WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ :- 2005 የተስፋ ዘመን
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 38, 39, 40 ... 53, 54, 55  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት


 
View previous topic :: View next topic  
Author Message
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sun Sep 18, 2011 5:25 am    Post subject: Reply with quote

በዓመቱ የአልማዝ ደረጃ የአትሌቲክስ ፉክክር የኢትዮጵያውያን አትሌቶች አጠቃላይ ውጤት ::

ምንጭ :- የወንዶች 800 ሜትር የሩጫ ውድድር ምድብ ::
5 ..... መሐመድ አማን _______ 4 ነጥብ

ምንጭ :- የወንዶች 1,500 ሜትር የሩጫ ውድድር ምድብ ::
5 ..... መኮንን ገብረመድህን ___ 2 ነጥብ

ምንጭ :- የወንዶች 5,000 ሜትር የሩጫ ውድድር ምድብ ::
1 ..... ኢማኒ መርጋ _________ 15 ነጥብ
3 ..... ደጀን ገብረመስቀል _____ 4 ነጥብ
5 ..... ታሪኩ በቀለ __________ 1 ነጥብ

ምንጭ :- የሴቶች 5,000 ሜትር የሩጫ ውድድር ምድብ ::
3 ..... ሥንታየሁ እጅጉ _______ 6 ነጥብ

የሴቶች 3,000 ሜትር የመሠናክል ሩጫ ውድድር ምድብ ::
2 ..... ሶፊያ አሰፋ __________ 10 ነጥብ
6 ..... ሕይወት አያሌው ______ 2 ነጥብ

አጠቃላይ ተሣትፏችን ጥሩ የሚባል ነበር :: ነገር ግን ባለፉት ዓመታት የበላይነት በነበረን በሴቶች 5,000 ሜትር ሩጫ ውድድር የተገኘው ውጤት ደካማ ነበር : እንዲሁም በሴቶች 1,500 ሜትር ሩጫ ውድድርም የነበረን ብልጫ በኬንያውያንና በሌሎች አገሮች ተወዳዳሪዎች ተነጥቀናል :: መፍትሔው አሁንም ቢሆን ከሥልጠና እስከ ውድድር ሜዳ ያለው ሥርዓት በአትሌቶች የግል ጥረት ብቻ ሣይሆን በተጠናከረ የአትሌቲክስ ተቋም መመራት ይኖርበታል ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Mon Sep 19, 2011 2:55 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ወገኖቼ :-

ዛሬ እሑድ መስከረም 7 ቀን 2004 .. በሚላን (ጣሊያን ) በተለያዩ ርቀቶች የሩጫ ውድድሮች ተደርገው ነበር :: 800 ሜትር ርቀት ሯጭ የሆነው ወጣቱ ኢትዮጵያዊ መሐመድ አማን በርቀቱ የዓለም ክብረ -ወሰን ባለቤት የሆነውን የኬንያውን ሯጭ ዴቪድ ሩዲሻን ቀድሞ በመግባት አስደናቂ ድል ተቀዳጅቷል :: እስኪ ይህ ልጅ በእንዴት ያለ ቁርጠኝነት በመጨረሻዎቹ 100 ሜትሮች ታግሎ እንዳሸነፈ ተመልከቱት ::

ምንጮች :-
1 ..... Diego Sampaolo for the IAAF, Sunday, 18 September 2011. Teenager Aman ends Rudishas win streak in rainy Milan.

2 ..... You Tube, Sun Sep 18, 2011. 800 Metres Men Notturna di Milano 2011
)::

በሌሎች ውድድሮች :-

ምንጭ :- በወንዶች 1,500 ሜትር ሩጫ ተስፋዬ ቸሩ 2 :

እንዲሁም

ምንጭ :- በወንዶች 3,000 ሜትር ሩጫ መኮንን ገብረመድህን 2 ሆነዋል ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed Sep 21, 2011 6:20 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ወግኖቼ :-

የሪፖርተር ጋዜጣ የቆይታ ዓምድ ዶክተር በዛብህ ወልዴን ስለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ስፖርት አጠቃላይ ችግሮች : በተለይም የዳ -- ውድድር ውጤትን በሚመለከት ቃለ -መጥይቅ አድርጎላቸዋል :: ባለሙያና አዋቂ ሰው እንዴት መልሱን አሣክቶ እንደሚያቀርብ ከእርሣቸው አስተያዬት ማገናዘብ ይቻላል ::

ምንጭ :- ሔኖክ ያሬድ : ሪፖርተር ጋዜጣ : እሑድ መስከረም 7 ቀን 2004 .. :: ‹‹የተዝረከረኩ ነገሮች ሰብስብ ከተደረጉና መልክ ከያዙ በለንደን ኦሊምፒክ ከሌላው ጊዜ ያላነሰ ውጤት ይመጣል የሚል እምነት አለኝ›› / በዛብህ ወልዴ፣ የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ::

Quote:
ዶክተር በዛብህ ወልዴ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ናቸው፡፡ ከዚህ ቀደም በኮተቤ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በአስተማሪነት፣ በትምህርት ክፍል ኃላፊነትና በረዳት ዲንነት አገልግለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዋና ጸሐፊ በመሆን ለሰባት ዓመታት ሲሠሩ፣ በርካታ ሜዳሊያዎች በተገኙበት የሲዲኒ ኦሊምፒክ የዝግጅት ኮሚቴ ጸሐፊም ነበሩ፡፡ በአሁን ጊዜ በኢትዮጵያ ኢሊምፒክ ኮሚቴ ሥር የስፖርት አስተዳደር ኢንስትራክተርና የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ናቸው፡፡ ወቅታዊውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ አስመልክቶ ሔኖክ ያሬድ አነጋግሯቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡ - በዴጉ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ውጤትን እንዴት ይገመግሙታል ?

/ በዛብህ፡ - ሁላችንም እንደምናየው ካለፉት ሻምፒዮናዎችና ሕዝብ ከጠበቀው ውጤት ጋር ሲታይ በጣም ደካማ ነው፡፡ የሆነ ተቃርኖ ይታያል፡፡ ምክንያቱም ፌዴሬሽኑ በሰው ኃይል፣ በገንዘብና በቁሳቁስ ተጠናክሯል፡፡ በርካታ ኤክስፐርቶች አሉት፡፡ በቢሮ በኩልም በጣም ተደራጅቷል፡፡ የገቢ ማስገኛ የሚሆን ሆቴልም ይዟል፡፡ ይህን ሁሉ መሠረተ ልማትና የሰው ኃይል ሲታይ ውጤቱ ግን እኔ ከጠበቅኩት እጅግ በጣም ዝቅ ያለ ነው፡፡

ሪፖርተር፡ - እንደባለሙያነትዎ ለውጤቱ መጥፋት ምክንያቱ ምንድን ነው ይላሉ ?

/ በዛብህ፡ - ለውጤቱ መጥፋት ምክንያቶቹ እጅግ በርካታ ናቸው፡፡ ዋነኛው ግን ልክ እንዳሁኑ ደከም ያለ ውጤት ሲመጣ፣ ለምሳሌ በፖላንዱ የአገር አቋራጭ አንድ የነሐስ ሜዳሊያ ብቻ ይዘው እንደተመለሱበት ወቅት ቆም ብሎ ማሰብ ይገባ ነበር፡፡ መገናኛ ብዙኀን በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በዓለም ላይ ያሉ ከስፖርቱ ጋር ትስስር አላቸው፡፡ ሁለቱ የግድ አብረው ይሠራሉ አንዱ አንዱን ይፈልጋል፡፡ ተደጋግፈው ይሠራሉ፡፡ ልክ እንዳሁኑ በርካታ ሐሳቦች ቀርበው ነበር፡፡ ፌዴሬሽኑ በዚያን ሰሞን ቢያዳምጥም አሠራሩን እንደቀደመው ነው የቀጠለው፡፡ ምንም የቀየረው ነገር የለም፡፡ እኔ እንደዋነኛ ድክመት የማየው ልንተገብራቸው የምንችል ግን የሚያልፉን ጥሩ ጥሩ ሐሳቦች ተደጋግመው ይነገራሉ፡፡ ለምሳሌ ለአትሌቶቹ የመንቀሻ ሚኒማ እንደምናዘጋጅና እርስ በርስ እንደምንወዳደር ሁሉ አሠልጣኞችም በዚያ መልክ መሄድ ነበረባቸው፡፡ ማለት አንድ አሠልጣኝ አትሌት ሲያፈራ እርሱም አብሮ ወደ ማዕከል የሚያድግና ወደ ውጭ የመሄድ ዕድል የሚያጋጥመው መሆን አለበት፡፡

ይህ አጋጣሚ ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ ያልፋል፡፡ የተለያየ መስፈርት እያወጡ የተወሰኑ ፊቶች በፌዴሬሽኑ አካባቢ ይበዛሉ፡፡ እኔ በግምባርም ለፌዴሬሽኑ አቅርቤያለሁ፡፡ የሚመለከታቸው ነበሩ፡፡ ተከራክረናልም፡፡ እናም እታች ለሚሠሩት አሠልጣኞች እንደ አትሌቶች ሁሉ ዕድል መክፈት፣ እነርሱም እርስ በርስ መወዳደር ነበረባቸው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ እስከዛሬ ድረስ አሠልጣኝ ከአሠልጣኝ ለመወዳደር ዕድል አልተገኘም፡፡ በሆነ መንቀሻ በተለይም ባላቸው ከፍተኛ ዲግሪ ብቻ ለዘለዓለም ይቀመጣሉ፡፡ ይህ ደግሞ አዳዲስ ተተኪ አሠልጣኞችን እንደዚሁም ተተኪ አትሌቶችን እንዳይመርጡ ያደረገው ይኸው ነው፡፡

ማዕከሉ ለመጣው ሁሉ ክፍት መሆን አለበት፡፡ ምናልባትም እንደመከራከርያ ነጥብ የሚያቀርቡት የትምህርት ደረጃ ሊሆን ይችላል፡፡ ትምህርት ለስፖርት ጠቃሚ ነው፡፡ ግን ሌሎች አጋዥ የሆኑ ከዚህ በፊት አትሌት የነበሩ የመሳሰሉትን በሚያጠቃልል መልክ መሆን አለበት፡፡ ዝም ብለን የወረቀቱንና የኢንተርናሽናል ፌዴሬሽኑን ሰርተፊኬት ብቻ እያየን ብዙ አጋጣሚዎች ያመልጡናል፡፡ ያለ የሌለ ኃይላቸውን ማን የብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ይሁን በማለት ያጠፉታል፡፡

እንደዚያ ያለው ብሔራዊ ቡድን ለማሠልጠን ተግባራዊ የሚደረገው የአመራረጥ ዘዴ አትሌቲክሱን በጭራሽ የሚያስፋፋ አይደለም፡፡ በጣም የጠበበና በአንድ ቡድን የተያዘና ዘለዓለም የማይቀየር ዓይነት ነው፡፡ ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራትና አሠልጣኙንም እንዳይበረታታ፣ ልጆቹም ክፍት ሆነው በብዛት እንዲመጡ አላደረገም፡፡ ይህ ብዙ ጊዜ ያጣነው ዕድል ነው፡፡

ሪፖርተር፡ - ዲግሪ ኖሮት በአስተማሪነት ውስጥ ያለና አሠልጣኝነት እንዴት ይያያዛሉ ? ጥሩ አስተማሪ የሆነ ጥሩ አሠልጣኝ እንዲሁም ጥሩ አሠልጣኝ የሆነ ጥሩ አስተማሪ ላይሆን ይችላል ? ይኼንን እንዴት ማስታረቅ ይቻላል ?

/ በዛብህ፡ - ይኼንን ማስታረቅ ምንም የሚከብድ ነገር የለም፡፡ አሠራሩ ለኢትዮጵያም ሆነ ለዓለም ምንም አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ፒኤችዲም፣ ማስተርስም ቢኤም ይኑረው ነገር ግን በአትሌቲክሱ ስፖርት በቀጥታ መምጣት አለበት፡፡ ክለብ ወይም ፕሮጀክት ውስጥ ገብቶ አትሌት ይዞ አብሮ መምጣት አለበት፡፡ በዓለምና ኬንያንም ጨምሮ የግል አሠልጣኝ የሚባል አለ፡፡ እኔ ዲግሪ ስለያዝኩ ብሔራዊ ቡድን ማሠልጠን አለብኝ የሚል ነገር የለም፡፡ ከክለብ ይዘህ ስትመጣ ውድድር ይኖራል፡፡ ከሌላው ጋር ትወዳደራለህ፤ ወረቀቱ ብዙ ጊዜ በሥራ መገለጥ አለበት፡፡

ፔዳጎጂ የተማሩ ሰዎች ከታች ለመሥራት ጥሩ መብትም ችሎታም አላቸው፡፡ ታች ያለውን ስትሠራ ድንገት ይወጣልህ ይሆናል፡፡ ያፈራኸው አትሌት ችግር ከሌለው አብረህ ወደ ላይ መውጣትህ ማዕከሉ ለሁሉም ክፍት ሆኖ በሥራቸው የሚመጡትን ማሸነፍ አለበት፡፡ ብሔራዊ ቡድን ለማሠልጠን ላይሰንሱ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ነገር ግን ላይሰንሱም ሆነ ዲግሪው ስላለኝ ማሠልጠን መብቴ ነው የሚል ነገር መኖር የለበትም፡፡ ሠርቶ መምጣት አለበት፡፡ ለምሳሌ እኔ በተማርኩበት ትምህርት ቤት ሉድሚላ የምትባል ጥሩ ዘላይ ነበረች፡፡ ከትምህርት ቤት ጀምሮ እስከ ዓለም አቀፍ ውድድሮች አብሯት የሚሄደው አስተማሪዋ ነው፡፡ የግል አሠልጣኟ ነው፡፡ ድንገት አስተማሪዋ አቅም የሚያንሰው ከሆነ የእኛ አቅም ይሻላል የሚሉ ካሉ አትሌቱ ሳይሆን አሠልጣኙ ላይ ነው ማተኮር ያለባቸው፡፡

ኤክስፖዠር (ልምድ ) ሥልጠናና መረጃ ያንሰዋል ከተባለ በብሔራዊ ደረጃ ያሉት ማብቃት አለባቸው፡፡ እዚህ አገር ያለው ግን መልሰው መላልሰው አንድ ዓይነት የቡድን ሥራ ነው የሚሠሩት፡፡ ለቡድን ጨዋታ ሊጠቅም ይችላል፡፡ የሚጠቀሙበትን ማኑዋል አንዳንድ ጊዜ በደንብ የሚያዩት አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም የአትሌቲክስ ማሠልጠኛ ማኑዋል የሚለው የሥልጠና የመጨረሻ ግቡ አትሌቱን ራሱን ማስቻል ነው፡፡ ላይ የደረሰና ደጋግሞ ያሸነፈ አትሌት የሥልጠና እገዛ የሚያስፈልገው በጣም በትንሹ ነው፡፡ እርሱ ላይ ጊዜህን ሳታጠፋ (እዚህ የምናያቸው አራት አምስት የሚፈልጉትን ዕርዳታ እየሰጠህ ) ትኩረትህን ሙሉ በሙሉ መሆን ያለበት በአዲሶቹ ላይ ነው፡፡ የእኛ ግን በተገላቢጦሽ ነው ጧትና ማታ ውይይት ነው፡፡ አንድ አትሌት ሁለት ዓይነት ውድድር እንዲሮጥ ከማድረግ ይልቅ እኔ ውስጡን አላውቅም ለምሳሌ መሠረት 10 ሺሕ ሮጣ 5 ሺሕ ላይ ተበላሸባት፡፡ ሥልጣኑ ያለው አሠልጣኙ ነው፡፡ መሮጥ ያለብሽ በአንዱ ነው መባል ነበረበት፡፡ ካለፈ በኋላ መናገር ቀላል ቢሆንም 5 ሺሕ ብቻ ብትሮጥ አጨራረስ ላይ እንደዚያ አትሆንም ነበር የሚል ግምት አለኝ፡፡ የማዕከል ብሔራዊ አሠልጣኞች ብዙ ግንኙነታቸው መሆን ያለበት ከክለብ አሠልጣኞች ጋር ነው፡፡

ዛሬ በዓለም ላይ የእኛ ዓይነት አሠራር የለም፡፡ የግል አሠልጣኝ አላቸው፡፡ ትምህርትም ልምድም ያላቸው አሠልጣኞች ከታች ያለው የግል አሠልጣኙን ዕርዳታ ሲፈልግ ወይም የሚጎድለው ካለ መመካከር ነው፡፡ ያን ወርቃማ አጋጣሚ አጥተውታል፡፡ ደግመው ደጋግመው ብዙ እገዛ በማያስፈልገው ላይ ይወያያሉ፡፡ ሁልጊዜም ያለው የሚያጨቃጭቅ ሁኔታ ነው፡፡ ጊዜና ኃይልን ወደ ታች በማምጣት አልተጠቀሙበትም፡፡ ትልቁ ድክመት እርሱ ነው የሚመስለኝ፡፡

ሪፖርተር፡ - አትሌቲክሱ ባለፉት ዓመታት ከውዝግብ አልራቀም፡፡ ብልጭ ይልበታል፤ እንደገና ቀዝቀዝ ይላል የሚባል ነገር አለ፡፡ ምክንያቱ ምንድን ነው ?

/ በዛብህ፡ - እኔ በሲዲኒ ኦሊምፒክ (1993 ..) ጊዜ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽንና የኦሊምፒክ ኮሚቴም ዋና ጸሐፊ፣ የሲድኒ ኦሊምፒክ ዝግጅት ኮሚቴም ጸሐፊ ነበርኩ፡፡ የሐሳብ ልዩነቶች በየስብሰባው ላይ ይነሳሉ፡፡ በአብዛኛው የሚነሱት ራስን እንጂ አትሌቱን ማዕከል ያደረገ አይደለም፡፡ ለምሳሌ ገዛኸኝ አበራ በግሉ ይሠራ ነበርና ሆቴል አይተኛም ተባለ፡፡ ገዛኸኝን በግሌ ሄጄ ችግር አለብህ እንዴ ስለው ኧረ የለብኝም ጥሩ እየሠራሁ ነው አለ፡፡ ተስፋዬ ቶላም ሌሎችም እንደዚሁ ተመችቶናል ይላሉ፡፡ ነገር ግን የሚመጣው ሪፖርት እንደ አልታዘዝ አሉ ዓይነት ነው፡፡ ያን ዓይነቱ ባህል መጥፋት አለበት፡፡ በነገራችን ላይ አንዳንድ አንጋፋ አሠልጣኞች ለምን እንደሚጠራጠሩ አላውቅም፡፡ በኦሊምፒክ ወይም በዓለም ሻምፒዮና ለማሸነፍ ከማንም ዜጋ፣ ከማንም አሠልጣኝ በላይ አትሌቱ ፍላጎት አለው፡፡ ይህ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ማዕከላዊነት መጠበቅ አለበት፡፡ ሆቴል መተኛት እንደ ትልቅ ግብ የሚቆጠርበት ሁኔታ አለ፡፡ አቅም ለሌላቸው ጥሩ ነው፡፡ ሆቴል ለማስተኛት ማስገደድ ግን አግባብ አይደለም፤ ወይም ደግሞ አትሌቱ ሳይፈልግ አሠልጣኝ መቀየር በጭራሽ አግባብ አይደለም፡፡ የግሉ አሠልጣኝ ነውና፡፡ እርግጥ አሠልጣኞች በትምህርት ደረጃ አይመጣጠኑም፡፡ ካልተመጣጠኑ ግን ለምሳሌ የጥሩነሽ አሠልጣኝ ማን እንደሆነ አላውቅም እርሷ ታውቃለች፡፡ ከጎን ሆኖ የሚታይ ችግር ካለ አሠልጣኙን ከየአቅጣጫው ማገዝ ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት አሠራር በጭራሽ አልለመድንም፡፡ አሁን እየተሰጠ ያለው አስተያየትም አሠልጣኞቹን እንጂ አትሌቶቹ ማዕከል ያደረገ አይደለም፡፡ መሆን ያለበት ማዕከሉ ልጆቹና ውጤቱ ናቸው፡፡ አሁን እንዲህ ቢሠራ ኖሮ የሚባለው አንዳንዱ በጣም ያለፈበት ነው፡፡ እነ ኃይሌ፣ ወርቁ ቢቂላ፣ ሀብቴ ጅፋር እየተጋገዙ ይሠሩ ነበር ነው፡፡
አሁን አንደዚያ ማድረግ አይቻልም፡፡ አሁን ያሉት ልጆች እንደ ወርቁም ሆነ ሀብቴ ዓይነት ቢኖሩ ማሸነፍ ይፈልጋሉ፡፡ እርስ በርስም ውድድር አለ ማለት ነው፡፡ ይኼም ጤናማ ነው ምንም ችግር የለውም፡፡ እንደዚያ ለመረዳዳት ደግሞ ሁሉም የላቁ መሆን አለባቸው፡፡ በጉልበትና በብቃት እንጂ በሐሳብ መረዳዳት አይቻልም፡፡ ይኼ ጤናማ አካሄድ ነው፤ አሠልጣኝ ከአሠልጣኝ መወዳደር አለበት፡፡ ማለት ያለብን እጅህ ከምን ነው ? በአትሌቱም እንደዚህ አሁን ኬንያዎችን ብናይ ያልተማከለ ሥርዓት አላቸው፡፡ መብት ሰጥተዋል፡፡

በብሔራዊ ቡድን ውስጥ ለመመረጥ ሁሉም ተዘጋጅቶ በአገሩ ማጣርያ ተወዳድሮ ማለፍ አለበት፡፡ ብዛትም አላቸው፡፡ እኛ እንደዚያ ለማድረግ አንድ የምንተማመንበት አትሌት እዚህ ተወዳደር ብንለው እምቢ ቢለን የሚተካው የለም፤ ችግር ሆኖብናል እንጂ አመራሩ ዕውቀቱን አጥቶ አይደለም፡፡ ዞሮ ዞሮ ግን ሁኔታው ለሌላ ስፖርትም ቢሠራ ጥሩ ነው፡፡ ምክንያቱም አንድ የብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ የሚሆን ሰው በእጁ የያዘው ነገር መኖር አለበት፡፡ ለምንድን ነው የብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ የምሆነው ? የትኛው አትሌት ነው የሚያውቀኝ ? ከየትኛው ጋር ነው የሠራሁት ? መባል አለበት፡፡ መከራከርያ ነጥባቸው አንዳንዶቹ ክለቦች በጣም ጠንካራ ናቸው፡፡ በጥሩ መሠረት ላይ ይገኛሉ፤ ብዙ ጊዜ የሚመረጡት እነርሱ ናቸው የሚል ነው፡፡ ለምንድን ነው አንድ አሠልጣኝ አሸንፎ የማይገባው ? ነፃ ገበያ ነው፡፡ ርስት ጉልት አይደለም፡፡ የተሻለ ዲግሪ አለኝ፡፡ የተሻለ አትሌት አመጣለሁ የሚል ካለ ደግሞ የተሻለ አደረጃጀት ባለው ክለብ ውስጥ ተወዳድሮ መግባት መብቱ ነው፡፡ ክለቦቹም ራሳቸውን ማየት አለባቸው፡፡ ይኼን ያህል ገንዘብ አፈሳለሁ፡፡ አሠልጣኙ ለዚህ ዓመት ያህል ይኼን ሠርቷል፡፡ የክለቡ አመራሮች እንዲህ ያለን ውጤት ምንድን ነው ብለው መጠየቅ አለባቸው፡፡ አሠልጣኙ ጤናማ ፉክክር ሲኖረው ለውጥ ያመጣል፤ ለዘመናት እኔ እዚያ ውስጥ ሆኜ ሞክሬ ያቃተኝ ነገር ነው፡፡

ብሔራዊዎቹ ግንኙነት የሚያደርጉት አለመታደል ሆኖ የግሉን አሠልጣኝ አልፈው ከአትሌቶቹ ጋር ነው፡፡ የመቀባበል ሁኔታ አለ፡፡ ብዙ የታዩ አስገራሚ ሁኔታዎች አሉ፡፡ አሁን ይረዳዳሉ ይባላል፡፡ አንድ ክፍል መተኛት የማይፈልጉም መኖራቸው ምንም ችግር የለውም፡፡ ምክንያቱም የሚወዳደሩት ከዓለም ጋር ብቻ አይደለም፡፡ እርስ በርስም ነው ምንም መጥፎ ነገር የለም፡፡

ሪፖርተር፡ - በዴጉ አንዳንዶቹ አንድ ላይ ልምምድ አይሠሩም ነበር ተብሏል፡፡ ዘጋቢያችንም የተመለከተው ነው፤ ክፍተትም አለ ይባላል፡፡

/ በዛብህ፡ - ጤናማ የሆነው ፉክክር ውጤታማ እንዲሆን መጠነኛ ሥራ ያስፈልጋል፡፡ እርስ በርስ መፎካከራቸው ግን ምንም መጥፎ ነገር የለውም፡፡ ይህን ለመያዝ የአሠልጣኞቹ ሚና ወሳኝ ነው፡፡ ሁሉም በብቃት ካሠለጠነ ሊሰምር ይችላል፡፡ ሁሉም የሚሰለፉት ለአገርም ለራሳቸውም ነው፡፡ አንዳንዴ ሰዎች ለገንዘብ ሲሆን ይሮጣሉ ለአገር ሲሆን አይሮጡም ይላሉ፡፡ እዚህም ገንዘብ አለ፡፡ ነገር ግን በአሠለጣጠን መጨረሻ ላይ የማቀናጀቱ ሥራ የብዙ ጊዜ ሥራ አይደለም፡፡ ከውድድሩ በፊት ሊሆን ይችላል፡፡ ለራስህ ስትል እስከተወሰነ ደረጃ ስለመተጋገዝ ማሳመን ነው፡፡ እንደ ዱሮ እንሠራለን ብንል ሠልጣኞቹ ዓላማቸው ሌላ ነው፡፡ ዓለምም ሌላ ነው፡፡ መታወቅ ያለበት የሥልጠና ማኑዋሉ የሚለው አትሌቱ በሒደት ራሱን እንዲችል የራሱን ፕሮግራም እንዲገነባ ማድረግ ነው፡፡ እኛ ሁልጊዜ የማንጠቀምበት ማንዋል ‹‹አንጋፋ ለሆኑ አትሌቶች አሠልጣኞች ዕቅድ ሲያወጡ በዚያ ሁሉ ያግዙ›› ይላል፡፡ እነርሱ የሚሉት ነገር ይኖራል፡፡ የሚያደረጉት አስተዋጽዖ ጠቃሚ ነው ይላል፡፡ ሲኒየር የሆኑትን አትሌቶች እንደጀማሪ ከሚገባው በላይ መከታተልም ይበዛል፡፡ ጊዜ ይበላሻል፤ ጭቅጭቅ ይኖራል፡፡

ለምሳሌ በባል፣ በቤተሰብ የሚሠለጥኑ አሉ ይባላል፡፡ ውጤቱ ከመጣ ምንም ይሁን ቅድም ያልኩት የመጨረሻ ሒደቱ ራስን ማስቻል ስለሆነ አንድ አትሌት የራሱ አካሄድ ይኖረዋል፡፡ ለምሳሌ መሠረት ራሷን ችላ ከሆነና አሁን የምትፈልገው ሰዓት የሚይዝላት ከሆነ ፍላጎቷ እዚያ ከደረሰ ፕሮግራሙን የምትመራው ራሷ ናት ማለት ነው፡፡ በዓለምም ያለ ነው፡፡ ኬንያዎች ተከታትለው ሲያሸንፉ ‹‹አሠልጣኜ ባሌ ነው አመሰግናለሁ›› ስትል ሰምተናል፡፡ ያንን አላግባብ መተርጐም የለብንም፡፡ ከዚህ በፊት የነበሩ አሠልጣኞችም ግብዓት አለ፡፡ በሥልጠና ሒደት የሚፈለገው ሠልጣኙ የአሠልጣኙ አጋር እንዲሆን ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነቱን መድረክ በጭራሽ አልተጠቀምንበትም፡፡

ኬንያ በተደጋጋሚ አይቻለሁ፡፡ እነ ፖል ቴርጋት የፌዴሬሽኑ አጋዦች ናቸው፡፡ ለልዩ ልዩ ዝግጅቶች ይጠቀሙባቸዋል፡፡ እኛ ይኼን አላየንም፡፡ አሁንም የባለቤትነት ጥያቄ ይነሳል፡፡ ቀነኒሳ፣ ኃይሌ የማነው ? እነርሱ’ኮ ራሳቸውን ችለዋል፡፡ እነርሱ ራሳቸውን ሊረዱ ከሚችሉበት ደረጃ ደርሰዋል፡፡ በእነርሱ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ ያለ የሌለ ዕውቀታችንና ገንዘባችንን ግን አዲስና ተተኪ ለማምጣት መሥራት አለብን፡፡ አዲስ እንዲመጣ ግን ማበረታቻው ደግሞ ምንድነው ? ማዕከሉ ክፍት መሆን አለበት፡፡ እያመጣ ለአንተ መስጠት የለበትም፡፡ ራሱ ይዞ መምጣት አለበት፡፡ ግልጽ ተሆኖ ችግራችን ያለበትን ለማቃለል ማዕከሉ አትሌትና ውጤት መሆን አለበት፡፡ ሌላው አጋዥ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ብንቀበልስ ? ለምንድን ነው ግትር የምንሆነው ?

ሥርዓት (ሲስተም ) መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡ ይኼን ያህል ዓመት ሠራሁ ማለት እኮ አንዳንዴ ሊያጠፋም ይችላል፡፡ ሲስተሙን ዘርግቼ ልክ እንዲመጣ አድርጌ ከወጣሁ ሊሠራ ይችላል፡፡ እኔ ስወጣ የሚበላሽ ከሆነ ምንም አልሠራሁም ማለት ነው፡፡ ሁሉንም ጠቅልዬ ይዤ አጠገቤ ሰዎችን ካላፈራሁ፣ አሠራሩንም ካላስተዋወቅሁ፣ እንደዚህ ዓይነት ችግር ይመጣል፡፡ ዘለዓለም የሞግዚት ነገርም ይሆናል፡፡ መዋቅር ዘርግቶ፣ ያልተማከለ ሁኔታን ፈጥሮ መጓዝ ያስፈልጋል፡፡ ብዙ ጊዜ የማይፈልጉት ቢሆንም አሁን ግን በግድ ይፈልጉታል፡፡ ምክንያቱም እውነታውን ካየን ሪፖርት እንደሚደረገው አይደለም፡፡ ባለፈውም ቢሆን እኔም እያለሁ አብዛኞቹ አትሌቶች የሚሠሩት በግል ነው፡፡ አሠልጥነዋል ተብለው የተሸለሙባቸው ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ የሚከፋኝ ነገር የለም፡፡ በአብዛኛው የሚሠሩት ለራሳቸው ነው፡፡ እኛ ደግሞ በአብዛኛው ጊዜ የምናባክነው ራሳቸውን በቻሉት ላይ በመወያየት ነው፡፡ ግን ስንትና ስንት በየጫካውና በየፕሮጀክቱ የሚሮጥ አለ፡፡ እዚህ ተሰብስበን አምስት እና ስድስትቱ ላይ ጊዜ ከምናጠፋ እነርሱ ራሳቸውን ይመራሉ፤ ያስተዳድራሉ፤ የሚሠሩትን ያውቃሉ ብለን ያው ባለን ትንሽ የሰው ኃይልና ገንዘብ አዲስ ሰው ማምጣት ያስፈልጋል፡፡ እከሌ የአሠልጣኝነት ብቃት የለውም ብለን ውይይት ከምናደርግ፣ እኔ ብቃት ካለኝ የእርሱን አትሌት የሚያሸንፍ አትሌት ማዘጋጀት ነው፡፡ ምንም ጭቅጭቅ የለውም፡፡

ሪፖርተር፡ - ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሳው የአደረጃጀት ጉዳይ ነው፡፡ የፌዴሬሽኑ አደረጃጀት ክለቦችን ያማከለ አይደለም፡፡ የክለቦች ተወካዮችም የሉበትም፡፡ ለምሳሌ አዲስ አበባ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ውስጥ ወኪል የለውም፡፡ በሌላ በኩልም በፌዴሬሽኑ ስብስብ አቅም ላይ የሚነሳ ጥያቄ አለ፡፡

/ በዛብህ፡ - አዎ ይነሳል፡፡ ትክክል ጥያቄ ነው፡፡ የአደረጃጀት ችግሩ አቅም እያጣ ይወድቃል እንጂ አንተ ያነሳኸው ጥያቄ እኔ እያለሁም ተነስቷል፡፡ አዲስ አበባ ካለው የአትሌትና የክለብ ብዛት አኳያ በምንም ዓይነት ውክልና ሊኖረው ይገባል በሚል በተደጋጋሚ ተነስቷል፡፡ ሆን ተብሎ ይሁን፣ የአሠራር ችግር ይሁን አዲስ አበባ አልተወከለም፡፡ አሁንም አልተወከለም፡፡ ፌዴሬሽኑ አዲስ አበባን እንደ አጋዥ አያየውም፡፡ ይመካሉ፤ ብዙ ክለብና አትሌት አለን ይላሉ ይላል፡፡ አሁን መንፈስ መጥፋት አለበት፡፡ ላንተ ጥያቄ መጽሐፉ እንደሚለው ከመለስኩልህ ፌዴሬሽን ማለት የክለብ ስብስብ ነው፡፡ እኔ ስለፈለግሁና ስላልፈለግሁ አይደለም፡፡ ፌዴሬሽን የክለቦች፣ ክለቦች ደግሞ የአትሌቶች ጥርቅም ናቸው፡፡ የአገሪቷን የዕድገት ደረጃና አንዳንድ ሁኔታ በማየት ክልሎች ገና ክለብ ለማቋቋም አልበቁም በሚል ወደዚያ ተሂዷል፡፡ አሁን ግን እንደማውቀው እኔ ከወጣሁ በኋላ ብዙ ክልሎች የአትሌቲክስ ክለቦች አሏቸው፡፡ ስለዚህ አደረጃጀቱን ለማስተካከል ጊዜው አሁን ይመስለኛል፡፡ አንድ ክልል አባል መሆን ይችላል፡፡ ግን በጥያቄ ምልክት ሆኖ በሒደት ክለብ ማቋቋም እንዳለበት ሊረዳ ይገባል፡፡

ምክንያቱም ፌዴሬሽን የክለቦች ጥርቅም ነውና፡፡ በሌሎችም ስፖርቶች የሚንፀባረቅ ነው፡፡ መጽሐፉ እንደሚለው መኬድ አለበት፡፡ ፌዴሬሽኑ የሚቋቋመው ደግሞ የመጀመርያ ዓላማው ለአትሌቶች ደኅንነት፣ ጥረትና ልማት ተብሎ ነው፡፡ አሁን ጊዜው የሚፈቅድ ይመስለኛል፡፡ ቢያዩት ጥሩ ነው፡፡ ሌላው ባለመብቶቹ ክለቦች ናቸው፡፡ አስቀድመህ የጠየቅከኝ ጥያቄዎች ሁሉ የሚመለሱት እዚያ ላይ ነው፡፡ ለምሳሌ ለአሠልጣኝነት የምመርጥህ ባፈራኸው አትሌት ሁኔታ ላይ ተመሥርቼ ነው፡፡ እንዲሁ የምትመረጥበት ሁኔታ የለም ብል ክለቦች ራሳቸውን ማየት ይጀምራሉ፡፡ የእኔ የት አለ ? አስመርጫለሁ ወይ ይላሉ፡፡ አሁን ምስቅልቅሉ የወጣ ነው፡፡ ራሳቸው በማዕከል ሲመድቡ፣ ከግል አሠልጣኙ ወስደው ወደ ሌላ አሠልጣኝ ሲመድቡ የአትሌቱን ፍላጎት መሠረት አያደርጉም፡፡ ሌላው አስገራሚው ነገር ማዕከሉ ላይ የሩጫውን ዓይነት (ዲሲፕሊን ) ይቀያይራሉ፡፡ አንዱን አሠልጣኝ መካከለኛና አጭር ያደርጉታል፡፡ አንዴ ረዥም ይወስዱታል፡፡ ማዕከሉ ላይ የአሠልጣኞች ያለመረጋጋት ሁኔታ አለ፡፡ ይኼ ደግሞ የበለጠ መጥፎ ነገር ነው፡፡ ቅድሚያ መሰጠት ያለበት ለክለብ ነበር፡፡ ክለቦች ግን ብዙ ሰው የላቸውም፡፡ አንዱ መጥፎ ነገር ነውና ይኼን ቢገነዘቡት ጥሩ ነው፡፡

ሪፖርተር፡ - ለንደን ኦሊምፒክ ዘጠኝ ወር ገደማ ቀርቶታል፡፡ ምን መደረግ አለበት ?

/ በዛብህ፡ - አንዳንድ የተጎዱ አትሌቶች አሉ ይድናሉ የሚል እምነት አለ፡፡ ተስፋ የሚጣልባቸው እነርሱ ናቸው፡፡ ሌላው ደግሞ የተሠራ ስህተት አለ፡፡ ግትርነት አያስፈልግም፡፡ ከተሠራው ስህተት መማር ነው፡፡ ራስን ማዕከል አለማድረግ ነው፡፡ እከሌ ስላሠለጠነ ሳይሆን አጠቃላዩን ማየት ያስፈልጋል፡፡ የመገናኛ ብዙኀን ሰዎች አትሌቶቹ ምን እንደሚሻላቸው ጠይቋቸው፡፡ ተጽዕኖ አለ፡፡ እነርሱ መሥራት በሚፈልጉትና አንጋፋ አሠልጣኞች በሚሉት ላይ ብዙ የሚጋጭ ነገር አለ፡፡ እነርሱ ሊናገሩ ወይም ሐሳባቸውን በትክክል ሊያንፀባርቁ ይገባል፡፡

ከእኔ ጋር ካልሠራችሁ አትገቡም በማለት ትራኩን እንደመያዣ የተጠቀሙ አሉ፡፡ ይኼ በአገር ደረጃ አሳፋሪ ነው፡፡ የሚፈለገው ውጤቱ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት አሜሪካ ኮሚኒቲ ትምህርት ቤት ሄደው የሚሠሩ አሉ፤ ያን በግልጽ ማጥፋት ነው፡፡ ጥያቄው መሆን ያለበት እንዴት መሥራት አለባችሁ ነው፡፡ ሚዲያውም እነ ኃይሌን፣ ቀነኒሳን፣ እነ ደራርቱን መጠቀም አለበት፡፡

ክለቦቹም ራሳቸውን መፈተሽ አለባቸው፡፡ ምን ይዘን ሄድን ? ምን አገኘን ? በክለቦች ውድድር በኢትዮጵያ ሻምፒዮና ምን አመጣ የሚለውን ማየት አለባቸው፡፡ ሌላው ነገር ወደ ፌዴሬሽን የሚያሯርጣቸው የሽልማት ጉዳይ ነው፡፡ ሽልማቱ አስገራሚ ነው፡፡ ተሸላሚው አብሮት የሚሄደው ነው፡፡ አስቀድመው ሕጉን አውጥተው ተሸላሚው የግል አሠልጣኙ ቢሆን ጭቅጭቅን ያስወግዳል፡፡ ስለዚህ የሰው ከምወስድ ይልቅ የራሴን መሥራት እጀምራለሁ ማለት ነው፡፡ ጥሩ ጥሩ ክለብና በጀት ያላቸው እያሉ የሚፈልጉት ሌላ ነው፡፡ የራሳቸውን ይዘው ከሚሄዱ ይልቅ በሆነ መንገድ በመጣው ላይ ይረባረባሉ፡፡

ሪፖርተር፡ - ሽልማቱ ሕግ አለው ?

/ በዛብህ፡ - አንደኛ ነገር ሕግም የለም፡፡ ሕግ እንዲወጣ ለረዥም ጊዜ ሐሳብ ቀርቦ ነበር፡፡ ጥናትም አቅርበናል፡፡ እርሱን ቢያወጡ ብዙ ነገር ያቃልልላቸዋል፡፡ ለምሳሌ የሲዲኒን ብነግርህ ጸሐፊ ስለነበርሁ የመጨረሻው ብዛት ያላቸው አሠልጣኞች የሄዱበት ኦሊምፒክ ነው፡፡ ወደፊትም የዚያን ያህል ይሄዳሉ ብዬ አልገምትም፡፡ ባገኘነው ቀዳዳ ሁሉ አሠልጣኝ ልምድና ትምህርት እንዲያገኝ በጣም ብዙ ተጠቅመናል፡፡ በዚያን ጊዜ የተሸለሙት የሄዱት ብቻ ናቸው፡፡ ምናልባት በሌላ አጋጣሚ አንድ ሊኖር ይችላል፡፡ የወርቅ ሜዳሊያ ባመጣ አትሌት የተመዘገበ አሠልጣኝ ቢሄድም ባይሄድም መሸለም አለበት፡፡ ሥራቸውን እንዲሠሩ ያደርጋል፡፡ የሽልማት ሕግ አሁንም ያላቸው አይመስለኝም፡፡ ሽልማቱ የዕድል ጉዳይ ነው፡፡ ለአንድ ወር ያህል የያዘው ተሸላሚ ይሆናል፡፡ ለረዥም ጊዜ ከአትሌቱ ጋር የሠራው (ከበቆጂ እስከ ማምጣት ድረስ ) እያለ ሕጉ ቢኖር ግን ይረዳል፡፡ የእርስ በርስ ጤናማ ፉክክር በአሠልጣኞቹ መካከል ይፈጥራል፡፡ የሚሸለመው ሰብስቦ ይዞ የሄደ ሳይሆን አትሌቱን ይዞ ለዚያ ያበቃውና አትሌቱ እከሌ አሠልጣኜ ነው ብሎ ያስመዘገበው ነው፡፡ አሁን ያለው አሸላለም ግብታዊ ነው፡፡ ወርቅ የሚሸለም ምን ያህል ገንዘብ ይሸለማል ብትል ሕጉን አታገኘውም፡፡ ከሮጡ በኋላ ነው የሚታወቀው፡፡ ኢብራሂም ጄይላን ምን እንደሚሸለም አናውቅም፡፡ እርሱም ራሱ የሚያውቅ አይመስለኝም፡፡ ብዙ ጊዜ ያየነው አንድ ጊዜ መኪና፣ አንድ ጊዜ መሬት፣ ሌላ ጊዜ መቶ ሺሕ ብር፣ የማይደጋገም ነገር ማለት ነው፡፡ እንደ ዓለም አቀፉ ፌዴሬሽን ሕጉን ማውጣት ያስፈልጋል፡፡ የሚሸለመው አሠልጣኝም እስከተስማሙ ድረስ የግሉ አሠልጣኝ መሆን አለበት፡፡ ጌታና ሎሌም አይደሉም፤ ካልተስማማህ መቀየር አለብህ፡፡ ሌላው ዓለም የግል አሠልጣኝ፣ ወጌሻ፣ ወዘተ መቅጠር ጀምረዋል፡፡ እኛም ወደዚያ ነው መሄድ ያለብን፡፡

ሪፖርተር፡ - ስለለንደን ኦሊምፒክ ምን ያስባሉ ?

/ በዛብህ፡ - ስለለንደን ብሩኅ ተስፋ አለኝ፡፡ ቅርብ ነው፡፡ የተንጠባጠበና ሜዳ ላይ የቀረ ውጤት አለ፡፡ በደንብ ሪፖርት አልተደረገም እንጂ ለምሳሌ ማራቶን ላይ ውኃ በሥነ ሥርዓት መወሰድ ያለበትን አሠልጣኙ ሮጦ ሰጥቶ ከውድድር እንዲወጡ የተደረጉ አሉ፡፡ እዚያ ያሉት እንዴት እንዳላዩት አላውቅም፡፡

ሪፖርተር፡ - ከዚህ ከእኛ ?

/ በዛብህ፡ - አዎ፡፡ እንደዚህ ያለ ነገር ስላለ እንደዚህ ትንንሽ ነገር ላለመድገም አሁን የሚነገረው መልዕክት ከጆሮ ሳይጠፋ ለንደን ይደረሳል፡፡ የዴጉ አንዱ ችግራችን የጊዜ ቀጣናው (Time Zone) ነው፡፡ ብዙ የሰዓት ልዩነት ስላለ መኝታ ይዛባል፡፡ የአየር ፀባዩም ምቹ አልነበረም፡፡ ለንደን ግን ችግር የለውም፡፡ በአንድ ቀን ሄደው የሚላመዱት ነው፡፡ በደጋፊም አንፃር የማይናቅ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን ይደግፋሉ የሚል እምነት አለኝ፡፡ አሁን ያለው የሕዝብ አስተያየት ከጆሯቸው ሳይጠፋ ይቀበሉና በይበልጥ ግልጽ ሆነው መሥራት አለባቸው፡፡ ራሳቸውን ሳይሆን ውጤቱን ማዕከል ማድረግ ያለባቸው አትሌቱንና ውጤቱን ነው፡፡ ሁልጊዜ መጠየቅ ያለበት አትሌቱ ነው ሲባል፣ እነ ቀነኒሳን ገና እተካለሁ ለሚለው አይደለም፡፡ እነ ኃይሌ፣ ቀነኒሳ መጠየቅ ያለባቸው ለምን ታመምክ፣ የአሠልጣኝ ሳይንሳዊ አለመሆን ወይስ የልምምድ ጫናው፣ የሚሠራበት ዳገት ቁልቁለት፣ የእከሌ አሠልጣኝ እከሌ እንዴት ነው ተብሎ መጠየቅ አለበት፡፡ ወደ ዴጉ ሲኬድ በማራቶን በሁለቱም ጾታ ጥሩ ነን ተብሎ ተበላሽቷል፡፡ ችግሩ ምንድነው ልጆቹንም መጠየቅ ያስፈልጋል፤ በተለያዩ የዓለም መድረኮች ጥሩ ጥሩ ውጤቶችን አምጥተዋል፡፡ ምን ይጎድላል ? መረጃ መለዋወጥ ዕውቀት ያሰፋል፡፡ ለእኔ ለንደን ጨለማ አይደለም ማስተካከል ነው፡፡

ለለንደን አዲስ ከታች ለማምጣት ፍላጎቱ ቢኖር እንኳ ተግባራዊ መሆን አይችልም፡፡ ከታች አምጥተህ ሚኒማ አምጥተው መሄድ አይችሉም፡፡ የተንጠባጠቡትን ነገሮች አስተካክሎ ከዚህ በፊት ሕዝቡ የለመደውንና አገር የምትጠብቀውን ውጤት ማምጣት ይቻላል ባይ ነኝ፡፡

ሪፖርተር፡ - በርካታ ሜዳሊያዎች ከተገኘበት ሲዲኑ መማር ይቻላል ?

/ በዛብህ፡ - ጥሩ ነው፡፡ ሲድኒ ላይ አሁን በምንነጋገረው ልዩነት ነበር፡፡ ልዩነት ግን መጨረሻ ላይ ጥሩ ሆነ፡፡ ሰዎች ልዩነት ይጠላሉ፡፡ የተለየ ሐሳብ የሚሰጥ ጠላት አይደለም፡፡ የምንወዳደረው በተለያየ የትምህርት ደረጃ ላይ ሆነን ነው፡፡ እሱን እንተወውና አትሌቱ ችግሩ ምንድን ነው ? ማየት ነው፡፡ ገንዘብ የማያበላሸው የለምና እርሱን መቆጣጠር በተለይ ለዚህች ዓመት እንኳ ቢሆን አስፈላጊ ነው፡፡ ማናጀሮችን ሥርዓት ማስያዝ የተጀመረው እኔ ባለሁበት ጊዜ ነው፡፡ ከያሉበት አገር ከሆላንድ፣ ከጣሊያን፣ ከአሜሪካ እዚህ ድረስ አስመጥተን ስምምነት አስፈርመናል፡፡ አሁን ምን ላይ እንዳለ አላውቅም፡፡ ፌዴሬሽኑ የሚሰጣቸው ፕሮግራም እንዲያከብሩ አድርገናል፡፡ ይኼን ፈርመው ተባብረው ነው የሚሠሩት፡፡ በተለይም ለእነሱ በኦሊምፒክም ሆነ በዓለም ሻምፒዮና ማሸነፍ ለወደፊቱ የመግቢያ ለመሰብሰብ መታያ መድረኩ እርሱ ነው፡፡ አሁን በዓለም ባለው የስፖርት በተለይም የአትሌቲክስ ባህል ማናጀሮች ያስፈልጋሉ፡፡ ግን በአግባቡ መጠቀም አለብን፤ በአግባቡ በቁጥጥር ሥር ውለው በፌዴሬሽኑ ፕሮግራም መሄድ ይገባቸዋል፡፡ የተዝረከረኩ ነገሮች ሰብሰብ ከተደረጉና መልክ ከያዙ በለንደን ኦሊምፒክ ከሌላው ጊዜ ያላነሰ ውጤት ይመጣል የሚል እምነት አለኝ፡፡

ሪፖርተር፡ - ለዘላቂው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ስኬት የአደረጃጀቱ ጉዳይ ምን ቢሆን ይመኛሉ ?

/ በዛብህ፡ - ፌዴሬሽን የክለቦች ጥንቅር በመሆኑ የአደረጃጀቱ ጉዳይ ለአንድ ሰሞን ቢመርም ማኑዋሉን መቀበል ግድ ነው፡፡ በጉዳዩ ላይ የሚሠሩ ባለድርሻ አካላት ክለቦች ናቸውና ድምፃቸው ሊሰማ ይገባል፡፡ ብዙ ነገር አለ፡፡ ለምሳሌ ትልቅ ኃላፊነት የሚወስድ ሥራ አመራር ውስጥ ያለ ሰው ብዙም መረጃ የሌለው ወይም በአትሌቲክስ ውስጥ ያላለፈ ይሆንና ለእርሱም ይቸግረዋል፡፡ ለስፖርቱም ምንም አይጠቅምም፡፡ ስለዚህ ቀላል የሚሆነው ለክለቦች አብዛኛው ቦታ ቢሰጥ ቢቻል፤ ሁሉንም ባይቻል ደግሞ አብዛኛውን ወሳኙን ስፍራ መስጠት ነው፡፡ ክለቦቹም ሲሰጣቸው ራሳቸው ይፈትሻሉ፡፡ በእነርሱ ችግር የለም ማለት አይደለም፡፡ ክለብ ሆነው ለረዥም ጊዜ ከፍተኛ በጀት ይዘው ምንም ውጤት ሳያመጡ ወደ ፌዴሬሽን የሚናገሩ አሉ፡፡ እነርሱም ቆም ብለው ራሳቸውን ማየት ያስፈልጋቸዋል፡፡ እንግዲህ ስለ አደረጃጀቱ ከኢትየጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መማር ነው፡፡ ብዙ ሲጨቃጨቁ ከርመው ክለቦች መብታቸውን ማግኘት ጀምረዋል፡፡ ይቀረው እንደሆነ ባላውቅም ጥሩ ጀምረዋል፡፡ የአትሌቲክስም ጊዜው አሁን ይመስለኛል፡፡

ሥራውን እየሠሩ ያሉት ባለድርሻዎቹ እነርሱ ቢወስዱት ትልቅ ማበረታቻም ነው፡፡ በጣም ኃላፊነትም ነው፡፡ ከክለብ ሄጄ እዚያ ውስጥ የገባሁት ምን ይዤ ነው ብሎ ራሱን ያያል፡፡ አሁን ግን ከዚያ ከፌዴሬሽኑ የራቁ ናቸው፡፡ ምንም ድምፅ የላቸውም፡፡ ምናልባት አዲስ አበባ ውስጥ ነው ትልቁ አቋም ያለው፤ የአዲስ አበባው ፌዴሬሽን የተደራጀው በክለቦች ነው፡፡ በአዲስ አበባ እንዳለው ሁሉ በብሔራዊውም ፌዴሬሽን በክለቦች መዋቀር አለበት፡፡ ቢያንስ ለጊዜው ወሳኙን የፌዴሬሽን ቁጥር እነርሱ ቢወስዱት ደስ ይለኛል፡፡
ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sat Sep 24, 2011 11:29 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

ሠሞኑን የዳ --ጉን ውድድር ተከትሎ በኢትዮጵያ የወያኔ የስፖርት ባለሥልጣኖች ላይ ከፍተኛ ውርጅብኝ እየደረሠባቸው ነው :: በተለይ ደግሞ በወያኔያዊ ሤራ ወደጎን ተገፍተው የነበሩት አሠልጣኞች ብሶታቸውን እና ለተፈጠረውም ችግር መንስዔ የሆነውን ጉዳይ ይፋ በማውጣት ላይ ናቸው :: እስኪ አቶ ካሡ ዓለማየሁ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአትሌቲክስ ቡድን አሠልጣኝ ምን ይላሉ ? የሪፖርተር ጋዜጣ ዘጋቢ ደረጀ ጠገናው ያደረገላቸውን ቃለ -መጠይቅ ተከታተሉት ::

ደረጀ ጠገናው : ሪፖርተር ጋዜጣ : እሑድ መስከረም 14 ቀን 2004 .. :: ‹‹አትሌቲክሱ ውስጥ እየነገሰ የመጣው ግለኝነት ነው›› አቶ ካሱ ዓለማየሁ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አትሌቲክስ ክለብ ዋና አሠልጣኝ ::

Quote:
የአትሌቲክሱ ውድቀት መነጋገሪያ ከሆነ ሰነባብቷል፣ ይመለከተኛል የሚሉ ሁሉ ለአትሌቲክስ አፋጣኝ መፍትሔ እያሉ ነው፡፡

በተለይ ደግሞ የአትሌቲክሱ ቀጥተኛ ተጠሪ በሆነው በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ላይ ‹‹የይፈተሽልን›› ተፅዕኖው በርትቷል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አትሌቲክስ ክለብ ዋና አሠልጣኝ አቶ ካሱ ዓለማየሁ ለዘርፉ ውድቀት የፌዴሬሽኑ ዝርክርክ መዋቅርና አሠራር በዋናነት ይጠቀሳል ይላሉ፡፡ ደረጀ ጠገናው አነጋግሯቸዋል፡፡

የአትሌቲክሱ ጉዳይ የወቅቱ መነጋገሪያ ለምን ሆነ ?

ለዚህ ሁሉ ያበቃው የፌዴሬሽኑ አሠራር ነው፡፡ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለበት መዋቅራዊ አደረጃጀት የለም፡፡ እነዚህ ነገሮች በሌሉበት ደግሞ ውጤት መጠበቅ የዋህነት ይመስለኛል፡፡

ይመስለኛል ሲሉ ?

በመመርያዎች መጣመም አትሌቶች ተገቢውን ሥልጠና እንዳያገኙ ከማድረጉም በላይ እርስ በርስ እንዳይተማመኑ እያደረገ ነው፡፡ ቀደም ሲል ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚታወቁበት አብሮ መሥራት የለም፡፡ ሁሉም በየፊናው በመሰለው እየሄደ ነው፡፡ ይኼ ደግሞ አትሌቶች በሥነ ሥርዓት እንዳይያዙና ሥልጠናቸውንም መከታተል እንዳይቻል አድርጓል፡፡ ቁጥጥርና ክትትል የለም፡፡ አትሌቶች ምን እንደሠሩና ምን እንደሚጐድላቸው የሚታወቅ ነገር የለም፡፡

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በደንብና በመመርያ እየሠራሁ ነኝ ይላል፡፡ እርስዎና እርስዎን መሰል ሙያተኞች ደግሞ አለ የሚባለው ደንብ የሚያሠራ ሳይሆን፣ ሙያተኞችንና አትሌቶችን የሚያጠፋ ነው ሲሉ በተደጋጋሚ ይሰማሉ፡፡ ከዚህ አንፃር የአትሌቶች የብቃት ደረጃ ማወቅ አልተቻለም ሲሉ በግልጽ ቢያስረዱን ?

ለእያንዳንዱ ነገር ጊዜና ወቅት እንዳለው ሁሉ፣ አትሌትም ከዚያ የተለየ አይደለም፡፡ በአሁኑ ወቅት አንድ አትሌት መቼና በምን ያህል ዕድሜው በምን ዓይነት ሩጫ መሳተፍ እንዳለበት ሳይንሱ ይነግረናል፡፡ ይኼ በአሁኑ ወቅት እየተሠራበት አይደለም፡፡ አንድ አትሌት ስለሮጠ ብቻ ዛሬ ትራክ ላይ፣ ነገ ደግሞ ግማሽ ማራቶን እንዲሮጥ ይደረገል፡፡ እንደገና ተመልሶ ሦስት ሺሕ ሜትር ይሮጣል፡፡ ይኼ እንዴት ይሆናል ? አትሌቱ ገንዘብ ማግኘቱን ካልሆነ ነገ ምን ጉዳት እንዳለው አያውቅም፡፡ መቆጣጠር ያለበት አሠልጣኙና ፌዴሬሽን ናቸው፡፡ የእያንዳንዱ አትሌት መወዳደርያው ተለይቶ መታወቅ አለበት፡፡ ችግሩን ለማስወገድ የሚቻለው መደማመጥ፣ መነጋገርና መወያየት ሲቻል ነው፡፡ ይኼ የለም፡፡ ሥልጠናውም፣ አመራሩም ችግር አለባቸው፡፡

ሥልጠናን በተመለከተ አትሌቶች ዋናውን ሥልጠና ማግኘት የሚገባቸው ክለብ ውስጥ ነው፡፡ ወደ ብሔራዊ ሲመጡ መሥራት የሚጠበቅባቸው የቅንጅት ሥራ መሆኑን የሚናገሩ አሉ፡፡ የክለብ አሠልጣኝ እንደመሆንዎ ምን ይላሉ ?
ቀደም ባሉት ዓመታት የምንሠራው በዚያ መልክ ነበር፤ አሁን ግን ቀርቷል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ፌዴሬሽኑ ለክለቦች ትኩረት አይሰጥም፤ አያከብራቸውም፡፡
ክብር አልተሰጠንም በሚል ማሠልጠን አቁማችኋል ማለት ነው ?

ማሠልጠንማ እያሠለጠንን ነው፡፡ ችግሩ ቀደም ሲል አትሌቶች ለብሔራዊ በሚመረጡበት ጊዜ እንዲህ እንዳሁን ክለባቸውን እርግፍ አድርገው የሚተውበት አሠራር አልነበረም፡፡ አሁን ግን አንድ አትሌት ብሔራዊ ነው ከተባለ ከክለብ ቁጥጥር ውጪ ነው፡፡ የክለብ ድርሻ ደመወዝ መክፈል ካልሆነ አትሌቱ የት ገባ ? ምን ዓይነት ሥልጠና እያገኘ ነው ? አይታወቅም፡፡ ተተኪ የሚባሉትም ትልልቆቹን አርዓያ እያደረጉ ለክለብ ትኩረት አይሰጡም፡፡ ማናጀር የሚለውን ካልሆነ፣ ክለብ ቀርቶ ፌዴሬሽኑን የሚሰሙት በሁለተኛ ደረጃ ነው፡፡ ልምድ ሳይኖራቸው ወደ ውድድር እንዲሄዱ እየተደረገ ነው፡፡ ሌላው ክለቦች ማዘውተርያ የላቸውም፡፡ ይህም ሌላው ችግር ነው፡፡

ፌዴሬሽኑ፣ ማናጀርና የክለብ አሠልጣኞች ምን ዓይነት ሥልጠና እንደምትሰጡ አትነጋገሩም ?

እንደዚህ ዓይነት አሠራር ከጠፋ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ቀደም ባሉት ዓመታት እነ ዶክተር ወልደ መስቀል ኮስትሬ ዋና አሠልጣኝ በነበሩበት ጊዜ፣ ለብሔራዊ ያስመረጡ የክለብ አሠልጣኞች ምን ዓይነት ሥልጠና እንደሰጠን የምንነጋገርበት ሁኔታ ነበር፡፡ አሁን ይኼ የለም፡፡ አሁን ያለው አሯሯጭ (ፔስ ሜከር ) በሚሉት እያንዳንዱ አትሌት ልምምድ ይሠራል፡፡ ከዚህ ይልቅ ስምምነቱን ፈጥሮ ሁለትና ሦስት አትሌቶች አንድ ላይ ልምምድ እንዲሠሩ ቢደረግ አንዱ ከሌላው የሚበልጥበትንና የሚያንስበትን ሁኔታ ማወቅ ይቻላል ብለን ጠይቀናል፡፡ ነገር ግን ይህን የምንል እንደ ጠላት እየተቆጠርን ከፌዴሬሽን እንድንርቅ ነው የተደረግነው፡፡

ለአትሌቲክሱ ውድቀት ነባር አሠልጣኞች ተጠራርገው እንዲወጡ መደረጉ ሌላው ችግር እንደሆነ የሚናገሩ አሉ፡፡

እውነት ነው፡፡ ምክንያቱም ሁላችንም በአንድ ጊዜ መውጣት የለብንም፡፡ መሆን የነበረበት በነባሩ ሥር ተተኪና ተምረዋል የሚባሉትን በማድረግ ልምድ እንዲቀስሙ ቢደረግ የተሻለ ይሆን ነበር፡፡ እኛ ድሮ የአትሌቲክስ ትምህርት ተምረን እንደመጣን በአንድ ጊዜ የብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ አልሆንም፡፡ መጀመርያ ወደ ክለብና ፕሮጀክት እየወረድን ተተኪ አትሌቶች እንድናመጣ ነው የሚደረገው፡፡ ወደ ብሔራዊ ቡድን እንድንመጣ ሲደረግም፣ በእነ ዶክተር ወልደ መስቀል ሥር ሆነን ልምድ እንድንቀስም ነው የተደረግነው፡፡ አሁን እየሆነ ያለው ግን በሰውነት ማጐልመሻ (ፊዚካል ኢዱኬሽን ) ዲግሪ ስላለው ብቻ ዋና አሠልጣኝ እንዲሆን ነው፡፡ ይኼ ዓለም አቀፉን ደንብ የሚጥስ ነው፡፡

ለምን ተነካን በሚል ምክንያት እንዳይሆን ?

በፍጹም፤ በግሌ ውስጤ ያለው የአትሌቲክስ ፍቅር ካልሆነ ምክንያት የሚባለው ነገር አይገልጸኝም፡፡ እስከ 2000 .. ድረስ የነበረው አሠራር ማናችንም ስንመረጥ ችሎታችን እየተገመገመ በተግባርም እየታየ ነበር፡፡ 2000 .. በኋላ ግን ቢፒአር ተብሎ ከመጣ በኋላ ነው ሁሉ ነገር መበላሸት የጀመረው፡፡

ቢፒአሩ ለመሆኑ ማሳመኛዎ ምንድነው ?

ምክንያቱን ይኼ ነው ማለት ባልችልም፣ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ግን ሰላም የለም፡፡ የምንተያየው የጐሪጥ ነው፡፡ በግሌ ችግር አለ ተቀራርበን መነጋገርና መወያየት አለብን የሚል ሐሳብ አቅርቤ ያተረፍኩት ጥላቻንና ቅጣትን ነው፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አትሌቲክሱ ውስጥ እየነገሰ የመጣው ግለኝነት ነው፡፡ በወቅቱ በተመደቡበት የአሠልጣኝነት ቦታ ትክክለኛ ሥራ አልሠራም ተብሎ የተባረረ አሠልጣኝ፣ ዛሬ ዋና አሠልጣኝ ተብሎ እንዲቀመጥ ተደርጓል፡፡ ከቤጂንግ ኦሊምፒክ መልስ እንገማገም ብዬ ነበር የሚሰማኝ አልተገኘም፡፡ የሆነው ግን ነባር አሠልጣኞች ዓይናችሁ ላፈር ነው የተባልነው፡፡

መነካት አልነበረብንም እያሉ ነው ?

እኔም ሆንኩ ሌሎች ነባር አሠልጣኞች ጥያቄያችን ለምን እንባረራለን ሳይሆን፣ አግባብ ባለው መንገድ ደካማና ጠንካራ ጐናችን ተገምግሞ መሆን አለበት ነው፡፡ አንድ ሙያተኛ በግለሰቦች ጥላቻ ብቻ የሚባረር ከሆነ ጥያቄያችን ችግር ያስከትላል ነው፡፡

እርስዎና ሌሎችም ውጤት እያለን ነው የተባረርነው እያላችሁ ነው፡፡ ነገር ግን ከሲድኒ ኦሊምፒክ በኋላ እርስዎም በነበሩባቸው ኦሊምፒኮች፣ የዓለም ዋንጫዎች፣ የዓለም አገር አቋራጭና እንዲሁም በወጣቶች ሻምፒዮና የአትሌቲክሱ ውጤት እየቀነሰ ከመምጣቱም በላይ የተገኘውም ቢሆን በጥቂት አትሌቶች ነው፡፡ እነዚያን ጥቂት አትሌቶች ለመተካት የፈጠራችሁት ነገር የለም፡፡

ከሲድኒ ኦሊምፒክ ቀጥሎ በነበረው የአቴንስ ኦሊምፒክ ላይ በአሠልጣኞችና በአትሌቶች መካከል ከፍተኛ ችግር ተፈጥሮ ነበር፡፡ ሁኔታ ተተኪ አትሌቶች ላይ እንዳንሠራ ያደረገ ይመስለኛል፡፡

ችግሩ ምን ነበር ?

በእነ ዶክተር ወልደ መስቀል ኮስትሬና ብርሃኔ አደሬ፣ እንዲሁም በሌሎችም መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ ነበር፡፡ ችግሩን ተከትሎ አንዳንድ የፌዴሬሽን ሰዎች ጣልቃ መግባት ጀመሩ፡፡ ቀጥሎ የዋናና የወጣት ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ በሚል እንድንበታተን ተደረገ፡፡ እኔ የወጣት ብሔራዊ ቡድን የአምስትና የአሥር ሺሕ ሜትር ዋና አሠልጣኝ ሆኜ ተመደብኩ፡፡ በዚያን ጊዜ የያዝኳቸው አትሌት ኢብራሂም ጀይላን፣ ሁነኛው መስፍን፣ አየለ አብሽሮ፣ ኢማና መርጊያና ደጀን ገብረ መስቀል ነበሩ፡፡ በሴቶችም እንደዚሁ አድርጌ ወደ 40 የሚጠጉ ወጣት አትሌቶች በመያዝ ውጤት አምጥቻለሁ፡፡ በግሌ ተተኪ አትሌቶችን አፍርቻለሁ፡፡ እንደነ መሠረት ደፋር፣ ሚሊዮን ወልዴና ሌሎችንም መጥቀስ ይቻላል፡፡ ለውጤቱ መውደቅ አትሌቶች ከማናጀር ጋር የመሥራት ፍላጎት እያሳደሩ መምጣትና የፌዴሬሽኑ ቁጥጥር ማነስ ያመጣው ጣጣ ይመስለኛል፡፡ ከዚያም አትሌቶች አብሮ ከመሥራት ይልቅ መለያየትን ሲመርጡና ዝም ሲባሉ ችግሩ የነገሮች መበላሸት ድምር ውጤት እየሆነ መጣ፡፡ ሌላው ቀርቶ አትሌቶች ለአገራዊ ውድድር አብረው መጓዝ ሲገባቸው ማናጀሮች አንዱን በቱርክ፣ ሌላውን በኢምሬትና በኢትዮጵያ አየር መንገድ እየበታተኑ እንዲሄዱ ነው ሲያደረጉ የነበረው፡፡ አሠልጣኞች እርስ በርሳችን እንዳንግባባ ይደረግ ነበር፡፡ ይባስ ተብሎ አትሌቱ በፈለገው አሠልጣኝ ይሠልጥን ተብሎ ብሔራዊ ቡድን እንዲፈርስ ተደረገ፡፡ መጨረሻውም እንደምንመለከተው ሆነ፡፡

አንዳንዶቻችሁ ዘመናዊ ሥልጠናን እንደማትከተሉ፣ ይኼ ደግሞ ከአካዳሚክ ጋር የተያያዘ ችግር እንደሆነባቸው የሚናገሩ አሉ፡፡

እየገረመኝ ያለው ይኼ አባባል ነው፡፡ ሳይንሳዊ ሥልጠናንና አትሌቲክስን በተመለከተ በጀርመን አገር ትምህርቱን የወሰድኩት ለዘጠኝ ወራት ያህል ነው፡፡ አትሌቲክስን ብቻ ማለት ነው፡፡ የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (አይኤኤኤፍ ) ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ያለውን የአሠልጣኝነት ደረጃ ሥልጠና የሚሰጠው 14 ቀናት ነው፡፡ እስከ አምስት ያለውን ደረጃ ደግሞ በአይኤኤፍ ሕግ ዲፕሎማ ይጠይቃል፡፡ ይህ ማለት በአማርኛ፣ በኬሚስትሪ፣ በባዮሎጂ ወይም በሒሳብ ማለት አይደለም፡፡ አሁን አሠልጣኝ እየተባሉ ያሉት በሰውነት ማጐልመሻ (ፊዚካል ኢዱኬሽን ) የማሠልጠን ሳይሆን የማስተመር ትምህርት ተምረው የመጡትን ነው፡፡ ልዩነታችን ይኼ ነው፡፡ ፌዴሬሽኑም ያልተረዳው ይህንኑ ነው፡፡ አስተማሪ አሠልጣኝ ሊሆን አይችልም፡፡

የተባረርነው በብቃት ችግር አይደለም እያሉ ነው ?

በችሎታ ቢሆንማ ኖሮ እንገማገም የሚለው መጀመርያ ሐሳብ ከእኛ ባልመጣ ነበር፡፡ ሌላው በአይኤኤኤፍ ሕግ አንድ አሠልጣኝ አሠልጣኝ ለመባል ታች ወርዶ መሥራት አለበት፡፡ አሁን አሠልጣኝ እየተባሉ የተቀጠሩት እንኳን ታች ወርደው ሊሠሩ ቀርቶ የአይኤኤኤፍ አንደኛ ደረጃ ሥልጠና እንኳ ያልወሰዱ ናቸው፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን ከስፖርቱ መርህ ጋር የሚቃረን የዓለም አቀፍ ሕግን የሚጣረስ ነገር ብሔርተኝነት በፌዴሬሽኑ ውስጥ ነግሷል፡፡ አመራሩስ ቢሆን የትኛው ነው የስፖርት አስተዳደር የተማረው ? አይኤኤኤፍን የሚመራው ላሚንዲያክ የስፖርት አስተዳደር ተማሪ ነው፡፡ ምክትሉ የስፖርት አስተዳደር ተማሪ ነው፡፡ ፕሮፋይላቸውን ማየት ይቻላል፡፡ እንደነዚህ ያሉት መሠረታዊ ነገሮች ቀርቶ በአትሌቲክሱ ዋነኛ ባለድርሻ የሆኑት ክለቦች የጠቅላላ ጉባዔ አባል አይደሉም፡፡ ክፍተቱ እስከዚህ ድረስ ነው፡፡
ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sat Sep 24, 2011 11:50 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ወገኖቼ :-

ዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬ ባለፈው ዓመት በጥር ወር 2003 .. (በጥምቀት አካባቢ ) ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን 'አርሂቡ ' መርሃ -ግብር ተጋባዥ ዕንግዳ ሆነው የተናገሯቸውን ቁምነገሮች ተከተታሉ :: በተቻላችሁ መጠን የጋዜጠኛውን አልባሌ አነጋገሮች ታግሣችሁ በእርሣቸው ንግግር ላይ አተኩሩ :: "የቡድን ሥራ ጠፍቷል : ግለኝነት አመዝኗል : ልምድ ያላቸው አሠልጣኞች ወደጎን ተገፍተዋል :" ሌላም ሌላም ብዙ ተናግረዋል :: ስለዚህ ከአንድ ዓመት በፊት በመጋቢት ወር 2002 .. ፖላንድ የዓለም የአገር አቋራጭ የሩጫ ውድድር በመሠለች መልካሙ በተገኘች 1 የነሐስ ሜዳሊያ ብቻ የተሸኘነውና ከዚያም ባለፈው ክረምት ደግሞ በዳ -- ውድድር በኢብራሒም ጄይላን 1 የወርቅ እና በሌሎች አራት አትሌቶች በተገኙ 4 የነሐስ ሜዳሊያዎች ብቻ የተወሰንነው ያለምክንያት አልነበረም :: ይህ የሚያረጋግጠው በተደጋጋሚ የታየው የውጤት መክዳት ከየትም የመጣ ሣይሆን ካለው ሥር የሠደደ የስፖርት አስተዳደር : ሥልጠናና መረጣ ችግር የመጣ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል :: ቃለ -መጠይቁን ተከታተሉት ::

ምንጮች :-

ክፍል 1:- Dr. WoldeMeskel Kostre - Arhibu Interview, Clip 1 of 6.

ክፍል 2:- Dr. WoldeMeskel Kostre - Arhibu Interview, Clip 2 of 6.

ክፍል 3:- Dr. WoldeMeskel Kostre - Arhibu Interview, Clip 3 of 6.

ክፍል 4:- Dr. WoldeMeskel Kostre - Arhibu Interview, Clip 4 of 6.

ክፍል 5:- Dr. WoldeMeskel Kostre - Arhibu Interview, Clip 5 of 6.

ክፍል 6:- Dr. WoldeMeskel Kostre - Arhibu Interview, Clip 6 of 6.


ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::


Last edited by ተድላ ሀይሉ on Sun Sep 25, 2011 12:12 am; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sun Sep 25, 2011 12:01 am    Post subject: Reply with quote

ገነነ መኩሪያ ከዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬ ጋድ ያደረገው ቃለ መጠይቅ ክፍል 3

ምንጭ :- ገነነ መኩሪያ : ሊብሮ ጋዜጣ : ቅዳሜ መስከረም 13 ቀን 2004 .. :: / ወልደመስቀል ኮስትሬ (ክፍል 3)::


Quote:
ሊብሮ፡ - ጊዮርጊስ ክለብ ውስጥ በአሠልጣኝነት ጊዜዎ የሚያስታውሱት ለየት ያለ ነገር አለ ?

/ /መስቀል ኮስትሬ፡ - ብዙ አለ፡፡ ምክንያቱም አብዛኛው የኳስ ትውስታዎች ያሉት ጊዮርጊስ ውስጥ ነው፡፡ በሜዳ ግጥሚያ ትዝ የሚለኝ በአንድ ወቅት በራሪ ኮከብ በጣም ስም ያገኘበት ጊዜ ነበር፡፡ እያሸነፈ፣ እያሸነፈ መጥቶ ከጊዮርጊስ ጋር ደረሰው፡፡ጊዮርጊስንም ያሸንፋል በሚል መርካቶ ለሁለት ተከፍሎ ነበር፡፡ በራሪ ጊዮርጊስን ካሸነፈ አብዛኛውን የመርካቶ ደጋፊ ወደእሱ መሳብ ይችላል፡፡ ነፍሱን ይማረውና ሰለሞን ተሰማ እኔን ለቃለ ምልልስ ጠርቶኝ ጥሩ የተጫወተ ያሸንፋል የሚል አስተያየት ሰጠሁ፡፡ ከበራሪ ደግሞ አቶ ይመስገን ነበር የተጠሩት፡፡ ‹‹ እንኳን ሳንጆርጅ ሳንቶስም ከብራዚል ቢመጣ…›› በማለት ከጨዋታው በፊት የሰጠው መግለጫ ፉክክሩን አባባሰው፡፡ በዚህ መሀል ጌታቸው /ዱላ / ጠፋ፡፡ በስንት መከራ ተፈልጎ መጥቶ እንደተጎዳ ተሠለፈ፡፡ በተፎከረበት ጨዋታም ጊዮርጊስ 71 አሸንፎ ነገሩን ሁሉ አረጋጋው፡፡ ያን ጊዜ ጊዮርጊስ ውስጥ የነበሩት ተጨዋቾች ክለቡን የመውደድ ስሜታቸውና ወኔአቸው ነበር ለውጤት የሚያበቃቸው፡፡ የዚያን ያህል ደግሞ ተጨዋቾቹ ትዕግስተኞች ናቸው፡፡ አንድ ጊዜ አስመራ ሄደን ድብድብ ተነሳ፡፡

ሊብሮ፡ - ከሜዳ ውጭ ነው ሜዳ ውስጥ ?

/ /መስቀል፡ - ሜዳ ውስጥ ነው፡፡ ከሀማሴን ጋር ነው የምንጫወተው፡፡ይህ ጨዋታ ለጊዮርጊስ ወሳኝ ነው፡፡ ጨዋታው እነሱ ሜዳ ቢካሄድ ለኛ ማሸነፉ ጠቃሚ ነው፡፡ እነሱ ረብሻ ለማስነሳት ፈልገዋል፡፡ አንዱ ትግርኛ ሰምቶ መጥቶ ለኛ ተጨዋቾች ነገራቸው፡፡ ነፍሱን ይማረውና ጌታቸው አብዶ በጣም ጎበዝ ተጨዋች ነው፡፡ እሱን አበሳጭተው ሊያስወጡት ፈልገዋል፡፡ በትግርኛ ሲያወሩ ሰምቶ የነገረንም ሰው ጌታቸው እንደሚፈልጉት በመግለጽ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶታል፡፡ እንደተጀመረ 20ኛው ደቂቃ ከበክረጽዮን ጋር ተላከፈ፡፡ ቢጫ ካርድ አየ፡፡ መሰመር ጋር ሄጄ ከእንግዲህ ወዲያ አትናገር አልኩት፡፡ ወዲያው ሊሄድ ሲል ጠራሁትና እልህ ውስጥ ከገባህ ልቀይርህ አልኩት፡፡ ምክንያቱም በቀይ ከወጣ ተጨዋች ይጎላል፡፡ ምንም ችግር የለም ተረጋግቼ እጫወታለሁ አለ፡፡ ዳኛው አልቢትር ተገኝ ነበሩ፡፡ ጌታቸው ይጣላል ብለው እየተከታተለ ነው፡፡ ከዚያ ከእስማኤል ጋር ለቴስታ መትተው ወደቁ፡፡ አልቢትር ተገኝ ከኋላው ቆሞ ያየዋል፡፡ ዞር ብሎ ዳኛ ማየት ሲገባው እልህ ውስጥ ስለገባ እስማኤልን በቴስታ ብሎ አደማው፡፡ በቀይ ወጣ፡፡ ዳኛው ሲያሰውጣው ከወጣሁ ላይቀር ብሎ እዚያው እስማኤልን መምታት ጀመረ፡፡ ከዚያ ተነሳና ከሌሎች ጋር ቦክስ ተያያዘ፡፡ ሌሎችም እርስ በርስ ተያይዘው ግብ ግብ ተፈጠረ፡፡ ውጭ ያሉት ተመልካቾች ገብተው በመገላገል ፀቡ በረደ፡፡ ጥቂት ቆይቶ በኩረጺዮን ሰበታን ጠልፎ ጣለውና ሪጎሬ አገኘን፡፡ እየተጨቃጨቁ እያለ አለማየሁ (ፊኛ ) እዚያ አካባቢ ይመጣና ለእነ ፓቼ ‹‹ ገንዘባችን እኮ ቀልጦ አልቀረም፡፡ 3 ብር ለበኩረጽዮን ሰጠነው ይኸው ጠልፎ ሪጎሬ አሰጠን›› እያለ ሲናገር እውነት መሰላቸውና እነሱ ከበኩረጽዮን ጋር መጣላት ጀመሩ፡፡ ከዚያ አለማየሁ ሌሎቹንም የሀማሴን ተጨዋቾች እርስ በርስ ያያይዛቸው ጀመረ፡፡ በኋላ የኛ ልጆች ተረጋጉ፡፡ ግን ሜዳው ውስጥ ያለው ሁኔታ መጥፎ ነበር፡፡

ሊብሮ፡ - ጨዋታው በሰላም አለቀ ?

/ /መስቀል፡ - እንዴት ይለቅ ? እነሱ እኮ በሜዳቸው ማሸነፍ ነው የፈለጉት፡፡ 11 እያለን መንግስቱ አገባና 21 አደረግናቸው፡፡ ከዚያ እነሱ ጸብና ድብድብ ጀመሩ፡፡ ሰበታን መተው ጣሉት፡፡ / ያየህይራድ ቅጣው የፌዴሬሽኑ ሀኪም ስለነበሩ ወደ ሜዳ ገብተው ሰበታን አናወጣም አሉ፡፡ ምክንያቱም በተኛበት ሰበታን በብሎን ጫማ የሀማሴን ተጨዋቾ ሊረግጡት ይፈልጋሉ፡፡ የዚያን ቀን ሰበታ በጣም ስላስቸገራቸው ተናደዋል፡፡ እኔ ገባሁና ሰበታን ተሸክሜ እየተንገዳገድኩ ይዤው ሄድኩኝ፡፡ ምክንያቱም በጣም ከባድ ነው፡፡ ሜዳው መስመር ላይ እየደረስኩኝ የእነሱ ተጨዋች በረከት መጣና እኔን የሚያግዘኝ መስሎ በቦክስ አፍንጫዬ ላይ ሲመታኝ ተላጠና ደማ፡፡ ሰበታን ይዤ እንደ እብድ ነው ያደረገኝ፡፡ ከዚያ ሰበታን አስቀምጬ ከእሱ ጋር ድብድብ ያዝን ፡፡ ገላጋዮች ቢገቡም እኔ አለቅም አልኩኝ፡፡ ተጨዋቾቹ እንደገና እኔን እየጎተቱ ይዘውኝ ወጡ፡፡ እንዲህ እያለ ጨዋታው አለቀ፡፡ በጣም ደስ ያለን ተጎድተንም ማሸነፉችን ነው፡፡

ሊብሮ፡ - ጊዮርጊስ በአሠልጣኝነትዎ የሚከፍልዎት ደሞዝ ስንት ነበር ?

/ /መስቀል፡ - ዋናው እኔ የምሠራው ፊዚካል ማሰልጠን ነው፡፡ ለቴክኒኩ አንዳንዶቹን ያመጣሉ፡፡ ጋሽ ይድነቃቸውም አንዳድ ጊዜ መጥቶ ቴክኒካል የሆኑ ነገሮችን ይመክራል፡፡ እንግዲህ አብዛኛው ስራ እኔ ጋር ነው ያለው ማለት ነው፡፡ ልምምድ ቀርቼ አላውቅም፡፡ ግን ወደ 4 ዓመት ያህል ሳሰለጥን አንድ ቀን ደመወዝ ተከፍሎኝ አያውቅም እኔም ጠይቄ አላውቅም፡፡ ክለቡ ያኔ ህዝባዊ ነው፡፡ ከጠላት ጊዜ ጀምሮ የህዝቡን ፍቅር ይዞ የመጣ ነው፡፡

ሊብሮ፡ - እርስዎ ለምን ደመወዝ አልጠየቁም ?

/ /መስቀል፡ - ጊዮርጊስ ለማንም ደመወዝ አይከፍልም፡፡ ይህ ከበፊትም ጀምሮ ተይዞ የመጣ ነው፡፡ ጋሽ ይድነቃቸው ለጊዮርጊስ ሲጫወትም ሲያሰለጥንም 5 ሳንቲም አላገኘም፡፡ ከሚሠራበት መስሪያ ቤት የሚያገኘውን ደመወዝ አብዛኛውን ሊጊዮርጊስ ክለብ ነው የሚያውለው፡፡ ስለዚህ ማንኛውም ሰው ጊዮርጊስ ውስጥ ሙያውን ገንዘቡን ይዞ መጥቶ ግልጋሎት ይሰጣል እንጂ የጥቅም ጥያቄ አያነሳም፡፡ ወይም ከክለቡ ምንም የሚያገኘው ነገር የለም፡፡ በኋላ ግን ለትራንስፖርት ተብሎ 1.25 ይሰጥ ነበር፡፡ ይህንንም የሚከፍሉት ክለቡን የሚደግፉ ግለሰቦች ከኪሳቸው እያወጡ ነው፡፡ መንግስቱ ወርቁ ሲጫወት ደመወዝ ተከፍሎት አያውቅም፡፡ ግን በቅ /ጊዮርጊስ ውስጥ ያገኘው ስም ከህዝብ ጋር አስተዋውቆታል፡፡ ያን ጊዜ ተጨዋች የነበሩትም አብዛኞቹ ሌላ መሳሪያ ቤት እየሠሩ ለጊዮርጊስ ይጫወታሉ እንጂ ጊዮርጊስ ክለብ ለተጫወቱበት አይከፍላወም፡፡ ለእኔም እንደዚሁ፡፡

ሊብሮ፡ - ክለቡ ከሜዳ ገቢ ያገኝ አልነበረም ?

/ /መስቀል፡ - ይህ ወደ በኋላ የመጣ እኮ ነው፡፡ ለትጥቅ መግዣ፣ ለቀለብ የሚሆነውን ደጋፊው ነበር የሚችለው፡፡ በኋላ የሜዳ ገቢ ሲመጣ ቡድኑ ብሉ ናየል ሆቴል መቀመጥ ጀመረ፡፡ ምክንያቱም ሻል ያለ ነገር ተገኘ፡፡ እንዳውም 1964 ይመስለኛል ከሜዳ ገቢ ለሆቴል ተከፍሎ 14 ብር ትርፍ ተገኘ፡፡ ያን ጊዜ ክለቡ ሀብት አገኘ ተብሎ ብዙ ተወራለት፡፡ ምክንያቱም ዓመቱ መጨረሻ ላይ ይህን ያህል ገንዘብ አትርፎ አያውቅም፡፡ ከዚያ በፊት ልምምድ ተሠርቶ አነስተኛ ሆቴል ነው ተጨዋቾቹ የሚመገቡት፡፡ እንዳውም በፊት አባሲዮን ሜዳ ልምምድ ከሠሩ በኋላ ጠላ በገንቦ ይመጣና አንዳንዶቹ ይጠጣሉ፡፡ በዚያው ወደቤትህ ትሄዳለህ፡፡ ዋናው ልገልፅ የፈለኩት ቲሙ በጥቅም ሳይሆን በመፋቀር የተመሰረተ ነበር፡፡

ሊብሮ፡ - እዚህ ሁሉንም በልጣችሁ ሻምፒዮና ሆናችሁ፡፡ ለአፍሪካ የክለብ ሻምፒዮናስ ውጤታችሁ እንዴት ነበር ?

/ /መስቀል፡ -ጥሩ አልነበረም፡፡ ከታንዛኒያው ያንግ አፍሪካ ጋር ነው የተጋጠምነው፡፡ እዚህ 00 ወጣን፡፡ እዚያ ያልተጠበቀ ሁኔታ ተፈጠረ፡፡ ተጨዋቾቹም ነርቨስ ሆኑ በዚህም 50 ተሸነፍን፡፡ እንዳውም ትዝ የሚለኝ ረብሻ ሁሉ ተነስቶ ነበር፡፡ 40 ከሆንን በኋላ ሰዓት ለማባከን በሚል የተጋጣሚ ቡድን ተጨዋቾች ኳሱን ወደ ማዕዘን እየወሰዱ ይዘውት ይቆማሉ፡፡ በዚህ ብቻ አላበቁም፡፡ ለመዘነጥ ብሎ አንድ የነሱ ተጨዋች ኳሱን አቆመና እግሩን ኳሱ ላይ አድርጎ የጫማውን ክር ማሰር ጀመረ፡፡ እንዲህ አይነት ነገር ደግሞ በጣም ያናድዳል፡፡ እኛ ተመርተናል፡፡ መመራቱ ያናድዳል፣ የልጁ ድርጊት ደግሞ ይበልጥ ያበሳጫል፡፡ ታምራት /ቴክስ / እየሮጠ ሄደና ልጁን በጠረባ ብሎ ጣለው፡፡ ተጎዳ፡፡ ሌሎች መጡና ታምራትን መቱት፣ተፈነከተ፡፡ የኛም ልጁች ድብድቡ ውስጥ ገቡ፡፡

ሊብሮ፡ - ሁሉም ?

/ /መስቀል፡ - /ሳቅ / አንድ ተጨዋች ሸሸ፡፡ የተፈጥሮ ነገር ሆኖ ፍራቻ አለበት፤ ሌሎቹ ግን ተደባደቡ፡፡ እንደገና ጨዋታው እየተካሄደ አንድ የእነሱን ተጨዋች ፔናሊቲ ኤሪያ ውስጥ አለማየሁ አፈረጠውና ሪጎሬ ተሰጠ፡፡ ገባ፡፡ ብቻ ጨዋታው ምስቅልቅሉ የወጣ ነበር፡፡

ሊብሮ፡ - ጊዮርጊስ ውጭ ሀገር ሄዶ በተጫወተበት ጊዜ አሸንፎ አያውቅም፡፡ ግን ሁሌም ምክንያቶች ይቀርባሉ፡፡ እርስዎም አሁን ለሽንፈቱ ምክንያት ነው የሰጡት፡፡ ትልቅ ችግር ግን ምን ይመስልዎታል ?

/ /መስቀል፡ - ዌል / እነዚህ ሰፋ ያለ ማብራሪያ የሚያስፈልጋቸው ናቸው፡፡ እርግጥ ነው እኔ አሰልጣኝ በነበርኩበት ሰዓት ጊዮርጊስ ኢንተርናሽናል ውድድር ላይ ጥሩ አልነበረም፡፡ ጥሩ ያልነበረበት ደግሞ ምክንያት አለው፡፡

ሊብሮ፡ - እነዚህና ሌሎችን ወደ በኋላ እንመለስባቸዋለን፡፡ ሳይንሳዊ ስልጠና በተገቢው መንገድ ለእግር ኳሱ ቢሰጥ ለውጥ ይመጣል ብለው ይገምታሉ ?

/ /መስቀል፡ - በትክክል፡፡ ግን የሚያሰራ ሰው ያስፈልጋል፡፡

ሊብሮ፡ - እርስዎ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን አሰልጥነዋል፡፡ የበፊቱንና የአሁኑ ልዩነት ያውቃሉ፡፡ አሁን ሳይንሳዊ ስልጠና ባለመሰጠቱ በእግር ኳሱ ከሌሎች ሀገሮች ጋር ስንተያይ ለውጥ አልመጣም የሚል ግምት ነው ያለዎት ?

/ /መስቀል፡ -ትክክል ሳይንሳዊ ስልጠና ፍጥነትና ጉልበት ላይ ነው ትኩረት የምታደርገው፡፡ የኛዎቹ ተጨዋቾች ኳስ ይችላሉ፡፡ ይህንን ካዳበርክ ለውጥ የማታመጣበት መንገድ የለም፡፡

ሊብሮ፡ - እንግዲህ ሳይንሳዊ ስልጠና ፍጥነትና ጉልበት ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡ እኛ ደግሞ በእግር ኳስ ድክመታችን እዚህ ላይ ነው፡፡ ፍጥነቱን እንዴት ማዳበር እንችላለን ? ለምሳሌ በአጭር ርቀት ሯጮች የኢትዮጵያ አትሌቶች ራሳቸው ፈጣን አይደሉም፡፡ ለኦሎምፒክ ቀርቶ በአፍሪካም ውጤት የላቸውም፡፡ ለእግር ኳሱ ታዲያ ፈጣን ተጨዋች ከየት ይመጣል ?

/ /መስቀል፡ - ለዚህ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ልሰጥህ እችላለሁ፡፡

ሊብሮ፡ - ማብራሪው ሰፋ ካለ ጥያቄዎችም ይከተሉታል፡፡ ይህንንም ወደ በኋላ እንመለስበታለን፡፡ ለመሆኑ ጊዮርጊስ ውስጥ በአሰልጣኝነት ብዙ ቆዩ ?

/ /መስቀል፡ - 4 ዓመት ያህል ሰራሁና የከፍተኛ ትምህርት እድል ስላገኘሁ እንደገና ወደ ሀንጋሪ ሄድኩኝ፡፡ የወጣሁት 1966 በመሆኑ ያኔ የለውጡ ግርግር ተጧጡፎ ነበር፡፡ እንግዲህ እኔ ኮተቤ 5 ዓመት ሰርቼ እንደገና ለድህረምረቃ ነው ወደ ሀንጋሪ ተመልሼ የሄድኩት፡፡ እዚያ 2 ዓመት ተማርኩኝ፡፡ ትምህርቴን እንዳጠናቀቅኩኝ 4 ዓመት በላይ በጥናትና ምርምር ላይ ቆይቼ ‹‹ ካንዲዴት ሳይንስ›› በሚል ትምህርት ተመረኩኝ፡፡ ጥናቱ እንግዲህ በዚሁ የስፖርት ዘርፍ ሆኖ የተለያዩ ነገሮችን ይይዛል፡፡ ለምሳሌ በከፍተኛና ዝቅተኛ የአየር ቦታ አትሌቶች ልምምድ በሚያደርጉበት ሰዓት የሚገኘው ውጤት ከሜክሲኮ የኦሎምፒክ ውጤት በመነሳት ጥናት አቅርቤአለሁ፡፡ እንግዲህ ይህ ከሚጠቀሱት ወስጥ አንዱ ነው፡፡ በዚህ ዘርፍ .ኤች . ለመስራት 4 ዓመት መቆየት ነበረብኝ፡፡ ይህንንም ያገኘሁት ከብዙ ውጣውረድ በኋላ ነበር፡፡ 4 ዓመት ከጨረስኩ በኋላ ለምረቃ ተዘጋጀን፡፡ እኔ እንግዲህ በአትሌቲክስ ነው የመመረቂያ ፅሁፌን ያዘጋጀሁት፡፡ አማካሪ ነበረኝ ከእሱ ጋር ነው አብረን የምንሰራው፡፡ 3 ዓመት ሪሰርቹን ጨርሰን፡፡ መጨረሻ ለምረቃ ተጠራን፡፡ አድቫይዘር ነው የሚያቀርበው አዳራሹ ውስጥ በጣም ብዙ ሰው አለ፡፡ ከኢትዮጵያ እኔ ነኝ ያለሁት፡፡ የሰራኸውን ስራ በአጭር ቃላት ታቀርባለህ፡፡ ከዚያ ገለፃ ታደርጋለህ፡፡ በዚህ ላይ ትክክል ለመስራቴ ሪፈር ያደረግኳቸውን መጽሐፎች ሁሉ ጠቀስኩ፡፡ ከዚያ ጥያቄ ይነሳል፡፡ ለነዚህ ሁሉ መልስ መስጠት አለብህ፡፡ ብዙ ባለሙያዎች ስላሉ የተለያዩ ጥያቄዎች ይቀርቡልሃል፡፡ አሉ የሚባሉ ታላላቅ ሰዎች በቦታው ይገኛሉ፡፡ ለነዚህ ሁሉ መልስ ሰጥቶ አማካሪዬም በጣም ደስ ብሎት እኔም በዚሁ ትምህርቴን አጠናቅቄ ማዕረጉን ሰጡኝ፡፡

ሊብሮ፡ - ወዲያው እንደጨረሱ ወደ አዲስ አበባ መጡ ?

/ /መስቀል፡ - ተመርቀህ እኮ አትወጣም 6 ወር ያህል ትቆያለህ፡፡ ከዚያ በኋላ ነው የመውጣት ፈቃድ የምታገኘው፡፡

ሊብሮ፡ - ለምን ?

/ /መስቀል፡ - የአንተ ጥናት በመጨረሻ አቅርበህ ከጨረስክ በኋላ በየክፍለ ሃገሩ እና ተቋማቱ ይበተናል፡፡ ሰርቀህ ሰጥተህ እንደሆነ በየቦታው ይጣራል፡፡ የሌላ ፅሁፍ ሰርቀህ አቅርበህ ከሆነ ጠቅላላ ትሰረዛለህ፡፡ የሌላ ጥናታዊ ፅሁፍ ማቀረብ ከፈለግክ መጥቀስ አለብህ፡፡ እነዚህ ሁሉ እስኪጣሩ መቆት አለብህ፡፡ 6 ወር ስትቆይ ወጪህን በሙሉ እነሱ ናቸው የሚችሉት፡፡ በዚያ መሐል ያቀረብካቸውን ጥናቶች ለሚፈልጉ ተቋሞች ሰጥተህ ገንዘብ ይሰጡሀል፡፡ ከምታገኘው ግንዘብ ላይ ለአማካሪህ ትሰጣለህ፡፡ ምክንያቱም አብሮህ ስለሰራ ግዴታ ነው፡፡ ሐንጋሪ ውስጥ በአካዳሚ ሳይንስ 802 ቁጥር ብለህ ብትጠይቅ /መስቀል ኮስትሬ ነው ይሉሃል፡፡ የእኔ የመመረቂያ ኮድ ነው፡፡ ለሁሉም ተመራቂዎች የየራሳቸው ቁጥር አላቸው፡፡ /ቤቱ 17ተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በጣም ታዋቂ ሰዎችን ያስመረቀ በመሆኑ ታላቅ ስም አለው፡፡ እንግዲህ 6 ወር ከቆየህ በኋላ ነው እውቅና የሚሰጡህ ከዚያ ሁሉም ተመራቂ ይጠራል፡፡ አካዳሚ ሣይንስ አለ፣ በእርሻ አለ፣ በስፖርት አለ በሁሉም ዘርፍ ያሉት ተጠርተው ትልቅ ዝግጅት ተደርጎ ማዕረጉን ከነእውቅናው ይሰጡሃል፡፡ እንግዲህ እኔም እንደዚህ ነው የተመረቅኩት፡፡ ብዙዎች ታላላቅ ድርጅቶችም ሆኑ ዩኒቨርስቲዎች ከዚያ መጥተው ተመራቂዎችን በከፍተኛ ሂሳብ ይወስዳሉ፡፡ እንግዲህ ከዚያን ጊዜ ጀምረህ በየወሩ እስከህይወትህ ፍፃሜ ድረስ 800 የእነሱን ገንዘብ ይሰጡሃል፡፡

ሊብሮ፡ - አሁን እርሰዎ ይህንን ገንዘብ ያገኛሉ ?

/ /መስቀል፡ - ተመርቀህ እዚያው ሐንጋሪ ውስጥ ብትሰራ ነው ዩኒቨርስቲው የሚከፍልህ፡፡ እኔ ግን ወደዚህ መጣሁ፡፡ ከመምጣቴ በፊት እዚያው እያለሁ አንድ ጓደኛዬንና እኔ ለአሰልጣኝነት ኩዌት ውስጥ ፈለጉን፡፡ እሱ በእግር ኳስ እኔን ደግሞ በአትሌቲክስ ነው፡፡ ጓደኛዬ በጣም ስለጨቀጨቀኝ ተስማማሁ፡፡ ሂሣቡም ብዙ ነው፡፡ ትኬት መጣ፡፡ በዚያ መሐል ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣኖች ሐንጋሪ መጥተው እዚያ የነበርነውን ወደ አገራችን ገብተን እንድንሰራ ቅስቀሳ ያደርጉ ነበር፡፡ አንዳንዶቹ እዚያ የተማሩት ትተው ወደ አሜሪካ ሄዱ፡፡ እኔም የኩዌቱን እየጠበቅኩ ነበር፡፡ ጓደኛዬ ሄደ፡፡ በጣም የሚገርምህ አሁን እሱ በእግር ኳስ አሰልጣኝነት ቱጃር ሆኗል፡፡ ሂድና እኔ እመጣለሁ ብዬው ነበር፡፡ በመጨረሻም የመንግሰት ባለስልጣኖች አገራችሁን እርዱ ሲሉ እኔም አገሬን የመርዳት ቃለ መሐላ ስለፈፀምኩ ወደ አገሬ ለመምጣት ትኬት ላኩልኝ አልኩኝ፡፡ እንግዲህ ወደ አገሬ ስመለስ በሙያዬ ለመስራት ነው ቃል ተገብቶልኛል፡፡ ወደ አዲስ አበባ ስመጣ የቢሮ ሰራተኛ አደረጉኝ፡፡ በሙያዬ መስራት አልቻልኩም፡፡ ጥቂት ቆየና ዘመቻ መሄድ አለብህ ተባልኩ፡፡ ከየቦታው የተመረጡ ነበሩ፡፡ የውትድርና ትምህርት ተሰጠን፡፡ ማታና ቀን በየጋራና ጫካው የተኩስ ልምምድ ስንማር ቆየንና በመጨረሻ ጠመንጃ ተሰጥቶኝ ወደ ገጠር ገባሁ፡፡

ይቀጥላል
ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወርቅነች

ዋና ኮትኳች


Joined: 03 Oct 2010
Posts: 564

PostPosted: Sun Sep 25, 2011 3:15 pm    Post subject: Reply with quote

ቅቅቅቅቅ ...ፈዛዛው ፈላሾች አይነ ሰውር ቱክረተ ቢስ መሆንህን አውቀው እኮ ነው የሚያፌዙብህ Laughing

ጀሚላ ከቸርችል ጎዳና
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ከንቲባ .

ጀማሪ ኮትኳች


Joined: 08 Jan 2010
Posts: 50
Location: Roma

PostPosted: Sun Sep 25, 2011 4:05 pm    Post subject: Reply with quote

ምን አይነት ልክስክስ ሠይጣን ነው በናታቹ
አንተ ውሻ ይሄ ያንተ ቦታ አይደለም የአንበሶች ቤት ነው ስትባል አትሰማም እንዴ ?
ውሻ ድሮስ ከመጮህ ሌላ ምናባቱ ያውቃል አይ ውሾ ወርቅነች !
_________________
Ethiopia tikdem
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Mon Sep 26, 2011 2:09 am    Post subject: Reply with quote

የወንዶች ማራቶን ሬኮርድንም በኬንያውያን ተነጠቅን : እንግዲህ ምን ቀረን ?

አምናና ዘንድሮ በአትሌቲክስ ስፖርት የሚደርሥብን የሽንፈት ፅዋ እጅግ መራር ነው :: ዛሬ ኃይሌ ገብረሥላሤ ብቻውን ከሚሮጥ ለምን ሌላ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ የማራቶን ሯጭ አብሮ እንዲሠለፍ እንዳላደረገ ሊገባኝ አልቻለም Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes ወደደም ጠላ ዕድሜው እየገፋ ስለመጣ በወጣቶቹ መተካቱ አይቀርም :: እርሱ በፈጠረው አጋጣሚ ተጠቅመው ኬንያውያን ሬኮርዱን ላፉት Evil or Very Mad Evil or Very Mad Evil or Very Mad Evil or Very Mad

ምንጮች :-
1 ..... Pat Butcher (organisers) for the IAAF, Sunday, 25 September 2011. Makau stuns with 2:03:38 Marathon World record in Berlin! - UPDATED.

2 ..... Berlin Marathon 2011 - Patrick Makau Berlin Marathon World record 2011.


ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Mon Sep 26, 2011 4:19 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ወገኖቼ :-

በአትሌቲክሱ ዙሪያ ሠሞኑን ከተጧጧፈው ውዝግብ ጋር በተያያዘ የሚሠጡ አስተያዬቶችን በተቻለ መጠን እያፈላለግሁ አቀርባለሁ :: እስኪ ዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬ ከአውራ አምባ ታይምስ ጋዜጠኛ ጋር ያደረጉትን ቃለ -መጠይቅ ተከታተሉት ::

ምንጭ :-

‹‹መንግስት ችግሮችን የሚቀርፍ ውሳኔ ሊሰጥ ይገባል›› / ወልደመስቀል ኮስትሬ : አውራ አምባ ታይምስ : ቅዳሜ መስከረም 6 ቀን 2004 .. : ገፅ 22::


Quote:
ስድስት ኦሎምፒኮች እና አስር የዓለም ዋንጫ ውድድሮች ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ /ቡድንን በዋና አሰልጣኝነት መርተዋል፤ ውጤታማዎቹን የአገራችንን አትሌቶች ያሰለጠኑት / ወልደመስቀል ኮስትሬ። በደቡብ ኮሪያ - ዴጉ ስለተካሄደው 13ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና እና ከአትሌቲክስ ጋር ተያያዥ በሆኑ መሰል ጉዳዮች ዙሪያ አነጋግረናቸዋል።

መነጋገሪያ የሆነውን የኢትዮጵያን አትሌቶች የዴጉ አክራሞት እንዴት አዩት ?
በጣም ትልቅ በሽታ እና ሀፍረት ሆኖብኛል። ባርሴሎና ኦሎምፒክ አንስቶ ብዙ ኦሎምፒኮች እና የዓለም ሻምፒዮናዎችን አሳልፌያለሁ። [.. 1984 በተካሄደው ሙኒክ ኦሎምፒክም በአሰልጣኝነት ሄደዋል። ] ምንም እንኳን መሸነፍ እና ማሸነፍ የስፖርት ፀባይ ቢሆንም ወደ እነዚህ መድረኮች የምንሄደው ለተሳትፎ ሳይሆን ለአሸናፊነት ነው። ውጤታችን እየቀነሰ ከመጣ የቆየ ቢሆንም የዴጉው ግን በጣም አዘቅዝቋል። በስራ ላይ ያለው ጣልቃ ገብነት እንዲቆም ብዙ ጮኸናል። አሰልጣኝ፣ የቡድን መሪና ስራ አስኪያጅ ኮሚቴ ሁሉም መስራት ያለበት የኃላፊነቱን ያህል ነው። አብሮ የመስራት እንጂ ጣልቃ ገብቶ አንዱ አንዱን የማዘዝ ባህል በፊት አልነበረም። ይህ ሲኖር ግን መግባባቱ ጠፋ :: የአምባገነንነት ፀባይም ይታያል።

አምባገነንነት ፀባይ የሚያሳዩት እነማን ናቸው ?
የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራሮች ናቸው።

አትሌቲክሱን የሚመሩ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ውስጥ በዋናነት የሚያይዋቸው ችግሮች ምንድን ናቸው ?
ዋናው ችግር ወገናዊነት ነው። እዚያ ውስጥ የሚገቡ ሰዎች ለጥቅም ሳይሆን አትሌቲክሱን ለማገልገል መሆን አለበት። የሚመጡት በየክልላቸው ‹‹አትሌቲክሱን ይጠቅማሉ›› ተብለው ተወክለው ቢሆንም በየጊዜው ሊፈተሹ ይገባል። በሳምንት እና በወር በየስብሰባው ላይ ስለመገኘታቸው ቁጥጥር ሊደረግ ይገባል :: የስራ ደረጃቸው ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡበት እንጂ ማስፈራሪያ መሆን የለበትም :: ሙያተኛን ‹‹አግድሀለው፣ አባርሀለሁ›› የሚሉ ከሆነ አይሆንም። ቦታው ላይ ዘለዓለማዊ ሆነው መቀመጥ የለባቸውም :: አንድ እና ሁለት ጊዜ [ተመርጠው ] ሊቀመጡ ይችላሉ። ሦስት እና አራት ጊዜ ግን ከተቀመጡ ርስት ሆነ ማለት ነው፤ ይሰለቻልም። ብዙ ዓመት በመቆየታቸው ቦታውን መኮፈሻ ወይም ማስፈራሪያ ሊያደርጉት አይገባም። የቁጥጥር ስራ በዚህ በኩል ሊሰራ ይገባል። የአማተርነት ተግባራቸውን መርሳት የለባቸውም :: የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት / ብስራት ጋሻው ጠና እና አቶ ዱቤ ጅሎ ለዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባልነት ታጭተው ነበር ግን አልተመረጡም። ለምን ? ብሎ መጠየቅ ይገባል።

እርስዎ፣ ይህንን አስተያየት የሚሰጡት ‹‹በክብር ተሸኝተዋል›› በሚል ከፌደሬሽኑ እንዲርቁ ስለተደረገ እንደሆነ የሚገልፁ አሉ። ይስማማሉ ?
የሚገርምህ ለስፖርት ስንት አስተዋጽኦ አበርክተን አመራሮቹ ሰላምታ እንኳን ሊሰጡን አይወዱም። ወንጀል አልሰራን… በተቻለ መጠን ልምድ ያለውን ሰው ማራቅ ነው የፈልጉት። ስድስት ኦሎምፒክ ላይ ውጤት ያመጣ ሰው ለምን ይጠላል ? ከታች ጀምሮ እኛ ላይ ሊያሳድሙ ይፈልጋሉ። ምን አደረግናቸው ? አገራችንን ስላስጠራን ? ሰንደቅ ዓላማዋን በአደባባይ ስላሰቀልን ? አያበሉኝ፣ አያጠጡኝ የምኖረው በራሴ ነው ግን ፊት
ሊነሱኝ ይሞክራሉ።

አትሌቶችም ላይ ግን በራስ ፍላጎት የመመራት ሁኔታ ይታያል።
አትሌቶች ላይ ግለኝነት (Individualism) ይታያል። ድሮ የነበረው አብሮ ልምምድ መስራት እና በጋራ ነገሮችን መከወን አሁን አይታይም። ይህ ስሜት ከበርሊኑ የዓለም ሻምፒዩና ወዲህ በጣም እየቀረ ቢመጣም ‹‹ተዉ›› የሚል ጠፍቷል። ልጆቹ (አትሌቶቹ ) ውድድር ስለሚያዘጋጁላቸው በማናጀሮቻቸው ብቻ ማመን ጀመሩ። የልምምድ ፕሮግራማቸውም በእነሱ የተቀመረ ሆነ። እነዚህ ሰዎች (ማናጀሮች ) ይሄን ያህል ውጤት ማስመጣት የሚችሉ ከሆነ ለምን ለየአገሮቻቸው አልረዱም ?

ማናጀሮች አትሌቶቹን በመከፋፈሉ በኩል አስተዋጽአ እንዳላቸው ይነገራል።
አዎ ማናጀሮች ይከፋፍሏቸዋል። ለድርጅት፣ ለእኛ ነው የምትሮጠው በሚል በገንዘብ እየያዙ እና በጥሩ ሁኔታ እያስተናገዱ ግፊት ከጀመሩ በኋላ የእኛ ልጆች አለመግባባት ጀምረዋል። በፊት (ነፍሱን ይማረው ) አቶ ንጉሴ ሮባም፣ እኔም የአዎንታ መልስ ካልሰጠናቸው በስተቀር ማናጀሮች ወስደው አያወዳድሯቸውም ነበር። የህዝብ ተወካይ እንደ መሆናቸው መጠን ይሄ መታረም አለበት። ይከልከሉ፣ ይታገዱ ሳይሆን አካሄዳቸው ስነ -ስርዓት ሊበጅለት፣ ህግ ሊኖረው ይገባል። ሽንኩርት ነጋዴ ቀረጥ ትከፍላለች። እነሱ ግን ቀረጥ እንኳን እንዳይከፍሉ መንግስት እድል ሰጥቷቸዋል። በፊት የሚከፍሉት 10 በመቶ ተነስቶላቸዋል። ይሄ ሲደረግላቸው አገራቸውን የሚወክሉበት መንገድ ግን ሊኖር ይገባል። ኢትዮጵያን ወክለው የሚያደርጉት ውድደር ላይ እውቅና፣ 200 ሺህ ዶላር የመግቢያ ክፍያ የሚያስገኝላቸውን የግል የሩጫ ውድድር ጥሪ ያገኛሉ። አገርን መወከል ደግሞ ኃላፊነት ነው። እነዚህ ነገሮችን አስተካክለን ከሰራን አስር ወር የማይሞላውን ጊዜ መጠቀም ይቻላል፤ ለለንደን።

ማናጀሮችን አስመልክቶ መውሰድ ያለበት ቁርጥ ውሳኔ ምን ሊሆን ይገባል ይላሉ ?
ከእኛ ጋር አቻ የነበረችው ኬንያ ዛሬ የበታቿ ሆነናል። ኬኒያ ላይም ማናጀሮች እንዲህ ያደርጉ ነበር። ብዙ ግን አላስገቧቸውም። ህዝብና መንግስት ሊያስቡበት ይገባል። የክለቦቻችን አደረጃጀት ጥንካሬ እና ዓላማ ሊኖረው ይገባል። መመሪያ እና ደንብም ካልፀደቀ በስተቀር እኔ ወደፊትም እፈራለሁ። ለለንደን ኦሎምፒክ የቀረን አስር ወር የማይሞላ ጊዜ ነው። ምን ሰርተን እዚያ እንደምንደርስም አጠያያቂ ነው። መንግስት ተከታትሎ ችግሮችን የሚቀርፍ ውሳኔ ሊሰጥ ይገባል። አለበለዚያ ያገኘናትን አንድ ወርቅ እና አራት ነሐስም ላናገኝ እንችላለን። የተከበርንበት፣ የተሸለምንበት እስከ መንግስት ድረስ የተመሰገንንበት ስፖርት ስለሆነ እንደ ባለሙያ ትኩረት ሰጥተን ስማችንን ማቆየት እንዳለብን ይሰማኛል።

ፌዴሬሽኑ ውጤት ከጠፋ እንዳይተች ከለላ እንዲሆኑት ሲል አትሌቶች እንደፈለጉት ለቋቸዋል፣ በተለይ ታላላቅ አትሌቶች ፌዴሬሽኑን ይቆጣጠሩታል እንጂ ፌዴሬሽኑ አትሌቶችን አይቆጣጠርም ይባላል። ምን ይላሉ ?
አትሌቶቹ ጨዋ ነበሩ። አሁን ግን ግለኝነት እየበዛ ሄደ። በደረጃቸው ይከባበሩም ነበር። ኃይሌ ፊጣ ባይሳን አልቀድምም እያለ አደፋፍረን እንዲቀድም ያደረግነው እኛ ነን። የዚህን ያህል ትሁቶች ነበሩ። አብሮ መብላት እና መስራት የተለመደ ነበር። አቶ ንጉሴ ሮባ ድሮ ሲነግረን አትሌቶች መነካካት እስከመፍራት ድረስ ግለኝነት ነበረባቸው። ከዚያ ግን አስትተው ግንኙነታቸው እንዲጠናከርና እንዲቀራረቡ አድረገው ነበር። [መነካካት ይፈሩ የነበሩት በባዕድ አምልኮ የተነሳ ውጤቴ እንዲበላሽ ያደርገኛል /ታደርገኛለች ከሚል ፍራቻ ነበር። ] አሁንም የልጆቹ እርስ በርስ ያለመተሳሰብ /ያለመረዳዳት እንዳለ በግልፅ ይታያል። [አገርን ወክለው ወደ ውድድር ከመግባታቸው በፊት ባሉ ደቂቃዎች እንኳን አብረው ልምምድ እንደማይሰሩ ይነገራል። ] አትሌቶች ሁሉም ሰው ላይ መልካም ፀባይ አያሳዩም ማለት አይደለም። የማያምኑበት ሰውን ‹‹እንዴት ያሰለጥነናል ?›› ይላሉ። ፕሮግራም አወጣጥ ላይም ቅሬታቸውን ይሰነዝራሉ።

ያው እንደሚታወቀው ለለንደን ኦሎምፒክ የቀረን አስር የማይሞላ ወር ነው። ይህ ደግሞ አጭር ጊዜ ነውና እንደ የቅርብ ጊዜ መፍትሄ ምን ቢደረግ መልካም ነው ይላሉ ?
አሁን ያለው የፌዴሬሽኑ አመራር ጥሩ አይደሉም። ልምድ ያላቸውን፣ ለአገራቸው ብዙ የሰሩ ሰዎችን ቢጠቀሙ ለእነሱም፣ ለአገሪቱም ለህዝቡም ጠቃሚ ይሆናል። መኮራረፍ፣ ማግለል፣ ፊት መንሳት ምንም ጥቅም የለውም። የአባት ገዳይ ይመስል ሲያዩን ለምን ፊታቸውን እንደሚያዞሩ አላውቅም። ድል የለመደውን እና ውጤት ሲጠፋ ቶሎ የሚከፋውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ላለማስከፋት ባለችው ጊዜ ከተሰራ ውጤት ይመጣል። ጠቃሚ ከሆነ የእድሜ ገደብ ምን ያስፈልጋል ? እኔ እቅድ መንደፍ እንጂ አልሮጥ፣ አልዘል…።

ካነሱት አይቀር ‹‹ዶ / ወልደመስቀል አርጅተዋል፤ ይበቃቸዋል›› የሚሉ አሉ።
አዎ አንዳንዱ ‹‹አርጅተሀል›› ይለኛል። አባባሉ ሞራልን የሚጎዳ ነው። እድሜ የሰጠው ሁሉ ያረጃል። [በሀበሻ እድሜ አቆጣጠር 65 ዓመቴ ነው ብለውኛል። ] እንዳልኩት እኔ እቅድ ነድፎ ማሰልጠን፣ መመዘን እንጂ አልሮጥም። አትሌቲክስ የአደግኩበት፣ የተሸለምኩበት ስፖርት ነው። ከቤጂንግ ተመልሰን መንግስት የመኪና ሽልማት ከሰጠኝ በኋላ በሙሉ አኮረፉኝ። ይኼ ማንም ከስራ የሚያገኘው በመሆኑ መኩራት እና ደስ ብሏቸው ለሌላ ሽልማት እንደመነሳት ለምን ቅር እንዳሰኛቸው ገርሞኛል።

ለተተኪዎች እውቀት እና ልምድዎን ለማስተላለፍ ፈቃደኛ አይደሉም። የተጠረዙ መረጃዎችን ለማንም አይሰጡም ተብለው ይታማሉ። ትክክል ነው ?
ለአገራችን ለመጥቀም በክፍል ውስጥ እናስተምራለን፤ አንደብቅም። ነገር ግን ለማንም ሰው ፋይሌን ከፍቼ አላሳይም። አንድ ውድድር እስከሚጠናቀቅ ድረስ የሚካሄድ ዝግጅት ምስጢር ነው። ለአንዱ ውድድር የተጠቀምንበትን ታክቲክ እና ስትራቴጂ በቀጣይ ስለሚለውጥ ከተጠናቀቀ በኋላ ግን ለማንም ግልፅ ነው። ‹‹ድብቅ ነው›› ይሉኛል። አሁንም ቢሆንም ለሚጠቅም ሰው እጠቅማለሁ። ለማይጠቅም ሰው ግን የሙያ ጥያቄ በመሆኑ አልጠቅምም። አሰለጣጠን ስርዓታዊ አካሄድ አለው። ያንን ለሚቀበለኝ ሰው አስተምራለሁ። ምስጢራችንን ከፍተን ለማንም አንሰጥም፤ ጥንቁቅ ነን። ይህ ወታደራዊ አካሄድ ነው። ክፉ ነው ይሉኛል። እያንጓጠጠኝ ላስተምረው ነው ? ደረቱን ነፍቶ ‹‹አዋቂ ነኝ›› ካለ በእውቀቱ ይስራ ‹‹ጋሼ አስተምረኝ›› ካለኝ ቁጭ አድርጌ አስተምረዋለሁ። ‹‹ድብቅ ነው›› ለሚሉኝ መልሴ በድብቅነቴ ተጠቅሜበታለሁ፤ አገሬን ጠቅሜበታለሁ ነው። ‹‹ደብተርህን፣ መፅሐፍህን አምጣ›› ለሚሉኝ ግን አይሆንም። ሜዳ ላይ ፈረንጅ መጥቶ ልምምድ እንዲያይ አልፈቅድለትም። በተማርንበት አገር (ሀንጋሪ ) /ቡድን ሲሰለጥን ተማሪያቸው ሆነን ገብተን እንድናይ አይፈቀድልንም። ይህ የስራው ፀባይ እንጂ ስስታምነት አይደለም።

ከፌዴሬሽኑ /ቡድኑን እንዲያገለግሉ አገራዊ ጥሪ ከቀረበልዎ ለመስራት ዝግጁ ነዎት ?
ምንም ችግር የለም :: ህዝብና መንግስት ስላስተማሩኝ አቅሜ እስከፈቀደ ድረስ እስከ ህይወቴ ፍፃሜ ድረስ የመስራት ግዴታ አለብኝ።

በመጨረሻ…
የኢትዮጵያ ህዝብ አኩራፊ ሳይሆን ታጋሽ ይሁን። የተቆጩበትን ውጤት እንዲክሷቸው እና የውጤት ድርቁ ወደፊት እንዳይደገም የፌዴሬሽኑ አመራሮች ላይ ቅሬታ ከመፍጠር ይልቅ ካሳ መጠየቅ አለበት።
ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Mon Sep 26, 2011 5:05 am    Post subject: Reply with quote

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአትሌቲክስ ቡድን ዋና አሠልጣኝ የሆኑት አቶ ካሡ ዓለማየሁ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ስፖርት አመራር ላይ የሚያይዋቸውን ግድፈቶች ፊት ለፊት በግልፅ በመተቸት ይታወቃሉ :: ሠሞኑን በዳ -- የዓለም አትሌቲክስ ፉክክር ስለደረሠብን ሽንፈት እና አጠቃላይ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ስፖርት አመራር ረገድ ስላለው ሥር የሠደደ ችግር ያላቸውን አስተያዬት ቅዳሜ መስከረም 6 ቀን 2004 .. በወጣው የአውራ አምባ ታይምስ ጋዜጣ ላይ በሠጡት ቃለ -መጠይቅ ተብራርቷል :- ተከታተሉት ::

ምንጭ :- አውራ አምባ ታይምስ : ቅዳሜ መስከረም 6 ቀን 2004 .. :: ‹‹አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ውስጥ ያሉ አምባገነን ግለሰቦች ወርደው በአዲስ አመራር መተካት አለባቸው››

ካሉ ዓለማየሁ /የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አትሌቲክስ ቡድን ዋና አሰልጣኝ / :: ገፆች 22 እና 23 ::


Quote:
13ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር የግል አስተያየትዎ ልነሳ ?
በአሁን ስፖርት ከፍተኛውን ቦታ የያዘው ውሸት ነው። እኔ ደግሞ የምፈልራው ውሸትን እንደሆነ እንዲታወቅልኝ እፈልጋለሁ። ስለ ዓለም ሻምፒዮና ከማውራታችን በፊት አንዳንድ ነጥቦችን ላንሳ… ከቤጂንግ ኦሎምፒክ መልስ በአመት ውስጥ ስለተደረጉ አጠቃላይ ውድድሮች ግምገማ እንዲደረግ ብንጠይቅም ፌዴሬሽኑ ‹‹ከአሁን ሰዓት ጀምሮ አትሌቶች የተበተኑ ስለሆነ ግምገማ መደረግ የለበትም›› አለ :: ‹‹ለምን /ቡድን ይበተናል ?›› ብንልም መልስ መስጠት አልቻሉም። ነገር ሁሉ የተበላሽው ያኔ ነው። አሁን ለተከሰተው የውጤት መጥፋት መንስዔው እሱ ነው። [ወቅቱ 2001 . ነው። ] ፋና እና ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ባካሄዷቸው ውይይቶች ላይ መልምለን፣ ኮትኩተን ለትልቅ ደረጃ ያደረስን ክለቦች እና አሰልጣኞች ሳናውቅ ፌዴሬሽኑ አትሌቶችን /ቡድኑን መበተን የለበትም በማለት ተቃውሞዬን ገልጫለሁ። አደገኛ ንግግር ተናገርክ ተብዬም /ቡድን ምርጫ ላይ እንዳልካተት ተደርጓል። ‹‹አትሌቶች በመረጡት አሰልጣኝ መስራት ይችላሉ›› መባሉ ዛሬ አደገኛ ሁኔታን ፈጥሯል። ፌዴሬሽኑ ባለሙያዎችን፣ ክለቦችን አቅፎ መስራት አለበት። ተንጠልጥሎ ያለው በክልል ፌዴሬሽኖች ላይ ብቻ ነው። ውጤት እያመጡ የብ /ቡድን ተሰላፊ አትሌቶችን የሚፈጥሩ ክለቦች ናቸው ግን የጠቅላላ ጉባኤ አባል እንዲሆኑ እንኳን አላደረጓቸውም። ክለቦች ባፈሯቸው አትሌቶች ተጠቃሚ አልሆኑም። ይህን ጉዳይ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ እና ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማኅበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አመልክተናል። አመራሮቹ ኢትዮጵያ ጠንካራ ክለብ እና አትሌት እንዲኖራት የሚፈልጉ አይደሉም የሚል አቋም አለን። ኢንተርናሽናል አማተር አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከሚያዘው በተቃራኒ የብሔራዊ ቡድን ምርጫ እከክልኝ፣ ልከክልህ በሚል ነው የተካሄደው። ሁሉ ነገር የሚደረገው በግለሰብ ነው።

ግለሰብ ሲባል ማነው ?
የፌዴሬሽኑ አመራሮች። የሚፈልጉትን ሰው ለማቅረብ የሚፈልጉትን መመሪያ ያወጣሉ። ስራ አስፈፃሚው ሳይወስን ግለሰብዎች ላይ የቅጣት ውሳኔ ያስተላልፋሉ። ስራ አስፈፃሚ የሚያወጣቸው መመሪያዎች እና ደንቦች ሁሉ ያገናዘበ አለመኖሩ ችግር ነው።

ስራ አስፈፃሚው ሲሉ ሁሉንም አባላት ነው ? ምክንያቱም በዋናነት የሚወስኑት አራት የማይሞሉ ሰዎች ናቸው የሚሉ አስተያቶች ይዳመጣልና ነው።
1986.. የኢትዮጵያ አትሌቲክስ እንደዚህ አይነት ችግር ውስጥ ገብቶ መንግስት ገምጋሚ ቡድን በመላክ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በመገምገም አትሌቲክስ ላይ ችግር የሚፈጥሩ ዘጠኝ አሰልጣኞች ከቦታው እንዲነሱ ተደርገዋል። እነዚያ የተባረሩ ሰዎች በአሁኑ ሰዓት በድጋሚ ተመልሰው የድሮ ስራቸውን እየሰሩ ነው። አጭር እና መካከለኛ ርቀትን ማሰልጠን የማይወድ፣ ለውድድር ሰሞን መጥቶ ከውድድር በኋላ የሚጠፋ፣ አራት ዓመት ጠብቆ የሚመጣ አሰልጣኝ ነው ዛሬ ዋና አሰልጣኝ ሆኖ እየሰራ ያለው። ለዚህ ሁሉ ተቃውሞ አቅርበናል።

ግልፅ ለማድረግ ያህል እየነገሩኝ ያሉት የኢትዮጵያ /ቡድን ዋና አሰልጣኝ ስለሆኑት / ይልማ በርታ ነው።
በተለያዩ መድረኮች [ፓርላማን ጨምሮ ] እና መገናኛ ብዙሐን ላይ እርስዎ እድል ካገኙ / ይልማ ላይ ተቃውሞዎትን ከመግለፅ ወደኋላ አይሉም። ምክንያትዎ ምንድን ነው ? ከመጡበት 1974 .. ጀምሮ ማንን ኮትኩተው፣ መርጠው ለውድድር አዘጋጅተው ያውቃሉ ? ‹‹ይሄን ልጅ አድርሰዋል›› ከተባለ ልቀጣ እችላለሁ። ኃይሌ /ሥላሴን በኢትዮጵያ አየር መንገድ አትሌቲክስ ፓይለት ፕሮጀክት እንዲታቀፍ ያደረጉት እሳቸው እንደሆኑ ይነገራል፤ ከአቶ ንጉሴ ሮባ ጋር በመሆን። ፖይለት ፕሮጀክት ሲመሰረት እሱ እዚያ የለም። ለመደጋገፍ ተብሎ የሚወራ ወሬ ነው። የነበሩት እነ ንጉሴ ሮባ፣ በየነ አያኖ፣ ትዕዛዙ ናቸው። / ይልማ የፌዴሬሽኑ እና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሠራተኛ ስለሆነ አንድ ነገር በሚመጣ ጊዜ ‹‹በሉልኝ›› ተብሎ የሚወራ ወሬ እዚያ ቤት (አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ) በአደገኛ ሁኔታ አለ። ዋናው ነገር የት ክለብ አሰልጥኗል ? የማራቶን 800 እና 1500 ሜትር /ቡድን አትሌቶች በእሱ የተነሳ ነው የተበተኑት።

በእሳቸው የተነሳ ተበተኑ ምን ማለት ነው ?
ውጤት ሲያጡ ነዋ። ያንን ሲያጡ አሁን ወደ አምስት እና አስር ሺህ መጥተዋል። እሱም ሆነ ሌሎች አሰልጣኞች ውጤት ለምን ጠፋ ? ተብለው አልተገመገሙም። ከማራቶን ተነስተው ቤጂንግ ኦሎምፒክ ላይ 800 እና 1500 ሜትር አሰልጣኝ ነበሩ። በርቀቱ ግን ውጤት አልነበረም። ለምን ውጤት ጠፋ ? ብሎ ግን አልተገመገመም። በአምስት እና አስር ሺህ ውጤት መጥቷል። እንዴት ውጤት መጣ ? ብሎ የገመገመ ግን የለም። አንድን አሰልጣኝ የምትለካው በክለብ ስራ ላይ መልምሎ ለዓለም አቀፍ ውድድሮች ሲያደርስ ነው። እኔ እሳቸውን የምቃወመው በዚህ ሂደት ነው፤ ምንም ሚና ስለሌላቸው ነው። ማንንም ባለሙያ ብትጠይቅ የሚነግርህ ይህንኑ ነው።

በፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትም ላይ ቅሬታዎን በተደጋጋሚ ያሰማሉ።
1992 .. ለሲድኒ ኦሎምፒክ ጊዜ የአመራር ስብጥሩ እንዴት ነበር ? የኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አቶ አሰፋ ማሞ፣ የኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር የነበሩት አቶ መላኩ ጴጥሮስ የክለብ ባለሙያዎች እና የሚመለከታቸው አካላት እየተጠሩ በየሦስት ወር ውይይት ይካሂዱ ነበር። ሰንዳፋ ሜዳ ላይ ሳይቀር ስብሰባ ነበረን። በውይይቱ በአትሌቶች፣ አሰልጣኞችና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ጠንካራ እና ደካማ ነጥቦች ላይ እንወያይ ነበር። ውጤት የመጣውም ለዚሁ ነው።

1996 .. በአትሌቶች እና በአሰልጣኞች መሀከል ጭቅጭቅ ነበር። ሁሉም ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት ጠንካራ ውይይት ተካሂዶ የሀሳብ ፍጭት ስለነበር ውጤታችንን አስተካክሎታል።

በወቅቱ የፌዴሬሽን አመራሮች በክልል ውክልና ሳይሆን እውቀትና ክህሎታቸው ያላቸው ይጠቅማሉ የተባሉ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ይሆኑ ነበር። አሁን ነገሮች ጥሩ አካሄድ ስለሌላቸው አትሌቶች፣ አሰልጣኞች እና ሌሎች ባለሙያዎች ተበታትነው ፌዴሬሽኑ የግለሰብዎች መጫወቻ ሆኗል። ስፖርት ኮሚሽን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት አስተያየት ስሰጥ እንደሰማኸው ‹‹ግለሰብዎች እንጂ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የሚባል ነገር የለም›› ብያለሁ። አሁንም ቢሆን በቅድሚያ ሊፈተሽ የሚገባው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ነው።

ፌዴሬሽኑ ቴክኒክ ኮሚቴ የለውም። [የፌዴሬሽኑ አቃቤ ነዋይ አቶ አማኑኤል አብረሀ ከትላንት በስቲያ በሬዲዮ ፋና በተደረገ ውይይት ላይ የስራ ክፍፍል ተደርጎ ቴክኒክ ኮሚቴ መፍረሱን ገልፀዋል ] ሲፈልጉ ይመርጡና ሲፈልጉ ያፈርሱታል። ንዑሳን ኮሚቴዎች የሚባሉ መኖራቸውን የምናየው ውድድር ሲመጣ መፅሄት ላይ ፎቷቸውን ነው። ከዚያ ያለፈ ሚና የላቸውም፤ አናውቃቸውምም።

ክለቦች፣ የአሰልጣኞች ማህበርና የአትሌት ተወካዮች የጠቅላላ ጉባዔ ተወካዮች አይደሉም። ፌዴሬሽኑ የሚያወጣው ደንብ እና መመሪያ ችግር አለበት። አመራሩ ውስጥ ያሉት የስፖርቱ እውቀት ስለሌላቸው ትንሽ የሚያውቅ ሰው ሲናገራቸው ይደነባበራሉ። ብቻ ብዙ ችግሮች አሉ።

የቀሩ ችግሮች አሉ ነው የሚሉኝ ?
በአጭር ርቀት ሚኒማ አምጥተው፣ ለዘጠኝ ወር ሆቴል ሆነው ልምምድ ሲሰሩ ከቆዩ በኋላ መጨረሻ ላይ አሰልጣኞችንም፣ አትሌቶችንም አስቀርተው መሄድ ምን ማለት ነው ? ይሄ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መኖሩን ያሳያል ? ድሮ በአጭር ርቀት ችግራችን ሚኒማ ማምጣት ነበር። ሚኒማ ያመጡ ልጆች የግዴታ ሄደው መወዳደር አለባቸው። የአገሪቱ 100 እና 200 ሜትር አሸናፊ የሆነው ወጠረ ገለልቻ ሚኒማ አሟልቶ አልሄደም። የእውነት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ቢኖር ለልጁ መታገል ነበረበት።

ሰኔ 13/2003 .. የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ሪፖርት በፓርላማ ባቀረበበት ወቅት አቶ አማኑኤል አብረሃም በፌዴሬሽኑ ላይ ቅሬታ የሚያሰሙት ስፖርቱን ሲገድሉት የነበሩ፣ ትምህርት ማዕከል ባደረገ የዘመናዊ ስርዓት ውስጥ መታቀፍ ያልቻሉ መሆናቸውን ገልፀዋል። ይስማማሉ ?
እንደዚህ አይነት ሰዎች ናቸው ከፌዴሬሽኑ መጥፋት ያለባቸው። አባባላቸው ስህተት ነው። እኔ ጀርመን አገር ተምሬያለሁ። በአትሌቲክስ ዲፕሎማ ካላቸው አምስት ሰዎች አንዱ ነኝ። በኦሎምፒክ፣ በዓለም ዋንጫ እና በሌሎች ውድድሮች ለአገሬ፣ ለህዝቤና ለክለቤ ውጤት አስገኝቻለሁ። ወረቀቱ ሳይሆን ‹‹ምን ሠራ ?›› የሚለው መታየት አለበት። ትምህርት ባይኖረኝ ኖሮ አራት ኦሎምፒኮች እና ዓለም ዋንጫዎች ላይ ሄድ ነበር ? ለምሳሌ አበበ ቢቂላን ያሰለጥን የነበረው ባሻ ፍቅሩ ደገፉ የሁለተኛ ክፍል ተማሪ ነበር። ወርቅ ያስመጡት በዚያ ትምህርታቸው ነው ? ሰርተፍኬት ሳይኖረው አሰልጣኝ የሆነ የለም።

ይህ ከሆነ ታዲያ እናንተ በአሰራር ስርዓቱ ውስጥ ለምን መታቀፍ አልቻላችሁም ?
ያልታቀፍነው የዓመቱ ውድድር ካላንደር እና ሌሎች ችግሮች አሉ ስንል የእኛን ውስጠ ምስጢር የሚያውቁት የቆዩ አሰልጣኞች ስለሆኑ እናርቃቸው በሚል ነው። ‹‹ትምህርት› ሽፋን ነች። / ወልደ መስቀልን ያራቁት ትምህርት ስለሌላቸው ነው ? እኔ ዲፕሎማ እያለኝ ሰርተፍኬት ያላቸው አሰልጣኞች እያሰለጠኑ ነው።

ሌላ ማስረጃ ልስጥህ። ዘንድሮ ዓለም ዋንጫ ማራቶን /ቡድንን ይዘው ይሄዱት አሰልጣኞች ሳይሆኑ ማናጀሮች ናቸው። [(ሐጂ አደሎ የቡድኑ አሰልጣኝ ነው ] የትምህርት ማስረጃ አላቸው ? የላቸውም። የእኛ ክለብ ኮትኩቶ ያሳደጋቸውን ዘጠኝ ልጆች ዓለም ዋንጫም ሆነ መላው አፍሪካ ይዘዋቸው የሄዱት ምንም ያልሰሩባቸው ሰዎች ናቸው። ‹‹ትምህርት›› አሁን የመጣች የማራቂያ ዘዴ ነች። ፌዴሬሽኑን የሚመሩት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትስ የአትሌቲክስ ትምህርት የተማሩ ናቸው ? አይደሉም።

ለጠቀሷቸው ችግሮች እንደ መፍትሄ ሀሳብ የሚያቀርቡት አለ ?
የግምገማዎች አለመኖር ያጠፋ እና ያላጠፋ ተለይቶ እንዳይታወቅ ስላደረገ እዚህ ላይ ከመንግስት ጀምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ትኩረት ሊሰጡት ይገባል። አትሌቶቻችንን በዴጉ ሻምፒዮና ስንመለከት ተከታትሎ የመሮጥ ፅናት (Pace Endurance) የላቸውም። ፍጥነታዊ የመሮጥ ፅናት (Speed Endurance) ስላልነበራቸው ተቆርጠው ይቀሩ ነበር። በውድድሮች ላይ ምንም የህብረት ስራ አልሰሩም። የልምምድ ችግር እንዳለባቸው ያስታውቃሉ። አትሌቶቹ ጠይቀው ምላሽ እየተሰጣቸው እንደልሆነ ይሰማል። የብ /ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አትሌቶቹን በጋራ ሰብስቦ አንድ ቀንም የጋራ ውይይት ሲያደርጉ አልተመለከትኩም። በአትሌቶቹ ዙሪያም ሆነ በሌሎች ሙያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ክለቦች እና ክልሎች አስተያየት እንዲሰጡ ያልተጋበዙም። እነዚህ ነገሮች በቶሎ መቀረፍ አለባቸው። ፌዴሬሽኑ መቅደም ያለበትን aላወቀም። ስለ ውድድሩ አስቀድሞ ያነጋገረው ማናጀሮችን ነው። ይሄ የኢትዮጵያን ህዝብ መናቅ ነው።

ድሮ ቡድኑን የሚመራ አምበል ነበር። በአትሌቶቹ መሀከል ፍቅር እና አንድነት የለም። የልምምድ ፕሮግራሞች በምንም አይነት እቅድ እንደወጡ እና አጠቃላይ ግምገማ መደረግ አለበት።

ታዋቂ አትሌቶች ታዛዥ አይደሉም፣ አትሌቶቹ ፌዴሬሽኑን ይመሩታል እንጂ ፌዴሬሽኑ አትሌቶችን አይመራም ይባላል። ምን ይላሉ ?
ልጆቹ /ቡድኑ ተበትኖ ከተለቀቁ በኋላ እንጂ በፊት ማንንም አይመሩም ነበር። ማን ባለሙያ እንደሆነ ያውቃሉ። እንደማይታዘዙ አውቃለሁ። የሚያምኑባቸው ሰዎች ካሰለጠኗቸው ግን በተገቢው ሁኔታ ይሰራሉ። የብ /ቡድን መበተን ስነ -ምግባር እንዳይኖራቸው፣ በዘፈቀደ እንዲጓዙ አድርጓል። ለክብር ሁሉ መሮጥ አቁመዋል። የአገር ውስጥ ውድድር አያደርጉም። ኃላፊነት እና ግዴታቸውን አውቀው የሚሰሩበት የተፃፈ እቅድ የለም። ጉዟቸው በዘፈቀደ ነው።

በለንደን ኦሎምፒክ የቀረው አጭር ጊዜ ነው። ምን መሰራት አለበት ይላሉ ?
አሁን ሰበብ አያስፈልግም። የሌለውን ወጣትና አዳጊ አትሌቶች ፈርተዋል ብሎ ማውራት አይገባም። አዳጊ የሚባው እድሜው 17 ዓመት ነው። ወጣት የሚባው 20 በታች ነው። ታዳጊ ወይም ወጣቱ አትሌት የቱ ነው ? ያሉት ልጆች ራሳቸው (የቀድሞዎቹ ) ናቸው። ስለለቀቅናቸው በሽተኛ ሆኑ። ታላላቅ አሰልጣኞችን አማክሮ እና አወያይቶ ልጆችን በስነ -ስርዓት ተይዘው እንዲሰሩ ከተደረገ ለለንደን ኦሎምፒክ ውጤት ይመጣል።

ዳግመኛ ጥሪ ቀርቦሎት ፌዴሬሽኑ ወደ /ቡድን አሰልጣኝነት ቢጠራዎት ለመቀበል ዝግጁ ነዎት ?
እኔን እኮ ያባረረኝ ፌዴሬሽኑ አይደለም። ፌዴሬሽኑ ውስጥ ያሉ አምባገነን ግለሰብዎች ናቸው ሳንገመገም እንድንወጣ ያደረጉት። እኛም ፌዴሬሽኑም የአገር ነን፣ ለአገር መስራት ግዴታችን ነው። ፌዴሬሽኑ ውስጥ ያሉ አምባገነን ግለሰብዎች ወርደው በአዲስ አመራር መተካት አለባቸው። ዋናው ቁም ነገር እሱ ነው።

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Mon Oct 03, 2011 11:57 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ወገኖቼ :-

በየዓመቱ በሁለቱም ፆታዎች ለዓመቱ የዓለም ምርጥ አትሌቶች እጩ ተወዳዳሪዎች ሲጠቆሙ ባለፉት ጊዜያት እንደምናየው የኢትዮጵያ አትሌቶች ተሣታፊ ብቻ ሣይሆን አሸናፊ የሆኑባቸው አጋጣሚዎች ነበሩ :: ዘንድሮ ግን ከሴትም : ከወንድም አትሌቶቻችን አንድም ለዚህ ውድድር የተጠቆመ የለም : ያሣዝናል Crying or Very sad Crying or Very sad Crying or Very sad

ምንጭ :- IAAF, Monday, 3 October 2011. IAAF Selects Candidates for 2011 World Athlete of the Year Award.

Quote:
ሥም ዝርዝሩ የቀረበው በተወዳዳሪዎች የወል ሥም (Sirname) መጀመሪያ ፊደል በእንግሊዘኛ ሆሄያት ቅደም -ተከተል ነው ::

የወንዶች ምድብ (Men)

1 ..... ዮሐን ብሌክ (Yohan Blake) : ጃማይካ (Jamaica)
2 ..... ኡሲያን ቦልት (Usain Bolt) : ጃማይካ (Jamaica)
3 ..... ፋራህ (Mo Farah) : ታላቋ ብሪታንያ (Great Britain)
4 ..... ሮበርት ሐርቲንግ (Robert Harting) : ጀርመን (Germany)
5 ..... ኪራኒ ጄምስ (Kirani James) : ግሬናዳ (Grenada)
6 ..... ፓትሪክ ማካው (Patrick Makau) : ኬንያ (Kenya)
7 ..... ኮጂ ሙሮፉሺ (Koji Murofushi) : ጃፓን (Japan)
8 ..... ዴቪድ ሩዲሻ (David Rudisha) : ኬንያ (Kenya)
9 ..... ክርስቲያን ታይለር (Christian Taylor) : አሜሪካ (USA)
10 ..... ጄሲ ዊሊያምስ (Jesse Williams) : አሜሪካ (USA)

የሴቶች ምድብ (Women)
1 ..... ማሪያ አባኩሞቫ (Maria Abakumova) : ሩሲያ (Russia)
2 ..... ቫሌሪ አዳምስ (Valerie Adams : ኒው -ዚላንድ (New Zealand)
3 ..... ቬሮኒካ ካምፕቤል ብራውን (Veronica Campbell Brown) : : ጃማይካ (Jamaica)
4 ..... ታታያና ቼርኖቫ (Tatyana Chernova) : ሩሲያ (Russia)
5 ..... ቪቪያን ቼሩዮት (Vivian Cheruiyot) : ኬንያ (Kenya)
6 ..... አና ቺቼሮቫ (Anna Chicherova) : ሩሲያ (Russia)
7 ..... ላሺንዳ ዴሙስ (Lashinda Demus) : አሜሪካ (USA)
8 ..... ካርሜሊታ ጄተር (Carmelita Jeter) : አሜሪካ (USA)
9 ..... አማንትል ሞንትሾ (Amantle Montsho) : ቦትስዋና (Botswana)
10 ..... ሣሊ ፒርሠን (Sally Pearson) : አውስትራሊያ (Australia)

እነማን በአሸናፊነት ይመረጡ ይሆን ?

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sun Oct 09, 2011 10:35 pm    Post subject: Reply with quote

አሊ አብዶሽ የዓመቱን የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር አሸነፈ ::

ለረዥም ሣምንታት ከድል ርቆ የቆየው አሊ አብዶሽ ዛሬ እሑድ መስከረም 28 ቀን 2004 .. የቦስተንን ግማሽ ማራቶን በማሸነፍ የድል ሃራራውን ተወጥቷል ::

ምንጭ :- Associated Press, Updated: October 9, 2011, 4:05 PM ET. Ali Abdosh wins Boston Half Marathon.

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Mon Oct 10, 2011 9:18 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ወገኖቼ :-

የዛሬው ዜና ስለ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አይደለም : ትላንት እሑድ መስከረም 28 ቀን 2004 .. በቺካጎ (አሜሪካ ) በተደረገው የማራቶን ውድድር ስለተከሠተ የአንድ አስደናቂ ሴት ሯጭ አስገራሚ ታሪክ ላቀርብላችሁ ፈልጌ ነው :: አምበር ሚለር ትባላለች : የማራቶኑን ውድድር ለመካፈል ስትወስን ነፍሰ ጡር መሆኗን አውቃለች : ለዚያውም ድርስ እርጉዝ :: ሐኪሟን አማክራ ግማሹን ርቀት እንድትሮጥ : ግማሹን ርቀት ደግሞ በእግር ጉዞ እንድታጠናቅቅ መከራት :: ውድድሩን ተካፈለች : 6 ሰዓት 25 ደቂቃ 50 ሴኮንዶች አጠናቀቀች :: በዚህ ሰዓት በመግባቷ የቀድሞ ሰዓቷን ባታሻሽልም ቢያንስ ቀርፋፋ ባለቤቷን ቀድማዋለች Laughing Laughing Laughing ጎበዝ :: ታምር የተፈጠረው ከዚያ በኋላ ነው :- ውድድሩን እንዳጠናቀቀች ለረሃቧ ማስታገሻ አንድ ሣንድዊቿን ገዝታ በቀጥታ ወደ ሆስፒታል አቀናች : 'ጁን ' ብላ የጠራቻትን ሁለተኛ ሴት ልጇን በሠላም ተገላገለች :: የዚች ሴት ጥንካሬ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የሚኖሩትን ጠንካራ ሴት ወገኖቻችንን አስታወሰችኝ :: ሙሉ ንባቡን ከአሶሼትድ ፕሬስ ታገኙታላችሁ ::

ምንጭ :- By Ronnie Reese and WGN-TV, 1:30 p.m. CDT, October 10, 2011. Photo finish: Woman gives birth after running (and walking) marathon.

Quote:
Amber Miller was nearly 39 weeks pregnant -- expecting her second child any day -- when she set off from the starting line of the Chicago Marathon Sunday.

She ran and walked even as contractions started kicking in toward the end of the race. But she managed to cross the finish line -- and grab a bite to eat -- before giving birth to baby girl June Sunday night.

"I got the OK from my doctor to run half, and my husband ran with me and supported me along the way," Miller told WGN-Channel 9 from her bed at Central DuPage Hospital. "I ran half and walked half, that's how I finished.

"Everybody just kind of stared as I'm running by.

Miller said she had been running throughout her pregnancy and marathon officials did not discourage her.

"Nobody tried to do that," she said. "It wasn't too bad, you know? I have been running all the way up until this point anyway so I'm kind of used to it."

She finished the marathon in 6 hours, 25 minutes and 50 seconds. Not her personal best, but she did beat her husband.

Without training for it, he actually got a little bit behind, Miller said. But he was out there with me.

Miller said the contractions started out "just randomly during the race.

But I think just from running throughout the pregnancy, Id usually get a contraction here or there anyway, she said. But then, a few minutes after I finished, I started feeling the contractions and they were coming every five minutes. So I think we waited an hour or so just to kind of make sure it was real labor. They were pretty consistent at that point.

After grabbing a sandwich, she headed for the hospital and June was born at 10:29 p.m. Seven pounds, 13 ounces.

Asked if she was going back to work today, Miller laughed and said, "No, I will not. I'm taking it easy today."
ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Mon Oct 17, 2011 1:31 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

35ኛው የስኮቲያ ባንክ የቶሮንቶ (ካናዳ ) ዓመታዊ የማራቶን ውድድር ::

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሴቶች ምድብ አሸናፊ እና 2 : በወንዶች ምድብ ደግሞ 2 ደረጃን አግኝተዋል :: በተለይ ቆረኔ እና ማሬ ያስመዘገቧቸው ሰዓቶች አዝማሚያ ምናልባት ለወደፊት በሴቶች ማራቶን ሬኮርድ ለመሥበር የሚያስችላቸው ነው ብዬ እገምታለሁ :: ሻሚ በአሸናፊው ኬንያዊ አትሌት በኬኔት የተቀደመው 0.3 ሴኮንድ ብቻ ነበር ::

ምንጭ :- የሴቶች ምድብ የውጤት ሠንጠረዥ ::
1 ..... ቆረኔ ጃለኔ ________ 2 ሰዓት 22 ደቂቃ 42.5 ሴኮንድ
2 ..... ማሬ ዲባባ _________ 2 ሰዓት 23 ሰቂቃ 25.0 ሴኮንድ
5 ..... ነፃነት አቼሞ አብዩ ___2 ሰዓት 32 ደቂቃ 50.0 ሴኮንድ

ምንጭ :- የወንዶች ምድብ የውጤት ሠንጠረዥ ::
2 ..... ሻሚ አብዱላሂ ዳዊት ____ 2 ሰዓት 09 ደቂቃ 50.6 ሴኮንድ
5 ..... ታደሠ አብርሀም ________ 2 ሰዓት 12 ደቂቃ 47.4 ሴኮንድ

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 38, 39, 40 ... 53, 54, 55  Next
Page 39 of 55

 
Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum


Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia