WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ETHIOPIAN FUN & ( .) ( .)
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 294, 295, 296 ... 311, 312, 313  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ደጉ

ዋና አለቃ

Joined: 15 Dec 2003
Posts: 5233
Location: afghanistan

PostPosted: Fri Sep 02, 2011 11:10 am    Post subject: (-: Reply with quote

....ውሻ ...ድመት ...እና የወንድ ልጅ አብሮ አደግ አንድ ምሽት ካምፕ ፋየር ዙሪያ ቁጭ ብለው ይጫወታሉ ....
...ውሻው የኔ ህይወት የተርገመ ነው ጌታዬ አመድ በተሞላ ሳጥን ውስጥ እንድቀመጥ (እንድጸዳዳ ) ያደርገኛል ...ሲል ድመት ተቀበለችና ምንም ማለት አይደለም ...የኔ ጌታ ለመቆፈር በማይመች አሸዋ ላይ ነው እንድጸዳዳ እሚያደርገኝ አለች ...ከዛ የወንድ ልጅ አብሮ አደግ በንዴት ግንፍል ብሎ ...ቢያንስ የናንተ ጌቶች ጭንቅላታችሁ ላይ የላስቲክ ከረጢት አጥልቀውባችሁ እስኪያስመልሳችሁ ድረስ ፑሽ አፕ አያሰሩዋችሁም ...!!! Twisted Evil Smile
_________________
" STUPID IS AS STUPID DOES " Very Happy
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ጁዲ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 30 Jun 2004
Posts: 77
Location: united arab emirates

PostPosted: Sun Sep 04, 2011 5:52 pm    Post subject: ምን ማለት ነው Reply with quote

ደጉ .. ደህና ነህ ? 40 ጊዜ እሚሆን ደጋግሜ አነበብኩት ግን አልሆን አለኝ የወንድልጅ ምን ነበረ እሚለው ተመልሴ ሄጄ ከማነብ የወንድልጅ ማደጊያ በቻ የሚለውን ምን ማለት ነው ጆኩ ምንም አልገባ አለኝ ....እና በናትክ ...
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
ደጉ

ዋና አለቃ

Joined: 15 Dec 2003
Posts: 5233
Location: afghanistan

PostPosted: Tue Sep 13, 2011 7:31 pm    Post subject: (-: Reply with quote

ጁዲዬ ሰላም ሰላም የኔ ቆንጆ ...የጻፍኩትን እኔ በመን መልኩ እንደማስረዳሽ ሳስብ 2 ሳምንት አለፈኝ ...እንደግና አንድ ሳምን ጊዜ ስጪኝና መልሱን አስቸኩዋይ እሰጥሻለሁ ...የደከምሽ እስኪ ፕራይቬትሽን ቼክ አድርጊ ...Smile
_________________
" STUPID IS AS STUPID DOES " Very Happy
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ደጉ

ዋና አለቃ

Joined: 15 Dec 2003
Posts: 5233
Location: afghanistan

PostPosted: Wed Sep 14, 2011 3:15 pm    Post subject: (-: Reply with quote

... እዚህ ዋርካ ላይ ያላየነው አይነት የሰው ችግር የለም ....ራሱን መግደል ለፈለገ ...በቀላሉ ሊሞትባቸው እሚችልበትን መንገድ ...በገመድ ...ወይ በክኒን ...ወይ ራሱን ገደል ወርውሮ ..ሌላም ካሰኘው ካራቴ እሚሞትበትን መንገድ ደከመን ሰለቸን ሳንል ህሳባችንን ለግሰናል ...
....ፍቅርም ያዘኝ ላለንም በቀላሉ እንደዛ አይነት አስቸጋሪ ፍቅር እሚላቀቅበትን መንገድ ሳንጠቁም አልፈን አናውቅም ...ከምር ብዙ ደጎች አለን ዋርካ ላይ ...እኔን ጨምሮ Wink

ስለ ፍቅር ሳነሳ ... ፍቅርና እኔ ስለ ግንኙንታችንን ትንሽ እንጫወት ...Smile
...መጀመሪያ ለማወቅ ያስቀደምኩትን ፍቅርን ሳይሆን ሴትን ልጅን ነበር ...ድሮ ምንም ሳላውቅ ፍቅር ከሴት ብቻ እሚይዝ ይመስለኝ ስለነበር ...Smile
..እናቴ አንድ ጊዜ መንገድ እየሄድን አይኔ አላርፍ ብሎ ዞር ብዬ የሆነች ሴት ልጅ ስመለከት የዛን ግዜ ገና ምንም አልጀመርኩም ...ግን ማየት ብቻ (ማየት ከጀመርኩ ቆይቼ ነበር ) ውሸት ምን ያደርጋል ...አለ አይደል ...ለጽጉራችን ለመልካችን ትኩረት እምንሰጥባት ጊዜ ነበረች ...ጸጉሬን አንዴ ካበጠርኩ .. ወንድ የሆነ ነክቶብኝ እምልባት ወቅት ...Wink አሁን በሰአት ለሚከፈለኝ ስራ እንኩዋን የዛን ያክል አልጠነቀቅም ነበር ...Smile
...እናም እናቴ ስትመክረኝ ..እንደ ታላቅ ወንድምህ እዛችም እዛችም አትበል ...አንድ ጸጉርዋ ረጅም የሆነች ..አረማመድዋ መልካም የሆነ መርጠህ እሱዋ ሁን ብላ የመከረችኝ ከጭንቅላቴ አልወጣ ብሎ ...ጸጉረ ረጅም ሳገኝ ..አረማመድ ይጎድላታል ....አንዳንዶቹማ መራመድ አይደለም ...መንገዱን ሁሉ እየ ለኩ (እየመተሩ ) ነው እሚራመዱት ..አረማመድዋ ቆንጆ ሲሆን ጸጉር እየጎደላት እስከ ዛሬ ፈላጊና ተፈላላጊ ሆነን ቀረን ...Sad
...ፍቅር አሁን ይዞኛል ...ፍቅር ብቻውን ማለት ቀላል ነው አደገኛ ፍቅር ነው የያዘኝ ...ታዲያ ችግሬ 20/ 80 መጠቀም እስኪያቅተኝ የተፈታተነኝ ...እውነቱን ለመናገር አሁን 80/20 ላይ ነው ... ማለት 80 ይወጣል ...20 ውጤት ይገኛል ....መሆን ያለበት 20 ወጥቶ 80 ያክል ውጤት ነበር መገኘት ያለበት ...Sad
....ከዚህ በፊት ከፍቅር ጋር ተያይዘን ተያይተናል ...እንተዋወቃለን ...በተለይ አንድ ጊዜ ሰው ተይዞበት ያየሁት የፍቅር አይነት ...እንኩዋን በወዳጅ በጠላት ላይ ደርሶ ማየት አልፈልግም ...Smile ከልቤ ነው እሱ ፍቅር አይደለም ... ስም እስካገኝለት ታገሱኝ Smile
...ፍቅር ለየሰው ሁሉ የተለያየ ነው .. እኔ በቀለም ጥቁርና / ነጭ ነው ...እኔ ድሮ አንድ ጊዜ የአይን ፍቅር እሚባል ይዞኝ አንጎል አድርጎኝ ነበር ...ከምር ስንት ቀን ምሳዬን ተቀጥቻለሁ ...Sad

...እመለስበታለሁ ጊዜ ሳገኝ
_________________
" STUPID IS AS STUPID DOES " Very Happy
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ጉዱ ካሳ

ኮትኳች

Joined: 22 Oct 2003
Posts: 431

PostPosted: Wed Sep 14, 2011 5:56 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ደጉሻ እንዴት ነህ ጃል ?! እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሰህ !

እረ ጁዲን ያልካትን አልገባኝም ምን ለማለት ፈልገህ ነው ፕራይቬትሽን ቼክ አድርጊ " ያልካት ? Smile ምን ይሻለኛል አንዳንዴ እኮ እንደ ውቃው ምንም አልገባኝ እያለ ተቸገርኩ !
_________________
ጉዱሻ
____________________________________
የምንወደውን ብንጠላ የምንጠላውን ብንወድ በራሳችን ላይ ከፍተኛ የሆነ የባህሪ ለውጥ አመጣን ማለት ነው!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ደጉ

ዋና አለቃ

Joined: 15 Dec 2003
Posts: 5233
Location: afghanistan

PostPosted: Wed Sep 14, 2011 8:11 pm    Post subject: (-: Reply with quote

ጉዱ ካሳ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ደጉሻ እንዴት ነህ ጃል ?! እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሰህ !

እረ ጁዲን ያልካትን አልገባኝም ምን ለማለት ፈልገህ ነው ፕራይቬትሽን ቼክ አድርጊ " ያልካት ? Smile ምን ይሻለኛል አንዳንዴ እኮ እንደ ውቃው ምንም አልገባኝ እያለ ተቸገርኩ !

...ጉዱ ጉዱ ...እንኩዋን አብሮ አደረሰን ወንድማችን ....! ለጁዲ በፕራይቬት የላኩላት የቃሉን ትርጉም ነው ...እዚህ ስላፈርኩ Embarassed
..አለገባ ያለህን ግን በዚህ አመት እንዲገባህ እናስገድዳለን ...Smile

_________________
" STUPID IS AS STUPID DOES " Very Happy
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ደጉ

ዋና አለቃ

Joined: 15 Dec 2003
Posts: 5233
Location: afghanistan

PostPosted: Wed Sep 14, 2011 8:58 pm    Post subject: (-: Reply with quote

...ፍቅር መቼ እንደ ጀመረኝ አላስታውስም ... ግን በጣም ትንሽ ሆኜ ስጦታ መስጠት እንደምችልበት ያወኩት ...አንድ ጊዜ የመጫወቻ ሽጉጥ ከመሬ አግኝቼ ምወዳት ልጅ በስጦታ መልክ የሰጠሁዋት በጣም ትልቁና የመጀመሪያ ስጦታዬ ነበር ...
...አሁን ካደኩ በሁዋላ ነው ለሴት ልጅ አበባ እንጂ ሽጉጥ እንዳምይሰጥ ያወኩት ...Sad
....ድሮ ማሞ እሹሩሩ ነበር ...አሁን እንደ ዘመኑ ዘፈን ፍቅር እሹሩሩ ..
....ከላይ እንደ ጠቀስኩት ...የእናቴ ህሳብ ጸጉረ ረጂም ..አረማመድዋ መልካም ...ጭንቅላቴ ውስጥ ሴቭ ተደርጉዋል ...እማልመውም እሱዋኑ ነው .....
...ይህቺን በጣም ወደኩዋት እና 20/80 መሆን ያለበትን ...80/20 አደረኩት ... ደግሞ ልጅትዋን እንዳጣት ትልቅ ምክንያት እየሆነ መጣ ...ያን ለማስተካከል ረጂም ጊዜ ፈጀብኝ ... አንዱ ትልቁ ችግር Trying to be "honest and sincere" with women. ሲሆን ሌላው ደገሞ ...Trying to get "slick" enough with her to be able to win her approval ይሄን እና ያን በመስሉ ነገሮች I am Looking for quick fixes...Wink
.... የቀረውን ለመለስበት ....Wink
_________________
" STUPID IS AS STUPID DOES " Very Happy
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ደጉ

ዋና አለቃ

Joined: 15 Dec 2003
Posts: 5233
Location: afghanistan

PostPosted: Mon Sep 19, 2011 5:56 pm    Post subject: (-: Reply with quote

...Being NEEDY ቶሎ ሴቶቹን መቅረብ እነሱ እኔ እማይፈልጉት መሆኑን ያወቁት በጣም ዘግይቼ ነበር ...በሌላው ነገሬ እኔ ጠዋት ጸህይ እስክምትወጣ እምትጠብቅ ሰው አይደለሁም ...Smile
...ብዙ ጊዜ ብዙ ወንዶች እኔን ጨምሮ በተለያዩ አጋጣሚዎች ፍጠን ብለን ሴቶች እንቀርባለን ...1 ወይም 2 ሰአት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በጣም ፍሬንድሊ ሆነን ለመገኘት እንሞክራለን ...ታዲያ ይሄ ሁኔታችን ሴቶቹን ..ተከላካይነት ፖዝሽን ላይ እንዲሆኑ እናደርጋቸዋለን ...እኔና የኔን መሰል ወንዶች በምናደርገው ድርጊት የሌሎቹን ወንድሞቻችንን ምሽት እናበላሻለን .. Very Happy እኔ ጎበዝ ከሆንኩ በሁዋላም የኔን ምሽት ያበላሹ ስላለኡ ነው ...አሁን ግን ንዴቴ በርዶልኛል Smile
.....ሴቶች ...ሴቶች ኮሚክ ፍጡሮች ናቸው ...አንዳንዴ ተኝቼ እንቅልፍ ልቤ ግራ ጎኔን ሲሰማኝ ...ፈጣሪ እንደግና ከግራ ጎኔ እምትሆነኝን እንደግና ሊሰጠኝ ነው ብዬ እንቅልፌን ጨርሼ አይቼ ያልኩበት ቀን ብዙ ነው ....ግን .. Crying or Very sad ማለት ራስህ ፈልግ መሆኑ ግልጽ መልስ ነው ...Wink
... የኛ ሴቶች /ሴቶች / ለመውቀስ ሳይሆን እሚሆናቸውን አያውቁም .... ድሮ በክረምት ጭለማ ሰፈር ውስጥ ስንሄድ ...ውህ የቁዋጠረ መሬት ለመዝለል ደርቁን ዘለን ውህ ውስጥ አርፈን አናውቅም ..?እነሱም እንደዛ ናቸው ...አንዳንዶቹ መወደዳቸው ሲነገራቸው ደህና የነበሩት ...ፈገግታቸው እነሱ አልፎ በአካባቢው ላለ ሁሉ እሚሆኑት ሁሉ ወዲያው ይቀየሩና መኮሳተርና መዘነጥ ይጀምራሉ ....አንዳንዶቹ ደግሞ እወድሻለሁ የእን በቀን ፍቅር ማረጋገጫ አድርገው ሲዜም መስማት እሚፈልጉ አሉ ....ሌሎች አይነቶች ደገሞ ...ቃሉ እውነትም ይሁን አይሁን ማመን አይፈልጉም ...ከበደ እወድሻለሁ ብሎ አታልዋት ነበር ...አሁን ሁሉም እሱዋ ከበደ ነው ...እምትሉት ነገር ቢኖር ከበደን ብታገኙት ...ድራሹን ነበር ...ግን ከበደ ስራውን ሰርቶ ሄዱዋል Evil or Very Mad
..... እኔ ሲፈጥረኝ መናገር አልችልም ነበር ...አሁን አሁን ግን መፈቀራቸው እንዲነገራቸው ለሚፈልጉ አሳምሬ እናገራለሁ ..ከልቤ :: ግን ውጤቱ እንደ አሰብኩት አይሆንም ...አንዳንዴ ድህና ገበያ አይገናኝም ...ሲነገራቸው ኩራት ለሚጀምራቸውም እየተናገርኩ ተቸገርኩ Very Happy
...ከልቤ አንድ ጊዜ ለሙከራ ሁለት ሴቶችን በተለያየ አቀራረብ ቀረብኩዋቸው ....ለአንደኛዋ ጀንትል ማን አይነት ነገር ሆኜ ....በሱዋ ላይ ከፍተኛ የሆነ ኢንተረስት ስላለኝ እና እሱዋን ማወቅ እንደምፈልግ ...በሌላ አነጋገር ካላገኘሁዋት ሞቼ እንደማድር ...ሌላኛውን ደግሞ በሌላ ጊዜ ....እመቤት ይህን ጫማሽን ጫማ ብለሽ ስትገዢ ድራግ ወስደሽ ነበር ...እግርሽ ሸፋፋ ነው በዛ ላይ የባሰ .. Very Happy
...እነዚህ ልጆች በመልክ አይይተናነሱም ...ግን ያው ከላይ እንዳነሳሁት ...የምጀምሪያዋ ዘነጠችብኝ ...ሁለተኛዋ ግን ትናደዳለች ብዬ ያስብኩዋት የበለጠ ቀረበችኝ ....አይገርሙም ትላላችሁ ...?
...አንድ ጊዜ የነጮች ልድት ጠሩን እና ሄድን ...ልጁ ማርቲን እሱዋ ሚካኤላ ትባላለች ...እሱ መህንዲስ ነው ..እሱዋ ስትዋርደስ ...እንዴት ተዋወቃችሁ ብዬ ስጠይቃት ...የሆነ ፓርቲ ላይ A$$ Hole አለኝ በዛው ተዋወቅን ...በቅርብ ጊዜ አንድ የዚህ አገር የፊልም አክተር እንዲሁ ስትጠየቅ ...ከዛሬው ባልዋ ሰድቡዋት እንደ ተዋወቁ ነው ...ምን ትሉዋቸዋላችሁ ...? Smile
.....ፍቅር ምን ማለት ነው ...? ለወደዳችሁዋት / ስትነገሩ እሚዘነጥባችሁ ከሆነ ....ካልነገራችሁ እምትሸሹ ከሆነ ....? ብዙ ጊዜ ሴቶች እሚወዱዋችሁ እናንተን እስከሚለውጡዋችሁ ድረስ ብቻ ነው ...ከለወጡዋችሁ በሁዋላ ግን አይወዱዋችሁም ...
....ጊዜ ካለኝ እመለሳልሁ ...
_________________
" STUPID IS AS STUPID DOES " Very Happy
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ንፋሱ

አዲስ

Joined: 09 Oct 2009
Posts: 10

PostPosted: Mon Sep 19, 2011 10:47 pm    Post subject: Reply with quote

please keep it up brother!! I am trying to learn for your experience. Right now, i am falling in love with a drama queen. The tought of her giving me blues everyday. I want to run away from this feeling but my hear is too weak to get over her. She neither rejected me direcly nor give me any hope. Eventhoght the painful reality make me understand i am also have ability fall in love blindly. i am experiencing the pain and the joy the same time. so i just keep wonderign where did i screw up? i am consider by many as a gentle man with sense of humor but that not scrach her emotional at all. it really true nice guy finish last huh. so i just searching myself in your words. just incase i found so clue. [/b]
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ከምካሚው

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 23 Mar 2008
Posts: 66

PostPosted: Tue Sep 20, 2011 2:58 am    Post subject: Re: (-: Reply with quote

ደጉ :

Try dating multiple girls at one time. It works for me.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሙዝ 1

ዋና አለቃ

Joined: 22 Feb 2006
Posts: 2669

PostPosted: Tue Sep 20, 2011 8:38 am    Post subject: Re: (-: Reply with quote

ደጉ እንደጻፈ(ች)ው:
...ድሮ ምንም ሳላውቅ ፍቅር ከሴት ብቻ እሚይዝ ይመስለኝ ስለነበር ...Smile

ይህቺ ነገር ትብራራልኝ ::

በተረፈ በፍቅር እንደመያዝ ጣፋጭ ነገር ያለ አይመስለኝምና ሰተት ብሎ ይግባ ... ፍቀድለት .... ይመምህ -- ህመሙ ዉስጥ ያለዉን ጥፍጥና የትም አታገኘዉም ... ድሮ ድሮ መፈቀሩ ጀብድ ነበር ... ጣዕም የሌለዉ ጀብድ ... ሜዳሊያ የማያሰጥ ጊዚያዊ ኩፈሳ ... አፍቃሪ አቻዎቻችን ሲሰቃዩም እንስቅ ነበር .... ቀላል ማላገጫ ነበር ?

ጊዜ ቢተርፍህ ተመኘሁ ... እንድትቀጥል Wink
_________________
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ደጉ

ዋና አለቃ

Joined: 15 Dec 2003
Posts: 5233
Location: afghanistan

PostPosted: Tue Sep 20, 2011 10:43 pm    Post subject: Re: (-: Reply with quote

ሙዝ 1 እንደጻፈ(ች)ው:
ደጉ እንደጻፈ(ች)ው:
...ድሮ ምንም ሳላውቅ ፍቅር ከሴት ብቻ እሚይዝ ይመስለኝ ስለነበር ...Smile

ይህቺ ነገር ትብራራልኝ :::

...ሰላም ሙዝ ወንድማችን ...Smile እንደው መንገድህን ስለ ገመትኩ ለመመለስ ያክል ...Wink
...ማለት የፈልኩት ... እናት አገር ፍቅር ... እናት ፍቅር ...የቤተሰብ ... ስራ ...ወዘተ ለማለት ነው ....የተመሳሳይ ጾታ ፍቅርን እነሱው እንተውላቸው ... Smile
_________________
" STUPID IS AS STUPID DOES " Very Happy
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ደጉ

ዋና አለቃ

Joined: 15 Dec 2003
Posts: 5233
Location: afghanistan

PostPosted: Wed Sep 21, 2011 3:49 pm    Post subject: (-: Reply with quote

... ከምካሚው Very Happy ስለ ፍቅር ስታወራ ስለ 1 ሰው ብቻ ነው እሚሆነው ....Wink ስትደርስበት ብቅ በል Wink
....የሰሞኑ ወሬ ደግሞ ...አንዱ 8 አመት አብሩዋት ትኖር የነብረችውን የአንዱዋን አይን አጠፋ ነው ...ነገሩ መነሻው ታውቆ ጥፋተኛ ይሄ ነው ባይባልም ...ነግሩ ሆነ :: አድራጊው ምን ያህል የከፋ ደረጃ ቢደርስበት እንደሆነ ባናውቅም ...ፍርድ ግን በተለያየ መልኩ በየግለሰቡ እየተሰጠ ነው ...

....እንደሚወራው ወንዶች እንቢ ሲባሉ አይችሉም ወደ ብቀላ ይሄዳሉ ይሉናል .... ችግር ወንዶች ላይ ብቻ ሳይሆን ሴቶችም እማይሆን ነገር ላይ ተለጥፈው ችክ እሚሉም እሉ ...እነዚህ አይነት ሴቶች ተነግሮዋቸው ምንም እሚገባቸው አይነት አይደሉም ...አልፎ አልፎ ለጊዜው ይጋባቸውና ከጥቂት ጊዜ በሁዋላ እዛው ያደጉበት ችግር ውስጥ ተዘፍቀው ይገኛሉ ...እንደነዚህ አይነት ሰዎች መተው እማችሉ ከሆነ እሚችሉበትን መንገድ ነርቭ የተደረገው ክፍል መፍትሄ ነው ያለውን ያደርጋል ....ነገሩ እኛ በነጻ አእምሮ እንደምናስበው አይደለም ...ራሱን መቆጣጠር እሚችል አለ ...እማይችልም አለ :: ከልቤ ነው ተው ስትሉት እማይሰማ ከሆነ ..እሚተውበትን አስቸኩዋይ መፍትሄ መፈለግ ግድ ይሆናል ::
....ቁም ነገሩ ግን በሁለቱም ወገኖች በኩል ትብብር ከተደረገ የዛን ያክል የከፋ ደረጃ እሚያደርስ ነገር ይፈጠራል ብዬ ግን አላምንም ....ለበቃኝ በቃኝ ነው የፍቅር ውሳኔ ...ብሉዋል ዘፋኙ ...
...ፍቅርና እና እልህን ለይተው እማያውቁ ሰዎች አሉ ....ፍቅር ፍቅር ነው ...ፍቅር አሪፍ ነገር ነው ...ፍቅር ይቅርታ ነው ..ፍቅር ሰላም ነው ...ሌላም ብዙ ነገር ...እልህ ግን ጥፋት ነው ...እልህ ነገርን አባብሶ ወደ ከፋ ደርጃ የማድረስ ችሎታ ብቃት አለው ...አንተ ወይ አንቺ ካለሽ የበለጠ እልህ ሌላውም ሰው ይኖረዋል ... ደግሞ እሚደርሰውን ጥፋት የሱማሌና የኢትዮጵያ ጦርነት ያደርገዋል ...በበኩሌ በተፈጥሮዬ ማንም በመንገዴ ላይ በክፋት ወይ በተንኮል መንገድ እንዲቆም አልፈልግም ....ከቆመ እኔና ሰው ይለይልናል ...በምድር እምንኖረው አጭር ጊዜ ከዛችውም ላይ ሰላም ማጣት ...:Very Happy.. አስተሳሰበ ስንኩል የሆነ ሰው ግን አርቆ ማሰብ መቼም አይችልም ....ችግሩ ይሄ ይሆናል ብሎ ያልጠበቀው ነገር ሲፈጠር ግን ጸጸትን ይዞ ይመጣል ....ይሄ ደግሞ ሁሌም እምናየው ነው ...አንድ ምሳሌያዊ አባባል ነበር ...ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ ...አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ ...ነገር ሲመዙት ይመዘዛል ...ነገሮችን ከፍተው እዛ ደረጃ ባይደርሱ ምናልባት አይንን ..ወይም ህይወትን እሚያክል ዋጋ ባላስከፈለ ነበር ...ጆሴፍ ስታሊን ባንድ ወቅት መስሎ ከታየህ ሰው መግደል ወንጀል አይደለም ብሉዋል ...Smile
..በዳይም ተበዳይም ራሳቸውን ይወደዱ ...እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል ..እማይሆን ነገር ላይ ሙጥኝ ማለት የት ሊያደርስ ...?? ቀይ መስመር አትለፉ ብለዋል ዲክታቶር የገሪቱ መሪ ...እባካችሁ ሴቶችም ወንዶችም ሌላው ያሰመረውን ቀይ መስመር አትለፉ ...!! አለዛ ታልቃላችሁ ...Wink
..ከዘመነ ሰላም ወደ ዘመነ ጭካኔ ከገባን ቆየን ልበል ...?Smile

ለልጅትዋ ፈጣሪዋ ቀላሉን ያድርግላት ..

ሰላም
_________________
" STUPID IS AS STUPID DOES " Very Happy
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ደጉ

ዋና አለቃ

Joined: 15 Dec 2003
Posts: 5233
Location: afghanistan

PostPosted: Wed Sep 28, 2011 10:37 pm    Post subject: (-: Reply with quote

ንፋሱ እንደጻፈ(ች)ው:
please keep it up brother!! I am trying to learn for your experience. Right now, i am falling in love with a drama queen. The tought of her giving me blues everyday. I want to run away from this feeling but my hear is too weak to get over her. She neither rejected me direcly nor give me any hope.... [/b]

...ንፋሱ አስተያየትህ ከልብ አመሰግናለሁ ...የደረሰብህ ደርሶብኛል ...ህመምህ ይሰማኛል ...Smile
...ወንድማችን አሁን እንደ ገና ወድጃለሁ እኔም ...ደስታና ህመም አንድ ላይ ይሰማኛል ...ከሚሰማህ ስሜት ለመሸሽ አትሞክር ....ቀርበህ እሚሆነውን ማየት ነው እሚሻለው ...ሽሽት እነ መንግስቱ ህይለማርያምን ለስደት ነው የዳረጋቸው ...Wink እሺም እምቢ መልስ ነው ብሮ ...ጠይቀህ ቁርጥህን ብታውቅ ነው እሚሻለው .... ከልብ እኔ ድሮ መሸሽ መፍትሄ ይመስለኝ ነበር ...ኢለመንተሪ /ቤት እያልሁ ...እነ ዘቢብ ..ሂሩት ከሚባሉ ቆንጆ ልጆች ስሸሽ ነበር ...ሁለቱን አንድ ላይ የጠራሁት ጉዋደኛሞች ስለነበሩ ነው ..የልጅነት ልቤ የተንሻፈፈው ግን ዘቢብ ነበር ...ለምን ነፍስ የማዳን ያክል ልጅትዋ ስሸሽ እንደ ነበር ግን እስካሁን አላውቀውም ...ደግሞ ክፋቱ ልጅትዋ እኔን ብላ ነቆንሻ (ሻንቆ ) በኩል እኔን ለመቅረብ መሞክረዋ ...
....ስምንተኛ ክፍል እያለሁ ትንሽ ተሻሽዬ ነበር ...ደብተር ተውሰው የወሰዱ ሁለት ሴት ልጆች .እንደሚወዱኝ አጭር ደብዳቤ ጽፈው በደብተር ውስጥ አድርገው ሰጡኝ ...እኔም ያን ደብዳቤ ክፍል ህላፊያችን ሰጠሁ ...ክፍል ሀላፊው ለዳይሪክተሩ ...ዳሬክተሩ አቶ እሸቱ 3ታችንንም ጠርተው ...ሁለቱ ሴቶች ፊቴ ተንበርክከው ተቀጡልኝ ...ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስበው መቼም የክፍል ሀላፊያችን ሳይናደድብኝ አይቀርም ...Winkእናንተም ሳትናደዱብኝ ታሪኩን እዚህ ላይ ላቁም ... Very Happy
.....አሁን አሁን ላፈቀሩት ሰው ጥሩ መሆን ጎበዝ የሆንኩ መስሎኝ ነበር ...ግን ለካ ጎበዝ መሆን አይቻልም ...እንዳይቻል ያደረገው የየሰው የተለያየ ጸባይ ነው ...ለአንድዋ ጥሩ ነው ብላችሁ ያደረጋችሁት ነገር ..ሌላዋን አያስደስትም ...አልፎም እንደ ሞኝ ልትታዩም ይችላል ...ቁም ነገሩ ግን አብራችሁ ያላችሁን ሰው ፍላጎት ለማጥናት መሞከር ነው ...ጊዜ ቢፈጅም ::
... ሴቶች ብዙ ያስተምራሉ ...ችግሩ ግን እኛ የተማርነውን እንረሳለን ...ወይ ቶሎ አይገባንም ...እኔ ድሮ ሮማንቲክ ማለት የሆነ ለስላሳ ሙዚቃ መክፈት ...የራሽያ ደብዛዛ አበባ መብራቶች አብርቶ ...አለ አይደል ...Wink
....በዚህ ወቅት ላይ ታዲያ በስራ አጋጣሚ አንድ የውጭ ዜጋ ጋር እንተዋወቃለን ...ትውውቃችን ቀስ በቀስ እየጠነከረ ሄደ ...ሮማንቲክ መሆን አውቃለሁ ብያችሁ አልነበረም ...?አዎ ! በጊዜ አንድ አዲስ ሬስቶራንት ሙሉ ዶሮ አሮስቶ አዘዝኩ ...ይሄን ታሪክ ከዚህ በፊት ፅፌው ይሆናል ...Smile
...ዶሮዋ ...ዶርዋ በቃ ዶሮ ነበረች ...የሴትየዋ አሰራር በጣም የተለየ ነበር ...ዶሮዋን አሮስቶዋ ከነ ሙሉ የዶሮ ሰውነትዋ (ገላዋ ) ስትሆን ውስጥዋ በአትክልት ተሞልቶ የተጠበሰች ነበረች ...ሴትየዋ ይዛት ስትመጣ ዶሮዋ ማቅረቢያ እቃው ላይ ቁጭ ብላ ሲሆን አንገትዋ ላይ ክካሮት የተሰራ ህብል ነበራት ...ከልቤ ነው :: ለዛ 20 ብር ነበር ኢንቬስት ያደርኩት ...Smile
...ከዛ የሆነ ፓርክ ይዠአት ሄድኩ ፓርኩ የዱር አራዊቶች ያሉበት ነበር ...ቲኬት የጠየቁኝ ስካዎቶች መግቢያው አካባቢ ነበሩ ..ከዛ በሁዋላ ግን ማንም አልነበረም ....በጣም ከፍ ያለ ቦታ ነበር ቦታው ...በግራ ከርቀት እሚታዩ እንስሶች ..በቀኝ ተራርሮችና ህይቅ ...አፋፍ ላይ ቁጭ ብለን ያካባቢውን ተፈጥሮ ማየት ጀመረን ...እስከዚህ ቀን ድረስ ምንም የፍላጎት ምልክት የለም ...ግን አሁን ሳስበው ሁለታችንም በውስጣችን ...ወይ የነበረው ሁኔታ ...አላውቅም !
...በዛ ሁኔታ ላይ ነበር በጣም ከባድ ዝናብ መዝነብ የጀመረው ...እኔ ዝናቡን አልወደድኩትም ...በቀን አንድ ጊዜ እማበጥረው ጸጉሬን .. Crying or Very sad እሱዋ ከተቀመጠችበት መነሳት አልፈለገችም ...ዝናቡ ደግሞ ቀላል አይነት አልነበረም ....እኔ ምን እዳ አለብኝ መኪና ውስጥ ገብቼ ለምን አልቀመጥም ብዬ ሄድኩ ...ካዛ ሳስበው የህንድ ፊልም ትዝ አለኝ ...ከዛ ተመለሼ ዝናብ አብሬ ለመደብደብ ወሰነኩ ...ምንም የለበስኩት ልብስ ሳይቀር ራሰ ...ከዛ ተቃቀፍን ..ተሳሳምን ...በቃ ሮማንቲክ ማለት ይሄ አይደል ...?Smile
...ከዛ ወደ መኪና ገብተን ከፓርኩ ወጣን ...መንገዱ መከራ ነበር እሚያበላው በዝናብ ...ግን ያው ሮማንቲክ ፕለስ አድቬንቸር ሆነ ...Smile ከዛ እንደ ወጣን ..ወደ ቤትዋ እንድወስዳት ወይ ከኔ እኔ ቤት እንድንሄድ ጠየኩዋት ...ግና ማሰብ ስትጀምር እኔ የቤቴን መንገድ ጀመረኩ ...አልተቃወመችም ...Smile
...እቤቴ ደረስን ቤቴን ታውቀዋለች ...ብዙ ጊዜ ቤቴ በተለይ በሪፖርት ወቅት መሬቱ ሁሉ ቀረቀት ነው ..እየተዘለለ ካልሆነ በቀላሉ መግባት አይቻልም ...ያን ቀን ግን ሰራተኛዋ በጊዜ መጥታ ኖሮ አካባቢውን አረጋግታ ሄዳ ነበር ...
..ከዛ ክፍል ሁለት ሮማንቲክ ተጀመረ ...የሞዛርትን ቅንብር አደረኩ ....ለዚህ ጊዜ ይሆኑኛል ያልኩዋቸውን ዲም መብራቶች አበራሁ .... አሪፍ አይደለሁ ..? ከዛ ልጅትዋ ውህ ስለፈለገች አምቦ ውህ ላመጣ መኪና ይዤ ወጣሁ ቶሎ ለመመለስ ...ከዛ አንዱ ባር ውስጥ ጉዋደኞቼ ሁሉ ተቃጥረው የተገናኙ ይመስል ከበው የሞቀ ወሬ ይዘውልኝ ደረስኩ ..ከዛ የገዛሁትን አምቦ ውህ እግሬ ስር አድርጌ ...ወሬውን ከሰማሁት ቦታ ጀምሬ ተሳታፊ ሆንኩ ...ጨዋታው ጦፈ ...ሳቅ ጨዋታው ደራ ...
...ከዛ ቡና ቤቱ መዘጊያው ሰአት ደረሰና ሲዘጋ ትዝ ይለኛል ..ለካ ሮማንቲክ ነገር ጀምሬ ነበር ..ልጅትዋን በሞዛርት ሙዚቃ ...ከዛም የደበዘዘ የራሺያ አበባ መብራት አድርጌ እንቅልፍ ዳርጌአት እኔም ሞት ይርሳኝና ርስት አድርጌያታልሁ ....

እስኪ ጊዜ ሳገኝ ደግሞ ልቀጥል ...
_________________
" STUPID IS AS STUPID DOES " Very Happy

Last edited by ደጉ on Thu Sep 29, 2011 10:07 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ደጉ

ዋና አለቃ

Joined: 15 Dec 2003
Posts: 5233
Location: afghanistan

PostPosted: Wed Sep 28, 2011 11:37 pm    Post subject: (-: Reply with quote

....ልጅ አባቱን አባዬ ነገ ፖለቲካ ትምህርት ልንጀምር ነው ...ስለ ፖለቲካ ምን ልትነግረኝ ትችላለህ ..? ብሎ ይጠይቃል ....
....አባትም ጥቂት ካሰበ በሁዋላ ...ስለ ፖለቲካ ለማስረዳት እንዲቀልህ አንድ ምሳሌ ልስጥህ ... እኔ ካፒልታሊስት ነኝ ...ምክንያቱም የቤተሰቡ አባወራ ሰርቼ ገነዘብ እማመጣው እኔ ስለሆንኩ ...እናትህ መንግስት ነች ምክንያቱም ሁሉንም ነገር ስለምትቆጣጠር ...የቤት ሰራተኛችን ደግሞ የሰራተኛው ክፍል ነች ምክንያቱም ለኛ ስለምተሰራ ...አንተ እንደ ህዝብ ነህ ምክንያቱም ለኛ ስለምትመልስ ...ያንተ ታናሽ ወንድም ግን የወደፊቱ ትውልድ ተረካቢ ነው ...የሰጠሁህ ምሳሌ ትንሽ ረዳህ ...? ይለዋል
...ልጅም አባዬ ስለነገርከኝ ምሳሌ በደንብ አስብበታለሁ ብሎት ይለያያሉ ...የዛኑ ቀን ለሊት ልጁ በህጻን ወንድሙ ለቅሶ ይቀሰቀስና ይነቃል ...ህጻኑ ልጅ ፓምፐሩ ሞልቱዋል ...እሚቀይርለት የለም ...ከዛ ወደ እናት አባቱ መኝታ ቤት ይሄዳል ...መኝታ ቤት ሲገባ እናቱ ድብን ያለ እንቅልፍ ወስዶአት ተኝታለች ..የአባቱ ቦታ ባዶ ነው ..ከዛ የእንግዳ ክፍል መብራት ስላየ ወደዛ ሄዶ በደንብ ባልተዘጋው በር ስር አሾልቆ ሲያይ ..አባቱ የቤ ሰራተኛቸውን ይነጫል ...ከዛ ልጁ ወደ አልጋው ተመልሶ ይተኛል፡፡
...በነጋታው ጠዋት ቁርስ ላይ ዳድ ...ይመስለኛል ፖለቲካ አሁን በደንብ ገብቶኛል ...Wink
..አባትም በጣም ደስ ብሎት ብራቮ ! ልጄ እስኪ የገባህን ንገረኝ .....
...ልጁም ጥቂት ካሰበ በሁዋላ ...የተማርኩት ...ካፒታሊዝም ሰራተኛውን ክፍል ሲነጭ ....መንግስት ህዝቡን ዘግቶ የተኛ ይመስላል ....ተተኪው ትውልድ ደግሞ .... Very Happy
_________________
" STUPID IS AS STUPID DOES " Very Happy
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 294, 295, 296 ... 311, 312, 313  Next
Page 295 of 313

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia