WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ስለዌይን ሩኒ እናውራ !!!

Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

View previous topic :: View next topic  
Author Message
አፍሪክ

ኮትኳች

Joined: 18 Feb 2005
Posts: 450
Location: united states

PostPosted: Sun Apr 09, 2006 9:27 pm    Post subject: ስለዌይን ሩኒ እናውራ !!! Reply with quote

ሶስት ወጣት ተጭዋቾች በመጭው አለም ዋንጫ ላይ ጥሩ ይንቀሳቀሳሉ ተብሎ ይጠበቃል :: የአርጀንቲናው ሊዮኔል ሜሲ , የስፓኙ ሴስ ፋብሪጋስ እና የእንግሊዙ ዌይን ሩኒ ::

እዚህ ጋር ሩኒን ከሁለቱ ወጣት ምን ይለየዋ ብለን ራሳችንን እንጠይቅ እስኪ ::ካይምሯችን ሊከሰት የሚችል የመጀመርያው መልስ ምናልባት በእድሜ ትንሽ ከፍ ማለቱ የሚል ሊሆን ይችላል :: ነገር ግን ትልቁ ልዩነታቸው ሆኖ የሚገኘው ሩኒ በልጅ ትከሻው ላይ የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ያለም ዋንጫ እድል በዋነኛነት የተጣለበት መሆኑ ነው :: ሰሞኑን በወጣው 4-4-2 መጽሄት ላይ ጆን ቴሪ "እንግሊዝ አለም ዋንጫን የምታገኝበት አስሩ ምክንያቶች " በሚል በዘረዘራቸው ነጥቦች በአንደኝነት ያስቀመጠው 1) wayne roony ብሎ ነበር :: አጭር ማብራሪያው ላይ የሩኒ ጤንነት እና በቡድኑ ውስጥ መኖር ለእንግሊዝ እጅግ ወሳኙ ነው ብሎ ካለምንም ማንገራገር ተናግሮለታል ::
ሩኒ ፍርሀት የሚባል የማያቅ ብዙዎች ሲናገሩ እንደሚሰማው ለእርሱ የእሁድ የሰፈር ጨዋታ እና የአለም ዋንጫ ፍጻሜ ጨዋታ አንድ ሆነው የሚሰሙት ለዚህ ልባም ባህሪው የመርሲሳይድ rough hood አስተዳደጉ አስተዋጾ እንዳደረገለትም አበክሮ ይነገርለታል ::
ጆን ቴሪ ስለባህሪው አክሎ ሲናገር " ሩኒ የመጀመርያው ትሬኒንጉን ከብሄራዊ ቡድን ጋር ተጠርቶ ሲሰራ እንደሌሎች ታዳጊ ተጫዋቾች ወደሆአላ አላለም :: እንደውም ከማስታውሰው ያገኛትን ኳስ አምስት የምንሆነውን አተራምሶ በማለፍ ባዶ ጎል ፊት ለፊት ኳሷን አቁሞ ዞር ብሎ ከተመለከተን በኋላ አንጠባጥቦ በሀይለኛ ምት መረቡ ላይ በጠበጣት :: ሁላችንም ባድናቆት አጨበጨብንለት ::"
የሩኒ ባህሪ ከቀን ቀደቀን የመሻሻል ሁኔታ እያሳየ መሆኑ ለሰር አሌክስና ኤሪክሰን መረጋጋትን ፈጥሮላቸዋል :: የሁለቱ ሰዎች በሩኒ ላይ ስጋታቸው አጉል ሰአት በቀይ ካርድ ተባሮ ቡድኑን የሚጎዳ ሁኔታ ይፈጠራል የሚል ነው :: ነገሩ እውነትነትም አለው ኤሪክሰን በተደጋጋሚ ሊቀይሩት የሚገደዱት ደክሞት ወይም ለቡድኑ የረባ ነገር ሳያረግ ሳይሆን ያቺኑ ቀይ እንዳይመለከት ብለው ነው :: ፈርጉሰን በበኩላቸው ሩኒን የመቀየር ባህሪ ባይኖራቸውም ልጁ ደጋግሞ ለቀይ የቀረቡ ስህተቶችን ሲሰራ ይታይ ነበር :: በተለይ አምና ከአርሰናል ጋር ሲጫወቱ ሆን ብሎ በእጁ ኳስ የነካው already ቢጫ የነበረበትን ሩኒ የሚያስወጣው አጋጣሚ ይሆን ነበር :: ዳኛው በዛ ጨዋታ አላግባብ ሩኒን እሹሩሩ ማለታቸው ምንም የማንችስተር ደጋፊ ብሆንም ቅር ብሎኝ ያለፈ ጉዳይ ነው ::

ሩኒ እና አርስናል
አርስናሎች ዌይን ሩኒን ከማንም በላይ ያስታውሱታል :: 2002/03 ሲዝን አርሰናል ወደሰላሳ ምናምን ጨዋታዎች ካለሽንፈት ገስግሶ ባለበት ሁናቴ ከኤቨርተን ጋር ጉዲሰን ፓርክ ላይ ሲጫወቱ ውጤት 1-1 እያለ 80 ደቂቃላይ ስሙ ብዙም ከጋዜጠኞች አፍ ያልዘለል 16 አመት ወጣት ተቀይሮ ገባ :: በነኛ አጭር አስር ደቂቃዎች በልብ ሙሉነት ብቅ ብቅ እያለ ቡድኑን አንዱ ሁለት ኳስ እያስነካ አርሰናሎችን ማስቸነቅ ጀመረ :: አስጨንቆም አልተዋቸውም 90 ኛው ደቂቃ ያገኛትን ኳስ አንዱን የአርሰናል ተከላካይ አሸማቆ በማለፍ ከፔናሊቲ ክልል ውጭ ሩቅ ባሀይል የመተራት ምት ምንም እንኳን ዴቪድ ሲማን ቢንጠራራም አግዳሚውን ነቅንቃ ጎል ከመሆን አላዳናትም :: 16 አመት ወጣት ዌይን ሩኒ ነበር - A STAR IS BORN! ጨዋታውም እንዳለቀ የአርሰናሉ አሰልጣኝ ዌንገር " እስካሁን ካየሁዋቸው እንግሊዛዊ 16 አመት ታዳጊዎች በችሎታው የላቀ " ሲሉ ሳይወዱ አሞካሽተውታል ::
የአርሰናል እና ሩኒ affair በዚ አያበቃም :: መድፈኞቹ አለምን ባስገረም ብቃት ካለምንም ሽንፈት 49 ጨዋታ በሊጉ ሲገሰግሱ 50ኛውን ለመሙላት ወደ ኦልድ ትራፎርድ ማቅናት ነበረባቸው ::በዛን ጊዜ የማንችስተር አቋምና የአርሰናል ብቃት የሰማይና የምድር ያህል የተራራቀበት ጊዜ ነበር :: አርስናሎች አይናቸውን እንኳን ጨፍነው ካለስህተት መቀባብል የሚችሉ የመሰሉበት ጊዜን ነው የማወራው :: በአንጻሩ ማንችስተሮች ደሞ አይናቸው ስር ታላቅ ስርወ መንግስት ሲፈራርስ እየተመለከቱ በትዝታ 90ዎቹን all conquering ቡድናቸውን የሚያስታውሱበት ጊዜ :: እናም አልቀረም "invisible" የተባሉት አርሰናሎች ማንችስተርና ዌይን ሩኒን በኦልድ ትራፎርድ ገጠሙ ::ማንቼዎች በቀይ አሸብርቀው በደንብ "visible" ሆነው ዌይን ሩኒም በሰማያዊው የመርሲሳይደሮች ማልያ ሳይሆን የታላቁ ማንችስተርን ቀይ ማልያ አድርጎ መድፈኞቹን ጠበቃቸው :: ምንም እንኳን ጨዋታው በንትርክ የተሞላ ቢሆንም ዋናው ታሪክ የሚያስታውሰው ትንሹ ልጅ ሩኒ ጎል አስቆጥሮና ሌላ ጎል መንስኤ ሆኖ (ተጠልፎ ሪጎሬ አስገኝቷል ) ማንችስተር ታሪካዊውን የአርሰናል ግስጋሴ ገታ ::

ታሪክ ራሱን ይደግማል ?
ዛሬም ሌላ ቀን ነው :: ቀን ይለወጣል ዌይን ሩኒ ግን ያው ነው ( atleast አርሰናልን ሲገጥም ):: ቼልሲን ዋንጫ ለማስጣል ያለን እድል ቀሪ ጨዋታዎችን እያንዳንዱን ማሽነፍ እንደመሆኑ ለማንችስተር የዛሬው ያርሰናል ጨዋታ ከባለፉት ሶስት ከነሱ ጋር ያረጉት ግጥሚያዎች ወሳኙ ነበር :: ግሩም የማጥቃት እንቅስቃሴ በሁለቱም በኩል የተስተዋለበት ጨዋታ ነበር ብል አላጋነንኩም :: ነገር ግን አሁንም ካርሰናል ጋር ሩኒ stole the show! ታላቅ ተጫዋችነቱን ምርጥ ግብ አግብቶና ለኮርያዊው -ሱንግ ፓርክ እንዲያገባ አመቻችቶ አቀብሎ ቀኑን ለማንቼዎች በደስታ ዘግቶላቸዋል ::
ከመጨረሴ በፊት ግን የኮሎ ቱሬ የግብ ጠባቂነት ችሎታ ለማድነቅ ይፈቀድልኝ ::

አለቀ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አንበርብር

ውሃ አጠጪ

Joined: 09 Apr 2005
Posts: 1090
Location: everywhere

PostPosted: Sun Apr 09, 2006 10:17 pm    Post subject: Reply with quote

አፍሪካ ጥሩ ብለሀል ............ ነገር ቢበዛ በአህያ አይጫንም ነውና ብዙም አልልም ነገር ግን ስላልከው ልጅ ስለ ሩኒ እኔም ትንሽ ልበል ........... በእርግጥ ያለው ጉልበት እና ፍጥነት እድሜው ጋር ሲነፃፀር በጣም አንቱ የሚያስብል ነገር ነው ... ፈጣን እና ጉልበታም ልጅ ነው ........ በጣም የሚያሳስበው ነገር ግን የፀባዩ ነገር ...የዘንድሮውን የአለም ዋንጫ ምን ይበላል በአልከው እና ማን የመጀመሪያው የቀይ ካርድ ሰለባ ይሆናል ላልከው ጥያቄ ዋኒ ሩኒ ነበር የእኔ መልስ .......የሩኒ ፀባይ ሜዳ ላይ ብቻ ሳይሆን ከሜድ ውጭም የሚያደርጋቸው አስከፊ እና የማይጠበቁ ድርጊቶችም አሉት ..............ከዚህ ከዚህ ቢቆጠብና ስፖርታዊ ጨዋነቱን የበለጠ ቢያዳብር ብዙ አድናቂ ሊያተርፍ ይችል ነበር !!!!!!!!!!! ሌላው የዘንድሮው የአለም ዋንጫ እንግሊዝ ልትበላ ትችላለች ለተበላው ..... እንደምክንያትም ሩኒን እዚህ ላይ ማንሳቱ ከዚህ በፊት የነበሩትን የእንግሊዝ ተጨዋቾች ደካማ ነበሩ የሚያስብል ይመስለኛል ........... እንደኔ እንደኔ አንድ እና ሁለት ሰው ጠርቶ ውጤት በነዚህ ምክንያት ይገኛል ማለቱ ውድድሩን ከእግር ኳስ አውጥቶ ወደ ጎልፍ :ዋና እና ቴንስ የሚወስደው ይመስለኛል ............ ስለዚህ በአሁኑ ሰሀት በእግር ኳስ ውድድር ውስጥ ማለት የሚያስደፍረው ከላይ እንዳልኩት የተወሰን ተጫዋቾችን ጠርቶ በእነዚህ ውጤት ይገኛል ሳይሆን አንድ መጥፎ ተጫዋች ካለ በዚህ ምክንያት ሽንፈት ይኖራል ማለቱ ይቀል ይመስለኛል >>>>>>>>>በእርግጥ ወጥን ለማጣፈጥ ቅመም እንደምንጠቀም ሁሉ ኳስንም የሚያጣፍጡ ልጆች መኖር አስተዋፅዖ ሊኖረው ይችላል <<<<<<< ልክ እንደ አርሰናሉ ሄነሪ !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!>>>>>>>>>>>>>
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
rooney

አዲስ

Joined: 31 Aug 2005
Posts: 36
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Apr 10, 2006 9:07 am    Post subject: ኧረ Reply with quote

......አፍሪክ ይመችህ በጣም ይመችህ ....እጅግ በጣም ..... ጆን ቴሪ ያለውን ነገር አንብቤ በጣም ተመችቶኝ ነበር ,......."ሩኒ እኔን ... ከመቶ ጊዜ በላይ ለማለፍ ቢሞክር ከመቶ ጊዜ በላይ ያልፈኛል .... ይሄንን ደሞ እኔ ላይ ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ተጫዋች በማለፍ አሳይቶታል '...ነው ያለው .... በተጨማሪ የሩኒን ዊኒንግ ስፕሪት እወድለታለሁ .... አግሬሲቭ መሆኑንም ጭምር .......... ይሄንን በትላንቱ THE ONE MAN SHOW .. አሳይቶታል .........

..... ኧረ ትላንት ግን የቬንገር frustration በጣም ገርሞኛል ...... ምክንያቱም ሄነሪን ቤንች ሲያረገው .... እኔ ይሄንን ታክቲክ አልለውም ... it is rather frustration....... ግን ተቀይሮ ሲገባ አይቼው ..... መጨረሻ ላይ ሩኒን ለመጨበጥ ... ሲጋፋ ነው ያየሁት ...ቂቂቂቂቂ ........... እንደ ወጌሻ ገብቶ ኩዋስ ሳይነካ ወጣ ......... አሂሂሂሂሂ ....... አስቶንቪላ ላይ ..... እዛው ..... ማንቼ ላይ .... ወጌሻ ነው .....

አንድ ልጨምር ሩኒ አርሰናል ላይ በኤቨርተን ማሊያ ሀይበሪ ላይ ጎል ማግባቱን ... እንዳንረሳ ..... ሚስኪን ቬንገር .. የውሀ መጠጫውን አጨራምቶ ኪሱ ወስጥ ከቱዋት ነበር ... አፍሪክ አስታወስክ ......... he is borned anti arsenal...borned... ይብቃኝ ...

FOREVER AND ALWAYS ONE UNITED
ROONEY
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
Cristiano

አዲስ

Joined: 03 Sep 2005
Posts: 13
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Apr 10, 2006 9:37 am    Post subject: Reply with quote

አፍሪክ ... it really was a very interesting post
እኔ እኮ የሚገርመኝ አንድ 20 አመት ልጅ ጨዋታው ተጀምሮ እስከሚያልቅ ድረስ ሙሉ ሜዳ እየተሯሯጠ እሱ አልበቃ ብሎት ደግሞ አንድ ጎል አግብቶ ሌላ ደግሞ አቀብሎ
የጨዋታው ኮከብ መባሉ ነው :: u can find players like him once in a blue moon!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አንበርብር

ውሃ አጠጪ

Joined: 09 Apr 2005
Posts: 1090
Location: everywhere

PostPosted: Mon Apr 10, 2006 10:12 am    Post subject: Reply with quote

Quote:
..... ኧረ ትላንት ግን የቬንገር frustration በጣም ገርሞኛል ...... ምክንያቱም ሄነሪን ቤንች ሲያረገው .... እኔ ይሄንን ታክቲክ አልለውም ... it is rather frustration....... ግን ተቀይሮ ሲገባ አይቼው ..... መጨረሻ ላይ ሩኒን ለመጨበጥ ... ሲጋፋ ነው ያየሁት ...ቂቂቂቂቂ ........... እንደ ወጌሻ ገብቶ ኩዋስ ሳይነካ ወጣ ......... አሂሂሂሂሂ ....... አስቶንቪላ ላይ ..... እዛው ..... ማንቼ ላይ .... ወጌሻ ነው .....

የዊንገር የትናንቱ አሰላለፍ ሁሉን ያስገረመ ነው !!!!! ነገር ግን አሰልጣኙ ምን እንዳሰበ ከእርሱ ውጭ ማንም ሊያውቅ አይችልም ከመገመት በስተቀር :: እናም እኔ አንድ ነገር ይታየኛል ,,,,,,, የሄነሪ መቆየት በጣም አጠራጣሪ ነው ስለዚህ ዊገር አሁን ፋበርጋስ ጋር የሚግባባ ተጫዋች መምረጥ ይፈልጋል ያንንም ስራውን ትናንት የጀመረ ይመስላል አስተውላችሁ ከሆነ 69 ደቂቃ ፋበርጋስ ሲወጣ ነው ሄነሪን ያስገባው ስለዚህ It is not about frustration man it is something else we don't know but he does>>>>. ሌላው ስለ ሄነሪ ችሎታ እንጃ ደፍረህ መናገር የምትችል አይመስለኝም ትህክለኛ የስፖርት አፍቃሪ ከሆንክ ልታደንቀው ይገባል እንጅ ልታንቋሽሸው አትችልም !!!!!! ሄነሪ 5 ወይም ከዚያ በላይ ጨዋታዎችን እንዳልተካፈለ የሚታወቅ ነው እናም ያም ሁኖ 21 ጎል በማስቆተር ኮከብ ግብ አግቢነቱን ከቫንስትሮይ ጋር በእኩል እየመራ ነው ያለው ...... ያለፈውን አመትም አስታውስ ''''''''''''''''
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
rooney

አዲስ

Joined: 31 Aug 2005
Posts: 36
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Apr 10, 2006 10:58 am    Post subject: Reply with quote

አንበርብር አትሳሳት .......I am always a fan for henry...... i admit zat ...... he is the best player zat i have seen live next to ...... eric cantona.......... he is the best player.......in english premier league these days.....but you know he aquired his talent through practice @ the age of 27 or 26.... but you know ROONEY'S talents are borned.....and he showed you @ the age of 16.... see the difference... borned... and wz practice......... don't compare zem........

ተግባባን ይሄን ያህል ካልኩ አይበቃውም .....ግን ስለ ሄነሪ ደፍረህ ማውራት አትችልም ላልከው .... ለምን አላወራም .... አትሊስት ከማየው ነገር ጋር ማነጻጸር እችላለሁ ...... ገባህ .... ስለ ፕሮፌሽናሊዝም እናውራ ካልን በደንብ እችላለሁ ...... ማለቴ ማነጻጸር ..... ደሞ ስለትላንቱ ጨዋታ ሄነሪን ያየሁት ሁለቴ ነው ..... አንዴ ሲገባ አንዴ ሩኒን ሊጨብጥ ሲጋፋ .... እንዳውም እጁን እስካሁን አልታጠበም አሉ .....

.... ደሞ ስለ ቫኒ አወራህ ....... he is simply a goal scoring machine.... ባይገርምህ ቫኒ ... ከብላክበርን ,ከሲቲ ,ከዊጋን , ከዌስትብሮም ,ከኒውካስትል ,
ከበርሚንግሀም ,ከቦልተን , ጋር ማንቼ ሲጫወት ያለምንም ጥፋት ቤንች ነበር 7 premierleague games.... you see.... ታዲያ ማነው የተጎዳው ቫኒ ወይስ ሄነሪ ..? አንተው መልስ ....

..... እና እባክህ ስለማታቀው ነገር ደፍረህ አታውራ እሺ ....

FOREVER AND ALWAYS ONE UNITED
ROONEY
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
አንበርብር

ውሃ አጠጪ

Joined: 09 Apr 2005
Posts: 1090
Location: everywhere

PostPosted: Mon Apr 10, 2006 11:18 am    Post subject: Reply with quote

Quote:
.... ደሞ ስለ ቫኒ አወራህ ....... he is simply a goal scoring machine.... ባይገርምህ ቫኒ ... ከብላክበርን ,ከሲቲ ,ከዊጋን , ከዌስትብሮም ,ከኒውካስትል ,
ከበርሚንግሀም ,ከቦልተን , ጋር ማንቼ ሲጫወት ያለምንም ጥፋት ቤንች ነበር 7 premierleague games.... you see.... ታዲያ ማነው የተጎዳው ቫኒ ወይስ ሄነሪ ..? አንተው መልስ ....

ታዲያ ሉይስ ሰሀ ከእርሱ በልጦ ስለተገኘ እንኮ ነው ቤንች ላይ የተዘፈዘፈው እንጅ በጉዳት እንዳልሆነ ሀገር ያወቀው ፀሀይ የሞቀው ነገር ነው .................ታዲያ ቫንስትሮይ ከሄነሪ ይበልጣል ነው የምትለው .......... 18 አመቱ ለምትለው ከዚህ በፊት ስለ ሮኒ የተናገርኩ መሰለኝ በዚህ እድሜው ስላለው ጉልበትና ፍጥነት ማንም ሊያደንቀው ይገባል ነገር ግን በእድሜ ማነስ ከመጣን አርሰናልም የያዘው ዋልኮት ምናልባት ነገ ብቅ ብሎ የሮኒን ታሪክ በትዝታ አስቀርቶ ሌላ ታሪክ ሊያመጣ ይችል ይሆናል ግዜን ግዜን ሲተካው ቀሪው ታሪክ ነው እንደሚሉት ...................
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Cristiano

አዲስ

Joined: 03 Sep 2005
Posts: 13
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Apr 10, 2006 12:27 pm    Post subject: ኧረ አንበርብር ! Reply with quote

Quote:

ታዲያ ሉይስ ሰሀ ከእርሱ በልጦ ስለተገኘ እንኮ ነው ቤንች ላይ የተዘፈዘፈው እንጅ በጉዳት እንዳልሆነ ሀገር ያወቀው ፀሀይ የሞቀው ነገር ነው

አሁን እኮ ቁምነገሩ ቫን ማን ስንት ጨዋታ ላይ ነው ያልተሰለፈው ነው እንጂ ለምንድነው ያልተሰለፈው አይደለም :: premierleague ኮከብ ግብ አግቢነቱን እኮ እየመራ እያለ እንዲሁም ጎል ማግባቱን ሳያቁዋርጥ ነው bench የተደረገው :: bench ከተደረገም በሁዋላ እኮ እየተቀየረ እየገባ ያገባል :: ያለፈውን አመት አስታውስ ላልከው ደግሞ ቫን ማን ባለፈው አመት ስንት ጨዋታ እንደተጫወተ እስቲ የዜና መረጃዎችን አገላብጠህ ድረስበት :: ከዚያ አብዛኛውን የአመቱን ክፍል በጉዳት ምክንያት እንዳልተሰለፈ ትረዳለህ :: ኧረ ጎበዝ keyboard መጠቀም ስለቻልን ብቻ ዝም ብለን ትርኪ ምርኪ አንጻፍ !
እናስተወል እንጂ ጎበዝ !!!!!!!!

አንበርብር ...ደህና እደር !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወሮበላው

ዋና ኮትኳች

Joined: 17 Oct 2004
Posts: 668
Location: united states

PostPosted: Mon Apr 10, 2006 2:40 pm    Post subject: ...FOREVER UNITED... Reply with quote

.....ከሁሉ በማስቀደም ለአፍቃሪ ማንቼዎች አንኩዋን ደስ አለን እላለው .....ምስጋናይዬ ደሞ በነዛ አፍላዎቹ ዘመኖቼ በኩዋስ ክህሎቱ መስጦና አስደምሞ ከማንቼ ጋር አጣምሮኝ ለቀረው ታላቁ cantona !!! ... merci beacoup !!!
አንበርበር ....እንደታዘብኩት ከሆነ እወንትን የምትሸሽ ይመስለኛል ...ሄነሪ 5 ጨዋታዎቺን ሳይካፈል ቫኒስትሮይ እኩል በጎል የመራል አልክ ..rooney ደሞ አንተ 5 ትገረማለህ ቫኒስተሮይ 7 ጨዋታዎች ሳይካፈል አይደል እንዴ አለህ ...አንተ ለዚህ መልስ ላለመስጠት ወይም ላለመረታት ...ሰሀ ስለበለጠው ምናምን ትላለህ .....
ይመስለኛል የትላንቱ ሽንፈት አዙሮብሀል ....አይዞህ ....አየር ወሰድ ተረጋጋ ...ማንቼ እስካለ ደረስ እንደዚህ አይነት ከስተት አይቀሬ ነው ....!!!!

.......FOREVER UNITED......!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia