WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ጦሳና የግጥም ሥራዎቹ ማሰባሰቢያ አምድ !

Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ዋኖስ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Nov 2004
Posts: 1571
Location: Mars

PostPosted: Wed Dec 21, 2005 3:34 pm    Post subject: ጦሳና የግጥም ሥራዎቹ ማሰባሰቢያ አምድ ! Reply with quote

እሳት ወይም አመድ !

በእንባ አልባ እንባ ለቅሶ : እንባ እየወረደው :

አባት በልጁ አምሳል : ስቆ የሚያለቀሰው :

እሳት በመቃጠል : አመድ ሲወልድ ነው ::

ዛሬም በኛ ትውልድ : የዚሁ ተምሳሌት : ፍችው በመድረሱ :

አባቶች በልጆች : አረው እየጨሱ :

ለቁሞቹ ቁም ሞት : ሙታኑ አለቅሱ ::

በእሳቶቹ ቦታ : ሙጀሌ ተፈጥሮ :

ሰው እየመረዘ : የደም ስር አቋጥሮ :

ከመራመድ ሲያገድ : ያገር እግር አስሮ :

እንደአመድ መዳፈን ምንድነው ? ዘንደሮ ::

ጤንነትን ሲያውክ : ተውሳክ ከሰው ሰርጎ :

ሙጄሌን ለመንቀል : ወደዚያ መጅርጎ :

ፊትም የሚሰራው : መዳኒት ወረንጦ :

በሳት ነበልባል ነው : ብረት ውስጡ ቀልጦ ::

ስለዚህም አሁን : አንት የዛሬ ትውልድ :

ሞት በሞት አሙቶ : እራስን ለመውለድ :

አለዚያም ቁም ሞቶ : በራስ ሞት ለመፍረድ :

ጊዜ አቅርቦልሀል : የመሆን ጥያቄን እሳት ወይም አመድ ::

ጠንቀኛው ሙጄሌ : እንዲህ ሲዘባነን :

ባገር -ግር ላይ ገኖ !

ፍሙ የወረስከው :

በውስጥህ ተዳፍኖ :

ተቃጥሎ ማቃጠል : መቻል ሳይቻለው :

እልብህ ላይ መክኖ !

በነበር ከቀረ እሳት አመድ ሆኖ !

አባትህ ባካልህ አምሳል ተደብቆ :

እንባ አልባ እንባ ያፍስ : እጅግ ተንሰቅስቆ ::

ወይንም ሙጄሌ : ካገር እግር መንቅያ :

የወረንጦ መስሪያ :

ብረት ለማዋሀድ :

እሳት ሆነህ ነደህ

እንደሳት በማንደድ :

አቃጥለህ ተቃጥለህ : አንተ ስታበራ :

መንፈሱ በሳቤህ : ሰርፆ ነፍስ ሲዘራ :

ያዳፈንከው ፍሙ : ተገልጦ ገድል ይስራ

ቃሉ ሞቶ እንዳይቀር : አለብህ አደራ ::

ሞት በሞት አሙቶ : እራስን ለመውለድ :

አለዚያም ቁም ሞቶ : በራስ ሞት ለመፍረድ :

የዘመኑ ምርጫ : የመሆን ጥያቄ : እሳት ወይም አመድ ::

Last edited by ዋኖስ on Wed Dec 21, 2005 3:43 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋኖስ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Nov 2004
Posts: 1571
Location: Mars

PostPosted: Wed Dec 21, 2005 3:38 pm    Post subject: በሞት ሞትን ማፍራት ! Reply with quote

የእንጨት ነገር : የንጨት ስራ :

በሞት ሞትን የሚያፈራ

ከሳት ገብቶ :

ሞቆ ግሎ !

ነዶ ጦፎ :ተቀጣጥሎ !

አመድ መሆን : ሌላው ሊሞቅ !

ይገርመኛል !! እንጨት ሲስቅ !

ፈሳሽ ወዙ እያረገ

መንበልበሉ : መንቦግቦጉ እያደገ

በሱ መንደድ : ሌላ አሙቆ

ውስጡ ሲያለቅስ ! ላዩ ስቆ

በል ተው ቻለው

መጠቃቱን : ሁሉን ችሎ

በሳት ነዶ

ተንበልብሎ

የብርዱንም : የራሱንም ነፍስ ቀጥፎ

ህይወት ገድሎ

የሌላውን : የሙዋቂውን

ነፍስ ሲዘራ : ሩህ ሰጥቶ

እንጨት ሲሞት : ውስጡ በግኖ

ቀለመ ነጭ : ነጫጭባ አመድ ሆኖ

(አዲስ አበባ : 1979)[/quote]
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋኖስ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Nov 2004
Posts: 1571
Location: Mars

PostPosted: Wed Dec 21, 2005 3:41 pm    Post subject: ቅኔዉ ሲፈታ Reply with quote

ቅኔዉ ሲፈታ

ሰምተው በዝምታ :

የዝምን ዝምታ :

የህዋ : የየብስ : የባህር ስጦታ :

ያለማችን ምስጢር : ቅኔዋ ሲፈታ :

ሹሚያ የሌለበት : የግርግር ሜዳ :

ሁሉ ሁሉ ሆኖ : ያንድ ላንድ ጨዋታ ::

(አዲስ አበባ : ህዳር 06: 1982)[/quote
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋኖስ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Nov 2004
Posts: 1571
Location: Mars

PostPosted: Wed Dec 21, 2005 3:58 pm    Post subject: እምባ አልባ Reply with quote

በእንባ ብዛት : እንባው ጠፍቶ እምባ ጨምቆ

በእንባ ሙላት : እንባው ደርቆ :

ምንም ቢታይ : ጥርሱ ስቆ :

ሰው ያለቅሳል : ሰው እያየው : ተደብቆ :

በእንባ አልባ እንባ ተንሰቅስቆ :
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋኖስ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Nov 2004
Posts: 1571
Location: Mars

PostPosted: Wed Dec 21, 2005 4:07 pm    Post subject: እዉን አንቺ እሷው ነሽ !? Reply with quote

እዉን አንቺ እሷው ነሽ !?

የሚፈሰው እንባሽ : ሲያርስሽ አድርቄ :

የዋጠሽ ጨለማ : ሲያፈዝሽ አድምቄ :

ያሰረሽ ሰንሰለት : ሲያስርሽ አስቦርቄ :

ከርሀብሽ - ጥጋብ

ከክሳትሽ - ውበት

ከኃዘንሽ - ፈገግታን

ከስርቆት ሰርቄ :

አጥንትሽ ሲወጋኝ - ሽንጥ ዳሌን አድንቄ :

እውን አንች እሱዋ ነሽ ?! አልኩኝ ተጨንቄ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ጦሳ

አዲስ

Joined: 20 Dec 2005
Posts: 16

PostPosted: Mon Dec 26, 2005 2:48 pm    Post subject: አቤት ያች ሌሊት ! Reply with quote

ደሳሳ ጎቹዋችን : ጨለማ ውጡዋት :
ውራጅ ነጠላችን : ብርድ አሽንፉዋት :
በስትንፋስ መልሰን : እኛ እያሞቅናት :
ተኝታ ላያችን : ልናሳልፋት :
በቀደም ሌሊቱዋን : እንደጀመርናት :
የእኔ አካል - በሱዋ ውስጥ :
የሱዋ በእኔ ውስጥ ቀልጦ : ተዋህዶ :
እንደ ሰም ስንነድ : ቦግ ባለው ብርሀን !
ድቅድቁ ጨለም : ላፍታ ተወግዶ !
ያካል ፍትጊያችን : ድንገት እሳት ጭሮ :
እኔና ፍቅርዬን : አንድ አረገንና : አቆላልፎ : አሳስሮ :
የትካዜ ክምር አመድ ሲሆን ነዶ :
ዋሽንቱን ሲነፋ : ኪሩቤል ከሰማይ : መሀላችን ወርዶ !
ልባችንን ያሬድ : በማራኪ ዜማው : በፍስሐ አርዶ !
ክዋክብት ሲረግፉ : መሬት ስትሆን ቁና :
ያለንባት መንደር ተለወጠችና :
የሰለጠነውን : ከተማውን ሆና :
ገብተን ከፎቅ ህንፃ : እጅግ ከሚል ደስ :
ተክቶት ጄንዲያችን : ባለሰፍነግ አልጋ የሚያነፈላስስ !
ደረብ አረግንና ያማረ ብርድ ልብስ : የሚለሰልሰ :
ምቾት ግብር ገብተን : ነጭ ጤፍ ስንቆርስ :
ከፍቅር መዲና : መሀል በመድረስ :
ችግር : ቼነፈርን የረሳንባት :
ዬዬሌክትሪክ መብራት : የሚበራባት :
ውሀውም በቡዋንቡዋ : የሚሳብባት :
ሁሉ ተትረፍርፎ : ሁሉ ሞልቶባት :
የድሎት አክርማን : የቀጨንባት :
አቤት ያች ሌሊት ! የሌሌንባት !
እንደት ትጥም ነበር !?
እንደት ትሞቅ ነበር !?
ማለፍ አሳልፎ : ለብርድ ባይሰጣት !
አቤት ያች ሌሊት ! የሌሌንባት !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia