WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የሙኒከ ቅዱስ ገብርኤል አስተዳዳሪ ችግር
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ethio-german

መንገደኛ

Joined: 20 Dec 2010
Posts: 9

PostPosted: Wed Jan 05, 2011 5:54 pm    Post subject: Reply with quote

ስላም ክርስቲያኖች

እነ መንገደኛ ጋዜጠኞች

በሙኒክ /ገብርኤል ቤተክርስቲያን ስር ለብዙ አመታት ለወንጀለኛው ለቄሱ እና ለሚስትየው እጅ መንሻ እንጀራቸውን ሸጉጠው ወሬ እያቀበሉ አሊያም በየቤታቸው ደግሰው እየጠሩ እከሌ እንዲህ አላችሁ እከሊት እንዲህ አለቻችሁ እያሉ ትኩስ ወሬም ካገኙ አላስችል እያላቸው ሰው ለጠዲቅ ያመጣውን እየደባበቁ ሰው ወደየቤቱ እስኪሄድ ጠብቅው የደበቁትን አውጥተው እየተገባበዙ እዛው ቤተክርስቲያን ውስጥ አሉ ባልታቸውን የሚተረትሩ እግዚአብሄርን እንኩዋን የማይፈሩ ባለጌነታቸውን አገር የሚያውቀው የጥቅም ሰዎች ዛሬ ደግሞ እንደለመዱት አንዴ ወደዚህ አንዴ ወደዚያ በማለት ዘዴያቸውን በመቀየር ሰው ለመሰብሰብ እናም ሁሌም ለመታወቅ በሚያደርጉት ጥረት የሞቱ ሰዎችን በምሳሌነት እያነሱ ሰው ሲሞት አስክሬን መላኪያ እድር ያስፈልጋል ገንዘብ እያጠራቀምን ማስቀመጥ በማለት በአንድ በኩል እያጋፈሩ ይገኛሉ አይናውጣ ይሉዋችሁዋል እንዲህ ነው ሰው የሚወዱ እየመሰሉ ያንን ጥርሳቸውን እያገጠጡ ከሰው አፍ ወሬ ለቅመው የሚሮጡት ሳያንሳቸው በቁም ሰውን እያባሉ ሰው ከሞተ በሁዋላ አስክሬን መልኪያ እናጥራቅም ምን ዋጋ አለው Rolling Eyes በሩቁም አልተቻላችሁ እንኩዋንስ በለቅሶ ሰበብ በየሰው ቤት ገብታችሁ እስካሁን ሰው በየቤቱ እንጀራውን ሲጋግር እናተ ተሰብስባች እንጀራውን የምትቆጥሩለት አልበቃም አላች Question እግዚኦ ይቅር ይበላችሁ
በጣም የሚገርመው ያንን የማይሞት ምላሳችሁን ቀላምዳችሁ የሙኒክ ዌብ ሳይት ላይ በብዛት ሰው ለመሰብሰብ እግራችሁን አስፍታች ለአገር የሚደክሙትን ሰዎች ለማተራመስ በአንዳድ ሰዎች ተከልላችሁ ማስታወቂያችሁን ስናይ ጉደኞች መሆናችሁ አስገርሞናል
ወገን እንድናስተውል ይገባናል --ይቀጥላል
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ethio-german

መንገደኛ

Joined: 20 Dec 2010
Posts: 9

PostPosted: Wed Jan 05, 2011 6:44 pm    Post subject: Reply with quote

ለመሆኑ ለእንደዚህ አይነቶች ሰዎች ethio munich website ላይ ማስታወቂያ የቃልኪዳን እድር እናቁዋቁም የሚል ማስታወቂያ እንዴት እንዲለጥፉስ ተፈቀደ Question ሌላ ቤተክርስቲያን እንዳትሄዱ የቶለቲካ ቤተክርስቲያን ነው እያሉ ሰውን ሲያከላክሉ የነብሩ ሰዎች ለጥቅማቸው ሲሉ ገን ብቅ አሉ ያሳዝናል አሁንስ ገራ እየተጋባን ነውና ሰዎች እናስተውል
ግልብጥ ሲሉ ግልብጥ ይሉዋችሁዋል ይሄ ነው
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሰዋሰው

አዲስ

Joined: 25 Nov 2003
Posts: 20

PostPosted: Wed Jan 05, 2011 7:40 pm    Post subject: Reply with quote

ethio-german

ያገር ልጅ ! ያሁኑ ጉዳይ ቄሱ ቤተ ከርስቲያናችን ስለዘረፉት 165 ሽህ ኦይሮ የምስኪን ኢትዮጵያዉያን ( ለዛዉም ያልወጣ ወጪ , ወጪ ተደርጉዋል ያሉት ሁሉ አንድ ነገር ጠብ ሳትል ተይዞላቸው እንደልባቸዉ ስለጨፈሩበት ገንዘብ ) እና በይብልጥ ወደፊት ይህቺ ቤተ ክርስቲያን በምን ወይንም እንዴት እንደምትተዳደር ለመወያየት ነው :: ስላነሳህዉም ጉዳይ ቢሆን ብዙ ሰው በየ ቤቱ የሚነጋገርበት ጉዳይ ነው :: ጥሩም ታዛቢ ነህ እነዚህ ሰዎች ምን ሊያደርጉ እንዳሰቡ እግዚአብሔር ይወቅ ገንዘብ ሰብስበዉ ቢያጠፉ እንኩዋን እነርሱ ቄሶች ወይንም ዲያቆናት አይደሉም እንደ ሰዉ ታዝበህ ዝም ትላለህ ወይንም አፍንጫቸዉን ትላለህ ወይንም በህግ ከሰህ ታርበደብዳለህ :: ነገር ግን አሁን ከሁሉም ነገር አስቀድመን ቤተክርስቲያናችንን ዲያብሎሶች መንጋጋ ፈልቅቀን ማስወጣት አለብን ይሄኛዉ በጣም ከባድ ነገር ነው ይህ መንፈሳዊ ተብዬዉ ሌባ ካህን ነኝ ብሎ ልብሰ ትክህኖ ለብሶ መስቅል ይዞ ቤተ መቅደስ ቆሞ ኢየሱስ ክርስቶስ አግልጋይ መስሎ እኔ ከደሙ ንጹህ ንኝ አትስረቅ አታመንዝር ሌላዉን ሰው እንደራስህ አድርገህ ዉደድ በዉሸት አትመስክር እያለ ሲሰብከን እራሱ ግን ከላይ ይተባለዉን አንዱንም በጎ ነገር የማያደርግ የማይፈጽም አዉሮፓዉ እያንጉዋለለ Laughing ነው :: እከሌ እንዲህ ናት እከሌ እንዲህ ነው መባባያ ሰዓት ይብቃ ካለፈው ጊዜ ብዙ መማር ያስፈልጋል :: ይልቅ ለቤተክርስቲያኑዋ ቅርብ ነን የምትሉ ሰዎች አስቸኩዋይ መፍትሄ ለዚህ ጉዳይ እንድናገኝለት የምታዉቁትን ነገር ወይንም ወደፊት ሊሆን ሊደረግ ይችላል የምትሉትን ነገር ምእመናኑ ጋር ተወያዩበት :: ስለዚህ ያሁኑ ጉዳይ ከምንም ነገር በላይ በጣም አሳሳቢና የሁላችንም ጉዳይ ስለሆነ ሌላዉን ለሌላ ጊዜ እንተወዉ ::
መድሀኔአለም ሃይማኖታችንን ይባርክልን ሀገራችንን ከእንደነዚህ ያሉ ውሾች ያጽዳልን ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጎዛመን

መንገደኛ

Joined: 06 Jan 2011
Posts: 3

PostPosted: Thu Jan 06, 2011 2:12 am    Post subject: Reply with quote

ሰዋሰው
ጉዳዩ ባሁኑ ጊዜ በየትም ቦታ ሲከሰት ማየት እነሆ ምን ዓይነት ቀን ላይ ደረሰን ያስብላል በእዉነትም ሞራል ይሰብራል ያናድዳል ያስለቅሣል ጀርመን የህግ ሀገር ነው እየተባለ እንዴት ነው እንዲህ ይሄንን የሚያክል ገንዘብ አንድ ቄስ ለብቻዉ ሊዘርፍ የሚችለው እኔ ይሄንን ለመቀበል ይከብደኛል ያም ሆነ ይህ ግን እኔ እንኩዋን ዋርካ ላይ መጻፍ አላዉቅም ብዙ ጊዜ ማንበብ ነው ደስ የሚለኝ ስለ ቄሱም የማዉቀዉ ነገር የለኝም ሀይማኖታችን ግን የትም ቢሆን አንድ ስለሆነች የሚያከብሩዋትን ማክበር የሚጠብቁዋትን መዉደድ ጥሩ የሚያስብላትን ሰዉ መደገፍ የግዴታ ስለሆነ አይዞህ አመለካከትህ ጥሩ ነው ኃጢአተኛ ቤተ መቅደሳችሁ ዉስጥ እንዳታስገቡ
በጣም ጥሩ አስተዋይ ሰው የሀይማኖት ወንድም ነህ ለሀይማኖቱ ክብር የሌለው ለቤተሰቡም ሆነ ለሀገሩ ክብር የሌለዉ ሰዉ ነው እንዲህ ዓይነቱን ቤተ ክርስቲያንን የሚያረክስ ሰዉ እስልምና ሀይማኖት ዉስጥ ቢሆን ኑሮ ወይ በድንጋይ ተደብድቦ ይገደል ወይ እጁ ይቆረጥ ነበር እንደዚህ ይደረግ ማለቴ ሣይሆን በትንሹ ቤተክርስቲያን ከእንደ እነዚህ ያሉ ኅጢአተኞች መጽዳት አለባት አለበለዚያማ ከጥዋት እስከ ማታ ከእነርሱ ጋር ጸሎት ተብሎ ሲጸልዪ ቢዉሉ ሀሰትን ሲማሩ ዉሎ መግባት ጊዜን ዝም ብሎ እንደማባከን ማለት ነው :: እንዲህ ዓይነትን ነገር ዝም ብሎ ማየት እጅህ ሲቃጠል ዝም ብለህ እሳት ላይ መያዝ ማለት ነው ገብኤልን ያልፈራ ሰዉ ማንን ሊፈራ ይችላል
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሊሊ 123456789

መንገደኛ

Joined: 07 Jan 2011
Posts: 1

PostPosted: Fri Jan 07, 2011 8:02 pm    Post subject: Re: የሙኒከ ቅዱስ ገብርኤል አስተዳዳሪ ችግር Reply with quote

ይህ ቅሌት በሙኒክ ብቻ ሳይሆን
በፍራንክፈርት እየተደገመ ይገኛል ስለዚህ ቄስ መርአዊ ተበጀ መፍትሄ ካላመጡ
በሳቸው ከለላ የሚደረገው ሴራ የራሳቸውንም ክህነት እንደሚያሳጣቸው እንዲያቁ በተረፈ በፍትሀ ነገስት ላይ ማየት ይቻላል
የሰረቀ የዋሸ ክህነቱን ይነጠቃል ይላል
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሰዋሰው

አዲስ

Joined: 25 Nov 2003
Posts: 20

PostPosted: Sat Jan 08, 2011 2:11 am    Post subject: Reply with quote

በመጀመርያ ዉድ ኦርቶዶክስ ልጆች እህትና ወንድሞች እንኩዋን ለብሃነ ልደቱ በሰላም አደረሣችሁ
ጎዛመን ለድጋፍዎ እግዚአብሔር ይስጥልኝ . እኔም ይህን ጉዳይ እዚህ ላይ የምጽፈው የተለየ /ክርስቲያን ቅርበት ወይንም ሌላ የምፈልገዉ ነገር ኖሮኝ አይደለም ሆኖም ግን /ክርስቲያንን መጠለያዬ የራሴ ቤቴ ናት ብሎ የራሱ አድርጎ አምኖ እቤቱ ዉስጥ የተቀመጠ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ የሀገራችን ሰዉ እዚህ አካባቢ ብዙ ነው ሌባው ቄስ ግን ስብሰባው እለት ልጆቻችሁን እስከዛሬ ክርስትና ሳነሣላችሁ ኖሬ እንዴት ዛሬ ገንዘብ ብወስድም እንዲህ ትወነጅሉኛላችሁ ብወስድም ይህን ለእግዚአብሔር ስጥታችሁ ሌላ ብር አሁን ቤተ ክርስቲያኑ ኪሣራ ዉስጥ ስለገባ አዋጡ እያሉ ሊቀባጥሩ ሲቃጣቸዉ ነበር :: የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ አድርቅ አሉ ይሉዋችሁዋል እንዲህ ነው :: በእርግጥ ግን ቤተክርስቲያኑ ምናልባት ካሁኑ ዘዴ ካልተፈለገ ከሁለት ወይንም ሶስት ወር በሁዋላ ሊዘጋ ይችላል ምክንያቱም ገንዘቡ እንደተባለው ሀገር ቤት የዶሮ እርባታ እና ቤት ቢዝነስ ብቻ ያልተባለ የለም ኢንቨስት አድርገዉበታል ቢዝነስ ማኑ ቄስ 165 ሽህ በቂ ኢንቨስትመንት ነዉ ለያዉም አንቱ የሚያስብል ! የሚያሳዝነው ሌባዉ ቄስ አሁንም ቤተ ክርስቲያን ማገልገላቸዉን አልተዉትም ሰዉ እስከሚያስቆማቸው ድረስ ነው የሚጠብቁት እሳቸዉ ገብርኤልን በጣም ነው የናቁት እኔ ስለ እዉነት ይሄ ድፍረታቸዉ በጣም ይገርመኛል :: ቄስ (መቸም አቶ እንዳልል ሀይማኖቴ ህግ አስፈርቶኝ ነው ) መስፍን /ማርያም ወደዱም ጠሉም ይህቺን ቤተ ክርስቲያን ለቅቀዉ መሄዳቸዉ ወይንም መታሠራቸዉ የማይቀር ነገር ነው ሰዉ ካልሆነ ገብርኤል እንደማይፈልጋቸው ካሁኑ እያሳየን ነው : ቤተክርስቲያናችንንና ምናልባት የተሰረቀዉንም ገንዘብ ሊያወርሱት ዲቁና የሰጡት ልጃቸዉ ከእስላም ሴት ጉዋደኛው ልጅ ሊያስወልድላቸው እያኮበኮበ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው እሳቸዉም የዉርደት መጀመርያቸዉን ሊከናነቡት ነው :: ይህ እንግዲህ ምልክት ነው ጄኔራሉ ሌባ የሚገባቸዉ ከሆነ :: ሌላው በየቀኑ ይቅር በሉኝ ሁለተኛ አይለመደኝም ሰርቼ እከፍላለሁ አተካሮ ምናልባት ሀገር ቤት ሊሰራ ይችላል ምክንያቱም እንደምናየው እዛም ፈሪሃ እግዚአብሔር እየጠፋ ስለሆነ በጉቦ በዘመድ ብዙ ጊዜ ስለሚስሰራ እዚህ ሀገር ግን ሊከሰት አይችልም መቶ ጊዜ ይቅርታ የሚባሉት ሰዎች ደግሞ እምነቱ ምናልባት ምንም የማይመስላቸው ዝም ብለዉ ሞኝ ቲፎዞዎች አሁንም ከእንደዚህ አይነቱ ሌባ አታላይ ከሀዲ ወሮበላ አድርባይ ካህን ተብዬ ጋር አብረዉ የሚጸልዩት መስቀል ከሌባ እጅ የሚሳለሙት ቢበዙ ሃያ ሰዎች ሌላዉን በስሙ ከካቶሊክ /ክርስቲያን ስይቀር ገንዘብ ሲጨረገድበት የኖረዉን ቢያንስ 2 ሽህ ሙኒክና አካባቢዉ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊ ከማሣዘን በስተቀር ሰዉየዉን በመጨረሻ ከምንም አያድኑዋቸዉም ምክንያቱም ቢያንስ ቢያንስ 165 ሽህ መልአኩን ቅዱስ ገብርኤል ቤት ደፍረዉ የየዋህ ኢትዮጵያዉያንን ገንዘብ ለመዝረፋቸዉ አምነዋልና ስለዚህ ማንም በዚህ ሀገር ኑሮ በዚህ ሀገር የኑሮ ዉድነት ለሃይማኖቴ ለእምነቴ ብሎ እየቸገረዉ የሰበሰበዉን ገንዘብ የማንም ዱርዬ ቅስናዉን ትከልሎ መስቀሉን ጨብጦ ሲዘርፈው ዝም አይልም እንደዉም እልክ ዉስጥ ነው የሚገባዉ :: እንደዉም እንደዛ ጽላት አቁመዉ ሁሉ እየሰደቡት ከክርስትናዉ ትምህርት የበለጠ የስድብ እና የሀሜት ዉርጅብኛቸዉን ዝም ብሎ ሲቀበል የኖረው እና አጉል ፖለቲካ ሳይንቲስትነታቸዉን ሲታዘባቸዉ የኖረዉ እንደ ብዙዎቹ ይሄንን አልሰማም ሃይማኖቴ ይህን አያስተምርም ብለዉ ጭራሽ ከቤተ ክርስቲያን እንደቀሩት እኔ ግን የለም ሁሉንም ስድቡንም እችላለሁ ቤተክርስቲያኔን ትቼ ወደየትም ፍንክች አልልም ብሎ እስካሁን ዝም ብሎ ሥራቸዉን የሚከታተለዉን ምእመን እንኩዋን የባሰ ያሁኑ ሥራቸዉ ያናድደዋል ብዬ ነው የማምነው ::
ሌላዉ የኔ እህት አንቺ ስለጻፍሽው ብዙ መጻፍ ባልችልም ከእንግዲህ በሁዋላ ቤተ ክርስቲያናችንን መጠበቅ ያለብን እኛው ነን :: እንደ ሃይማኖታችን የረጉ በኦርቶዶክሳዊነታቸው የነጡ በክህነታቸዉ የሚኮሩ እና የሚያኮሩ በክርስትና እዉቀታቸዉ የበለጸጉ ፖለቲካን ከመንፈሣዊነትአርቀዉ ያስቀመጡ መመሪያቸዉ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሲኖዶስ ፍንክች የማይሉ ስንት አይነት የማይጠገቡ ሀግራቺን ዉስጥ በየ ገዳማቱ ዉስጥ በቀን አንድ ጊዜ እንኩዋን ከሚበሉት ለእኔ ቢጤ የሚያካፍሉ እንኩዋን ሌብነት ይቅርና አለማዊነትን ፈጽሞ የናቁ የሚጣፍጡ አባቶች ሞልተዋል እነርሱን ነው ጎርጉረን እንደምንም ማምጣት ያለብን እዚህ ያሉትንም ወጣቶች ቢሆን ከእዉቀት በስተቀር መንፈሳዊነታቸው ለእኔ ያን ያህል እንደምጠብቀዉ አይደለም (ቢሆንም ግን ወቀሣ አይደለም ይኑሩልን ልቦናም ይስጣቸዉ ) :: እነዚህ አንዱ አንዱን እየሸፈነ ሃይማኖታችንን የሚያደቅቁልንን ሌቦች ግን ድራሻቸዉን ማጥፋት አለብን እዚህ ጀርመን ብቻ ሳይሆን በመላዉ አለም ላይ እንዲህ አይነት የሚፈጽሙትን ከቤተ ክርስቲያን የግዴታ ማግለል ያስፈልጋል ::
መድኃኔአለም ሁላችን ጋር ዪሁን ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ethio-german

መንገደኛ

Joined: 20 Dec 2010
Posts: 9

PostPosted: Sat Jan 08, 2011 9:26 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ወገኖች

ባለንበት አገር ሙኒክ ከተማ በቤተክርስቲያን ያውም በእግዚአብሄር ቤት ተከልለው ቄሱን ብቻ ሳይሆን ከዚህ ከሌባ ቄስ ለብዙ አመታት ሲጫወቱብን የኖሩ ባንዳዎችንም መዋጋት ያለብን ከበፊቱም አንዳንድ መእመናን ስለ ገንዘቡ ሁኔታ እናም ሌላም አስተያየት ስለ ቄሱ በመናገር እኝህ ቄስ ሰውን እያስቀየሙ ነው በቤተክርስቲያን ውስጥም ህግ እየተጣሰ ብዙ ድፍረቶች እየተሰሩ ነው ለምሳሌ ሰው ከሰው እየተለየ የሚሰራው ግፍ ሳያንሳቸው ዝሙቱን ሁሉ ሲያካሂዱበት እየታየ ምንድን ነው የምንጠብቀው በማለት ሲናገሩ እያንዳንዱዋ ወሬኛ እየተነሳች ወሬ ስታቀብል በምእመናኑ ገንዘብ አገር ቤት ንብረት ሲያከማቹ አብረው እየሄዱ ሲመርቁላቸው ከርመው ቄሱ የጋብቻ በአላቸውን አገር ቤት ሊያከብሩ ነው ገንዘብ እናዋጣላቸው እያሉ ከየሰው ገንዘብ ሰብስበው ገጸ በርከት እየሰጡ አብረው ሲጋልቡ ከርመው የቄሱ ወሬ አቀባዮች እየተጠቃቅሙ ከኖሩ በሁዋላ ብዙ ብዙ ነገር እየተሰራ ቄሱም ቀኝ እጃቸው ሆነውላቸው እከከኝ ልከክህ ሲባባሉ በኛ በስደተኞቹ ገንዘብ ይህው እግዚአብሄር ሲፈርድ ዛሬ ቄሱ ጠግበው ጠግበው ደረታቸውን ሲነፉባቸው ጉዳቸውን ማውጣት ጀመሩ እኛም የሞተ ፈረስ ጋላቢ ሆንን Embarassed ካሁን በሁዋላስ ገንዘባችንን እናገኛለን ብላችሁ ታስባላችሁ Question ሌባ ግን መቀጣት ስላለበት ይልቁኑ ሳያመልጥ ማስረጃ ሰብስቦ ወደ ፍርድ ቤት መሄዱ ይሻላል እስካሁንም ተዘገየ

አንዳንድ ሰዎች ወደ ቄስ መራዊ እንክሰስ እያሉም ነው በጣም ያሳዝናል ዋናው ሌባ እሱ ያስቀመጣቸው እየሆነ ወደ እሱ ማመልከቱ አይታየንም ከላይ ስለሱ ታሪክ ዋርሶ የሚባል በመጠኑም ቢሆን ገልጾታል እስኪ አንብቡት

ይሄ ሌባ ቄስ የዘረፈውስ ገንዘብ ይሄ ብቻ ነው Question አገር ቤት ያከማቸው በዚህ ገንዘብ ብቻ አይመስለንም Cool ያም ሆነ ይህ ሌባ በየትኛውም ህግ መቀጣት አለበትና ዝም አንልም እሱን ብቻ ሳይሆን ከለላ ሆናችሁ ሰውን ግራ ስታጋቡ የኖራችሁም የመንደር ሴቶች እግዚአብሄር ይፈርድባችሁዋል ግልብጥ ሲሉ ግልብጥ ተሸፋፍኖ አይቀርም ለሁሉም ጊዜ ነው

እግዚአብሄር አይቸኩልም ግን ይፈርዳል እግዚአብሄር ይርዳን አሜን - ይቀጥላል
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሰዋሰው

አዲስ

Joined: 25 Nov 2003
Posts: 20

PostPosted: Thu Jan 13, 2011 10:57 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ወገኖቼ እንግዲህ መጽሐፉም ዝም ቄሱም ዝም እንዳይሆን ሌላ ገፅ ላይ ያገኘሁትን ላካፍላችሁ እናንተም እቤት ውስጥ ብቻ ከመናደድ ይመለከተናል የምትሉ ሰዎች እባካችሁ አስተያየቶችን እና ሀሳቦችን ወይንም ስለ ወንበዴው መስፍን /ማርያም (የሙኒኩ እያንጉዋለለ ) የቤተክርስቲያናችንን ገንዘብ የት እንዳደረሰው ፍንጭ የምታሳዉቁት ነገር ካለ እዚህ ላይ ወይንም ሌላ ዌብ ሳይት ላይ ፖስት አድርጉ ቤተ ክርስቲያናችን ከሌቦች መጽዳት አለባት ::
እኔ እያንጉዋለለ የምለዉ ያለ ምክንያት አይደለም ይህ ሰው እዚህ ቤተክርስቲያን ከሚመጡት ሴቶች ጋር ምናልባት ከሀይማኖታዊ ግንኙነት ዉጪ የሆነ ግንኙነት ያለዉ ስለሚመስለኝ ነው :: ምክንያቱም እንዲህ እይነት ጥፋት አጥፍቶ አሁንም ቤተ መቅደስን የሚደፍር ጨርሶ እንኩዋን ኦርቶዶክሳዊ ትህትና ሊኖረው ከሀገራችን ዱርዬዎች እንኩዋን የማይወዳደር አረመኔ ሰው መሆኑን ነው የሚያሳየዉ :: ስለዚህ ባሎች ሚስቶቻችሁን እስቲ መርመር አድርጉ ሁሉም ነገር ለበጎ ነው : እስቲ በምን ምክንያት ነው 165 ሽህ ኦይሮ የዘረፈን ሌባ አይዞህ አለሁልህ አይነት ይህን ያህል እሹሩሩ ..... ብላችሁ ጠይቁዋቸዉ ምናልባት መልስ ወይንም ምክንያቱን ሊነግሩዋችሁ ይችላሉ እንዲህ አይነት ነገር ግን ለመኖሩ እኔ ጥርጥር የለኝም :: ለዚህ ነው ሀገር ቤት ጠንቁዋይ ነኝ ብሎ ስድስት አመት በምድር ላይ ስለምኖር ከዛ በኁዋላ ሌላ እንደኔ አይነት ጎበዝ ጠንቁዋይ ስለማይኖር እያለ እንደሚወራዉ እንኩዋን ዝም ብሎ ባለ ትዳር ሴት ይቅርና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሚስት ሳይቀር ሞክሩዋል የሚባልለት እያንጉዋለለ ቄስ ንኝ ብለዉ የታቦት ገንዘብ ከሚዘርፉት ሌባ ጋር በጣም ተቀራራቢ ጸባይ ስለሚታይባቸዉ ነው እኔ ካሌለሁ ይህ ቤተክርስቲያን አይኖርም ምናምን አሁንማ ጭራሽ ያዉ ስብከቱን ማንም ከእንግዲህ ስለማይቀበል ቲፎዞ ቢሆንም , ከቅዳሴ ብሁዋላ ማሳረጊያ ዘራፍ ነው የቀረዉ እንጂ ፉከራ ሆኑዋል አሉ :: የሚገርመው ነገር በጣም ሀይማኖተኛ የሚመስሉት እስራቸዉ የሚያጨበጭቡት ሴቶችም ሌባዉ ቄስ የተጠቀሙበትን ጉዋንታቸዉን ወይንም ካኔተራቸዉ ለማስታወሻ ሳይጠይቁ አይቀሩም . እነዚህ ሴቶች ግን በጣም ነው የሚያሳዝኑት እስከ ዛሬ ቄስ ተብዬዉን ቃል ሳይሆን መልክ ብቻ እያዩ መኖራቸው ምን ያህል ተበድለዋል ወይንም ምናምን ቢጤ ቀባ አድርገዋቸዉ ይሆናል በዚህ ደግሞ ጎንደር ካህን የሚደርስበት የለም : ባለሙያ ነው :: ለማንኛዉም እያንጉዋለለን ቪዲዎ ይመልከቱት :: http://www.youtube.com/watch?v=UE7pucFPOJs
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሰዋሰው

አዲስ

Joined: 25 Nov 2003
Posts: 20

PostPosted: Thu Jan 13, 2011 11:12 pm    Post subject: Reply with quote

እየዘረፍኩኝ አሁንም ቄስ ነኝ መንፈሳዊ ለእግዚአብሔር የተገዛሁ ፈጣሪ አምላኬን የምፈራ አገልጋዩና ባርያው የእናንተን ኃጢአት ይቅር የማስብል መልእክተኛችሁ ነኝ የሚሉት ዱርዬ ሌባ አሸንፌያለሁ እኔ ገንዘብ አለመስረቄን በደንብ አስረድቻለሁ ከእንግዲህ ማንም ሊጠይቀኝ አይችልም እያሉ ይገኛሉ ስለዚህ ቤተክርስቲያናችንን ነጻ እናዉጣ ::
ለማንኛዉም ስለ አርእስቱ (ስለ ሌቦች ካህናት ) ከኢትዮ ሙኒክ ወይንም ቁዋጠሮ ላይ የተወሰደ ......

ቀድሼ እከፍላለሁ ወይስ ቦድሼ እከፍላለሁ ?
ከምእመናን አንዱ
የፈረንጆች ዓመት አልፎ በሌላ አዲስ ዓመት ተተክቷል። የሃገራችን ሰው ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም ይሉ ነበር
የፈረንጅ ሃገር ሰው ጉድ ሳይሰማ ጃንዋሪ አይገባም ቢል ደግሞ እንደኛው መስከረም ማለት ነው የፈረንጁ አዲሱ
ዓመት እንደኛ በሳቅ ያስጀምራችሁ ብዬ ልመርቃችሁ ?D በዚህ አዲስ ዓመት በእኛ ላይ የደረሰው ግን ምርቃት ሊሆን
አይችልም የእኛ ሳቅ የእውነት ምሬት ነውና ከዚህ ያውጣችሁ ብል ይሻላል።
ይህ የማቀርብላችሁ በጀርመን ውስጥ የሚገኙ የሦስት አብያተ ቤተክርስቲያናት ታሪክ ነው ብዙም መፃፍ አልችልም።
ከጅምሩ ስለማላውቀው የሚያውቁት በሚገባ እንደሚጽፉት አልጠራጠርም ለማንኛውም ይህንን ከዚህ በታች
የምጽፈውን የቅሌት መዝገብ ከፍቶ ለተመለከተው ምን ያህል እንደዘቀጥን የሚረዳው ይሆናል ።። ነገሩ እንዲህ ነው
ሦስቱ ቤተክርስትያኖች የሚገኙት
1.በኮለን ከተማ የሚገኘው የቅዱስ ሚካኤል በቄስ መራዊ የሚተዳደር
2. በፍራንክፈርት የምትገኘው የቅድስት ማርያም በአባ ሲራክ የሚተዳደርና
3, በሙኒክ ከተማ የሚገኘው የቅዱስ ገብርኤል በቄስ መስፍን የሚተዳደር ነው
እነዚህ ሦስተ ቤተ ክርስቲያኖች በወያኔው አባ ጳውሎስ ሥር የሚተዳደሩ ሲሆኑ ቄስ መራዊ የእነዚህ የበላይ ሆነው
ያገለግላሉ።
የአባ ጳውሎስ አስተዳደር ከሥር መሠረቱ የተበላሸ፣ በዚህም አስተዳደር ዙሪያ የተሰበሰቡትም የተበላሹ፣ እንደሆነ
ሲነገርው አልሰማም ያሉ ብዙ ምእመናን በእነዚህ ቤተ ክርስቲያኖች አካባቢ መሰባሰብ ከጀመሩ ሰንብቷል እነዚህ
ከላይ ስማቸው የተጠቀሰው ካህናት በሙሉ በአፍቅሮተ ነዋይ የተሞሉ ሲሆኑ በጀርመን ውስጥ ከምእመናን የሚገኘውን
ገቢ እንደፈለጉ የሚያዙበት የሚያደርጋቸው ማህበር (EintragenD Verein) ለማቋቋም የሚፈቅደውን ሕግ በመጠቀም
ነው
ነገሩ የተጀመረው ፍራንክፈርት ቅድስት ማርያም ቤተክርስትያን ነው የሰበካ ጉባዔ ምርጫ ሲደረግ የፍራክፈርቱ
ማርያም አስተዳዳሪ አባ ሲራክ አቶ አምሃ የሚባል ግለሰብ ካልተመረጠ ብለው አጥብቀው ይከራከራሉ ምእመናኖቹ
አይሆንም ቢሉም አቶ አምሃ በቄሱ ጥረት ይመረጣል ታዲያ አባ ሲራክ ተደስተው ስብሰባው ያልቃል አቶ አምሃ
ለካ ከቄሱ በላይ ማርያምን ይወድ ነበርና ማርያምን አላታልልም ብሎ ስራውን ይጀምራል ።የገንዘብ ቁጥጥር ይደርጋል
በዛ ያለ ገንዘብ እንደ ጠፋ ያውቃል ቄሱን ስለ ገንዘቡ ቢያነጋግራቸው ከወያኔ ጋር ባላቸው ፍቅር በትምክህት
በመሞላት ዞር በል ይሉታል ይህ የማርያም ልጅ ነኝ ብሎ የተነሳ ግለሰብ ለጀርመን መንግሥት ባለስልጣናት
ሁኔታውን ያጋልጣል አባ ሲራክም በትግሬነቴ ይህ ደረሰብኝ በማለት ቤተ ክርስቲያኑን በዘር ለመከፋፈል ጥረት
ያደርጋሉ።በቤተክርስትያኑ አካባቢ ያሉትን የትግራይ ተወላጆች ማሰባሰቡን ቢቀጥሉም መጀመሪያ አልተሳካላቸውም
ነበር። ወረቀቶች መበተን ሲጀምሩ ጉዱ ሁሉ አደባባይ ላይ ይዘረገፋል ቄሱ መውጫ መንገድ ሲያጡ የዘር ችግር
ለማድረግ ጥረታቸወን ይቀጥላሉ
የጀርመን በአባ ጳውሎስ ሥር ያሉ ቤተክርሰቲያኖች ሃላፊ የከለኑ ቄስ መራዊ ይህ ሁኔታ ሰላላማራቸው ምንአልባትም
ተዛምቶ እሳቸው በሚመራው ቤተክርስቲያን ውስጥም እንዲህ ዓይነት ችግር ከተፈጠረ የሚያደርሰውን አደጋ
በማስተዋል ለማስታረቅ በአደባባይ ሲጥሩ በውስጥም በኩል ደግሞ ይህንን ጉዳይ ያጋለጠውን አቶ አምሃን ለመጉዳት
ሴራ ይጀምራሉ
ይህ ቁጥጥሩን አድርጎ የገንዘብ ጉድለቱን ያገኘው ግለሰብ ቤተክርስቲያኑ አካባቢ እንዳይደርስ (በጀርመንኛ
Houseverbot) በጠበቃ ይታዘዛል የደረሰው ደብዳቤ እንደሚጠቅሰው አቶ አመሃ ቤተክርስቲያኑ አካባቢ ቢደርስ
ለሚደርስው ችግር ተጠያቂ እንደሚሆን ነው ወያኔዎቹ ይህንን ደብዳቤ ከደረሰው በኋላ ቤተክርስቲያኑ አካባቢ
ቢደርስ ብጥብጥ ለማስነሳት ዝግጅት ላይ እንደነበሩ በፍራንክፈርት ከተማ የተወራ ሲሆን አቶ አምሃም በግል
የሚደርስበትን ችግር በመረዳትና የጀርመን ሕግ ነውና ወደዛ መሄዱን ያቆማል አባ ሲራክም አንዳንድ የትግራይ
ልጆችን በማሳመን ነገሩ እንዲቀዘቅዝ ይደርጋሉ ውስጥ ውስጡን ግን የጀርመን ሕግን ጥሰዋልና በአባ ሲራክ ላይ
ምርመራው መቀጠሉ አይቀርም በነገራችን ላይ አባ ሲራክ የመኖሪያ ፈቃዳቸውን ያገኙት የፖለቲካ ስደተኛ ሆነው
ሲሆን የጀርመን መንግሥት የሚከለክለውን ሕግ ጥሰው በየወቅቱ ወደ ኢትዮጵያ በዚ |ያውም የአባ ጳውሎስን እጅ
ለመንሳት አሁንም ይመላለሳሉ
በፍራንክፈርት የተጀመረው ጉድ ሌሎችንም ማነቃቃት ይጀምራል በሙኒክ ገብርኤል ቤተክርሰረቲያን መሪ በቄስ
መስፍን ላይ ቁጥጥር ይጀመርና መቶ ስድሳ አምስት ሺህ ኤሮ (165000)D ለቤተክርስቲያን ማሠሪያ የተዋጣ ገንዘብ
መጎደሉ ይደረስበታል ስብሰባ ተደርጎ ቄሱ የት እንዳደረሱት ሲጠየቁ ሂሳብ ስለማልችል ጎደለብኝ ብለው ያሳብባሉ
ሕዝብ በተሰበሰበበት በትምክህት፣ምን ይመጣብኛል በማለት የጎደለውን ገንዘብ አምነው ይቅርታ ይደረግልኝና ቀድሼ
እከፍላለሁ ብለው ሃሳብ ያቀርባሉ
የእሳቸው መስረቅ አልገረመም። ገና ቁጥጥሩ ሳይጀምር በሙኒክ ከተማ ቄስ መስፍን አዲስ አበባ ውስጥ ቤት ከነ ዋና
ቦታው እያሰሩ መሆኑን ያልሰማ አልነበረም ጥርጥሩም ቁጥጥሩም የተጀመረው ከዚያ በኋላ ነው በጣም
የሚገርመው ቄስ መራዊ የከለኑ ሚካኤልና የጀርመን በወያኔ ሥር የሚተዳደሩ ቤተክርስትያናት አላፊ የሕዝብ ገንዘብ
ከማስመለስ ወይም ከማጋለጥ ይልቅ ከቄሱ ጎን በመቆም አጥብቀው ምህረት ሲጠይቁ መታያታቸው ነው
"ምእመናን መሃሪ ናቸውና ምሕረት አድርጉ " ብለው ሰበኩ ሁኔታው ነገ በእሳቸው ላይ የሚመጣውን በማሰብ
ዛሬውኑ ብልሃት እንደዘየዱ በሆናቸውን ምእመናኑ ገብቷቸዋል ለነገሩ ነው እንጂ የከለኑ ቢመረመር ስንት እንደሚሆን
መገመት ያዳግታል ?Dቄስ መራዊ በዚህ በዘረፋ ልምድ እንዳላቸው ማንም የሚያውቀው ሐቅ ነው
ይህ የሙኒኩ የዘረፋ ተግባር እንደተሰማ ከሁሉ የሚገርመውና የሚያስቀው የፍራንክፈርቱ አባ ሲራክ እኔ ያጎደልኩት
አስር ሺህ ብር ያነሰ ሲሆን ቄስ መስፍን አማራ ስለሆነ ይህንን ሁሉ ሲጎድልበት ምንም አልተባለም በእኔ ላይ
የጠነከረው ትግሬ ስለሆንኩ ነው ብለው ሰዎች ሰብስበው ሲያማርሩ ነበር ተብሎ ፍራንክፈርት ውስጥ ተወራ ጉድ
ሳይሰማ ማለት ይሄኔ ነው
በአሁኑ ወቅት የሕዝብ ገንዘብ ተበልቶ መቅረት የለበትም የሚሉ ብዙ መእምናን እንዳሉ የሚታወቅ ነው ጉዳዩ ወደ
ፍርድ ቤትም መቅረብ እንዳለበት ሕዝቡ ያምናልም፣ ይፈልጋልም የወያኔ ደጋፊዎችና ቄስ መራዊ በዝምታ ምንም
እርምጃ ሳይወሰድ እንዲያልፍ ይፈልጋሉ ዛሬ ለእውነት እንዲሠሩ የተመረጡት ኮሚቴዎች ይህንን የሕዝብ ገንዘብ
የማስመለስ ሃላፊነት አለባቸው በይሉንታና በፍርሃት ካለፉት ግን ከዘራፊው ቄስ መስፍን ወይም ከተባባሪው ከቄስ
መራዊ የማይሻሉ ሆነው ነው የሚቀሩት ታሪክ ጭራ ነውና ለእውነት መቆም ዛሬውኑ አስፈላጊ ነው
ዛሬ በጀርመን የአባ ጳውሎስ ተወካዮች ዘረፋውን በሰፊው ተያይዘውታል ካለአንዳች ተጠያቂነት ምእመናን በተለይም
በሙኒክ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአካባቢው ከሚደርስባቸው ዘረኝነት ጋር ተዋግተው ሽንት ቤት ጠርገው
የጉልበት ሥራ ሠርተው ወገባቸው ተበጥሶ፣ በሽተኛ እየሆኑ (D ይህንን እያንዳንዱ የጀርመን ነዋሪ የሚውቀው ነው )D
መጽናኛ ይሆነናል ብለው፣ ሊያሰሩት ላሰቡት ቤተክርስቲያን ይውላል ብለው የሰበሰቡት ገንዘብ እንዲህ በቀን ጅብ
ሲበላ ምንኛ እኛነታችን ያስጠላናል ?Dበአንድ የእግዚሐብሄር አገልጋይ ነኝ በሚል ካህን ይህንን ያህል ግፍ በሃገሩ ሰዎች
ላይ ሲያደርስስ ምን ይሰማው ?Dየዚህስ ካሃን የወደፊት ሕይወት ምን ትመስል ?Dይህንን ኃጢያት በግፍ በተወሰደ ገንዘብ
የተሠራ የዋና ቦታ ያፀዳው ይሆን ?Dበዘር የሚከፋፍልስ ከሃን እንዴት ሆኖ የቤተክርስትያን አገልጋይ ይሆን ?D
ውድ ምእመናን
እነዚህ የተደራጁ ዘራፊዎች ብቻ አይደሉም ጥፋተኞች ምእመናንም ቢሆኑ ይህንን ልቅ የሆነ ዝርፊያ ስንፈቅድ ጥፋቱ
ከኛም ነው ።ከበርካታ መእመናን የሚዋጣ ገንዘብ በአንድ ካህን እጅ ያለ ጥንቃቄ እንዲወጣ ለምን እንፈቅዳለን ?Dችግሩ
ከመድረሱ በፊት ለምን መ፣ፍትሄ አንፈልግም ?DDእነዚህ ካህናት በልዩ ልዩ ዘዴ እየከፋፈሉን እንገኛለን። ከአሁን በኋላ
በሌብነት እጁ ከቆሸሸ ቄስ መስቀልን መሳለም እንዴት ይቻለን ይሆን ?Dቀድሶ ነው ወይስ እንደለመደው ከሕዝብ ገንዘብ
ቦድሶ ነው የሚከፍለው ?
ክቡራን የጀርመን ድምጽ ራዲዩ አዘጋጆች
ሕዝብ እውነትን የማወቅ መብት አለው ጋዜጠኞች ደግሞ የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው እንዚህን ካህናት የኮሚቴ
አባላት ቃለ መጠይቅ በመጠየቅ እውነትን ሕዝብ እንዲረዳው ያስፈልጋል በጀርመን ሃገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን
ለጀርመን መንግሥት የሚከፍሉት ቀረጥ ለዚህ ቀን እንኳ ሊረዳቸው ይገባል አለበለዚያ ግን የጋዜጠኝነት ግዴታችሁን
እንዳልተወጣችሁ በዚህ ኃጢያት ውስጥ በተዘዋዋሪም እንደገባችሁበት ልትገነዘቡት ይገባል
ከሁሉ የሚገርመኝ እኛ ኢትዮጰያውያን ምን ነካን ?D ቅስና ሳይኖራቸው ቆብ በጫኑ ወንበዴዎች ስንዘረፍ ለመቃወም
ምነው ፈራን ?D አደባባይ ላይ አባ ሲራክ አማራን ሲዘልፉ ምነው ፍርሃት ዋጠን ?D ቄስ መራዊ በድብቅ ከወያኔ ጋር
ሲደራደር እያወቅን በገንዘብ ስንረዳ አልነበረም ?Dቤተክርስቲያን ማሠሪያ ገንዘብ ሲዘረፍ አያገባንም ማለት ምንድነው ?D
በእንደዚህ አይነት ዘራፊዎች የተመሠረተ ቤተክርሲቲያን ነው ብለን መቀበል ምንድነው ?D
እግዚአብሔር ከእንደዚህ ዓይነት ካህናት ይሠውር
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ስማያት

ኮትኳች

Joined: 18 Aug 2009
Posts: 103

PostPosted: Fri Jan 14, 2011 2:52 am    Post subject: Reply with quote

የባሕል አባዜ ሆኖብን እክሎች ላይ እናተኩራለን , ከዚያም አንዳችም የማስተካከያ መፍትሄ ሳናቀርብ ወይንም የመፍትሄውን ትግበራ ለሌሎች ሰይመን እናልፋለን :: ይኽ እንደ ነቀርሳ የተጠናወተን ባሕላዊ እንከን ነው ::

በኔ አስተሳሰብ ለሁሉም እክል ወይንም ሳንካ መፍትሄ አለው :: አንዳንዱ መፍትሄ ዝየዳዊ መላዎችን ይሻል , አንዳንዱ ደግሞ ወትሮ የተደነገጉ ተግባራዊ ድንጋጌዎችን ወይም ልምዶችን ማስፈን ይሻል ::

በኔ አስተያየት እያንዳንዱ ደብር ወይንም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ስብስብ በወረት ድንቅ ሆኖ ይጀምርና ከጊዜ በኍላ በድርጊትም ሆነ በመንፈስ እየነቀዘ ሄዶ ኍላ እድምተኞችን በሙሉ አስከፍቶ ይፈራርሳል :: ይህ እንዲሆን መንገድ የሚከፍቱ የጋራ የሆኑ ባህላዊ የአሰራር ልምዶች አሉብን :: ለምሳሌ

- አስተዳዳሪ አካል መርጦ የዚያን አስተዳደር አባላት አሰራር ጥራት ላይ ቁጥጥር አለማድረግ

- የሥነ -ምግባር መስፈርቶች አለመንኖር በተለይ የአስተዳደር አባላትን በተመለከተ :: ቢኖሩም በሥራ ላይ አለማዋል :: የአስተዳደር አባላትን ብልግና አይቶ እንዳላዩ ማለፍ

- ገንዘብ አዋጥቶ ገንዘብ ምን ላይ እንደዋለ አለመጠየቅ

- / እየመጡ አስቀድሶ እና ጠበል ጠዲቅ ቀምሶ ብቻ መሄድ

- ችግር ሲኖር በቀላሉ ተወያይቶ እንደመቅጨት ሥር -ሥሩን በሚሄድ አሉባልታ ጎልቶና ገዝፎ እንዲነቅዝ ማድረግ

- እንደ አንድ ማህረሰብ ሳይሆን ተከፋፍሎ በወገን በቤተሰብና በጋብቻ ረገድ ተወስኖ ጎጠሰብ መሆን

- ይህ ሁሉ አስተዳደር ላይ ያሉ ሰዎች ተስተዳደሩን እንዲንቁ , እንዲዳፈሩ , በእብሪትና በጥላቻ ሞገደኝነት እንዲዋጡ ያደርጋቸዋል :: ይህ ሁኔታ ማንኛውንም ካጀማመሩ በጎ አሳቢ ሰው ወደ ብልግና እና ሌብነት እዲያመራ ይገፋፋል ::

----------------- መፍትሄው

- አስተዳደሩ ተግባራዊ በሆነ ስልሰ -ጊዜ ስብሰባውን ከእድምተኛው ፊት ማድረግ

- የእድምተኛውን ጥያቄዎች መመለስ , አስተያየቶችን አዳምጦ , ተግባራዊ የሚሆኑት ለመፈጸም የጊዜ ጽልመትና ተግባሪ ሰይሞ , ሂደቱን ለእድምተኛዊ ማቅረብ

- የማስተካከያም ሆነ የመተካኪያ እጀታዎችን በአሰራሩ ደምብ ውስጥ ማስረጽ

- ምእመኑም ይሁን እድምተኛው በጎጥ ክልል እንዳይወሰን ከዚሁም ጋር ተያይዝዞ በጉባኤም ግዜ ሆነ በሌላ ግዜ የህብረቱን መሻሻያ መንገዶች እንዲያብላላ ርእስ እየሰጡ , በጎጥ ሳይሆነ እርስ -በርስ ቀላቅሎ በጠረጴዛ ዙሪያ አስቀምጦ የውይይት መድረክ መፍጠር ::

- ብዙውን ጊዜ አጥፊዎች አሉባልታን እንደ መሳሪያ ይጠቀሙበታል :: አሉባልታ ደግሞ እጅግ ፍቱን የጥፋት መሳሪያ ሊሆን ይችላል :: አሉባልታን መቅረፍ የሚቻለው ደግሞ የግልጥነትን ልምድ በማስፈን ነው ::

- ነገሩን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ / ውስጥ ስናየው ይኸው ችግር ይገኛል :: /ክርስቲያኒቱ እንደመተዳደሪያ ደምብ በተጠና እና በተማከለ ሁኔታ ከላይ እንጻፍኳቸው ነጥቦች የተሰፈሩ የአስተዳደር ድንጋጌዎችን በማሰራጨት , ህግጋቱ መተግበራቸውን መቆጣጠር የምትችልበት መንገድ ሊፈለግላት ይችላል ::

-------

ምናልባት ሀሳቤ አለመኝነት ያዘለ ጉዳዮችን አልጋ ባልጋ አርጎ የሚያይ ይሆናል ነገር ግን የአስተሳሰባችንና የውይይታችን ቅዝምዝም , በማንኛውም ርዕስ , ዝየዳዊ ምፍትሄዎችን በማግኝትና በመተግበር መስመር ላይ ቢሄድ ደስ ይለኛል ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሰዋሰው

አዲስ

Joined: 25 Nov 2003
Posts: 20

PostPosted: Fri Jan 14, 2011 5:28 am    Post subject: Reply with quote

ሰማያት ስለ አስተያየት አመሰግናለሁ
ሌላዉን ቦታ ጉዳይ ባላዉቅም እዚህ አካባቢ እንደሆነ ከእንግዲህ ወዲህ በህግ የሚፈጸም ጉዳይ ብቻ ነው በትንሹ 165 ሽህ ኦይሮ በእኛ አመለካከት ደግሞ ወደ 300 ሽህ የሚጠጋ ብር ነው እኚህ ሰዉ ከቤተክርስቲያናችን የዘረፉት ስለዚህ እንዲህ አይነት ሌባ ነገ ታቦት ይሸጣል . ስለዚህ እርስዎ ላሉት መፍትሔዉ ጀርመን ሕግ ነው ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሕግማ እንደሌለ ይቁጠሩት ህግማ ቢኖር ሌባ ሌባው ወደ እስር ቤት ወይም ክህነቱን ይነፈጋል :: እስቲ ስንቶቹ ናቸው የቤተክርስቲያን ገንዘብ ዘረፉ የሚባሉት ? ምነዉ አንዱም ታሰረ ወይንም ክህነቱን ተነጠቀ ሲባል አልሰማንም ? እዚህ ላይ ደግሞ ስለመጻፉ አሉባልታ አለመሆኑን ይረዱት እዚህ ላይ መጻፉ የሚጠቅመው ሁሉም ሰዉ ስለ ሰዉየዉ ግንዛቤ እንዲኖረዉና የሚያዉቀዉም ነገር ካለ እንዲያሳዉቀን እና በተጨባጭ መረጃ (እዚህ ያሉት ሌባ እያንጉዋለለ አምነዋል ) ወደ ጀርመን ማረፊያ ቤታቸዉ ለመሸኘት ነው :: ሌላው እዚህ ላይ የሚጻፍ ነገር እሳቸዉን የሚያዋርድና ስራቸዉን የሚያጋልጥ እንጂ ለርሳቸዉ መጠቀሚያ በምንም አይነት መንገድ ሊሆን አይችልም :: ምክንያቱም ሌባ ለመሆናቸዉ ኮለኑ መርአዊ ባሉበት አምነዋል ሌባን ደግሞ ሌባ ካላሉት እኛኑ ሌባ ነው የሚለን :: እኔ እዚህ ላይ አስተያየት ወይንም የምታዉቁትን ነገር ጻፉ ስል ጉዳዩ ምንም ሳይደረግ ችላ ተብሎ አይደለም ግድየለም በሂደት ላይ ነው ነገር ግን 20 አመት ሙሉ ድራሹ የጠፋዉ ሰነድ በደንብ ተስተካክሎ ነው ወደ ፍርድ ቤት መቅረብ ያለበት :: የሚያናድደዉ ጉዳይ እስከሚጣራ እየተባለ እስከዚያ ድረስ ቤተመቅደሳችን በሌባ ስትረክስ ያናድዳል ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ምንቸቱ

መንገደኛ

Joined: 26 Jan 2011
Posts: 2

PostPosted: Wed Jan 26, 2011 6:14 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ወገኖች

ይገርማል መቼም የኝህ ደፋር ቄስ ነገር በጀርመን አገር ህግ ተፍቶ ሳይሆን ደህና ተንካራ ሰው ጠፍቶ ነው በሕዝቡ ላይ የቀለዱት በተለይ ባለፈው ወንዱንም ሴቱንም ሲያንቀጠቅጡት እኔ ቄስ መስፍን እያሉ ምን ታመጣላችሁ አይነት ሲደነፉ ሰውን ረጭ ነው ያደረጉት እኝህ ካድሬ ቄስ በሰረቁት ገንዘብ የልባቸውን አድርሰዋል .... አሁንም ማስረጃ ከሌለ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም ሽምጥጥ አድርገው የሚክዱ ደፋር ናቸው በጣም የሚያሳፍረው አብዛኛው ምእመናን ማለት ይቻላል በራሳቸው የማይተማመኑ ሾካካ ብቻ ነው የተሰበሰበው ከቄሱ ተጣልተን ወዴት እንሄዳን አይነት ሹክክክክ በተለይ አዋተን እንከፍልላቸዋለን የሚሉት ወሬ በቁናዎች ለእያንዳዱ ሰው 500euro ለዚህ ሁሉ ሰው ሊመልሱ መቀባጠራቸው ማደናገሪያና ሰውን ወደ እነሱ ለመሳብ የሚያደርጉት ዘዴ ነው እናውቃቸዋለን እንደለመዱት በዛ በውሸታም ምላሳቸው ሰውን አግባብተው ከዛም ሰውም ልብ የሌለው ነው እየተጎተተ እየሄደ እንደገና እንጀምር በአዲስ ብለው ሊነሱ ነው ያው ሌባውን ቄስ እያጀቡ አምላክን ሳይሆን የሚያመልኩት ሌባውን እያመለኩ ለጥቅማቸው ሲሉ መኖር ነው እነሱ ካዋጡት በላይ ስለ ተጠቀሙ ለነሱ ምንም አይመስላቸውም .....

በተለይ / መቅደስ ደጉ እና መሳዮቾዋ እንጀራዋን ወሽቃ እየሮጠች አጥንት በሌለው ምላሶዋ ከቄሱ ሚስት ሰውን የምትገል አዋጡ የማይሰለቻት የስዋ ቢጤዎቾዋን እያሰባሰበች ሰው ላይ ተንኮል የምትሸርብ ይህው ቤተክርስቲያኑ ከተቁዋቁዋመ ጀምሮ ወሬና አሉባልታ የእጀ መንሻ ይዛ የምትቀርብ በግልጥ እኔ ከቄሱ ሞት ነው የሚለየኝ በላ የተናገረች ሀይማኖቱዋን ሳይሆን ቄሱን የምታመልክ ለጥቅም የተገዛች አሮጊት እና መሳዮቾዋ ናቸው ቄሱን ለዚህ ያደረሱዋቸው ለምን እዚህ ሙኒክ ውስጥ ሌላ ቤተክርስቲያን ይቆቆማል ብለው ሄደን እንስደባቸው ያሉ ምላሳሞች ናቸው ጥቅም እንዳበደ ውሻ ያክለፈልፋቸዋል

ተሰብስበው ስለ ሰው ማውራት የማይሰለቻቸው እግዚአብሃር ይቅር ይበላችሁ የሚያወሩት ሁሉ የሚዘገንን ያቺ ቆማ ቀረች .. እከሊት እስላም .. አገባች እከሌም እስላም አገባ እንዳቦኩ ይህው እግዚአብሄር ሲያሳያቸው የቄሱ ልጅ ያውም ዲያቆኑ እስላም አስረግዞላቸው ቁጭ አለ አሳያቸው ቆማ ቀረች እንዳልባል እየተባለም በመከራ በሰው ብርታት ባልም አገር ቤት እይጎተቱ መጋባትም ጀምረዋል ብቻ እያሳየን ነው የገብኤል የተዋጣ ገንዘብ በልታችሁ ገና ብዙ ያሳየናል ::

ታቦት ጽላት አቁመው አዋጡ እያሉ የሰበሰቡት እንኩዋን የትና የት እግዚኦ ለጤናም አይሆንላችሁ : Embarassed
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 811

PostPosted: Wed Jan 26, 2011 8:14 pm    Post subject: Reply with quote

ይሕን አጀንዳ ይዞ ወደመድረክ የመጣው በራሱ ችግር አለበት ::
ተከራካሮውች ሆይ ! አንድ ነገር እወቁ :: ባሁኑ ጊዜ ወረኛው በጣም ብዙ ነው :: ሁሉም ሰው እጅና እግሩ ሳይቀር ተቀይሮ አፍ የሆነበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው :: እና : አንድ ነገር ስለአንድ ሰው ስትጽፉ : የሚያነበው ሰው " ምን አይነት መጥፎ ቄስ ናቸው ?" ይላል ብላቹ አትጠብቁ :: ባንድ በኩል የተጻፈው ሙሉ ለሙሉ ውሸትና እንዲያውም የእውነቱ ተቃራኒ ሊሆን ይችላል ብሎ ያምናል :: ስለዚህ በግማሽ ልብ ነው የሚያነባቹ :: እና የምትቃወሙዋቸውን ሰውዬ ራሳችሁ ኮንፍሮንት ካላደርጋቹ በቀር በከንቱ መቸክቸክ ይሆናል እጣ ፈንታችሁ ::

ልምከራቹ ብዬ ነው :: ታላቃቹ እሆናለሁ መቼ M. Wink
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሰዋሰው

አዲስ

Joined: 25 Nov 2003
Posts: 20

PostPosted: Sat Jan 29, 2011 4:46 am    Post subject: Reply with quote

ምነው ጌታዬ እንዴት ሆኖ ነው ዉሸት ነው የሚባለዉ ? እሳቸዉ ያመኑትን ገንዘብ እርስዎ ሊዋሹላቸዉ ነው ?? ወይንስ እራስዎ ሌባው ነዎት የሚጽፉት ? መቼም እርስዎ የሚሣኖት ነገር የለም ሲፈልጉ ፓልቶክ ስፈልጉ ኢቲቪ ሲፈልጉ ዋልታ አንዳንድ ጊዜም አይጋ ፎረም ላይ ነው የሚያዘወትሩት ይባላል ስለዚህ ዋርካም እሩቅ አይደለችም ሃይማኖታዊዉን ትምህርት ግብጽ ሀገር ጨርሰዉ ስለመጡ ጀርመን ላለዉ ምእመን ከበቂ በላይ ኖት በተለይ ሙኒክ ላለነው ብዙ እዉቀት ያለዉ ሰው ምንም ስለሌለ ተማርኩ የሚለዉም ወይ ቼክ ወይ ራሺያ ስለሆነ እንደ አዋቂ መቁጠር አያስፈልግም እርሶም ዉዳሴማርያም የእለት መድገም አያስፈልጎትም ::
ለመሆኑ ምንድነው የሚጠብቁት ? መልቀቂያ መጥቶልዎት የለም እንዴ ? ግድ ቤተክርስቲያን ዉስጥ እንዴት ይገብባል ነዉር አይደለም ? ወይንስ ታቦቱንም ሰርቀዉ ለመሄድ እየተመቻቹ ነው ?? ይሄስ ንቀትዎት እስከ መቼ ድረስ ነው ? ሰዉ ቤተክርስቲያን አሁንም ቢመጣ እኮ እርስዎን ደግፎ የመጣ አድርገዉ የሚመጻደቁት ለምንድነው ? ጌታዬ ይሄ የሙኒክ ኢትዮጵያውያን ወይንም ጀርመን ዉስጥ ያለን ኢትዮጵያዉያን ጉዳይ ብቻ አይደለም ከላይ የጻፉት ሰው እዉነት የኦርቶዶክስ ወዳጅ ከሆኑ የሁሉም ዓለም ላይ ተበትኖ የሚኖረዉን ጨምሮ ሀገራችን ያለውን ሕዝብ ኦርቶዶክስ አማኝን ሁሉ ይመለከታል ማንም ሰዉ ከመሬት ተነስቶ ማንንም መወንጀል መብቱም የለዉም የሚያረካዉም ነገር በዚህ ምክንያት አይኖርም የተትረፈረፈ ጊዜም የለም የራስ ህይዎት ሩጫ ናት ሌላዉ ደግሞ እግዚአብሔር ፈቅዶልን በነጻነት ነጻ ሜዲያ ተጠቅመን ስለሃይማኖታችን ወይንም ስለ ሀገራችን ወይንም ስለ ችግራችን እዚህ መጻፉ እኮ ታዋቂ ለመሆን ወይንም ሽልማት ለማግኘት አይደለም ምነው ዋርካ ፖለቲካ የሚለዉን ይንኩት እስቲ ስንት የማይረባ ነገር ይጻፍ የለም እንዴ ስለዚህ እዚህ ላይ መቸክቸኩ ችግር የሚያመጣ አይመስለኝም እንደዉም ሌባው ምናልባት ከወያኔ ጋር ባላቸዉ ግንኙነት ክዚህ እንኩዋን ተነስተዉ (ማን ያዉቃል ? ፈሪሃ እግዚአብሔር እንደሁ እነርሱ ጋር የለም ) ወደ ካናዳ ወይንም አሜሪካ አዉስትራሊያ ቢልኩዋቸዉ እዛ ያሉት ኦርቶዶክስ ተከታዮች ስለሚመጣባቸዉ ሌባ ቀድመዉ ያዉቃሉ ማለት ነው :: እና ይሄ መጥፎ ነገር አይደለም እንደዉም ይልመድብን የሚያስብል ነዉ ::
ምናልባት ግን ምን ተጠራጠርኩ መሰለዎት ከብዙ ሰዎች ጋር አልፎ አልፎ ስወያይ በተለይ ከእነዚህ ከዘመኑ ሰዎች ጋር ስነጋገር መስቀለኛ አነጋገር እየሰማሁ ነው ወደ ቤተክርስቲያንም ድሮ የሌሉ አዳዲስ ፊቶች (ምናልባት መስሎኝ ይሆናል ) ግን ብቅ ብቅ እያሉ ነው እኛ ስናምጽ እነርሱ ሊወርሱ ይመስላል የቄስ መስፍን የእስከዛሬዉ ዘዴ ይሄዉ ነበር ወይ በዘር ወይ ፖለቲካ ሰዉን እያናቆሩ ቤተክርስቲያን ገንዘብ መዝረፍ ::
ሌላዉ ደስ የማይለዉ ነገር ግን ዝም ብሎ እዚህ አርእስቱ ጋር የማይሄድ የግል ጥል አምጥቶ ስድብ መጻፍ እዉነት ያስጠላል በጣምም ያስንቃል ስለዚህ እንዲህ አይነት ነገር ይቁም :: እንዲህ አይነት ነገር የባሰ እኛን መጠቀሚያ እንድንሆን ነው የሚያደርገዉ :: ስዉየዉም እንዲህ አይነቱን ነገር ይፈልጉታል ቤተ መቅደስ ቆመው ዋርካ ላይ እንዴት እንደሚሰዳደቡ አይታችሁዋል እያሉ ነው የሚቀልዱት :: ስለዚህ የእራሳችንን ስሜት እንተወዉ እና በመጀመርያ ቤተክርስቲያናችን ነጻ ትዉጣ ::
መድኃኔአለም ለሀገራችን ሰላም ለእኛም ብርታቱንና ጤንነት ይስጠን ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሰዋሰው

አዲስ

Joined: 25 Nov 2003
Posts: 20

PostPosted: Thu Feb 10, 2011 4:20 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም የክርስቶስ ቤተሰቦች እንግዲህ ምናልባት ያልሰማችሁ ካላችሁ ቄስ መስፍንን ጉዳይ እልባት ለመስጠት ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ /ክርስትያን የአዉሮፓው ጳጳስ ስለሚመጡ እና አጠቃላይ ስብሰባ ስለሚደረግ ቅዳሜ 12/02/2011 ቀኑ 14:00 ላይ በሙኒክ እና አካባቢዉ የምትኖሩ ኢትዮጵያዉያን በሰዓቱ /ክርስቲያኑ አዳራሽ ዉስጥ እንድትገኙ በቅዱስ ገብርኤል ስም ተጋብዛችሁዋል ::
እባካችሁ ላልሰሙት ጉዋደኞቻችሁ በዚህ ቀን እንዲመጡ መልእክት አስተላልፉ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7  Next
Page 2 of 7

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia