View previous topic :: View next topic
Author
Message
ብራንጎናትርን Joined: 29 Dec 2006 Posts: 608
Posted: Fri May 16, 2008 2:31 am Post subject:
"ደስታ የምናገረውን አሳጥቶኝ ነው ::" አልኩዋት :: ውስጤን ደስ ብሎታል :: ፈንጠዚያውን አልቻልኩትም :: እዛው በተቀመጥንበት ልስማት ፈለግሁ :: ሰው ምን ይለኛል ? አልኩና ተውኩት እንጂ :: በዚያ ላይ ደግሞ ገና ዛሬ ነው የውስጣችንን የተነፈስነው ::
ብሌን በሐሳቤ ብቅ አለች :: ልቤ ይሸበር ጀመር :: ሰዓቱን ሳይ የሻይ ግዜያችን እየተገባደደ ነው :: አምስት ደቂቃ ብቻ ነው የቀረን ::
"Talk to me ... you know I am listening. I want to hear more." አለችኝ በተለምደው እንግሊዝኛዋ ::
"I am serious. I am so happy. And I don't really know what to say."
"You have heard what I said right? I mean I just told you that I am in love with you."
" I know Mekiya. I also have feelings for you and that is what I was trying to tell you in the beginning."
እኔም በፍቅርሽ ተይዣለሁ ልላት አስብኩና ቃሉ ከበደኝ :: ጠብቄ ሌላ ግዜ ብነግራትስ ? አልኩ :: አሁን ካልነገርኩዋት ደግሞ "ወደድኩህ ስላልኩኝ ኮራህ ምናምን " ልትለኝ ነው :: ግራ ገባኝ :: በዚያ ላይ ብሌንን ነገ ለማየት ወስኛለሁ :: ሁለት ሴት ባንዴ ልጠይቅ :: ብሌን እሺ ብትልስ ? ምን ሊውጠኝ ነው ? ነው ወይንስ የብሌንን ጉዳይ ላርዝመው ? ለሌላ ግዜ ላቆየው ? ግራ የሚያጋባ ነገር ነው ::
እንደ በቆሎ እሸት ብርቅ የሆነች ልጅ ፊቴ ቁጭ ብላ እንደምትወደኝ እየነገረችኝ የምን ሌላ እሸት መመኘት ነው ?
ዘንድሮ ሳላብድ አልቀርም :: ሴቶች ሊያሳብዱኝ ነው ::
ያበጠው ይፈንዳ ብዬ ከመኪያ ጋር የፍቅር ጉዞ ለመጀመር ቆረጥኩ :: ብሌን ስትፈልግ ገደል ትግባ :: የሷ ፍቅር መዘዘኛ ነው :: ገና ከጅምሩ እንዲህ ፈተና የበዛብኝ ስጀምረው ደግሞ ምን ሊውጠኝ :: ሆሆ !
"መኪያ የዓይኖችሽ ውበት ልቤን እንደሚያሸብረው ነግሬሽ የለም ?"
"እና ?"
"ቅቅቅ እናማ በቃ ብዙ አትይኝ :: አልቃለሁ ::"
"ቅቅ አረ ባክህ :: ውይ ስታሳዝን :: የማነህ ቀብራራ ::"
ቀብራራ ስትል ሲያምርባት ! የመኪያ "የማነህ ቀብራራ የጌታ ልጅ መሳይ የማነህ ቀብራራ የጌታ ልጅ መሳይ ለሌላ እንዳይመስልህ አንተን ቆሜ ሳይህ ..." የሚለው ዘፈን ጆሮዬ ውስጥ እንደ ንጹህ ጅረት ይፈሳል :: ፍሰቱ ደስ ብሎኝ እያዳመጥኩ የኔዋን መኪያ ትኩር ብዬ አያታለሁ ::
"ምነው ፈዘዝክ ? መኩራት መጀመረህ ነው ወይንስ እንደኔው ፍቅር ያሳውርህ ጀመር ?" አለችኝ ሳቅ እያለች ::
"አይ አንቺ ... ፍቅር ሳያሳውረኝ አይቀርም ዘንድሮ :: ማሳወር ብቻ አይደለም ገደለም ሳይከተኝ አይቀርም ::"
"ተው እንጂ ...."
"ከምር ! አሁን ለምሳሌ የተነጋገርናቸውን ቃላት እያጠነጠንኩ ነው :: ምን ያህል ፍቅርሽ ልቤ ውስጥ ስር እንደ ሰደደ ዛሬ ነው የተረዳሁት :: በዚያ ላይ ደግሞ ስሜቱ የጋራ መሆኑ አስደስቶኛል :: እናም እያሁሽ ውዬ እያየሁሽ ባድር አልጠላም :: አይኖችሽ መስተፋቅር ሳያስደግሙብኝ አይቀሩም ::"
"ቅቅቅ አረ ባክህ :: እኔኮ ሙስሊም ነኝ ::"
"ቅቅቅ ምን ይታወቃል ብለሽ ነው :: የዘንድሮ መስተፋቅር ሙስሊም ክርስትያን አያውቅም :: ዘር ቀለም አይለይም ::"
" You are funny. I swear."
እጄን ያዘችው :: በእጆቿ መሀል አስገብታ ትዳብሰው ጀመር ::
"I swear I am in love with you. Take me somewhere. Let's fly. Like birds in the sky. I want us to go somewhere where it's quiet. Somewhere pleasant. Somewhere peaceful. You know what I mean? Let's fly freely like the birds of heaven."
በጣም ሮማንቲክ ሆነችብኝ :: ነጻነት ተነፍጋ የኖረች ወፍ መስላ ታየችኝ :: ርግብ :: መብረር እያማራት መብረር እየቻለች ነገር ግን ሳትበር የኖረች ርግብ ::
የኔንም ህይወት ስቃኘው ብዙም ከሷ የተለየ አይደለም :: ብዙ አልበረርኩም :: እናም አብሪያት መብረር ፈልግሁ :: ታየኝ :: እኔና እስዋ በነጻነት ሰማየ ሰማያትን እያቆራረጥን አየሩን እየቀዘፍን ስንበር :: ዘምባባ እየዘነጠፍን ስንበር ::
"Sure let's go somewhere. Let's fly. I wanna take you somewhere. What are you doing this week-end?" አልኩዋት በደስታ እየተፍለቀለቅኩ ::
"Are you serious? I really don't have any plans." እንሂድ ስላት አላመነችኝም መሰል :: ምን ያህል ፍቅሯ እንደራበኝ አልገባትም :: የብሌንን ሀሳብ የሚያስርቅ ፍቅር እንዳስያዘችኝ አልገባትም ::
የት ልውሰዳት ስል አሰብኩ :: ልዩ የሆነ ቦታ መውሰድ እንዳለብኝ ደመደምኩ :: አሁን ከምነግራት ለምን "ሰርፕራይዝ " አላደርጋትም ? አልኩ በሀሳቤ ::
"I will come up with the plan and I will let you know tomorrow. How does that sound to you?"
"Sounds perfect."
ደስ ብሏታል :: ፍቅር እንደ ድንገተኛ አደጋ ነው :: አሁን ይሄ ይከሰታል ብሎ ማን አሰበ :: እርግጥ ነው ስራ ቦታ መኪያን ባየሁዋት ቁጥር ልቤ ይደነግጥላት ነበር :: ግን እዚህ ደረጃ ላይ እንደርሳለን ብዬ አልጠበኩም :: ለነገሩ አሁንም ቢሆን ተጀመረ እንጂ አልተፈጸመም :: ነገ ምን እንደሚመጣ ማን ያውቃል ::
የሻይ ሰዓታችን አለቀ :: ወደ ስራ ቦታ ተያይዘን ወጣን :: አልተፋፈርንም ስንተቃቀፍ :: አዲስ የፍቅር ወፎች :: እጆቻችንን ቆላልፈን ከፐርፕል ወጣን :: ትራፊክ መንገዱን እንዳጨናነቀው ነው ::
የባለ ታክሲዎች ግርግር ጡፏል :: ቤተ ዛታ ክሊኒክ አከባቢ ሰዎች ይላቀሳሉ :: ሰው ሳያርፍ አይቀርም :: ለመኪኖች ቀይ የትራፊክ መብራት ሲበራ እኔና መኪያ ተያይዘን የእግረኞችን መንገድ አቁዋርጠን ወደ ቢሮ አቀናን :: ልቤ ትደንሳለች :: አዲስ ፍቅረኛ አግኝታለች ::
"Wow this is true. I can't believe it. We are more than friends now. Right, Israel? Tell me this is true. I am the happiest girl right now."
"Yes yene konjo. እውነት ነው :: እኔና አንቺ የፍቅር ጉዞ ጀምረናል ::" የመስሪያ ቤቱ በር ጋር ስንደርስ ጉንጯ ላይ ሳምኩዋት ::
ይሄ እንግሊዝኛ እየቀላቀልን የምናወራው ነገር እየገረመኝ ነው :: ሳልወድ በግድ ለሷ ስል ፈረንጅኛ ማውራቱ እየጣመኝ መጥቷል :: የፍለን መምህሮቼን በልቤ አመሰገንኩ ::
ስስማት ....
ቅቅቅ እሷ ::
ቅቅቅ እኔ ::
የደስታ ሳቅ :: የአፍላ ፍቅር ሳቅ :: እንጭጭ ፍቅር ::
ብሌን ለግዜው ትዛታ ትሆለች :: የአዕምሮዬ ካዝና ውስጥ የተቆለፈች ሆኖም እንደ ነገሮች አመቺነት ተከፍታ ልትታይ የምትችል የተከበረች የፍቅር ጣዖት ::
ድራማ ነው :: ህይወት ድራማ ናት ::
ሀላፊያችን ምን ይል ይሆን ?
ጉንጯን ስስም ቀስ ብላ እየፈራች ከንፈሬን ስማ ሮጣ ቢሮዋ ገባች :: አይናፋር :: እንደሳመችኝ አይኖቼን እንኩዋ አላየችም ::
የኔስ ምን ይባላል ? ሰውን እወድሻለሁ እያሉ ጉንጭን መሳም ? ሆሆይ ... እሷ ተሽላ ተገኘች ::
ልቤ የደስታ ከበሮ እየደለቀች የቢሮዬን በር ከፍቼ ገባሁ ::
ምንም የመረበሽ ስሜት ሳይሰማኝ ስራዬን ጀመርኩ ::
ነገ ሌላ ቀን ነው :: ነገ ጁማዓ ነው ::
በስራዬ መሀል ቀና እያልኩ በር በሩን አያለሁ :: ወፊቱ ብቅ ትል ይሆን እያልኩ :: ርግቢቱ ካሁኑ ትናፍቀኝ ጀመር :: ብሌንን የማስብበት ሰዓት የለኝም ::
በሩ ሲጥጥ ብሎ ተከፈተ :: ቀና ስል ... _________________ "The purpose of education is not to fill buckets, but to light fires." – Yeats
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
መልከጻዲቅ Joined: 08 Aug 2007 Posts: 675
Posted: Fri May 16, 2008 7:44 am Post subject:
አሽብር የመስሪያ ቤታችን ደብዳቤ አመላላሽ ነው :: አሽብር በተላላኪነት ተመድቦ ይስራ እንጂ ከድርጅቱ ባለቤት ጋራ ዝምድና ብጤ ስላለው በውስጡ የአለቅነት ስሜት ይሰማዋል :: ስራ የጀመረኩ ሰሞን የባለቤቱ ቀኝ እጅ መሆኑን ሊያሳየኝ ቡዙ ሲደክም ነበር :: አንድ ጊዜ ባለቤቱ እኔ ቢሮ ውስጥ መሆኑን ሳያቅ እንደለመደው ሳያንኴኴ ሲገባ አጉራ -ዘለልነትና ብልግና መሆኑን ሁለተኛ የትኛውም ቢሮ ሳያንኴኴና ከውስጥ ይግቡ የሚል ድምጽ ሳይሰማ ዘሎ እንዳይገባ ማስጠንቀቂያ ከሰጠው በኌላ ነው አደብ የገዛው :: "" ታዲያስ አሸብር ምን ነበር ?"" አልኩት "" ይቺን ደብዳቤ አንድ ልጅ ናት እባክህ በእጁ ስጥልኝ ብላ የሰጠችኝ "" ለኔ ማን ትሆን ?"" አልኩት ፊቱ ላይ መልስ የተጻፈ ይመስል ትክ ብዬ እያየሁት :: "" ማንነቷንማ ደብዳቤው ይነግርሀል "" አለኝ ደብዳቤውን እያቀበለኝ :: ""ከብሌን "" ይላል ክው አልኩ :: እንዴት እዚህ መስራቴን አወቀች ? አሸብር በሩን ዘግቶ ሲወጣ እንኴን አላስተዋልኩም ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ብራንጎናትርን Joined: 29 Dec 2006 Posts: 608
Posted: Fri May 16, 2008 9:07 am Post subject:
ደብዳቤውን እየገለባበጥኩ አየሁት :: ደስታ አይሉት ድንጋጤ ሰውነቴ ውስጥ ይተረማመስ ጀመር :: ከተቀመጥኩበት ወንበር ዘልዬ ተነሳሁ ::
ደብዳቤውን እያገላበጥኩ ከሳምኩት በሁዋላ "Why NOW? Why TODAY? WHY? WHY?" እያልኩኝ ማማረር ጀምርኩ ::
ንዴቴ እንደ ቡና ይንተከተካል :: ደስታዬ ደግሞ ቅጡን አጥቷል ::
ይሄ ምን ይባላል ? ቆይ አሁን ለመኪያ ምን ልላት ነው ? የመኪያን ነገር ምን ላደርገው ነው ? እያልኩ ራሴን ጠይቃለሁ ::
ደብዳቤውን ከፍቼ ሳላነበው በተለያዩ ሐሳቦች ትርምስምሴ ወጣ ::
ልቤ ምቷ ጨምሯል :: እየተርበተበትኩ ደብዳቤውን ከፈትኩት ::
ወይኔ የጅ ጽሁፏ ማማሩ :: ልቅም ያለ ነው :: በሰማያዊ ብዕር በብሌን ጣቶች የተጻፉ ቃላት :: ልቤ ዘለለች :: የተጻፈውን ለማንበብ ቸኮልኩ ::
በመሐል በሩ ተንኩዋኩዋ :: በድንጋጤ የምሆነውን አጣሁ :: የሰረቀ ሰው ይመስል በራስ መተማመን የሚሉት ነገር ጠፋ :: ደብዳቤውን ጭምድድ አድርጌ ኪሴ ውስጥ ከተትኩት ::
መኪያ ናት ::
መደናገጤን አይታ ነው መሰለኝ "ሰላም ነህ ? ምነው ያልብሀል እሳ ?" አለችኝ በሀዘኔታ ::
"ሰላም ነው :: ወበቁ ሳይሆን አይቀርም የሚያልበኝ ::" አልኩዋት :: ልቤ ምቱን አላቆመም :: እንድታውቅብኝ አልፈለግሁም ::
ደብዳቤው :: ኪሴ ውስጥ ሆኖ እንደ ኤሌክትሪክ ይነዝረኛል :: መኪያ ቢሮውን ለቃ እንድትወጣልኝ አላህን ተማጸንኩ :: ደብዳቤውን እስካነበው ድረስ ትዕግስት አጥቻለሁ :: ውስጤ ርብሽብሽ ብሏል :: መነፈሴ ይጨነቃል :: ብሌን የአዕምሮዬን ካዝና በጉልበቷ ሰብራ ወጥታለች :: አርበደበደችኝ :: ክፍሉ ውስጥ የምትታየኝ ሁሉ ብሌን ናት :: ብሌን ብሌን ይላል የማየው ነገር ሁሉ :: መኪያን ሳያት ራሱ ብሌንን የማይ እየመሰለኝ ነው :: ብሌን የኔ ባለ ድርብ ጥርስ :: የናሆም እህት :: የቦቢ ወዳጅ :: ብሌን ያይኔ ፍቅር :: ብሌን :: የሙዝ ልጣጭ ... እናቷ ... የመርቲ ቲማቲም ጣሳ ... የዛገ በር ... ቀይ ግቢ ... የላዳ ሹፌር .... ሀገር ፍቅር ... ጠመዝማዛ መንገድ ያለው ሰፈር ... የብሌን ሳቅ ... ፈገግታ ... ሁሉም ብቅ ጥልቅ እያሉ በህሊናዬ ውስጥ እንደ አስማተኛ "ትሪክ " ይጫወቱብኝ ጀመር :: ብሌን የዓይኔ ብሌን :: ደብዳቤው :: ነዘረኝ :: ሙቀት ተሰማኝ :: አልቻልኩም :: ውይይይይይ !
መኪያ በትዝብት ቆማ ካየችኝ በሁዋላ "የሆነ ነገር ግን ሆነሀል :: ለምን አትነግረኝም :: የኔ ቢሮህ ድረስ መምጣት ከሆነ አታስብበት :: ሀላፊያችን ልኮኝ ነው :: ቅድም የሰጠሁህን ፕሮጀክት ከምን ላይ እንዳደረስከው እንድጠይቅህ ነው የተላኩት :: ካሁን አሁን በተላኩ እያልኩ ስመኝ ነው ሀላፊው የላከኝ ::" አለችኝ ፈገግ እያለች ::
የሷን ፈገግታ ደግሞ አልችለውም :: ዓይኖቿ :: ውብ እንቁ ዓይኖቿ ልቤን ያደክሙታል :: ያንሰፈስፉታል ::
ተጠጋችኝ :: አልራቅሁዋትም :: ይበልጥ ቀረብኩዋት ::
"ኤል ነው የምልህ ከዛሬ ጀምሮ :: ቅር ይልሀል ?" ስትል ጠየቀች የዓይን ብሌኔን አትኩራ እያየች ::
"ይመቸኛል :: ደስ እንዳለሽ አቆላምጪኝ :: ያንቺው ነኝ ::" አልኩዋት ከልቤ ይሁን ካንገት በላይ ሳልረዳ ::
"ኤል ቅድም ያወራነው ነገር በደስታ ብዛት እረፍት ነስቶኛል :: ከዚህ ቢሮ ውጭ ተገናኝተን በግል እስክናወራና የልባችንን እስክንገላለጽ መጠበቁ በጣም የራቀ መስሎ ተሰምቶኛል ::"
ይበልጥ ቀረበችኝ ::
"እኔም እንደዚያው መኩ ::" አልኩዋት ዝቅ ባለ ድምጽ ::
ቀስ ብዬ ከንፈሬን ሰጠሁዋት :: ተቀበለችኝ :: በስሜት ቀለጥን :: በፍቅር እንደ ርግቦች በሰማይ ላይ በረርን :: ዓይኖቼን ከፍቼ ሳያት ዓይኖችዋ ክድን ብለዋል :: እነሱንም ሳምኩዋቸው :: እቅፍ አደረኩዋት :: አጸፋውን መለሰች ::
ልቤ ደግሞ ሰው በሩን ከፍቶ እንዳይገባ ይፈራል :: ፈሪ ! ወኔቢስ !
"መኩ ለሌላ ግዜ ይቆየን :: ቢሮ ውስጥ ከተያዝን ጥሩ አይሆንም ::" ብንቀጥል አልጠላም ::
"ልክ ነህ የኔ ቆንጆ :: ግን አንድ ነገር ልንገርህ :: ፍቀድልኝ :: በዚህች ቅጽበት ልቤ በፍቅርህ እየቀለጠ ነው :: ከንፈሮችህ አይጠገቡም :: ፍቅር ይዞኛል :: በቅፍህ ውስጥ መሆን አምሮኛል ::" አለችኝ በሚያሳዝን ዓይነት ቅላጼ :: አንጀቴን በላቸው :: የደስታ እንባዎች ከነዚያ ውብ ዓይኖቿ መንታ መንታ እየሆኑ ዱብ ዱብ አሉ :: በጣቶቼ ቀስ ብዬ ከጉንጮችዋ ላይ ጠረግሁዋቸው :: የሮማን ፍሬ መስላ ታየችኝ :: ለስላሳ ከንፈር :: እንደ ቲማቲም ቀይ ጉንጮች :: አሳዘነችኝ :: ልቤ ወደዳት :: መልሼ ልቧ ጥፍት እስኪል ድረስ ሳምኩዋት :: እሷም ሳትሰስት ምላቹን ሰጠችኝ ::
በቃ ፍቅሯ ይዞኛል ::
"እኔም እወድሻለሁ " አልኩዋት ድምጼ እየተቆራረጠ ::
ብርድ የያዛቸው ይመስል እጆቼ ይንቀጠቀጣሉ ::
"ከቢሮ ስትወጣ ጠብቀኝ እሺ :: አብረን እንሄዳለን :: ወንድሜ ቤት እንዲያደርስህ እነግረዋለሁ :: እወድሀለሁ የኔ ጌታ ::" ብላኝ ወደ በሩ ስታቀና መላ ቁመናዋን ቃኘሁት :: ፈዝዤ ቀረሁ :: ፍቅሯ አደንዞኛል :: የኔ ሙሉ እመቤት ሳታሸንፈኝ አትቀርም ::
ወጥመድ ውስጥ ገብቻለሁ :: መውጪያ ቀዳዳዋ የጠፋባት አይጥ እመስላለሁ ::
"በቅፍህ ውስጥ መሆን አምሮኛል " ያለችው ባምሮዬ ውስጥ ተቀርጾ ቁጭ አለ :: በቅፌ ውስጥ ሳኖራት ታየኝና እንደ ጥጃ መቦረቅ አማረኝ ::
ልክ መኪያ ስትወጣ መከረኛው ልቤ ወደ ብሌን ዞረ ::
እጄን ኪሴ ውስጥ በፍጥነት ሰደድኩት ::
ያጨማደድኩትን ወረቀት ቀስ ብዬ በስርዓት እዘረጋው ጀመር :: የብሌን ደብዳቤ :: የብሌን ጣቶች ያረፉበት ወረቀት :: የብሌን ቃላቶች :: እምምምምምምም !
ብሌንንንንንንን !
መኪያያያያያያ !
በሁለት ሴቶች ፍቅር መውደቄ እውን ሆኖ ታየኝ ::
ደብዳቤው :: የብሌን ደብዳቤ አፍጦ ያየኛል :: ቆጣ ብሎ "አንብበኝ እንጂ " ያለኝ መሰለኝና "አረ እሺ በሚገባ " በማለት የመጀመሪያው ዐረፍተ ነገር ላይ ዓይኖቼን አሳረፍኩ ::
"ውድ እስራኤል እንደምን ዋልክ ? ይህ ደብዳቤ ይደርስሀል የሚል ተስፋ አለኝ :: ... "
ዓይኖቼ በእንባ ተሞሉ :: "የሁለት አመት ልፋቴ ከንቱ አልሆነም ::" አልኩኝ በልቤ ::
ደብዳቤው ቀጠለ ... _________________ "The purpose of education is not to fill buckets, but to light fires." – Yeats
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ጦምኔው Joined: 14 Jan 2007 Posts: 1433 Location: Right here
Posted: Fri May 16, 2008 3:06 pm Post subject:
በድንገት ማንበቡን ኣቋርጬ ራሴን እጠይቅ ገባሁ :: ከየት አወቀችው አድራሻዬን ? ጭራሽ የስራ ቦታዬን ? ፖስታውን ደግሜ አየሁት :: "ከብሌን " ይላል :: ከብሌን ......ድንገት ፈገግ አልኩ :: ተጃጅያለሁ መሰለኝ ልክ የሷ ስም ስጠራው ውስጤን ደስታ ይሰማዋል :: የራሴ ነገር አንዳንዴ ግርም ይለኛል :: ነገሮችን ቶሎ መቀበል እችላለሁ :: ደስታንም ሆነ ሀዘንን በአንድ ጊዜ ማዋሀዱ ለኔ ቀላል ነው :: የቀኑን ውሎዬን መልሸ ቃኘሁት :: ጠዋት ላይ እንደዚያ ስርበተበት የነበርኩ ሰውዬ ወዲያው ከቤዛ ጋር ያለኝን ስሜት ማሰላልሰል ጀመርኩ :: ስቀጥል ያችው ብሌንን ፍለጋ መልሼ ሰፈር ለሰፈር ስንቀዋለል የዋልኩት እና የብሌን እናት ግልምጫ ችዬ ማሳለፌ :: አሁን ደሞ እዚህ ከመኪያ ጋር ያለኝን ቅልጥ ያለ ፍቅር አሰብኩት :: ተጭበረበረብኝ :: የቱ ነው ቆይ የኔ ትክክለኛ ስሜት ? ማንኛዋን ነው ያፈቀርኩት ? ሰው እንዴት በአንድ ጊዜ የሄዋንን ዘር በሙሉ ያፈቅራል ? " ወይ ጣልያን " አለ ያ ጓደኛዬ ! ያ ጓደኛዬ ! ወዲያው አንድ ሀሳብ ብልጭ አለልኝ :: እንዲህ በባዶ ሜዳ ነገሮችን ከማምታታ የሰው ምክር ያስፈልገኛል :: የጓደኛ ምክር :: ስልኬን አወጣሁት :: ስልኬን ሳያት ሁል ጊዜ ሳቄ ይመጣል :: ድክም ያለች ኖኪያ ናት :: ኖኪያ 3310:: በዚህችው ስልክ ያልፎገረኝ ሰው የለም "" ያቺ ቤዛ በተለይ እንደምናደድ ስለምታውቅ ብቻ ደጋግማ በሷው ስልክ መቀለድ ያረካት ነበር :: ትንሻ ሚሚ እንኳ ሳትቀር " እኔ ይህንን ስልክ ይዘህ ሳይህ ሳይህ አማርኛ አስተማሪያችን እየመሰልከኝ ዳስተር ተቀብዬ ብላክ ቦርዽ አጥፊ አጥፊ ይለኛል " ብላ በቤተሰብ ሙሉ ፊት ያሳቀችብኝን አልረሳውም :: ሰው እስኪ አሁን ምን አገባው ? እኔ የፈለኩትን ስልክ ብይዝ ? የስልክ ዋናው ዓላማ ለኮሚዩኒኬሽን አይደል ? ታዲያ የኔዋ ኖኪያ መች ያንን አጎደለችብኝ ? ወዲያው ሀሳቤ ዘሎ ከደብዳቤው ላይ አረፈ :: ደግሜ ማንበቡን ፈራሁት :: ቃላቱ ጦር መስለው ታዩኝ :: እንዴት አባቷ ነው ስራ ቦታዬን ያወቀችው ? አሁን እፈራት ገባሁ :: ግራ ገባኝ :: ስልኬን አንስቼ ጭርር አደረግሁት :: ከወዲያኛው ጥግ " ሀሎ ታላቅ ሰው ?" የሚል ድምጽ ከጆሮዬ ገባ :: ሱራፌል ነው :: የልጅነት ጓደኛዬ :: ከሕጻንነታችን ጀምሮ የልብ ጓደኞች ነን :: አንድ ነገር ካለኝ አስቀድሜ የማሰማው ለርሱ ነው :: ኖሮኝ የማያውቀውን የወንድም ቦታ ሸፍኖልኛል :: ምን ብዬ እንደምነግረው እያሰልካሰልኩ
" ሰላም ጎረምሳው " አልኩት
" እንዴት ነህ ባያሌው ጃል ?" ቀጠለ ሰላምታውን -:
" ይመስገነው አለን አባ :: እንዴት ነህ አንተ ?" ማናት የሀበሻነት አንዱ ምልክት አራት አምስት ጊዜ በተለያዩ አባባሎች ሰላምታ መለዋወጥ ነው ያለችው ?
" አለሁ ባክህ :: አንተ በቃ ይህንን ስልክ ቢጤ አልጥልም ብለህ እኛ አንተን ለመስማት ስቃይ ገባን እኮ " መቀለዱ ነው ::
' ባክህ እሱን ተወውና አሁን ለአንድ ጉዳዬ ፈልጌህ ነበር :: ባክህ እዚህ .....ማለቴ ....የሆነች .......ስልህ ........" የምለው ጠፋኝ ::
" ምን ? " ሱራፌል የምለውን እየጠበቀ ነው :: እንደምንም ትንፋሼን አሰባሰብኩና .... _________________http://www.youtube.com/watch?v=_jIwsS_eT5w
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=22540&start=105
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ብራንጎናትርን Joined: 29 Dec 2006 Posts: 608
Posted: Sat May 17, 2008 3:54 pm Post subject:
የውስጤን ልተነፍስ ስል ድንገት ስልኩ ተቁዋረጠ :: "ብሽቅ !" አልኩ በሆዴ :: መልሼ ስደውል "የደወሉላቸው ደንበኛ መስመር ለጊዜው ከአገልግሎት ውጭ ነው ::" የሚል አስቀያሚ የሴት ድምጽ በጆሮዬ አስተጋባ :: "ይዝጋሽ !" አልኩና ሞባይሉን ጠርቅሜ ኪሴ ውስጥ ከተትኩት ::
ቀልቤ ወደ ደብዳቤው ነው :: ላንብብ አላንብብ ? ተምታታብኝ :: በዚያ ላይ ለሱራፌል ምን ብዬ ነው የምነግረው ? ባንዴ ሁለት ሴቶችን አፈቀርኩ ብዬ ? ጥርሶቹ ፍርስ እስኪሉ ሲስቅብኝ ታየኝ :: እሱ ድሮም እንኩዋን ዘንቦብሽ ነው ::
"ይሄን ጉድ ራሴ መወጣት አለብኝ " አልኩና ደመደምኩ ::
ደብዳቤውን ካስቀመጥኩበት አንስቼ ስከፍተው ድንገት በሩ ተንኩዋኩዋ ::
ገባ :: ሀላፊዬ ነው ::
"ሥራ እንዴት ነው ? ቢዚ ትመስላለህ ?" ሳቅ እያለ ::
"ጥሩ ነው ምንም አይልም ::"
"ቅድም መኪያ የሰጠችህን ፕሮጀክት ከምን አደረሰከው ?" አሁንም ሳቅ እያለ ::
"የደንበኛችንን ፕሮፖዛል ጥሩ ሆኖ አግኝቼዋለሁ :: የኛን ምላሽ እየጻፍኩ ነው :: ላገባድድ ትንሽ ነው የቀረኝ ::"
"በጣም ጥሩ :: ዛሬ የምትጨርሰው ይመስልሀል ?"
"በሚገባ ::" ሳቅ እያልኩ ::
"በጣም ጥሩ :: በነገራችን ላይ መኪያ ጥሩ ልጅ ናት :: ደህና አድርገህ ያዛት ::" ዘና ብሎ ነው የሚያዋራኝ ::
ምን አባቱ አየ ? እንዴትስ አወቀ ? እንዴ ስንሳሳም አይቶን ይሆን እንዴ ? ክው አልኩ :: ወይንስ የተጠራጠረው ነገር አለ ::
"አይዞህ አትደንግጥ :: ምነው አነጋገሬ ያደናበረህ ትመስላለህሳ ?" ሊያረጋጋኝ ሞከረ ::
"አረ አልደነገጥኩም ::" እጄን አልቦታል ::
"ምልህ ጉዋደኛሞች ብትሆኑ የምትመቻቹ ስለመሰላችሁኝ ነው :: ብዙ እስዋን የሚያድኑ ጭልፊቶች መኖራቸውን አትዘንጋ :: አንተ ሙቭ ካላደረክ እነሱ ይቀድሙሀል ::" ሳቅ እያለ ::
ተነፈስኩ :: መሳሳማችንን እንዳለየ እርግጠኛ ሆንኩ :: ጥሩ አማካሪ ማግኘቴም ደስ አለኝ :: የብሌንን ለራሴ ትቼ የመኪያን ላዋየው እንደምችል ተማመንኩ ::
"አስብበታለሁ ::" አልኩት ፈገግታ እየሰጠሁት ::
"መልካም :: አስብበታለሁ ብቻ አይደለም :: ፍጥነት ይጠይቃል :: በርታ ... በማነኛውም ነገር ከጎንህ ነኝ ::" በማለት እንደ ልጁ ትከሻዬን ቸብ ቸብ አድርጎ ሳቅ እያለ በሩን ከፍቶ ወጣ ::
የሀላፊዬ ደግነት የማያልቅ ሆነብኝ ::
ላንብብ አላንብብ ? ደብዳቤው በተማጽኖ ያየኛል ::
ስልኩ ጭርር አለ :: ማን ይሆን ? ሞባይሌን ከኪሴ አውጥቼ የደዋዩን ቁጥር ተመለከትኩ :: _________________ "The purpose of education is not to fill buckets, but to light fires." – Yeats
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
መልከጻዲቅ Joined: 08 Aug 2007 Posts: 675
Posted: Tue May 20, 2008 2:44 am Post subject:
የሱራፌል ቁጥር ነው :: ""እፎይ "" አልኩ :: "" ስልክህን ምን ነካው ?"" አለኝ :: መቼም በዚች በኔ ስልክ ሰሞኑን የአዳም ዘር ሁሉ ተነስቶባታል :: ትንሿም ሚሚ ሳትቀር :: ሱራፌል ደግሞ አንድ ውጭ ሀገር የሚኖር ጔደኛችን ቆንጆ ቀፎ ስለላከለት የሌሎቻችንን ስልኮች በተላይ የኔዋን ኖኪያ በሼውራሬ ማየት ጀምሯል :: "" ምን በኔ ስልክ ታሳብባለህ ካንተም ሊሆን ይችላል እኮ የተቌረጠው ..."" አልኩት ትንሽ ቆጣ ብዬ :: ሱራፌል አላረፈም :: "" እንዴ መእምን እስራኤል አንተ ኖኪያ ለሙከራ የሰራውን ስልክ ይዘህ እየተጠቀምክ ......"" ሳይጨርስ አቌረጥኩት "" ቀልዱን ተውውና አሁን ላገኝህ እፈልጋለሁ "" "" ምነው በደህና ?"" ካነጋገሬ አንድ ነገር እንደደረሰ መገንዘብ ችሏል :: "" ዘ -ኬቭ በር ላይ ዛሬ 10.00 አካባቢ እንድንገናኝ ተቀጣጥረን ስልኩን ዘጋሁት :: **************
የስራ ሰአት አልቆ ከቢሮዬ ስወጣ መኪያ ወደኔ አቅጣጫ ስትመጣ አየኌት :: "" ሀይ አለችኝ "" አጠገቤ ስትደርስ "" ሀይ "" አጸፋውን መለስኩ :: ጉዳይ እንዳለበት ሰው ፈጠን ፈጠን እያልኩ ቢሮውን መቆለፍ ጀመርኩ :: መኪያ ትታዘበኝ ኖሯል "" የቸኮልክ ትመስላለህ ምነው በደህና ?"" "" እቤት ምን እንደተፈጠረ አላውቅም ትንሿ እህቴ አሁን ደውላልኝ ..."" ሳልጨርስ ካፌ ተቀበለችኝ "" ምነው ደህና አይደሉም እንዴ ..??"" አለችኝ :: ትህትናዋ ሀዘኔታዋ ልቤ ውስጥ ገባ :: "" አይ ደህና ናቸው ታናሽ እህቴ ሙጢ ብጤ ናት የተሰጣ እህል በዶሮ ሲበላ ካየች እንኴን ትደውላለች "" አሳቃት :: "" አንድ ቀን ታስተዋውቀኛለህ አይደል !"" ባይኗ አናገረችኝ :: "" አረ -ምን ገዶኝ አስተዋወቅሻለሁ ምን ችግር አለ ? "" አልኴት :: አብረን እንሂድ እንዳትለኝ በልቤ ጸሎት ያዝኩ :: ከሱራፌል ጋር ያለኝ ቀጠሮ እንዲበላሽ አልፈለኩም :: እሷም አልወጣትም :: "" በል ደህና አምሽ ነገ አይሀለሁ ባላቃትም ትንሿን እህትን ሰላም በልልኝ "" "" እሺ አደርሳለሁ መኪያ "":: .*****************
ከመኪያ እንደተለየሁ በቀጥታ የሄድኩት ሱራፌልን የቀጠርኩበት ቦታ ነው :: አዎ ሸክሜን ለማውርድ ሁነኛው አማራጭ አሁን ሱራፌል ነው :: ሱራፌል አብሮ አደግ ጔደኛዬ ነው :: የወንድም ያህል እንቀራረባለን :: ተጣልተንም እንኴን ቢሆን ካላየሁት ቅር ቅር ይለኛል :: ይህ አይነቱ ስሜት በሱ ውስጥም አንዳለ አንድ ጊዜ በጨዋታ መሀል ሲያወራ ሰምቸዋለሁ :: "" ዘኬቭ ስደርስ ሱራፌል ቀድሞኝ አገኝሁት ሰላምታ ከተለዋወጥን በኌላ ጸጥ ያለ ቦታ ፍለጋ ሽቅብ ወደጊዮርጊስ ቤተ -ክርስቲያን አመራን :: የእሳት አደጋ ብርጌድ ያለበትን እንዳለፍን ካሉት መደዳ ቡናቤቶች ጸጥ ያለውን መርጠን እኔ ቡና በወተት ሱራፌል አንድ ቢራ አዞ ተሰየምን :: "" ሱራፌል ሁለቴ ቢራውን ተጎነጨና "" እሺ ማንነው የሞተው ?"" አለኝ :: "" "" ሞቅ አለህ እንዴ ገና ባንድ ቢራ ?"" ሽርደዳውን በሽርደዳ መለስኩበት :: "" ቀልዱን ተወውና በል የሆነውን ንገረኝ "" አለኝ በተቀመጠበት ወንበር ላይ እየተመቻቸ :: "" ሳንዲውች ሆኛለሁ "" አልኩት :: ሱራፌል ሳቀ :: ሲስቅ አጉል ልምድ ሆኖበት የታችኛውን ከንፈሩን ወደ ቀኝ ያንሻፍፈዋል :: አና ለማያውቀው ሰው ሳቁ የውሽት ሳቅ ይመስላል :: "" ወንድሜን ታዲያ በሉሻ "" አለኝ እንደዛው እየሳቀ :: ""የሚበላ ይብላህ ዝም ብለህ አዳምጥ "" አልኩት ግንባሬን ኮስተር አድርጌ :: "" Ok go ahead! እንስማው "" አለኝ :: "" እኛ መስሪያ ቤት የምትሰራውን ጸሀፊያችንን ታውቃታለህ አይደል ? "" አልኩት :: "" አዎ ያቺ አደሬ የምትመስለዋ ልጅ መቅለሚያ እያደረገች ትመጣለች ምናምን ያልከኝ ?"" ""አዎ አዎ እሷ ናት ...አንዴ እንደውም ዘንግተሀው አንደሆን እንጂ ከሩቁ አሳይቼህ ነበር "" "" አዎ ትክክል እያለ ማስታወሱን ለመግለጽ ራሱን ነቀነቀ :: "" "" ታዲያ እሷ ምን ሆነች ?"" "" አሷ ማ ምን ትሆናለች ያው ትጽፋለች ጥሩ ታይፒስት ናት በዛ ላይ እርጎ የሆነ ጸባይ አላት .....ግን .." "" ግን ምን ?"" ሱራፌል ለወሬ ሲቸኩል ሳያስበው ቢራውን በእጁ ገፍቶ ሊደፋ ሲል ቀድሞ ያዘው :: "" እናማ ዛሬ ምሳ ልጋብዝሽ አልኴት በኌላ በጨዋታ ጨዋታ ለሷ የተለየ ስሜት እንደሚሰማኝ ስነግራት ተመሳሳይ ስሜት እሷንም እንደሚሰማት ገለጸችልኝ ::"" "" እናስ ? "" ሱራፌል የቀረችዋን ቢራ ባንድ ትንፋሽ ሳባት :: ለረጅሙ ሩጫ የተዘጋጀ ይመስላል :: ባዶውን ጠርሙስ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠና "" ታዲያ ችግሩ የት ላይ ነው ያለው ?" አለኝ ካይኖቼ ውስጥ መልስ ያለ ይመስል ትክ ብሎ እያየኝ :: "" አሀ ገባኝ ነገሩ "" አለ አንድ ትልቅ ሚስጥር እንደተገለጸለት :: "" ምንድነው የገባህ ?"" አልኩት :: "" እቺ ልጅ ሙስሊም ናት አይደል አንተ ደግሞ ክርስቲያን ነኝ ባይ ነህ ..አይደል "" ""አይ ሱራፌል ፍቅርን እምነትህ አይጋርደውም አምላክ ተፋቀሩ አለ እንጂ በኔ ምክንያት ተለያዩ አለ እንዴ ??"" "" እሺ የኛ የግሪክ ፈላስፋ እኔ ይህንን መቼ አውቅልህና ..... ቅቅቅቅቅ "" አንድ ቢራ ለመድገም አስተናጋጇን በምልክት ጠራት :: "" የሆንክ የማትረባ "" የቀልድ ቁጣ ተቆጣሁት :: "" ይሀውልህ ሱራፌል ችግሩ የእምነታችን ጉዳይ አይደለም ስሜት ለስሜት ተግባብተናል ባይገርምህ እንደውም ኮሪደሩ ላይ ሳምኴት :: "" ጭራሽ "" ሁለተኛውን ቢራ መለሽለሽ ጀመረ :: "" እህ "" ጭንቅላቴን እየነቀነቅኩ እውንተኛነቱን አረጋገጥኩለት :: "" ዛሬ በዛሬው ተዋውቃችሁ ምን አይነት ድርቅና ነው እባክህ ? እሷስ ብትሆን ምንም አላለችም ?"" "" የሚገርምህ እሱ ነው ምን እንዳሰበች አላውቅም ምንም አላለችኝም "" :: "" ዝምታ የመስማማት ምልክት ነው ዝም ካለችህ ተስማምታለች ማለት ነው :: አለኝ ሱራፌል በርጋታና በጽሞና :: "" ይመስለኛል "" አልኩት ውጭ ውጭውን እያየሁ ወዲያውም ስለብሌንና ደብዳቤዋ ታሪክ እንዴት አድርጌ እንደምጀምርለት እያሰላሰልኩ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ብራንጎናትርን Joined: 29 Dec 2006 Posts: 608
Posted: Tue May 20, 2008 6:15 am Post subject:
ከሩቅ ወደ ተቀመጥንበት ቦታ የሆነች ልጅ ስትመጣ ሳይ ልቤ ድንግጥ አለ :: በደንብ አትኩሬ ሳያት ተመልሼ ራሴን አረጋጋሁ :: ቁርጥ ብሌንን :: በዚህ ሰሞን የማያቸው ሴቶች ሁሉ ብሌንን እየመሰሉኝ በጣም ተቸግሬያለሁ :: ሙጢዋም እህቴ ብሌንን መስላ ቤት እንዳትጠብቀኝ እንጂ ለሌላዎቹ ችግር የለውም ::
"ወሬውን ቀጥላ ... ማንን የምጠብቅ መሰለህ ? በነገራችን ላይ ያቺን ቺክ አየሀት ? ፓ ፓ ፓ ሴቱ በጭማቂና በቸኮላት ብቻ ማደግ ጀመረ እንዴ ?" በማለት ከሄድኩበት ሀሳብ ሱራፌል መለሰኝ :: _________________ "The purpose of education is not to fill buckets, but to light fires." – Yeats
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ጦምኔው Joined: 14 Jan 2007 Posts: 1433 Location: Right here
Posted: Tue May 20, 2008 4:35 pm Post subject:
" ኧረ ባክህ ይሄ የቻይና ልባብ ከገባ ቺኮቻችን ሁሉ ዓይናችንን ሊያጠፉት ደርሰዋል ::" ሁለታችንም ፈገግን :: ወተቱን አንስቼ ተጎነጨሁት :: በወሬው ተመስጬ ኖሮ ሳልጠጣው ቀዝቅዟል :: አስተናጋጁን ጠራሁትን እንዲያሞቅልኝ አልኩት :: ሱራፌል ሁለተኛውን ቢራ አጋምሶታል :: ሲጠጣ መጣጭ ነው :: አይሰክርም :: በአባቱ ወጥቶ ነው መሰለኝ :: አባቱ ሰፈራችን ውስጥ የታወቁ ጠጪ ናቸው :: "ፋንቱ ማንዶዬ " ይሏቸዋል የሰፈር ልጆች ሲያላግጡባቸው ::
' ፍሬንዴ አማን አይደለም እንዴ ?" ሱራፌል በእጁ ወዘወዘኝ :: " ኧረ ነቃ በይና አጫውተኝ እንጂ :: ምንድነው እሱ የሆንከው ?"
" ቤዛን አስታወስካት ?" ጠየቅሁት :: ከት ብሎ መሳቅ ጀመረ ::
" ቤዛ ? የድንግልናዬ እናት አትልም :: ቅቅቅ ......እንዴት ይረሳል አለ መሀሙድ " ሳቁ እኔንም አሳቀኝ :: " እሷ ልጅ ዓረብ ሀገር አልሄደችም እንዴ ?"
" ሱራፌል ደሞ ቧልት ታበዛለህ :: እውነቴን እኮ ነው :: ዛሬ ጠዋት ከየት መጣች ሳይባል መገኘት ባልነበረበት ቦታ መጥታ አስቀይሜ አሰናበትኳት "
" እንዴት እንዴት ? መገኘት ባልነበረባት ቦታ ስትል ?'
" ዋናው ነገር እሱ እኮ ነው :: እንዴት ብዬ ላስረዳህ ሱሬ ?"
" እንዴት ብዬ ላስረዳህ ? ወይ ጣልያን :: አባው ፎንቃ ጠለፈሽ እንዴ ?"
" አዎን ሱሬ :: ተይዣለሁ :: በሔዋን ዘር ፍቅር ተይዣለሁ :: ከሁሉም የበለጠ ግን የብሌን ፍቅር ይዞናል ::" ልክ ስሟን ስጠራው አዕምሮዬ ሁለት ዓመት ወደ ኍላ ተጉዞ የመጀመሪያ ቀን ብሌንን ያየሁበት ቀን ከዚያም ደሞ እርሷ ስከታተል ያሳለፍኳቸውን አስቂኝና አስገራሚ ጊዜዎች ያስብ ገባ :: የተንከራተትኩትን ሳስብ ዕምባ ዓይኔ ላይ ሙልት አለ :: ላለማልቀስ ብታገለውም ላቆመው አልቻልኩም :: በሁለቱን ዓይኖቼ ኩልል ብሎ መውረድ ጀመረ :: ሱራፌልን አፈርኩት :: እንዳያየኝ አንገቴን አቀርቅሬ በእጆቼ ሸፍኘ መንሰቅሰቁን ቀጠልኩ :: ሱራፌን አይቶኝ ኖሮ .
" ኧረ በለው :: እስርሽ ምን ነካህ አባ ? ሰላም አይደለሽም እንዴ ? ኧረ ባክህ ተረጋጋና የሂንከውን ንገረኝ ::"
እንደምንም ብዬ ማልቀሱን አቆምኩና ቀና አልኩኝ :: የሀፍረት ሳቅ እየሳቅሁ ሱራፌልን አየሁት :: ደንግጧል :: በግርምት እና እንግዳ በሆነ አስተያየት ያየኛል :: የበለጠ አፈርኩ ::
" ባክህ ፍቅር ሳይዘኝ አልቀረም ::" ተነፈስኩለት ::
" ፍቅር ? ከማን ጋር ? ደሞ ብሌን ምናምን ያልካት ልጅ ማናት ?" ሱራፌል አሁን በቁም ነገር ያወራኝ ጀምሯል :: አፈጠጤብኝ :: መልሧን አሁኑኑ አምጣ የሚለኝ ይመስላል :: ስለብሌን ነገርኩት :: ሁለት ዓመታት መሰቃየቴን እና እስካሁን እየተከታተልኳት መሆኑን ነገርኩት :: ዛሬ ጠዋት ያጋጠመኝንም አጫወትኩት :: ስለእናትየው ስነግረው ሱራፌል ለረጅም ሰዓት ነው ስቆ እኔንም አሳቀኝ :;
" የሚገርምህ ደሞ ቅድም ቢሮ ሆኜ አንድ ደብዳቤ ደረሰኝ :: " ከብሌን " ይላል "
" ከብሌን ? አንግባባም አላልከኝም እንዴ ?" ሱራፌል ግራ የተጋባ ይመስላል :: ለምን ግራ አይግባው የማይገናኙ ታሪኮች ተገጣጥመው ሲሰማ ::
" እኔም እሱ ነው የገረመኝ :: እንዴት እንደደረሰኝ እንኳ መድሀኔዓለም ይወቀው :: ቢሮ ድረስ ስልህ :: ደሞ አላነበብኩትም ::"
"ለምን ? አላነበብከውም ?"
" ፈራሁ ::" ሱራፌን አስተናጋጁን ጠራውና ሁለት ተጨማሪ ቢራ እንዲያመጣ አዘዘው :: አስተናጋጂ ሲሄድ ወደ እኔ ዞሮ
" አንተ ልጅ እኮ በጣም የምትገርም ፍጡር ነህ :: በአንድ ቀን ከሶስት ሴት ፍቅር ያዘኝ አልከኝ :: አሁን ደሞ መልሰህ ደብዳቤ ማንበብ ፈራሁ ትለኛለህ "" ምንድነው የሆንከው ጃል ? እንዴት አድርጎ ነው ከሶስት ሴቶች ጋር በአንድ ጊዜ ፍቅር የያዘህ ?" አስተናጋጁ ቢራውን ይዞ ሲመጣ አንዱን ቢራ አስጨበጠኝና " በአንድ ትንፋሽ ጨልጠው :: so that we both can be on the same page" አዘዘኝ :: ተእዛዙን አማላሁለት :: ቀዝቃዛው ሜታ ጉሮሮዬ ላይ ጉርጭጭጭ እያለ ቅዝቃዜው እየሰነጠቀኝ ሲወርድ እርካታ ተሰማኝ ::
" ደብዳቤን አውጣው " አለኝ ሱራፌል :: አላቅማማሁም :: አውጥቼ ሰጠሁት :: ወረቀቱን ገለጦ ድምጹ ከፍ አድርጎ ሁለታችንም እንድንሰማ ያነበው ገባ :: _________________http://www.youtube.com/watch?v=_jIwsS_eT5w
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=22540&start=105
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ብራንጎናትርን Joined: 29 Dec 2006 Posts: 608
Posted: Wed May 21, 2008 10:03 am Post subject:
" እስራኤል ከዚህ በታች የጻፍኩትን በጥሞና አንብበው ::
ላለፉት ሁለት ዓመታት በሰፈራችን ስትመላለስ ዓይኖቼ ያንተን መምጣት ይናፍቁ ነበር ::"
ቅቅቅ "አረ ረ ችኪት አደገኛ ጻፊ ናት ::" ሱራፌል ማንበቡን አቋርጦ በሳቅ ይንፈረፈራል ::
"እንግዲህ አታብዛው :: ታነብ እንደሆን ቀጥል :: አለበለዚያ ራሴ ላንብበው :: አምጣ !" አልኩት ብስጭት ብዬ ::
"እንዴ እስርሽ ቢራ ሳብ ሳብ አርጊ :: የምን ቆጣ ቆጣ ነው :: ችኪት የምትመች ነች :: ገና ሳላያት ቀልቤ ወዷታል :: አጻጻፏ የሚያስቅ ሆኖ ስላገኘሁት ነው ::" እንዳልቀማው ደብዳቤውን ከኔ እያራቀ ...
"እሺ ቀጥላ ... አንተ ደግሞ ችኮ ነህ ::"
"ይቀጠላል ... ይቀጠላል ... " ከንፋሩን እያጣመመ ማንበብ ጀመረ :: ሳቅ ወጥሮታል :: የሆነ የሳቅ ወፍጮ ነገር ...
"አድራሻህን ማግኘቴ መቼስ ሳያስገርምህ አይቀርም :: አንድ ቀን ስንገናኝ እንዴት እንዳገኘሁት እነግርህ ይሆናል ::
እስራኤል የሆነ በጣም የምነግርህ ነገር ነበር :: አሁን ግን ምን ያደርጋል ተወው :: ለመሆኑ ጠዋት ከመቼው ከሰፈር ስልብ አልክ ? ቤት ቦርሳዬን አስቀምጬ ላናግርህ ስወጣ አንተ በቦታው አልነበርክም :: እንዴት ቅጥል እንዳልኩኝ አልነግርህም ::
ለምን በሰፈራችን እንደምትመላለስ ባላውቅም እኔን ግን አጉል ልማድ አስተምረኸኛል :: የዓይን ህመም :: ህመሙን አሁን አልነግርህም :: አንድ ቀን ራስህ ታውቀው ይሆናል ::
ጠዋት እንዴት እንዳሳቅከኝ ? የሆንክ የምትገርም ነህ :: ውሀ ጠጣ ተብሎ ይሰጥሀል አንተ በመርቲ ጣሳ ሻወር መውሰዱን ተያያዝከው :: ቅቅቅ እናቴ አደናበረችህ መሰል ? ትንሽ አደገኛ ቢጤ ናት :: ልቧ ግን ሩህሩህ ነው :: ክፉ ብትናገርም ደግ ከመስራት አትቆጠብብም :: አትፍረድባት :: አንድ ቀን አንዱ "ራበኝ ዳቦ ስጡኝ " ብሎ ግቢ ከገባ በሗላ እሷ ዳቦ ልታመጣ ስትሄድ ታጥቦ የተሰጣውን ልብስ (እርጥቡንም ደረቁንም ) በማዳበሪያ ጠቅጥቆ ሄደ :: ከዚያ ጊዜ ወዲህ ሰው አታምንም ::
ጠዋት ሳይህ በጣም ነበር ደስ ያለኝ :: ከስራ በፊት አይቼህ ከስራ መልስም ሳይህ ደግሞ ያልጠበኩት ነገር ሆነብኝ :: አጥራችን ላይ ተደግፈህ ሳይህ ከሩቅ መጀመሪያ ላይ ሌባ መሰልከኝ :: እየቀረብኩ ስመጣ ግን አንተ መሆንህን ሳውቅ የሆነ የማላውቀው ስሜት ይሰማኝ ጀመር :: አሁን ግን እርሳው ::
ለማነኛውም ይሄን ልነግርህ ነው የጻፍኩት :: ቅድም ፐርፕል ካፌ አብራህ የነበረችው ልጅ ቆንጅዬ ናት :: ስትሳሳቁና እጅለጅ ተያይዛቹ ከፐርፕል ስትወጡ ስታስቀኑ ::
ብሌን ነኝ
ከምታውቀው ሰፈር "
"ዱድ እቺ ልጅ ደራሲነት የምትቀላውጥ ትመስላለች :: ቅቅቅቅቅ እንዲህ ዓይነት ደብዳቤ ከሴቶች ሳልቀበል ይኸው ሐያቴ ባለፈው ጥርስዋን ነቀለች :: እንዴ እንዴ ... የዓይኔ ህመም ምናምን ... ቅቅቅ ... ሺት ሜን አይታቹሐለች ግን !" ሱራፌል የነገሩ አሳሳቢነት የተሰማው ይመስላል :: ቢራውን መቀምቀም ጀመረ :: "እህሳ ምን ትላለህ ?" ብሎ ሲጠይቀኝ ... _________________ "The purpose of education is not to fill buckets, but to light fires." – Yeats
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
መልከጻዲቅ Joined: 08 Aug 2007 Posts: 675
Posted: Thu May 22, 2008 6:49 am Post subject:
""ይገርማል "" አልኩኝ ለራሴ :: ""ምኑ ? "" አለ ሱራፌል :: ስናገር የሰማኝ አልመሰለኝም ነበር :: "" ምኑ ? አሁንም ደገመና ጠየቀኝ :: "" እቺ ልጅ ይህንን ሁሉ ማወቌ ከመኪያ ጋራ ሆነንም አይታናለች ማለት ነው ? "" ጥያቄውን በጥያቄ መለስኩለት :: ""አዎ እንደ ደብዳቤው ከሆነ ተበልታችኌል "" ሱራፌል ፈገግ አለ :: "" ታዲያ ምን ይሻላል ትላለህ ?"" ሱራፌል ቶሎ መልስ አልሰጠኝም ትንሽ አሰበ :: ቁም ነገር መጭመቅ ሲጀምር አይፈጥንም ይረጋጋል :: "" ስማ እስራኤል ራስህን ሁን "" አለኝ :: ""ምን ማለትህ ነው እኔ ድሮስ ማንን ሆንኩኝ አንተን ሆንኩ ሌላውን ሆንኩ ...ያለሁ የነበርኩ የምታውቀኝ እኔው ራሴ ነኝ :: "" በሀሳብ ላለመሸነፍ ድንበሬን ማጠር ጀመርኩ :: "" የለም የለም እሱን ማለቴ እኮ አይደለም እስራኤል "" ታዲያ ምንድነው የምትለው ?"" ሳላውቀው ጮህኩበት :: "" ራስህን ሁን ስልህ የምትፈልገውን ነገር እወቅ ልልህ ፈልጌ ነው አየህ አንተ አልገባህም እንጂ እንደ ፋሲካ የቅርጫ ስጋ እየተከፋፈልክ ነው ... በፊት ከቤዛ ጋር ስታብዱ ነበር እኛን እንኴን ዞር ብለህ የማያ ጊዜ አልነበረሀም አሁን ደግሞ ባንድ ቅጽበት ከሁለት ኮረዶች ጋር በፍቅር ሾርዬአለሁ ትለኛለህ :: "" አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ ? "" ትችላለህ ቀጥል "" ልብህ እንዴት ባንድ ጊዜ ሁለት ሰው ማፍቀር ይችላል ?"" ሱራፌል ቢራ ሳይሆን አጠፋሪስ በጥብጦ የጠጣ ነው የመሰለኝ :: "" አረ -ቀስ ይሄን ቢራ ቀስ እያልክ ቸልስ "" አልኩት :: እሱ ግን አልለቀኝም :: የጠጣው ቢራ ይሁን ወይ ሌላ ዛሬ በጣም ጠጠረብኝ :: "" ልንገርህ አንድ ነገር !"" አለኝ አስተናጋጇ ያመጣችውን 3ተኛ ጠርሙስ ቢራ ለመጠጣት በቀኝ እጁ ይዞ "" እሰመሀለሁ ቀጥል "" "" እንግዲያው ይሀውልህ ሁለቱንም አላፈቀርካቸውም አራት ነጥብ :: "" አፍቅሬአለሁ !""
""አላፈቀርክም ""
""አፍቅሬአለሁ "" ቃሉን አጠበኩበት ::
""አላፈቀርክም "" አስረገጠና ነገረኝ ::
""አንተ ቆይ የኔን ስሜት በምን ልትረዳው ትችላለህ ?"" አልኩት ንዴት ውስጤን እያበገነው :: ሱራፌል ጔደኛዬ ሳይሆን ክፉ የነፍስ አባቴ ሆኖ ታየኝ :: "" እየው እስራኤል አትቆጣ አየህ አንድ ሰው ልቡ ባንድ ጊዜ ሁለት ነገሮችን መውደድ አይችልም ነጮቹ Obsession ይሉታል ፍቅር ሳይሆን Obsessed ሆነሀል ይህ ላለመሆኑ እርግጠኛ ነህ ?"" ለጥቂት ጊዜ በሁለታችን ውስጥ ዝምታ ሰፈነ :: ትክ ብዬ ሱራፌልን አስተዋልኩት :: ወይም አፈጠጥኩበት ብል ይሻላል :: አይኖቼ እሱ ላይ ይሁኑ እንጂ አእምሮዬ ግን የተናገራቸው ነገሮች ባስነሱት የሀሳብ ወጀብ ይታመስ ነበር :: "" እንዴት ሁለት ሴት ባንዴ አፈቅራለሁ ? ራሴን ይሆን እንዴ እየወደድኩ ያለሁት ውስጣዊ ስሜቴ የሚጠይቀኝን ረሀብ ለማስታገስ ነው ወይስ መኪያንም ብሌንንም የሚያስቀምጥ ዳስ ልቤ ውስጥ ፈጥሬአለሁ ?"" በዚህ አይነት ሁኔታ በሀሳብ ስመከነከን በውስጠ የነበረውን ሱናሚ ጸጥ እረጭ ያደረገ አንድ ክስተት በመስኮቱ በኩል ታየ :: የመስሪያ ቤታችን ጸሀፊ አፈቅሬታለሁ እያልኩ ምስክርነቴን ለጔደኛዬ ለሱራፌል የስጠሁላት ጸባየ -ሸጋዋና ውቧ መኪያ ከዚህ በፊት አይቼው ከማላውቀው አንድ ሰው ጋር እኔና ሱራፌል ወዳለንበት ቡና ቤት አቅጣጫ ሲመጡ አየኌቸው :: ልቤ ስራዋን ላፍታ ያቆመች መሰለኝ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
መልከጻዲቅ Joined: 08 Aug 2007 Posts: 675
Posted: Thu May 22, 2008 11:58 pm Post subject:
አስፋልቱን ተሻግረው ሲመጡ አይኔን እነሱ ላይ ተክዬ አስተዋልኴቸው :: መኪያ ዙሪያውን ቀይ ጥለት የተጠለፈበት ረጅም ቀሚስና ከጥለቱ ጋር አብሮ የሚሄድ አላባሽ ታረሓ አንገቷ ላይ ጣል አድርጋለች :: አብሯት ካለው ሰው ጋርም የቆየ ትውውቅ ያላቸው ይመስላል :: የመኪናውን መንገድ ሲሻገሩ የግራ እጇን በቀኝ እጁ ያዝ ሲያደርገው የልቤ ምት ጨመረ :: ሱራፌል ሁኔታዬን አላስተዋለም :: ቡዙ ስላወራ ነው መሰለኝ የደረቀውን ጉሮሮውን በገብስ ጭማቂ እያረሰረሰው ነበር :: መኪያና እንግዳው ሰውዬ ቡና ቤቱ ውስጥ ገብተው ያልተያዘ ወንበር ፍለጋ ግራ ቀኝ ሲማትሩ አይን ላይን ተጋጠምን :: መጀመሪያ ትደነግጣለች ወይንም አይታኝ እንዳላየ ትሆናለች ብዬ አስቤ ነበር :: እንዳየችኝ ግን አብሯት ለመጣው ሰውዬ የሆነ ነገር ነግራው በቀጥታ እኔና ሱራፌል ወደ ተቀመጥንበት ጠረጴዛ ይዛው መጣች :: ልቤ ከቅድሙ በላይ መንጠር ጀመረች :: ሁለት ነገሮች ክፉኛ አሳሰቡኝ አንድ ቅድም ከስራ ስንወጣ አስቸኴይ ጉዳይ ስላለኝ ወደቤት እንደምሄድ ነግሬአት ስለነበር ሁለተኛም ደግሞ ይዛው የመጣችውን ሰውዬ ቀልቤ ስላልወደደው ነው :: ሁኔታቸውን ላየ የቆዩ ፍቅረኛሞች ነው የሚመስሉት :: ሳላውቀው ውስጤ በቅናት ትኩሳት እየጋመ መጣ :: አንድ ጽሁፍ ላይ "" ቅናት የፍቅር ምልክት ነው "" የሚል አረፍተ -ነገር አንብቤአለሁ :: እንዲህ ከሆነ መኪያ በኔ ልብ ውስጥ የፍቅር ዘሯን ዘርታለች ማለት ነው ...... "" ታዲያስ እስራኤል "" የሚለው ድምጽ ከገባሁበት የቀን ህልም አባነነኝ :: "" እንዴ ታዲያስ መኪያ እዚህ ምን እግር ጣለሽ ? "" አልኴት ምንተ -ህፍረቴን :: "" አንተን እዚህ ምን እግር ጣለህ ? እኔ ልጠይቅህ እንጂ "" አለችኝ የአሽሙር ፈገግታዋን እያሳየችኝ :: "" ይሀውልሽ ይሄ ጔደኛዬ ነው ሱራፌል ይባላል አስቸኴይ ነገር ስላጋጠመኝ እፈልግሀለሁ ብሎኝ በቃ የሱ ነገር ስለሆነብኝ እዚህ መጣሁ "" አልኴት :: ሱራፌል ክፉኛ በአይኑ ገረመመኝ :: መኪያን ግን ባክብሮት ብድግ ብሎ ""ጠይና ይስጥልኝ "" አላትና እጁን ለሰላምታ ዘረጋላት እሷም አጸፋውን መለሰችለት :: በተራዋም ይሄ ደግሞ አብዱል ይባላል ውጭ ሀገር የሚኖር የአባቴ የወንድም ልጅ ነው እንግዲህ ለኔ አጎቴ ማለት ነው አይደል አለች ሳቅ እያለች :: ""ትክክል ... ትክክል "" አልኩኝ ጮክ በማለት :: ልቤ ወደቦታዋ ስትመለስ ተሰማኝ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ብራንጎናትርን Joined: 29 Dec 2006 Posts: 608
Posted: Fri May 23, 2008 1:13 am Post subject:
ቀልቃላው ሱራፌል ወንበር ስቦ እንዲቀላቀሉን ጋበዛቸው :: እነሱም አላንገራገሩም :: ከጥቂት ደቂቃዎች በሁዋላ ወሬው ደርቶ እየተሳሳቅን ቢራ መኮምከም ጀመርን :: መኪያ አልኮል ነክ ነገር አልቀምስም ስላለች የሐረር ሶፊ አዘዝኩላት :: ከኔ ጎን ነው የተቀመጠችው :: ሱራፌልና አጎቴ ያለችው እንግዳ እንዴት ባንዴ እንደተግባቡ ወሬያቸውን ይሰልቁ ጀመር :: እኔና መኪያ እነሱ በሚያወሩት እንስቃለን :: ሱራፌል መቼስ የቀልድ ጎተራ ነው :: ከየት እንደሚመጣለት እኔ አላውቅም :: በቃ የሚጥላቸው ነገሮች ሁሉ ጥርስ የሚያስከፍቱ ናቸው :: የመኪያም ዘመድ ስለ ውጭ ኑሮው ይተርክልን ጀመር :: ሳውዲ ዓረቢያ ኗሪ ነው :: እናም ስለ ዓረብ ሀገር ኑሮ እየተረከልን ጨዋታው ደርቷል :: በመሀል መኪያ ማንም ሳያይ እጅዋን በጠረጴዛው ሥር አሾልካ የቀኝ እጄን ጣቶች ታፍተለትላቸው ጀመር :: የልቤ ትርታ እየጨመረ ሲመጣ ... _________________ "The purpose of education is not to fill buckets, but to light fires." – Yeats
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ጦምኔው Joined: 14 Jan 2007 Posts: 1433 Location: Right here
Posted: Sat May 24, 2008 4:10 am Post subject:
ግራ እጄን ወደ ጠረጴዛው ሰደድኩት :: ቢራውን አንስቼ ተጎነጨሁለት :: የመኪያ እጆች ልስላሴ እና የቢራው መራራ ጣዕም ተደባልቀው ድፍረት ሰጡኝ :: ቢራውን ወደ ጠረጴዛው መልሼ ግራ እጄን የቀኝ እጄን እንዲያግዘው ከጠረጴዛው ስር ሰደድኩት :: አራቱ መዳፎቻችን እርስ በራሳቸው ያዝኩህ አልያዝከኝም ዓይነት ጨዋታ ይጫወቱ ጀመር :: የእጆችዋ ልስላሴ እንዳልለቃቸው አስገደደኝ :: ዳበስኳት :: ለወራት ሀሳብ ብቻ የነበረችውን የዓይኔን አምሮት ዛሬ ቀን ታርቆኝ ከእጆቼ ላይ ጣላት :: ለካስ ስጋ እና ነፍስ ያላት የምትነካ እርካታ ያላት ናት :: ለካስ ዝም ብዬ ነበር ከራሴ ጋር ስሟገት እና ራሴን ወደ ኍላ ሳስቀረው የነበረው :: መኪያ አንዱን እጇን ከታፋዬ ላይ አኖረቸው :: ነዘረኝ :: የእጇ ግለት ከለበስኩት ጥቁር ሲልኪ ሱሪ አልፎ ተሰማኝ :: ሰውነቴ ሁሉ ሲወጣጠር ይታወቀኛል :: መኪያን ዘወር ብዬ ሳያት ዓይኖቿን ጨፍናለች :: ደነገጥኩ :: ምናልባት አጎቷ ቢያያት ምን ይላል ? ኧረ የኔው ጉድ ሱራፌልስ ምን ይሰማው ይሆን :: ሁለተኛውንም እጇን መጀመሪያ ወደላከችው እጇ ሰፈር ሰደደችው :: ሁለቱ እጇቿ ተባብረው አቅሌን አሳጡኝ :: ምን ;; እንደማደርግ ጠፋኝ :: የመኪያ ስራ የደስታ ስሜት እና ሁለቱ ቢያዩ ምን ይሉ ይሆን የሚለው የሀፍረት ስሜት ተደበላለቁብኝ :: አንዱን እጄን ወደ መኪያ ሰደድኩት :: የለበሰችው ቀሚስ ሁለቱን ታፋዎቿን ወጥሮታል :: እጄን ከሁለቱ ታፋዎቿ መሀል ገና ሳሳርፈው " አሀህ ..." የሚል የሲቃ ድምጽ ከመኪያ አንደበት ሲሰማ አጎቷ እና ሱራፌን እኩል ቀና ብለው ዓይኖቻቸውን ወደኛ ሰደዱት :: ለደቂቃዎች ሁላችንም ተፋጠጠጥን :: የመኪያ አጎት መኪያ ላይ ዓይኑን አፍጥጦ ..... _________________http://www.youtube.com/watch?v=_jIwsS_eT5w
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=22540&start=105
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ብራንጎናትርን Joined: 29 Dec 2006 Posts: 608
Posted: Sat May 24, 2008 5:16 am Post subject:
የሆነውን ነገር ለማወቅ የጉዋጉ በሚመስሉት ዐይኖቹ ያስተውለን ጀመረ ::
መኪያም የገባት ናትና "እንዴ ጣቶቼን ረገጥካቸውኮ :: ጫማህህን ..." ስትል በሙሉ ኃይል አቃሰተች :: "ብልህ ሴት ለባልዋ ዘውድ ናት !" ነው ያለው መጻፉ ? እኔም ታዲያ "ውይ ይቅርታ ! ጎዳሁሽ !?" በማለት አዛኝ ነብሰ ገዳይ ሆኜ ጨዋታውን ቀጠልኩ :: አጎት ተብዬው አሁን ቀልቡ መለስ ያለ ይመስላል :: ሱራፌልም ተረጋግቷል :: ግን የሆነ የጠረጠረው ነገር አለ :: አጎቷም እንዲሁ :: ሆኖም በሚያስገርም መልኩ ከጉድ ተገላገልን -- እድሜ ለመኪያ ::
ይበልጥ ለማስመሰል ጎንበስ ብዬ የግርዋን አቧራ (የሌለ አቧራ ) ማራገፍ ጀመርኩ :: እሷም እየሳቀች "አረ ቀና በል :: አይገባም ::" በማለት ተለሳለሰች :: የግር ጣቶችዋ ደስ ሲሉ :: ጎንበስ ብዬ ብስማቸው አልጠላም ::
ቀና ብዬ አየሁዋት :: አየችኝ :: ካይኖችዋ ቀያይ የፍቅር ጨረቃዎች ደምቀው ሲበሩ ታዩኝ :: ልቤ እንደ ሻማ ሲቀልጥላት ተሰማኝ :: እጅዋ አሁንም አላረፈም :: ቀስ ብላ ታፋዬ ላይ አሳረፈችው :: በዚህ ሰዓት ግን ለመረጋጋት ሞከርኩ ::
የገባው ሱራፌል አጎትዬውን ሲጋራ ያጬስ እንድሆን ጋበዘው :: ተስማሙ ::
"በል ወንድሜ እነዚህን ጻድቃኖች በጥሲ እንዳንበክላቸው ወደ ውጭ ወጥተን ሳብ ሳብ አርገን እንመለስ ::" በማለት አጎትዋን ይዞት ወጣ :: "የልብ አውቅ " አልኩኝ በልቤ :: የመኪያ ፊት በደስታ ሲፈካ ታየኝ :: አጎትዋ የጎሪጥ አየት አርጎኝ ሱራፌልን ተከትሎ ወጣ ::
እኔና መኪያ ብቻችንን ቀረን :: ቡና ቤቱ ውስጥ ራቅ ብለው የተቀመጡ ሁለት ሰዎች አሉ :: በወሬ ተጠምደዋል :: ባቅራቢያችን የተቀመጠ ማንም የለም ::
የነ ሱራፌልን እግር ተከትላ መኪያ እኔ ላይ ጥምጥም አለች :: እኔም ተጠምጥሜ ከንፈርዋን ከሞጨሞጭኩት በሁዋላ ትኩር ብዬ አያት ጀመር :: _________________ "The purpose of education is not to fill buckets, but to light fires." – Yeats
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
መልከጻዲቅ Joined: 08 Aug 2007 Posts: 675
Posted: Sun May 25, 2008 2:56 am Post subject:
ሱራፌልና የመኪያ አጎት አብዱል ተመልሰው መጡና ተለምዶዋዊውን "" ነወር -ነወር "" ሰላምታ ተለዋውጠን ወሬው ቀጠለ :: አብዱል ግን እንደቅድሙ ፈታ ብሎ መጫወት ተሳነው :: በጨዋታዎች መሀል እንደመቆዘም ሲል አስተዋልኩት :: እኔ ወይ ሱራፌል አለያም መኪያ እየገፋፋን ለወሬ ካልጋበዝነው በስትቀረ ቡዙ ለመጫወት ፍቃደኛ አልነበረም :: ቅድም በጥሩ መንፈስ ይጫወት የነበረው ሰውዬ አሁን ኩፍኝ የያዛት ዶሮ ይመስል ለምን ኩፍ እንዳለ ለማወቅ ጊዜ አልፈጀብኝም :: የመኪያ ጉንጮች ከማር ሰፈፍና ከለጋ የሸኖ ቅቤ የተሰሩ ይመስል መቅለጥ ጀምረዋል ;; ክንፈሮቿ ደግሞ ሊፈነዱ እንደደርሱ ቀይ አበቦች አባብጠዋል :: ""ያንተ ያለህ "" አልኩ ለራሴ :: ምን ስናደርግ እንደነበረ የመኪያ ፊት በትክክል ያሳብቃል :: ሱራፌል የጨዋታውን መንፈስ ለመቀየር የባጥ የቆጡን ቢዘላብድም የአብዱልን ቀልብ ለመሳብ ግን አልቻለም :: ትንሽ ቆይቶ አብዱል ሰአቱን አየና መኪያን ባደርኛ ቌንቌ አናገራት :: እሷም በተመሳሳይ መልኩ መልስ ሰጠችው :: ካነጋገራቸው አንድ ያልተግባቡበት ነገር ያለ ይመስለኛል :: እሷ መሄድ አልፈለገችም አብዱል ግን ረዘም ያለ መልስ ሰጣት ......እኔና ሱራፌል በደመ - ነፍስ አንዳቸው የሚሉትን እየተከተልን የሌላውን ምላሽ ለመስማት እንጠብቃለን :: በኌላ ግን መኪያ ቅር እያላት ብድግ እያለች "" በሉ ደህና አምሹ እኛ መሄድ አለብን "" አለች እኔንም ሱራፌልንም ተራ በተራ እያየች :: እኔም ቅር እያለኝ መሄዳቸውን ተቀበልኩት :: አብዱል ሳያንገራግር ብድግ አለና "" በሉ ደህና እደሩ ከመሄዴ በፊት ባገኛችሁ ደስ ይለኛል "" አለን :: ""ጥሩ ነው እኛም ብናገኝህ ደስ ይለናል ጥሩ ጊዜ ነበረን "" አለው ሱራፌልም በተራው :: ሁለቱ ተያይዘው ከወጡ በኌላ ሱራፌል ወረደብኝ "" ምን ነክቶሀል እስራኤል ?"" "" ምነው ?"" አልኩት ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ :: "" እኔኮ ሁኔታችሁ ደስ ስላላለኝ ነው ልጁን እንውጣ ብየው ይዥው የወጣሁት .."" አለኝ :: "" እኔ ምን ላድርግ ሱራፌል እሷ እኮ ናት የጀመረችው "" አልኩት ለመጠጣት የቡና ስኒውን ወደአፌ እያስጠጋሁ :: "" እንዴ ቢሆንስ አታስብም እንዴ አንደኛ አጎቷ አለ ደስ ላይለው ይችላል ...ሌላም ሰው ሊታዘበኝ ይችላል ብለህ ማሰብ አለብህ ቱሪስት አይደለህ "" በቃ አሁን ተወው አንዴ አልፏል ግን ልጁ ማለቴ አብዱል ያወቀ ይመስልሀል ?"" "" እንደገመትኩት ሳይጠረጥር አይቀርም ከንፈሯ ምን እንዳከለ አላየሀውም ....ሳምከው ወይስ በላሀው ?"" የሱራፌል ንግግር አሳቀኝ :: ለማንኛውም ነገ ስራ ቦታ ስትገናኙ ያላትን ጠይቃትና እንድትነገረኝ "" አለኝ :: በሀሳቡ ተስማማሁ :: "" እሱም እኮ ሊያገኘን እንደሚፈልግ ነግሮናል ለምን ይሆን ?"" አልኩት ያደረብኝን ጥርጣሬ ወደሱራፌል እያስተላለፍኩ :: "" ተዘጋጅተህ ና ወደ 9 ትናንሽ ነገሮች ሊለውጥህ ይችል ይሆናል ቁመቱንና የሰውነቱን ግንባታ አይተህዋል አይደል ? "" አለኝ እየሳቀ :: እኔም አብሬው ሳኩኝ :: ውስጤ ግን እንደገና መኪያን ማየት ተመኘ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator