም እንዳፈሰሰ አልተጻፈም ?

በዘመናችንስ በሱናሚና በመሬት መንቀጥቀጥ በቅጽበት የመቶ ሺዎች ህይወት እንደተቀጠፈ በመቶ ሺዎች እሚቆጠሩ ህጻናት ወላጅ አልባ እንደሆኑና ሚሊዮኖች ቤት አልባ እንደተደረጉ ዘነጋህና ነው ስለ ፍቅሩ እምታወራው ? እኔስ ያላየሁትን አይቻለሁ እምል ቀጣፊም ባለጌም አይደለሁም :: ያላየሁትን ፍቅር አልመሰክርም :: ወገኖቼ ካመት አመት በርሀብና በበሽታ ሲረግፉ እያየሁ ባልወቅሰውም ስለ ፍቅሩ እማወራበት ልሳን የለኝም :: ሀጢያተኛ ሰይጣንና ሰዉን ያለፍላጎቱ ፈጥሮ እሳት ከሚዶል ጨካኝ የበለጠ አለ ?

እኛ የሰው ልጆች ግን ወንጀለኛን እንኳን ሳናንገላታ ነው አግተን እምናቆየው አይደለም በዘላለም እሳት ልናንበልብለው :: ይልቅ አንተ ስላላየኸው ፍቅር ባታወራ አይሻልም ? ስለ ፍቅርና ምህረት ባወራ ባልጠላሁ :: የሰው ልጅ በጥረቱ ይቺን አለም ይለውጣታል :: እነ ሱናሚ ወደፊት ያሁኑን አይነት ጥፋት አያደርሱም :: ያኔ አምላካችሁ መሀሪ ይባላል ::

Quote:
በአለማችን ያሉት ክርስቲያኖች አንተ እንዳልከው የዋሆች ቢሆኑም ካንተና ከመሰሎችህ የተሳሉ ጠቢባን ናቸው :: ከየት እንደመጡ ምን እንደሚሰሩና ወዴት እንደሚሄዱ የሚያውቁ የምሁር ምሁር ናቸው ::

መስመሩን ለቀቅክ ስለ ክርስቲያኖች አላወራሁም ልሳን እንናገራለን ስለምትሉት እንጂ :: ስለ [/quote]ትምህርት ደረጃችሁም አላወሳሁም ::

ያላየውን እማይመሰክረው
አፈ -ጉባኤ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Goto page 1, 2, 3 ... 12, 13, 14  Next
Page 1 of 14

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia