WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
በምናኔ በሚኖሩ ሰዎች ከሰይጣን የሚደርስባቸው ፈተና ::

 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General


 
View previous topic :: View next topic  
Author Message
ደብረ ዲማ

ኮትኳች


Joined: 17 Mar 2005
Posts: 275
Location: united states

PostPosted: Fri Nov 18, 2005 6:11 am    Post subject: በምናኔ በሚኖሩ ሰዎች ከሰይጣን የሚደርስባቸው ፈተና :: Reply with quote

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ::

6ተኛው አንቀፅ ከሥራ ሁሉ ይልቅ የምታስቸገር በምናኔ በሚኖሩ ሰዎች ከሰይጣን የሚመጣ ልዩ ልዩ የሚሆን ነገር ይናገራል :: ጸላታችን ዲብሎስ ህግ በመጠበቃቸው ቀንቶ :: አንድም ክብሬን ነሱኝ ቦታዬን ወሰዱብኝ ብሎ በተንኮል አንድም ' በርቀት ይኖራልና :: ሕግ ለመጠበቅ በተዘጋጁ በሚዋጉት በምነኮሳት ይተነኮላልና :: ፆሩን ያወረውርባቸው ዘንድ እንደ ፅናታቸው መጠን አለ :: ጋሻ እንደአያያዛቸው እንዳመካከታቸው ::እንደ ወንበዴ ጋሻ አንግቦ ገብቶ ጦሩን ነጥቆ ያየው እንደ ሆነ ይህስ ሳይጥለኝ አይቀርም ብሎ ያሳልፈዋል :: ዝሎ ደክሞ ያየው እንደሆነ ጦሩን ይጥልበታልና :: እንዲህ አለ :: ባሕርያቸው ግብራቸው '' እንደተገለጸለት መጠን ፆሩን ይለዋውጣል :: ሰነፎች ሁነው የሚያያቸውን በሥራቸው የደከሙ ሁነው የሚያያቸውን የጀመሩትን ሥራ የማይፈጽሙ ሁነው የሚያያቸውን ግን አስቀድሞ ፈጥኖ ሊወጋቸው ይነሣል :: ጽኑ ፆር ያስነሳባቸዋል :: የጀመሩትን ሥራ ደስ ያሰኛቸዋል ብሎ ፈርቶ :: ሥራ በጀመሩ ጊዜ በመጀርያው ፆር ጊዜ ፍርሐት ይመጣባቸዋል :: ምናኔ የምታስቸግር የምታሳዝን እንደሆነች ትገለጽላቸዋለች :; መንገዷ ቀጠና ዳጽ እንደሆነች ትገለጽላቸዋለች :: የምናኔ መጀመርያ ሥራ እንዲህ ወጣ ገባ አስቸጋሪ ዳጽ ከሆነ በምናኔ ውሥጥ ያለ መከራን መቀበል :: አንድም / በምናኔ ተዘጋጅቶ ያለ ትሩፋትን መሥራት ማን ይችለዋል :: እንዲሉ ያደራጋቸዋል ::መከራው እስከመቸ ነው እንዲሉ ያደርጋቸዋል :: አንድ ወገን ሐዘን አንድ ወገን ፍርሐት ስላገኛቸው ስለ ፈሩ ትሩፋት መሥራት አይቻላቸውም :: ሰይጣን ፆሩን ያጸናባቸዋል :: ፈጽመው ይሸሹ ዘንድ ጽንዕ ጌትነት ያለው እግዚአብሔር ሰይጣንን እንዲያሰናብተው እንናገር ዘንድ ይገባል :: በምንም በምን ፈጽሞ አይረዳቸውም :: ክብር ይግባውና ስለሱ ወደሚቀበሉት መከራ እየተጠራጠሩ እየፈሩ እየተባረዱ ገብተዋልና :: ለጊዜው ኤርምያስ ለፆር ተናግሮታል ብሎ ለሚዋጋ እጁን ከመስለብ የከለከለ ርጉም ነው ተብሎ እንደ ተነገረ :: ፍፃሜው ግን መከራ ከመቀበል ትሩፋት ከመስራት የተከለከለ ርጉም ነው ተብሎ እንደ ተነገረ :: ዳግመኛ የጸኑትን ፈጥኖ ይሰማቸዋል :: እግዚአብሔር ሳንፈራ ሳንበርድ ጸላታችንን እንገጥመው ዘንድ ያዛልና :: ሳይቀድምህ ቅደመው ብሏልና አንድም / ፈጥነህ ድል ንሣው ብሏልና ትዋጋው ዘንድ መር ብለህ ቁንጮውን ያዘው ከቁንጮው ላይ ውደቅበት ብሏልና ጸንተህ ተዋጋው :: በምድራውያን ጸላቶችህ ሁሉ ፍርሐት አሳድርባቸዋለሁ ብሏልና :: እግዚአብሔር ዋጋዬን ይሰጣኛል ብለህ አንተ አውቀህ መከራ ካልተቀበልህ ግድ ሞተ ነፍስ ትሞታለህ ይኽውም መለየት ለብቻህ እድል ፈንታህ የሚሆን ነው ሞተ ሥጋ ለሁሉ ነው መተ ነፍሥ ግን ለየብቻው ነውና :: ስለመንግሥተ ሰማያት ብለህ ኃላፊውን መከራ ለመቀበል አትጥላ ወደ መንግሥተ ሰማያት ትገባ ዘንድ መግባቱን አትጥላ :: ለእግዚአብሔር ብለህ መከራ በመቀበል ብትሞት በሥጋ ነውና አትጽላ አንድም ለእግዚአብሔር ብለህ መከራ በመቀበል በሥጋ ብትሞት እሱ ያከብርሐል አካልህን ያከብረዋል :: { የሰለስቱ ደቂቅን አካላቸውን አጽማቸውን መከራ በመቀበሉ አንዳከበረ } ዳን , 3. 27.} ያከብርሃል ብየ እንደተናገርሁ :: ሥራ በመጀመሩ ጊዜ ቸል የሚሉ ድውያን የሚሆኑ ሰዎች ሥጋቸውን የሚወዱ ለምናኔ ለመከራ አሳልፈው የማይሰጡ ነፍሣቸውን ከሥጋቸው የሚለዩበትን መከራ የማይቀበሉ አንድም እንሙት ብለው መከራ የማይቀበሉ አንድም ሁዋላ ነፍሳቸውን ከገሃነም የሚያድኑበትን መከራ የማይቀበሉ በሰልፍ ጊዜ በሁሉ ዘንድ ፈጽሞ ቸልተኞች ሁነው የሚገኙ :: በሐኬት { በትዕቢት } ሰጥመው የሚገኙትን ሰዎች ግን ከሐገር አስወጥተው ይሰዷቸው ዘንድ ይዋጛቸው ዘንድ ክቡር እግዚአብሔር እንዲያሰናብታቸው እንናገር ዘንድ ይገባል :: ጌታን በእውነት አልፈለጉትምና :: እንደ ጸሐፍት እንደ ፈሪሳውያን ግብረ እግዚአብሔርን ሠርቶ መፈጸምን ወደዱ እንጂ ስላላመኑ ስለ ፈሩ ሰይጣን ሥራ በጀመሩ ጊዜ አወቀባቸው :: ልማሞች እንደሆኑ የሕሊናቸውን አናዋር አወቀባቸው :: ነፍሳቸውን እንዳይወዱ ለሥጋቸው እንዲያዝኑ :: ስለዚህ ነፋስ መሬቱን እንዲጸርገው እንዲበትነው ድል ይነሳቸዋል :: ወትሮ ከቅዱሳን ያይ እንደ ነበረ የንፍስ ጥብዓትን { ሃይማኖትን } አላየባቸውምና ክብር ይግባውና እግዚአብሔር ቢጸና ሰውን ይረዳዋልና :: መጠበቁን ለርሱ እንዲያስብለት ይገልጽለታል :: ሰው እግዚብሔርን እንደማሰቡ መጠን ልቡናው ጨልጦ ገርኝቶ ወደሱ እንደ መሄዱ መጠን ትሩፋትን ቸል ካላለ ሰይጣን ወደ ሰው መቅረብ አይቻለውምና :: መከራ አያመጣበትም :: ቸል በማለቱ እግዚአብሔር ካላሰናበታቸው ወይም ወደ ክፉ ሥራ ካልተሳበ በትምክህትም ቢሆን ::በትዕቢትም ቢሆን በልብ መጠራጠርም ቢሆን በፍርሃትም ቢሆን ወደ ክፉ ሥራ ካልተሳበ ጸላኢ ዲያብሎስ እንዲህ ያሉትን ሰዎች ሊወጋቸው ይሻል :: ከተወለዱ { አንድም } ከመነኑ ያልዘገዩ ከመነኮሱ ዘመናቸው ጥቂት የሆነ :; ፈልጥ የሌላቸው አላዋቆች መነኮሳትን ግን ሰይጣን መከራ ያመጣባቸው ዘንድ አይካሰስም :: በፍጹማን ሐዋርያት እንደ ተካሰሰ { ሉቃ ' 22. 31. } ክብር ይግባውና ጌታ እንዳያሰናብተው በጁ እንዳይጥላቸው ሰይጣን ያውቃልና :: ጥቂት መከራ ነው እንጂ ብዙ መከራ ለመቀበል እንዳልበቁ ያውቃልና :: ኃይለ እግዚአብሔር ርቆ ይጠብቃቸዋልና አንድም ባጠገባቸው ሆኖ ይጠብቃቸዋልና :: ይቆየን ደብረ ዲማ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ደብረ ዲማ

ኮትኳች


Joined: 17 Mar 2005
Posts: 275
Location: united states

PostPosted: Sat Dec 03, 2005 8:52 am    Post subject: ስለ እግዚአብሔር ብሎ መኖር መቻል :: Reply with quote

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ::

ሰላም ክርስቲያን ኦርቶዶክስ ወገኖቼ የእግዚአብሔር ሰላም ከሁላችን ይሁን አሜን ::

ከማር ይስሐቅ የተወሰደ መንፈሳዊ ምግብ ለነስፍ ::

በልቼ ጠጥቼ አይቼ ሰምቼ ንጽሕ ጠብቄ ከሴት እርቄ መኖር ይቻለኛል አትበል ::
ተፈትነህ ራስህን የማይለውጥ ሁኖ እስክታገኘው ድረስ በአርምሞ ኑር { በዝምታ }
ሰውነትህን እንዲህ ፈትነው : በሥራው ሁሉ የቀናች ሃይምኖትን ገንዘብ አድርግ :: አጋንንትን ድል ትነሳ ዘንድ :; ልቡናህ ዝንጉ አይሁን ተዘክሮተ እግዚአብሔርን አትተው ::በኔ ኃይል ሥራ እሠራለሁ አትበል :; የባሕርይህ ድካምነት እንደአንጋዳ ሁና አሰናክላ ጠልፋ እንዳትጥልህ ::አንጋዳ ሁና በጣለጭ ጊዜ ድካምህን ታውቀዋለህ :: አዋቂ ነኝ አትበል :: አዋቂነኝ በማለትህ ሰይጣን በትቢት እንዳይዝህ :: በምትናገርው ነገር ገራገር ሁን :: ሻካራ ነገር { ውሸት } ተናግረህ ተዋርዶ እንዳያገኝህ የለዘበ የለዘብ ነገር ተናገር አዋቂነኝ ጻድቅ ነኝ አትበል :: አዋቂ ጻድቅ ሳትሆን ቀርተህ አንዳታፍር :: ክብር ይግባውና እግዚአብሔር ሰውነቱ ያዋርድድ ዘንድ ሰው የሚመካበትን ሥራ በሚለውጠው ገንዘብ የሚለውጥበትን ሥራ ያመጣልና :: እግዚአብሔርም ሁሉ እንዲለውጥ አስቀድሞ አውቆታል :: ከዚህ ዓለም ያለ ሁሉ ማናቸውም አንድም የሥጋ ባሕርይ የማይለወጥ አይምሠልህ :: እንዲህ ያለ ነገር በማሰብ ኑር አንድም አስብ ::ሕሊናህ ክቡር ልኡል ወደሚሆን ወደእግዚአብሔር ስቀለው እንዲህ ያሉትን ሰዎች መላእክት ይጠብቆአቸዋልና :: ክብር ያለው እሱን ግን ከንጹሐን እሱን ከሚፈሩ ሰዎች በቀር አያዩትም :: መላእክት ፈጽመው ይገለጹላቸዋል :: ሰለ እግዚአብሔር ብለው የሚቀበሉትን ብዙ የሚያስፈራ መከራ ቢያመጹባቸው ባመጹባቸው ጊዜ ያን ጊዜ አንዱም አንዱ እያንዳንዱ እሱን እስከማየት ደርሰው ይረዱታል :: ፈጥኖ በሚሰጣቸው በማዕርጋት መጠን እግዚአብሔር መነኮሳትን በሥራ ለማነቃቃት ይህን ይሠራልና :: በኢዮብ እንደ ተደረገ '' ለኢያሱ እንደተደረገ ቅዱስ ሚካኤል በአጭር ታጥቆ ዘገር ነጥቆ በቀኝ በቀኙ ሲሄድ እምኔኑ [ አለው } ባንተአይደለም ጠላትህን ቁንጮውን ይዤ አጠፋዋለሁ ብሎታል :: ለሠለስቱ ደቂቅ የተደረገውን መልአከ ጠል ቅዱስ ገብሬል ወርዶላቸዋል :: ለጴጥሮስ የተደረገው ካሥራ ስድስት ዘበኛ ከሁለት ቁራኛ አድኖታል :: የልኡል እግዚአብሔር አገልጋዮች መላእክት በተገለጹላቸው በቅዱሳን እንደ ተደረገ :: በሰው አምሳል በታያቸው በጎ ሥራ ለመስራት ሊያጸኑአቸው :: ለእነዚአያ በልኡል እግዚአብሔር ቸርነት መላእክ ተገልጾላቸዋል :: መላእክትን ለማየት በቅተዋል ትለኝ እንደሆነ ይህ አብነት { ምልክት } ይሁንህ :: በብዙ ድካም ስለክርስቶስ ብለው መከራ በተቀበሉ ጊዜ በፈራሽ ሥጋ በመታሠር በመገረፍ ልዩ ልዩ መከራ ተቀበሉ ::ይህችውም የሰው ባህርይ የማይችላት ናት ይህችን የሥጋ መከራ ያለፈ { ንኡድ ክቡር ነው } ክብራን መላእክት ለእንደነዚህ ላሉ ሰዎች ተገለጹ :: መላእክት እንደጠበቆአቸው እንዱ አንዱም ያውቁ ዘንድ :: ለክርስቶስ ብለው መከራ የጠቀበሉ ሰዎች በፍጹም መከራ በጽዋትዎ መከራ በጎ ድል መንሳታቸው :: ቅዱሳን በመጠን እንደ መጠናቸው መላእክትን በማየት አጋንንትን ወስነው ገተው ባመጹባቸው መከራ ጸንተዋልና ከትግሥታቸው ብዛት የተነሳ አጋንንት እንደ ግሥላ ተቆጥተው ይኖሱባቸዋል :: ስለትግሥታቸውና ስለጽናታቸው ልኡል እግዚአብሔር ዋጋቸውን ከፈላቸው :: አሜን ::

ደብረ ዲማ ::መልካም የገና ጾም ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

 
Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum


Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia