WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የእናት ፍቅር
Goto page 1, 2, 3, 4  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ማህቡብ

ኮትኳች

Joined: 18 Aug 2005
Posts: 253

PostPosted: Sun Jan 22, 2006 10:54 am    Post subject: የእናት ፍቅር Reply with quote

ይህንን አርእስት መክፈት የፈለግኩት ሁላችንም ልንዘነጋው የማይገባንን እናት ከእርግዝና እስከ ውልደት ለልጅዋ የምታደርገውን እንክብካቤ ዋቢ በማድረግ ፍቅራችንን እንዴት ነው ልንገልጽላት የምንችለው ?? በማስከተልም ለመወያየት ያክል ትዳር ከተመሰረተስ በሁዋላ ለእናት ያለን ፍቅር ምን ያህል ነው የሚሆነው ? እንደሚስተዋለው ለምሳሌ አንዳንድ
ወንዶች እናቱንም ሚስቱንም ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ፍቅሩን
ያበረክታል አንዳንዱ ደግሞ በአንጻሩ ነው ::

በመጨረሻ ግን ማለት የምፈልገው እናት ከሁሉም በላይ ናት ምንም ነገር ሊወዳደራት የማይችል ::

ከአክብሮት ጋር
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Monica****

ዋና አለቃ

Joined: 26 Dec 2003
Posts: 3937
Location: 999 Total eclipse st. Venus

PostPosted: Sun Jan 22, 2006 11:27 am    Post subject: Reply with quote

ማህቡብ የኔ ቆንጆ
ስንበት እንዴት ይዞሀል ?
የሚገርምህ ነገር አሁን የማሪቱ ለገስን ዘፈን "አምባስል " my favourite !!!! እያዳመጥኩኝ ነው ይሄንን የጻፍከው .....እና ግጥሟን ስምቼ ግርም ሲለኝ አንተ ደሞ ስለእናት መጻፍህ ገረመኝ
ምን ትላለች መስለህ
እንክዋን እንጉርጉሮ ስንት ያውቃል አምባስል
በሆድ ብዙ ችሎ ያልተከፉ መምስል
አሳድሮ ደጅ ዛሬ ነገ እያለ
ተከፍቶ ብናየው በሆዱ ስንት አለ !!
ወንድሙን ወንድምኑ ተጭኖ ገደለው
እንስፍስፍ እናቱን ሆዱ ቢያታልለው
ያስተኛውን አንጀት ከባርም አላለው
እናትና መሬት ስንቱን አበቀለው ??

እናት ማብቀል ብቻ ሳይሆን ስንቱን ጉድ የምትችል ጊዜና ሀብት የማይቀይራት ምንግዚም አብራህ ነዋሪ እናት ብቻ ናት !!!!
ከእናት በላይ ማንም የለም ......!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አክየ

ዋና አለቃ

Joined: 28 Jul 2005
Posts: 2591

PostPosted: Sun Jan 22, 2006 12:16 pm    Post subject: Reply with quote

ስለ እናት ጉዳይ ሲወራ እና ሲነሳ በጣም ደስ ይለኛል

እናት ማለት የልጆቿን ክፉ የማትሻ ልጆቿ ወጥተው እስከሚገቡ የማታምን ሩህሩህ ናት አባት ልጆቹን ሊቀጣ ወይም ሊገርፍ ሲያስብ እናት እንደምንም ብላ ልጆቿ እንዳይመቱባት የማታደርገው ነገር የለም ልጅ አምሽቶ ከመጣ አባት ቀድሞት ከገባ እና ልጁን በጓሮ ደብቃ ነው አይደል የምታስገባውውውውውውውውው እስኪ ትዝ አይላችሁም ከአባት ዱላ ወይም እጅ ስንት ጊዜ አትርፋችሗለች

ግርማ ሞገሴ ነሽ እምየ እናቴ
የህይወቴ ብርሀን የዘጠኝ ወር ቤቴ
ከፉሽን አልስማ እማ እስከለቴ ሞቴ
ከፉሽን አልስማ እማ እስከለቴ ሞቴ

from bruk
_________________
"Say what you have to say in the fewest possible words"
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ማህቡብ

ኮትኳች

Joined: 18 Aug 2005
Posts: 253

PostPosted: Sun Jan 22, 2006 3:10 pm    Post subject: እናት Reply with quote

ሞኒካዬ የኔ ቆንጆ :- ሰንበቱ ምንም አይልም አንችሽ ቆንጆ ?
እርግጠኛ ነበርኩ የመጀመሪያዋ ተሳታፊ እንደምትሆኝ በእና
ዙሪያ ሞኒነት , የእናት ውለታ ይህ ነው ብለን ልናቆም አንችልም ......... እስቲ ለማምያችን የሚሆን ስጦታ እናዘጋጅ
ለእናቶች ቀን :: አመሰግናለሁ ቆንጆ

ወድ አክየ እናት ለልጅዋ ከምታደርጋቸው ቀንጠብ አድርገህ
ያቀረብከው በተለይ በተለይ እናት ልጅዋን በጉዋሮ ደብቃ
ነው የምታስገባው ያልከው Smile Smile Smile እማዬ ካባዬ በትር
ከለላ የሆነችበትን አስታወስከኝ ውይ እናት እኮ .........
ለመልካሙ ተሳትፎህ አመሰግናለሁ ::

ከአክብሮት ጋር
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ምርቃና

ኮትኳች

Joined: 24 Feb 2004
Posts: 276

PostPosted: Sun Jan 22, 2006 5:16 pm    Post subject: Reply with quote

የናት ፍቅር እንደ በሽታም የሚሆንበት ጊዜ አለ
እንደዛሬው ልባችን ሳይደነድን በፊት እነ አቻም የለሽ የናታችንን ቦታ መጋፋት ሳይጀምሩ በፊት >>>>

ድሮ እኔ የሰፈር ልጆች ወደ ክፍለሀገር ዘመድ ሊጠይቁ ሲሄዱ ሞቼ እገኛልሁ እኔም ካጎቴ ጋር መሄድ አለብኝ ብዬ ወደ ወሎ ጉዞዬን አቀናሁ >>>> ይገርማችዋል 14 ወም 15 አመት ልጅ ነበርኩኝ የዛኔ ግን በገባው በንጋታው ምግቡም ጦሳም ሁሉም ነገር አልመች አለኝኝ ታመመኩኝ በናፍቆት >>> ይህን የሰማች እናቴ 4 ቀን በኅላ ይመስለኛል ስትመጣ በሽታዬ ሁላ ጠፋ ውይ እንደዛ ቀን ደስ ያለኝ ቀን በህይወቴ እሳክሁን አላስታውስም >> እና የናት ፍቅር እንደ በሽታም ይጥላል ባይ ነኝ >>>>>>

ማህቡብ እናስመሰግናለን እናታችንን እንድናስብ ስላደረክ !

ግን እኮ ክፉም እናቶች አሉ አሉ እጅህን እሳት የሚያቃጥሉ ከምር አንዲት ገር ፍሬንድ ነበረችን የሌባ ጣትዋና መሀል ጣትዋ እንደ ዳክዬ የገጠመ በዚሁ ሳቢያ >>>> እስቲ ስለሱም አስተያየት ጣል አርጉ .....
በሉ ልዋበው >>>>>!
_________________
Just chat, dont consider it>>>> Love 4 all>>
figaww.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ማህቡብ

ኮትኳች

Joined: 18 Aug 2005
Posts: 253

PostPosted: Sun Jan 22, 2006 5:44 pm    Post subject: እናት Reply with quote

ምርቃና ወንድሜ :- ጥሩ ብለሀል ...... የእናት ፍቅር ተፈትሯዊም ሆነ ሰው ሰራሽ የሆነ ግዙፍ ነገር በልባችን ያለውን የእናት ፍቅር ቦታ ሊተካ አይችልም :: Laughing Laughing እናቻምየለሽ ደግሞ የእናትን ቦታ ቢጋፉም ትክክለኛውን ቦታ ግን አያገኙትም ::

ከአክብሮት ጋር
_________________
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቀብራራው

ዋና ኮትኳች

Joined: 05 Dec 2004
Posts: 589

PostPosted: Sun Jan 22, 2006 9:13 pm    Post subject: Reply with quote

ስለ እናት ስታወሩ አስቀናቹኝ ....ተሰምቶኝም አዘንኩኝ :: እኔ እናቴ 4 አመት ልጅ እያለሁ ነው ታማ የሞተችው :: በጣም ጭላንጭል ትዝታዎች /ብልጭታዎች ብቻ ነው ያሉኝ ...... ልትወጣ ስትል በመስተዋት እያየች ጸጉሯን የምታስተካክለውን ...እና ....ታናሼ ምን እንዳለ ትጠይቀኝ የነበረውን (የሱን ቋንቋ የምረዳው እኔ ብቻ ነበርኩ ):: ብቻ ሁሌም በጣም እየናፈቀችኝ እንዳደኩ ትዝዝዝዝ ይለኛል :: በልጅነት አእምሮዬ "ሰው ለምን ይሞታል ...እንደብረት ቢጠነክር ኖሮ እኮ አይሞትም ነበር " እያልኩ ለብቻዬ አወራ ነበር :: እናቴን ስለነጠቀኝም ሞትን በጣም ነበር የምጠላው :: አንዳንዴ በጣም ስትናፍቀኝ ድንገት ካገኘኃት እያልኩ ለብቻዬ መቃብሯ ጋር እሄድ ነበር ::

ብቻ እናት ስላልነበረኝ ...አንደኛ ደረጃ ስማር በእኩዮቼ ምን ያህል እቀናና እተክዝ እንደነበር አትጠይቁኝ :: ይባስ ብሎ ... የአንደኛና የሁለተኛ ክፍል መዝሙሮች ሁሉ ደግሞ ስለእናት ብቻ ስለነበሩ በደንብ እችላቸው ነበር ...ስዘምርም አለቅስ ነበር በሀዘን :: ከጊዜ በኃላማ ያው በቃ እየለመድኩት መጣሁ ...ተቀበልኩትም :: እስካሁንም ግን እናቴን አለማወቄን ሳስበው በጣም አዝናለሁ -- እለሰልሳለሁም :: ይሄን ስጽፍላቹ ራሱ እምባዬ እየወረደ ነው :: እጅግ በጣም ደግና ሩህሩህ እናት እንደነበረኝ ሁሉም ሲያወራ ይቆጨኛል ... ቆንጅዬና በሰፈር ውስጥ ሁሉም እንደሚወዳትም ይነግሩኝ ነበር ::

ሌላው በልጅነቴ ያሳዝነኝ የነበረው አባቴ ነው ...ከራሱ በላይ የሚወዳት ሚስቱን ሲያጣ ብዙ ነገር ደርሶበታል ::
_________________
peace for all
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እድላዊት

ኮትኳች

Joined: 27 Nov 2004
Posts: 362
Location: united states

PostPosted: Sun Jan 22, 2006 11:47 pm    Post subject: Reply with quote

ቀብራራው እንደጻፈ(ች)ው:

ሰላም ለናንተ ይሁን ማህቡብዬ የኔ ቆንጆ ጥሩ ሀሳብ ናት ስለናቴ ጨዋታ ሌላ ግዜ ልመለስ እና ትንሽ ለቀብሬው አንድ ልበለው ቀብሬ የኔ ቆንጆ የጻፍከው ልብ ይነካል የናትን ፍቅር የሚያቅ ያውቀዋል ግን ልልህ የምፈልገው አይዞህ ሁሉ ነገር አላፊ ነው አንተ እናትህን ሳታቅ እንዳደክ ደሞ ካላባት ያደገ ይኖራል እና ይህ የሰውልጅ እጣፋንታም ቢሆን ችሎ መቀበል ነው አምላክ ደሞ የናትን ፍቅር በሚስት ይተካልህ ወይም እናትህን የመሰለች ልጅ ሴት ልጅ ይሰጥሀል ማን ያውቃል አይደለ ?አምላክ የሚወዳቸውን ይወስዳል አክባሪህ እድል
ማህቡብዬ ስለኔና ስለናቴ ትንሽ ለየት ያለ አለኝ ሌላ ግዜ ይዣት እመለሳለው በሰፊው
_________________
hany
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail AIM Address Yahoo Messenger Report post
እድላዊት

ኮትኳች

Joined: 27 Nov 2004
Posts: 362
Location: united states

PostPosted: Mon Jan 23, 2006 12:14 am    Post subject: Reply with quote

እናት አለም አንቺ የፍቅር አስተማሪ
አካልሽ በሙሉ የፍቅር ዘካሪ
ውድድ የማረግሽ ስስት የምልልሽ
ውድዬ ውዲቱ እማምዬ አንቺ ነሽ
እናቴ ፍቅርዬ ወዳጄ የልቤ
ብዙ አመት ባንቺ ላይ የጣልኩት ሀሳቤ
ለጄ ይህ ይበጃል ይህ ስሻላል ብለሽ
እድሜዬ ቡገፋም ያው ነው እሹሩሩሽ
እረ እማማ ያንቺስ ከማንስ ይገጥማል
አረሳም አለብኝ ሆዴ ይሸበራል
እማማ ወልደሽኝ አሳደግሽኝ በፍቅር
ምንም ሳይጎልብኝ አርገሽ ሽቅርቅር
ቢከፋሽ ቻል አርገሽ ስቀሽልኝ ለኔ
ትይኝ የነበረ ወርቅና ብርሀኔ
እማማ ዛሬማ ገባሽ ከአንጀቴ
ሲናፍቅሽ ያድራል መላው አከላቴ
እናቴን አርግዠ ሽሉ ይላወሳል
ሳምጣት ሳምጣት አንጀቴ ተላውሶዋል
በሀሳብ አርግዠሽ ሳይሽ ቀኑ እጥር
እረ ለምን ይሆን የሚለው ብርር
እማ ካንቺ ጋራ 2ወር 2ቀን
ይልብኛል ልቤ ብክን ብክንክን
ወድሻለው እማ ከልብ ከአንጀቴ
እስቲ እይእማምዬ ይናገራል ፊቴ

እድሜ ለናት ሁሉሉሉ እናቴን ውድድድድድድድድድድድድድድድድ ነው የማረጋት ይህን ግጥም ዋኖስ ቢያየው ያለቅስ ይሆናል ውይውይ Smile
_________________
hany
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail AIM Address Yahoo Messenger Report post
አኒታ

ዋና ኮትኳች

Joined: 29 May 2004
Posts: 747
Location: City of angels

PostPosted: Mon Jan 23, 2006 1:07 am    Post subject: ለቀብራራው Reply with quote

ይሄን ስጽፍላቹ ራሱ እምባዬ እየወረደ ነው :: እጅግ በጣም ደግና ሩህሩህ እናት እንደነበረኝ ሁሉም ሲያወራ ይቆጨኛል ... ቆንጅዬና በሰፈር ውስጥ ሁሉም እንደሚወዳትም ይነግሩኝ ነበር ::

ሌላው በልጅነቴ ያሳዝነኝ የነበረው አባቴ ነው ...ከራሱ በላይ የሚወዳት ሚስቱን ሲያጣ ብዙ ነገር ደርሶበታል ::
________________
ይቅርታ .. እስካሁን በመዘግየቴ ግን እስካሁን ካነበብኩት ውስጤ ነክቶ ያስለቀሰኝ እንደ እዚህ ጽሁፍ የለም ... እንባህ ተጋሪ ነበርኩኝ ... እግዚአብሄር ይክስሀል !እናትን ማጣትን ሳስብ የኔን እናት አስብና ሳይሆን አለቅሳለሁ
አባቴን 1 አመት 6 ወር እያለሁ ነው የሞተው ..ብዙም አላቀውም .. ምንም ላስታውስበት የምችለው አእምሮም የለም ብቻ እናቴ ግን ብዙ ውጣ ውረድን አሳልፋለች .. አሁንም ለልጆቿ ሟች ነች .. በጣም ነው ጥንካሬዋን ፍቅሯን አሁንም ማይሻር ማንነቷን ሳስብ እናት በላይ እኔ የለም .. እንጃ ባጣትም ምን እንደምሆን አላቅም .. ብቻ በምን ልክሳት እንደምችል ሳስበው .. ሁሉም ያንስባታል .. እርሷ ስለኔ ያየችውን እኔ ለሷ ማድረግ አልቻልኩምና ...እራሷን ዝቅ አርጋ ነው ሰው ያረገችኝ እናቴ .. እኔ እናቴ .. ምትክ የሌላት አንድ ትልቅ ሀብቴ ናት ! እርሷን ማንም አይተካትም ! ከሁሉ የማልረሳው አዲስ ስራ ገብቼ ቦታ ጠፍቶብ ከከተማ ሆኜ ማታ ደወልኩና . እንደ ጠፋብኝ ስነግራት . አስፋልት እግሯ ወጥታ ነበር የጠበቀችኝ ሳያት የማላቀው እንባ ነበር የፈሰሰው .. ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ .. ከሁሉም ከሁሉም ለልጆቿ ምትሆነውን ሳስብ ክፉ ይሆንባታል ብዬም ማሰብ አልፈልግም ! እርሷን ክፉ ለኔ ያርገው !
እናቴን እወዳታለሁ .. ወደፊት ባሌንም እንደ እርሷ ባይሆንልኝም ግን እንደ እርሷ ልወደው እንደምችል አምናለሁ .. ግን እርሷ አልተካውም !
እናት ልዩ ነች !
ቀብራራው .. ወደፊት እንደ እናት ምትሆንህ ሚስት እንድትገጥምህ መተኪያም እግዚአብሄር እንደሚሰጥ አምናለሁ እናም አምላክ የልብህ ይስማህ ዘንድ ጸሎቴ ነው !
አክባሪህ /አክባሪያችሁ
አኒታ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዋኖስ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Nov 2004
Posts: 1570
Location: Mars

PostPosted: Mon Jan 23, 2006 1:44 am    Post subject: ትድረስ ለእማምዬ ! Reply with quote

በሕይወቴ እጂግ የሚያስደስተኝ የምረካበት ነገር ቢኖር ለቤተሰብ ቅን -ታዛዥ ከሆነ ሠዉ ከልምዱ -ብዙ ነገር መማር ! ርዕሱ በምናቤ ወደ ኋላ ብዙ እንድጓዝ ካደደረጉኝም በሳል ኃሳቦች አንዱ ነው :: እናም በአንድ ወቅት ዛሬም ቢሆን ከአገር ዉጪ እየኖርኩ ራሴንና ቤተሰቤን እመራለሁ በምልበት ሰዐት የእናትነት ፍቅሯ አልቀንስ ብሎ አስገራሚ :_ አስደማሚ :- ንፁሕ የእናትና የልጂ ፍቅር አስተማሪነቷ :-መቼም ቢሆን የማይጠፋ መሆኑን ለመግለፅ በወቅቱ ከቋጠርኩት ሥንኝ እንካችሁ እያልኩ በዚሕ ዙሪያ ከቻልኩ ለየት ባለሥራ ካልቻልኩ ደግሞ ኃሳባችሁን ጨምቄ በተለመደችው ለማጂ ብዕሬ ለማቋደስ እሞራክለሁ :: ለጊዜዉ እነኋት ! ትንሿን

Rolling Eyes ትድረሥ -ለእማምዬ Rolling Eyes

ለእኔነቴ ተሥፋ ለዉስጤም ርካታ

ጣቶችሽ በረከት ክንዶችሽ መከታ

የአንገቴ -መኃለቅ የደስታዬ አለኝታ

<U><I>የተፈጥሮ -ዋሻ የገነት -ኮረብታ </U></I>

የረድዔት ሥሪት የትህትና ጎታ

ደግሠው አንቺ ነሽ ያኑርልኝ ጌታ ::

ሕይወቴ እንዲሰምር እንዲያምር ጂምሩ

ደፋ ቀና ብለሽ ሁሉን አሳልፈሽ እንደዬ ምግባሩ

ለዛሬዉ ሕይወቴ ሥኬቱ ሚስጥሩ

ደግ ሰው አንቺ ነሽ መልካም -ስመ _ጥሩ ::

በሥደትም ብኖር ከአንቺ ተለይቼ

ከአጠገብሽ ባልኖር ባላይሽ በዓይኖቼ

ሁሌም ከጎንሽ ነኝ መንፈሴን አፅንቼ ::

ምንም እንኳ ባልችል ባይረዳኝም አቅሜ

ችግርሽን ባልቀርፈዉ በችግርሽ ቆሜ

ከእናትነት ሚስጢር ከየዋሁ ልብሽ

ተሥፋን ፍቅርን ደግነት ተሞልተሽ

ተርበሽ ....ተጠምተሽ ....እንዳይሆኑት ሆነሽ

ለዚህ ለአበቃሽኝ በምክርሽ አንፀሽ

ትድረሥ ምስጋናዬ ደግሠዉ አንቺ ነሽ ::

====ከልጂሽ ===>ከዳሞት ===
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ቀብራራው

ዋና ኮትኳች

Joined: 05 Dec 2004
Posts: 589

PostPosted: Mon Jan 23, 2006 1:44 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም እድልና አኒታ
ለማጽናኛቹ አመሰግናለሁ :: በልጅነቴ በጣም ብዙ ሰው ሊያጽናናኝ ይሞክር እንደነበር ትዝ ይለኛል :: ግን እኔ ድርቅቅቅ ትክዝዝ ያልኩ ነገር ነበርኩ :: ህጻን እያለሁ በጣም ትወደኝ ስለነበር በጣም ቅርቧ ነበርኩ ...እናም ሳጣት ማመን አቅቶኝ ነበር :: ሲቀብሯት በጣም አስቸግሬ እንደነበርም ትዝ ይለኛል :: በዛ ምክንያት ይመስለኛል ያኔ ላባቴ የነበረኝን ፍቅር ቀንሶብኛል ...ጠልቼውም ነበር :: ሊያድናት ይችል ነበር ... እንዴት ስትቀበር ዝም ይላል እያልኩ እጠይቅ ነበር :: አባት ስለነበር ሁሉም ነገር ማድረግ የሚችል ይመስለኝ ነበር :: ብቻ ካለእናት ማደግ የመሰለ አስከፊ ነገር ያለ አይመስለኝም .... አስታዋሽ አይኖረውም ... ሊርበው ይችላል :: ምንም ነገር ስለማያውቅ ቢያለቅስ እንኳን ሌሎቹ አትጩህ /አትጨማለቅ ብለው ሲጮሁበት ...እናት ብቻ ነች ምን ሆኖብኝ ይሆን ብላ የምትጨነቀው :: ይመስለኛል ... አባት የሚያስፈልገው ትንሽ አደግ ካለ በኃላ እንጂ ለአንድ ህጻን የበለጠ የምታስፈልገው እናት ትመስለኛለች ::

አኒታ ሚስት ይስጥህ አልሽኝ ... እስቲ እናያለን :: እንጃ እንግዲህ እንደናቴማ የምትሆን ሚስት ከየት ትመጣለች ብለሽ ነው ?? ባሁኑ ሰዐት እኮ ሁሉም ነገር ከንዋይ ጋር ተቆራኝቷል :: እና አንዷ ብትወድሽ እንኳ በደህናሽ ጊዜሽ ብቻ ነው :: አንቺ ለራስሽ ጥሩ በሆንሽና ራስሽን የበለጠ በምትወጅበት ሰዐት ሰዎችም የሚወዱሽ ሲመስሉ ታያለሽ :: ከዛ በተረፈ ግን አንቺ ላይ አይተውት የመጡትን ነገር ሲያጡት ሌላው ላይ ለመፈለግ ጀርባቸውን ይሰጡሻል :: የእናት ፍቅር ግን unconditional ይመስለኛል ::
_________________
peace for all
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አኒታ

ዋና ኮትኳች

Joined: 29 May 2004
Posts: 747
Location: City of angels

PostPosted: Mon Jan 23, 2006 2:03 am    Post subject: ሁሉን ቻይ አምላክ አለህ ! Reply with quote

ሰላም ቀብራራው እባክህ ይህን ልብ ሰባሪ ቃላት በወረወርክ ቁጥር እኛንም እያስደመመን .. ቁጭ ብዬ እንደ ህጻን ማንባት ጀመሬያለሁ እና .. ብትችል ሁሉን መጽናኛ የሆነ ተስፋ ነውና .. ደግሞ ላንተ ያለውን አታጣውም .. ቀን ጊዜ ይፍጅ እንጂ እሩቅ አይሆንም .. ያንን እመን ከሁሉ በላይ ደግሞ መጎዳትን ያየ አምላክ ይክሳል እንጂ አያስደብብም ሁሌ ቅን ሰው ሁን .. አምላክ ቀናውን ይሰጥሀል .. ያንተ መልካምነት ለነገ ህይወት ትልቅ መሰረት አለውና .. ሁሌ ልቦናህና አመለካከትህ ያንተ ንጹህ ይሁን ሞትን አንተርሶ ጀርባ ለሚሰጥ ሰው አትጨነቅ .. ሁሉም እኮ ጀርባ ቀሪ ነው ! ማሰብ ያለብህ .. አምላክ ሲክስ .. ከሁሉ በላይ ነው እና ኤልሻዳይ አምላክ እንደሚክስህ እምነቴ ነው ከሁሉም ነገር .. አንተ ብርቱ ስላረገህ ማመስገኑ ትልቅ ነገር ነው .. እኔ እናት አለችኝ ብዬ አልታበይም እርሷ ብመካ ቀናተኛና ሚነጥቅ አምላክ ስላለ አምላኬን እፈራዋለሁ እርሷም በላይ እንደሚያስብልኝ አምናለሁ .. እንደ ቃሉ አምላክ እናትና አባት በላይ የሚራራና የሚወድ ነውና ..! ያንን አስብ .. ሁሌ ካንተ ጋር ያለ አምላክ አለህ ! እርሱም የልብን መሻት ይፈጽማልና .. መልካምን ሴት እንደሚሰጥህ እናትህን መልካም ስራና እንክብካቤ ልጅነትህ በላይ እንደምትሰጥህ አስብ .. ጊዜ ደግሞ እሩቅ አይሆንምም እግዚአብሄር ጋር ሁሉም ይሆናል ! እምነትህ አይጓደል ! እርሱ ጎዶሎ ህይወት አይሰጥምና ! እኔ ሁሌ በጸሎቴ ላስብህ ቃል እገባለሁ ! ፍቅር .. ሰላምን ... የልብህን መሻት አምላክ እንዲሰጥህ ፈቃዱ ይሁን !
አክባሪህ ወዳጅ እህትህ
አኒታ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዋኖስ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Nov 2004
Posts: 1570
Location: Mars

PostPosted: Mon Jan 23, 2006 3:26 am    Post subject: የእናት ዉለታዋ ! Reply with quote

ዕስኪ በጋራ እንዘምረው !! ዜማዉ በሚታወቀዉ ይሁን !!

Rolling Eyes የእናት ዉለታዋ !Rolling Eyes

የበዛ ነዉ እጂግ የእናት ዉለታዋ !

ተርባ ተጠምታ ደብቃ ጉያዋ

ፍትፍት ታጎርሳለች እናት ወለላዋ ::

ፍትፍት ታጎርሳለች እናት ወለላዋ ::

ሠዉነቴ ሲሞቅ ሲያተኩሥ ገላዬ

ከራሴ ጀምራ ድረስ ከጫማዬ

የምትዳሥሰኝ የማር -ወለላዬ

እናቴ ብቻ ነች መጠጊያ ጓዳዬ ::

እናቴ ብቻ ነች የኔ መጠጊያዬ ::

የበዛ ነው እጅግ የእናት ዉለታዋ !

ተርባ ተጠምታ ደብቃ ጉያዋ :-

ፍትፍት ታጎርሳለች እናት ወለላዋ ::

ፍትፍት ታጎርሳለች እናት ወለላዋ ::

ክፉሽን እንዳላይ ሥቃይሽን ሁሉ

የአምላክ ቸርነቱ የምሕረት ቃሉ

ሑሌም አይለይሽ ይደርብሽ በአንች

አይንካሽ ትካዜ ኑሪ ሳትሞች ::

አይንካሽ ትካዜ ኑሪ ሳትሞች ::

የበዛ ነው እጅግ የእናት ዉለታዋ :-

ተርባ ተጠምታ ደብቃ ጉያዋ :-

ፍትፍት ታጎርሳለች ዕናት ወለላዋ ::

ፍትፍት ታጎርሳለች ዕናት ወለላዋ ::

ፀባዬ ቢከፋ ባልመች ለአባቴ

ሠፈሩን ሳሳድድ ቢሠበር ጉልበቴ

ፈተናም ብወድቅ ቢቀንሥ ዉጤቴ

አፅናኝ አበረታች አንድ እሷ ነች ኃብቴ ::

አፅናኝ አበረታች አንድ እሷ ነች ኃብቴ ::

የበዛ ነው እጂግ የእናት ዉለታዋ !

ተርባ ተጠምታ ደብቃ ጉያዋ

ፍትፍት ታጎርሳለች ዕናት ወለላዋ ::

ፍትፍት ታጎርሳለች ዕናት ወለላዋ ::

ችግር ሲበዛብኝ ርኃብ ሲጠና

ወይ ! ዕናቴ ድረሽ ብዬ አሥብሽና

እጠግባለሁ በአንቺ ከረኃብ ቀጣና ::

እርጂናዉ ቢጫንሽ ጣትሽንም ቢያጥረው

ዕናቴ ኑሪልኝ ዕጂሽ መኃሪ ነው ::

የበዛ ነዉ እጂግ የዕናት ዉለታዋ

ተርባ ተጠምታ ደበቃ ጉያዋ

ፍትፍት ታጎርሳለች ዕናት ወለላዋ ::

ፍትፍት ታጎርሳለች ዕናት ወለላዋ ::

ፍትፍት ታጎርሳለች ዕናት ወለላዋ ::

---------- ... .... ...

..................

------

====ዳሞት ====

በጊታር እንዳጂብላችሁ www.ethiodamot.org ብቅ ይበሉ ::

( .)
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዩፎ

ኮትኳች

Joined: 25 Dec 2004
Posts: 259
Location: united states

PostPosted: Mon Jan 23, 2006 5:47 am    Post subject: Reply with quote

ቀብራራው ....ይቺ ጽሁፍህ የኔንም እንባ ተፈታተነች :: የምስራቅ እስያ ጨዋታ ላምጣ :: አንድ እናት በጣም የምትወደውን ልጁዋን ባጣች ጊዜ አምርራ ለቡድሀ አለቀሰች :: ቡድሀም በድንገት ተከሰተና እንዲህ አላት 'ይህን ኩባያ ይዘሽ ሂጂና ሀዘንና ሞት ከሌለበት ቤት ውሀ ቀድተሽ ሙይው ከዚያ ቡሀላ ልጅሽን አስነሳልሻለሁ ":: እናቲቱም በደስታ ሮጣ ሄዳ የእያንዳንዱን ቤት በር ብታንኩዋኩዋ ሁሉም ቤት ዘንድ ሀዘን እንዳለ አስተዋለች :: አምርራም አለቀሰች - 'ቡድሀ ሆይ ይቅር በለኝ ለካስ ይሄ ነገር በሁሉም የሰው ልጅ ላይ የመጣ ነገር ነው ' አለች ይባላል ::

እናም አስተዋዩ ቀብራራው ሆይ - ይህቺ አለም unfair የሆነች አለም ነች :: ነገሮቹዋ ሁሉ do not make sense. ተስፋችን ግን አንድ ቀን የሰማዩ አባታችንን ያገኘን ቀን ሁሉም ነገር will make sense. የሁላችንም ቆይታ አይናችንን ጨፍነን ለመክፈት ከሚፈጅብን ጊዜ በላይ አይደለምና ...ይቺን የቀረችዋን የሰከንድ ክፍልፋይ በማዘን ከሰማይ ሆነው የሚያዩህን እናትህን አታስከፋ :: በሰማይ ከእናትህ ጋር እስክትገናኝ ድረስ መቼም መጽናናት ከአምላክ ነውና አምላክ መጽናናቱን ይስጥህ ::

-ዩፎ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር All times are GMT + 1 Hour
Goto page 1, 2, 3, 4  Next
Page 1 of 4

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia