WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ለዋርካ አስተዳዳሪዎች ማሳሰቢያ ::
Goto page 1, 2  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ግሸንማርያም

ኮትኳች

Joined: 15 Aug 2005
Posts: 349
Location: ethiopia

PostPosted: Fri Dec 02, 2005 3:53 am    Post subject: ለዋርካ አስተዳዳሪዎች ማሳሰቢያ :: Reply with quote

በስመ አብ በስመ ወልድ በስመ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ::

የተከራችሁ ዋርካዎች ለጠናችሁ እንድመን አላችሁ ?

ወደ መጣሁበት ቁም ነገር ሳልፍ እኔ እዚህ ዋርካ ላይ ግሸንማርያም የሚል የራሴን የብህር ስም አውጥቼ እግዚአብሔር ያቀበለኝን ቤተ ክርስትያኔ ከእኔ የምትጠብቀውን ትምህርት ለወገኖቼ ለክርስትያኖች ሳስተላልፍ ነበር ::

እኔ ግሸንማርያም የሚል የብህር ስም አውጥቼ ለብዙ ወራት በዋርካ ላይ ስሳተፍ ነበር :: ነገር ግን በዛሬው እለት Deceber 01 2005 ማለትም ዛሬ የኔን ስም ማለትም ግሸንማርያም የሚል ስም ለአንድ ሰው ተሰጥቶት ሰዎችን በእኔ ስም እያወናበደ ነው :: የእኔ ሐይማኖት ሐዋርያት ከክርስቶስ የተቀበሉት ሲሆን :: ዛሬ ግሸንማርያም ነኝ ጌታን ተቀበለ እያለ ሲናገር የነበረው ልጅ ደግሞ እርግጠኛ ባልሆንም የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ነው /ነች ስለዚህ በሁለታችን መካከል የሐይማኖ ልዩነት ስላለ ክርስትያኑን ሕዝብ በእኔ ስም በመጠቀም ከአሁን ቡሐላ እንዳያወናብድ ይታገድልኝ :: ምክንያቱም ያንን ስም እኔ ከብዙ ወራት በፊት አውጥቼው እስከ አሁን እየተጠቀምኩበት ነው ::

እንዴት ለአንድ ሰው ተመሳሳይ የሆነ የብህር ስም ይሰጣል ? ወይስ ይህ ሰው ከእናንተ ውስጥ አለ ? ይህንን ግልጽ አድርጉልኝ ::

በዋርካ ላይ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የራሱ የሆነ የብህር ስም አለው :: እኔም ግሸንማርያም የሚለውን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን የሚያስታውሰኝ ስም ቀድሜ ስላወጣሁ ልጁን እንድታግዱልኝና ::

በዋርካ ላይ የሚሳተፈውን የክርስትያን /ኦርቶዶክስ ሐይማኖት ተከታዮችን ይቅርታ እንድትጠይቁ በሐያሉ አማላክ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሳስባቹሀለው ::

ስለዚህ ነገሩ ወደ ትልቅ ችግር እንዳያመራ ልጁን አግዱልኝ ::

የእግዚአብሔር ቸርነት የእመቤታችን የንጽህይተ ንጹሀን የቅድስተ ቅዱሳን የድንግል ማርያም አማላጅነት የጻድቃን የሰማእታት ጸሎትና ምልጃ የቅዱሳን መላእክት ጥበቃና አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን :: ስራችሁንም ቅድስት ድንግል ማርያም ትባርክልኝ አሜን ::

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለ ወላዲቱ ድንግል ወለ መስቀሉ ክቡር ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
4get.this

ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Feb 2005
Posts: 1110
Location: escaped from nursing home

PostPosted: Fri Dec 02, 2005 2:58 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ::

አንድ አይነት ስም መሆን እንደማይችል ሁላችንም የምናውቅ ይመስለኛል :: ግን የዚያ ስም ባለቤት ፎንቱ ላይ ያለውን የፊደላት መመሳሰል በመጠቀም : ግሽንማርያም ( (1) ሳይሆን (6)) በመጠቀም ነው ስም ያወጡት ::

እርሱን የሚከለክል ደንብም ሆነ ሌላ ነገር ያለ ባይመስለኝም : እስካሁን የምታውቁኝ እገሌ ነኝ ብሎ ሌላ ሰውን impersonate ማድረግ ግን በኢንተርኔትም ሆነ በዋርካ ተቀባይነት ያለው አይመስለኝም ::

ስሙን እነርሱ እንዳልሰጡት አሁን እርግጠኛ ሆነን መናገር እንችላለን አይደል Smile
_________________
ተመለስኩ ማለት ነው? Confused
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዘርዐይ ደረስ

ውሃ አጠጪ

Joined: 23 Oct 2004
Posts: 1087
Location: ethiopia

PostPosted: Fri Dec 02, 2005 3:45 pm    Post subject: Reply with quote

4get.this ባለው ላይ ለመጨመር ያህል :-

ይህ የብዕር ሥምን አስመስሎ የመጠቀም ጉዳይ በተለይ ዋርካ ፖለቲካ ላይ የተለመደ ነው ::ለምሳሌም ወዲ ሰባርጉማ ወዲ ሰበርጉማ አጋሜው አጋሜዉ ቃኘው ቃኝው ወዘተ ::አንተ ምናልባት እዚህ ዋርካ ላይ ኃይማኖት ነክ ከሆኑ ውይይቶች ውጭ በሌሎች ርዕሶች ላይ ስለማትወያይ ይሆናል አዲስ የሆነብህ ::እናም ላንባቢዎችህ ግሸን ማርያም የሚለውን ሥም ሲያዩ ዋርካ ላይ የተመዘገብክበትንም ቀን እንዲያመሳክሩ ማሳሰብ ጠቃሚ ይመስለኛል ::ምክንያቱም ያንተን ወይም የሌላን ሰው የብዕር ሥም አስመስሎ የሚጠቀም ሰው ቀኑን መቀየር አይችልምና ነው ::የቀረውን 4get.this ብሎታል :.የዋርካ አድሚኖች ፍላጎትህን ሊያሟሉ የሚችሉ አይመስለኝም ::

4get.this:-
በእንግሊዝኛ (በላቲን ) ፊደል ግን የሌላውን የብዕር ሥም እንዳለ መጠቀም ይቻላል አይደል ?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
ኣክሱምማርያም

አዲስ

Joined: 02 Dec 2005
Posts: 17

PostPosted: Fri Dec 02, 2005 4:00 pm    Post subject: Reply with quote

ምን ተነካና አለች አሉ ሴትዮዋ ::ምን ግሽንማሪያም ብቻ እነም ወደጴንጤነት ተቀይራለሁ ::ይመስገነው ነው ::ዛሬ ቀኑን ሙሉ ከግሽንማርያም ጋር ስንወያይና ሲያስተምረኝ ነበር ::እያንዳንዳችሁ የሚያዋጣችሁን ለማወቅ መፈለግ እንጂ ለኦርቶዶክስ ቀንቼ ወይም ከሌሎች ስለተጣላችሁ መንግስተ ሰማየት እንደማትገቡ እወቁ ::እንግዲህ ኢየሱስን ሲገድሉ ድሙ በኛና በልጆቻችን ይሁን እንዳሉት ነው ::ጌታ እራሱ ፍቅር አይደል ?
ሁላችሁም እውነቱን አንድ ቀን ታውቃላችሁ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጌታ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Apr 2005
Posts: 3350
Location: ዶሮ ተራ

PostPosted: Fri Dec 02, 2005 5:05 pm    Post subject: ለግሽንማርያምና ለአክሱምማርያም Reply with quote

በኔ አመለካከት ሁሉም የክርስትና ሃይማኖት ዘርፎች ከአተረጓጎም ጋር በተያያዙ ጥቃቅን ነገሮች ይለያዩ እንጂ መሠረታዊ በሆኑት እንደመጽሃፍ ቅዱስ ; ክርስቶስና አስርቱ ትዕዛዛት ላይ የጋራ አቋም አላቸው ::

በሌሎችም እምነት ብንሄድ አትዋሽና አትስረቅ ቋሚ ሕጎች ናቸው :: ሃይማኖት በሌላቸው ሰዎች ደግሞ የሞራል ወይም የወንጀል ሕግጋት እንዲያከብሯቸው ያስገድዷቸዋል ::

አሁን እናንተ (አንተ ) ዋሽቼና ቀጥፌ ሰዎችን ወደ ጴንጤነት እመልሳለሁ ብትል እግዚአብሄርም አይወደውም :: በእምነት ተከታዮች ዘንድ ከሄድክ ደግሞ ኦርቶዶክሶችን ብቻ ሳይሆን ጴንጤዎችንም እያስቀየምክ ነው :: ሃይማኖት የለሽ ከሆንክም ኅሊናህን ተጠቀም ::

ጽድቅና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም
ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም

ብሏል ያገሬ ጠቢብ ::

ሰውን ወደራስ ለመሳብ ጥሩ እየሰሩ በማሳየት እንጂ እየዋሹ አይደለም ::

ግሸን ማርያምና አክሱም ማርያም ደግሞ በተገኘው አጋጣሚ አንባቢን ሁኔታውን ለማሳወቅ ሞክሩ እንጂ አትበሳጩ :: ነገሩን እንደ አንድ ፈተና ቁጠሩት :: በያዛችሁት እምነት በርቱ :: ሁሌም እውነትንና ጥበብን ከመሻት አትቦዝኑ ::
_________________
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
ደጉ

ዋና አለቃ

Joined: 15 Dec 2003
Posts: 5233
Location: afghanistan

PostPosted: Fri Dec 02, 2005 6:07 pm    Post subject: ግሽንማርያም Reply with quote

.... ከላይ ስለመለሱልህ ብዙ እምለው አይኖርም ..ይሄ ዛሬ አንተ ላይ ብቻ የተከሰተ አይደለም .... ነገር ግን ዋርካ የዋርካ አዲምኖች ምንም ማድረግ አይችሉም ማለት አይቻልም ...በተመሳሳይ ስም መጻፉ ብቻ ሳይሆን ጥፋቱ በአንተ ስም ያልሆንከውን ሆነ ብሎ በማወናበዱ የዋርካ አድሚኖች ስሙን ሊያግዱ ይገባል ባይ ነኝ :: እኔ ነገሩን "" እና "" ብቻ ልዩነት ብቻ አላየውም .... ሌላው ግን የጴንጤ ህይማኖት ተከታዮች ምን ያህል አጭበርባሪዎች እንደሆኑ ከዚህ መረዳት ይቻላል ....ቢመቻቸው መግደል ሳይጀምሩ ይቀራል ...?? ለመሆኑ የትኛው ምእራፍ ነው አታላችሁ አሳምኑ እሚለው ...?? ለሁሉም ወንድማችን በግል ልከህላቸው ስሙን እንዲያግዱልህ ጠይቅ ...ብዙ ሰው የተመዘገበበትን ቀን ሳይሆን ስም ብቻ ነው እሚያየው ... አንተ ግን በዚች ትንሽ ጉዳይ ማድረግ ከምትችለው አትታቀብ ::

ከሰላምታ ጋር Smile
_________________
" STUPID IS AS STUPID DOES " Very Happy
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
አፈ -ጉባኤ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Mar 2005
Posts: 566
Location: united states

PostPosted: Sat Dec 03, 2005 6:40 am    Post subject: የማነህ ደፋር ? Reply with quote

በነጻ መስተናገድህ ሳያንስ ባለቤቶቹ ይቅርታ እንዲጠይቁህም ያምርሀል ? ገንዘባቸውን ከፍለው በፍርድ ቤት የባለቤትነት ስም እሚያወጡም እንዲህ እንዳንተ ተኩራርተው አይናገሩም ::

እርግጥ አስመሳዩ ስማቸውን በየሳምንቱ እንደሚቀያይሩት የወያኔ ጸሀፍት ባይሆንና በራሱ ተማምኖ ቢመጣ መልካም ነበር :: ማመሳሰል ግን መብቱ ነው ::

ልብ ብላችሁ ከሆነ በፓለቲካው አምድ (ጥቂት ወያንያንን ሳይጨምር ) ብዙ መከባበር መደማመጥና መተማመን አለ :: በሀይማኖቱ መድረክ ግን ይህ አይታይም ሁሌም መናከስ መናቆር መደናቆር ብቻ ነው ::

ለኔ ሁለታችሁም ስልቻ ቀልቀሎ ቀልቀሎ ስልቻ ናችሁ :: ሁለትና ሁለት ስድስት ነው ሰባት ነው ብላችሁ ዝንተአለም እምትሟገቱ :: ማነህ ግሸንማርያም ደርሰህ አካኪ ዘራፍ አትበል ያለመብትህ ::

ከወገናዊ ሰላምታ ጋር
አፈ -ጉባኤ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
4get.this

ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Feb 2005
Posts: 1110
Location: escaped from nursing home

PostPosted: Sat Dec 03, 2005 11:47 am    Post subject: Reply with quote

ዘርዐይ ደረስ እንደጻፈ(ች)ው:
የቀረውን 4get.this ብሎታል :.የዋርካ አድሚኖች ፍላጎትህን ሊያሟሉ የሚችሉ አይመስለኝም ::

የዋርካ አድሚኖች ምንም ማድረግ አይችሉም ማለቴ አልነበረም :: በርግጥ ሁሌ እዛጋ ቁጭ ብለው የቱ ስም ተመሳሳይ አለው : የቱ የለውም እንዲሉ መጠበቅ ያለብን አይመስለኝም :: እንዲሁም : በመደበኛው : ተመሳሳይ ስሞች መከልከል አለባቸው ብዬ አላምንም :: እንዲህ አይነቱ : ሆን ተብሎ የሌሎችን ማንነት ለመቀማት የሚደረግ ጥረት ግን የሆነ እርምጃ የሚፈልግ ይመስለኛል ::
Quote:
4get.this:-
በእንግሊዝኛ (በላቲን ) ፊደል ግን የሌላውን የብዕር ሥም እንዳለ መጠቀም ይቻላል አይደል ?
በሌላ አነጋገር : 4get.thisንም ሆነ debzi ሌሎች ሰዎች እንዳሉ ሊመዘገቡባቸው ይችላሉ ወይ ማለትህ ከሆነ : መልሱ አይመስለኝም ! ምናልባት ደግሞ አማርኛው ላይ ያልኩት ግልጽ ካልሆነ ... አንዱ (ግእዝ ) ሌላው ( ሳድስ ) ነው የሚጠቀሙት :: እንዲሁ ስናያቸው ግን ልዩነቱን ማግኘት ቀላል አይደለም :: ያንን ማለቴ ነበር :: (የፎንት መጠን በማሳደግ መሞከር ይቻላል )
ከሰላምታ ጋር
_________________
ተመለስኩ ማለት ነው? Confused
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ግሽንማርያም

አዲስ

Joined: 02 Dec 2005
Posts: 26

PostPosted: Sat Dec 03, 2005 1:40 pm    Post subject: Reply with quote

4get.this
Quote:
እንዲህ አይነቱ : ሆን ተብሎ የሌሎችን ማንነት ለመቀማት የሚደረግ ጥረት ግን የሆነ እርምጃ የሚፈልግ ይመስለኛል ::

ኦርቶዶክስ መሆንህን በጣም በመቆርቆር በዚህ አርእስት በመመላለስ አሳውቅሀን ::እባክህን አዲስ ህግ አስወጣ ::አዲሱ ህግ ጴንጤዎች እዚህ ውይይት ክፍል እንዳይገቡ የሚያደርግ ቢሆን ሳይሻል የሚቀር አይመስለኝምና እንግዲህ ልታስወስድ ያስብከው እርምጃ በደንብ ተግባራዊ እንዲሆን የተቻለህን ሁሉ አድርግ ::
ፍርደ ገምድል ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዘላለማዊ

ዋና ኮትኳች

Joined: 16 Aug 2004
Posts: 680
Location: ethiopia

PostPosted: Sat Dec 03, 2005 8:08 pm    Post subject: የብዕር ስም መመሳሰል Reply with quote

ሰላም የተከበራችሁ የሳይበር ኢትዮጵያ አስተዳዳሪዎች :: የዋርካ ፎረም መከፈቱን ከሚያደንቁት መካከል ልመደብ እችላለሁ :: ለኃይማኖት ቦታ ስለተገኘ ሳይሆን በአጠቃላይ ኢትዮጵያውያን አሳባቸውን (አርቱቡርቲም ይሁን ; ቁምነገር ) መካፈል በመቻላቸው ::

በብዕር ስም ላይ ያላችሁን ሕግ አላውቅም ; ሆኖም ይህ ተቀራራቢ በሆነ የብዕር ስም የመመሳሰል ወይም የማጭበርበር ባህርይ ያላቸውን ሰዎች ማስቆም የሚቻልበት መንገድ ሊኖራችሁ ይገባል ባይ ነኝ :: በአንድ ወቅት ትንሽ የዳታቤዝ አድሚኒስትሬተርነትን ስለሞከርኩ የተጠቃሚዎችን ስም በተመለከተ ስርዐት ማበጀት እንደሚቻል አውቃለሁ :: ይህ በእርግጥ ተጨማሪ ስራ ነው የሚሆንባችሁ :: ሆኖም እናንተ እራሳችሁ በየእለቱ ይህን ባትከታተሉ ከተጠቃሚዎች የሚቀርብን አቤቱታ ወስዳችሁ እርምጃ ልትወስዱ የሚገባ ይመስለኛል ::

ነገር ግን ያለባችሁን የስራ ጫና ሳስበው ይህ በጣም ትንሽ ችግር ሊሆን ይችላል ::

ሠላም ይብዛላችሁ
_________________
በነፍስህ ለቍጣ ችኩል አትሁን ቍጣ በሰነፍ ብብት ያርፋልና
መጽሐፈ መክብብ 7፡9
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ቤንይሁዳ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 23 Apr 2005
Posts: 93
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Dec 05, 2005 12:26 am    Post subject: ለግሽንማርያም Reply with quote

ምክር በዓለማችን ብዙማረያሞች አሉ : በጣም የምትታወቀዋ
የፈረንሳይ አገሯ ሉርድ ማርያም ስትሆን
ሁለተኛዋ የፖርቱጋሏ ፋጢማ ማርያም ናት
ከዚያም ፍሪምናጦስ የተከላት ጽዮን ማርያም ናት
ቀጥሎም ያንተው ግሽን 1 ቀንቀን ግሽን 2 ማታማታ
እያደረግህ ተረትህን መወተል ትችላለህ በቅርቡ ንስሀ ገብተህ
ካልተመለስክ በቀመስክ ቁጥር 33 ቱን የማሪያም ምስል በፊትህ ይደቀናል ስለዚህ መዳን ዛሪ ነው !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አክሱምማርያም

ኮትኳች

Joined: 13 Sep 2005
Posts: 357
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Dec 05, 2005 1:08 am    Post subject: Reply with quote

እኛ ስለብዙ ማርያሞች ምን አገባን ??? የእግዚአብሄር እናትን ቅድስት ድንግል ማርያምንስ ታውቃታለህ ??? ዲያብሎስ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
4get.this

ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Feb 2005
Posts: 1110
Location: escaped from nursing home

PostPosted: Mon Dec 05, 2005 8:42 pm    Post subject: ይህም ቀናዊነት መሆኑ ነው ? Reply with quote

አክሱምማርያም እንደጻፈ(ች)ው:
እኛ ስለብዙ ማርያሞች ምን አገባን ??? የእግዚአብሄር እናትን ቅድስት ድንግል ማርያምንስ ታውቃታለህ ??? ዲያብሎስ

ሰላም በድጋሚ !

ይህ የመጨረሻው ቃል ትክረቴን ሳበውና ሌላ ነገር ከማለቴ በፊት እንዴት እዚህጋ ሊገባ እንደቻለ ለማብራራት እድሉን ብሰጥዎ ብዬ ነው ::
-----------
@2ኛው ግሽን ማርያም ... አይቸዋለሁ ... መልስ የማያሻው ሆኖብኝ ነው የዘለልኩት :: ለማን መልስ እንደሰጠሁ በጣም ግልጽ ነበረ እና !
_________________
ተመለስኩ ማለት ነው? Confused
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አክሱምማርያም

ኮትኳች

Joined: 13 Sep 2005
Posts: 357
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Dec 05, 2005 10:45 pm    Post subject: Reply with quote

4get.this ሰላም እንደምን አለህ ወገን ? ከላይ quote ያደረግከውን ቃል የጻፍኩት እኔ ነኝ የጻፍኩበትም ምክንያት ከኔ በላይ ከፍ ብሎ ያለው ሰው የጻፈው ጽሁፍ offensive ሆኖ ስላገኘሁት ምላሽ መሆኑ ነው :: ነገር ግን ስለ ግሸንማርያም የጻፍከው ምንም ግልጽ ስላልሆነልኝ ግልጽ ብታደርግልኝ ደስ ይለኛል :: ከአክብሮት ጋር
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
4get.this

ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Feb 2005
Posts: 1110
Location: escaped from nursing home

PostPosted: Tue Dec 06, 2005 6:31 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም በድጋሚ

ያንኛው አጋጣሚውን በመጠቀም 2ኛው (_) ማርያም የተጻፈ ነው :: ግልጽ ካልነበረ ይቅርታ ::

ጸሐፊውን እኔም offensive ሆኖ አግኝቼዋለሁ :: እንደውም ሆን ተብሎ የተደረገ በመሆኑ ያናድዳል :: ያም ሆኖ እንዲህ አይነቱ መልስ አንተኑ የሚያስገምት ነው የሚሆነው :: አንድ አባባል አስታወሰኝ ... አህያ ስትረግጠው መልሶ የሚረግጣት ነው መሰለኝ የሚለው :: አግባብ ያለው ተግሳጽም ሆኖ ስላልታየኝ ነው :: ከተሳሳትኩ ይቅርታ
በተረፈ ያንተንም ሆነ የሌሎችን ትምህርት እና ቀናኢነት አድናቂ ነኝ ::
_________________
ተመለስኩ ማለት ነው? Confused
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Goto page 1, 2  Next
Page 1 of 2

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia