WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የቦሬ ልጆች በዋርካ ጥላ ስር :
Goto page Previous  1, 2, 3, 4 ... 64, 65, 66  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ሳኚናማ

አዲስ

Joined: 25 Oct 2006
Posts: 36
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Oct 30, 2006 6:51 pm    Post subject: Reply with quote

በዉነቱ ብዙ ትዝታ የሚቀሰቅስና አስደሳች ናው :;
በተለይም ከብዙጊዜ በፊት ከዚ አለም በሞት የተለየ የቅርብ ዘመዴን ስም እያየሁ እንባ እያነቀኝ ነው ያነብብኩ ;ሁሉም ሰው ይህንን የማንበብ እድል ብያገን ደስ ይል ነበር :;
ግርማ አልቤኑ ሩዳን ረሽድ አሁን የአእምሮ በሽተኛ ነቸው ድሮ ምን የመሰሉ እሳት የሆኑ ልጆች ነበሩ
ማርናወተት ከበረኛ ያልጥራኸው ተሾመ ንጎሴ ከተጫዋች ካሱ ማሞ ግን በጣም አድንቄለሁ የማስታወስ ችሎታህን
ገዛኸኝ ማሞ (ፌጮ ) አንድ ትልቅ ክለብ ቀደም ሲል ተጫዋች መሆኑን ሰምቼ ነበር እስኪ ምታቁ ንገሩኝ
ማነንደሆን እንጃ ስለ እርቂሁን አንስቶ ነበር የቱ ነው ?
ቦሬ የነበሩ እርቂሁኖች ሁለት ሲሆኑ አንዱ እርቂሁን ዘሪሁን (የአባባ ዘሪሁን ምትኩልጅ ) ከወጣ ብዙ የቆየ አንዳንዴ አውስትራልያ ነው ይባል ነበር እርግተኛ አይደለሁም ሌላው እርቂሁን ወርቁ ሲሆን ከጦ /ሰርስዊት ከተመለስ ውዲህ ናይሮቢ ኬኒያ ነው በልጅነቱ ረብሸኛ ነበር ያለ ቅጽል ስም ሲጠራ ስላየሁ ማን እንደሆነ ለመለየት ነው
ከቅጽል ስም ትዝያለኝ ልጨምር
አቶ ከበደ ማሞ (ካባ )
ስንታየሁ አሸናፊ (ቦኦ )
ሀብተወልድ ደስታ (ቡላ )
አቶእሸቱ ጸጉር አስተካካዩ (ፎቆሮ )
_________________
as
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Visit poster's website AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Tue Oct 31, 2006 6:00 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ;;ሰኚ ናማ አንዳንዴ ቀስ ብለህ ጣል የምታደርጋት ቅጽል ስም የመጨረሻ የሚሳቅኝ ነው ;;ለነገሩ አንተ ጉደኛ ሰው ነህ ;;በል አራት ኪሎና ክበብ ብትሄድ ታገኘዋለህ ያልከውን ልጅ ሰላም በልልኝ ;;ሌላው እርቂሁን ያልከው ወታደር ቤት የነበረው ሲሆን በቅርብ ግዜ ከናይሮቢ ወደ ካናዳ ገብቷል ;;አሁን እንደውም ረባሽነቱና ተደባዳቢነቱ ቀርቶ የቤተክርስትያን ልጅ ከመሆኑ ውጪም በካልጋሪ የሚገኘው የቅዱስ ገብሬል ቤተክርስትያን ዘማሪም ጭምር ነው ;;

ሌላው ላነሳ የምወደው በዚህ ፔጅ ላይ እየተሳተፍን ካለነው ውጪ ሌሎቻችንም መቀላቀል እንዳለብን ይሰማኛል ;;በተለይ በውጪ የምንኖር አይምሯችን በስራና በትምህርት ተወጥሮ እንደዚህ ግዜ ሲገኝ ስለሀገራችንና ስላደግንባት ሀገርና አካባቢ በማንሳት ዘና ማለት የምንችል ይመስለኛል ;;በዚህ በኩል ሀገር ቤት ያሉትም ብዙ ነገሮችን ካሁኑ እያዛመዱ ሊስታውሱንና ሊረዱን ይችላሉ ;;በመሆኑም ስማጩን ለግዜው የማስታውሰው :

አሜሪካ

የዲሲዎቹ ;
ሰለሞን አየለ
ታመነ ካሱ
ደረጀ ከበደ
ከዲርና አብድዬ

የፖርትላንዶቹ ;
የምስራች አሸናፊ
ትርንጎ መኮንን
የምስራች አሸናፊ

የቺካጎው ;
ተሰማ አሬሪ

የኒዮርኮቹ ;
ቹቹና ህብስት

የአትላንታው ;
ሀብተወልድ ደስታ (ቡላ )

የካናዳዎቹ ;
እርቂሁን
እውነቱ
አለም ሴፉ

የዱባዩ ;
አባ ሳሙኤል

የአውስትራልያዎቹ ;
ሀረገወይን መኮንን
ህይወት መኮንን
እርቂሁን ዘሪሁን
ቴሹ ኡዴሳ

የናይሮቢዎቹ ;
ዮናስ ቡታ
መርድ ቦጃ

ከኖርዌይ ; ራሄል ወልደማርያም (ሙኒት ) እና ሌሎቻችሁም ተሳትፏጩን እንተብቃለን ;; ሀገር ቤት ያላችሁ ጥሩ እንቅስቃሴ እያረጋችሁ ስለሆነ በርቱ ;;ሰኚ ናማም በዚህ በኩል ድርሻህን እንድትወጣ አደራዬ ነው ;;ቸር ያሰንብተን ;;
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1053
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Oct 31, 2006 12:58 pm    Post subject: Reply with quote

በጣምም ደስ የሚል ስራ ነው
እንክዋን ለዚህ አበቃቹ ጎሮቤቶቼ ....
ሳያቹ ደስስስ ነው ያለኝ በውነት ...

እኔም ቦሬ ላይ የገጠመኝንና ማስታውሰውን ይዤ መጣለሁ

እንደው እንደው ግን የገረመኝ ምን እንደሆነ ታቃላቹ
ሞፊቲ እዛ ቤት ውስጥ ታፍኖ ሊፈነዳ ደርሶ እንደነበር ነው የተሰማኝ

ይህንን ሁሉ የመፃፍ ችሎታ እያለው ምነው ዝም ማለቱ ስል .... ለካስ ታፍኖ ኖሯል
አፈነዳው እኮ ይህንን የማያልቅ የቦሬ ነጭ ማር የመሰለ - ወሬ

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

እመለሳለሁ በትዝታዬ

አንድ ቀን .. ሲመች ነው ታዲያ
እንድውው አይቼ እንዳላልፍ ብዬ እንጂ ... ጊዜ እንደቁምጣ ነው ያጠረን

በነገራችን ላይ ጋሽ ዝኑን ሚያቅ ማነው ....
ብዙ ጊዜ እሳቸው ጋር እናድር ነበር ባስ ሲበላሽ ወይ ቦሬ ላይ ሲመሽብን

ሰላም ቆዩኝ

ወዳጃቹ
ባለሱቅ ከአዶላ ወዩ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ማርና ወተቴ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 13 Oct 2006
Posts: 72
Location: england

PostPosted: Tue Oct 31, 2006 8:22 pm    Post subject: Reply with quote

ወንድማችን ባለሱቅ እንኳን ደና መጣህ !
ኢድ ሙባረክ ! ብያለሁ , የአዶላ ልጆች ፔጅ ላይ በዝና እናዉቃሀለን ;መሳተፍ ባንችልም ሁሌም ከማንበብ ወደህዋላ ያልንበት ጊዜ የለም : አንተን ,አዶቆርሳን ,ራስብሩን እንደንቃችህዋለን :;የእናንተ ሞራልም ነው ያነሳሳን :ልብ ብለኸው እንደሆነ የመጀመሪያው ገጻችን ላይ ጥሪ አድርገንላችኋል ::ትንሽዋ ቦሬ ከታላቅዋ ክብረ መንግስት ተማረች ማለት ነው ::ስለተሳትፎህ እያመሰገንን በዚሁ ቀጥል እንላለን ::
ወንድሜ ሰኚነማ = የምታነሳው ጉዳይ ሁሉ አስደሳችና ግፋበት የሚያሰኝ ሆኖ ግን አንድ ላርምህ የምፈልገው ነገር አለ ::
ይሄዉም አቶ እሸቱ ጸጉር አስተካካይ ብለህ ያልካቸው ሰው ሙሉ ስማቸው አቶ እሸቱ መልካ ሲሆኑ ሙያን እንደአባት ስም መጥቀስ ትክክል ስለአልመሰለኝ ነው :የአባት ስም ካላወቅን ስም ብቻ መጻፉ ይመረጣል :አስተያየቴን እንደምትቀበለው እተማመናለሁ :
ሌላው ለጠየከው ጥያቄ _ገዛኸኝ ማሞ (ፌጮ ) ይጫወት የነበረበት ክለብ አዲስ አበባ እንደነበረው ምድር ጦር ቡድን ቀደም ሲል አስመራ ዋልያ የሚባል የሁለተኛው አብዮታዊ ሰራዊት የእግር ኳስ ክለብ ዉስጥ ሲሆን :አስመራ በወቅቱ ከነበሩት እንደ ኤርትራ ጫማ , ኤሌትሪክ ,ከመሳሰሉት ጠንካራ ክለቦች ጋር ከፍተኛ ፉኩኩር የሚያደርግ ክለብ ነበር ::
የረሳህዋቸውን ተጫዋቾች ስለአስታወስክ አመሰግናለሁ ::
ዛሬ ደግሞ በአንድ ወቅት ስለነበረው የታዳጊ ኳስ ትንሽ ልበል :
ትንንሽ ልጆች እያለን የቦሬ ከተማ አራት የሰፈር ቡድኖች ነበሩ : አንዱ አንዱን እየጠራ መጋጠም ነበር :ቡድኖቹ ባስታዉስም ልጆቹን ትንሽ ዘንግቻለሁ :

(የቤተክርስቲያን ቡድን >
ጌታቸው ብዙነህ (ቀጨሊ )
ክፍሌ ስዩም
ፍርዴ ስዩም
ሩዳን ረሺድ
አብነት ጂሎ
አብዲልፈታ ቡሴር
ወንድሙ ማእረግ
ሌሎችም ------

2= <የገበያ ክፍል ቡድን >
ፍላቴ ለማ
ሙሉጌታ ለማ
ሰይፉ ለማ
ማቲዎስ በቀለ
ሰለሞን አየለ
ሸዋንግዛው በቀለ
ኤልያስ ይስማ
ሌሎች -------

3=<የካምብ ቡድን >
ገዛኸኝ ማሞ (ጡጢ )
ለማ ግዛቸው
መክብብ አየለ
ግርማ አየለ
ታምራት ቦጋለ
ሌሎችም ----

4=<የጨፌ ቡድን >

ሺባባው ብዙነህ
ያለው ካሳ
አለማየሁ አቦሰጡኝ
ሙሉጌታ አጥናፉ
ዘውዱ ብዙነህ (ቡሱሩ )
ካሱ ታምሩ
ኮንትሮ ማሞ ሜጬሬ
እርቂሁን ወርቁ
ሌሎችም ----
ከሁሉም ጠንካራና ሀይለኛ የጨፌ ቡድን ነበረ : ያው ጊዜው በመርዘሙ ብዙዎችን ዘነጋሁ :
ያው ከግጥሚያ መልስ
,<አይቻልም የኛ ልጅ አይቻልም !
አሀሀ ! እያልን እንዲሁም
<ማረኝ አለ እከሌ ማረኝ አለ >
አሀሀ !!እያልን ምንጨፍረው ትዝ ይለኛል ::
ከዚያ በህዋላ 1986 1987 አካባቢ ጥሩ የኳስ እንቅስቃሴ ነበረ :
አንደኛ ደረጃ /ቤት
ሁለተኛ ደረጃ /ቤት
የነጋዴ ቡድን
የትራንስፖርት (ያቦሌ ) ቡድን
የከነማ ቡድን
ጠንካራ ዉድድር ያደርጉ ነበር የያቦሌ ቡድን ከነጋዴ ቡድን ጋር ለዋንጫ ሽሚያ ሲጋጠሙ ሁለት ተጫዋቻቾችን ከአዋሳ ዱቄት ቡድን ገዝተው እስከማምጣት ደርሰው ነበር ::
ግለሰቦችም ቡድኖችን የበላይ ጠባቂ በመሆን መስርተው ነበር : ለምሳሌ ነፍሱን ይማረዉና ሀኪም ታምራት ደስታ የትራንስፖርትን ቡድን እንዲሁም :አብነት ጂሎ የነጋዴን ቡድን በመርዳትና በማስተባበር ትልቅ አስተዋጾ አድርገው ነበር ::
ቦሬ ይጫወቱ ከነበሩ ልጆች (ወጣቶች )መሀል እኔም ማደንቃቸው ነበሩ ለምሳሌ እንደተባለው :
እሼቴ ከበደ
አስናቀ ጫላ
አስራት ተሾመ
ትልቅ ደረጃ ሊደርሱ የሚችሉ ነበሩ ሌሎችም ጥሩ ችሎታ የነበራቸው ልጆች ነበሩ ::
እረ ጉድ ፈላ !!!!!
የቸልሲ ባርሲሎና ጫወታ ሊያመልጠኝ ነው
ቻዉ !!!!!!!
_________________
az
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
የቦሬ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 27 Jan 2006
Posts: 85
Location: USA

PostPosted: Tue Oct 31, 2006 9:43 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ያገር ልጆች ህንደምን ከረማቹ :: ማርና ወተቴ ልትመሰገን ይገባል :: ቦሬን ውድድ የማደርጋት የትውልድ ሀገሬ ናት :: የክብረመንግስት ልጆች ለመሳተፍ ብሞክርም ክብረመንግስትን ያየሁት አንድ ግዜ ብቻ በመሆኑ ብዙም ትዝታ ስለሌልኝ መቀጠል አልቻልኩም :: የክ / ልጆች ደስ የሚሉ የምያስቀኑ ናቸው :: የቦሬዋ የሚለውን የቦኔያን ዘፈን ማግኘት የሚቻል ከሆነ ላኩልኝ ::
በተረፈ በጣም አወዳችዋለሁ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሳኚናማ

አዲስ

Joined: 25 Oct 2006
Posts: 36
Location: ethiopia

PostPosted: Wed Nov 01, 2006 12:11 am    Post subject: Reply with quote

ዛሬ ደስይላል ሞቅሞቅ ብሏል የቦሬ
ባለሱቅ እንክዋን ደህና መጣችሁልን
ባለሱቅ ገበያ ደህና ነው ወይ ?በስም ያዶላ ልጆች ላይ ስትጽፍ አነብ ነበር ግን መጀመሪያ ምትጽፈው ለመረዳት ይከብደኝ ነበር በህዋላ ለመድኩት
ያልከው ዘመድህ አቶ ዝኑ አደም ደህና ኔው :የአዶላ ጉብኝትህ የጻፍክው ከነክትፎዉና አይቤው ልዩ ነበር
ማርናወተት የሰጠኸኝን አስታየየት በምስጋና ተቀብያለሁ እኔም ከላኩ በህዋላ ተሰምቶንኝ ነበር
ሌላው የድሮ ታዳጊ ኳስ ያነሳኸው የኔንም ስም በማግኘቴ ደስ ብሎኛል
ባለፈ ድሮ ተደብቆ የቀረ ቅጽል ስሜን ፈልፍለህ አወጣህ አሁንም ብዙእንድምታስነብበን ንው በርታ ;
ሞፊቲ ዉጭ ካሉ ስትጠቅስ ምስራች ሁለቴ ነው የተቀስከወ እህትዋን መታሰቢያ ማለትህ መሰለንኝ
ሌሎች ዉጭ ያሉ ለመጨመር
አመሪካ እንደሰማሁት
-አሰገደች ወልደማሪያም
ገነት ውልደማርያም
አጉዋጉ ወልደማርያም
አስናቀች አየለ
ካፒቴን መንግስቱ አየለ (ኬፕ ቨርዲ )

ካናዳ
ሲቲና ከማል
ያለምሰው አዱኛ
የሌሎች የሰማሁትን አረጋግጬ እጽፋለሁ
_________________
as
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Visit poster's website AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Wed Nov 01, 2006 2:00 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ;;ወንድሜ ባለሱቅ ለሰጠኸኝ ሞራል ከልብ አመሰግናለሁ ;;ይሁንና ግን እኔ የሀገሬ ፍቅርና ናፍቆት ብቻ ስላለብኝ እንጂ ምንም አየነት የመጻፍ ችሎታ እንደሌለኝ እወቅልኝ ;;ከዚሁ ያዶላ ልጆች ጋም ስሳተፍ ይህንኑ ድፍረቴን ይዤ እንጂ እንዳየኸው የረባም ነገር ጽፌ አላውቅም :;ባጠቃላይ ግን ለዚህም ቢሆን ያደረሰኝ ይኸው ያዶላ ልጆች መድረክና የናንተም ማበረታታት በመሆኑ ምስጋናዬ እጥፍ ድርብ ነው ;;እንግዲህ አንተም በገባኸው ቃል መሰረት ሲመችህ ብቅ እያልክ ጎብኘን ;;

ስለጋሽ ዝኑም ለጠየከው በጣም ነው የማውቀው ;;ባንድ ወቅት የቀበሌ ሊቀመንበር እንደነበር ሁሉ ትዝ ይለኛል ;;ይሁንና ግን ጋሽ ዝኑ መሳርያ መያዝ አይወድም ነበር ;;ምናልባት የግድ መያዝ ካለበትም ጥይት ያልጎረሰ ወይም የተበላሸ መሆን አለበት ;;

ሰኚ ናማ ስሙን ስላስተካከልክልኝ ምስጋናዬ ይድረስህ ;;ማርና ወተቴም የጠቀስካቸው ተጫዋቾን ስም ሳይ በማስታወስ ችሎታህ ተገርሜአለሁ ;;ግን አብነት ጂሎ ኳስ ይጫወት ነበር እንዴ ?ወይስ አራጋቢ ነው ?(ባሁኑ መስመር ዳኛ ማለቴ ነው );;ማቲወስ በቀለን በማንሳትህም ደስ ብሎኛል ;;ምክንያቱም አንድ እግሩ ታማሚ ሆኖ በረኛ እንደነበር ትዝ ስለሚለኝ ነው ;;በነገራችን ላይ ሞጎስም እግሩን ታማሚ ሆኖ በረኛ እንደነበር አስታውሳለሁ ;;እንግዲህ የተጫዋቾችን ስም ካነሳህ አይቀር ስለታዋቂው ዳኛ በዻሶም የሆነ ነገር ጀባ እንደምትለን እምነቴ ነው ;;ቸር ያሰንብተን ;;
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1053
Location: ethiopia

PostPosted: Wed Nov 01, 2006 2:49 am    Post subject: Reply with quote

እናንተ ልጆች ዛሬም መጣሁ እኮ
ሳይጠሩት አቤት እንዳልባል ብቻ .....
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ስለጋሽ ዝኑ ሞፍቲ የፃፍከውን አይቼ ግርምምም አለኝ .... መሳሪያ መያዝ አይወዱም ለካስ .... ቀበሌ ሊቀመንበርም ነበሩ ?... ህምምም ብቻ ሰው አሳስረዋል አስገድለዋል እንዳትለኝና እንዳይዘገንነኝ ...
በልጅነቴ ስለሆነ ማቃቸው ... ከስማቸው በስተቀር ብዙ ማቀው ነገር የለኝም
ዛሬ የቦሬ ትዝታዬን ይዠላቹ ነበር የመታሁት ...
እናንተ የሰው ስም ደርድራቹ ደርድራቹ ቤቱን ሞላቹት እኮ ...
ትዝታ የላቹም እንዴ ..
የልጅነት
የት / ቤታቹ
....
እኔ 10 ወይም 11 እያለሁ ነው መሰለኝ .... ያመኛል ...
እንደጦር ይወጋኛል ... የአይኔ ኳስ .... በተለይ ፀሀይ ሲበዛ እና ጥናት ሲበዛ
እናላቹ
የዛን ጊዜ ቦሬ ውስጥ አንድ "ጎሳ " የሚባል የጣሊያኖች ሆስፒታል ይሁን ክሊንክ ዝነና ሆኖ ነበር /መንግስት
እና እዛ እንድሄ ቤተሰብ ገፋፋኝና ... ህእድኩ
በዘመድ መኪና .... ሌሊት 11 ይሆናል የተነሳነው ...
እቃ ስለጫነ ... ቀስስ እያለ ነበር ሚግዋዘው .. ወዳዲሳባ
ቦሬ ስንገባ ገና ጠዋት ነው ...
ቡሉኮ .. ብርድ ልብስ ... ጋቢ የተከናነቡ ሰዎች ውር ውር ማለት ጀምረዋል ...
ጭጋጉ ላይን ያዝ ያደርጋል
ውይይይይ ብርዱ
እየተንዘፈዘፍን ወርደን ቆቆር ሻይ ... ግጥም አድርገን .,.. እኔ ዘመዶቸን ሸኝቼ ብቻዬን ቀረሁ ...
ሰሙ ሆቴል አካባቢ መሰለኝ
ሰው ጠየኩ ... "ጎሳ " የት ነው ብዬ
ነገሩኝ 5-10 ኪሎ ሜትር ወጣ ያለና ... ፈረስ ካለኝ በፈረስ .. አለበለዚያ በደንብ ሲነጋ ... አይሱዙ ይመጣል .. እሱን ጠብቅ ተባልኩ
እትትትትትትትት
ብርዱ

ነጋ መሰለኝ .. የቦሬ ፀሀይ ከጠዋቱ ... 1 ወይም ሁለት ሰአት ላይ ወጣች ....
ብርዱ ግን ውይይይይይ
ከየሰዉ ትንፋሽ የሚወጣው እንፋሎት ... ከርቀት ስታይ .. ያገሩ ሰው ሁሉ ሲጋራ አጫሽ ሆነ እንዴ ያሰኛል ...
እንዴት እንደሆነ አትጠይቁኝ ..
አንድ መቶ ብር አገኘሁ (ወይም ወሰድኩ ልበላቹ .... ሰረቅኩ ብዬ መቸም እራሴን አላዋርድ ባደባባይ )....
ከየት ብሎ መጠየቅ በህግ ያስቀጣል
እና ጠዋት ሁለት ሰአት ላይ ይመስለኛል ... በአይሱዙ ላይ ተጫንን .... የቆመ እንጨት /ችቦ ይመስል ... ቆመን ነው ምንሄደው ... አይሱዙአችን ላይ ....
ዥውውው ዥውውው እያደረገ .. እያከነፈ ...
ጎሳ ሆስፒታል ደረስን ....
መቸም ሆስፒታል ካላልኩት ምን ልበለው ... ለክሊኒክማ /መንግስትስ አለ አይደል እንዴ እንዳትሉኝ ....
ያው ነጭ አምላኩም ስለሆንን ይሆን ...
ጣሊያን ሚሺነሪዎች ናቸው አሉ ... የሚያክሙት ...

ለግዜር ቅርብ ስለሆኑ ... እንደው በሽታዬን ቶሎ ቢያድኑልኝ .. ብዬ ነበር መሄደ .. ይመስለናል
መፎገር ክልክል ነው እናንተ !
እና ተመዘገብኩ .. ገባሁ
እንግሊዘኛ .. እችላለሁ ብዬ አስተርጓሚ አልፈልግም አልኩኝ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
እና ነግሬአቹዋለሁ እንዴት እንደሚያመኝ
እንደጦር ነው ሚወጋኝ ብያቹዋለሁ
ታዲያ ጦር ማለት ስፒር ነው .... ይህንን መናገር ያቅተኛል
ንግርርርርርርርር
- what is your problem
- like spear here... ያይኔን ቦሎች እየነካካሁት
- what spear...? ግራ የተጋባችው አሮጊት ሚሽነሪ ጣሊያናዊት
- here like spear .. ጭቅጭቅ ያደርገኛል
አይ ቲንክ መቀጠል አልቻለችምና ... አስተርግዋሚ ተጠራች
አበሻዋ ወጣት .... እንደመታዘብ እያለች
መጀመሪያ ችላለሁ አላልክም ... ብላ እያሾፈችብኝ
ምንድነው በሽታህ አለችኝ
ይወውልሽ እንደጦር ይወጋኛል እዚህ አይኔ ላይ ... ከግራ ወደቀኝ አይኔ ይሯሯጣል በየቀኑ ...... ብዬ አሳዝኜ ብነግራት
አስተርጓሚዋ
He got pain on his eye and forehead
አትልልኝም መሰላቹ
እረ ባክሽ ፔን ብቻ አይደለም ... ከፐንም ፔን እንጂ
እንደጦር እኮ ነው ሚወጋኝ ... ይህንን ተርጉሚልኝ
ትስቅብናለች
ጭቅጭቅ
ተናደድኩኝ
በመጨረሻ መዳኒት ታዘዘልኝ
ምን እንደታዘዘልና ታቃላቹ
ፓራሴታሞል 10 ፍሬ
ይይይይይይይይይይይይይ
ሲያናድድ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ሳስበው ያስቀኛል
ከዚያ በኃላ ... በቃ
ያችን መቶ ብር ወደ አንድ አንድ ብር ዘረዘርክዋትና ...
ብዙ ብር ሲሆንልኝ ጊዘ
ቡና ገዛሁና ... ወደ -አዶላዬ
ቡና ለማዘሬ ... 10ኪሎ ሳይሆን ይቀራል
ከዚያ በኃላ ያለው ታሪክ የክ /መንግስት ነው
እሱን እዛው ስንገናኝ
...
የቦሬ ጎሳ ክሊኒክ /ሆስፒታል ትዝታዬን አጫወትክዋቹ

ፓራሴታሞል ለመግዛት ከአዶላ ቦሬ ድረስ ...

አላሳዝንም

አይ ባለሱቅ

በሉ እናንተ አስለፍላፊዎች
ስራ አታስፈቱኝ

ቻዎ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1053
Location: ethiopia

PostPosted: Wed Nov 01, 2006 2:52 am    Post subject: Reply with quote

ሶሪ ሳልነግራቹ

በሽታዬን እኮ አወኩት
ፍሮንታል ሳይነስ ይባላል
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
አሁን ተሽሎኛል
ይመስገናው ለረቢ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
anferara

ኮትኳች

Joined: 27 Sep 2006
Posts: 384

PostPosted: Wed Nov 01, 2006 4:00 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ቦሬዎች

የናንተን ገጽ ሳይ በጣም ነው ደስ ያለኝ .

እኔ የክብረ መንግሥት ልጅ ብሆንም ቦሬ በምንም አኳኃን ቆም ብለን ካልተዝናናንማ አይሆንም .

የታወቀውን የቦሬ የማር ጠጅ ""ፉት "" ለማለት ከዚያም የሚችሉትን ያህል አገር ያስመሰገነውን ""የገብስ ቆሎ "" ተሸክሞ ለመሄድ ለክብረ መንግሥቶች አማራጭ የሌለው ነበር .

ቦሬን በጣም እንወዳታለን . እኔ በበኩሌ በጣም እወዳታለሁ .

ለማንኛውም የጉርብትናየን ሰላም ለማለት ነው ቤታችሁ የገባሁት . እናንተም ወደ "ራስብሩ ክብረ መንግሥት ፔጅ " ጎራ በሉና ቡና ተጋበዙ .

በነገራችን ላይ ኢርባንና አገረ ሰላምን አንርሳ .

በሉ በደህና ቆይሉን .
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Wed Nov 01, 2006 4:05 am    Post subject: Reply with quote

ባለሱቅ ለጉድ ነው ያሳከኝ ;;ለነገሩ ያለመተዋወቃችን እንጂ የዛኔ ብንተዋወቅ ኖሮ
አሁን ላልከው ህመም የሚሆን መድሀኒት ለብርዱ ሙቀት የሚሰጥህን ጊንቢቾ እጋብዝህ ነበር ;;
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Wed Nov 01, 2006 4:14 am    Post subject: Reply with quote

ባለሱቅ የጻፈውን አይቼ መልሱን ፖስት እንዳረኩ ሌላ ታላቅ እንግዳ በር ላይ ስላገ
ኘሁ ነው የተመለስኩት ;;አንፈራራ እግዜር ያክብርልን ;;የጎረቤት ጥሩ እንደዚህ ነው ;;በቦሬ ልጆች ፔጅ ስም አመሰግናለሁ ;;ቡናውንም እንደተለመደው እየመጣን እንጠጣለን ;;እንዳልከው ኢርባንና ሀገረሰላምንም የምናነሳበት አጋጣሚም ወደ ፊት
በምናነሳቸው ጉዳዮች ሁሉ ይኖራሉ ;;ደህና ሁኑልኝ ;;
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የግልነስ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Feb 2005
Posts: 787
Location: united states

PostPosted: Wed Nov 01, 2006 4:21 am    Post subject: Reply with quote

ስላምምም ለቦሪዎቸ እንዲት ናቸው ?
መቺም ባለሱቅንን ተከትዩ መግባት ሆናል ስራዩ
ቅቅቅቅቅቅ ትዝታቸው ደስስ ይላልል ቦሪ
ሲነሳ ""አማረ እንዳለ "" ""መታፈሪያ "" እንዳለ 2ቱን
ወንድማማቸ ስም ፈልጊ ሳጣ ነው የጠየኳቸው
እንደ ቤተስብ የማያቸው ናቸው እና አረሳቸውም
(የአማረ እንዳለ ) አድራሻ ያለው ብታቀብሉኝኝ ደስ ይለኛል
ሞፈቲ , ውቢ -ጃሎ , የቦሪዋ አትጥፋ እኛም ብቅ በሉ
ወዩዎቸ ጋም እነጠያየቅ በተረፈ መልካም ጨውውት
ብያለው ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

የግልልልልልልልልልልልል ነኝ
ከአዶላ ምድርርርርርርርርርርር
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ደጉ

ዋና አለቃ

Joined: 15 Dec 2003
Posts: 5233
Location: afghanistan

PostPosted: Wed Nov 01, 2006 1:52 pm    Post subject: :-) Reply with quote

...መቼም ቦሬን አላውቅም ብል እዚህ ያሉ ሰዎች ይታዘቡኛል ....Wink ስለ ቦሬ የተጻፈውን ብዙውን ባላነብም እሚወራው ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉን ወደ ሶስት ከሚሆኑት ...ቡሬ ...ቦሬዎች ውስጥ አንዱዋ ደቡብ በአሁኑ በቦረና ክልል የሲዳሞ አዋሳኝዋ መሆኑን መረዳት ችያለሁ ....ስለ ቦሬ አዋሳ ርቀት ይህ ነው ብዬ ባልልም በኔ አቆጣጠር 120 ኪሜ ላይ እምትገኝ ቀዝቅዛ መህረብ እምታክል ከተማ ነች .... ከተማዋን ደመቅ እሚያደርጋት የአውቶቡስ እዛ ለምሳና ለአዳር መመረጥዋ ሲሆን ...ሁሉም እንደሚለው ቦሬ በነጭ የገተሜ ዛፍ ማር እና በቆሎ ከዛም አልፎ መንገድዋ ላይ ጫት በልተው በደነዘዙ ልብ አድርቅ ፍየሎችዋ ትታወቃለች .... ቦሬ ያለው የወያላ ብዛት ከከተማዋ አቅም በላይ ነው .... ሹፌሮች ሆቴል በራፍ ላይ ቁጭ ብሎ ለሚታዘብ ግርግሩ ታሪክ ነው ..... ሆቴሎች ለመፈለግ ችግር አይኖርም ሁሉም ከመንገዱ ዳር ላይ ናቸው .... ቦሬ ከወደ አዲስ አበባ ሲገባ በርቀት ከሚታየው መንግስቱ ህይለማርያም ያስተከተለው ዛፍ በግራ እና በቀኝ ይታያል በሁዋላ በሁዋላ ለስልክ እንጨት ብሎ አዲሱ መንግስት ሲጨፈጭፍ ነበር ያሁኑን አላውቅም .....ሌላው ወደ ሶላሞ መሄጃ ያለው ጥሩ እና ቆንጆ እምለው የተፈጥሮዋ አካባቢ ነበር .....ከተማዋን በስእል ለማስቀመጥ ያክል ...ገና ስትገቡ ወደ ግራ ከመታጠፋችሁ በፊት የህይስኩል አጥር ይታያል ከዛ እንደ ዞራችሁ ቁልቁለቱን ስትጀምሩ የቦሬ ቤተክርስቲያንን የባንኩን አጥር አስታኮ ይታያችሁዋል ...በግራና በኩል የቀርቅህ አጥር ያላቸው ቤቶች አሉ .....ከባንኩ ፊት ለፊት ፖስታ ቤት ሲኖር በዚህ ፖስታ ቤት የላኩትም ሆነ የተላክልኝ ፖስታ ደርሶኝ አያውቅም ...ልጅትዋን በዚህ ምክንያት አልወዳትም ነበር ....ከዛ ኬላውን እንዳለፋችሁ በቀኝ ካለው ዝነኛው ፋርማሲ አሁን ለጊዜው ስሙ ጠፋኝ ...ከዛ የወጣቶች ካፍቴሪያ የነበረው (በሁዋላ የሙሉ ሆቴል ) ወደ አስተዳደር አቅጣጫ በግራ ስልክ ቤት ...አንቱ ብዬ አክብሬ እስክምወጣ ያኮረፈችኝ ወፍራም ጥቁር ሴትዮ ..ሴት ልጅዋ በሁዋላ መሞትዋን ሰማሁ ...Sad ከዛ አስተዳደር , ፖሊስ ፍርድቤት ..ወዘተ ...ከሁሉ እማስታውሰው አስተዳደር በቀለ ደንቢ Smile ክወያኔ ተወካይ ደግሞ /መስቀል ....ለነገሩ ስራ ያገናኘኝ የነበረው ከኢሰፓ ወኪል ከነበረው አሪፍ ሰው ጋር ነበር /ጉዋድ ካሳ / በሁዋላ ህዝብ ነጻ ያወጣው ..ከምር የስራ ሰው ነበር ....ከባንክም እነ አይናለምን በሚገባ አውቃቸዋለሁ ..አይናለም አሪፍ ሰው ነበር ....
ከዛ በሁዋላ ያለው የከተማዋ አቀማመጥ በግራ ጎሚስታ ...ሹፌሮች ሆቴል ...በቀኝ ደስይበል ሆቴል ከሱ ጎን ደግሞ አንድ ጠጅ ቤትና ሱቆች ...Smile በሱ ተርታ ከሚገኙት ውስጥ የታንጉት ጠጅ ቤት ....ስለ ሴትየዋ ባል ሳስብ ይርባ ሙዳ ላይ በህዋርያት ቸርች ተከታዮች በድንጋይ ተቀጥቅጦ የተገደለው የግል አውቶቡስ ሹፌር ትዝ ይለኛል ...የዋህ ብቻ ሳይሆን ጅል ትራፊክ ነበር ....እስቲ ለሁሉም ስለ ቦሬ እማውቀውን ቀስ እያልኩ እናገራለሁ ....Smile
_________________
" STUPID IS AS STUPID DOES " Very Happy
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ማርና ወተቴ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 13 Oct 2006
Posts: 72
Location: england

PostPosted: Wed Nov 01, 2006 6:50 pm    Post subject: Reply with quote

ዛሬስ አይኔን ማመን ነው ያቃተኝ : ማለቴ እንግዳ በዝቶብን :
በድጋሚ ባለሱቅ
አንፈራራ
የግልነስ
ደጉ
እንኳን ደህና መጣችሁ ቤት ለእንግዳ ብያለሁ :ለተሳትፏችሁ ምስጋናዬ ይህ ነው አይባልም ::
ባለሱቅ =ለአይን ህክምና ወደ ጎሳ ያደረከው ጉዞ የተደረገልህ ህክምና አስገራሚ ነው : ጋሽ ዝኑ የቀበሌ ሊቀመንበር የነበረ ቢሆንም የተመረጠው ቀይ ሽብር ካበቃ በህዋላ ነበር እናም በአብዛኛው የተሰማራው የቤት አበል በመክፈል ላይ ስለነበር አትስጋ ::
ወንድማችን አንፈራራ = በእዉነቱ አሁን የክ / ልጆች ገጽ ላይ የምትጽፈው ቀደም ያለ ታሪክ ደስ የሚል ነው :;እኛ ሁሌም የናንተን እናነባለን የናንተም ሞራል ነው ያነሳሳን :እንዳልከው ይርባሙዳን አገረሰላምን አንረሳም ለምሳሌ እኔ ሁለቱም ከተሞች ተምሬያለሁ እና ያለንን ትዝታ ወደፊት ጠቀስ እናደርጋለን :ለጉብኝትህ በድጋሚ ምስጋና ይድረስህ ::
የግልነስ ==ደህና ነሽ ወይ ? አንቺንም የአዶላ ልጆችን ፔጅ ሳነብ በዝና እንደሌሎቹ አዉቅሻለሁ ዛሬ እኛን ለመጎብኘት ብቅ በማለትሽ ደስ ብሎናል ::
ያልሻቸው ልጆች አማረ እንዳለ ከነቅጽል ስሙ ትርጉም ቀደምባሉት ገጾች ላይ ወንድሙ ተሰማ እንዳለን (ባቡሮን ) ጨምሮ ተጠቅሷል :ስላላየሽው ይሆናል አማረ ሞያሌ ነው ያለው በህክምና ሙያ ይሰራል አድራሻዉን ከፈለግሽ ወደፊት ልገልጽልሽ እችላለሁ ::
ሌላው ያልሽው መታፈሪያ እንዳለ (ሻምበል ) በቤተሰቡም ሆነ በሌሎች ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የነበረ ሲሆን እሱም ኤርትራ (ሳህል ) ዉስጥ በእስር ላይ እንደነበር አንዳንድ የአይን ምስክሮች ሳይቀሩ ሚናገሩ ቢሆንም እስከአሁን ይሄው 15 አመት ሊሆን ነው ሁኔታው አይታወቅም ::
<ወንድሜ ደጉ >
በድጋሚ እንኳን ደህና መጣህ ! ጽሁፍህን ሳየው በጣም ነው የተደሰትኩት ብዙ ቦታ ዋርካ ላይ ስለ ተለያዩ ከተሞች የምትሰጠውን አስተያየት እያነበብኩ ይገርመኝ ነበር :ይህ ሰው ቱሪዝም ነው ሚሰራው ሁሉ እልነበር :
አንዴ እንደዉም አሁን ገጹን ባላስታዉስም እዚሁ ዋርካ ላይ ስለቦሬ ተነስቶ ሱኬ ቀሌ የተባሉ የገጠር ቀበሌዎችን ሁሉ አንስተህ የጻፍከውን አንብቤ እንደነበር አስታዉሳለሁ :አሁንም ስለ ቦሬ ያስቀመጥከው ድንቅ ነው :
በተለይ በጣም ያሳቀኝ ---
በደላላ ብዛት ያልከው እርግጥ መሆኑና የጫት ገራባ በልተው የሰከሩ ፍየሎች ያልከው በተለይ በጣም አስቆኛል :;
በተለይ እንግዳ ሰው ቆሎ በላስቲክ ገዝቶ ወደ አዉቶቢሱ ላይ ሊሳፈር ሲል ከህዋላ ተከትለው ጠብቀው ላስቲኩን በአፋቸው ሲጎትቱት ይደፋል , ሰዉዬው ሮጦ ይሳፈራል እነሱ ስራቸውን ይሰራሉ : ይህንን እራሱ ቆሞ ማየት አንድ ድራማ ነበር ::
ሌላው ያነሳኸው የታንጉት ባል ይርባ በአዉቶቢስ
ሹፌሩ ላይ በተደረገው ዘግናኝና አሰቃቂ ግድያ ሁሌም ተወቃሽ ነው : ሁሉንም እግዚያብሄር ነፍሳቸውን ይማረው ::
እና ደጉ በጣም ነው ያስደሰትከኝ ስለበቀለ ደንቢ ገብረ ዮሀንስ ወደፊት አጫዉትሀለሁ ::
ወንድሜ ሞፊቲ ደጋግመህ በመግባት እንግዶችን በማስተናገድህ ትደነቃለህ :
ሌላው ባለፈው የረሳሁት የልጆች ዝርዝር አለኝ
ለጨፌ የተጫወቱ ከሰው ነው የተነገረኝ
ሀረገ ወይን መኮንን
ጌታቸው ዘርፉ (ኮቶላ )
ሲሆኑ ሌሎች ከቤተሰብ ጋር ቦሬ መጥተው ሲማሩ በተለያዩ ሰፈር ይጫወቱ ነበር እነርሱም =
-ሞገስ ለማ (የመምህር ግዛው ለማ ወንድም )
-ደረጀ ይርጋሸዋ (የመምህር ብዙሰው ታመነ ወንድም )የደስደስ ያለው ልጅ ጉንጩ እስከአሁን ትዝ ይለኛል ::
-አዉራሪስ ወንድይራድ (የመምህር ጌታሁን ወንድይራድ ወንድም ) አዉራሪስ በተለይ ሚታወቀው ከሽቦ ከጫማ ቀለም ቆርቆሮ መኪና በመስራት መብራት ሁሉ ሳይቀር አድርጎ በመንዳት ነው እኛም እሱን ተከትለን ስንጎረጉር ነበር ምንዉለው ::
-የተስፋዬ ቀልቤሮ ልጆች
-አዲሱ ተስፋዬ
-ምህረት ተስፋዬ
እና ሌሎችን ሳስታዉስ ------
ሞፊቲ ሌላው ያነሳኸው የአብነት ጉዳይ ሲሆን እዉነት ለመናገር በመሬት የሚመጡ ኳሶችን አይችልም እንጂ ሰው የጠፋ ቀን ለቤተክርስትያን ቡድን በረኛ ሆኖ ሲሰለፍ አይቼዋለሁ ::
ባይይይይይ -------
_________________
az
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4 ... 64, 65, 66  Next
Page 3 of 66

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia