WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
***የየጁ ኩማንዳ ጠባ ልጆች ***
Goto page Previous  1, 2, 3, ... 13, 14, 15  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

View previous topic :: View next topic  
Author Message
እሪኩም

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Apr 2005
Posts: 981
Location: ወሎ

PostPosted: Sun Oct 01, 2006 11:35 am    Post subject: የጁ እና ቁንጅና Reply with quote

ሠላም የጁ እና ታዳሚዎች !

የጁ እና ቁንጅና

ውጫሌን አልፌ ውርጌሳ ስገባ :
አለባቸው ተካ ነበር የተቀባ ::

ሊብሶ ሱዳን ሰፈር ደረስኩኝ መርሳ :
ውበት ማድነቅ ብቻ ተፈሪ አይረሳ ::

ስሪንቃን አድንቄ ስወጣ አቀበቱን :
በስተ ግራ በኩል አየሁ ኃይሉ አባተን :
በክብር ተኝቶል ተማርኩ ጀግንነትን ::

አፋፉ ላይ ሁኜ ሳይ ወልዲያን :
ጨዋታ ለማዬት እንደዚህ ልሁን ::

ቲንፋዝ ውስጥ ስገባ ጐዳናን አልፌ
ሸሁ ታዬ አሉ ልፈወስ አርፌ :
ችግርን ሲፈቱ - ሞቱ - በደርግ መርፌ ::

.............ይቀጥላል

መልካም ጊዜ
እሪኩም ከቦሩ ሜዳ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የጁ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 28 Sep 2006
Posts: 66

PostPosted: Sun Oct 01, 2006 8:44 pm    Post subject: Reply with quote

ሠላም ያገር ልጆች !!

ወንድሜ እሪኩም "አለቤ " ቢሞትም ሥራዎቹ ህያው ሆነው ይኖራሉ የጁ አሁንም ቢሆን እንደነ መፋቅር ድንቁ የመሳሰሉትን ኮትኩታለች ::

ከታላቅ አክብሮትና ፍቅር ጋር ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሽማግሌው

ዋና ኮትኳች

Joined: 08 Nov 2003
Posts: 584

PostPosted: Mon Oct 02, 2006 2:26 am    Post subject: Reply with quote

ኦነግ ወሎ የኦሮሞ ሀገር ነው : ሀበሻው ወራሪ ነው ይላል ::
ማፓቸውን ብታዩት ወሎን ይጨምራል :: ወሎዬዎች ምን ትላላችሁ ለዚህ ምላሽ ? እውነት ወሎ የኦሮሞ ሀገር ነው ?
አንድ ወሎዬ ሲያጫውተኝ ወሎ አማራ ነው : ያሉት ኦሮሞዎችና የኦሮሞ ስም ለከተሞች የሰጡት የወራሪው የግራኝ አህመድ ጀሌዎች ናቸው ብሎኝ ነበር :: እውነቱ የትኛው ነው ?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እሪኩም

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Apr 2005
Posts: 981
Location: ወሎ

PostPosted: Mon Oct 02, 2006 8:36 am    Post subject: አንድ ኢትዮጵያ Reply with quote

ሠላም ሽማግሌው !

[quote="ሽማግሌው "]ኦነግ ወሎ የኦሮሞ ሀገር ነው : ሀበሻው ወራሪ ነው ይላል ::

ጨዋታውን አደበላለከው ጃል :: ፍየል ወዲያ ቁዝምዝም ወዲህ እንደ ማለት ነው :: ለማንኝውም ካለቦታው የሰነዘርከውን ሃሳብም ሆነ አሉባልታ ዋርካ ፖለቲካ ውስጥ ብታስቀምጠው እና ብትወያይበት ይሻላል ::

ኦሮሞ አማራ ትግሬ ጉራጌ ወላይታ ሲዳማ አፋር ጋምቤላ ሶማሌ ወዘተረፈ - ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች - ኢትዮጵያ ከዳር እስከ ዳር አገራቸው ነው :: ማንም ሊከለክላቸው አይችልም :: እደፈለጋቸው መንቀሳቀስ መኖር መውለድ እና መክበድ ይችላሉ ::

ሽማግሌው - እንደ ስምህ ምራቅህን የዋጥክ መስሎኝ ነበር :: ነገር ባትጭር ጥሩ ነው ::

ከአክብሮት ጋር
እሪኩም ከቦሩ ሜዳ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሽማግሌው

ዋና ኮትኳች

Joined: 08 Nov 2003
Posts: 584

PostPosted: Mon Oct 02, 2006 7:54 pm    Post subject: Reply with quote

እሪኩም ምነው ነገር ነገር አለህ ልጄ ? ጥያቄ መጠየቅ ነገር መጫር የሆነው ከመቼ ጀምሮ ነው ?
እስኪ ደሴ የት እንደተቀመጠች ማፑን እይና ንገረኝ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እሪኩም

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Apr 2005
Posts: 981
Location: ወሎ

PostPosted: Mon Oct 02, 2006 9:25 pm    Post subject: ሠላም ለኢትዮጵያ Reply with quote

ሠላም ሽማግሌው !

የነበረው የኢትዮጵያ ካርታ እና ክፍላተ ሃገራት :

በአሁኑ ሰአት የኢትዮጵያ ካርታ እና ክልሎች :

አሁንም ቢሆን ያልተረዳኽው ነገር አለ :: የኦነግን ካርታ አምጥተህ ከምታሳያኝ እና ከምትለጥፍ - ዓለማም - ዐጠፋም - የወቅቱን የኢትዮጵያ መንግሥት ካርታ ብታስቀምጥልኝ ደስ ይለኝ ነበር :: ለማንኛውም ቸር ይግጠምህ ::

የፖለቲካ መድረክ አናድርገው :: በዚህ የተነሳ ብዙ ማውራት አልፈልግም ::

ከአክብሮት ጋር
እሪኩም ከቦሩ ሜዳ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እሪኩም

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Apr 2005
Posts: 981
Location: ወሎ

PostPosted: Tue Oct 03, 2006 8:03 am    Post subject: Reply with quote

ሠላም የጁ !

ለመሆኑ መፋቅር ድንቁ እና ሮመዳን እንዲሁም ሌሎች ነባር ከያኒዎች አሉ ወይ ? በመጠኑም ቢሆን አጫውተኝ ::

መልካም ቀን
እሪኩም ከቦሩ ሜዳ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የዜናዊ ልጅ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 27 Aug 2006
Posts: 55

PostPosted: Tue Oct 03, 2006 9:53 am    Post subject: Reply with quote

ሠላም ውድ እሪኩም !

ከረጅም አመታት በፊት የወልድያ ከተማ የኪነት ጓድ ጋር ይሰሩ የነበሩት መፋቅር ድንቁና ሮመዳን አሁንም በህይዎት አሉ :: መፋቅር ድንቁ ባሁኑ ሳአት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር ውስጥ ሲሰራ ሮሜ ለጊዜው አዲስ አበባ እንደሚኖር አስታውሳለሁ ከዚሁ ከወልድያ የኪነት ጓድ ጋር የማልረሳቼው ሰዎች ሲሳይ አሰፌ ,ነጋሽ ፈለቀ ,ግርማ ከበደ ,ጫልቱ ዘውዴ ,አቻምየለሽ ጫኔ ,አለማየሁ አስረስ ,ንጉሴ በሪሁን ወዘተ የወልድያ እንቁ ልጆች ነበሩ ::

ከታላቅ አክብሮትና ፍቅር ጋር ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እሪኩም

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Apr 2005
Posts: 981
Location: ወሎ

PostPosted: Tue Oct 03, 2006 10:03 am    Post subject: Reply with quote

ሠላም የዜናዊ ልጅ !

በጣም አመሰግናለሁ :: በትዝታ ወደ የጁ - ወልዲያ - ወሰድከኝ ጃል ::

መልካም ቀን
እሪኩም ከቦሩ ሜዳ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሀዱድ

ኮትኳች

Joined: 08 Jan 2004
Posts: 367
Location: uk

PostPosted: Tue Oct 03, 2006 11:23 am    Post subject: Reply with quote

ቅቅቅቅ እሪኩም እንዳትቆጣኝ እንጂ የጁ እሳት ይዞዋል በእጁ ማለት ምን ማለት ነው ?

ደሴ ዳውዶ ሆጤ አይጠየፍ ቤቴ
ገራዶ ኮምቦልቻ የጁ ጎረቤቴ
በፍቅር ልሞት ነው ደከመ ጉልበቴ

አንተ የወሎልጅ ጠንበለል ሸበላ
ቆዳህ ለስለስ ያለ ከንፈርህ ወለላ
እኔ ካንተ እርቄ እህልም አልበላ

ልታጠን በሪኩም ልታጠን ባደስ
ልቀባ ልኩዋኩዋል የክቴን ልልበስ
ወደቤት ሲመጣ ልቡ እንዲለው ደስ

አምባሰል ገራዶ ቆንጆ እያፈለቀ
የጁ እራያ ቆቦ በቂቤ በአደስ እየተጠመቀ
ልቤ ማለፍ ሳይችል ሀይቅ ላይ ወደቀ

አንተ የሀይቅ ልጂ ልቤን እዋኝተህ አምጣ
በአንገትህ ማተብ ባጠለቅከው ቁምጣ
ያሳ መረቅ ይዘህ በህልሜ እንዳትመጣ

ያለማጣው ጉብል ጊሊ የታጠቀው
ጉራማይሌ ጥርሱን ፈገግ ቢያደርገው
ልቤን ህሊናየን የሱ ምርኮ አረገው

ወይ የወሎ ልጆች እውዳችሁዋለሁሁሁሁሁሁሁሁሁ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እሪኩም

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Apr 2005
Posts: 981
Location: ወሎ

PostPosted: Tue Oct 03, 2006 12:07 pm    Post subject: እየመጣሽ ቃኚን Reply with quote

ሠላም ሀዱድ !

የጁ እሳት ይዟል በእጁ - ለሚለው ሰፋ ያሉ መግለጫዎች ከየጁ እና ከሌሎች ታዳሚዎች እስከሚገኝ ድረስ በአጭሩ እንደዚህ ለመመለስ እሞክራለሁ ::

የጁ አውራጃ ሁለት ወረዳዎች አሏት :: ሓብሩ እና ጉባላፍቶ ::

ለቀዳማዊ /ስላሴ መንግስት አገዛዝ አመች ያልሆኑ መሳፍንት መኳንንት እና ነፍጠኞች የፈለቁባት አውራጃ ስለነበረች በጥቅሉ ህዝቡን መዋጋት እና ማስተዳደር ስላልተቻለ "የጁ እሳት ይዟል በእጁ " በማለት ኃይለ ስላሴ እና መሰሎቻቸው ተናገሩ - ተነበዩ :: የጁ ለሠላም እንጂ ለጠብ አይመችም ::

አንቺን እኔ አይቼ መቼ እለቅሻለሁ :
አሸን ክታብሽን ሃራ አስጥልሻልሁ ::

ብቅ ብለሽ አጫውችኝ ለምን ትፈሪአለሽ :
መጎንተል አልችልም እስቲ ልጠቃቅስሽ :
መርሳ አባ ጌትዬ - አሉልሽ አይዞሽ ::

በይ አትጥፊ - እየመጣሽ - ቃኚን
እሪኩም ከቦሩ ሜዳ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የጁ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 28 Sep 2006
Posts: 66

PostPosted: Tue Oct 03, 2006 2:50 pm    Post subject: Reply with quote

ሠላም ያገር ልጆች ! ከላይ እሪኩምን ሀዱድ በጠየቀችው መሰረት የጁ እሳት ይዟል በዕጁ ለሚለው በሚቀጥለው ጠይቄ እስክመለስ በእሪኩም ሃሳብ እንቆይ :: በዚህ አጋጣሚ ሀዱድ እንኳን ደህና መጣሽ እኛም የየጁ ልጆች እንወድሻለን !! አምባሰል ለገደል ምን ያሽሟጥጡታል ፈረስ ባይወጣበት ልጅ ይወጣበታል ::

ወዳጄ የሮያል ልጅ :)...... ከላይ የጠቀስካቼው ሰዎች እንዳልከው የወልድያ ብርቅዬ ልጆች ናቸው መምህር ሲሳይ አሰፌ የወልድያ የኪነት ጓድ አስተዋዋቂ ነበር :: ንጉሴ በሪሁን (አባቱ በሪሁን ደገኛ ) የተባሉት ግን ወደ ደጋው ስለሚኖሩ ይሆን ? በነገራችን ላይ ደገኛ የሚባሉት ሳንቃ ቀበሮ ሜዳ ጃርሳ እና አካባቢው የሚኖሩትን ህብረተሰብ ነው አካባቢው በጣም ቀዝቃዛ ነው ::

እስቲ ዛሬ ደግሞ "ሀራ " ስለምትባለው አገር ትንሽ ልበል ሀራ ከወልድያ 30 ኪሎ ሜትር አካባቢ እርቃ የምትገኝ ከተማ ናት ሞቃት የአየር ጸባይ ያላት ቆላማ ቦታ ናት ባለፈው ስራተ ማህበራት እምብዛም ያልበለጸገች ብትሆንም አሁን ግን በንግዱ አለም የወደፊት ታላቅ ተስፋ የተጣለባት ከተማ ሆናለች ..... ምናልባትም ጅቡቲን የሚያገናኘው የባቡር መስመር ከተከፈተ ባካባቢዋ ላሉት መንደሮች አስማት ትርጓሜ ባውቅ ምንኛ ደስ ባለኝ ቆርኬ , ቂላዳሜ , አላሌ ሱቡላ , ጎመጅ , እና ሌሎች :: የሀራ ልጆች ቡርሽጥ የሚባለውን የውበት ማድመቂያ እጃቼውን እና እግራቼውን በመሞቅ ይዋባሉ :: ከዚሁ ጋር እዚሁ ወሎ ክፍለሃገር ቃሉ አውራጃ ውስጥ ባቲ አካባቢ የሚገኙ ሴቶች ቦሎቂያ ሰውነታቸውን ይታጠናሉ ይህም ጥሩ መአዛን እንደሚሰጥ ይነገራል እንዲሁም አንቻሮ አካባቢ ብርጉድ የሚባለው ጢስ መልካም ጠረን እንዳለው ይነገራል እስቲ ስለዚህ ዕውቀቱ ያላችሁ አሳውቁኝ :: ሀራ አካባቢ ከሚበቅሉ ፍራፍሬዎች በደና እና እንኮይ የማይረሱኝ ጣፋጭ ፍሬዎች ናቼው ::

ከታላቅ አክብሮትና ፍቅር ጋር ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዶኑ

ኮትኳች

Joined: 01 Apr 2005
Posts: 463

PostPosted: Tue Oct 03, 2006 9:39 pm    Post subject: Re: ***የየጁ ልጆች ብቅ ብቅ በሉ *** Reply with quote

የጁ እንደጻፈ(ች)ው:
እንጀራው መርሳ ላይ እየተጋገረ !
ወጡ ጉባላፍቶ ሲሼተኝ አደረ :

ሰላም ያገር ልጆች ! ፍቅርና ሰላም ከናንተ አይጥፋ እያልኩ ""ወልድያ "" ጣይቱ ብጡል መልካ ቆሌ እና ሁለተኛ ደረጃ /ቤት የተማራችሁ እስቲ እዝች አለን በሉን :: አምዱ ሁሉንም ያሳትፋል ::

ከታላቅ አክብሮትና ፍቅር ጋር

ሰላም የጁዬ

'ወሎ ሲገቡ ለቅሶ ሲወጡም ለቅሶ " ........ትክክል !
ትዝታዬን ቀሰቀስክብኝ .......ወይ ደብረ ገሊላ ! ወይ አዳጎ ! እረ ስንቱ እረ ምኑ ?
የወሌ ብጡል ሀገር ! ወይ ነዶ !!

ወሌ ...ወሌ ወሌ ቢሏችሁ :
የውረባቦ እንዳይመስሏችሁ !
የእሳቱ ጉማጅ መርጦ አለላችሁ ..

መርጦ ኢየሱስ የጁን በየጁንትዋ ይጠብቃት !

አሜን !!
_________________
TO DOUBLE YOUR JOY DIVIDE IT BY TWO
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሀዱድ

ኮትኳች

Joined: 08 Jan 2004
Posts: 367
Location: uk

PostPosted: Wed Oct 04, 2006 12:57 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም እሪኩም ጥያቄየን ስለመለስክልኝ አመሰግናለሁ
ያው የጊዜ ነገር ታውቃለህ አይደል
በርቱ ተበራቱ እንደገና ብቅ እላለሁ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የመንደራው

ኮትኳች

Joined: 05 Oct 2006
Posts: 189

PostPosted: Fri Oct 06, 2006 11:24 am    Post subject: Reply with quote

ያገሬ ልጆች እንዴት ናችሁ ? ጨው ሪጋ ሙጋድ አባዲንሳ እስላም ቀበሌ መልካ ቆሌ ሜዳ መቻሬ ሜዳ ወልዲያ ውስጥ የሚገኙ የሰፈር ስሞች ናቸው ::

እነ ብሮቤን ንጉሴ ታከለ ወሎ ሀብተማሪም ከስፖርቱ የሚያውቅ ሰው ይኖር ይሆን ?

ስለቦለቅያ ለጠየቅከው ልጅ

ቦለቅያ በቤት ውስጥ ጉድጓድ ይቆፈርና በጭቃ ትንሽ ቤት ነገር ይሰራል :: ወይራ ሰበንሳ ቆራስማ የመሳሰሉ ጥሩ ሽታ ያላቸው እንጨቶች (እርጥቡ ) ጉድጓዱ ውስጥ ይገባል :: ከዛ ፉም እሳት ይጨመርበታል :: እንጨቱ መጨስ ሲጀምር ሴቷ ከወገቧ በታች ያለውን ሰውነቷን ጉድጓዱ ውስጥ ትከተዋልች እሙሙዋ በጭሱ ትክክል መሆን አለበት :: ራቁቷን ሆና በብርድልብስ ነው የምትጠቀለለው :: ከዛ ላብ በላብ ስትሆን ትወጣለች ::

እሙሙው ጠበቅ እንዲል ያደርገዋል ወዲያው ያገኘው ምን ብየ ልንገርህ

አንተ አሹለህ ስትለቅበት እሱ እየጠበቀ እንቅ ነው :: እንተ ምንጭቅ እያደረግክ የተፈጠረበትን እስኪጠላ ድረስ አሳሩን ማሳየት ነው ::

ብዙ ጊዜ አዲስ ያገቡ ሴቶች ይጠቀሙበታል ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, ... 13, 14, 15  Next
Page 2 of 15

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia