WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የቦሬ ልጆች በዋርካ ጥላ ስር :
Goto page Previous  1, 2, 3, ... 64, 65, 66  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ወቤ (ጃሎ )

ኮትኳች

Joined: 28 Jul 2004
Posts: 201

PostPosted: Sun Oct 22, 2006 11:33 pm    Post subject: Reply with quote

እንደምን አላችሁ ? ወዳጆቼ !
የዚህን አምድ መጀመር ከሰማሁ የቆየሁ ቢሆንም ወዲያው ለመጻፍ በጊዜ እጥረት አልቻልኩም ነበር :እና በጣም ነው ደስ የሚለው ምክንያቱም ብዙ ሰው ያቀራርባል , የማናውቀዉን ያሳዉቃል ,ብዙ ያለፉ ትዝታዎችን እንድናስታዉስ ይረዳል ,ሌላም ,ሌላም !
አምዱን ለጀመርከው ለተሳታፊዎች ምስጋናዬን እያቀረብኩ በርቱ እንበርታ እላለሁ :: እንዲሁም ብዙ ልጆች በተለያዩ የዉጪ አገሮች አገር ቤት ያሉትን በማሳወቅ በሰፊው እንዲሳተፉ የማድረግ ሀላፊነት የሁላችንም ነዉና ላልሰሙት እናሰማ !!!
ወንድሜ ቺኮኩባኖ =በግል የላክልኝ መልእክት ምላሽ ወዲያው ልኬያለሁ ደረሰህ ወይ ?
ሌሎች ጉዳዮችን ይዤ እመለሳለሁ ::
ቸር ይግጠመን !!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
ቺኮኩባኖ

ኮትኳች

Joined: 14 Sep 2006
Posts: 259
Location: usa

PostPosted: Mon Oct 23, 2006 5:02 am    Post subject: Reply with quote

ማርና ወተቴ እንዴት ንህ ወዳጄ ? ይቅርታ ጠፋሁ
ትንሽ የቆንቆ ነገር ሆኖ ብኝ ነው
እንዳልከው ሳህለማርያም በጣም ቀልደኛ እና ተጫዋች ነበር አፈሩን የቅለለውና
ማርና ወተቴ ላልካቸው ቅጽል ስሞች እኔ እማውቃቸው ወይንም ከቦሬ ከወጡ በሁዋላ የተሰጣቸው ግዛቸው [ቂንጨ ]
ሙላቱ [አዋሽ ] ከፍሌ [ግራ ] መላኬ [ቁልባ ]ሴይፉ [ጥቁሪ ]አሳየ [ሞርኮታ ] በአንድ ወቅት አስቸጋሪ ከነበረው ዘራፊ ጋር አመሳስሎ ሰይፉ ነው ያወጣለት ሲሳይ [ባንጋ ]ሌሎቹን ደግሞ ሳስታውስ እከትበዋለሁ ቦሬ በጣም የሚወደዱ እና የስራ ፍቅር ያላቸው ልጆችን ያፈራች አገር ናት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Tue Oct 24, 2006 4:37 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ;;አንድ ወንድሜ ዛሬ ደውሎልኝ ምነው የዛን ሁሉ ቅጽል ስም ስታነሱ አስማማው ጦሳን ረሳችሁት ብሎኛል ;;እኔም እኔን ይርሳኝ ብያለሁ ;;ከሁሉም ያሳቀኝ ግን ከሰለሞን አየለ ስለቦሬ ሰዎች እያነሳን ስንጫወት <<እባክህ ሽብሩ በህይወት ይኖር ይሆን እንዴ ?>>ሲለኝ እኔም ስሙ ስላልመጣልኝ ሽብሩ የቱ ስለው ተቀርጥፈሽ ውጪ እያለ ጫት የሚሸጠው ነዋ ሲለኝ ሳቄን ማቆም አልቻልኩም ;;ወቤ ጃሎ ስለዚህ ሰው የሆነ ነገር ጀባ እንደሚለን እምነቴ ነው ;;

ቺኮኩባኖ አሳየ -ሞርኮታ መባሉን አሁን ካንተ ነው የምሰማው ;;ይገርማል ;;እኔ እያለሁ አባ ገዳ እያሉ ነበር የሚጠሩት ;;የሙሌ የሚገባው ስም ነው ;;አሁንም ያው እዛ ዲፖ (ድራፍት መጥመቅያ ) እየሄደ አዋሽ እንደሆነ ነው የሚመለሰው ;;

በዚህ አጋጣሚ ብዙ የማውቃቸውን ልጆች እያነሳህ ስለሆነ ከነሱ ስለማይለየው ኮንጎ ምን ትላለህ ;;አንዴ ዲቪ ሞልቶ እንዴት ነው ይደርሰኝ ይሆን እንዴ ብሎ ሲጠይቀኝ ዘንድሮ የሞላ በሙሉ ለመጨረሻ ግዜ ስለሆነ ሁሉም ይወጣለታል ብየው የጋበዘኝን ግብዣ አልረሳውም ;;ቸር ያሰንብተን ;;አንተ ከባ ማንበብ ብቻ አይደለም ከትብ እንጂ ?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ማርና ወተቴ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 13 Oct 2006
Posts: 72
Location: england

PostPosted: Wed Oct 25, 2006 12:19 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ወገኖች !እንደምን ሰነበታችሁ ?በእውነቱ የቅጽል ስሞች ጉዳይ በጣም ነው ያሳቀኝ ; በተለይ ሰይፉ ምን ቢያደርገው ነው ለአሳየ እንዳለ ሞርኮታ የሚል ስም የሰጠው ? በተክለ ሰውነት አሳየ ረዥም ወፈር ያለ ሲሆን , ሞርኮታ ደግሞ ቀጠን ያለና አጭር እንደሆነ ነው እና እንድ የተደበቀ ሚስጥር አለና (የስም አወጣጡ ) ማለቴ ነው ቺኮ ኩባኖ እንደምታጫዉተን ነው :;እረ የሙላቱ ተሾመ (አዋሽ ) መባልስ ? ከዉሀ አወሳሰድ ጋር በተያያዘ ነው ወይስ አዋሽን በዋና ስለአቍረጠ ነው ?
የክፍሌ ተሾመ ደግሞ ሁሌ ትዝ የሚለኝ ጣቶቹን ብር እንደሚቆጥር ሰው ዝም ብሎ የሚያንቀሳቅሰው ሲሆን , የኮንጎ የሰማሁት ደግሞ አይሱዙ መኪና እንደገዛ አሉ ምንም ልምምድ ብዙ ሳይኖረው የራሱን መኪና ከቆመበት አንስቶ እንደ አጥፍቶ ጠፊዎች ከትልቅ ዛፍ ጋር አጋጭቶ ከፍተኛ ጎዳት ማድረሱ የአንድ ወቅት ዜና ነበር ::
ነፍሱን ይማረዉና ሳህለማርያም በአንድ ወቅት ዉሀ ወሳስዶ ከመሸ ወደቤታቸው ግቢ ይገባና ዛፍ ላይ ወጥቶ አልወርድም ይላል : ከዚያ አባቱ ደጋግመው አትወርድም !አትወርድም !ይሉና መጥረቢያ አምጡ !መጥረቢያአምጡ !ሲሉ , ምናልክ አባቱን ,መጥረቢያ አምጡ !እቺን ዛፍ ንካና የመንግስት ደን በመጨፍጭፍ ጸጉርህን ተላጭተህ ትገባታለህ ብሎ በወቅቱ የነበሩትን ሁሉ አስቋል አሉ ::
በተረፈ በግል አድራሻዬ የላካችሁ ልኝ ልጆች እያመሰገንኩ እባካችሁ እየገባችሁ በቅርቡ እንደምትሳተፉ
አምናለሁ ::
ሽብሩን እኔም አዉቀዋለሁ ወደፊት ስለእሱም ሆነ ስለ ብዙ ጉዳዮች እያነሳን እንጫወታለን \!!
ወተት =በቡቂ (ቆራሱማያለው )=
ማር =በመርመሮ (አነስተኛ ቆርቆሮ )ወይም ድሮ በኮባ ቅጠል ሁሉ የማር ሰአት ሲደርስ በሳንቲም ቤት እየገዛን በዳቦ የሚበላዉን
የተለመደ የቦሬን ሰነፍ ቆሎ
ጋብዤያችኋለሁ !!!!
_________________
az
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ሳኚናማ

አዲስ

Joined: 25 Oct 2006
Posts: 36
Location: ethiopia

PostPosted: Wed Oct 25, 2006 4:30 pm    Post subject: Reply with quote

በርቱ ,በርቱ ጥሩነው ብዙትዝታ እንለዋወጣልን
በውነቱ ያሳዝናል ታደስ መሞቱን አልሰማሁም ነፍሱ ይማር
ቡሩንዶ የሚል ስም የወጣለት ዱሮ ቂጡ ቀዳዳ ያለው ቦጌ ቁምጣ ይለብስ ነበራ ቀይ ስለሆነ በቀዳዳ የሚታየው ቂጡ ቀይ ቡሩንዶ ስጋ ይመስላል ተብሎ ነው የወጣዉ
በታም ያሳቀኝ ሽብሩ መነስቱ ነው ,ወቢ ስለሱ ይበል ነው የተባለው ስለዚ ይቅር ከኔ የበለጥ ደንበኛው ነበረ
ስለቅጽል ስም እንም ልበል
አስማማ ሰይፉ -ጦሳ ማር ይነግዳል 1ኪሎ በላይ ማር ባንዴ ይበላል አዋሽም ነው
ዮናስ /ማርያም -ቡታ (ዛሎዲን )የሪህ መዳኒት ነው
አማረ እንዳለ -nto (ብሄራዊ አስጎብኚ )አዲስ ሰው ቦሬ ከመጣ ከሱ ጋር ነው ሚታይ
ተስፋዬ -ቀጮ
ጽጋዬ -ሞፎ
ሳሙኤል ሰሙ -ጭንቁ
በሌላ እንገናኝ
ሁላችሁ ሰላም ብያለሁ (ይቅርታ [/quote]
_________________
as
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Visit poster's website AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ነጭ ማር

አዲስ

Joined: 15 Oct 2006
Posts: 46
Location: america

PostPosted: Thu Oct 26, 2006 12:23 am    Post subject: Reply with quote

ጤና ይስጥልኝ :: ሰኚ ናማ እንኳን ደህና መጣህ እላለሁ ::ቡታን ስታነሳ አንተ እንዳልከው ቡታዞሎዲኑ ትዝ አለኝ ;;ይገርምሀል የገበያ ቀን ሲያልቅበት ነፍሳቸውን ይማርና ከአባባ አኪሊሉ ላይ ሁሉ ሄዶ ይበደርና ይሸጥ ነበር ;;አሁን ያለሁበት ሀገር ሆኜ ቡታዞሎዲን እጅግ እጅግ በጣም የተወገዘ የተከለከለ መድሀኒት መሆኑን ስሰማ ዮናስ ስንቱን ሰው እግራቸውን ቆልምሞ እንዳስቀረ እራሱ ይቁጠረው ::

ሌላው ስለሽብሩ ሲነሳ ምንግዜም የማልረሳቸው ቢአርንና ቡጡን ነው ;;ልክ እነሱ ሲመጡ የሽብሩ አንካሴ ካብደላ ቆቆር ቤት ጠረቤዛ ስር ብቅ ትላለች ::እስከቅርብ ግዜ ድረስም ሽብሩ እነሱን ሲያይ በሽታው ሁሉ ነበር የሚነሳበት ;;እንደሚመስለኝ ያልከፈሉት የመልጋኖ ጫት ወይም ሌላ እነሱ የሚተዋወቁበት ነገር ይኖር ይሆናል ::

ሙሽተሪን ደግሞ አሚር ቦጃ (መርድን )ሲመለከት የፈታውን ሀቃራ ማሰር ይጀምራል ;;ልክ አጠገቡ ሲደርስ ቦጃ መጣህ ?ላጥናፉ ሳልነግርልህ ከአጠገቤ ጥፋ ሲለው እራሱን ማከክ ይጀምራል ::.......እንመለሳለን ::እስከዚያው ድህና ሁኑልኝ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ማርና ወተቴ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 13 Oct 2006
Posts: 72
Location: england

PostPosted: Thu Oct 26, 2006 8:01 pm    Post subject: Reply with quote

ሳኚ ናማ እንኳን ደህና መጣህ , ቤት ለእንግዳ ብያለሁ :
ስለ ሽብሩ ብዙ ተብሏል እኔም ትንሽ ለመጨመር ከመልጋኖ ጫት እያመጣ በመሸጥ የሚተዳደር ሲሆን ትንሽ የጤና ችግር አለበት ,ብቻዉን ይነጋገራል :ዝም ካለም እሱን ለማነሳሳት አንዱ ----<አረጋሽ >ብሎ ካለ <ተቀርጥፈሽ ዉጭ ,አቃጣሪ >ምናምን እያለ ፊቱን እያጣመመ ያነበንባል ::
በእዉነቱ እኔ እስከማዉቀው ድረስ ከሽብሩ ማንም ሰው ጫት የሚሰርቀው አልነበረም :ሌላው ጠና የተባለ ሰው እንዲሁ በፈረስ ጫት እየጫነ የሚመጣ (መምህር ተስፋዬ /ጊዮርጊስ )በረንዳ ላይ የሚሸጥ ነበር ;ብዙ ሰው እንደሚያታልለው አዉቃለሁ ;
ታዲያ አንዴ አቶ ጠና አንዱን ጀንብ (ግማሽ ጥቅሉን )ከፈረስ አዉርዶ ወደ ተስፋዬ ቤት ሲያስገባ ፈረሱ አጠገብ ዉጭ የቀረዉን አንድ ጀንብ ጫት ,ገዛኸኝ ማሞ (ፌጮ )ተሸክሞ ይሮጣል ;እኔና ሸዋንግዛው በቀለ ከርቀት አይተን ተከተልነው ትምህርት ቤት አንዱ ክፍል ዉስጥ እንደሚሆን አደረግነው ; ግማሹን እንዳይሸጥ ወሬው ተሰምቶ እያዛለሁ ብሎ ፈራ :ታዲያ ምን ያደርጋል የኛ ጉንጭ ተቆራርጦ አለቀ ....የልጅነት ነገር !
የቅጽል ስም ነገር ከተነሳ እስኪ እኔም ማስታዉሰዉን ትንሽ ቀደም ያሉትን ላንሳ ::
ገዛኸኝ ማሞ ማዳ -(ፌጮ )
ገዛኸኝ ማሞ ወልዴ (ጡጢ )
ናስር አብዲሽኩር (ጮራ )
ሰለሞን አየለ (አዮ )
ሙህዲን ከማል (ኤኬራ )
አስታጥቄ ካሳ (አንጉዬ )
ጌታቸው ታደሰ (ቀንጢና )
ፋንቱ በቀለ (ፋንቱ ደጌ )
ታምራት ቦጋለ (ቡላ )
መክብብ አየለ (ሱባ )
ዮሴፍ /መድህን (ቡባ )
ጌታቸው ብዙነህ (ቀጨሊ )
ሙሉጌታ አጥናፉ (ዩሪ )
በሀይሉ /መድህን (ቁሮ )
ከድር ከማል (ሞኙ )
በጋሻው አያኖ (ኩርኬ )
አባተ ካሱ (ጫኪሌ )
ስንታየሁ ካሳ (ቾንቤ )
ሲሳይ ተፈራ (ጩሉቃ )
ሙሉጌታ ለማ (ሻንቆ )
ጌታቸው ዘርፉ (ኮቶላ )
ተረፈ ደስታ (ደብል )
አበባየሁ መታፈሪያ (ሆኮላ )
ተሾመ ንጉሴ (ቀንጦ )
ጋርሴ ቀሬ (አኒቻ )
ካሱ ታምሩ (ሞራ )
______
ብዙ እንዳሉ ነው ማስታወስ አቃተኝ (ደከመኝ )
_________________
az
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Fri Oct 27, 2006 4:07 am    Post subject: Reply with quote

ሰኚ ናማ ሰላም ላንተ ይሁን ;;ደግሞም በጣም ደስ የሚል ስም ነው ;;የታደሰ ቡሩንዶን ያጫወትከን ታሪክ የሚያስቅ ነው ;;ጸጋየ ሞፎስ አሁን የት ይሆን ያለው ባክህ ?እሱ ልጅ አንዴ ወደ ሀረር ብሎ ከቦሬ ወጣ ከዚያ ወዲህ ወረውንም ሰምቼ አላውቅም ;;

ማርና ወተቴ ካነሳሀቸው ቅጽል ስሞች ውስጥ ምነው የግርማ ሰለሞንን ረሳኸው ?እንግዲህ የድሮዎቹን ስላነሳህ የጤናዬን ;የባዩሽን ;የተሰማን ;የአብረሀምን ;የሙሴን ወዘተ መጨመር ግዴታህ ሊሆን ነው ;;እስቲ ቸር ያቆየን ነገ እመለሳለሁ ;;
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሳኚናማ

አዲስ

Joined: 25 Oct 2006
Posts: 36
Location: ethiopia

PostPosted: Fri Oct 27, 2006 7:28 pm    Post subject: Reply with quote

በውነት በጣም ነው ያሳቀኝ አንዳዶቹን ቅጽል ስም አላውቅም ነበር ,
ሰሞኑ ጽሁፍ ስለማመድ ነው የቆየሁ በደንብ ለመጻፍ ጎበዝ እየሆንኩ ነው :
ቦሬ ለየት ያለ ከሁሉም ቦታ ያላት በመስቀል ማግስት ያለው የፈረስ ጉግስ ነው ድሮ በጣም ይደምቃል የሚመጡት ፈረሶች ልዩ የሆኑ ,ሰዎቹ ,(ጋላቢዎች ) ከጉግስ መልስ በየቤቱ እየሄዱ ሆካዎ !ሆካዎ ! የሚሉት ልዩ ነበር ያሁን የቅርብ እዛ ነበርኩ እንዳድሮ አይድለም ቀዝቃዛ ነው ባህሉ እየተረሳ ነው
ተጠየከኝ ጸጋየ ሞፎ ካየሁት ቆይቷል ግን እንደምሰማወ የፈለገው አራትኪሎ ውይም ፋብሪካ ክበብ አያጣውም አሁን ብትሄድ ታገኘዋለህ
የሁለት ትልልቅ ስዎች ቅጽል ስም ልበል ይቅርታ
ጋሽ አጥናፉ -ኦልሬዲ
አለሙ አንለይ -ቤሴሶ
_________________
as
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Visit poster's website AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ማርና ወተቴ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 13 Oct 2006
Posts: 72
Location: england

PostPosted: Sat Oct 28, 2006 12:06 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም እንደምን አላችሁ ?
ሳኚ ናማ እዉነትህን ነው : መስቀል ቦሬ ለየት ባለ ነው ሚከበረው :በአንድ ወቅት ባሌ ( ጎባ ) ከተማ ዉስጥ ጉግስ ሲጋለብ አይቻለሁ እንዲሁም ለመስቀል ሸዋ ዉስጥ አንዳንድ ቦታ የፈረስ ጉግስ ቢኖርም የቦሬ በብዙ መልኩ ይለያል : ይሄዉም ፈረሰኛው ሁሉ በመስቀል ደመራ ማግስት ጠዋት የከተማዉም ሆነ ከገጠር የሚመጣ ወደ ቤተ ክርስትያን ሄደው ይሳለሙ ምሽት ከተቃጠለው ደመራ ;ከሰሉን በማንሳት ግንባራቸው ላይ መስቀል ከሰሩ በህዋላ : ከተማዉን አቋርጠው ሜዳ ላይ ጉግስ መጫወት ነው ::
አንዳንዴ በጣም ዘግናኝ አደጋም ይደርሳል ;በአንድ ወቅት ማስታዉሰው ከሁለት አቅጣጫ እየጋለቡ የነበሩ ፈረሶች ተጋጭተው ሁለቱም ፈረሶች ወዲያዉኑ ሲሞቱ ,አንዱ ፈረስ ላይ የነበረው ግርማ አየለ ( አበባየሁ አየለ =ዶሉ ወንድም )የእግሩ አጥንት ደቅቆ ነበር የተሰበረው ::
አንዳንዴም የግሩፕ ጸብ አይጠፋም , አንዳንዱ ተሸንፎ ካቃተው የሚቀጥለው አመት ብድሩን ለመመለስ ቀጠሮ ይዞ ይለያያል ::ከዚያ መልስ በግሩፕ ሆነው በየሰዉ ቤት እየዘፈኑ ገንዘብ ይቀበላሉ ::
ሆካዎ ! ሆካዎ !
አባ ኪያ
ሲኬኑ , ኑኬኒ
ቡሎ ጦሬ
ኡቴ ኢጆሌን
ወራ ቦሬ
ሆካዎ ዱራ ጎሪ ራይሶ ወታደራ !!!!
አንዳንዱ ከነፈረሱ ቤት ዉስጥ የሚገባ አለ ; ታዲያ ፍቅር አለ ሁሌም ሰላም ነው ::
ሳኚናማ እንዳልከው አሁን እንደ ድሮ አለመሆኑና መቀዝቀዙ ያስቆጫል :
ካስታወስኩት ቅጽል ስሞች ጥቂቶቹ
ፈለቀ እሸቱ ( አር )
ባዩሽ በቀለ (ሆድዋ )
ተሰማ እንዳለ (ባቡሮ )
መስፍን ተስፋዬ (ጀልዶ ) ወሲላ
ግርመ ሰለሞን (ተርኪ )
ድሮ ይርጋ አለም ስንማር የተገጠመለት ግጥም
ኬሬዶ ትከርድ ክረምት በጋ :
ወዴት ዉላ ይሆን ተርኪቾ መንጋጋ ::
ሰላም ሁኑ !!!
_________________
az
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Sat Oct 28, 2006 12:44 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ;;ሰኚ ናማ እንዳልከው የመስቀልን በአል በልዩ ሁኔታ ነበር የምናከብረው ;;በተለይ ሆካሆ በፍጹም የሚረሳ ትዝታ አይደለም ;;እኔ በበኩሌ በቅርቡ በሞት የተለየንን ማሙሻ መራዊንና ቦብሽን ፈረስ ላይ ቁጭ ብለው ማየት ያስደስተኝ ነበር ;;መስቀል ከመድረሱ ከወራቶች በፊት የማን ፈረስ ሀይለኛ እንደሆነ ያጠኑና ባለቤቶቹ የገበያ ቀን ሲመጡ ጠጅ ጋብዘው ነበር ለመስቀል እንዲሰጡአቸው ፕሮሚስ የሚያስገቧቸው ;;

ከዚሁ አለሙ ቤሴሶን መጥቀስህ ድንቅ ቢሆንም ቦሬ ውስጥ ብቸኛ ስለሆነው ስለሱ ፎቅ አለማንሳትህ ለምን ?

ማርና ወተቴም ያነሳሀቸው ትዝታዎች ልዩ ናቸው ;;የግርማ ሰለሞንን ስም በመጥቀስህ አንድ ነገር ትዝ አለኝ ;;አዲስ አበባ የሆነ ድራፍት ቤት እንገናኝ ነበርና ልክ እንደገባ ጆሮውን በጥጥ ይደፍነዋል ;;መጀመርያ ነገሩ አልገባኝምነበርና ስጠይቀው የዚህን ጉርኛ ዲጄ ሙዚቃ ላለመስማት ብዬ ነው አለኝ ;;ለካ ልጁም በሁኔታው እየተበሳጨ ልክ እሱ ሲመጣ ሙዚቃውን በሀይል ይለቀዋል ;;
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Sat Oct 28, 2006 12:49 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ;;ሰኚ ናማ እንዳልከው የመስቀልን በአል በልዩ ሁኔታ ነበር የምናከብረው ;;በተለይ ሆካሆ በፍጹም የሚረሳ ትዝታ አይደለም ;;እኔ በበኩሌ በቅርቡ በሞት የተለየንን ማሙሻ መራዊንና ቦብሽን ፈረስ ላይ ቁጭ ብለው ማየት ያስደስተኝ ነበር ;;መስቀል ከመድረሱ ከወራቶች በፊት የማን ፈረስ ሀይለኛ እንደሆነ ያጠኑና ባለቤቶቹ የገበያ ቀን ሲመጡ ጠጅ ጋብዘው ነበር ለመስቀል እንዲሰጡአቸው ፕሮሚስ የሚያስገቧቸው ;;

ከዚሁ አለሙ ቤሴሶን መጥቀስህ ድንቅ ቢሆንም ቦሬ ውስጥ ብቸኛ ስለሆነው ስለሱ ፎቅ አለማንሳትህ ለምን ?

ማርና ወተቴም ያነሳሀቸው ትዝታዎች ልዩ ናቸው ;;የግርማ ሰለሞንን ስም በመጥቀስህ አንድ ነገር ትዝ አለኝ ;;አዲስ አበባ የሆነ ድራፍት ቤት እንገናኝ ነበርና ልክ እንደገባ ጆሮውን በጥጥ ይደፍነዋል ;;መጀመርያ ነገሩ አልገባኝምነበርና ስጠይቀው የዚህን ጉርኛ ዲጄ ሙዚቃ ላለመስማት ብዬ ነው አለኝ ;;ለካ ልጁም በሁኔታው እየተበሳጨ ልክ እሱ ሲመጣ ሙዚቃውን በሀይል ይለቀዋል ;;በኌላ ላይ ለዲጄውም ግርማ የቦሬ ልጅ እንደሆነና ለግርማም ዲጄው የክብረመንግስት ልጅ እንደሆነ ነግሬአቸው የሀገር ልጅ ተባብለው ተቃቅፈው ሰላም ማውረዳቸው ይታወሰኛል ;;ቸር ያሰንብተን ;;
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቺኮኩባኖ

ኮትኳች

Joined: 14 Sep 2006
Posts: 259
Location: usa

PostPosted: Sat Oct 28, 2006 3:07 am    Post subject: Reply with quote

አካም ኢጆሌ ቦሬ አኒ ባዬ ሲጃለዳ
እንዴትናችሁ ስለ መስቀሉ ትዝታቹ በጣም ነው ደስ የሚለው ማሙሽ መራዊን አውቀዋለሁ ግን በቀርቡ ነው መሞቱን የሰማሁት ነብሱን ይማረውና ጥሩ ልጅ ነበር .

ኢጆሌ ቦሬ ከያላችሁበት
ብቅብቅ በሉ እንጨዋወት
ትዝታ ያላችሁ ይዛችሁ ከማጀት
አውጉን እንስማው እንድንደሰት
የቦሬ ቆሎ ጠጅ ከፊት
ምገዛው ቂቤ ከኑጌ ቤት
ትዝ እያለኝ ካለሁበት
በሀሳብ ሄዳለሁ ከአገር ቤት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ነጭ ማር

አዲስ

Joined: 15 Oct 2006
Posts: 46
Location: america

PostPosted: Sun Oct 29, 2006 6:20 am    Post subject: Reply with quote

ጤና ይስጥልኝ ;;ቺኮ እኛም በጣም እንወድሀለን ;;ወይኔ በናትህ ኑጌን ከየት አመጣኸው ባክህ ?ከቆሎ መሸጥ ተነስቶ እጅግ በጣም ያደገ ልጅ ነው ;;ለረዥም ግዜ ሱቁን ለቤተሰቡ አደራ ብሎ እሱ እንጦጦ ማርያም ሱባኤ እንደያዘ ሰምቻለሁ ::በሀይማኖቱ ጥንካሬም በጣም ነው ደስ ያለኝ ::ግጥምህም ድንቅ ናት አቦ //

ዛሬ ስራ ቦታ ሆኜ አንድ ነገር ትዝ ብሎኝ ስገረም ነበር ;;መላከ ገነት ተስፋየ ደረቶን የማያውቃቸው አይኖርም ;;አሁን አባ ተብለዋል ::ብዙወቻችን የምናውቃቸው በሀይማኖት አባትነታቸውና በጥንካርሬያቸው ይመስለኛል ::ፍጹም እውነተኛ አባት ናቸው ;;ላሳደገችን ለእመቤታችን ደጅ ደግሞ የለፉና የደከሙም ናቸው ::እኔ ግን ዛሬ ላስታውሳቸው የፈለኩት በእግር ኳስ ችሎታቸው ነው ::ከቤተክርስትያን አገልግሎታቸው ውጪ ለቦሬ ከነማ ኳስ ይጫወቱ ነበር ::በጣም ሀይለኛ ሹተር ነበሩ ::ጉልበታቸውና ፍጥነታቸው ልዩ ነው ::እስከዛሬም ለኳስ ያላቸ ፍቅር እንዳለ ነው ::ይህንንም ልል የቻልኩበት ባንድ ወቅት አዲስ አበባ መትተው ሰው ለመጠየቅ የሄዱበት ቤት ሲገቡ እንዳጋጣሚ የሪያል ማድሪድና የባርሴሎና ጨዋታ ይተላለፍ ነበርና በስሜት ቁጭ ይላሉ ::ከዚያ በቃ ኳሷ ወደ ሄደችበት የተቀመጡበት ቦታ ላይ ሆነው እግራቸውንና እጃቸውን ሲያወንጭፉ ወይኔ የኔታ አሁንም ወኔያቸው አለ ያስብል ነበር ::ብዙውን ግዜያቸውን የተጫወቱት ከነጋርሴ ቀሬ ከነ አህመዲን ; ፈለቀ ንጉሴ ከመሳሰሉት ነባር ሰዎች ጋር ነበር ::

ነገሬን ለማጠቃለል ያህል ቦሬ ውስጥ ድሮ የነበረው የኳስ ፍቅር ልዩ ነበር ;;እስከቅርብ ግዜ ድረስ እነሲሳይ አሰፋ የቡድን መሪ ሆነው ወደነጌሌ ቦረና ይዘውት የሄዱትን ቡድን የሚያበሉት አተው ክላሽንኮፍ ጠመንጃ አሲዘው እስከመገቧቸው ድረስ የነበረው የኳስ እንቅስቃሴ ጥሩ ነበር ::በኔ ግምት በፊት በተጫዋችነታቸው ትልቅ ደረጃ ይደርሳሉ ብየ ከማስባቸው ጠንካራ ተጫዋቾች መሀከል እሼቴ ከበደን ልዩ ቦታ እሰጠዋለሁ ::እስቲ እናንተም ትዝታችሁን ጀባ በሉን ;;ደህና ሁኑልኝ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ማርና ወተቴ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 13 Oct 2006
Posts: 72
Location: england

PostPosted: Sun Oct 29, 2006 11:08 pm    Post subject: Reply with quote

አካም ጂርታን ኢጆሌ ኬኛ !
ቺኮ ኩባኖ ሰላም ነህ ወይ ? የቋጠርካት ስንኝ ድንቅ ናት :ያነሳኸው ልጅ ኑጌ ድንቅ ጸባይ ያለውና ታታሪ ልጅ ነው ::
ነጭ ማር ስለ ድሮ የቦሬ ስፖርት ማንሳትህ በጣም የሚባልለት ስለአለው ጥሩ ነው :መምሬ ተስፋዬ ደረቶ (መላከ ገነት ) ትልቅ የኳስ ፍቅርና ችሎታ ነበራቸው :በተለይ አብሯቸው የሚሰለፈው አቶ አህመዲን ሀሰን (የናስር አብዲሽኩር አጎት )ሁለቱም ግዙፍ , ጠንካራ ተከላካዮች ስለነበሩ እንሱን ማለፍ በጣም አስቸጋሪ ነበር ::
በአንድ ወቅት ትዝ የሚለኝ ቦሬ አገረሰላም የእግር ኳስ ግጥሚያ ነበራቸውና የመልስ ጫወታው አገረሰላም ላይ ሲደረግ ቦሬ አንድ ለባዶ እየመራ ነበር : የአገረሰላም አጥቂዎች (ነፍሱን ይማረዉና ተሰማ አሰፋ ) ሌሎች መለከ ገነትን ማለፍ በፍጹም ያቅታቸዋል ;ታዲያ በዚህ የተበሳጩ የአገረሰላም ደጋፊዎች <ቄሱ ይዉጡ !ቄሱ ይዉጡ !>እያሉ መጮህ ጀምረው ነበር ::
ከዚያም ደጋፊ ለደጋፊ ብሽሽቅ ተጀምሮ ,አገረሰላሞች ቦሬዎችን <አሬራ !አሬራ !>ማለት ሲጀምሩ ቦሬዎች ደግሞ በአጸፋው <ፉርፉራሜ ! ፉርፉራሜ !> ሲሉ ቆይተው የተጀመረው የቃላት ጦርነት ወደ ድብድብ አምርቶ እንደነበር ሁሉ አስታዉሳለሁ ::
ልበሙሉ ደፋሩ በችሎታው ተደናቂው መምህር ነጋሽ አብዬ መምህር ተክሌ አስፍሀ ለቦሬ ስፖርት ያደረጉት አስተዋጾ ብዙ ሲሆን :ሁለቱም በወቅቱ እጅግ ገናና ለነበረው ለይርጋአለሙ ትራንስፖርት ቡድን እየሄዱ ይጫወቱ ነበር ::
ቀደም ሲል የነበረው ቡድን አሰላለፍ በጥቂቱ ለማስታወስ ;
በረኞች =
ንጋቱ -ጌታቸው ዘዉዴ -ሰምረአብ በቀለ
ተጫዋቾች =
መላከ ገነት (መምሬ ተስፋዬ ደረቶ )
ጋርሴ ቀሬ (አኒቻ )
አህመዲን ሀሰን
ፈለቀ ንጉሴ
አረጋ ትርፌ
አብረሀም ረዲ
ጌታቸው ጭልፎ (የነ ካሱ ተሰማ ወንድም )
ነጋሽ አብዬ
ተክሌ አስፈሀ
መምህር ሀይለአብ ክፍሌ
መምህር አይን እሸት
መምህር ሀይለማርያም
ናስር አብዲ ሽኩር (ጮራ )
ገዛኽኝ ማሞ (ፌጮ )
ሩዳን ረሺድ
ግርማ ገብረመድህን (ጄት , አልቤኑ ዲማ )
አባተ ካሱ (ጫኪሌ )
በሀይሉ ገብረመድህን (ቁሮ )
ሙላት ሁሴን የተባሉ የእድገት በህብረት ዘማቾች ድንቅ ተጫዋቾችም ነበሩ : ሙላት በወቅቱ የጊዮርጊስ , ሁሴን ደግሞ የድሬዳዋ ሲሚንቶ ተጫዋቾች ሆነው ነበር ቦሬ ዘመቻ የመጡት በቆዩበት አጭር ጊዜ ድንቅ ችሎታ ትምህርት አሳይተውን ነበር ::
በተለይ ሙላት የተባለው የሚመታቸዉን (ወደ ህዋላ ወደ ጎን )መቀስ ምቶች ሌላ ነበሩ ሁሌም ይህንኑ ሲለማመድ በተመስጦ ነበር ምከታተለው ::
ለቦሬ ይጫወቱ የነበሩ እነዚህ ብቻ ሳይሆኑ አሉ ማስታወስ አቅቶኝ እንጂ :
በሚቀጥለው ደግሞ ስለወጣት ተጫዋቾች እናነሳለን ::
ከእነዚህ ተጫዋቾች በፊት ግን አንጋፋ የቦሬየእግርኳስ ቡድን ነበር :የተነሱትን ፎቶ ግራፍ በአንድ ወቅት ጸጋዬ አሸናፊ እናቱ / መሳይ አክሊሉ ያስቀመጠችዉን አግኝቶ የማየት እድሉ ገጥሞኝ ነበር :
የለበሱት ማሊያ እንደ /ጊዮርጊስ <V> አለው
ዳኛ = ሱፍ ለብሳ --ምትታየው ፍቃደ ዘሪሁን
አሰፋ ጩሉቄ
አሸናፊ ታደሰ
ስንታየሁ አጠላ
እና ሌሎች አሁን ማላስታዉሳቸው ነበሩ እስኪ ምታውቁትን ጣል ጣል አድርጉ ::
ሰላም ያቆየን !!!!!
_________________
az
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, ... 64, 65, 66  Next
Page 2 of 66

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia