Posted: Wed Dec 21, 2005 3:34 pm Post subject: ጦሳና የግጥም ሥራዎቹ ማሰባሰቢያ አምድ !
እሳት ወይም አመድ !
በእንባ አልባ እንባ ለቅሶ : እንባ እየወረደው :
አባት በልጁ አምሳል : ስቆ የሚያለቀሰው :
እሳት በመቃጠል : አመድ ሲወልድ ነው ::
ዛሬም በኛ ትውልድ : የዚሁ ተምሳሌት : ፍችው በመድረሱ :
አባቶች በልጆች : አረው እየጨሱ :
ለቁሞቹ ቁም ሞት : ሙታኑ አለቅሱ ::
በእሳቶቹ ቦታ : ሙጀሌ ተፈጥሮ :
ሰው እየመረዘ : የደም ስር አቋጥሮ :
ከመራመድ ሲያገድ : ያገር እግር አስሮ :
እንደአመድ መዳፈን ምንድነው ? ዘንደሮ ::
ጤንነትን ሲያውክ : ተውሳክ ከሰው ሰርጎ :
ሙጄሌን ለመንቀል : ወደዚያ መጅርጎ :
ፊትም የሚሰራው : መዳኒት ወረንጦ :
በሳት ነበልባል ነው : ብረት ውስጡ ቀልጦ ::
ስለዚህም አሁን : አንት የዛሬ ትውልድ :
ሞት በሞት አሙቶ : እራስን ለመውለድ :
አለዚያም ቁም ሞቶ : በራስ ሞት ለመፍረድ :
ጊዜ አቅርቦልሀል : የመሆን ጥያቄን እሳት ወይም አመድ ::
ጠንቀኛው ሙጄሌ : እንዲህ ሲዘባነን :
ባገር -ግር ላይ ገኖ !
ፍሙ የወረስከው :
በውስጥህ ተዳፍኖ :
ተቃጥሎ ማቃጠል : መቻል ሳይቻለው :
እልብህ ላይ መክኖ !
በነበር ከቀረ እሳት አመድ ሆኖ !
አባትህ ባካልህ አምሳል ተደብቆ :
እንባ አልባ እንባ ያፍስ : እጅግ ተንሰቅስቆ ::
ወይንም ሙጄሌ : ካገር እግር መንቅያ :
የወረንጦ መስሪያ :
ብረት ለማዋሀድ :
እሳት ሆነህ ነደህ
እንደሳት በማንደድ :
አቃጥለህ ተቃጥለህ : አንተ ስታበራ :
መንፈሱ በሳቤህ : ሰርፆ ነፍስ ሲዘራ :
ያዳፈንከው ፍሙ : ተገልጦ ገድል ይስራ
ቃሉ ሞቶ እንዳይቀር : አለብህ አደራ ::
ሞት በሞት አሙቶ : እራስን ለመውለድ :
አለዚያም ቁም ሞቶ : በራስ ሞት ለመፍረድ :
የዘመኑ ምርጫ : የመሆን ጥያቄ : እሳት ወይም አመድ ::
Last edited by ዋኖስ on Wed Dec 21, 2005 3:43 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Posted: Wed Dec 21, 2005 3:38 pm Post subject: በሞት ሞትን ማፍራት !
የእንጨት ነገር : የንጨት ስራ :
በሞት ሞትን የሚያፈራ
ከሳት ገብቶ :
ሞቆ ግሎ !
ነዶ ጦፎ :ተቀጣጥሎ !
አመድ መሆን : ሌላው ሊሞቅ !
ይገርመኛል !! እንጨት ሲስቅ !
ፈሳሽ ወዙ እያረገ
መንበልበሉ : መንቦግቦጉ እያደገ
በሱ መንደድ : ሌላ አሙቆ
ውስጡ ሲያለቅስ ! ላዩ ስቆ
በል ተው ቻለው
መጠቃቱን : ሁሉን ችሎ
በሳት ነዶ
ተንበልብሎ
የብርዱንም : የራሱንም ነፍስ ቀጥፎ
ህይወት ገድሎ
የሌላውን : የሙዋቂውን
ነፍስ ሲዘራ : ሩህ ሰጥቶ
እንጨት ሲሞት : ውስጡ በግኖ
ቀለመ ነጭ : ነጫጭባ አመድ ሆኖ
(አዲስ አበባ : 1979)[/quote]
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Posted: Wed Dec 21, 2005 3:41 pm Post subject: ቅኔዉ ሲፈታ
ቅኔዉ ሲፈታ
ሰምተው በዝምታ :
የዝምን ዝምታ :
የህዋ : የየብስ : የባህር ስጦታ :
ያለማችን ምስጢር : ቅኔዋ ሲፈታ :
ሹሚያ የሌለበት : የግርግር ሜዳ :
ሁሉ ሁሉ ሆኖ : ያንድ ላንድ ጨዋታ ::
(አዲስ አበባ : ህዳር 06: 1982)[/quote
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Posted: Wed Dec 21, 2005 3:58 pm Post subject: እምባ አልባ
በእንባ ብዛት : እንባው ጠፍቶ እምባ ጨምቆ
በእንባ ሙላት : እንባው ደርቆ :
ምንም ቢታይ : ጥርሱ ስቆ :
ሰው ያለቅሳል : ሰው እያየው : ተደብቆ :
በእንባ አልባ እንባ ተንሰቅስቆ :
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Posted: Wed Dec 21, 2005 4:07 pm Post subject: እዉን አንቺ እሷው ነሽ !?
እዉን አንቺ እሷው ነሽ !?
የሚፈሰው እንባሽ : ሲያርስሽ አድርቄ :
የዋጠሽ ጨለማ : ሲያፈዝሽ አድምቄ :
ያሰረሽ ሰንሰለት : ሲያስርሽ አስቦርቄ :
ከርሀብሽ - ጥጋብ
ከክሳትሽ - ውበት
ከኃዘንሽ - ፈገግታን
ከስርቆት ሰርቄ :
አጥንትሽ ሲወጋኝ - ሽንጥ ዳሌን አድንቄ :
እውን አንች እሱዋ ነሽ ?! አልኩኝ ተጨንቄ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
You cannot post new topics in this forum You cannot reply to topics in this forum You cannot edit your posts in this forum You cannot delete your posts in this forum You cannot vote in polls in this forum