WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home | About us | Advertise with us | Contact us
የዳሞት ግጥሞች
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 56, 57, 58, 59, 60, 61  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ኦኑፈያሮ

ኮትኳች

Joined: 04 Aug 2005
Posts: 166

PostPosted: Sat Apr 02, 2011 10:25 am    Post subject: Reply with quote

ሠላም !የአንድነት ዋርካ በትዝታ ሜዳ የተኖረለታ

ሠላም የደስታ ምንጭ የመኖር አለኝታ

ቢጠጡት የማያልቅ የዘላለም ውሃ

ሠላም የውበት ምንጭ ደግሞም የፍሰሃ

ሠላም አብነት ነው መርምሮ ላወቀው

ለሕሊና ጭንቀት የልብ ዕረፍት ነው

የማስተዋል ጎጆ የጥበብ ጎዳና

ሠላም ድምቀት አለው ግሩም ንጽህና

የድህነት አውታር የመኖር አለኝታ

የትብብር ጽዋ የተስፋ ገበታ

ሠላም ለሠው ልጆች የዘላለም ደስታ

የጸና ግንብ ነው ደግሞም ያለም ዋልታ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ኦኑፈያሮ

ኮትኳች

Joined: 04 Aug 2005
Posts: 166

PostPosted: Tue Apr 19, 2011 7:01 am    Post subject: Reply with quote

ኢትዮጵያዊው አፈር አንተ የናሳው ጀግና

ሞትን ለምን መረጥክ ሥራ እያለህ ገና

ቸክችከህ ቸክችከህ በመመራመሪያው በወረቀትህ ላይ

የንድፍህን ውጤት አዲስ መገረሚያ ድንቅ ነገር ሳናይ

አንተ ያበሻ ፈርጥ አንተ የናሳው ጌታ

ለምን ተለየኸን እንደ ቀልድ በዋይታ

ቅጣው ተባልክ እንዴ ባዘን ያዳምን ዘር

በቅርጫት ኳስ ሰበብ የተጓዝክ ወዳፈር

እንግዲህ ማን አለን አንተን ተመስሎ የሚያስጠራን ባለም

መንኮራኩር ሰርቶ ጨረቃ አናት ደርሶ ስለ እኛ የሚያልም

ማን አለን ያላንተ ያፍሪካ አባውራ ቁንጮ የሚያደርገን

ያው ካንተ ቀብር መልስ ወገን መግቢያ ጠፍቶት ጎርፍ አጥለቀለቅን

አንተን የመሰለ የምርምር ንጉስ የምርምር ጌታ

ነፍስህን እንዲምር የሠራዊት ጌታ

ከመለመንና ከመጸለይ ውጭ ጧትም ሆነ ማታ

አቅሙ ስለሌለን ሸኘንህ በዋይታ

አቅም የለን እኛ ናሳን በግሩ አቁመን አለምን ማስገረም

ላሳር ከቅጣው ውጭ እንዳንተማ የለም

የተረገመ ኳስ የሚነጥርበት የቅርጫት ጨዋታ

አንተን አስቀረብን እንደ ቀልድ በዋይታ

እንደሚወራው ግን ላንተ ሕይዎት መጥፋት የሠው እጅ ካለበት

ሠማይና መሬትን የፈጠረ እግዚያብሄር ያለርህራሄ እጥፍ ይፍረድበት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ኦኑፈያሮ

ኮትኳች

Joined: 04 Aug 2005
Posts: 166

PostPosted: Thu Apr 21, 2011 2:32 pm    Post subject: Reply with quote

የተኮነነች ጻድቅትየገጠሯ እመቤት ችግር ያጎደፋት
ለሲኦል የሾማት ከጽድቅ የገደፋት
እድል አለቅልቆ ከሠው ታች የደፋት
ለግረት የሾማት ማዳት የሸለማት
ያች የትዳር ሰማት
ሆድ ለጀርባ ሆነን ዛሬ ብርቃትም
በስም በስል እንጅ ባካል ባላያትም
ያው ትታየኛለች የገጠሯ ቆዲ
ቀሚሷ ቡትቶ መቀነቷ ጋዲ
ያችዋ አይኔ አንዳንዴ ያያታል ፈልጎ
እንደውል ክፉ ልጥ ቆዳዋ ጠውልጎ
የረሀብ ምች አዝሏት አንጀቷ ተልጎ
ያው እምባ ስትዘራ ብሶት ስታዘምር
ድህነትን ልትንድ ድካም ስትከምር
ያልጸደቀች ጻድቅት በሆድዋ ነፍሰጡር በወገቧ እመጫት
እየው ደሟ ሲፈስ አጋሙ ሲቆርጣት ጋሬጣው ሲነጫት
እከክ ችፌ አጥቅቷት ቅማል ቅጫም ወርሷት
ችግር በጥፍሩ አንቋት ችጋር ባፉ ጎርሷት
ይኸው ዛሬ ደግሞ ተነስታ ማለዳ
እሩቅ ከወንዝ ወርዳ ውሃ ልትቀዳ
ትልቁን ማድንጋ አንግታ በጠፍር
እይዋት ስትራመድ እግሯ ቁር ሲደፍር
ከዚያ ስትመለስ ላሞች አገናኝታ
ባሏን ቁርስ አብልታ ቤት ጋጡን አጽድታ
ወዲያው ነፍሷን አጥታ ቁልቁል ስትጋልብ
እንጨት ትወርዳለች እሳት ልትቀልብ
እየው ያች ጻድቅት ሳትውጥ ምራቋን
ጅጇን እያጠባች እረፍትም ሳያምራት
ለጉዳቷ ካሳ ለግብሯ ወሮታ ለጽድቋ ብድራት
ምሳ አቆየሽ ብሎ ባል እንዳይወግራት
ጊዜው በመርፈዱ ልቧን ገብቶት ፍራት
ማሳ እየጋገረች ደግሞ ለማት እራት
ጥሬ በቆሎዋን አቅርባ በቁና
ቅንጨ ለመከካት ወፍጮዋን ደቅና
ልጇን ተሸክማ ነውና ግዳጇ
ወፍጮ እየዛወረች ገል በመሰለ እጇ
ብሶቷን ስታዜም ያቻት ከነ መጇ
እንዲህ ስትዋትት ለራቧ ማብረጃ
አንድ ዝግን ጥሬ መቆርጠሟን እንጃ
እዚህ እሩቅ ሆኘ አትኩሬ ሳያት
ኑሮዋ አልተሻለም ከሷ እናት ከኔ አያት
እንጀራ ጠፍቶባት እንዲህ ስትባዝን
አንጀት ስትበላ እይዋት ስታሳዝን
2000 አመት እንዲህ ስትኖሪ
ማዘር ባንች ላይፍ አይ አም ቬሪ ሶሪ
ጥሬ እያረረብኝ በንዲህ ያለ ግረት
ቆመሽ መላወስሽ ጠንካራ ነሽ ብረት
በፈረንሳይ በህንድ ባሜሪካን አገር
ሮማ ብንወጣ ኩባ ብንሻገር
ስሙ በጠፋበት ፖቨርቲ ሐንገር
እንደዚህ እንዳንች ቆዳው እስኪከስል
ቀን ሌቱን ግሮ ነፍሱ እስክጸላሰል
ችጋር ያማቀቀው ቅጫም የወረሠው
በፈረንጆች ሃገር አይኖርም አንድ ሠው
ግን አንድ ቀን ድንገት ትግስቷ ቢሟጠጥ
ወደኋላ አትልም ሃቁን ለማፍረጥረጥ
ኧረ ለመሆኑ ልጄ ሆይ ምን አልኩህ
መጣፊያና ክርታስ አስይዠ የላኩህ
የተደበቀውን የመሰልጠን ጥበብ
ከሠው በመጠየቅ ከመጣፍ በማንበብ
ብላቱን ዘዴውን በወረቀት ጥፈህ
የችግር መዳኒት በለሲቱን ቀጥፈህ
አምጥተህ አገር ቤት ከትውልድህ ሠፈር
እንድታለማይ እዚህ በኛው አፈር
ይህን ያህል አመት በመማር ስትፈጅ
ሞፈር መብሳት ሳትችል መኪና ሳታበጅ
እራስህን ጠልተህ እንድትሆን ነው ፈረንጅ ?
አየ አለመታደል ድካሜ እሳት ገባ
ዘላለምክን ታዝለህ በምጽዋት አንቀልባ
አዎ ያቻትና የሷ ድንቁርና ከኔ እውቀት ባይብስም
ግረቷን እየጋርኩ ላቧን ባላብስም
አዎ እጠራታለሁ አውቃታለሁ በሥም
ጠረኗን እንድምግ ወተቷን እንድጋት
እሷ እንዳልሸሸችኝ ያኔ ስፈልጋት
ዛሬ አለሁ ባልላት እሷ ስትፈልገኝ
ኑሮዋ ሞቶባት ለቅሶዋ ባልገኝ
እንዳዘለች ጡሬ ብድር ባልመልስም
ጉድጓድ እስክገባ መቸ እረሳታለሁ
ጻድቋን ተኮናኝ በሥም አውቃታለሁ
ያቻት ያች ግልቱ በሩቅ አያታለሁያች
ያች ያልጸደቀች ጻድቅት ያች የወላድ መካን
ያች የኑሮ ካስማ ያች የሃዘን ድንኳን
ያሳር ካብ ተጭኗት ቁጣ Rእት ሥማ
ኑሮዋ ሞቶባት ሙሾ ስታሰማ
ከባህር ተጠምቶ ሲተርፉት ተርባ
ወርቀዘቦ እያላት ያዘን ማቅ ደርባ
ያቻት ከማጀት ውስጥ ከተራራው ጀርባ
እግሮቿን አጣሟት የውርጩ ቁርጥማት
አንጀቷን አድፍሯት የበረሃው ጥማት
ያችው ከሳቱ ላይ ጠቁራ እንደ ድስት ጥፊያ
ያችው ከማጀት ውስጥ ከስላ እንደ መጋፊያ
ገላዋ ለስልሶ አልባሷ ባያምርም
እናቴ ለማለት አንደበቴ ቢያፍርም
ያቻት ምስሏን መስላ አመዳይ አጥልቋት
ስትል ክስም ክስም በግር ባልመስላት
ድራቷን ባልከፍልም
አውቃታለሁ በሥም
ከቤት ሳይሞላላት ከደጅ ላታስታጉል
ያቻት ከማሳው ውስጥ አረም ስትጎለጉል
.................................

...................................
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ኦኑፈያሮ

ኮትኳች

Joined: 04 Aug 2005
Posts: 166

PostPosted: Thu Apr 21, 2011 3:22 pm    Post subject: Reply with quote

ያበሳ እዳ አጥልቋት እስካንገቷ ድረስ
ብታረጅ አትጦር ብትወልድ አትታረስ
እርቧት ስትበላ አሟት ሳትታከም
ያቻት ከቃርሚያው ውስጥ ነዶ ስትሼከም
የቆላ አራሙጫ የበጋ ትኩሳት
አናቷን የዋይ ዶፍ እግሯን የሼዋ እሳት
ንፍርም ፍምም ሆኖ ቆልቶ እየጠበሳት
እንጨት ትሰብርና ድብሏን አንግባ
ትንፋሽዋ እስኪቆረጥ ሲንቆረቆር ላቧ
ዳገቱን ስትሮጥ በጊዜ ልትገባ
ስለቷም ባልጩት እግሯን ቢበሳት
እዩ ያች ደሐ ጥቁር ደም ሲፈሳት
ከዚያ እልፍ ስትል ነገር ሲፈልጋት
ከታች ተቀብሎ ያጋም እሾህ ወጋት
እቤቷ ስትደርስ በሁለት እግር አንክሳ
ደም የሚያዠው ቁስሏን በሞራ ተኩሳ
አመድ ደምድማበት በማበሻ ጠብሳ
የደፈቃትን ላብ በቀሚሷ አብሳ
እንዲህ ስትዋትት ለራቧ ማብረጃ
አንድ ዝግን ጥሬ መቆርጠሟን እንጃ
ለሠው ቀን መሽቶለት ማታ ቀን ሲጨልም
በንቅልፍ እፎይ ብሎ ብሩስ ተስፋ ሲያልም
እንደዳፉር ጋንጩት ብቻዋን ተቀምጣ
ያቻት ከምድጃ ዳር መጄሌ ስታበስል እሾህ ስታወጣ
ሁሌ ማታ ማታ እሷ እንቅልህ አታውቅም
ስትባዝን ውላ በተረፈ አቅም
የልጆቿን ልብሶች ሰብስባ ስጠቅም
ወይም እፎይ ብላ ከምታንቀላፋ
እንዝርቷን አብጅታ ባዘቶዋን ነድፋ
ያች የቀየዋ አድባር የቤቱ መጋቢ
ፈትል ትፈትላለች ለራሷ ነጠላ ላባውራው ጋቢ
ያች ችግር ገቢ ያች የሳት ማንኪያ
አንዴ ብትሰበር የለላት መተኪያ
ያች የሠው ውርጋጥ ያች የኔ መሳቂያ
ያች ገበና ከታች ሚስጥር መደበቂያ
ቢሰድቧት አትመልስ ቢስቋት አኩራፊ
ሱሷ ጥረት ግረት ምሷ የባል ጥፊ
የሕይዎቷ ቅመም የእንባ እንጥፍጣፊ
ማጌጫዋ ማዲያት ምግቧ ትርፍራፊ
ነጭ ላብ አፍስሳ ጥቁር መልክ አትራፊ
መጠሪያዋ ደዌ ቀብሯ ባንድ እራፊ
እዚህ እሩቅ ሆኘ አትኩሬ ሳያት
ኑሮዋ አልተሻለም ከሷ እናት ከኔ አያት
እንጀራ ጠፍቶባት እንዲህ ስትባዝን
አንጀት ስትበላ እዮዋት ስታሳዝን
ግን አንድ ቀን ድንገት ትግስቷ ቢሟጠጥ
ወደኋላ አትልም ሃቁን ለማፍረጥረጥ
ገላህ ስለናቸ ያለህ ቢመስልህም
እንደተቀጽላ ከታች ሥር የለህም
በማይሰምር ምኞት ልብህ ተንጠልጥላ
ከሥር ሥር ሳጸድ ከላይ ሳትሆን ጥላ
ሠው እየተከተልክ አንተ ሠው ሳታክል
የደረቀ ለታ የለጠፈህ ተክል
ዛፍ ሆነህ ሳጸፋ ዘር ሆነህ ሳትበቅል
ወድቀህ ትቀራለህ እንደ ሰባር ቅል
እኔ ግን ኮስምኘ ገላየ ቢደቅም
ስሬ ስር አውጥቶ አይደርቅም
ደግሞም ሰምቻለሁ የንሳሃ አባቴ
መጣፉን አምጥተው ዘርግተው ከፊቴ
የግዚያብሄርን ትዛዝ ምንጭ ሳያዛቡ
እንደተረዳሁት መንፈሴ እንዳወቀው
በሥጋው ተጉላልቶ በነፍስ የሚልቀው
በምድር የራበው ነው በቁሙ ያነባ
ዘላለም የሚስቅ ሰማይ ቤት ሲገባ
ትለኛለች ደፍራ አውቃለሁ አመሏን
ልቧ ቅሬታ ሲያዥ ሲጓጉተው ቁስሏን
አዎ ያቻትና የሷ ድንቁርና ከኔ ወተት ባይከስም
ግረቷን እየጋርኩ ላቧን ባላብስም
አዎ እጠራታለሁ አውቃታለሁ በሥም
ጠረኗን እንድምግ ወተቷን እንድጋት
ዛሬ አለሁ ባልላት እሷ ስትፈልገኝ
ኑሮዋ ሞቶባት ሃዘኗ ባልገኝ
እንዳዘነች ጦሬ ብድር ባልመልስም
እንደ ልጅ ልመረቅ ጉልበቷን ባልስምም
ጉድጓድ እስክገባ መች እረሳታለሁ
ጻድቋን ተኮናኝ በሥም አውቃታለሁ
ያቻት ያች ገልቱ በሩቅ አያታለሁ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ኦኑፈያሮ

ኮትኳች

Joined: 04 Aug 2005
Posts: 166

PostPosted: Tue May 10, 2011 3:13 pm    Post subject: Reply with quote

ጩኸት !

አልጋው ተጨነቀ

አለ ቋቋ ቋቋ

ብሶቱን ለማውራት

እያጠረው ቋንቋ

ወይም ከሚስቲቱ

ወይ ከባልየው

የሚሰማ ጠፍቶ

ጩኸቱን የሚሰማው

ሁሉም ባዲስ አለም

ጭልጥ ብለው ሄድው

የፈለገ ቢጮኽ

ማንስ ሊያዳምጠው

ምናልባት አንድ ሠው

ግድግዳ ለግቶ

ቢደርስለት እንጅ

ኡኡታውን ሰምቶ

በርግዶ ቢገባ

ወይም በር አንኳኩቶ

ወይም በፍቅር

ወይ በዱላ ነርቶ

ካልገላገለው በቀር

ጉዳቱን አውቆለት

ምንም ዋጋ የለው

የደንቆሮ ጩኸት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ኦኑፈያሮ

ኮትኳች

Joined: 04 Aug 2005
Posts: 166

PostPosted: Tue May 17, 2011 3:09 pm    Post subject: Reply with quote

የልጅ ጥሮተኛ !

አቅሙ የደከመ አንዳች ሳይሰራ

ታታሪ ለወሬ ተግባር የሚፈራ

መሆንን የማይችል መስሎ የሚኮራ

አዎንታ እርቆ አሉታ እሚዘራ

እራሱን ዘንግቶ ስለ ሠው እሚያወራ

ለፍቶ መለወጥን አምርሮ እሚጠላ

ማረፍ የሚፈልግ በሌሎቹ ጥላ

መደበቅ የሚሻ በብርቱዎች ከለላ

ያለድካም ሚመኝ ምቾትና ተድላ

ያን አፍላ ጉልበቱን አቅፎ የሚተኛ

ሳይሰራ መክበርን የሚሻ ሕልመኛ

ያለድጋፍ መቆም የማይችል ጉደኛ

በዎላጅ እርዳታ የሚኖር ጉረኛ

መሥራት እየቻለ የሠው እጅ ጠባቂ

ሃብት ብልጽግናን ሳይሰራ ናፋቂ

በቤተሰብ ትከሻ ተንጠልጥሎ ኗሪ

የልጅ ጥሮተኛ አርጎታል ፈጣሪ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ኦኑፈያሮ

ኮትኳች

Joined: 04 Aug 2005
Posts: 166

PostPosted: Sat Jun 18, 2011 6:59 am    Post subject: Reply with quote

መድሃኒት አለው ዎይ የሥልጣን በሽታ
የዳነ አላየሁም የማታ የማታ
ካላንገላዎደ አውርዶ ካልጣለ
ከስልጣን በሽታ የዳነ የታለ ?
ኧረ አሁንስ በቃኝ ይከተል ተረኛ
አያሰኝም እኮ የሥልጣን መጋኛ
ልቡ የቆሰለ ብሎ ሲነሳ
መግቢያ መውጫ ማጣት ያኔ ነው አበሳ
ጆሮን ይደፍንና አይኑንም አውሮ
አይሰማ አያዳምጥ የሕዝቡን ሮሮ
ችግርና ግፉ እጅግ የበዛበት
ልክ እንደ ማእበል ሲወጣ ባንድነት
መድፍና መትረየስ ታንኩ ቢብተለተል
ከሥልጣን በሽታ የዳነ ሠው የታል
ይኸው አየናቸው ተዋርደው ሲረክሱ
በቃን ቢሉ ኖሮ ከዚህ ባልደረሱ
የሥልጣን በሽታ ያደርጋል ወራዳ
እያንደፋደፈ በቅሌት በረንዳ
በግልጽ በደንብ አይተን እንረዳ
እስቲ አምባገነኖች ባግቦን ተመልከቱ
የታሪኩን ምሁር ባለዶክትሬቱ
በክብር ቢለመን እምቢ በማለቱ
የሥልጣን በሽታ እያንደፋደፈ
በከንቱ ተመትቶ ተይዞት ታረፈ
ይኸው ጋዳፊንም እያንፏቀቀው ነው
ሳይገድል የማይለቅ መጥፎ በሽታ ነው
ሠውነትን ሁሉ በጣም ያከረፋል
አይዞህ ያለው ሁሉ ካጠገብ ይጠፋል
እንደው ጥርስን ነክሶ በቃኝ ካለማለት
ለስልጣኝ በሽታ የለውም መድሀኒት
ለሃገር ለወገን ለመፍጠር ሠላም
ከበቃኝ በስተቀር መድሃኒት የለም
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ኦኑፈያሮ

ኮትኳች

Joined: 04 Aug 2005
Posts: 166

PostPosted: Sat Jul 02, 2011 3:02 pm    Post subject: Reply with quote

እናት ዓለም !

ግርማ ሞገሴ ነሽ እምዬ እናቴ
ስራብ እንጀራየ ስጠማ ወተቴ
ያኔም ነሽ ኩራቴ ዳግም ነሽ ኩራቴ
የብርሃንሽ ጸዳል ለሠራ አካላቴ
መቼም እወድሻለሁ እስከለተ ሞቴ
ሳለሁ በዝች አለም አለኝ የምለው ሠው
ከፈጣሪ በታች እናቴን ብቻ ነው
ጋሻ መከታዬ ውበቴ ስስቴ
አምሳያ የሌለሽ ብቸኛዋ እናቴ
እንደዚህ እላለሁ ፈጣሪ አምላኬን
ምኞቴን ተረድቶ ከሰማው ጸሎቴን
አኑራት እላለሁ እማምዬ እናቴን
ከልቤ ማህደር መቸም የማልፍቅሽ
አንችን መሳይ ፍጡር ወደር አቻ የሌለሽ
ፍቅርና ደግነት ፈጣሪ ያደለሽ
[/u]ውበት የተሞላች እጅጉን ያማረች
ቸርነት ተላብሳ ፍቅርን ይዛለች
ከአለም እስካለም ዝናዋ ይሰማ
የትም አይገኝም ከቶ እንደ እማማ
ለራሴ ሳትይ እራስሽን ጥለሽ
እሩህሩህ ለልጅሽ የሚጣፍጥ ፍቅርሽ
እንደዚህ እላለሁ ፈጣሪ አምላኬን
ምኞቴን ተረድቶ ከሰማው ጸሎቴን
አኑራት እላለሁ እማምዬ እናቴን
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዋኖስ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Nov 2004
Posts: 1571
Location: Mars

PostPosted: Sat Jul 02, 2011 4:41 pm    Post subject: ሰላም Reply with quote

አሜን ::

ጸሎተሕ ተሰምቶ እንዲኖሩ እማማ :

ከእርሳቸዉ ልብ -ዉረስ :

ሩሕሩሕ ሁን አንተም : ተሳሰር በመንፈስ :

ከአምላክሕ ተስማማ ::ከመልካም ምኞት !ኦኑፈያሮ እንደጻፈ(ች)ው:
እናት ዓለም !

ግርማ ሞገሴ ነሽ እምዬ እናቴ
ስራብ እንጀራየ ስጠማ ወተቴ
ያኔም ነሽ ኩራቴ ዳግም ነሽ ኩራቴ
የብርሃንሽ ጸዳል ለሠራ አካላቴ
መቼም እወድሻለሁ እስከለተ ሞቴ
ሳለሁ በዝች አለም አለኝ የምለው ሠው
ከፈጣሪ በታች እናቴን ብቻ ነው
ጋሻ መከታዬ ውበቴ ስስቴ
አምሳያ የሌለሽ ብቸኛዋ እናቴ
እንደዚህ እላለሁ ፈጣሪ አምላኬን
ምኞቴን ተረድቶ ከሰማው ጸሎቴን
አኑራት እላለሁ እማምዬ እናቴን
ከልቤ ማህደር መቸም የማልፍቅሽ
አንችን መሳይ ፍጡር ወደር አቻ የሌለሽ
ፍቅርና ደግነት ፈጣሪ ያደለሽ
[/u]ውበት የተሞላች እጅጉን ያማረች
ቸርነት ተላብሳ ፍቅርን ይዛለች
ከአለም እስካለም ዝናዋ ይሰማ
የትም አይገኝም ከቶ እንደ እማማ
ለራሴ ሳትይ እራስሽን ጥለሽ
እሩህሩህ ለልጅሽ የሚጣፍጥ ፍቅርሽ
እንደዚህ እላለሁ ፈጣሪ አምላኬን
ምኞቴን ተረድቶ ከሰማው ጸሎቴን
አኑራት እላለሁ እማምዬ እናቴን
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋኖስ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Nov 2004
Posts: 1571
Location: Mars

PostPosted: Fri Jul 08, 2011 3:09 pm    Post subject: ሮሮ "ፌዝ -ቡክ " Reply with quote

ሮሮ "ፌዝ -ቡክ "
ገምሶና አለስልሶ መሬቱን ገበሬ፤

ያዘጋጃል ለዘር ለጤፍ፣ ለበርበሬ።

ጊዜና ወራቱን "በልጉን " ቀን ጠብቆ፣

“አደራ !" በማለት
ከሠማይ "ዶልዷሌን " በአንድ ዓይን አጮልቆ፣

ዘር ዘርቶ ይገባል፤ በሰኔ በሐምሌ ከጭቃ አጣብቆ፣

የነገዉን ተስፋ፤ ቡቃያዉን ሽቶ፣ አዲስ ትዉልድ ናፍቆ።

የአረም፤ የኩትኳቶዉ ወራቱ እንደባተ፣

ደፋ፣ ቀና ብሎ የአዲስ ሰብል መዓዛ ናፍቆ እያሸተተ፣

አረሙን፣ ተባዩን፣ አዕዋፍ - አራዊቱን ህሉን ተከላክሎ፣

በዓመት መጨረሻ ዓይን -ሆዱ ይጠግባል፤ ይደሰታል ዘሎ።

ይሕ ሁሉ መከራ፣ ! ሁሉ ሰቀቀን፣

በሌለበት አገር የክረምት ዝናቡ፣ የበጋ ሐሩሩ፣

የተዘሩ ልጆች ከእኛው ዉስጥ ማሕፀን፣

"የቴክኖሎጅ -አረም " የባሕል -ሽንቁሩ፤

ዘር እንዳያሳጣን፤ ለልጅ አስተዳደግ ምንድን ነው ? ምስጢሩ።
ዳሞት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋኖስ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Nov 2004
Posts: 1571
Location: Mars

PostPosted: Mon Jul 11, 2011 3:40 pm    Post subject: የዛሬ ሰዉ Reply with quote

የዛሬ ሰው :

ያለፈዉን ሲያመሰግን : ሲያደንቅ :

የዛሬዉን ሲያንቋሽሽ : ሲንቅ :

መጪዉን በጉጉት ሲናፍቅ : ሲጠብቅ :

ደስ ሳይለዉ : ተያይዞ መዉረድ መቅ ::

ዳሞት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋኖስ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Nov 2004
Posts: 1571
Location: Mars

PostPosted: Sun Jul 17, 2011 7:19 pm    Post subject: መንትዮቹ Reply with quote

መንትዮቹ :አንድ ማንኪያ ፍቅር፤ ዘጠኝ ስኒ ተስፋ፣

አንድ "ድርጎ " ፀባይ፤ ሳቅሽን ግን በአካፋ፣

ዝቀሽ ስጭኝና `ምከፍለዉ በኋላ፣

ላሳይሽ ምስጢሩን "የቅናትን ሒሳብ " የፍቅርን ፎርሙላ።

======//======ፀባይሽ፤

እምነ -በረድ አይደል፤ አልጠርብ በመዶሻ፣

ሥብራቱ አይታይ፣ አልወስድሽ ሐኪም ቤት፤ አልጠራ ወጌሻ፣

አላስተካክለዉ አልቀጥር "ኢንጂነር "

"ሰማዩ -አናጺ " የሰራሽን ነገር።

እንዲያዉ ፈጥሮ፣ ፈጥሮ፣

ጀምሮ ጀምሮ፣ ከዉስጥም ጀምሮ፣

ከላይም ጀምሮ፤ በጅምር ትቶሻል ሲያስበዉ ተማሮ።

=====//=====

ዳሞት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋኖስ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Nov 2004
Posts: 1571
Location: Mars

PostPosted: Mon Jul 25, 2011 2:19 pm    Post subject: የተስፋ ሥንቅ ! Reply with quote

"የተስፋ ሥንቅ !"ምላስ፣ ከናፍሬን እንደ "ጀላቲ " መጥጬ፣

ዓይኖቼ ዉኃ እንዳቆሩ፣ በምናብ -ዓለም ሰምጬ፣

ደረቅ -ሕዋ ዉስጥ ዓይኔን እንደጦር ሰክቼ፣

ላይከደኑም በልጥጬ፣

ድምፅ፣ ሳቅሽን ተርቤ፣

ጣፋጭ ሐተታ ጦማርሽን እንደጨረስኩ አንብቤ፣

“የተስፋ -ሥንቅ ! ብዬ አልኩሽ፤ በሐሳቤ፣

ቃለ -ጦማርሽ ፈዉሶኝ፤ ቋሳዊ -ፍቅርሽን አንግቤ።

ዳሞት

This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋኖስ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Nov 2004
Posts: 1571
Location: Mars

PostPosted: Fri Aug 19, 2011 2:36 pm    Post subject: ሰላም Reply with quote

ለመላው የዋርካ አፍቃሬ -ክርስቲያኖች ! እንኳን ለደብረ -ታቦር (ቡሄ ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ ::

ባለጠጎቹ :
የምንተነፍሰዉን ዓየር

ቢቸበችቡት ኖሮ በዶላር

ቆጣሪ በተከሉልን ከእንጥላችን መባቀያ ሥር ::

ከዚያም :

"እዘጋዋለሁ !" የሚለዉ ዛቻቸው

እየከፈልንም ገድሎ በጨረሰን ፍራቻዉ ::

ዳሞት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ኦኑፈያሮ

ኮትኳች

Joined: 04 Aug 2005
Posts: 166

PostPosted: Tue Sep 06, 2011 6:57 am    Post subject: Reply with quote

ለፈጣሪ የተጻፈ ደብዳቤ !

በሠማያት ያለህ በዐርያም
መልዕክቴ ይድረስህ መድህን የአለም
ሃጥያት እየሰራ ሠው ሁሉ እየዋሸ
ፍጥረት አዘነብህ በነጋ በመሸ
እንደ ሠው ጌታዬ ምድር ተበላሸ
በሃጥያት በተንኮል ተበላሽቷል ምድር
ይህን ተወውና አዲስ ነገር ፍጠር
ለሃጥያት ለበደል ሕዝብህ ተነሳሳ
በፈቀደው ሄደ ሕግህንም እረሳ
ፍርድህም ዘገዬ ሁኔታው ተዛባ
ሴት ከወንድ ቀርቶ ወንድ ከወንድ ተጋባ
ጽፈህ የሰጠኸን ሕግህም ተጣሰ
በሀጢያት በዝሙት ምድር እረከሰ
ክፋት ምቀኝነት ዝሙቱ ተስፋፋ
ትልቅ ሠው መካሪ አስታራቂ ጠፋ
በስምንተኛእ ሽህ አሁን ባለንበት
የወንጌል ሰባኪው የሀይማኖቱ ብዛት
በየአውራጎዳናው በየመንገዱ ዳር
ሳያውቁ ማጠንጠን ሳይማር ማስተማር
ለገንዘብ መገዛት በሀሰት መመስከር
ከዚህ ሁሉ ስቃይ ከዚህ ሁሉ ነገር
ምነው ብታደርገው አዲስ ቢሆን ምድር
ያኔ መጄመሪያ መሬት ስትፈጠር
አሸብርቃ ደምቃ ባረንጓዴ በሳር
በነጋ በመሸ ከጧት እስከ ማታ
ሕይዎት ያድስ ነበር የአበባው ሽታ
ሠው የሚባል ፍጡር በምድር ላይ ያለ
ደኑን መነጠረ ሳሩን አቃጠለ
አራዊቱን ሁሉ አሳድዶ ገደለ
በቆሻሻ ሞላ ዓለም ተበከለ
የሠው መጥፎ ሥራ አእምሮን አዙሮ
አለቀሰች ምድር ኡኡ አለ ተፈጥሮ
ብርዱ ቸነፈሩ ጩኸቱን አሰማ
በቆሻሻ ሞላ ወንዙ ሁሉ ገማ
ያኔማ በጫካው አእዋፎች ሲያፏጩ
ቁልጭ ጥርት ብሎ ሲንቆረቆር ምንጩ
ምድር ስትፈጠር ያኔ በፊትማ
ውሀው ሁሉ ንጹህ አየሩ ጤናማ
አሁን በዚህ ዘመን ተፈጥሮም ጨከነ
ነፋሱ መትረየስ ውሀው መርዝ ሆነ
የበሽታው አይነትኧረ ምኑ ቅጡ
ኤድስና ኮሌራው ትውከቱ ተቅማጡ
ተፈጥሮን የሠው ልጅ ስለተቃወመ
ተፈጥሮ ከሠው ጋር ጦርነት ገጠመ
እስቲ ልጠይቅህ አንተ መድህን የዓለም
ለምን ተቃጠሉ ገሞራና ሠዶም
ድንገት ሳያስቡት በሳት ውስጥ የቀሩ
ከዚህ የባሰ ግፍ እነሱስ ምን ሠሩ
ስለዚህ አንድየ አለሁኝ ካልክሳ
ሁሌ ዝም አትበል ድምጽህን አሰማ
እኔ ያየሁትን ይህንን ጽፌያለሁ
መልሱን ካንተ ደግሞ ቶሎ እጠብቃለሁ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 56, 57, 58, 59, 60, 61  Next
Page 57 of 61

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia