WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ለሚታረዱት የአርሲ ክርስቲያኖች እስኪ ግድ ይበለን !

 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General


 
View previous topic :: View next topic  
Author Message
ዲጎኔ

ዋና አለቃ


Joined: 19 Aug 2005
Posts: 4208
Location: united states

PostPosted: Mon Dec 12, 2005 7:20 pm    Post subject: ለሚታረዱት የአርሲ ክርስቲያኖች እስኪ ግድ ይበለን ! Reply with quote

በስመአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም አንድ አምላክ

ወገኖቼ አሁን በትክክል እንደሚታየው የኢትዮጵያዊያን ሁሉ ልሳን የሆነችው መማማሪያችን ዋርካ በወያኔ መሰሪዎች ተወርራ አላስፈላጊ የሀይማኖት ንትርክ ሲካሄድ ወገኖቻችን ግን በቆሬ አርሲ እንደበሬ እየታረዱ ቤታቸው እየተቃጠለ መሰደዳቸው ቀጥሏል ::
ባለፉት ሳምንታታ የቆሬ አርሲ ካህን ቄስ አበበ ፈንቴ ያቀረቡልንን የድረሱልን ጩህትና የጸሎት ጥያቄ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለን ወይም እያዘናጋን ዛሬ በሀገራችን የተከሰተውን

የፖለቲካና የሀይማኖት ሰቆቃ ችላ ብንል በእግዚአብሄርና በታሪክ የምንጠየቅ እንሆናለን ::
ጌታ እራሱ መንጋውም አንድ እረኛውም አንድ ነው ያለን ክርስቲያኖች እንዴት እንደዚህ በከንቱ እየተባላን መከራ የበዛባቸው የወገኖቻችንን ድምጽ ማስተጋባት ያለመቻላችን የሚያሳፍርሲሆን ለመሰሪዎቹ የወያኔ ደጋፊዎች ደግሞ ነገ በነጻ ፍርድ ቤት የሚያስጠይቃቸው ነው ::

የለሎቹ ሀገሮች ክርስቲያኖች ሲታረዱ የሚጮሁ ተሟጋቾች ሁሉ እንደፖለቲካው የሀገራችን ክርስቲያኖችን መታረድና መሰደድ ችላ ማለታቸው እድሉ ያለን የእኛ ስንፍና ነው ::

ስለዚህ ከፊሉ ቤተሰባቸው ታርዶ የተቀሩት ደግሞ የተሰደዱ ወገኖቻችን እረኛችን ክርስቶስ አንድ ነውና እናስባቸው ለምናውቀው ተቕም ሁሉ እናስረዳላቸው ::


Last edited by ዲጎኔ on Mon Dec 12, 2005 11:43 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ድራኮላ 7

ኮትኳች


Joined: 25 May 2005
Posts: 116
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Dec 12, 2005 8:27 pm    Post subject: Reply with quote

ጅሀድ እያወጅክ ነው !!! ያለው ሰቆቃ አይበቃምና ሌላ ክብሪት ትለኩሳለህ ሠላሙን ያውርድ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዲጎኔ

ዋና አለቃ


Joined: 19 Aug 2005
Posts: 4208
Location: united states

PostPosted: Mon Dec 12, 2005 11:38 pm    Post subject: ምነው ድራኮላ ድረሱልን ማስተጋባቴን አጣመምክብኝ ? Reply with quote

ምነው ደራኩላዬ

የትነው ግደሉና ጃነት /ገነት ትገባላችሁ ያሰፈርኩት ?እኔ ተጠንቅቄ ክርስቲያኖቹን ያረዱት አክራሪ ሙስሊሞች መሆናቸውን ያልጠቀስኩት ግጭቱን ላለማባባስ ነበር ::
ግድያውን የፈጸሙት የአንተ አለቃ አሽከሮች እነጁነዲን ሳዶ " ቅንጅት የክርስቲያን ፓርቲ ነው " ብለው የፖለቲካ ኪሳራቸውን በህዝብ መተላለቅ የተኩት ናቸው :: እነርሱና መሪያቸው አስረስ ዜናዊ 3 ሚሊዮን ህዝብ በሰላም ተሰልፎ ቤቱ በገባበት ምሽት አላስፈላጊ አስቸኩዋይ ጊዜ አዋጅ አውጆ የህዝብ እልቂት ላደረሱት የሚጠየቁበት ሩቅ አይደለም ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጃንተከልዋርካ

አዲስ


Joined: 12 Dec 2005
Posts: 28

PostPosted: Thu Dec 15, 2005 12:13 pm    Post subject: Reply with quote

ይህች ክርስቴያንን የማረድ ጉዳይ ወደ ፋሲል ቤት መጥታ ቢሆን 44 ልጆች ጉድ ያፈሉ ነበር
_________________
I always love u S
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሙስሊም

አዲስ


Joined: 20 May 2004
Posts: 24
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Dec 15, 2005 10:21 pm    Post subject: በአርሲ የክርስቲያኖች መጨፍጨፍ ... Reply with quote

በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ እና እጅግ በጣም ርህሩህ በሆነው


በአርሲ የክርስቲያኖች መጨፍጨፍ እና የአንድ ካህን ተማጽኖ” በሚል የጀርመን ሬድዮ የአማርኛው ክፍል ያስተላለፈውን ዘገባ በማስመልከት የቀረበ ጥሪ

ለአንድ ባለታሪክ ህዝብ ከብሄራዊ ችግር የባሰ ሊያሳዝነው፣ ሊያስጨንቀውና ሊያስቆጨው የሚችል ነገር አይኖርም። በአሁኑ ወቅት አገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ ችግሮች ተወጥራ ትገኛለች። ይህም ሁኔታ በተለይ ከግንቦት 15 1997 ምርጫ በኋላ ተባብሶ እና ተወሳስቦ ይገኛል። ታድያ ማንኛዉም ችግር በሰላማዊ ዉይይትና በድሞክራሲያዊ የአሰራር ሂደት መፍትሔ እንዲያገኝ አስካልተደረገ ድረስ ህዝቦች በእርስ በርስ ጦርነት ዉስጥ ሊዘፈቁ ብሎም ሀገሪቱን የማፈራረስ አደጋም ሊያስከትል እንደሚችል መታወቅ ይኖርበታል። እንደዚህ በመሳሳሰሉ ችግሮች ዙሪያ፤ ለእኛ ኢትዮጵያን የመቻቻል አስፋላጊነትን፤ እንደዚሁም በአሉባልታ ላይ የተሞረከዙ ዉንጀላዎችን በተመለከተ ኔትወርካችን በተለያዩ አጋጣሚዎችና መድረኮች ያለዉን አቋም ሲገልጽ ቆይቷል።

ዛሬም በኅዳር 7 እና 8 1998 (እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ) በአርሲ “በአርሲ የክርስቲያኖች መጨፍጨፍ እና የአንድ ካህን ተማጽኖ” በሚል በኖቭምበር 27/29 ዝግጅቱ የጀርመን ሬድዮ የአማርኛው ከፍል ያስተላለፈውን ዝግጅት በማስመልከት ለህብረተሰባችን እንደዚሁም ይመለከታቸዋል ብለን ላመንባቸው ክፍሎች ከታች የቀረበዉን ጥሪ ለማቅረብ ተገደናል። ለዚህም ያነሳሳን በእዉነት ላይ የተመሰረተ ሚዛናዊ መረጃ እና የመረጃ አሰጣጥ ለአገራችንና ለወገኖቻችን ሰላምና መረጋጋት ብሎም እድገትና ብልጽግና መሠረት ነው የሚል ፅኑ እምነታችን ነው። እንኳንስ 80 በላይ የሚሆኑ ብሄር እና ብሄረሰቦች ለሚኖሩባት፣ ያንኑ ያክል ቋንቋዎች ለሚነገሩባት እና የተለያዩ እምነቶች ለሚተገበሩባት አገራችን ይቅር እና የአንድ ዘር ያላቸው፣ አንድ ቋንቋ ለሚናገሩ እና አንድ እምነት ለሚከተሉ ህዝቦችም አንኳ እውነታ የጎደለዉም ሆነ ሚዛናዊነትን ያልጠበቀ ዘገባ እና የዘገባ አቀራረብ ሊያስከትል የሚችለዉ መዘዝ ቀላል አይሆንም። እኛም በጀርመን ድምፅ የአማርኛው ክፍል የተላለፈውን ዘገባ ካዳመጥን እና ካነበብን በሁዋላ ባደረግነው ክትትል ተከሰተ የተባለዉ ጉዳይ ከሞላ ጎደል እዉነታነት ያለዉ ቢሆንም በዘገባው ላይ “የሀይማኖት ልዪነት” እንደመነሻ ተደርጎ መቅረቡና “ታጣቂ ሙስሊሞች ክርስቲያኖችን ጨፈጨፉ” መባሉ ከእዉነታው በእጅጉ የራቀ፣ በአቀራረቡ ደግሞ ሚዛናዊነት የጎደለው፣ ይልቁንም የአቅራቢዉ ወገንተኝነት ጎልቶ የታየበት ሆኖ አገኝተነዋል። ከምንም በላይ ያሳዘነን ነገር ቢኖር በህዝቦች መካከል ብጥብጥ እና ጥላቻን የሚያነግስ ዘገባ ሲቀርብ ድርጊቱን ፈፀሙ ከተባሉትና ዉንጀላና ወቀሳም ከቀረበባቸው ከሙስሊሙ ህብረተሰብ በኩል ክስተቱን እና መነሻዉንም ለማጣራት ምንም አይነት ጥረት አለመደረጉ ነው። በተለያዪ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ችግሮች መሰቃየቱ አልበቃ ብሎ ይህ አይነቱ ዘገባ እና የዘገባ አቀራረብ ልንወጣው ወደማንችለው ማጥ ሊዘፍቀን ይችላል የሚል ፍርሀት ስላደረብን ጥሪዉን ለማድረግ እንገደዳለን። ለዚህም፦

. ኢትዮጵያ ሀገራችን የመጀመሪያ የሙስሊም ስደተኞችን ያስተናገደች፣ በቀያቸዉ እና በህብረተሰባቸው ዉስጥ የእምነት ነፃነት አጥተው ከለላ ለፈለጉ ሙስሊሞች በሯን ከፍታ ተቀብላ ያስተናገደች፣ ለእስልምናም እዉቅና በመስጠት እና በመቀበል በዓለም የመጀመሪያ ሀገር መሆኗን ስናስታዉስ፤ የዚያኑ ያክል ሀይማኖቱም ሆነ አማኞቹ አሁን ካሉበት ወቅት ለመድረስ የበቁት ከብዙ የመከራና የስቃይ ዘመናት፤ የዜግነት እዉቅናን እስከማጣት የደረሱ የአስተዳደር በደልና ግፎችን በማሳለፍ እንደሆነ፤ በሌላ በኩል የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ራሷን ከገዥዎች ጋር በቀጥታ በማቆራኘቷ ችግሩ ሀይማኖታዊ ገጽታ የተላበሰ መሆኑ ሳይካድ፤

በወራሪ አፄዎች በሙስሊሞችና ከኦርቶዶክስ ክርስትና ዉጭ ባሉ የሌሎች እምነት ተከታይ የሆኑ ኢትዮጵያን ላይ የደረሰው ስቃይና መከራ፣ ይህም ያስከተለውን የተዛባ የህዝቦች የታሪክ ዘገባ እና ግንኙነቶችን ከግምት በማስገባት፤

በሌላ ወገን የክርስቲያኑና የሙስሊሙ እንደዚሁም ከእነዚህ ሁለት እምነቶች ዉጭ ያሉ ሕዝቦች በአንፃራዊ ስምምነቶች ሰላም ኖሯቸው በዚቹ ኢትዮጵያችን ጎን ለጎን ለብዙ ምዕተ -አመታት እንደኖሩ በማስታዎስ፣

የሚከተሉትን ጥሪዎች ለመንግስት፣ ለእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ /ቤትና ለሙስሊሙ ህብረተሰብ ተወካዮች፣ ለቤተ -ክህነት፣ ለመገናኛ ብዙሃን እና ለጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ እናቀርባለን።


1. ለኢትዮጵያ መንግስት

አሁን ተከሰተ ተብሎ የቀረበዉ አይነት ክስተት በተለያዩ ቦታዎች የተከሰተ ወደፊትም በማንኛዉም ቦታና ጊዜ ሊከሰት የሚችል ሲሆን፤ የተለያዩ ቡድኖችም ሁኔታዉን ከእዉነታዉ በመነጠል ለራሳቸው አኩይ አላማ ሊያዉሉት ሲሞክሩ ታዝበናል። ይህም በህብረተስባችን ዉስጥ አላስፈላጊን ዉጥረትና የግንኙነት መሻከር ያስከተለበት ሁኔታንም አይተናል። ስለዚህ እንደዚህ አይነቱን መጥፎ ሂደት መታደግ ይቻል ዘንድ፦ መንግስት ከተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት፤ የሀገሪቱ ጎሳዎችና ወኪሎች የተዉጣጣ ሁሉን አቀፍና ከመንግስትም ገለልተኛ የሆነ ሕጋዊ አካል እንዲያቋቁም፤ ይህም አካል ችግሮችን ከመከሰታቸዉ በፊት እንዲቀርፍና ከተከሰቱም የመነሻ ምክኒያታቸዉን በማጣራት ለህብረተሰቡ ትክክለኛውን መረጃ እንዲያቀርብ፣ ለመሰል ክስተቶችም ዘላቂ መፍትሔ ያመነጭ ዘንድ ማንኛንም አይነት እገዛ እንዲደረግለት፤


2. ለእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ /ቤት እና ለሙስሊሙ ህብረተሰብ ተወካዮች

እስልምና በሰላም፤ በመቻቻል እና በመከባበር አብሮ መኖር የሚያስችል ሙሉ የህይወት መመሪያ ነው። ሙስሊሞችና የሌላ ዕምነት ተከታዮች ጎን ለጎን በሚኖሩባት ሀገራችን ይህ በመቻቻል አብሮ የመኖር ዘይቤ ለኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች አዲስና አስቸጋሪ የሆነ ነገር አንዳልሆነ ግልፅ ነው። ሆኖም ግን ዕለታዊ ግጭቶችንም ሆነ በታሪክ ከደረሰው በደል የተነሳ ለሚከሰቱ ችግሮች አስቀድሞ ዘላቂነት ያለው መፍትሄ ለመስጠት ይቻል ዘንድ ሙስሊሙ ህብረሰብ ተከታታይ እና ቋሚ የሆነ ትምህርት እንደዚሁም እገዛ ሊደረግለት ይገባል። ለዚህም ገቢራዊነት መጂሊሱ እና ሌሎችም በዳዕዋ ስራ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች ህብረተሰቡ በራሱ ዉስጥም ይሁን ከሌሎች ጋር ሊያጋጥሙት የሚችሉ ችግሮችና አለመግባባቶችን በዉይይት ይፈታ ዘንድ አስፈላጊዉን ስልት በመንደፍ እንዲንቀሳቀሱ፣ ይህንም ለማህበረሰቡ እንዲያስተምሩ፤ ያለአግባብ በአሉባልታ እና በቂም በቀል የሚወሰድ ማንኛዉም አይነት እርምጃ ከእስልምና አስተምህሮት በእጅጉ የራቀ መሆኑን እንዲያስገነዝቡ፤


3. ለቤተ -ከህነት

በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል ለሚታየዉ የዘርም ሆነ የሀይማኖት አለመግባባት ህዝቦች ካለፉበት የጭቆናና የስቃይ ዘመን ጋር በቀጥታ ተያያዥነት አለዉ ብለን እናምናለን። ይህም ሀይማኖታዊ ገፅታ ሊኖረው እንደሚችል ከላይ ጠቆም አድርገን ለማለፍ ሞከርናል። የነበረ ቁስል ይድን እና ህዝቦች በውስጣቸው መተማመን ኖሯቸው በመካከላቸዉ የሚከሰቱ ችግሮችን አስቀድመዉ ራሳቸዉ ማስወገድ ይችሉ ዘንድ ቤተ -ክህነት የራሷን አስተዋፆኦ ማድረግ ይገባታል። ለዚህም ገቢራዊነት ቤተ -ክህነት የአብዛኛዉ ችግር መነሻ ለሆነው ታሪካዊ ክስተት አካል የነበረች መሆኗን ማመን ቅድሚያ ሁኔታ በመሆኑ፣ ይህንኑ በግልጽ ተቀብላ ለአገርና ለወገን ሰላምና ደህንነት ስትል አስፈላጊዉን እርምጃ እንድትወስድ፣ የበኩሏንም ጥረት እንዲታደርግ፤


4. ለመገናኛ ብዙሃን

ለአንድ አገርና ህዝብ ሰላምና መረጋጋት ብሎም እድገትና ብልጽግና የመገናኛ ብዙሃን የሚጫወቱት ሚና ይህ ነው ተብሎ የሚገለፅ አይሆንም። ታድያ ይህ የሚሆነው የሚያቀርቧቸው ዘገባዎች እውነታን የተሞረከዙና ሚዛናዊነትን የተላበሱ ሲሆኑ በተለይም የህዝቦችን ሰላም እና አብሮ መኖርን የማይረብሹ ከሆነ ብቻ ነው። ይህ ካልሆነ ግን ዉጤቱ ከላይ የተጠቀሰው ተቃራኒ እንደሚሆን አጠያያቂ አይደለም።ስለዚህ በኢትዮጵያ ጉዳይ የሚዘግቡ ሚድያዎች ሁሉ በአሉባልታ ላይ የተመሰረቱ ዘገባዎችን እንዳያቀርቡና ሚዛናዊነትን እንዲጠብቁ፡ ለአንዱ የአናት ልጅ ለሌላው ደግም የአንጀራ እናት ሆነዉ ከመቅረብ እንዲቆጠቡ፤ ለአድማጭ ምን አዲስ ነገር ይዘን እንቅረብ ከሚለው ጥረታቸው ጎን ለጎን ይዘው የሚቀርቡት ዘገባ በህብረተሰባቸው መካከል ምን ተፅዕኖ ሊኖረው እንደሚችል አስቀድመው እንዲገመግሙ፤


5. ለመላዉ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ

አገራችን ኢትዮጵያ ዛሬ ካለችበት ዉስብስብ ችግር ልትወጣ የምትችለው በህዝቦቿ ትብብር አንደዚሁም በመካከላቸው በመከባበር እና በመግባባት ላይ የተመሰረተ ሰላም ሲኖር ብቻ ነው። አገራችን የተለያዩ ባህሎች ወጎች አና ልማዶች ያሏቸው ብዙ ህዝቦችና ማህበረሰቦች መኖሪያ፤ የተለያዩ እምነቶችም የሚተገበሩባት አገር እንደመሆኗ መጠን እነዚህ የተለያዩ ህዝቦችና ማህበረሰቦች በታሪካችን ደረሱብን የሚሏቸው ብሶቶች አሏቸው። በተቃራኒው ደግሞ በታሪካችን የነበረንን ቦታ አጣን ወይም ተነፈግን የሚሉም ሊኖሩ ይችላሉ። ታድያ እንደነዚህ አይነቶችን ታሪካዊ ክስተቶች በመጠቀም ህብረተሰቡን መቆሚያ ከማይኖረውና መፍትሄም ከማይገኝለት አጣብቂኝ በመክተት የራሳቸዉን ጠባብ እና መናኛ አጀንዳ ለማራመድ የሚጥሩ ቡድኖችን በተለያዩ አጋጣሚዎች ለማየት ችለናል። ከዚህም በመነሳት ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ መሰረተ ቢስ ለሆኑ ዘገባዎች ጆሮ እንዳይሰጥ፤ አንዱን ህብረተሰብ ወይም እምነት ጠላት ሌላዉን ደግሞ ነብስ -ዓድን አሳቢና ተቆርቋሪ አድርገው ከሚይዙ እና ከሚንቀሳቀሱ ቡድኖችም እራሱን እንዲጠብቅ፤ ከምንም በላይ የአገራችን ኢትዮጵያ ዉበትና ጌጥ የብዙ ህዝቦችና ማህበረሰቦች፣ ባህሎችና ወግ -ልምዶች፣ አምነቶችና ቋንቋዎች ባለቤትነቷ በመሆኑ፣ ለእነዚህ ልዩና ብርቅየ እሴቶቻችን ልዩ አትኩሮትና ቅድሚያም እንድንሰጥ በማለት ጥሪያችንን እናጠናቅቃለን።
የህዝቦች መቻቻልና መግባባት ለአገራችንና ለህዝቦቿ ዘላቂ ሰላም ብቸኛ መሰረት ነው።

ኢትዮጵያ ለሁሉም ልጅቿ ዉድ እናት ነች።

በአዉሮፓ የኢትዮጵያን ሙስሊሞች ኔትዎርክ

December, 2005
ምንጭ፡ http://www.ethiopianmuslims.net/Arsi_NEMECall.htm
--------
ሙስሊም
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዲጎኔ

ዋና አለቃ


Joined: 19 Aug 2005
Posts: 4208
Location: united states

PostPosted: Fri Dec 16, 2005 6:10 am    Post subject: ሙስሊሙ ወገኔ አስተያየትህን በደስታ ተቀብያለሁ Reply with quote

የተከበርከው ሙስሊሙ ወገኔ

ይህንን ርእስ ልከፍት የቻልኩበትን መሻቴን ከመጣጥፍህ ስላገኘሁ በጣም አመሰግናለሁ :: በዚሁ አምድ ጉዳዩን ወደሀይማኖታዊ ፍጥጫ ለማስለወጥ የሚማስነው ወያኒያዊው ብእረኛ ዳርኩላ እንደሆነም ከምልልሳችን ትረዳለህ ::

በአጠቃላይ ህዝባችን በብዙ በጨቁዋኝ መሪዎች እየተሰቃየ አላስፈላጊ የሀይማኖት ግጭት እንዳይፈጠር ማለፊያ ሀሳብ ያቀረቡትን የአውሮፓ ወገኖቻችንን አመስግንልኝ ::


ይህን ቀናና አስማሚ ሀሳባችሁንም ወደምድራችን ላኩልኝ ::

በነገራችን ላይ ባለፈው በሎንደን በቅርቡ ደግሞ በሞሮኮ በአሸባሪነት በስህተት ተጠርጥረው የሚሰቃዩት ወገኖቼን መከራ በመንፈስ እንደምጋራና Protest መላኬን እገልጻለሁ

ዲጎኔ ሞረቴው የወረገኑ አርሲ ኢተያና ከፊቾ ትውልድ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

 
Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum


Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia