WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የአዲስከተማ ሰዎች ካላቹ
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 18, 19, 20, 21  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ዲጎኔ

ዋና አለቃ

Joined: 19 Aug 2005
Posts: 4208
Location: united states

PostPosted: Fri Feb 05, 2010 6:54 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችን ይሁን
ውድ ቶድ ጌትሽና የተቀራችሁ የዚያች ብሩክ አዲስ ከተማ ፍሬዎች እንዲህ ስሜን በበጎ አንስታችሁ በግል መልክትም ስትፈልጉኝ ምንም ጊዜ ቢጠፋ ለእናንተስል ብቅ ብያለሁ ::
በትክክል ትውልድ ከተባለው ታናሹ ሆኜ ወደትግሉ ሳልገባ መጀመሪያ ማህደረስብሀት ልደታ ቀጥሎ በልደታ መካነኢየሱስ ሰንበትትምህርት ቃል እንዳልክድ ቢደግፈኝም
በሁዋላ ላይ ግን በነጎህ ቅስቀሳ በየዋህነት እኒያ አንዳች ጥቅም ሳይሆን የህዝብ አርነት የበለጠባቸውን ጉዋዶች እነ ሀይለገብርኤልን ከባልቻ አባነፍሶ ተከትዬ ነበር ::ነገር ግን
የነበረው እንዳልነበር ሆኖ አንጃው መካካዱ ሰፍቶ እነሆ እስከአሁንም የዚያች እናት ሀገራችን እርም ሆኖ በቀጣዩ በነጻው ፕሬስና በአክራሪዎች ዛቻና እንግልት ተሰድጃለሁ ::
የጨፌ ሜዳ ግጥሚያችን YMCAእና ፊትለፊቱ የነበረው ሻሚታ ዛሬ ከየት ይምጣ ? የእንዳለ ስጋ ቤት ቁርጥማ ተውኝ ! የካምቦዲ ትርምስ የግምጃ ጠጅ ቤት ወግና ጨዋታ አሁን ድረስ ትዝታዬ ናቸው ::አንድ ቀን ሀገሬ ስመለስ ጠጁ ቢቀር ብርዝ እየኮመኮምን የምናወጋ ይመጣል ::የእኛ ዘመን ጉልቤዎች ሙሉጌታ ቸሩ ተፈራ አለማየሁ ቱርኪ ነበሩ ::በእግርኮሱ እያያን ባለፈው ቺካጎ አገኘሁ እነቢረጋ ፍቃዱ ሙለታ ሪኮና ኒኒ ከመብራት ሀይል አይረሱኝም ::በሉ አዲስ ከቴዎች በሰላም በደስታ በጤና በአይን ለመተያየት ያብቃን ::በሚቀጥለው በእግርኩዋሱ ሳመር ላይ እንተያይ !ይቀጥላል
ዲጎኔ ሞረቴው ከባሻ ጂማ ጠጅ ቤት ማዶ ሚሽን ግቢ

Last edited by ዲጎኔ on Fri Feb 05, 2010 7:12 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዲጎኔ

ዋና አለቃ

Joined: 19 Aug 2005
Posts: 4208
Location: united states

PostPosted: Fri Feb 05, 2010 7:10 pm    Post subject: Reply with quote

ቀጣይ
ውድ ቶድ ጌትሽና ሌሎች የዚያች ብሩክ አዲስከተማ ወገኖች
ምንም እንኩዋን ኑሮና ስራ ፋታ ባይሰጥም ለእናንተ ለውዶቼ ስል ብቅ ብያለሁ ::በትክክል ትውልድ ከሚባለው ታናሽ ሆኜ ወደትግሉ ሳልገባ በማህብረስብሀት ልደታ ማርያምና በልደታ መካነየሱስ በጎ ምክሮች ሰምቼ ነበር
ሆኖም ግን በነጎህ መጽሄትና በእኒያ የህዝብ ፍቅርና አርነት በነካቸው ጉዋዶች ጥሪ ትግሉን ተቀላቀልኩ ::ዛሬ ማርክሳዊ ርእዮትን ብክድም በትግሉ አምናለሁ ትልቁን አታጋይ ክርስቶስን ይዣለሁና ::ያለፈው እንዳልነበረ ሆኖ መካካዱ አንጃነቱ በዝቶ እስከዛሬ ድረስ የዚያች ምድርቻን እርም ባያባራም እነደሚቃና ተስፋ አደርጋለሁ ::እንዳላችሁትም የአዲስ ከተማ ትዝታዬ እጅግ ብዙ ነው ::ከጨፌ ሜዳ ግጥሚያ እስከ YMCA ውድድሮች በመዝናኛው ከካምቦዲያ ሰፈር እስከ ተክለሀይማኖት ዳንስ ቤት ያልዘለልንበት አልነበርም ! የሞላ ማሩ ሻሚታው የግምጃ ጠጅ ቤት ወግና ጨዋታ ወደፊት በሰላም ሀገር ስንገባ በብርዝ ተክቼ እናወጋዋለን ::የኛ ጊዜ ጉልቤዎች እነሙሉጌታ ቸሩ ተፈራ አለማየሁ እነቱርኪ ነበሩ :: በእግር ኩዋሱ ቢረጋ እነፍቃዱ ሙለታ ኒኒና ሪኮ ነበሩ ::እያያ ባለፈው ቺካጎ አግኝቼዋለሁ ::
በሉስኪ አንድ ቀን ሳመር ላይ እግርኩዋሱ ላይ እንተያይ !
ዲጎኔ ሞረቴው እንዳለ ስጋ ቤት ማዶ ካለው የሳጠራ ቻፕል
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Getsh

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 09 Aug 2003
Posts: 94

PostPosted: Tue Feb 09, 2010 7:51 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ዲጎኔ ሰላም ቶድ በሚያብርቀርቅ ብዕሮቻችሁ አዲስ ከተማን ከላይ እስከታች በየመንደሩ እየገባችሁ ስታሳዩን በጣም ስእላዊ ሆኖ ነው የሚታየኝ : ጽሁፎቻችሁን ሳነብ አንዳንዴ እዛው የተባረከና ልዩ የሆነ የፍቅር ከተማ ውስጥ በሀሳቤ ያመላልሰኛል : ለዛሬ ብዙም የምለው አይኖረኝም በአጋጣሚ ቶድ የአየለን ጅቦ ስም ስላነሳ ስለሱ የተባለውንና የሰማሁትን ላካፍላችሁ ብዬ ነው :

ጊዜው አየለ ጅቦ ከዚህ አለም የተለየበት አካባቢ ነው : አየለ በፈረጠመ ሰውነቱና በጥቁረቱ ብቻ አስፈሪ ተክለስውነት ያለው ልጅ ነበር : እናም አንዱን የድርጅት ቀጣሪ አስፈራርቶ ያለውድድር ይቀጠራል ከዛም እዛው ድርጅት ውስጥ በጉልበቱ ተፈርቶና ተከብሮ ሰላማዊ ኑሮውን እዛው የሚሰራበት ክፍለሀገር ውስጥ እየኖረ ሳለ ይታመማል : በህክምናም ሊያድኑት አልቻሉም : ለቅሶ ላይ ይመስለኛል አየለ በሚሰራበት መስርያ ቤት ተቀጥረው ይሰሩ የነበሩ የጥበቃ ሰራተኛ : ልጄ ልጄ አለቃ አይደፍረህም ነበር : ባለስልጣንም አይደፍርህም ወታደርም ቢሆን አይደፍርህም : ሰው ሁሉ አይደፍርህም ነበር ግን ትንሽዋ ትንኝ አንበረከከችህ እያሉ አለቀሱ : መቼም ያገርቤት ለቅሶን ታውቁታላችሁ ብዙውን ልጽፈው አልቻልኩም አንኳር አንኳር ነው ያልኩትን ብቻ ነው የጠቀስኩላችሁ : አይደፈሬውን አየለን ለሞት ያበቃችው ትንሽዋ የወባ ትንኝ ነበረች : በዚህ አጋጣሚ ነፍስ ይማር ብያለው :

ቸር እንሰንብት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቶድ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 04 May 2007
Posts: 80

PostPosted: Tue Feb 16, 2010 1:46 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለመርካቶ ቤታችን እና ለውድ ሀገራችን ይሁንልን ::

ሰላም ሰላም ....... አቦ ጌትሽ .... ስለአየለ ጅቦ የተፃፈው ፉገራ በጣም ነው የተመቸኝ :: ቅቅቅቅቅቅቅቅ
ለነገሩ ትንሽን ነገር መናቅ አይገባንም :: ፈረንጆቹም እንደሚሉት '' ትንሽ ቀዳዳ ትልቁን መርከብ ታሰምጣለች ይላሉ '' !!!!!!!

አቦ ኧረ የመርኬ ልጆች የት ጠፋችሁ !!!!! ይገርማችኌል ያሁኑን አያድርገውና የመርካቶን ድምቀት ሳስበው .......... መሰደዴን ዕለት በዕለት ነው የማማርረው :: በሌሊት የእድር ጠሪው ጡሩንባ ........ በጥባት የወያላው የታክሲ ጥሪ ጩኽት ...... ሜክሲኮ ቄራ ሳሪስ !!!! .... እስቴዲዮም ላንቻ ጎተራ !!! ፒያሳ አራት ኪሎ መገናኛ !!!! መሳለሚያ ኮልፌ አጠና ተራ !!!! ጳውሎስ ዊንጌት አስኮ !!! ጦር ኌይሎች አየር ጤና አለምገና !!! እና የመሳሰሉት ........... ደግሞ በጥኌት የፀሐይ መብራት የእነዛ ውብ ኮረዳ ተማሪዎችና የጎረምሳው ትርምስ !!!! የሎተሪ አዙዋሪው .... የቀረፋ ቅርንፉዱ ...... የአሪቲና የእጣኑ ጠረን ...... የቄጤማው ልምላሜ የአደይ አበባው ፍካት ..... የሙዚቃ ቤቶች የዘፈን ድምቀትና ...... በተለይ በተለይ ደግሞ የህዝቡ ፍቅር .... ኩራት ...... ለጋሽነት .... ሐይማኖተኛነትና እጅግ በጣም የሚያኮራው ሐገር ወዳድነቱን ሳስበው ........ ዛሬ በስደት አለም ያለው ህይወቴ ከባዶ ቀፎነት ባሻገር ምንም የሚሰማኝ ደስታ የለም !!!!!! ከዛ ማንነቱን በቃላት ተፅፎ ከማያልቀው ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዝብ አብራክ .... አልፎም ተርፎም ከመርኬ አዲስ ከተማ መንደር መፈጠሬ በራሱ ትልቅ መታደል ነውና ...... በእውነትም በስደት እጅግ በጣም ታላቅ ነው ከሚባል ቦታ ከምዝናና ወይንም የስደትን ትልቁን ስጦታ ከማገኝ ይልቅ (የለውም እንጂ ) በሐገሬ አፈር በኩራት ብቀበር ........ እጅግ በጣም ታላቅ ክብር ነው :: እባካችሁ መርኬዎች እንሰባሰብ !!!!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወልጋዳው

መንገደኛ

Joined: 16 Feb 2010
Posts: 5
Location: chancho

PostPosted: Tue Feb 16, 2010 10:07 am    Post subject: Reply with quote

ስላም ብለናል መርኪወች እስቲ ሰለ ሀደረ ሰፈረ ቪዲዮ በቶች ምን ትዝታ አላችሁ ?????????
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቶድ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 04 May 2007
Posts: 80

PostPosted: Tue Feb 16, 2010 12:04 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ወልጋዳው !!!!!

የነምስራቅ ሸረፋን ቪዲዮ ቤት ትዝታ ነው ወይንስ የህንድኛ የሚተረጎምበትን ነው የምትለው ?????? እባክህ ትንሽ ዘርዘር አድርገው ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወልጋዳው

መንገደኛ

Joined: 16 Feb 2010
Posts: 5
Location: chancho

PostPosted: Tue Feb 16, 2010 7:41 pm    Post subject: Reply with quote

እጅ ነስተናል ቶዳችን !!!!
እኔ እንኩዋን ለማንሳት የፈለኩት የህንድ ቤቶቹን ነው 18ቀበሌ ያሉትን አቤት ትኬት ቆራጮቹ !! ስው እኮ አያሳልፉም በተለይ ከማልረሳቸው ትኬት ቆራጮች አቦሬ ቹቹሬ እና ጋንፉሬ የሚገረመው ሶስቱመ ወንድማማቾች ናቸው ስማቸው ብቻ ሳይሆን ፊታቸውም ያስፍራ ነበር :: የሂሩት ቪዲዮ ቤት በጣም የታወቀ ነበር አቤት ህንድ ፊልም ተጨፈጨፈ !!!!!!! ቶዳችን የነ ምሰራቅ ቤት በአሁን ስአት ኳስ ነው የሚታየበት ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቶድ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 04 May 2007
Posts: 80

PostPosted: Wed Feb 17, 2010 12:57 am    Post subject: Reply with quote

ወልጋዳው እንደጻፈ(ች)ው:

እኔ እንኩዋን ለማንሳት የፈለኩት የህንድ ቤቶቹን ነው 18ቀበሌ ያሉትን አቤት ትኬት ቆራጮቹ !! ስው እኮ አያሳልፉም በተለይ ከማልረሳቸው ትኬት ቆራጮች አቦሬ ቹቹሬ እና ጋንፉሬ የሚገረመው ሶስቱመ ወንድማማቾች ናቸው ስማቸው ብቻ ሳይሆን ፊታቸውም ያስፍራ ነበር :: የሂሩት ቪዲዮ ቤት በጣም የታወቀ ነበር አቤት ህንድ ፊልም ተጨፈጨፈ !!!!!!! ቶዳችን የነ ምሰራቅ ቤት በአሁን ስአት ኳስ ነው የሚታየበት ::

ቅቅቅቅቅቅቅቅ አቦ ወልጋዳው በሳቅ ነው የገደልከኝ !!!! የጠቀስካቸውንም ልጆች ባልሳሳት የማውቃቸው መሰለኝ :: በአንድ ወቅት ከጋዝ ተራ ልጆች ጋር በተፈጠረው ፀብ መርካቶ አውድማ መስላ ነበር :: ባይገርምህ እዛ ሰፈር በጣም ብዙ ጓደኞች ነበሩኝ :: ለመጥቀስ ያህል እንኳ ... እነ ሰይድ አጭሩ ... እነ ነቢል ... ኢብራሂም ዲጄው .... ምስራቅ ሸረፋ እና ሌሎቹም በጣም አሪፍና አራዳ ልጆች ነበሩ :: ..... ደግሞ እዛ ሰፈር ..... ኪካዎቹማ ታይተው የማይጠገቡ ነበሩ :: ለመሆኑ ጠልፎ ቤት አሁንም አለ ይሆን ???????
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወልጋዳው

መንገደኛ

Joined: 16 Feb 2010
Posts: 5
Location: chancho

PostPosted: Wed Feb 17, 2010 4:31 pm    Post subject: Reply with quote

ጠልፎ ቤትን ከጠራህማ ሀይለኘ አድቃቂ ነበርክ ማለት ነው Laughing Laughing Laughing ይገርምሀል በአሁን ሰአት ጫት ተራ አከባቢ አንድም መቃሚያ ቤት የለም በሙሉ ማለት ይቻላል የቨቀጥ ሱቅ ሆነዋል :: ስይድ አጭሩ ሀይለኘ ጫት ነጋዴ ሆኖልሀል ምስራቅም ቢሆን የቪዲዬ ቤታቸው ካሽር ነው አባው የነሱ ቤት ገቢ አዲስ አበባ ስታዲየም አያሰገባውም ደግሞ ኾስ ነው የሚያሳዩት ፊልም ድሮ ቀረ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዲጎኔ

ዋና አለቃ

Joined: 19 Aug 2005
Posts: 4208
Location: united states

PostPosted: Fri Feb 19, 2010 4:03 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችን
ውድ ወልጋዳው አንተ ደግሞ ወቅታዊውን ጀባ ስላለከን ተባረክ ! ከበርበሬ ተራ በታች ቁልፍ ሰሪዎች አጠገብ የነበረው እራሱ ህንድ የሚመስል ሰውዬ ሻይ ቤት አሁን ምን ደርሶ ይሆን ? አዲስ ከተማ ሲኒማ ቤት በሽልንግ የምንገባበት አሁንም አለን ?ሀጂስ ተክተው አልፉ ? ሲኒማ አድዋ በጉቦ እገባለሁ ብዬ የተሸወድኩት አይረሳኝም አዲስ ከተማ ግን ሀጂ አያስቀምሱም ነበር ::ልደት ኬክ ቤት እንዴት ነው ? በዚያ ዘመን ጥሩ መተዋወቂያ ስፍራ ነበር ;

ወልጋዳው እንደጻፈ(ች)ው:
እጅ ነስተናል ቶዳችን !!!!
እኔ እንኩዋን ለማንሳት የፈለኩት የህንድ ቤቶቹን ነው 18ቀበሌ ያሉትን አቤት ትኬት ቆራጮቹ !! ስው እኮ አያሳልፉም በተለይ ከማልረሳቸው ትኬት ቆራጮች አቦሬ ቹቹሬ እና ጋንፉሬ የሚገረመው ሶስቱመ ወንድማማቾች ናቸው ስማቸው ብቻ ሳይሆን ፊታቸውም ያስፍራ ነበር :: የሂሩት ቪዲዮ ቤት በጣም የታወቀ ነበር አቤት ህንድ ፊልም ተጨፈጨፈ !!!!!!! ቶዳችን የነ ምሰራቅ ቤት በአሁን ስአት ኳስ ነው የሚታየበት ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለከዘራ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 23 Apr 2008
Posts: 74

PostPosted: Sun Feb 21, 2010 9:18 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም መርካቶዎች , እኔም ሰፈሬ የደሮው ክፈተኛ 5 ቀበሌ 17, ሰባተኛ አካባቢ ነው ተወልጄ ያደግሁት :: መቼም መርካቶ ብዙ አደቬንቼር የነበረበት ሰፈር ነበር :; አሁን ግን ቢዙ ነገር እየተቀየረ ነው : ሰው ከመበዛቱ ከትርምሱ ተደምሮ ድሮ የነበረውን ለዛውን እያሳጣው ነው :
እረ ቶድ ! መርካቶን አብጠርጥረህ ታውቀዋለህ , ጉድ ነው ! እኔም በእነዚያ በእሳቶቹ እድሜዬ ላይ መርካቶ ገዛቴ ነበር :: ያለገባሁበት ቦታ የለም ነበር :: ብዙም ሳልቅይ በሱዳን መርካቶ አመለጠኝ ::

አሁንማ መርካቶ ተምድረ ገጽ ሊጠፋ ነው እየተባል ነው
ማለት እኔ እዝያ በነብርክ (የዛሬ ስድስት ወር አካባቢ ) ኮንዶሚንየም ሊሰራ ነው ተበሎ ተመዝገቡ እየተባለ ነበር :
እውነት ተሆነ ... መቼስ ይሁን ...

ተላይ ኢሕአፓ ሰትሉ ቢዙ ነገር አስታወሰኝ ...መቼም የማያልፍ የለም ... እኔ እንኩዋን በዚያ በሚጢጢ እድሜዬ ላይ ... 12 - 13 አመት ሆኜ . . . . ሚስጥራዊ ታዳጊ ወጣቶች ማህበር አባል ሆኘ አገልግያለሁ ...ያኔ የነበረንን ወኔ ሳስበው ይገርመኛል :: ቶድ ... ሰለሞን ኪሹ ...ታወቅውቅለሁ ወይ ? ... በሉ ለዛሬ በዚህ ይብቃ ::
በኬር ይግጥመን ::
_________________
nuro kalut telaja yimokal
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቶድ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 04 May 2007
Posts: 80

PostPosted: Sat Feb 27, 2010 6:22 am    Post subject: Reply with quote

ውድ ባለከዘራ እንኳን ወደዚህ አምድ
በሰላም መጣህ :: ሰለሞን ኪሹን ታውቀዋለህ ወይ ላልከኝ ጥያቄ ....... አዎ በዝና በጣም አውቀዋለሁ ..... ነገር ግን አንተ በመጠኑም ቢሆን ትንሽ ስትዘረዝር እኔ ደግሞ የማውቀውን እጨምርበታለሁ :: ዳሩ 17 ቀበሌ ትዝታ በጣም ብዙ ነው :: ከእነ ስለሺ ባሪያው ጀምሮ ..... አብዱ ኪያር ዘፋኙ (መርካቶ ሰፈሬ ) .... አሊ ካራቲስቱ .... ሰይድና ቡጥዬ (ኳስ ተጫዋቾቹ ) ..... የመነንና ትንሳዔ ግሮሰሪ ትዝታ .... የነሙሉጌታ ወጨፎ ግሩፕ እነ መኮንን ፍጹም ቹቹ ባሪያው እና ባጠቃላይ 17 ቀበሌ ከተወሰኑት የመርካቶ አንዱ ፈርጥ መሆኑ ብዙ እንዲባልለት የሚጋብዝ መሆኑን አትጠራጠር :: አንተ እንዳልከው 17 ቀበሌ ልጅ ከሆንክ በብዙ ትዝታዎች ትጀምርልን ነበር እንጂ በጥያቄ አትነሳም ነበር :: ለማንኛውም እስኪ እባክህ ስለ ሰለሞን ኪሹም ሆነ ስለ 17 ቀበሌ ሰፋ ባለ ሁኔታ ዘርዘር አድርገህ አውጋን ......

ወንድም ዲጎኔ ስለ አዲስ ከተማ ፊልም ቤት ስለ ሀጂና የሽልንግ ትዝታህ እንዲሁ በቀላሉ መቆም የለበትም ...... እጅግ በጣም አስቂኝ እና አዝናኝ አርስት በመሆኑ እባክህ ዘርዘር አድርግና ተመለስበት አደራ !!!!!!!!!!!!!

ሰላም ለመርካቶና ለውድ ኢትዮጵያ ሐገራችን !!!!!!!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቶድ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 04 May 2007
Posts: 80

PostPosted: Mon Mar 01, 2010 10:34 am    Post subject: Reply with quote

አቦ መርኬዎች !!!!!!!!!!!! ደግሞ ተነሳብን እንዴ ????? ብቅ ብቅ በሉ እንጂ !!!! ለመሆኑ የዋርካው ''ዋናው '' እኔ ሳልሰማ ለሌላ ሰፈር ተሸጧል እንዴ ????? ወደዝች ሰፈር ብቅ ካለ ሰንበትበት ብሏል !!!!!! በሰላም ይሆን ይሆን ?????

ውድ ባለከዘራው ወዴት ወዴት ጎበዝ ????

ወንድም ዲጎኔ እባክህ የሀጂንና የሽልንጓን ትዝታ ሰፋ ሰፋ አድርገህ አጫውተን !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዲጎኔ

ዋና አለቃ

Joined: 19 Aug 2005
Posts: 4208
Location: united states

PostPosted: Mon Mar 01, 2010 4:34 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለአዲስ ከቴዎችና ታዳሚዎቻቸው ሁሉ ይሁን
ውድ ቶድ ኑሮ በአሜሪካ ሲባል ድሮ በጋዜጣ በሬዲዮ ከተገነዘብነው በላይ ፋታ የማይሰጥ ስለሆነ ዋርካን ብዙ መቃኘት እያዳገተ ነው ::ለውዲቷ ሰፈሬ አዲስ ከቴ ልጆች ግን ወደሁዋላ አልልም !
ሲኒማ /ሙቪ በቁልምጫ የምንለው የጀመርኩት የስድስተኛ ክፍል ሚንስትሪ በተፈተንኩ ማግስት ነበር ::የመጀመሪያው ሲኒማ ቤቴ ሲኒማ ራስ ሲሆን በሰልፉ መጨናነቅ መሀል ገብቼ ተቸጨፍልቄ ነበር ::የሲኒማ መግቢያውን የምናገኘው አንዳንዶቻችን ድሮ መዳብ ለሚገዙ እያጠራቀምን በኪሎ ብረት ተራ ወስደን በመሸጥ ነበር ::እኔም በልጅነቴ አያቴ ጠበቃ ስለነበሩ ስራ ሳግዝ ድጎማ በሚሰጡኝና ቡሄ ጨፍረን ከምናገኘው ወይም አበባ ወረቀት በመሸጥ ነበር :ያኔ አዲስ ከተማ ሲኒማ ቤት በሽልንግ የሚገባበት ሲሆን እንደሌሎቹ ሲኒማቤቶች በጉቦ እንዳገባ ሀጂ በትር ይዘው አያነቃንቁም ነበር ::መቸስ ዛሬ በህይወት አሉ ለማለት ያዳግተኛል ያኔም በእድሜ የገፉ ነበርና ::ስኒማ አዲስ ከተማ ከሲኒማ አምፒር ጋር ሽርክና ስላላቸው አምፒር የታየ ፊልም ሲቀየር አዲስ ከተማ ይመጣልናል ::አምፒር በሁለት ብር ከማየት አዲስ ከቴ ጠብቀን በሽልንግ እናይ ነበር ::በጉቦ ፊልም መግባት ዋጋው ርካሽ አንዳንዴ ከሽልንግ በታች ፊልሙ ከተጀመረና ሰው ብዙ ከሌለ ነበር ::በጉቦ መግባት እርም ያልኩት የሲኒማ አድዋ በረኛ በውሸት ሽልንጌን ተቀብሎ በሲኒማ አድዋ ዙርያ አንከራቶ ከሸወደኝ በሁዋላ ነበር ::በጣም ክምወዳቸው ሙቪዎች የህንድ ሀቲ ሜሪ ሳቲ /ዝሆን ጉዋደኛየ ወክትና ማዘር ኢንዲያ ሲሆኑ ከአሜሪካ ፊልሞች በርትላንካስተርና ጆንዌይን የመሳሰሉት ከጣልያን አቺሌና የማፊያ ሙቪዎች ነበሩ :: አዲስ ከተማ ሲኒማ ቤት ከሀገር ቤት ሳልወጣ በዙርያው ብዙ ቡቲኮች ተከፍተው ነበር አሁን ይኑር አይኑር አላቅም ለእኛ ግን በዚያ ዘመን የሲኒማ እውቀት እንዲኖረን ረድቶናል ::በጣም ደስ የሚለን ደግሞ ሙቪውን መተረክን ጨፌ ሜዳ እንደሙቪ አክት እያደረግን የምንሰራው ድራማ ነበር ::በዚያ ትውልድ እልቂት ተጨናገፈ እንጂ ሻውል ደማ ትምህርት ቤት የቲያትር ልምምድ እያደረግን ኪነጥበቡን አስተዋውቀን ነበር :: በልጅነት ልምዳችን መሰረት ዛሬ በሚድያ የሚሰሩ እነሚናስ ገብረመስቀል ትምህርት በሬዲዮ የዚያው አዲስ ከቴ ልጅ ነበር ::ሌላው የአዲስ ከቴ ልጅ ሚናስ ተክሌ ደግሞ እንግሊዝ ሀገር ያለ በቅርቡ በጀርመን ድምጽ ሬዲዮ በክራር ሙዝቃ በሲዲ እንዳቀናበረ ኢንተርቪ ሰጥቷል ::ሁዋላ ፊልም ድርጅት ሲዋቀር የላጋሮቹ ፎቶሊቴና እነአብዱራማን ሰንጋተራ የነበረ ፎቶ ቤታቸው በቴክኖሎጂ ለማሳደግ ሲጣጥሩ ነበር ::መጣጥፍ በማቀናበር የሚተባበሩን የጌጃ ቃለህይወት ደረጀ አበባና በሲኒማ ጥበብ የተካኑ እነታምር አበራ ኤልሳቤጥ መላኩ የጀመሩት ፕሮጀክት ቢኖርም ዛሬ በህትመት ችግር መጽሄቱ ቆሟል ::ተስፋ የተጣለበት የሲኒማ ራስ ቲያትር ከያኒና አቀናባሪ ይግረም ረታ ከስራው ተፈናቅሎ እንደሚንከራተት ከሀገር ቤት በቅርቡ የመጣ ሰው ያጫወተኝ ሲሆን የፊልሙን ስራ ሌላው ከያኒ በመንጠቆ ስራ የማደንቀው ጥላሁን ጉግሳ እደጀመረ ሰምቻለሁ ይሳካለት ዘንድ ጸሎቴና ምኞቴ ነው ::በህይወት ዙርያ ኢትዮጵያዊ ፊልም ጥሩ ጅምር ትእግስት አዘጋጅውን በመብት ክፍያ በመክሰሷ አሳዛኝ ነገር ተፈጥሯል ::በሀገራችን ኪነጥበብ እንዳያድግ ይህን መሰሉ ችግር መወገድ ለሰራተኛ ተገቢ ድካሙ ሊከፈል ሲገባ በከንቱ መወነጃጀል ግን ሙያውን ሀገርንም ይጎዳል ::
በተረፈ ያቺ አዲስ ከትማ ይህን ሁሉ ለመዘገብ ባለንበት ስቴትም ማህበራዊ የኮሚኒቲ ተሳትፎ ለአበሻውና ለሌሎቹም እንድናደረግ መነሻ የሆነችን ዘወተር ስትታሰብ ትኖራለች ::
ዲጎኔ ሞረቴው ከሲኒማ ራስ ሀይሉ ትይዩ ሲኒማ አዲስ ከተማ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Getsh

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 09 Aug 2003
Posts: 94

PostPosted: Tue Mar 02, 2010 3:51 am    Post subject: Reply with quote

ሠላም አዲስ ከቴዎች

ቶድ እስኪደንቀኝ ድረስ ያዲስ ከተማን አፍና ቂጥ ስለምታውቀው እኔ በራሴ እያፈርኩኝ ነው : እዛ ሰፈር ውስጥ ተወልጄ ማደጌም ጥያቄ እየሆነብኝ ነው : የዲጎኔ ደግሞ ለየት ያለ ነው : ያልነካካው ሰፈርና ያልደረሰበት ቦታ የሚኖር አይመስለኝም : ከንቲባውም የሱን ያህል አያውቃትም : ባለ ከዘራና ወልጋዳውም በጥሩ ሁኔታ ዶሮ ተራን አስቃኝተውናል : እዚህ ላይ ሙሉጌታ ወጨፎ ስትሉ ሌላ ትዝታ ውስጥ ከተታችሁኝና ለናተም ላውጋችሁ :: ልጅ ሆኜ ለቤተሰብ ጋዝ ግዛ ተብዬ ወደ ሰባተኛ ሞቢል ይሁን አጂፕ ከጉዋደኛዬ ጋር እየሄድን እያለ GS ሙዚቃ ቤት በታች ካለው ቅያስ ላይ ስንደርስ ይሄው ጉደኛ ልጅ ያለምንም ምክንያት በርግጫና በኩሩኩም ያጣደፈን ጀምረ ቀዳዳ ሳገኝ እግሬ አውጭኝ አልኩኝ :ወደ ቅያሱ ስሮጥ : ውስጥ ለውስጥ አባሮ ያዘኝና ያለህን አውጣ ሲለኝ ምንም የለኝም አልኩት ያው ምንም ገንዘብ እንደሌለኝ እርግጠኛ ስለነበርኩኝ : ፈትሾኝ መናጢ ታድያ ምን ያስሮጥሀል ብሎኝ በማሳረጊያ ኩሩኩም ሸኘኝ : ኪሴ ውስጥ ለጋዝ መግዣ የተሰጠኝን ብር ያስታወስኩት አጂፕ ስደርስ ነበር : ለካስ ሙሉጌታ ያችን አግኝቶ ነው ሳያስፎግር በኩርኩምና በስድብ ያሰናበተኝ :: ታድያ ካደኩኝ በኋላ የማያረጀው ጉደኛ ሙሉጌታ ወጨፎን ብሌን ሆቴል ውስጥ አገኘሁትና ልጅ ሆኜ ያደረገኝን ለጉዋደኞቼ ስነግራቸው እነሱም ጠሩና ነገሩት : አፈ ጮሌው ሙሌም ጋዝ 85 ሳንቲም በነበረብት ጊዜ የሆነውን አሁን መክፈል አልችልም ብሎን አረፈ ::

ቶድ የአየለ ጅቦ ታሪክ ጆክ አይደለም እውነት የሆነውን ነው ያወጋውህ :

በተረፈ ቸረ ይግጠመን
Getsh
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 18, 19, 20, 21  Next
Page 19 of 21

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia