WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ትዝታዬ : ናፍቆቴና ግርምቴ ! እናቴ !
Goto page Previous  1, 2, 3, 4 ... 14, 15, 16  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ዉቃው

ዋና ኮትኳች

Joined: 07 Jan 2007
Posts: 969

PostPosted: Sat Apr 14, 2007 9:03 pm    Post subject: Reply with quote

እስኪ አሁን ደግሞ ወደ ግርምቴ ልግባ ::

ግርምቴን በልጅነት ገደብ አልወስነውም :: ወደዛም ወደዚህም አደርገዋለሁ ::
አንዳንዶቻችን ፍቅር የሚባል ነገር ይዞንም ሆነ ገጥሞን የማያውቅ ሲሆን አንዳዶቻችን ደጋግሞናል :: በተለይ የመጀመሪያዋን ፍቅር የማያስታውስ የለም :: ከመጀመሪያዪቱ ልጅ ጋር ድብን ያለ ፍቅር የያዘኝ በዘጠነኘኛው ክፍል ነበር :: እሷን ማየቱ ብቻ ነበር የሚያስደስተኝ :: ሳልነግራት ሳታውቀው ምንም ሳንባባል : እኔ ግን ግብግብ እንዳልኩ አስራ ሁለተኛ ክፍል አልቆ ተለያያን :: ልጅቷን ሰለወደድኳት ነበር መሰለኝ ያልቀርብኳት እንጂ : ከነቦጌ ጋር በዚያ ጉዳይ ገባ ወጣው ከተጀመረማ ቆይቷል ::

ከዘመናት በኋላም እንዲሁ ካንዲት ልጅ ጋር የመተዋወቅ እድል ገጠመኝ :: እንደመጀመሪያው ድብን ያደረገ ፍቀር ባይሆንም የሆነ ነገሯን ግን በጣም ወድጄዋለሁ :: በኔ አሪፍነት ሳይሆን በሷ የድሬ ልጅነት ቶሎ ተግባባን :: አብረን አበድን :: ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ድሬ ሲባል ጆሮዬ ይቆማል ::

አንድ ጊዜ ግን ቆም ብዬ ሳሰብ : ሁለቱንም የወደድኳቸው
እግሮቻቸውን አይቼ ነው :: Shocked ብዙ ሰው እገሊትን ወደድኩ ሲል ጸጉሯ : ዓይኗ : አስተሳሰቧ : ቅርጿ : ጥርሶቿ ወዘተ ይላሉ :: እኔ ግን ለእግር እሞታለሁ :: በተለይ እኔ የምወዳቸውን የእግር ጣቶች ካየሁ : ከወገቤ በታች የሆነ ነገር መላወሱ አይቀርም :: እግሮች ተርን ኦን ያደርጉኛል :: እነጌታ አቀርቅሬ ሰሄድ ሲያዩኝ
"እሱ ' ዓይናፋር ነው " ይላሉ :: እኔ እማቀረቅረውስ ጥሩ እግር ፍለጋ ! እንግዲህ ደግሞ ሌላ ነገር እንዳትሉኝ :: booty እና booby ከፍተኛ አድናቂ ነኝ ::

ብቅ እላለሁ ወደኍላ ::
ግን ለምን ይሆን እግር እንዲህ የምወደው ?
_________________
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Ethio Girl

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 18 Aug 2004
Posts: 92
Location: united states

PostPosted: Sun Apr 15, 2007 9:33 pm    Post subject: Reply with quote

Laughing Laughing Laughing Laughing በናትህ ቶሎ ቶሎ ቀጥልበት
_________________
If you want your life to be a magnificent story, then begin by realizing that you are the author and every day you have the opportunity to write a new page."
Mark Houlahan –
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አንቴ

ኮትኳች

Joined: 10 Sep 2005
Posts: 242
Location: ethiopia

PostPosted: Sun Apr 15, 2007 10:45 pm    Post subject: Reply with quote

ውቃው ዋርካ አንተን በማስተናገዷ የዋርካ አድሚኖች ሊኮሩ ይገባቸዋል ::በጣም የወጣልህ ቀልደኛ ነህ ::ችግሩ ልብ ማንጠልጠል ትወዳለህ ::ግዴለም ይህንንስ ማን አየበት ! በል ጻፍ ጻፍ አርገዋ Exclamation Exclamation Very Happy Very Happy Very Happy Very Happy
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዉቃው

ዋና ኮትኳች

Joined: 07 Jan 2007
Posts: 969

PostPosted: Tue May 22, 2007 1:42 am    Post subject: Reply with quote

ፒያሳዬ

አቤት ፒያሳን ስወዳት ! አሁንም ልቤ እስኪጠፋ እወዳታለሁ :: ምን አስነክታኝ ይሆን ? አድጌም ሆነ ልጅ ሆኜ የፒያሳ ትዝታ ብዙ ነው ::

ከፒያሳ ጋር በቀዳሚነት ያገኛኘኝ ቢስክሌትና ሲኒማ ናቸው :: ለአራዳ ህንጻ ሰራ መንገድ በመዘጋቱና ስራውም በመጓተቱ ምክንያት : የነገዛኸኝንና ሰበታን ቢስክሌቶች ድርሻቸው እስኪጠፋ አልፈተናቸዋል :: ገዛኸኝ የብሲክሌቶቹ ባለቤት ሲሆን : ትንሽ ቆጣ ያለ ቢጤ ነበር :: መደበኛ ሰራው የአውቶቡስ ኪስ አውላቂ የሆነው ሰበታ : ገዛኸኝን እየመጣ ያግዘዋል :: እኛ የምንወደው ግን ሰበታን ነው : አንድ ሁለት ዙር ሰለሚመርቅልን :: አሁንም ድረስ በጣም የሚገረመኝ ግን : የሰበታ ጓደኞች የኪስ ማውለቅ ስራ በማይበዛበት ወይም በሚቀዘቅዝበት ሰዓት ተሰብሰብው የሚያወሩት ነገር ነው :: ሰለዓለም ጉዳይ አንድ አይቀራቸውም :: ይተነተናሉ : ያብራራሉ አንዳንዴ ደግሞ ለገላጋይ እስኪያስቸግሩ ደረስ ይከራከራሉ :: ከሌባም ቁምነገር እንደሚገኝ ያውኩት ያኔ ነው ::

ከቢስክሌቱ በኋላ ሙዚቃ በነጻ እንሰማለን :: ወይ ፎቶ ብርሀን አጠገብ ካለው ሙዚቃ ቤት ካልሆነም ማህሙድ ሙዚቃ ቤት ስር እንቆማለን :: የዝፋኞቹንም ፖስተር ማየት አንዱ መዝናኛችን ነበር :: አያሌው ሙዚቃ ቤትን ግን ብዙም አንወደውም ነበር :: አኸ ! እኛ መስማት የምንፈለገው የንዋይን አያሌው የሚክፍተው የጥላሁንን ! በዛ ላይ በጣም የድሮ ዘፈን ! እንደዛሬው የተገላቢጦች የድሮ ሙዚቃ ወዳጅ ሳልሆን ማለቴ ነው :: Very Happy

ሌላው ፒያሳን ግርም የሚይስብለኝ የሊስትሮውና የወያላው ብዛት :: ያኔ ድሮ ሚባስ ታክሲዎች ሳይመጡና ውይይት ብቻ በነበረበት ጊዜ በፒያሳ በደንብ የማሳታውሰው የወያሎች አለቃ (ተራ ስከባሪ ) ዲስኮ ይባል ነበር :: ጠቆር : ቀጥ ያለና ቀጭን ነው :: ሲናገር ፈጠን ፈጠን ይላል :: በህይወቴ ስቆ አይቼው አላውቅም :: መሳቅ የሚችልም አይመሰለኝም :: ታዲያ አንዳንዴ ዲስኮ በል ሲለው ተራቸው ያልደረሰ ወያሎችን ሰብሰቦ ከሙዚቃ ቤቱ እኩል አብረው እንደዘፍኑ ያስገዳደቸው ነበር :: በቃ ያው ወያላውም ሊስትሮውም ይሰበስብና ከአስቴር ዘፈን እኩል ወይኔ ወይኔ ሲል ይውላል ::

ሌላው ልጅነቴን የሚያስታውሰኝ የፒያሳ ትዝታ : የአካባቢው ልዩ መዓዛ ነው :: መቼም ለፒያሳ ውበት ሲባል : በዚያ ዘመን : በክፍቱ ባዶ ቦታ ላይ የበኩሉን ከፈሳሹ እሰከደረቁ ያላበረከተ የለም :: ለፒያሳ ግብር የተበረከተው ሰጦታ : ጥቂት ጸሀይ ካገኘ በቂው ነው :: አካባቢውን በጣፋቹ ሽታው ያውደዋል :: አንዳንዴ ጠንከር ያለ ነፋስ ከገጠመ : መተንፈስ ማቆም ግድ ይላል :: ግን ደግሞ ይለመዳል :: አንድም ቀን ሲያማርር የስማሁትም ሰው የለም :: ባይወዱትም ለምደውታል ማለት ነው :: ከላይ ደግሞ በበጋ አቧራው በክረምት ደግሞ ጭቃው ላይ እኔነኝ ያለ እግርኳስ ግጥሚያ ይከናወናል :: ከበጋው ግን የክረምቱ ያዝናናል :: በቃ ኳስ ይጫወታሉ ሳይሆን ጭቃ ያቦካሉ ቢባል ይቀላል :: በርግጥ ጨዋታው አልቆ ወደየመጡበት ሲበታተኑና ቤታቸው ሲገቡ : ኳስ ተጫውተን መጣን እንጂ ጭቃ ሰናቦካ ውለን መጣን አይሉም :: አይ የፒያሳ ልጆች !
_________________
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዉቃው

ዋና ኮትኳች

Joined: 07 Jan 2007
Posts: 969

PostPosted: Tue May 22, 2007 2:45 am    Post subject: Reply with quote

ፒያሳዬ

ከፍ እያልኩ ስመጣ : ቢስኪሌትና ሙዚቃ የፋራ ስራ ሲሆንብን : ወደሲኒማና ሞተርሳይክል ከፍ አልን :: ሞተርሳይክሉ ግን ሳንፈልግ ወደስቴድየም ወሰደን :: እሱ ደግሞ ሌላ ታሪክ ነው :: የፒያሳዬ ግን ከሲኒማው ጋር የመኮንን ቤት ባቅላባ ወጪ ይህ ነው ከማይባሉ ቆራሌዎች ጋር አስተዋውቆኝ ነበር :: የቅባት ጠርሙስ : የሳልሳና የሰርዲን : ባዶ ዕቃዎች አልቀው ወደሌላም ከፍ ብዬ ነበር :: ቆራሌዎች በበራችን ሲያልፉ ከተለመደው በተለየ መልኩ አንድ ሶስቴ በመደጋገም : ቆራሌዎ ማለታቸው አይቀርም :: በበር እያለፍን ማለታቸው ነው :: የተሸጠው ተሽጦ ሩጫ ወደ ሲኒማ ኢትዮጵያ !

ሲኒማ ኢትዮጵያ ከህንድ ፊልም ወደ ሆሊውድ እየተሸጋገረ ሰለነበር ጊዜው ለኛ አሰደሳች ነበር :: ብዙው የሚቀረበው ፊልም ግን በጃንሆይ ጊዜ የተሰራው ነበር :: አንዳንዴ አጠገብ የተቀመጠ ሰው ሳይታዘዝ ፊልሙን መተረጎም ይጀምራል :: ምናልባት ከሱ አጠገብ የተቀመጠው ትርጉሙ ትክክል አይደለም በሚል ክርክር ሊጀምሩ ይችላሉ :: አንዱ ከወዲያ ጥግ :አንተ ዝም አትልም ?" ይላቸውና ዝም ይላሉ ::

ከሁሉ የሚያሰቀኝ የነበረው ደግሞ : ምናልባት በፊልሙ ላይ የመሳሳም ወይም የወሲብ ትዕይንት አሊያም ከፊል እርቃኗን የምትታይ ሴት ካለች : ከአዳራሹ የተለያዩ አቅጫዎች የማጓራትና የሲቃ ስሜቶች መሰማት ይጀምራሉ :: አንዱ አንዱን እየተከተለ ልባችን እስኪፈርስ ያስቁናል ::
ደግሞ ሌላው አስገራሚ ነገር ደግሞ : መሪ ተዋናዩ ጠላት የሚባሉትን ማሸነፍ ሲጀምር : ሲኒማ ቤቱ በጭብጭባ ይቀልጣል :: ከግራ ከቀኝ በለው : ግደለው የሚሉ ቃላት በእልህ መወርወር ይጀምራሉ :: ተመልካቹ ትያትር ቤት ገብቶ ለተዋናዮቹ እንደሚሰጠው ጭብጨባ : በሲንማ ቤትም ለማያዩንና ለማይሰሙን አክተሮች ጭብጭባ እንለግሳለን :: ያው በስሜት እየተዋጥን የምናደርገው ነበር ::
_________________
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ትትና

ውሃ አጠጪ

Joined: 23 Feb 2005
Posts: 1474
Location: united states

PostPosted: Tue May 22, 2007 10:59 am    Post subject: Reply with quote

Very Happy ውቃው ሙት በጣም የምታስቅ ልጅ ነህ ! እንዴት እንዴት እንደምታቀነባብረው ! የፍሪጁማ ገደለኝ ! ልክ እኛ ቤት ብፌ ውስጥ ተቆልፎባቸው እንዳሉት ብርጭቆዎች ማለት ነው :: ሁሌ ጌጦች :: እርካሽ ይገዛል እንጂ የድሮውን ማን ነክቶት ! እኔ ሄጄ ለማውጣት ብሞክር መቼ እንደምመለስ ጥያቄ ቀረበልኝ Very Happy "ብርጭቆዎቼን "! የሚለው የማዬ ድምጽ ሁሉነው የመጣብኝ :: አቤት እነዛ የዳንቴል የሶፋ ጨርቆች Very Happy ውይይ የእድሜያቸው እርዝመት !

ትዝታውም ግርምቱም
ሀሪፍ ነው !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቤቲ _13

ዋና ኮትኳች

Joined: 18 Sep 2006
Posts: 723
Location: ethiopia

PostPosted: Tue May 22, 2007 1:22 pm    Post subject: Reply with quote

Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing እረ እዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑ አሀሀሀሀሀሀሀ ፍፍርፍር አሀሀሀሀሀሀዐ ወይ ጉድ በቃህ ቀጥል ይሉታል እንዴ እረ ሆዴን እዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑኡ አሀሀሀሀሀ ፍርፍርፍር ከት ከትከት የልቢን ሲነግሩት አሉ ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ አሀሀሀሀሀሀ እኡዕዕዕዕዕዕዕዕዕዕዕዕዕዕዕዕዕዕዕዕዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑዑ የተረገምክ ልጅ .....
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website MSN Messenger Report post
yammi

ኮትኳች

Joined: 28 Jul 2006
Posts: 436

PostPosted: Tue May 22, 2007 10:49 pm    Post subject: Reply with quote

ውቃው

ይገርማል :: ትዝታህ ያልተጋነነ ........የማያሰለች ..........ከሁሉም በላይ ልብን የሚያንጠለጥል ትክክለኛ የህይወት ቅንጫቢ ነው ::ከአሁኑ ነገ ደግሞ ምን ይጽፍ ይሆን ብዬ ማሰላሰል ጀምሪያለሁ :: እባክህ ቶሎ ቶሎ ጻፍ ::

ያሚ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የመንደራው

ኮትኳች

Joined: 05 Oct 2006
Posts: 189

PostPosted: Tue May 22, 2007 10:53 pm    Post subject: Reply with quote

ውቃውየ የሰው ዘር ሰላም ነህ በርታልኝ እስኪ ጨመርመር አደገው በል ሰላም ሁን ባለህበት እስኪ ፍርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርጥ ብየ መውጣቴ ነው

የመንደራው ነኝ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቤቲ _13

ዋና ኮትኳች

Joined: 18 Sep 2006
Posts: 723
Location: ethiopia

PostPosted: Fri May 25, 2007 2:11 pm    Post subject: Reply with quote

እስኪ ዉቃዉ ....ያቺ ቅቅ በግል የነግርከኝን ባደባባይ ለጥፋት ካልሲ እየሰረቅክ ኳስ የምትሰራት ቅቅቅቅ ትዝ ይልሀል እድር ሊከፍሉ ሲመጡ ሁለት አይነት አድረግዉ የመጡት አጎትህ ሲማረሩ በልጃቸዉ አንተ አባልገህባቸዉ ልጃቸዉን ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
አብዮት ጥበቃ ቅቅቅቅ በካልሲ ማሰረቅ አንድ ቀን የቁንጫ ቤት ቅጣት የትፈረደብህ ቅቅቅ እስኪ እስዋን አጣጥመህ አቅርብላቸዉ
የሰፈርህ ልጅ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website MSN Messenger Report post
ቤቲ _13

ዋና ኮትኳች

Joined: 18 Sep 2006
Posts: 723
Location: ethiopia

PostPosted: Fri May 25, 2007 2:17 pm    Post subject: Reply with quote

ያቺስ በልዩ አጠራርዋ መዙሌ .....(ማዘጋጃ ) ቡሌ ለመጥለፍ ቅዳሜ እሁድ ዘንጥነጥ ብለን በየሸሚዛችንን እና -ሸርታችን ሱሪያችን ዉስጥ በደምብ ወሽቀን እዛ ዉስጥ የደፋነዉን አጥንት በብብታችን ስር ከተን ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ ዑዑዑዑዑዑዑዑ እስኪ ባንተ አፍ ቀመመም አድርገህ አቅርባት ....በቃ ....እንግዲህ .....
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website MSN Messenger Report post
ዉቃው

ዋና ኮትኳች

Joined: 07 Jan 2007
Posts: 969

PostPosted: Sat Jul 07, 2007 3:08 am    Post subject: Reply with quote

The Homeless Wonderer ---በእማሆይ ጽጌ ማርያም ደንቅ እናት !

ወደኋላ በደምብ የሚመልሰኝ ሙዚቃ ሰለሆነ እየሰማሁት ነው የምጽፈው :: በተለይ የእሁድ እሁዱን "ከመጻህፍት ዓለምን " ወከክ አድረጎ ያስታውሰኛል ::

ሰሞኑን በጣም ተረስቶል ይሄ ቤት ! ጠረግ ጠረግ ሸርሪቱን !

_____________________________________

Space 1999

ባንድ ወቅት ልባችንን ቀጥ ያደረግ ፊልም ! የምር ልቤ ቀጥ ልትል ደርሳ የተመለሰችበት ቀናት ቀላል አይደሉም :: ከዛ በማግስቱ እኔ ኮማደር ነኝ አንተ ቶኒ : ያኛው አለን አንቺ ደግሞ ማያ : እሷ ደግሞ ባርባራ እየተባባልን ተጣልተናል :: ፊልሙ ላይ እንዳለው የጦር መሳሪያ አይነት በቆርቆሮ ጩዝ ጩዝ ተባብለን ተገዳድለናል ::

በጣም የጨሰና ምርጥ ፊልም ነበር :: ተቀየር ተቀይሪ እንደማያ ተባብለን ኩልልልልል እያልን ራሳችንን አሞኝተናል :: የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ያኔ ፊልም የሚያሳየው ከምሽቱ አንድ ሰዓት ሰለነበር : የእንቅልፍ ችግር የለም ::ችግር ያለው የሳምንቱ ታላቅ ፊልም ቀን ቅዳሜ ነው :: ዛሬ ቁጭ ብዬ እንቅልፍ ሳይዞር ሌቱን እንዲህ ሊነጋ ያኔ : አራት ሰዓት መደረስ ራሱን የቻለ ፈተና ነበር ::

ከስፔስ 1999 በፊት ደግሞ ትዝታው እየደበዘዘብኝ የመጣ A (The) Man from Atlantic ocean የሚባልም ሌላ ልብ ሰቃይ ፊልም ነበር :: ካልተሳሳትኩ ዋነኛ ተዋናዩ ማርክ ወይም ማይክ የሚባል እና በውቂያኖስ ውስጥ እንደአሳ እየዋኘ (እንደሰው ሳይተነፍስ ) ባህር ወስጥ የሚገኙ ለየት ያሉ ፍጡራንን የሚያድን ሌላ ልብ ሰቃይ ፊልም ነበር :: ከፊልሙ በተለይ ከውቂያኖስ ውስጥ ሆኖ "ኤሊዛቤት " ብሎ የሚጣራው ነገር ትዝ ይለኛል ::

ወደ ስፔስ ስንመለስ : በፈረንጆቹ 1999 ይሆናል ያሉት ሳይደርስ አልፏል :: ምናልባት በኢትዮጵያ አቆጣጠር ይሆናልና የሰሩት በቅርቡ ሊሆን እንድሚችል እግረ መንግዴን ማሳሰብ እወዳለሁ ::

የስፔስን ኢንትሮ ከላይ ያለውን ሊንክ በመጫን ዘመኑን ያስታውሱ
_________________
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ጌታ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Apr 2005
Posts: 3229
Location: ዶሮ ተራ

PostPosted: Sat Jul 07, 2007 3:25 am    Post subject: Reply with quote

ውቂቾ

ያን ዘመን እኔም በጣም አስታውሰዋለሁ :: በሬድዮም ሆነ በቲቪ ጥሩ ነገር የምታገኘው በሳምንት እጅግ ለተወሰኑ ሰዓታት ነው :: እነዛም ሰዓቶች እጅግ ተናፋቂ ነበሩ :: ስፔስ 1999 እኮ በቃ እኔ ራሴ ሌላ ዓለም ውስጥ የገባሁ ነበር የሚመስለኝ :: ታላቅ ፊልም ??? እኔ ድሮም አሁንም ከሰው ኋላ ያስቀረኝ እንቅልፌ ነው :: ወንድምና እህቶቼ አምሽተው ሲያዩ እኔ 4 ሰዓት ድረስ መቆየት አልችልም ነበር :: ካመሸሁም እዛው ፎቴ ላይ ሽብልል ነበር የምለው ::

ካልክስ ከእንግሊዛኛ ዜና ቀጥሎ ጠብቄ ማየት የምችለው ሬሲሊንግ ነበር :: የእንግሊዞቹ ነጻ ትግል ንጹህ ስፖርት እና ፉክክር የሚታይበት ስለነበር ስንጯጯህ ነበር የምናመሸው :: ሁሌም ቀጠን ደከም ላለው ነበር የምናግዘው :: ሲደበደብ መቆጨት ሲማታ ደግሞ በለው ፍለጠው ማለት ነው :: ቢግ ዳዲ ብዙ ጊዜ ለሁለት ነው የሚመጡት :: እሳቸው ከቀጭን ልጅ ጋር ተጋጣሚዎቻቸው ደግሞ ሁለት ግብዳዎች ነበሩ :: እነዛ ግብዳዎች ቀጮን ገመዱ ጋር እንዳይደርስ አድርገው ከወቀጡት በኋላ ቢግ ዳዲ እንደምንም እጁን ነክተው ሲገቡ ድራሻቸው ይጠፋ ነበረ ::

ሌላ ካዕምሮዬ የማይጠፋው ፊልም ሲገል አይላንድ የሚባል ነበረ :: እንዴት ያስበጭጨኝ ነበር :: የኔንም ትዝታ ቀሰቀስከው :: ታዲያ እኛ ቤት እንደናንተ ዓይነት ብላክ ኤንድ ዋይት ፊሊፕስ ቲቪ ሳይሆን 56 ኢንች ፕላስዝማ ቲቪ ነበር የነበረን :: Laughing Laughing እርግጠኛ ነኝ ይህ ወሬ እነቤቲ _13 እና ሙዝ ዓይነት ፍንዳታዎች አልደረሱበትም ::
_________________
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
ዉቃው

ዋና ኮትኳች

Joined: 07 Jan 2007
Posts: 969

PostPosted: Sat Jul 07, 2007 3:55 am    Post subject: Reply with quote

U cann't touch this

ኤም ሀመር ያኔ ሸገር ብቅ ብሎ ቢሆን ኖሮ ዛሬ የወደቀበት ቦታ አይደርሰም ነበር :: ዘፈኑን እኩል መዝፈን አይደለም ከሱም በልጠን ነበር :: በኛ ተጽናንቶ ይበረታ ነበር :: ቨኒላ አይስ : ስናፕስ : ብላክ ቦክስ : ማርክ ሞሪሰን : ሚሊ ቫኒሊ : እንደነሱ ሆነናል አብደናል :;

የመጀምሪያው ንቁ የአራዳ ልጅ መለያ : ኮሌታ ማቆም ነው :: ድሮ አንገትያቸው የሚበላና ተገብጠው ለሁለተኛ ዘመን አግልግሎት ይዘጋጁ የነበሩ ሸሚዞች ዕድሜያቸው እንደዛ ዘመን ረዝሞ አያውቅም :: ቀጥ ብለው ስለሚቆሙና ከአንገት ጋር ንክኪያቸው ሰላበቃ ! ባንጻሩ ከታች ያለው የሸሚዙ ክፍል በአሰቃቂ ሁኔታ ይበላና ያልቅ ጀመር :: ቁልፍ መቆለፍ ፋሽኑ አልፎ መቋጠር ሰለተጀመረ :: ድምቅ ብለው የተነከሩ ጂንሶች : በጣም ይገርሙን ጀመር :: ደማቅ ጂንስ ልብሶ አንድ ሰው ካየን ወዲያው ማን እንደሆነ እናውቀዋለን :: እሱ ወታደር ነው ::

እነዚህ ዓመታት በሰለሞን ላደኩት ለኔው : ልዩና ወርቃማ ጊዜያት ነበሩ :: አዲስ ጂንስ የሚያደርጉትም ቢሆኑ : ልክ እንደኛው ቀለሙ የልቀቀውን እንዲለብሱ የዘመኑ ፋሽን አስገደዳቸው :: ጭራሽ በደንብ ቀለሙ እንዲልቅላቸው በበርኪና ያጥቡት ጀመር :: አዲስ ለባሾቹንና እንደኛ ያለውን ሰሌ ለባሽ : በለበስነው አይቶ : የሀብታም ልጅ ነው : የድሃ ልጅ ነው ማለት ቀረ :: ዋና መለኪያው ልብስ ሳይሆን ጫማ ሆነ :: እናቱንና ጫማ ግን ጉድ አረገን :: የጫማን ቂም አሁንም አልረሳሁትም ::

ከዚህ በፊት ግን የጆንትራ መጨረሻና የፓንክ መጀመሪያ ለይ በመድረሳችን : ከዉቃው እናት ጋር እሰጣገባው ከባድ ነበር :: ጸጉር ቤት ሄዶ መስተካከል ቆመ :: የውቃውን እናት መሸወድ ቀላል ነበር :: በተለይ በደንብ ላደገ ጸጉር ! ከቤት ሲወጣ ጽጉሩ በደንብ ይበጠራል :: የማሚን ኮንፊርሜሽን ካየሁና ከቤት ክወጣሁ በኍላ /ቤት ሳልደረስ መንገድ ላይ በሁለት እጆቼ ድብን አድረጌ ግራና ቀኝ ጭንቅላቴን ተጭኜ የቀኑን ፓንክ እሰራለሁ :: ያው ቀኑን ሙሉ ሲደመድሙ መዋል ነው እንግዲህ ! ይህ እንግዲህ ሲጀመር ነው :: በኍላ ግን አንዴ ታወቀና በግልጽ ፓንክ መቆረጥ ተጀመረ ::
ከዛ ደግሞ ከታች ጂንሱ ጠባብ ቢሆንም ጥብቅ ብሎና ታጥፎ መጠቅለል አልበት የሚባል ፋሽን መጣና : የነውቃው ጂንስ ወደ እጀጠበባብ (በያሚኛ እግረ ጠባብ ) ተመልሶ ገባ :: እሱም ብቻ አይደለም ኮትም ሆነ ጃኬት እጅጌው ታጥፎ ወደላይ መጠቅለል ፋሽን ሆነና እሱን ደግሞ እንጠቀልል ገባን :: ከዛ ደግሞ የወታደር ፊልድ ጃኬት መልበስና : የወታደር ጫማ ማድረግ ፋሽን ሆነ :: ወደኍላ ላይማ ሽጉጥ መያዝ ሁሉ ፋሽን ሆነ :: ክፍል ውስጥ የኔን እየው የኔን እየው የሚሉ ባለሽጉጦችን ማየት ማስገረሙ ቀረ :: ምን ነካን ግን !

አይ ፋሽን ! እንደጉድ ተፈሸነ ::
_________________
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዉቃው

ዋና ኮትኳች

Joined: 07 Jan 2007
Posts: 969

PostPosted: Sat Jul 07, 2007 4:07 am    Post subject: Reply with quote

ጌትሽ ስጽፍ ስለነበር ያንተን ፖስት አላየሁትም :: የነቢግ ዳዲንማ ተወኝ :: እኔ ሁሌም ለቢግዳዲ ነበር የማግዘው :: ቢግዳዲም ሁሌ እንዳሸነፈልን ነው ::

በቲቪያችን ለመላጥ መሞከርህ አሳዝኖኛል :: የኛ ቲቭ የነበረው በዘምኑ ታዋቂ የነበረውና ባለ 24 ኢንቹ ናሽናል ነው :: እላዩ ላይ ምን የመሰለ ዳንቴል ለክብሩ ሲኖረው : የአያቴ ፎቶ እንዲያደምቀው ከላዩ ይቀመጥበታል :: አይ ቲቪያችን ! አሳደገን እኮ ! Very Happy አይ ሲበላሽ የምናለቅሰው ለቅሶ !

Some of the best hits in my days.

Snap እስኪ እስኪ እስኪ እሷን አሳይኝ

ዙምባይ snap

Poison

I don't Know any bodyelse- Black box my favriote

Ice Ice baby- Vanilla Ice
_________________
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4 ... 14, 15, 16  Next
Page 3 of 16

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia