WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home | About us | Advertise with us | Contact us
__________///__________
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ዉቃው

ዋና ኮትኳች

Joined: 07 Jan 2007
Posts: 970

PostPosted: Sat Mar 20, 2010 7:43 pm    Post subject: Reply with quote

እኔ ደደብ ነኝ !

4 ክፍል ..ጥንት

የሙዚቃ መምህራችን ቲቸር ዘውዱ ..በጦር ሠራዊት ውስጥ ትራምፔት ተጫዋችና ሙዚቀኛ ነበሩ :: አለባበሳቸው ቀጥ ጽድት ያለና ..በካዥዋል ድሬስ ቆፍጣና ወታደር ....ምናልባት ያኔ በግምት 50ዎቹ ዕድሜ አጋማሽ ነበሩ :: ልጃቸውም (አንድ ሁለት ክፍል ከኛ ያንስ የነበረ ) ሁሉ ነገሩ እንዳባቱ እንደነበር ትዝ ይለኛል :: የሚለውን የሙዚቃ ..ከነ ቁልፎቹ ..የነ ሞዛርትን ሃይደንን ሾፕንን ታሪክ የተረኩልን እሳቸው ነበሩ :: በሳቸው ክፍለ ጊዜ ትምህርት እየሰጡ ንቅንቅ ማለት የለም :: ዝምብ አፍህ ወስጥ እንኳ ብትገባ !

አንድ ቀን ...አፍሪቃ አፍሪቃ የሚለውን እና በነርሲስ ናልባልዲያን ለአፍሪቃ ህብረት ምስርታ የተዘመረውን የክፍሉ በሶስት ቦታ ተከፍሎ ያጠናል ::

አፍሪቃ አፍሪቃ
አፍሪቃ ሐገራችን

አፍሪቃ ሀገራችን
አለች ነቃ ነቃ
የአፍሪቃዊ ህብረት
ልማት ነው ለአፍሪቃ

አፍሪቃ አፍሪቃ ....

እየዘመርኩ ሳለ ...ውጪ በመስኮት አሻግሬ ... ተማሪዎች በስፖርት ክፍለጊዜው ኳስ ሲጫወቱ አያለሁ :: መዘምሩን ባላቆምም ...ዓይኔ ግን እየሰረቀ ወደውጪ መመልከቱን አላቆመም :: እጄን እንዳጣመርኩ ..በመዝሙሩ መሃከል ዓይኔ ሳላዘው ወደውጭ ቀስ ብሎ ይሄዳል ::

" ውጣ !!!" እንደብራቅ የጮኸ የቲቸር ዘውዱ ድምጽ በህብረ -ዜማው መሀከል የክፍሉን አስደነገጠ :: ማንን እንደሆነ ለማወቅ ማን ይቻለዋል ?!
መጥተው ኮሌታዬን በመጨምደድ እያንገላቱ ወደ ጥቁር ስሌዳው አካባቢ ወሰዱኝ :: ተማሪዎቹ ፊት እንድቆም አረጉኝና ቀሰ ብለው ቀበቶዋቸውን እየፈቱ " በል የምልህን መልሰህ በል " አሉኝ :: "ስምህ ማነው ? " ነገርኳቸው ::

"እኔ ዉቃው ...ደደብ ነኝ " እሳቸው የሚሉትን እደግማለሁ ..ለተማሪዎች ::
" የማልርባ አህያ ደደብ ነኝ :: "እንደገና

እንደገና አሁንም .... ደግሞ እንደገና ሶስት አራቴ " እኔ ዉቃው ..የማልረባ ... ደደብ .... የማይገባኝ አህያ ነኝ " እያልኩ ለክፍሉ ተማሪዎች ቃሌን በተደጋጋሚ ሰጠሁ ::

"በል ሱሪህ አውልቅና አጎንብስ ::" እሳቸውም ገረፉኝ ... እስኪበቃቸው :: እየተብስከስኩ ወደመቀመጫዬ ተመለስኩ :: ዝማሬው ቀጠለ :: በቡሃ ላይ ቆርቆር እንዲሉ ዕረፈት ሲወጣ ... ያየኝ የክፍሉ ተማሪ ሁሉ ..."እኔ ደደብ ነኝ " እያለ ይጠራኝ ጀመር :: በመጀመሪያው ብናደደም ...ያየኝ ሁሉ እኔ ደደብ ነኝ ሲለኝ በቆይታ ብዛት ለመድኩት :: ቲቸር ዘውዱን ግን የመጨረሻ ጠላኋቸው :: ዓመቱም አልቆ ../ቤቱ ለክረምት ዕረፈት ተዘጋ :: መስከረም 3 5 ክፍል ስንመጣ የመጀመሪያው ነገር የቲቸር ዘውዱ መሞት በድምጽ ማጉያ መነገሩ ነበር :: የልጅነት ቂም እጅጉን ቋጥሬ ለነበርኩት ..ግን የሞት ምንነቱ ለማይገባኝ ለኔው ....ያኔ ተሰምቶኝ የነበረውን ደስታ መግለጽ ያቅተኛል :: እኔን ስለገረፉ ..በተማሪም መዘባበቻ ስላደርጉኝ እግዜር እንደገደላቸው እርግጠኛ ነበረኩ ::

ብዙ ዓመታት አለፉ :: ...ኋላ አድጌ ለአፍሪቃ ህብረት ምስረታ የተዘመረውን ኦሪጅናሉን መዝሙር በሰማሁ ጊዜ ...ደደብነቴን አረጋጥኩ :: ቲቸር ዘውዱ ...1 ክፍል ጀምረው ..የሙዚቃ ሁን አስቆጥረው ....4 ክፍል ስንገባ ..ያንን ረቂቅ እና በህጻናት ልጆች ሊዘመር የማይችል ሙዚቃ ...ያለምንም ስህተት ሃርመኒውም ሳይዛባ ልዩ በሆነ ሁኔታ ሊያዘምሩን ችለው ነበር ! ጂኒየስ !

መታሳቢያነቱ ..ለቲቸር ዘውዱ ....በሳቸው ለተተኩትና ሰባት ልጆችን ወልደው ሰባቱንም መቅበራቸውን በሃዘን ያወጉን ለነበሩት ለቲቸር ታደሰ : እንዲሁም በጣም እንወዳቸው ለነበሩት ለሸበቶው ባለጥቁር መነጽሩ የብዙ ዓመት መዝሙር መምህራችን ..ለሻለቃ ግርማ ሐድጉ ይሁን ::

ፒስ !
_________________
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ቆንጂት 08

ዋና ኮትኳች

Joined: 19 Dec 2007
Posts: 735

PostPosted: Sat Mar 20, 2010 10:52 pm    Post subject: Reply with quote

ዋይ ውቃው የሆነው ነገር ሳስበው ይዘገንናል በርግጥ የኢትዮጵያ አስተማሪዎች ብዙ እንድናውቅ ያደርጉት ጥረት
አሁን ብወጭው አለም ከማያቸው አስተማሪዎች ጋር ሳመዛዝናቸው እንዳው ነጮቹ ለደሞዝ እንጂ ልልጆች ማወቅ ምንም ግድ የላቸው ብዙዎቹ በሌላም በኩል ልጁ ባይማር አስተማሪው ቀጣሁ ብሎ እንኩዋን መመታት ይቅርና አንዲት ክፉቃል ብትናገረው የልጁ ወላጆች የልጀን ሞራል ነካች ብለው ለፍርድ ያቀርቡሀል ሆኖም ግን የኢትዮጵያን ዱላ ባልደገፈውም የብዙዎቹ አስተማሪዎች ከልብ የመነጨ እንድናውቅ ሲያረጉ የነበረው ጥረት የሚረሳ አደለም
ወላጆች እራሳቸው ልጄን ተማር እያላችሁ አትጨቅጭቁ
ይደግልኝ እንጂ ሞራሉ ሳይነካ ገበያ ቆሞ ድንችስ ሸጦ ቢተዳደር ምን ያጋባችሁዋል የሚሉም ወላጆች አጋጥመውኛል ....የውጭው አለም ይህን ይመስላል
ወደ ሀጋራችን ስንስመለስ 5 ክፍል ተማሪ ሆኜ እደጅ ለሬዲዮ ትምህርት ወጣንና ከለሎች ተማሪዎች ጋር ተቀላቅለን ስናዳምጥ ከፊትለፊተ አንዲት ሙላትዋ ከበደ የምትባል ልጅ በውትድርናው ስልጣን ያለው ልጅ ናት የመትባል የምትለብሰው ከሁላችን ለየት ያለ ነበር እና ሁል ጊዘ ጎልታ ትታይ ነበር . ውቃው እንዳልከው ወደሌላ ስትመለከት አስተማሪው አይቷት ሳታስበው ከመሀላችን ጎቶት አውጥቶ እንዴት መላ አካላቱዋን ብካልቾ እንደረገጣት ልጅትዋም ወዲያው ፈንት ሆና ስትንፈራፈር
ትምህርቱም ቆሞ ልጅትዋን ሀኪም ቤት ወሰድዋት ከብዙጊዘ ህክምና በሁዋላ ወደት /ቤት ተመለሰች ሲዘግንነኝ የሚኖር መጥፎ ትዝታ ነበር
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Sun Apr 18, 2010 1:22 am    Post subject: Reply with quote

ዉቃው እንደጻፈ(ች)ው:
እኔ ደደብ ነኝ !

4 ክፍል ..ጥንት

የሙዚቃ መምህራችን ቲቸር ዘውዱ ..በጦር ሠራዊት ውስጥ ትራምፔት ተጫዋችና ሙዚቀኛ ነበሩ :: አለባበሳቸው ቀጥ ጽድት ያለና ..በካዥዋል ድሬስ ቆፍጣና ወታደር ....ምናልባት ያኔ በግምት 50ዎቹ ዕድሜ አጋማሽ ነበሩ :: ልጃቸውም (አንድ ሁለት ክፍል ከኛ ያንስ የነበረ ) ሁሉ ነገሩ እንዳባቱ እንደነበር ትዝ ይለኛል :: የሚለውን የሙዚቃ ..ከነ ቁልፎቹ ..የነ ሞዛርትን ሃይደንን ሾፕንን ታሪክ የተረኩልን እሳቸው ነበሩ :: በሳቸው ክፍለ ጊዜ ትምህርት እየሰጡ ንቅንቅ ማለት የለም :: ዝምብ አፍህ ወስጥ እንኳ ብትገባ !

አንድ ቀን ...አፍሪቃ አፍሪቃ የሚለውን እና በነርሲስ ናልባልዲያን ለአፍሪቃ ህብረት ምስርታ የተዘመረውን የክፍሉ በሶስት ቦታ ተከፍሎ ያጠናል ::

አፍሪቃ አፍሪቃ
አፍሪቃ ሐገራችን

አፍሪቃ ሀገራችን
አለች ነቃ ነቃ
የአፍሪቃዊ ህብረት
ልማት ነው ለአፍሪቃ

አፍሪቃ አፍሪቃ ....

እየዘመርኩ ሳለ ...ውጪ በመስኮት አሻግሬ ... ተማሪዎች በስፖርት ክፍለጊዜው ኳስ ሲጫወቱ አያለሁ :: መዘምሩን ባላቆምም ...ዓይኔ ግን እየሰረቀ ወደውጪ መመልከቱን አላቆመም :: እጄን እንዳጣመርኩ ..በመዝሙሩ መሃከል ዓይኔ ሳላዘው ወደውጭ ቀስ ብሎ ይሄዳል ::

" ውጣ !!!" እንደብራቅ የጮኸ የቲቸር ዘውዱ ድምጽ በህብረ -ዜማው መሀከል የክፍሉን አስደነገጠ :: ማንን እንደሆነ ለማወቅ ማን ይቻለዋል ?!
መጥተው ኮሌታዬን በመጨምደድ እያንገላቱ ወደ ጥቁር ስሌዳው አካባቢ ወሰዱኝ :: ተማሪዎቹ ፊት እንድቆም አረጉኝና ቀሰ ብለው ቀበቶዋቸውን እየፈቱ " በል የምልህን መልሰህ በል " አሉኝ :: "ስምህ ማነው ? " ነገርኳቸው ::

"እኔ ዉቃው ...ደደብ ነኝ " እሳቸው የሚሉትን እደግማለሁ ..ለተማሪዎች ::
" የማልርባ አህያ ደደብ ነኝ :: "እንደገና

እንደገና አሁንም .... ደግሞ እንደገና ሶስት አራቴ " እኔ ዉቃው ..የማልረባ ... ደደብ .... የማይገባኝ አህያ ነኝ " እያልኩ ለክፍሉ ተማሪዎች ቃሌን በተደጋጋሚ ሰጠሁ ::

"በል ሱሪህ አውልቅና አጎንብስ ::" እሳቸውም ገረፉኝ ... እስኪበቃቸው :: እየተብስከስኩ ወደመቀመጫዬ ተመለስኩ :: ዝማሬው ቀጠለ :: በቡሃ ላይ ቆርቆር እንዲሉ ዕረፈት ሲወጣ ... ያየኝ የክፍሉ ተማሪ ሁሉ ..."እኔ ደደብ ነኝ " እያለ ይጠራኝ ጀመር :: በመጀመሪያው ብናደደም ...ያየኝ ሁሉ እኔ ደደብ ነኝ ሲለኝ በቆይታ ብዛት ለመድኩት :: ቲቸር ዘውዱን ግን የመጨረሻ ጠላኋቸው :: ዓመቱም አልቆ ../ቤቱ ለክረምት ዕረፈት ተዘጋ :: መስከረም 3 5 ክፍል ስንመጣ የመጀመሪያው ነገር የቲቸር ዘውዱ መሞት በድምጽ ማጉያ መነገሩ ነበር :: የልጅነት ቂም እጅጉን ቋጥሬ ለነበርኩት ..ግን የሞት ምንነቱ ለማይገባኝ ለኔው ....ያኔ ተሰምቶኝ የነበረውን ደስታ መግለጽ ያቅተኛል :: እኔን ስለገረፉ ..በተማሪም መዘባበቻ ስላደርጉኝ እግዜር እንደገደላቸው እርግጠኛ ነበረኩ ::

ብዙ ዓመታት አለፉ :: ...ኋላ አድጌ ለአፍሪቃ ህብረት ምስረታ የተዘመረውን ኦሪጅናሉን መዝሙር በሰማሁ ጊዜ ...ደደብነቴን አረጋጥኩ :: ቲቸር ዘውዱ ...1 ክፍል ጀምረው ..የሙዚቃ ሁን አስቆጥረው ....4 ክፍል ስንገባ ..ያንን ረቂቅ እና በህጻናት ልጆች ሊዘመር የማይችል ሙዚቃ ...ያለምንም ስህተት ሃርመኒውም ሳይዛባ ልዩ በሆነ ሁኔታ ሊያዘምሩን ችለው ነበር ! ጂኒየስ !

መታሳቢያነቱ ..ለቲቸር ዘውዱ ....በሳቸው ለተተኩትና ሰባት ልጆችን ወልደው ሰባቱንም መቅበራቸውን በሃዘን ያወጉን ለነበሩት ለቲቸር ታደሰ : እንዲሁም በጣም እንወዳቸው ለነበሩት ለሸበቶው ባለጥቁር መነጽሩ የብዙ ዓመት መዝሙር መምህራችን ..ለሻለቃ ግርማ ሐድጉ ይሁን ::

ፒስ !

እስከዛሬ ሳላነባት እኔ ራሴ ደደብ ነኝ ...
ደስ የምትል ትዝታ ...

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዉቃው

ዋና ኮትኳች

Joined: 07 Jan 2007
Posts: 970

PostPosted: Wed Jun 02, 2010 5:57 am    Post subject: Reply with quote

ባንድ ወቅት ዳላስ ጁፒተር መንገድ ላይ በሚገኘው /ክርስቲያን በእንግድነት ተገኘተን : ብጥብጥ አንጎሌን ቢያዞረው : ምን ነው ምን ነካኝ ዓይነት ነገረ በዚሁ ትሬድ ገጽ አምስት ላይ ቀብጣጥሬ ነበር መሰል ! እሱም ሆነና በቅርቡ ጠቡ ተባብሶ ዜና ሲሆን "አይገርመኒ " አልን ::

በቸርች አስተዳደር : አሸናፊ ዋንጫውን ይወስዳል ዓይነት ነገር ነው :: ስረ መነሻውም ያዕቆብ :: የመጨረሻ ጨላጣ ያራዳ ልጅ ማለት እሱ ነው :: እንግዲህ ያኔ ጥንት ጂፒኤስ እና ሴልፎን ምናምን ባልነበረበት ፋራው ኤሳው ፒፕሉን አስከትሎ ለዳዲ ይስሀቅ ባርቢክዩ ሲንከራተት : ያዕቆብ ሆዬ እቤት የኤሳውን ፍየል አረዶ : ቆዳውን ለብሶ ዳዲ ይስሃቅን ሸወደበት :: ዳዲ ይስሐቅ የያዕቆብን እጅ ነካካና : "ስማ አባው ... የእጅሽ ጸጉር የኤሳውን ይመስላል ...ድምጽሽ ግን አልተመቸኝም ...ያዕቆብ ነሽ እንዴ ? " ዓይነት ነገር ደጋግሞ ጠይቆታል አሉ :: ያዕቆብ ሽምጥጥ አርጋ ካደች :: ልብ በሉ : ይህ ሁሉ ሲሆን ማሚ ርብቃ ቆማ ታያለች :: ምን ማየት ብቻ ..የመፍንቅለ - መባረኪያው ጠንሳሿ እሷ ናት እንጂ :: እንግዲህ ኤሳው ብኩርናውን አስቀድሞ ሽጧልና መባርኩ ላይገባው ይችል ይሆን ይሆናል :: እሱም ሆኖ ቢሆን እንኳ ቢሆን የሽያጩ ስምምነት በዳዲ ይስሃቅ አልጸደቀም ነበር ::

ያዕቆብ በዚህ አላቆመም :: አንድ ቀን ምድረ በዳ ውስጥ ኩሼ ብሏል :: አንድ ሰው መጥቶ በሰላም ከተኛበት በቡጢ ይቀሰቅሰውና ለሊቱን ሙሉ ሲካንቱ ያድራሉ :: በመጣፉ ታሪክ "ታፍ ጋይ " የሚባለው ሳምሶን ነበር :: ያዕቆብ ግን ትግል የገጠመው በመጨረሻው ሰዓት ላይ ነፋሳትን በአራቱም የዓለማችን አቅጣጫ .ገትረው ያቆማሉ ከተባሉት አንዱ መልዓአክ ጋር ነበር :: ኋላ ላይ ሁለቱም ተዳክመው ሲንጋጋና ያዕቆብ ሲያየው : ሰውየው ሰው ሳይሆን ለካ የግዜሩ መልዓአክ ነው :: ያራዳው ልጅ ያዕቆብ ምኑ ሞኝ ነው ..ሲቦቅሰው ያደረውን መልዓአክ ..አሁን ደግሞ ካልባረከኝ አልቅህም ብሎ እግሩ ላይ ተጠምጥሞ ቁጭ ! መልዓኩ ምን መባረክ ብቻ ስሙንም ለውጦ ኢስራኤል አለው " አንተ አንኳን ሰውን ለዝጋቤርም አልተመለስክ " ሲል :: መልዓኩም ብልጥ ነው :: ከመለያየታቸው በፊት ግን ያዕቆብን እግሯ ላይ ለመታሰቢያ እንዲሆን ደህና አርጎ አቅምሷታል :: የግዜር ምት !

እና ኑሮም እንዲሁ ግብግብ ነው :: ልውሰድ አትውሰድ ! የኔ ነው ...የለም የኔ ነው ! አይገባህም ... ይገባኛል ! መንጣጠቅ ...መቀማማት ..በዚህም በዚያ ብሎ
ለማሸነፍ መሯሯጥ ... ብልጥ ..ያራዳ ልጅ ሆኖ መገኘት ነው ...ልክ እንደ ያዕቆብ !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
yammi

ኮትኳች

Joined: 28 Jul 2006
Posts: 436

PostPosted: Wed Jun 02, 2010 10:35 am    Post subject: Reply with quote

ውቅሽዬ እርግጠኛ ነኝ የመጽሀፍ ቅዱስ ታሪክ በዚህ መልኩ ተጽፎ ቢሆን ኖሮ ሰው ሁሉ ማንበብ ብቻ አይደለም በቃሉ ይሸመድደው ነበር Laughing Laughing :: ለማንኛውም መጽሀፍ ቅዱስን (በተለይ ብሉይ ኪዳንን ) እንደታሪክ ብቻ ለሚያዩት እና ለምናየው ጥሩ ማመዛዘኛና መማሪያ ናት :: አትጥፋብን ::

ያሚ

ዋንሽዬ ሰላም ብያለሁ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ኡኬ

መንገደኛ

Joined: 16 Jun 2010
Posts: 5

PostPosted: Thu Jun 24, 2010 2:02 am    Post subject: Reply with quote

አመሰግናለሁ ያሚታ ቆንጆ ! የጠፋሽ ሰው ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
ኡኬ

መንገደኛ

Joined: 16 Jun 2010
Posts: 5

PostPosted: Wed Jun 30, 2010 9:15 pm    Post subject: Reply with quote

.

Last edited by ኡኬ on Sat Jul 03, 2010 12:12 am; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
ገልብጤ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 26 Jun 2010
Posts: 1525

PostPosted: Wed Jun 30, 2010 9:48 pm    Post subject: Reply with quote

ኡኬ እንደጻፈ(ች)ው:
The Forgotten War 60th Anniversary

የባለታሪክ ልጅ መሆን ዕዳ ነው :: የተሸከሙት ..የሚያወሩት ....የሚተነትኑት ብዙ አለና :: የደረጄን "አባቴን ያቺን ሰዓት " ባነበብኩ ጊዜ የተሰማኝን እና ልገለጸው የማልችለውን ለመናገር ....ስለእግዚአብሄር እውነት ቃላት ያጥረኛል :: ዝም ብዬ የባለታሪክ ልጅ መሆን ዕዳ ነው ልበለው :: ዕዳዬን ግን በጣም በጥቂቱ ዛሬ ላካፍል .. እንደደረጄ በጥቂቱ ቢቀልልኝ !

አሜሪካ 2004

ኮኒ የማውቃት በነቤርሁዱ ቮዩንተሪ ሰርቪሳችን ነው :: ኮሪያ - አሜሪካዊት ናት :: የዛሬ ስድሳ ዓመት ለደቡብ ኮሪያዋም አገር ነርስ ነበረች :: በጦርነቱ አጋጣሚ ለአሜሪካውያኑ ነርሶች ረዳት ሆና ተመደበችና አንድ ቀን ..ባሜሪካውያኑ ዳንስ ምሽት ላይ ተገኘች :: በጣም የምትወደው አሜሪካዊ ወታደር ነበራት :: አንዳንድ ቃላትም ተለዋውጠዋል :: በዳንስ ምሽቱ ወቅት ...አሜሪካዊው ሌላ ሴት ይዞ መደነስ ጀመረ :: እሱን ለማስቀናት ባይኗ ስትፈልግ ጄነራል ዊልያምን አየች :: አጭር : አስቀያሚ ...የማይመረጥ ...ይዞ ቁጭ ያለ ነበር :: አስነሳችውና አብረው ደነሱ :: በዛው ተጋቡ ....ወልዱ ....::
ዳውን ሲንድረም ያለበት ልጃቸው ዊልያም ጁኒየር በማክበር የሰጠኝ ..አባቱ የሰጠው .... ያባቱ 1950 ዊሊስ ጂፕ ቶይ ...አሁንም ለመታሰቢያነት ተቀምጣለች ..በቤቴ :: ለጀነራል ዊልያምስ ..በወቅቱ አባቴ በኮሪያ ተነስቷቸው የነበሩትን በርካታ ምስሎች ...ጸጉራቸውን ይቆርጡ በነበሩበት ቦታ በቀጠሮ ተገናኝተን አሳየኋቸው :: እዛ የነበሩት ሁሉ አከበሩኝ :: አጠንክረው ጨበጡኝ : ለኔ ሳይሆን ደሙን አብሯቸው ስላፈሰሰው አባቴ ክብር !1979 አዲስ አበባ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል

የማልረሳው ....ሁሌም .....የማስታወሰው ....ጭንቅ አሁንም ወጥሮኛል :: አባቴ እንደደረጄ አባት ታሪክ ሊያስታቅፈኝ ቆርጦ ተነስቷል :: "ይሸከመው ይሆን ወይ " ብሎ ፈጽሞ አልሰጋም :: አሁና አሁን ሳስበው ስራውን ከጀመረ ቆይቷል :: ጦር ሃይሎች ሆስፒታል ቀውጢ ሆኗል :: እንድወትሮው እቤት ዋሉ የምንባል ልጆች ...አሁን ከአባቴ ጋር መዞር ከጀመርኩ ከራርሟል :: የጦር ሃይሎች ሆስፒታል ህንጻ መግቢያው ከውስጥ በር ላይ እዚህ ጠብቀኝ አለና ...ካይኔ ጠፋ :: ጦር ኃይሎች እንደ ጦር ሰራዊት መኮንኖች ክበብ አልነበረም :: እጅግ በጣም ያስፈራል :: ቁስለኞች : እግራቸው ላይ ብዙብረት የታሰረበት ሰዎች ይመላለሳሉ :: ጥቂት ቆይቶ እዚያው በር ላይ እሳካሁን የማልረሳው ...ከፊቱ ግራ ዓይን እስክ ግራ አገጩ የሚወርድ ሰፊ ጠባሳ ያለበት ..አስፈሪ ራሱ ላይ ነጭ ሄልሜት በካኪ ፋቲግ ያድረገ ወታደር ፖሊስ ፊቴ ተገተረ ::

እሽ ይቀጥሉ ..ጋሽ ውቃው (ኡኬ ) እንደ ባራምቢ ጰንጤ ቆስጤ ሆነው ነው የሚተውኑታ ? ያቦራ እና የእሙሙ ነገር እንዴት ሆነሳ
_________________
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Tue Sep 14, 2010 1:32 am    Post subject: Reply with quote

ኮንቺ (በጃፓንኛ )

አንዳንድ ዓለማቀፍ ድረ -ገጾችና ጡመራዎች (ብሎጎች ) ላይ ዋናው በሚለው ስሜ ሎግ -ኢን ሳደርግ ብዙዎቹ ጃፓናዊ እመስላቸዉና በቋንቋው ያዋሩኛል ... እኔም ቅርብ ጊዝ ነው ዋናው የሚል የጃፓን ስም መኖሩን ያወቅኩት ...
እስቲ ዛሬ ትንሽ ልዘብዝብ አቦ ...
አዲስ ዓመትም ሆነ አሮጌው ተሽኘ ... ግን ለምንድነው ዓመታት ሁሉ መስከርም ሙሉ ሆነው ጳጉሚትን አጭር ሆነው አገልግሎታቸዉን ጨርሰው ሲሄዱ ሸኚ ቤት አያደርስም ብለው ብቻቸዉን ሚጠፉት ... ተደብቆ ማየት ቢቻል የት እንደሚገቡ ባውቅ ደስ ይለኛል ... የዘመን አዲስና አሮጌ የለዉም 'ምትሉኝ ካላችሁ አለው እውነት እውነት አለው ... ባይኖረው መስከረም ባደይ አበባ ፈክታ ትኩስ ሆና ባልመጣች ... ነሀሴም አርጅቶ ሰማዩ ባላደፈ ...
ደግሞም የዘመን እርከን ባይኖር የሠው ልጅ ጊዜን ሲሰፍር አንድ ወጥ ያደርገው ነበር ለምሳሌ የአንድ 30 ዓመት ሰው 30 ዓመቱ ከመባል በደቂቃዎች ወይም በሌላ የጊዜ መስፈሪያ ተለክቶ እንደካርድ ነምበር በቁጥር ይንቆጠቆጥ ነበር ...
ስለዘመን ስወሻክት ዝብዛቦቴን የቸከልኩበት ጉድጓድ ሳይጠፋኝ እንዲህ ልበል ... የሠው ልጅ በዘመኑ ሲኖር የራሱ መክሊት ... ግዴታ ... ድርሻዉና ስእተቱ አብሮት እንደሚኖር አይካድም እነኚህን እያቋመረና እያስታረቀ ሲኖር ሳይፎርሽ ወደእርከኑ ያሻቅብና ትንፋሹን ጨርሶ እርሱም እንደዘመን እርከን እንደትላንቱ አሮጌ አመት አዲዮስ ይላል ዓመቱስ በሩፋኤል ፀበል ተባርኮ በችቦ ጪስ ይሸኛል ዘመኑን የተቋመረው ፍጡር ግን ፍትሃቱን በእንባ ቢያስ 'ሳርግም ከሸረፈው ዘመን ላይ ያልተከለው የዘመን ማስታወሻ ከሌለ ... ሞቱ ድርብ ይሆናል ... ዘር መተካት ብቻ አይደለም ... እሱንማ ጉማሬም ቢሆን ተወልዶ በዘመኑ ሲኖር ራሱን ይተካል ... ምናልባትም በጉማሬያዊ ሕይወት ውስጥ ብዙ ድርሻም አበርክቶ ... ዛፍና አረምም ምን ዓይነት ውጣ ውረድና ፈተናን አልፈው ሕይወታቸዉን እደሚመሩ በዴቪድ ኤደንብራ ሳይናስዊ ዘገባ አይተናል ...
እናም በዘመኑ ውስጥ 'ሚኖር ሠው ሁሉ የቀረበለትን በልቶ ብቻ ከተኛ እስረኛ መባሉ አይቀርም ... ውስጡን አዳምጦ ራሱን ታዞ ድንጋይ መፈንቀል አለበት ... አንዳንዴ ራስን ስለመታዘዝ ሳስብ ... ምናለበት ሁሉም ስሜታዊ እርካታዎች ላንድ ሠው አንድ የራሱ የሆነ ብቻ ቢሆንና ያንን ደግም ለማግኘት ድንጋይ ካልፈነቀለ ልክ እንደመሠረታዊ ፍላጎቶች አለመሟላት ... እንደመታረዝና መራብ ውስጡ ባዶ ቢሆን ... ለምሳሌ አንድ ሰው ሚሰማውና ሚያስደስተው ሙዚቃ ብዙ ዓይነት ቢሆንም ስሜቱን ግን በደምብ 'ሚያረካው አንድ የራሱ ብቻ ቢኖርና ያንን የመፈለግ ግዴታ ቢኖረው ... ይሄ ቢሆን ዘመንን በዛብሽ ብለን አሁን የኮነንናት የላቀች ሆና እናገናት ይሆን ነበር ... እንደነ አንጀሎ እንደነዳቬንቺ እንደነሃዲሰን ... ዓይነቶች በየዘመኑ ተደጋግመው ተፈጥረው ይሆን ነበር ::
አንዳንዴም አሁንኛን ሆነን ሪተርን ኢኖሰንት ያምረን የለ ... ጊዜዉን በጣቶቼ እንዳልቆጥር ሁለት እጅ ብቻ ኖረኝ እንጂ የዛሬ ምንትስ ዓመት ኮንሶ ውስጥ አንዲት ፈረንሳዊት አግኝተን ነበር የራሷ አገር ጨርቋን ብትጥል ብርቅ ስላልሆነ ኮንሶ ሄዳ ጨርቋን ጥላ አግኝተናታል ... ሁሉንም ረስታ እንደነርሱ እሕል በመጅ ፈጭታ ውሃ ባናት ተሸክማ ስትኖር ... ምናልባትም ዘመኗ ውስጥ ስትኖር አምጪ አምጪ 'ሚላትን ጉዳይ ወይ ጉግል ውስጥ ገብታ መጎልጎል አለያም አውርዳ መጫንን አላሰበችም ዲፑሊኬት የተደረገ ሕሴትን ውስጧ መመገብ አልፈለገችም ...
አንድ ሳልል ሁለት ማለት ይፈቀድልኝ
ሁለት
ዓለማችንን 'ሚያሽከረክሩ ከመቶ በጣት የሚቆጠር እጁ ብቻ ናቸው ይባላል (ለነገሩ ዓለማችን በሠው መዳፍ ምትዞር አይደለችም ... ብቻ እንበልና ... ) እነርሱ በዘመናቸው ለራሳቸዉም ይሁን ለሌላ የሠሩት ይኖራል ... ከመሰበክ ተሽቀንጥረን እንሽሽና አንዱ ያበጀው ለሁሉም ልክ ይሆናል የሚለው እምነት እናስበው እስቲ ... ሕይወትን ለመታገድ የግድ ሮው ሞዴል ያስፈልገን ይሆን ...?
የተሰባጠረው ግራሞቴን ድጋሚ ፐውዤ ለራሴ ለማየት ከራሴ ልቃጠርና ... ከዘመኔ ውስጥ ያገኘዋቸዉን ወይም ምፈልጋቸዉን ክስተቶች ለማደን አዲሱን ዓመት አሃዱ ልበል ... ውስጤ አንድን ነገር ከፈለገ ነገር ዘመኔ ውስጥ መኖሩ ግድ ነው ...
አሁን መሮጥ እፈልጋለሁ ያቺን ብሽኪሊሊት ልፈናጠጣት ዳገት ከወጣች ቁልቁለት አያቅታትም መሽከርከር ከቻለች መፍጠንም መቆምም 'ማትችልበት ምክኒያት የለም ::

ድጋሚ በጃፓንና
ጃኣ_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Mon Mar 14, 2011 1:09 am    Post subject: Reply with quote

ኬፍ ....

በዚች ቤቴ ቅዥቅዥ ያለ ዘመንኛን ማወደስና መኮነን ማስንበቤ ወይም ጫጭሬ ለራሴ ማንበቤ የቅርብ ጊዚያት ትዝታዎቼ ናቸው ... ፊዚሺያን ዶክተር ማቺኦ ካኩ በዚህ ቪዲዮ ላይ ዓለማችን 2030 ምን እንደምትመስል የዳሰሰዉን ሳይ ትንሽ ግርምምም አለኝ :: ግን ' ዓለማችን በዚህ አያያዟ እንዴት ነው እስከዛ ምትዘልቀው ..? እንደጠላ ቂጣ እየተገመሰች ከፊል ጎኗ ትንቀጥቅጦ እየራደ ከፊል ጎኗ ፍም ሆኖ በእሳት ነበልባል እየሳቀ እንዴት ነው እስከ 30 'ምትቆየው ?

ለማንኛዉም ፈጣሪ ደጋጉን ብቻ ያቅርብላት ብለን እንቆይ ... እስቲ እዚች አምድ ዘው ላላችሁ ማጣቀሻዉን ጠንቁሉና ቱቦ ሄዳችሁ እዩት : ለሠካራሞች ተስፋ የተሠጠበት ፓርት ተመችቶኛል ...

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዉቃው

ዋና ኮትኳች

Joined: 07 Jan 2007
Posts: 970

PostPosted: Mon Apr 11, 2011 1:07 am    Post subject: Reply with quote

ኬፓሶ አሚጎስ !

ለክቡር ለዚህ ርዕስ -አልባ አርዕስት ባለ -ቤት ጓድ ዋናው የተለመደ አክብሮቴ ይድረስ ::
አንዷ ቆልማሚት ..."ታሪክ ይሰራል እንጂ ይነበባል እንዴ " አለችና አስቀባጠረችኝ :; ድሮውንስ ከቆሮቆንዳ ራስ ቆልማማ ቆልማሚት ዘንድ የተንቆላመመ ቁልምም እና የተንቆርቋንደ ነገር እንጂ ሌላ ምን ይጠበቃል ?! ስራሽ ያውጣሽ !!!!
በረጅሙ በረራ ላነበው ያዘጋጀሁትን አንድ ሶሶት መጽሀፍ ይዤ ነበር :: ያነበብኩት /የደገምኩት አንዱን ብቻ ነው ...ያውም አልጨርስኩትም :: የዶ / ሀሊማ በሽር ቲርስ ኦፍ ዴዘርት ..... ገብሩ ታረቀ ኢትዮጵያን ረቮሉሽን እና ሮናልድ ኬስለር ኢንሳይደ ፕሬሲደንትስ ሲክሬት ሰርቪስ ! ደግሜ ላነበው የቻልኩት ግን የገብሩ ታረቀኝን ብቻ ነበር !
በርግጥ ታሪክ ይሰራል ...ተስርቶ ሲያልቅ ...ጊዘው ሲያልፍም ይነበባል :; አይቀርለትም :: ታሪክ ልስራህ ብለው ላይሰሩትም ይችላሉ :: ሳይፈለግ አጋጣሚም ይሰራዋል ..ደሞም ታስቦ ይሰራል :: ተሰርቶ ሆና ሳይሰራ ጎድሎም ቢያልቅ ...ሲጨረስ ..ሲገደብ ...ሲገነባ ተዘፍኖ ...ተጨፍሮ ... ግዳዩ ተጥሎ ሲያልቅ ..ታሪክ ይሆናል :: ታሪክ ሲሆን ...ለኔ ቢጠዎቹ አንባቢዎች ሲነበብ ደስ ይላል :: (በዚህ አጋጣሚ ክብር ለታላቁ ኮሚኒስት ወዳጄ ፓን ሪዚኮ )

ይህን አስታወስኩ .......ሳሙኤል ደሳለኝ :: የጀግናው የኮሎኔል ደስለኝ አበበ (ኋላ ደርግ የገደላቸው /) ልጅ ከኪንደርጋርተን እሰከ 12 ድረስ አብረን ተምርናል ::
ነጻ አውጪው አብዮታዊ ጦራችን
እንደካራማራ እንደ ጪናክሰን
.
ሰሜንም ደግመህ በድል ኩራ እያልን /ቤት ስንዘምር ሳሙኤልም አብሮን ይዘምር ነበር :: ከኮሞልቻ ተነስቶ ካራማራ በለዋ ..ጪናክሰን ..ኤጀርሳ ጎሮ ... ጉርሱም ..ሜሎንን ነጻ አውጥቶ ..ከዛም ጂጂጋ ላይ ሰንድቃችንን ያውለበለበው አባቱ መሆኑን እንኳን እኛ እሱም አያውቀው :: ባለታሪክ አባት በበርሃ ... ልጅ እኛ ክፍል በፒያሳ ! አንድ ቀን ዋሽንግተኖች ሳሙኤልን ካለበት ወይም ታላቁና በጣም ጎበዝ ተማሪ የነበረውን ወንድሙን ኢሳይያስ ደሳለኝን ጠርተው ሰላባታቸው ያከብሩልኝ ይሆናል !(ለዋሽንግተኖች ቅድሚያ ምስጋና ) (2009ኙም ደራሲ ገብሩ ታረቀ ምስጋና )

ከኢትዮጵያ ስመለስ ግን ..ሻንጣዎቼን የሞላሁት ...በእልሳ ቆሎ (ሾፌሯን ወዳ ....ባሏን ፈታ ...... ልቧ ጠፍቶ የዱከሙ ቆሎዋ በአዲስ ፍቅር ምክኛት ..ተበላሽቷል ቢባልም ) እና በመጻህፍቶች እንዲሁም በቅቤና ሚጥሚጣ ነበረ :: ቆሎው አሁን አልቋል :: እመኑኝ የጨረሱት ግን በአብዛኛው አሜሪካውያን ናቸው :: መጻህፍቱም በስስት ቢነበበቡም ቀናቸውን ጠብቀው ቶሎ አለቁ :: የልብ ፍቅር ከመጻህፍት የያዘኝ ግን እምሩ ታምራት ይገዙ ካሳተሙት ከልዑል ራስ እምሩ ኃይለስላሴ መጽሃፍ ጋር ነው :: ፈልጉት ..አግኙት ታሪክ ነውና አንብቡት :: የማሞ ውድነህ ትዝታዎችም መሳጭ ናቸው :: የተስፋዬ ርስቴ ምስክርነት ...የበዥሮዎንድ ተክለሀዋርያት ...ግለ ታሪኮችም ልዩ ናቸው :: በፒያሳ ልጅ ..አፈንጉስ ቅጣው ይግለጡን ከነሜዳቸው አገኝኋቸው ...የጊዮርጊሱ ተጫዋች ያየህይራድ ቅጣው ድንገት ድቅን አለ ...ያውም ከነ ልጁ ! አይ ታሪክ !!!! ..በቃለክርስቶስ አባይ እና አንድ ስሙን ለጊዜው በማልግልጸው መጻሀፍ ላይ ደግሞ ያባቴ ስም ሳገኝ ከመጠን በላይ ተደስቻለሁ :: ታሪክ ይሰራልም ይነበባልም አልኩ ! ለራሴ ! በተለይ በተለይ አባቴ "በተላያዩ ጊዜያት ካጠራቀምኳቸው ማሳታወሻዎች የተገኙ " በማለት 315 ገጾች 1938-1961 ድረስ ያዘጋጀው ያልታተመ መጽሀፍማ እጄ ሲገባ ደስታዬ እጥፍ ድርብ ነበር :: ቃላት የምር አጠሩብኝ !

ራስ እምሩ ኃይለስሴ ባለ ታሪክ ነበር :: ለሌ // ታምራት ይገዙም እንዲሁ :: የልጅ ልጃቸው እምሩ ታምራት ይገዙ ታሪካቸውን ባያሳትም ኖር ራስ እምሩን እንዴት እናውቃቸው ነበር ? እናም እምሩ ባለ ታሪክ ነው ::

በዚህ አጋጣሚ ላለፉት አስራ አምስት ዓመታት እስማቸው የነበሩትን ካሴቶች ጥብቃ ላቆየችዋ ውብ ልጅ ምስጋ ይድረሳት ! እምጵዋሽ የኔ ቆንጆ ..እወድሻለሁ !

_________________
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
እንሰት

ውሃ አጠጪ

Joined: 30 Jan 2005
Posts: 1211
Location: united states

PostPosted: Mon Apr 11, 2011 2:57 pm    Post subject: Reply with quote

ዉቃው እንደጻፈ(ች)ው:
ኬፓሶ አሚጎስ !

ለክቡር ለዚህ ርዕስ -አልባ አርዕስት ባለ -ቤት ጓድ ዋናው የተለመደ አክብሮቴ ይድረስ ::
አንዷ ቆልማሚት ..."ታሪክ ይሰራል እንጂ ይነበባል እንዴ " አለችና አስቀባጠረችኝ :;
!
በርግጥ ታሪክ ይሰራል ...ተስርቶ ሲያልቅ ...ጊዘው ሲያልፍም ይነበባል :; አይቀርለትም :: ታሪክ ልስራህ ብለው ላይሰሩትም ይችላሉ :: ሳይፈለግ አጋጣሚም ይሰራዋል ..ደሞም ታስቦ ይሰራል :: ተሰርቶ ሆና ሳይሰራ ጎድሎም ቢያልቅ ...ሲጨረስ ..ሲገደብ ...ሲገነባ ተዘፍኖ ...ተጨፍሮ ... ግዳዩ ተጥሎ ሲያልቅ ..ታሪክ ይሆናል :: ታሪክ ሲሆን ...ለኔ ቢጠዎቹ አንባቢዎች ሲነበብ ደስ ይላል :: (በዚህ አጋጣሚ ክብር ለታላቁ ኮሚኒስት ወዳጄ ፓን ሪዚኮ )

..በቃለክርስቶስ አባይ እና አንድ ስሙን ለጊዜው በማልግልጸው መጻሀፍ ላይ ደግሞ ያባቴ ስም ሳገኝ ከመጠን በላይ ተደስቻለሁ :: ታሪክ ይሰራልም ይነበባልም አልኩ ! ለራሴ ! በተለይ በተለይ አባቴ "በተላያዩ ጊዜያት ካጠራቀምኳቸው ማሳታወሻዎች የተገኙ " በማለት 315 ገጾች 1938-1961 ድረስ ያዘጋጀው ያልታተመ መጽሀፍማ እጄ ሲገባ ደስታዬ እጥፍ ድርብ ነበር :: ቃላት የምር አጠሩብኝ !

ራስ እምሩ ኃይለስሴ ባለ ታሪክ ነበር :: ለሌ // ታምራት ይገዙም እንዲሁ :: የልጅ ልጃቸው እምሩ ታምራት ይገዙ ታሪካቸውን ባያሳትም ኖር ራስ እምሩን እንዴት እናውቃቸው ነበር ? እናም እምሩ ባለ ታሪክ ነው ::

እንዴት የሚያስቀና ጽሁፍ መሰለህ :: Thank you!!!!

አባ እንዳትወቃኝ እንጂ ጎሸም ላደርግህ ነው :: ምነው እምሩስ የአባቱ ልጅ ሆኖ ስራቸውን አሳተመ ይህንን ድንቅ የጽሁፍ ችሎታ ይዘህ ያባትህን ቅርስ ወርሰህ ዝም ይባላል ? ተው ተው መላ በለው እና እናንብብ ምነው ወኔ እንኩዋን ከፈረሰኛው አባ ፈርዳ ባይሆን ተዋስ እንጂ ::

መልካም ቀን
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዉቃው

ዋና ኮትኳች

Joined: 07 Jan 2007
Posts: 970

PostPosted: Sun Jul 03, 2011 3:32 am    Post subject: Reply with quote

መቅባጠሪያውን ጂንየሱ ዋናው ሲፈጥረው ...ርዕስ የለውም ..እዚህ እዚያ እንዲቀባጠርበት ለራሱ አመቻችቶ ፈጥሮታል :: እኔ በግድ .....ጣልቃ ገብቼ እቀባጥራለሁ :: ዕዳ እኮ ነው !

ስለዘመነ ኢንላይትመንት ያውቅኩት ኮሌጅ የወርልድ ሂስሪ 1 2 ምናምን ክላስ በግድ ሰወስድ ነበር :: ዘመኑ አስራስምንተኛው ክፍለዘመን ነበር አሉ :: ዝርዝሩን ግን አሁን ረሳሁት ::

በኢትዮጵያ ደግሞ ኢንላይትመንት የጃንሆይ ኃይለስላሴ ዘመን መሆኑን ለራሴ አምኜ እኔ የደርጉ ልጅ ተቀብያለሁ :: ክላሲክ ዘመን ..ክላሲክ ጸሀፊያን ...ክላሲክ ደራሲያን ....ክላሲክ ምሁራን ...ካልሲክ ፖለቲከኞች ...ምኑ ቅጡ ...ዘመኑ ልዩ ነው ... ነበርም ::

ጠዋት ስራ ስሄድ ..በመኪናዬ ለግማሽ ሰዓት ሰዓታትን እየሰማሁ ነው :: ግዕዝ ...አይገባኝ አልገባው ...ግን ግዕዝ .......ከትራፊክ ጃሙ ..ከሎካል ሬድዮ ከንቱ ልፈፋ ...በረዶ ጸሀይ ግለት ዝናብ ማስፈራሪያ ... ቅራቅንቦ ጂኒ ጃንካ ...ምናምኑ ....እኔ አባ ዉቃው ...በተመስጦ ....ነጉዳለሁ :: አዕምሮዬ ወስጥ ያለውን የክሬዲት ዕዳ ..ስቱደንት ሎን ...ጃብ ሴክዩሪቲ ...ሞርጌጅ ....ህመም ...ጭንቀት ..ዋርካ ...ዋናው ...ኮንጂት ...ሙዝ ...ህመምተኛው ወንድሜ ...ምስኪን እናት ...አሪፍ አብሮ አደግ ጓደኛ ..እንጀራ መግዛት ...እሙሙ ...ሁሉም ....ይጠፋሉ :: ሰዓታት !

ስለእምነታቸው መንኩሰው የሞቱት አያቴ በመቶ ምናምን አመታቸው በተስኪያን ..ሲሄዱ ..ጎናቸው ስከተል ...ምዕመን ባክብሮት ሰላም ሲላቸው ...መንገዱ ...ሰላሙ ..ባህርዛፉ ....ዳገቱ ...የጉልላቱ ሽውሽውታ ....የኔብጤው ...ቄጠማው ...የጠጅሳሩና አሪቲው ሽታ .... በምናብ ይመጣል :: ከትከሻዬ / ማዥራቴ ላይ ተጋግሮ የነበረው የማላውቀው ክባድ ነገር በኖ ይጠፋና ..ስራ የፋይቭ አወሩን ኢነርጂ ድሪንክ እንደጠጣው ሆኜ እከስታከሁ :: እንዴት ? አላውቅም ..አራት ነጥብ
_________________
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ናፖሊዮን ዳኘ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 18 Apr 2008
Posts: 1878

PostPosted: Sun Jul 03, 2011 4:33 am    Post subject: Reply with quote

አንዳንዴ የንባብ ጥም የሚቆርጥ አንጀት ላይ ጠብ የሚል ነገር ያጋጥማል :: ይቺኛዋን እና ከላይ ያለውን ፖስትህን ካነበብኩ በኍላ ለረዥም ጊዜ ወደዚህ መድረክ ባለመግባቴ ብዙ ቁም ነገር ያለው ውይይት ያለፈኝ መስሎ ተሰማኝ ::

አብዮት ሁሌ የኢንላይትመንት ውጤት ነው ብለው ከሚያምኑ ...እንደዛ ብለው የሚያምኑ ካሉ ...ወገን ነው ራሴን የምመድነው :: ፈረንሳይ ውስጥ የነበረው ኢንላይትንመንት ልክ እንደፍልስፍናው ድንቅ የሆነ የፈረንሳይ አብዮት ወለደ :: ነጻነት እና ለውጥ የሚፈልግ ዓለም ወደ ፈረንሳዮች ልምድ ነበር የሚያየው :: እኛም በጃነሆይ ጊዜ የጠቀስከው አይነት የጥብብ ስራዎች ያቆጠቆጡበት ( የኛ ኢንላይትንመንት ) ጊዜ ስለነበረ ለውጥ አስፈላጊ ሆኖ እንዲታይ የበኩሉን ድርሻ ሳይፈጥር አልቀረም :: ለውጡ ሳካ አልነበረውም ማለት አይቻለም :: የመሬት ላራሹን አቢዮት የሰራተኞች ፖርቲ በመመስረት ለማራመድ ሲሞከር ትልቅ ጥፋት ጠፍቷል :: ሌላ አፈናም ተፈጠረ :: በአፈናውም ውስጥ ግብ ኢትዮጵያዊነት በመንግስትም ሆነ በአዘማኖች (ራሳቸውን እንደኢንላይትነት የሚያዮ ) ፈተና አልገጠመውም ነበር :: ምልከታው ወደ ውስጥ ነበር :: እንደገባኝ ጥበብ ርቆ አራቀም ከሀገር ::

እንድንዴ ጥበብ እንዳረጉት የሚሆን ይመስለኛል ( ልሳሳት እችላለሁ ) ላንቃበት ካልክ ታነቃበታለህ :: ላደንዝዝበት ካልክ ታደነዝዝበታለህ :: ወደ ውስጥ የሚያሳይ ውስጥን የሚኮረኩር ጥበብ ንቁ የሚያደርገውን ያህል ውጪ ውጪን የሚያሳይ ጥበብ ደሞ የሚያዘናጋ እና የሚያደነፍፍ መስሎ ይታየኛል ::

ጃም ላይ ሆነህ ልብህ ግዕዝ እና ቀደም ያሉ ክላሲካል ብለህ ያስቀመጥካቸውን ስራዎች እና ያሰብከው ዘመን ባንኖርበትም እውነትም ድንቅ ነበሩ :: ከአይምሮ የማይጠፋ ነገር ድንቅ ቢሆኑ ነው :: በጥላሁን እንኳ ብቻ ሙዚቃዎች ብዙ ቁምነገር ይታያል :: ጥላሁን ወገን አለኝ እያለ ሲዘፍን ያለቀሰውን ለቅሶ ያየ ...ምን አይነት ጥልቅ ስሜት እና ፍቅር እንደነበራቸው እንረዳለን :: እውነትም የድሮዎቹ ስራዎች ኃይል ነበራቸው :: ቁምነገር ያውቃሉ :: ያነቃሉ !

እስቲ እቀጥላለሁ :: ማለፊያ ጽሁፍ ነው ውቃው ! አሁንም ኢንላይትንመንት ያስፈልጋል :: የሚያነቃ !

ናፖሊዮን ዳኘ ::

ዉቃው እንደጻፈ(ች)ው:
መቅባጠሪያውን ጂንየሱ ዋናው ሲፈጥረው ...ርዕስ የለውም ..እዚህ እዚያ እንዲቀባጠርበት ለራሱ አመቻችቶ ፈጥሮታል :: እኔ በግድ .....ጣልቃ ገብቼ እቀባጥራለሁ :: ዕዳ እኮ ነው !

ስለዘመነ ኢንላይትመንት ያውቅኩት ኮሌጅ የወርልድ ሂስሪ 1 2 ምናምን ክላስ በግድ ሰወስድ ነበር :: ዘመኑ አስራስምንተኛው ክፍለዘመን ነበር አሉ :: ዝርዝሩን ግን አሁን ረሳሁት ::

በኢትዮጵያ ደግሞ ኢንላይትመንት የጃንሆይ ኃይለስላሴ ዘመን መሆኑን ለራሴ አምኜ እኔ የደርጉ ልጅ ተቀብያለሁ :: ክላሲክ ዘመን ..ክላሲክ ጸሀፊያን ...ክላሲክ ደራሲያን ....ክላሲክ ምሁራን ...ካልሲክ ፖለቲከኞች ...ምኑ ቅጡ ...ዘመኑ ልዩ ነው ... ነበርም ::

ጠዋት ስራ ስሄድ ..በመኪናዬ ለግማሽ ሰዓት ሰዓታትን እየሰማሁ ነው :: ግዕዝ ...አይገባኝ አልገባው ...ግን ግዕዝ .......ከትራፊክ ጃሙ ..ከሎካል ሬድዮ ከንቱ ልፈፋ ...በረዶ ጸሀይ ግለት ዝናብ ማስፈራሪያ ... ቅራቅንቦ ጂኒ ጃንካ ...ምናምኑ ....እኔ አባ ዉቃው ...በተመስጦ ....ነጉዳለሁ :: አዕምሮዬ ወስጥ ያለውን የክሬዲት ዕዳ ..ስቱደንት ሎን ...ጃብ ሴክዩሪቲ ...ሞርጌጅ ....ህመም ...ጭንቀት ..ዋርካ ...ዋናው ...ኮንጂት ...ሙዝ ...ህመምተኛው ወንድሜ ...ምስኪን እናት ...አሪፍ አብሮ አደግ ጓደኛ ..እንጀራ መግዛት ...እሙሙ ...ሁሉም ....ይጠፋሉ :: ሰዓታት !

ስለእምነታቸው መንኩሰው የሞቱት አያቴ በመቶ ምናምን አመታቸው በተስኪያን ..ሲሄዱ ..ጎናቸው ስከተል ...ምዕመን ባክብሮት ሰላም ሲላቸው ...መንገዱ ...ሰላሙ ..ባህርዛፉ ....ዳገቱ ...የጉልላቱ ሽውሽውታ ....የኔብጤው ...ቄጠማው ...የጠጅሳሩና አሪቲው ሽታ .... በምናብ ይመጣል :: ከትከሻዬ / ማዥራቴ ላይ ተጋግሮ የነበረው የማላውቀው ክባድ ነገር በኖ ይጠፋና ..ስራ የፋይቭ አወሩን ኢነርጂ ድሪንክ እንደጠጣው ሆኜ እከስታከሁ :: እንዴት ? አላውቅም ..አራት ነጥብ

_________________
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዉቃው

ዋና ኮትኳች

Joined: 07 Jan 2007
Posts: 970

PostPosted: Tue Feb 14, 2012 6:29 pm    Post subject: Reply with quote

ግሬይ ጉሴን አንጠፈጠፍኩና ጥቂት ጎንጨት አልኩለት :: አዎ .ዛሬ ...ብዙ ለማሰብ ጠንክር ያለውን መጎንጨት አለብኝአለኩ ለራሴ :: ትክክለኛ ውሳኔ ቢሆንም ቮድካው አልቋል :: ባለፈው ዓመት ያልተከፈለ የገቢ ግብር አለብህ ብሎ .ለማስከፈል ... አይ አር ኤስ ... የላከልኝን ማስጠንቀቂያ ይዤ መጸዳጃ ቤት ተሰየምኩ :: ገንዝቡን ብከፍልም ..የማስጠንቀቂያው ሀተታ ግን አንብቤው እስካሁን አልወጣልኝም :: የተመረጥከው ራንደምሊ ነው ይላል :: "ሎተሪው " ብዙ ሚሊየነር ባለእዳዎችን አልፎ እኔን ወደደ :: ባጭር ቃል በየአመቱ ከሚወጣው የአይ አር ኤስ የእዳ ዕድል . መካከል ... የሁለት ሺህ አሳራ አንድ አሸናፊዎች ውስጥ ካሉበት አንዱ ሆኛለሁ :: ጃክ ፓት ..ሜጋ ሚልየን ...ስማችሁን ቄስ ይጥራው !

ጉዳዬን ከመጸዳጃ ቤት ጨርሼ ..ሶፋው ላይ ተኮፈስኩ :: ሀሳቤ ወደ ሜገን ተፈተለከ :: ሰሞኑን እንጣጥ እንጣጥ ማለት ያበዛችበትን ምክንያት አሰላስል ገባሁ :: እንዴት እንዴት ነው የሚያረጋት ?! ከመጠን በላይ የሁሉንም ወንዶች አትኩሮት መሳብ ትፈልጋለች :: ህጉ ..የኤቲክሱ ወይም የሴክሹዋል ሀራስመንቱ በሉት ....ስሙ ጉዳዬ አይደለም ..ብቻ ለአለባበስ ደንብ አለው :: ለሜገን ብቻ ..የወስጥ ሱሪዋ ሊታይ ጥቂት ሲቀረው የተሸፈነ ቀሚስ ለብስሽ ስራ ነይ የሚል ፈቃድ የለውም :: ስራ እኮ ናይት ክለብ አይደለም :: ግን ደግሞ አይደለም መናገር አተኩሮ ማየት ሴክሹዋል ሀራስመንት ነው በተባለበት አገር ..አላየነም አልሰማንም ብለን ቁጭ ብለናል .. ! እሷ ዞር ስትል ....ወሬው ስለጭኗ ነው ...ወሬው የለበሰቸው ተብሎ ስለሚገመተው ቶንግ ነው .....ወሬው ምንም ነገር ከውስጥ አላረገችም ነው ..ወሬው እሙሙዋ ነፋስ እየመታው ነው እኮ ይሆናል :: እሷ ብቅ ስትል ....ዝም ! አንዳንዴ እኮ ግራ ይገባኛል ! ያለነው አዳምና ሄዋን ይኖሩበት የነበረው ገነትም ነው እንዴ ! በለሷ ከተቀመሰች ወዲህ እኮ ራኡትነታችን ታውቆ መልበስ ጀመረናል :: አሁንማ ...ሜገን ..ነገ ስራ ራቁቷን ብትመጣ ..አባቡዬ የሚቆም አይመስለኝም :: ተፈጥሮዬን ደብቄ የገነቱን አዳም ሆኛለሁ :: መጠጡ አልቋል :; አሁን ጸልዮ መተኛት ...የቀኑ ኃጢያቴ ቢስተሰረይ !

ግን ምን ዋጋ አለው እየሱስ ስድ ...ነብዩ መሀመድም ሸሌ ተብለዋል :: እምዬ ማሪያምና ...ታላቁ አላህ ..ክብራቸው ተዋርዷል :: ለማን ይስተለያል ? ግና ጌቶ ሜንታሊቲ ድንቁርና ነው :: ጥቂት እውቀት ደግሞ ...ኡህ ....እሱ ደግሞ እጅግ የባሰ መጥፎ ድድብና ነው :: መሃይምነትና ድድብና ደግሞ ...ፈጽመው ይለያይሉ :: አሁን የገጠሙን ከመሃይመነት የተላቀቁ ደደቦች ናቸው :: መድረኩ ለጌቶ ሜንታሊቲዎች ስፍራ ሲፈቅድ ለቅቆ መሄድ ግድ ይላል :: በነባራዊው ህይወትም ያለው ይሄው ነው :: ከሚመስልህ ጋር ትውላለህ ::
_________________
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8  Next
Page 7 of 8

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia