View previous topic :: View next topic
Author
Message
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4451 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Mon Oct 17, 2011 1:45 am Post subject:
እሑድ ጥቅምት 5 ቀን 2004 ዓ .ም .
የ 36ኛው የአምስተርዳም (ሆላንድ ) የማራቶን ውድድር ::
የሴቶችን ምድብ ኢትዮጵያውያቱ ተከታትለው በመግባት ውድድሩን ተቆጣጥረው ጨርሠዋል :- ቲኪ እና እየሩሣሌም :: ያስመዘገቧቸው ሰዓቶች በቅርብ ጊዜ የዓለምን የሴቶች የማራቶን ሩጫ ሬኮርድ ኢትዮጵያውያት አትሌቶች እንደሚሠብሩት ተስፋ የሚሠጥ ነው ::
በዚህ ውድድር ወንዶች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአሸናፊዎች ተርታ አልነበሩበትም ::
ምንጭ :- Wim van Hemert for the IAAF, Sun Oct 16, 2011. Chebet sizzles sub-2:06, course record for Gelana in Amsterdam.
1ኛ ..... ቲኪ ገላና _________ 2 ሰዓት 22 ደቂቃ 08 ሴኮንድ
2ኛ ..... እየሩሣሌም ኩማ ___ 2 ሰዓት 24 ደቂቃ 55 ሴኮንድ
4ኛ ..... ገነት ጌታነህ _______ 2 ሰዓት 25 ደቂቃ 57 ሴኮንድ
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4451 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Tue Oct 18, 2011 1:44 am Post subject:
እሑድ ጥቅምት 5 ቀን 2004 ዓ .ም .
የ 33ኛው የዩራሲያ ጥምር -አህጉር የማራቶን ውድድር : ኢስታንቡል (ቱርክ )
በሴቶቹም ሆነ በወንዶች ምድቦች ኢትዮጵያውያን ውድድሩን ተቆጣጥረው ጨርሠዋል :: በእርግጥ በወንዶቹ ምድብ ኬንያዊው ቪንሴንት ኪፕላጋት ቀዳሚነቱን ወስዶባቸዋል ::
ምንጭ :- Yelena Kurdyumova and Sergey Porada (IAAF), Mon Oct 17, 2011. Kiplagat defends in cold and rainy Istanbul.
የሴቶች ምድብ ::
1ኛ ..... አለሚቱ አበራ _____ 2 ሰዓት 27 ደቂቃ 56 ሴኮንድ
2ኛ ..... ፋጡማ ሣዶ ደርጎ ___ 2 ሰዓት 28 ደቂቃ 01 ሴኮንድ
3ኛ ..... ጸጋ ገላው ________ 2 ሰዓት 28 ደቂቃ 38 ሴኮንድ
4ኛ ..... አሹ ቃሲም ________ 2 ሰዓት 30 ደቂቃ 37 ሴኮንድ
የወንዶች ምድብ ::
1ኛ ..... ቪንሠንት ኪፕላጋት (ኬንያ )_____ 2 ሰዓት 10: ደቂቃ 58 ሴኮንድ
2 ..... ታሪኩ ጁፋር (ኢትዮጵያ ) _______ 2 ሰዓት 11 ደቂቃ 31 ሴኮንድ
3 ..... ጸጋይ ገብረሥላሤ (ኢትዮጵያ ) __ 2 ሰዓት 13 ደቂቃ 39 ሴኮንድ
4 ..... ቃሲም አዲሎ ሮባ (ኢትዮጵያ ) ____ 2 ሰዓት 14 ደቂቃ 20 ሴኮንድ
ከዚህ በተጨማሪ በ 15 ኪ .ሜ ርቀት በተደረገው የሩጫ ውድድር የሁለቱም ምድቦች አሸናፊዎች ኢትዮጵያውያን ሆነዋል ::
የወንዶች ምድብ
1ኛ ..... አጸዱ ጸጋይ ተስፋይ ___ 44 ደቂቃ 05 ሴኮንድ
2ኛ ..... አባይነህ አየለ _______ 44 ደቂቃ 13 ሴኮንድ
የሴቶች ምድብ
1ኛ ..... ሦሥና ግዛው ________ 50 ደቂቃ 45 ሴኮንድ
እኒህ ውጤቶች በሎንዶኑ ኦሎምፒክ ጥሩ ውጤት ለማምጣት ተስፋ ይፈነጥቁ ይሆን ?
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4451 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Tue Oct 18, 2011 4:11 am Post subject:
እሑድ ጥቅምት 5 ቀን 2004 ዓ .ም .
የሬሚስ (ፈረንሣይ ) የማራቶን ውድድር ::
ይህ የማራቶን ውድድር በዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር የነሐስ ደረጃ የተሠጠው ነው :: ቢሆንም ውድድሩ ከፍተኛ ፉክክር ተደርጎበታል :: በወንዶች ምድብ ኢትዮጵያዊው ደምሰው ጸጋ አሸናፊ ሲሆን በሴቶች ምድብ ኬንያዊቷ ጁሊያ ሞምቢ ቀዳሚ በመሆን ጨርሣለች :: በአጠቃላይ በወንዶቹም ሆነ በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያውያን ያስመዘገቡት ውጤት ጥሩ ነበር ::
ምንጭ :- Pierre-Jean Vazel for the IAAF, Monday, 17 October 2011. In debut, Tsega triumphs in Reims.
የወንዶች ምድብ
1ኛ ..... ደምሰው ጸጋ _________ 2 ሰዓት 09 ደቂቃ 44 ሴኮንድ
2ኛ ..... ኃይሉ አበበ ዶጋጋ ____ 2 ሰዓት 09 ደቂቃ 52 ሴኮንድ
7ኛ ..... አብዲሣ ሦሪ _________ 2 ሰዓት 10 ደቂቃ 25 ሴኮንድ
የሴቶች ምድብ ::
1ኛ ..... ጁሊያ ሞምቢ (ኬንያ ) ____ 2 ሰዓት 29 ደቂቃ 35 ሴኮንድ
2ኛ ..... አበራሽ በዴሣ ____________ 2 ሰዓት 29 ደቂቃ 46 ሴኮንድ
3ኛ ..... አየሉ ለማ ______________ 2 ሰዓት 32 ደቂቃ 25 ሴኮንድ
4ኛ ..... አሽቴ ዲዶ ______________ 2 ሰዓት 33 ደቂቃ 58 ሴኮንድ
5ኛ ..... መሠረት ደበሌ __________ 2 ሰዓት 42 ደቂቃ 25 ሴኮንድ
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4451 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Mon Oct 24, 2011 12:50 am Post subject:
እሑድ ጥቅምት 12 ቀን 2004 ዓ .ም .
26ኛው የቬኒስ (ጣሊያን ) ማራቶን ውድድር ::
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በወንዶች ምድብ አሸናፊ : የ 3ኛ : 4ኛና 8ኛ ደረጃ እንዲሁም በሴቶች ምድብ ደግሞ ከ 2ኛ እስከ 4ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ በውድድሩ የበላይነታቸውን አስመስክረዋል ::
ምንጭ :- የወንዶች ምድብ የውጤት ሠንጠረዥ ::
1ኛ ..... ታደሠ አረዶ ____________________ 2 ሰዓት 09 ደቂቃ 13 ሴኮንድ
3ኛ ..... ደበበ ወልዴ _____________________ 2 ሰዓት 09 ደቂቃ 57 ሴኮንድ
4ኛ ..... ደስታ ገብረሕይወት ገብረመድህን ___ 2 ሰዓት 11 ደቂቃ 55 ሴኮንድ
8ኛ ..... ፀጋዬ አሰፋ ሂርጶ ________________ 2 ሰዓት 16 ደቂቃ 47 ሴኮንድ
ምንጭ :- የሴቶች ምድብ የውጤት ሠንጠረዥ ::
2ኛ ..... ማክዳ ሐሩን ____________ 2 ሰዓት 27 ደቂቃ 30 ሴኮንድ
3ኛ ..... ፋንቱ ኢተቻ ጅማ _______ 2 ሰዓት 30 ደቂቃ 25 ሴኮንድ
4ኛ ..... ወርቅነሽ ቶላ ____________ 2 ሰዓት 33 ደቂቃ 01 ሴኮንድ
ብዙ ጊዜ እንደተከታተልኩት ሴት የማራቶን ሯጮቻችን ቅድሚያ የሚወሰድባቸው ከግማሽ ማራቶን (21 ኪ .ሜ ) በኋላ ባለው ርቀት ነው :: ይህንን ድክመት በሥልጠና ለማሻሻል : ወይም ከአመጋገብም ከሆነ ያንን ማስተካከል ያስፈልጋል :: ይህንን ድክመታቸውን ካስተካከሉ በዓለም ዙሪያ በሚደረጉ የማራቶን ውድድሮች በሴቶች ምድብ ከኢትዮጵያውያት ሯጮች ሌላ አሸናፊ ማዬት ብርቅ ይሆናል ብዬ አምናለሁ ::
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4451 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Tue Oct 25, 2011 11:39 pm Post subject:
ሰላም ውድ ወገኖቼ :-
የዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬ ክፍል 4 ቃለ -መጠይቅ እንደወረደ ተከታተሉት ::
ገነነ መኩሪያ : ሊብሮ ጋዜጣ : ማክሰኞ ጥቅምት 14 ቀን 2004 ዓ .ም . :: ዶ /ር ወልደመስቀል ኮስትሬ (ክፍል 4)::
Quote: ሊብሮ፡ - ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት መቼ ነው ?
ዶ /ር ወ /መስቀል ፡ - በ 1972 ዓ .ም መጋቢት ላይ ነው፡፡ ትኬት ስለላኩልኝ ነው የመጣሁት፡፡
ሊብሮ፡ - ባይልኩልዎትስ ?
ዶ /ር ወ /መስቀል፡ - በቃ ! እዚህ አልፈለጉኝም በሚል ወደ ኩዌት ሄጄ እሠራለሁ፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ ሀገሬ እመለሳለሁ የሚል ግምት ነበረኝ፡፡ ነገር ግን በወቅቱ የነበሩት ባለስልጣኖች በውጭ ሀገር የምትገኙ ሙያተኞች ሀገራችሁ ገብታችሁ መስራት አለባችሁ የሚል ቅስቀሳ በማድረጋቸው ለጊዜው ሌላ ቦታ ሄጄየማገኘው ጥቅም ይቅርና ሀገሬ ሄጄ መስራት አለብኝ የሚለው በማመዘኑ ወደዚህ መጣሁ፡፡
ሊብሮ፡ - እርስዎ እዚህ ኮሚሽን ውስጥ ከተመደቡ በኋላ የኢሠፓ ሙሉ አባል ነበሩ፡፡ ታዲያ እንዴት የተሻለ ቦታ አላገኙም ?
ዶ /ር ወ /መስቀል፡ - እንግዲህ ያን ጊዜ ባለሙያን የመመልመል ሁኔታ ነበር፡፡ ስፖርት ኮሚሽን ውስጥ ያሉ አብዛኞቹ አባል ሆነው እየሠሩ ነው፡፡ ለእኔ ቢሮ ሰጥተው እዚያው አስቀመጡኝ፡፡ ፍላጎቴ አሰልጣኝ ሆኜ በመስክ ስራ ላይ መሠማራት ሲሆን ወደዚህ ለመምጣት ትልቅ እንቅፋት ነው የተፈጠረብኝ፡፡ በጥቅሉ ባዶ ቢሮ ነው የሰጡኝ፡፡ ምንም የለም፡፡ ምንም ነገር ስለሌለ ተቃውሞዬን አሰማሁ፡፡ ምክንያቱም የተማርኩትን ትምህርት ወደ ተግባር መለወጥ አልቻልኩም፡፡ በየክፍለሀገሩ እየዞርኩ አንዳንድ ስራ ማከናወን ጀመርኩኝ፡፡ በኋላ ስልጠናውም ቀረና የድርጅት አባል ስለሆንክ ወደ ጫካ እየሄድክ ህብረተሰቡን ማደራጀት አለብህ በመባሌ የስፖርቱን ሙያ ትቼ ወደ ሌላ ነገር ገባሁ፡፡ ከአመት በላይ የሰራሁት ጋምቤላ ነው፡፡ ወደ ጠረፍ አካባቢ ስለምትሄድ የውትድርና ትምህርት መማር አለብህ፡፡ አጋጣሚ ሆኖ እኛ ያለንበት ቦታ የጆን ጋራንግ ወታደሮች፡ ከሱዳን መንግስት ጋር የሚዋጉበት ስፍራ ስለሆነ የግድ እራስህን መጠበቅ አለብህ ፡፡ ወደዚያ ከመሄዳችን በፊት በልዩ ልዩ የቶር ካምፕ ውስጥ ገብተን መሳሪያ አፈታትና ተኩስ ልምምድ ተማርን፡፡ ተራራና ጫካ ውስጥ እየገባን ለብዙ ጊዜ ይህንኑ የመሳሪያ ልምምድ በምሽትና ለሊት ማከናወን፡ነበረብን፡፡ መጠሪያችን ‹‹ ተርብ ሻለቃ›› የሚል ነበር፡፡ ስራው አሰልቺ ነው፡፡ ግን በቦታው አስከተመደብክ ድረስ ግዴታዎች ይኖርብሀል፡፡ በመጨረሻም የውትድርናውን ስልጠና ጨርሼ መሳሪያ ተሰጥቶኝ ነው ወደ ጋምቤላ የሄድኩት፡፡ እዚያ አካባቢ ሰፋሪዎችን ለማደራጀት ጥናት እየተካሄደ ነበር፡፡ ከዩንቨርስቲዎች የተመለመሉ ተማሪዎች በገጠር ያለው ህብረተሰብ እንዴት እየኖረ አንደሆነ ማየት ስለነበረባቸው እነሱ እስኪመጡ ቦታዎችን እናመቻቻለን፡፡
ሊብሮ፡ - የጆን ጋራንግ ወታደሮችን ትረዱ ነበር ? ማለቴ መሳሪያ ስለያዛችሁ በአካባቢው ከእነሱ ጋር ስላላችሁ መሳተፋችሁ አይቀርም በማለት ነው፡፡
ዶ /ር ወልደመስቀል፡ - እንደሱ እንኳን አይደለም፡፡ እርግጥ በጋራ የምንሰራቸው ነገሮች ነበሩ፡፡ በእነሱ ስራ አንሳተፍም፡፡ ሆኖም የጆን ጋራንግ ወታደሮችን በሳምንት የተወሰነ ቀን እያመጣን እኛ ጋር እናሰራቸው ነበር፡፡
ሊብሮ፡ - ጆን ጋራንግ እናንተ ያላችሁበት አካባቢ ይመጣ ነበር ?
ዶ /ር ወልደመስቀል፡ - አዎ፡፡ እዚያ ጋምቤላ አካባቢ ቤት ነበረው፡፡ እናም አንዳንድ ጊዜ ከእነሱ ሰዎች ጋር እንነጋገራለን፡፡ ምክንያቱም አካባቢውን መጠበቅ ነበረብን፡፡ የኛ ተርብ ሻለቃ ይባላል፡፡ ውትድርናን በደንብ አድርጎ የሰለጠነ በመሆኑ የአካባቢውን ሠላም በማስፈን ትልቅ ሚና ተጫውቷል፡፡ የእነሱን ወታደሮች አምጥተን ቤት እናሰራ ፣ ጉድጓድ እናስቆፍር ነበር፡፡
ሊብሮ፡ - ከአዲስ አበባ ባለስልጣኖች እናንተ ጋር ይመጡ ነበር ?
ዶ /ር ወ /መስቀል፡ - አዎ፡፡ እዚያ አካባቢ ያለው ስራ በደንብ መልክ ከያዘ በኋላ መጥተው ነበር፡፡ ይገርምሀል አካባቢው በጣም ለም ነው፡፡ ልዩ ልዩ ፍራፍሬዎች ገና በእሸትነታቸው ሰው ሳይጠቀምባቸው መሬት ላይ ወድቀው ይቀራሉ፡፡ ትዝ ይለኛል የሀገሪቱ ርዕሰ ብሔርና ትልልቅ ባለስልጣኖች ወደዚያ በመጡበት ጊዜ ከእያንዳዱ ፍራፍሬ ተቆርጦ ተሰጥቷቸው በጣም ነው የተገረሙት፡፡ ታዋቂ ዘፋኞችም እዚያ መጥተው ትርኢታቸውን አሳይተው ነበር፡፡ ንዋይ ደበበ ያንን ከተመለከተ በኋላ ነው ‹‹ እሸት በላሁኝ›› የሚለውን የዘፈነው፡፡ እርሱም እዚያ ሊዘፍን መጥቶ ቦታውን በማየቱ ተገርሞ ነበር፡፡
ሊብሮ፡ - እዚያ ምን ያህል ጊዜ ቆዩ ?
ዶ /ር ወ /መስቀል፡ - ከአመት በላይ ቆይቻለሁ፡፡ 538 ካድሬ ነው ወደዚያ የሄደው፡፡ያ ሁሉ በየጊዜው አካባቢውን ሲያደራጅ ነው የሚውለው፡፡ የሚያስፈራው ከዋናው መንገድ ተገንጥለህ መውጣቱ ነው፡፡
ሊብሮ፡ - ሽፍታ ነው ?
ዶ /ር ወ /መስቀል፡ - አይደለም፡፡ አውሬ በጣም አለ፡፡ አንበሳና ነብር ትንሽ ወደ ጫካው ገባ ካልክ የእነሱ ስፍራ ነው፡፡ ሌላም አውሬ አለ፡፡ (ሳቅ ) ስለዚህ ከመንገድ ለቀህ አትወጣም፡፡ተማሪዎች ከዩንቨርስቲ በመጡ ጊዜ መጀመሪያ ያስጠነቀቅናቸው ወደ ጫካ እንዳትገቡ ነው፡፡ ጫካው እልም ያለ ደን ያለበት ሲሆን አትክልትና ፍራፍሬም በወፍ ዘራሽ የበቀለ እዚያ አለ፡፡ አንድ ጊዜ 2 ተማሪዎች ጠፍተውብን በግድ ነው ያገኘናቸው፡፡ አንዱ ልዋኝ ብሎ በዚያው ጠፍቶ ቀረ፡፡ አንደኛው መሳሪያ ልፈትሸ ብሎ ቃታ ሲስብ ከተመታው በስተቀር ሌላ አደጋ አልደረሰም፡፡
ሊብሮ፡ - ዋናው ስራችሁ ምንድን ነው ?
ዶ /ር ወ /መስቀል፡ - እኛ ካድሬዎቹ መቀስቀስ ነው፡፡ በአካባቢው የጉድጓድ ውሀ እናስቆፍራለን፣ ት /ቤት እናሰራለን፣ ድልድዮች እናስቆፍራለን፣ መኖሪያ ቤት እናሰራለን፣ በገጠር ያለውን ነዋሪ እናግዛለን፡፡ በቃ ገጠርን ማልማት ነው፡፡
ሊብሮ፡ -አሰልጣኝነትዎት ቀረ ? ለመሆኑ ይህን ነገር ስትሠሩ የተለያዩ ሙያተኞችን ታገኙ ነበር ?
ዶ /ር ወ /መስቀል፡ - አዎ፡፡ መሳሪያ ይዤ ገጠር ስለገባሁ ከሙያው ርቄአለሁ፡፡ የቀረው በውስጤ ያለው የስፖርቱ ስሜትና እውቀት ብቻ ነው፡፡ በተግባር ግን ሌላ ነገር እየሠራሁ ነው፡፡ ነገር ግን ከኢትዮጵያን ወገኖቼ ጋር ገጠር እነሱን መስዬ፣ የሚኖሩትን መኖሬና ያንን ነገር ማየቴ ለእኔ ትልቅ ትምህርት ነው የሰጠኝ፡፡ ሙያተኞችን በተመለከተ ዋናው የኛ የካድሬዎቹ ስራ ሌሎቹን ማስተባበር ነው፡፡ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከኮንስትራክሽን፣ ከግብርና፣ ከውሃ ልማት ከሁሉም ዘርፍ የተውጣጣውን ባለሙያ እንቀሰቅሳለን፣ እናደራጃለን፡፡ እነሱ ይሠራሉ፡፡
ሊብሮ፡ - እርስዎ በኃላፊነት ደረጃ ይሠሩ ነበር ?
ዶ /ር ወ /መስቀል፡ - 7 ሰራ አስፈፃሚዎች አሉ፡፡ ከእነርሱ ውስጥ አንዱ ነበርኩኝ፡፡ ትዕዛዝ ብናወጣም እራሳችንም እንሠራለን፡፡ ምክንያቱም ያለነው ጫካ ውስጥ ለምሳሌ አንድ ሠፈራ ጣቢያ ከጋምቤላ 135 ኪ .ሜ ርቀት ታታ ዙሪያ የተባለቦታ አለ፡፡ እዚያ አካባቢ ነበር ያለነው፡፡ ዝሆኑ ከመሸ ስለማያስኬድህ በጊዜ ነው የምትገባው፡፡
ሊብሮ፡ - ጋምቤላ ስራ ጨርሳችሁ ወደ አዲስ አበባ፡ስትመለሱ እርስዎ ወዴት ሄዱ ?
ዶ /ር ወ /መስቀል፡ - መጀመሪያ ከውጭ ስመጣ ባዶ ቢሮ ሰጡኝ፡፡ ከዚያ ወደ ጫካ ሄድኩኝ፡፡ ስመለስ እዚያው ቢሮ ግባ ሲሉኝ አልፈልግም ኮተቤ እገባለሁ ብዬ ፕሮሰስ ጀመርኩኝ፡፡ ምክንያቱም ስፖርት ኮሚሽን ምንም ካልሠራሁ ኮተቤ መምህራን ማሰልጠኛ ባስተምር ይሻላል በማለት ነው፡፡ የለፋሁበትን የደከምኩበትን ውጤት ስፖርት ኮሚሽን ሊጠቀምበት ስላልቻለ እንደዚህ የዘመቻ ስራ ሲመጣ በየቦታው ከሚልከኝ አንድ ውሳኔ ወስኜ መውጣት አለብኝ አልኩ፡፡ ከዚያ ከብዙ ትግል በኋላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እንድሠራ ተመድቤ አሰልጣኝ ሆንኩኝ፡፡ ነፍሱን ይማረውና ንጉሴ ሮባ አማካሪ ሆኖ እኔ አሰልጣኝ በመሆን በጋራ መሰራት ጀመርን፡፡
ሊብሮ፡ - መቼ ነው ይህ የሆነው ?
ዶ /ር ወ /መስቀል፡ - በ 1977 ፣ 78 አካባቢ፡፡ ወደ ክፍለ ሀገር እየሄድን አትሌቶችን መመልመል ጀመርን፡፡ በሙያዬ ቦታውን ለማግኘት የነበረኝ ፍላጎት ከፍተኛ ስለነበር ቀኑን ሙሉ በስልጠና ላይ ነበር የማሳልፈው፡፡ በዚያን ወቅት ተተኪ አትሌቶችን ማምጣት የነበረብን በመሆኑ ብዙ ተሰርቷል፡፡ ግን ወቅቱ ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ የምትካፈልበት ጊዜ አልነበረም፡፡ ሎስአንጀለስ ላይ ሳትካፈል ቀረች፡፡ እንደገና ሴኡል ላይ ሳትካፈል ስለቀረች ስራችንን ማሳየት አልቻልንም፡፡ ከሴኡል ቀጥሎ ባርሴሎና ነበር፡፡ እንግዲህ ያን ጊዜ ነው እነ ደራርቱ ውጤት ያመጡት፡፡ ኢትዮጵያ ያን ጊዜ ኦሎምፒክ 8 ዓመት ሳትካፈል ስለቆች የልምድ ማጣቱ ሌሎቹን ጎድቷቸዋል፡፡ እንግዲህ አሁን በደረጃ ስታየው ለውጥ እያመጣ ነው፡፡ ባርሴሎና አንድ ወርቅ ሜዳልያ መጣ፣ አትላንታ ደግሞ 2 ወርቅ ሜዳልያ መጣ፣ አሁን በሲዲኒ 8 ሜዳልያ መጣ፡፡ ይህ እየተሻሻለ እንደሄደ ያሳያል፡፡ እንግዲህ አሁን ይህን ጠብቆ መሄዱ ነው ዋናው ነገር፡፡
ሊብሮ፡ - ከባርሴሎና በኋላ እርስዎ እንዲወጡ ተደርጎ ነበር…
ዶ /ር ወ /መስቀል፡ - ያኔ አፈርሳታ ተብሎ ብዙ ችግር መጣ፡፡ ቦታ ለመያዝ ሽሚያ ይመስላል፡፡ ማንም ሰው እኮ ሠርቶ ውጤት ካመጣ እኛም ቦታውን መልቀቅ እንችላለን፡፡ ሆኖም በወቅቱ የነበሩት ባለሙያዎችና ኃላፊዎች ጥሩ ነገር አልሠሩም፡፡ መራበሽ አትሌቲክሱን ይጎዳል እንጂ አይጠቅምም፡፡ እኔ በቦታው ሆኜ ጥሩ ውጤት ካመጣሁ ማበረታታት እንጂ መወንጀል የለባቸውም፡፡ ወቅቱ የመንግስት ለውጥ ያለበት በመሆኑ ከሌላ ነገር ጋር እያያዙ አትሌቲክሱ ውስጥ ጥፋት እንደፈጸምን ተደርጎ ከአካባቢው እንድንርቅ የተሞከረው በእውነት በአትሌቶቹና በስፖርት ቤተሰቡ ጥረት ወደ ቦታችን ተመልሰን አሁን የተሻለ ውጤት እንዲታይ ማድረግ ችለናል፡፡ ለፍርድ ሁሉ የሚያስቸግር ነበር፡፡ይህ የተከሰተው ከባርሴሎና ኦሎምፒክ ማግስት ነው፡፡ ውንጀላው ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ድረስ የደረሰ ሲሆን በኛ ላይ መጥፎ ነገር አንዲወሰን ነበር፡፡ ግን በወቅቱ የሀገሪቱ ፕሬዘዳንት የነበሩት ክቡር አቶ መለስ ዜናዊ ‹‹ ትላንት እነዚህን ጀግና ብለን ሸልመን ዛሬ እንደገና እንዴት ወንጀለኛ ይባላሉ ?›› በሚል ምላሽ ከሠጡ በኋላ ነገሩ እየታየ ሲመጣ ጥፋተኛ አለመሆናችን ታውቆ እንደገና ወደስራው ተመልሰን ለመስራት ችለናል፡፡
ሊብሮ፡ - በሲድኒ አሎምፒክ የተገኘው ውጤት በርስዎ ዘንድ ምን ስሜት ፈጥሯል ?
ዶ /ር ወ /መስቀል፡ - እንግዲህ እኔ በእግሬ ላይ ጉዳት ደርሶ በዱላ ነው የምሄደው፡፡ ይህ አደጋ ስለደረሠብኝ ብዙ ነገር ተሠምቶኛል፡፡ እንደዚህም ሆኖ አሰልጥኜ ይህን ያህል ሜዳልያ ይዘን ወደ ሀገራችን ስንመለስ ህዝቡ ያሳየን ልባዊ አቀባበል እኔ እራሴን እንደ ጉዳተኛ እንዳላይ አድርጎኛል፡፡ ህዝቡ የጣለብንን አደራ ተቀብለን ይህ ምላሽ በመገኘቱ ደስታዬ ወሰን የለውም፡፡ ጡረታ ብወጣም ገና ነገም ለህዝቡና ለሀገሬ አንድ ነገር ለመስራት ትልቅ ፍላጎት አለኝ፡፡
ሊብሮ፡ - እስቲ ወደ እግር ኳሱ ደግሞ እንመለስ፡፡ በአትሌቲክስ እንዳዩት ረጅም አመት በኢንተርናሽናል ውድድር ውጤት አለን፡፡ የአጋጣሚ ሆኖ ህዝቡ ለእግር ኳስ ያለው ስሜት ከፍተኛ ነው፡፡ በእግር ኳሱ ውጤት ባለመምጣቱ የህዝቡ ስሜት እየተነካ ነው፡፡ ለእግር ኳሱ መውደቅ ዋናው ምክንያት ምንድነው ብለው ይገምታሉ ?
ዶ /ር ወ /መስቀል፡ - ብዙ ነገሮችን ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ ሜዳ፣ ዘመናዊ ስልጠና፣ አያያዝ፣ አስተዳደር እነዚህ ሁሉ ለውጤቱ መዳከም አስተዋፅኦ ያደርጋሉ፡፡
ሊብሮ፡ - ለምሳሌ በፊት ብዙ ሜዳዎች ነበሩ፡፡ በዚያ ጊዜም ለውጥ ማምጣት አልተቻለም፡፡ አያያዝ ደግሞ ከበፊቱ አሁን ተሽሏል ፡፡ ለእግር ኳሱ ብዙ ገንዘብ እየወጣ ነው፡፡ ግን በዚህም ለውጥ አልታየም፡፡ ስለዚህ ዋናው ችግር ስልጠናው ላይ ይመስላል፡፡ በዚህ ላይ ያለዎት አስተያየት ምን ይመስላል ?
ዶ /ር ወ /መስቀል፡ - እርግጥ ነው ስልጠና ወሳኝ ነው፡፡
ሊብሮ፡ - የሳይንሳዊ ፉትቦል ስልጠና ለእግር ኳሳችን ለውጥ ያመጣል ?
ዶ /ር ወ /መስቀል፡ - በደንብ ከተሰራበት እግር ኳሱን ማሻሻል የማይቻልበት ሁኔታ የለም፡፡ አሁን የህፃናት ፕሮጀክት ስላለ በሳይንሳዊ ስልጠና በደንብ ኮትኩቶ ማሳደግ ከተቻለ ለውጥ ማምጣት ይቻላል፡፡ ሌሎች ሀገሮች እኮ በፕሮጀክት ስልጠና ለውጥ ማምጣት ችለዋል፡፡
ሊብሮ፡ - ሳይንሳዊ ስልጠና ከህፃናት ጀምሮ ይሰጥ ከተባለ በኛ በኩል ድክመት የሆነው ፍጥነትና ጉልበት ነወ፡፡ ሳይንሱም ፍጥነትና ጉልበት እንዲያዳብሩ ነው የሚረዳው፡፡ይህን ማዳበር እና ለውጥ ማምጣት ይቻላል፡፡ ግን በንፅፅር ከሌሎች ጋር እኩል መቆም እንችላለን ?
ዶ /ር ወ /መስቀል፡ - አሁን እኮ በጣም ተራርቀናል፡፡ መጀመሪያ ያንን ማጥበብ አለብን፡፡ አንድ ተጨዋች ፈጣን ካልሆነ፣ ጥንካሬ ኖሮት መጋፋት፣ ወድቆ መነሳት ካልቻለ እንዴት አድርጎ ነው መቋቋም የሚችለው ? ለዚህ ደግሞ ፍጥነትህንና ጉልበትህን የምታዳብርበት ዘመናዊ ስልጠና መውሰድ አለብህ፡፡
ሊብሮ፡ - ባለፈው እንደገለጹልኝ እርስዎ ቅ /ጊዮርጊስ ውስጥ በአብዛኛው አካል ብቃትን ስልጠና ነው ይሠሩ የነበሩት፡፡ በዚያን ጊዜ ክለቡን ከተረከቡ ጀምሮ በወወክማ፣ ጅምናስቲክ ስራ እንዲሁም በአዲስ አበባ ስታዲየም ሚዞሎቪች ባዘጋጃቸው የአካል ብቃት ማዳበር ስፍራ ማቴሪያሎች በመጠቀም ተጨዋቾቹ ጠንካራ እንዲሆኑ አድርገዋል፡፡ በዚህም ቡድኑ ሻምፒዮና ሆኗል፡፡ ነገር ግን ለአፍሪካ የክለብ ሻምፒዮና ሲጫወት በያንግ አፍሪካ 5ለ 0 ተሸነፈ፡፡ በቀጣዩ ዓመት ደግሞ በኡጋንዳው ሲምባ 4ለ 0 ተሸነፈ፡፡ ከሀገር ውጭ መሸነፉ ብቻ ሳይሆን አንድም ጎል ሳያገባ መምጣቱ መቋቋም እንዳልቻለ ያሳያል፡፡ እንዲያ ተሠርቶ ለውጥ ካልመጣ ችግሩ ምን ነበር ?
ዶ /ር ወ /መስቀል፡ - እርግጥ ነው ችግሩ በአካል ብቃት መበለጥ ብቻ አይደለም፡፡ በዚያን ወቅት የክለብ አደረጃጀትና አያያዙ በሀገር ውስጥ እንጂ በኢንተርናሽናል ብዙም የምትገፋበት አይደለም፡፡ ተጨዋቾቹ ደመወዝ የላቸውም፣ በሳምንት የተወሰነ ቀን ነው የሚሰሩት፡፡
ሊብሮ፡ -እንደዛም ሆኖ እኮ በሀገር ውስጥ ሻምፒዮና ሆነዋል፡፡
ዶ /ር ወ /መስቀል፡ - እርግጥ ነው በሀገር ውስጥ ሻምፒዮና ነበሩ፡፡ ግን በኢንተርናሽናል ውድድር መሳተፍና በዚያ ሁኔታ መቀጠል አስቸጋሪ ነበር፡፡
ሊብሮ፡ - 7ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሱዳን ላይ ሲካሄድ እርስዎ ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር አሰልጣኝ ሆነው ሄደዋል፡፡ በዚያ ውድድር አንድም ጨዋታ ሳናሸንፍ መጥተናል፡፡ በሱዳን 3ለ 0 ተሸነፍን፣ በካሜሩን 3ለ 2 ተሸነፍን፣ በአይቮሪኮስት 6ለ 1 ተሸነፍን፡፡ ከሀገር ውጭ ብዙ ጊዜ ውጤት የለንም፡፡ ከሱዳን በስተቀር ሁለቱ አይቮሪኮስትና ካሜሩን ሀገራቸው አይደለም፡፡ ግንአሸንፈውናል፡፡ መቋቋም ያልቻልንበት ምክንያት ምን ነበር ?
ዶ /ር ወ /መስቀል፡ - በዚያን ጊዜ ቡድኑ ጥሩ አልነበረም፡፡ የጨዋታ ማቆሚያ ጊዜያቸው የደረሱ ተጨዋቾች አንዲሰለፉ መደረጉም ተገቢ አልነበረም፡፡ እነ መንግስቱ፣ ፍስሐ ብዙም ከቡድኑ ጋር ሳይለማመዱ ነው የገቡት፡፡ ሌሎችም እንደዚሁ፡፡ ወጣቶቹ ሙሉ ለሙሉ ቢጫወቱ ይህን ያህል ሽንፈት ባልመጣ ነበር፡፡ ወደ አዲስ አበባ ከተመለስን በኋላ ይህን ሪፖርት አድርገናል፡፡ ሽማግሌዎቹ ወጥተው ወጣቶቹ ቢጫወቱ የተሻለ ነበር፡፡
ሊብሮ፡ - የወጣት ነገር ከተነሳ እንዲህ አይነቱ ነገር ያን ጊዜ ለሽንፈቱ ምክንያት ተደርጎ ተወስዶ ነበር፡፡ እነ መንግስቱ፣ ሉቻኖም… . ሌሎችም ተጨዋቾች ወጥተው በወጣቶች ተገንብቶ ለ 8ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በኬንያ ተሸንፎ ከውድደሩ ወጥቶ ጭራሽ ማለፍ አልቻለም፡፡ በ 7ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ችግሩ የወጣቶቹ አለመጫወት ከነበረ በ 8ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ወጣቶች ገብተው ማጣሪውን እንኳን ማለፍ እንዴት አቃታቸው ?
ዶ /ር ወ /መስቀል፡ - በዚያን ጊዜ እኔ ከብሔራዊ ቡድኑ ጥቂት ጊዜ ሰርቼ ትቼ ነበር፡፡ 8ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያው ላይ ብዙም ተሳትፎ አልነበረኝም፡፡
ሊብሮ፡ - ተሳትፎ ባይኖሮዎትም በወጣቶች ይተካ ተብሎ ለምን ቡድኑ ማጣሪያውን ማለፍ አቃተው ? ዋናው ጥያቄ በኢንተርናሽናል ጌም በተለይ ከሀገር ውጭ ባለጋራዎቻችን የሚያሸንፉትን በፍጥነትና ጉልበት ከሆነ እኛ ለምንድነው በዚህ መንገድ የምንሄደው ?
ይቀጥላል
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ጌታ Joined: 17 Apr 2005 Posts: 3225 Location: ዶሮ ተራ
Posted: Fri Oct 28, 2011 5:51 pm Post subject:
ውድ ተድላ
የዛሬ ወር ግድም አንዲት አፍሪካን የመጎብኘት ፍላጎት ያላት የሥራ ባልደረባዬ "እናንተም እንደኬንያ ሩጫ ታውቃላቹ ?" ብላ ስትጠይቀኝ በስሜት እንዴ ! የማራቶን የ 10 ሺህ እና የ 5ሺ ሬከርድ ባለቤቶች ; ያበበ ቢቂላ የኃይሌ ገብረስላሴ አገር እያልኩ ደነፋሁና ድንፋታዬን በማስረጃ ላስረግጥ ጉግል ሳደርግ ማራቶኑ ካንድ ቀን በፊት እንደተወሰደ ተረዳሁ :: ቢሆንም ቅሉ ላለፉት ብዙ ዓመታት በኛ እጅ እንደነበር ማሳየት ችያለሁ :: በቅርቡ አንዱ አንበሳ መልሶ እጃችን እንደሚያስገባ አልጠራጠርም :: አይዞን :: _________________ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4451 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Fri Oct 28, 2011 7:53 pm Post subject:
ጌታ እንደጻፈ(ች)ው : ውድ ተድላ
የዛሬ ወር ግድም አንዲት አፍሪካን የመጎብኘት ፍላጎት ያላት የሥራ ባልደረባዬ "እናንተም እንደኬንያ ሩጫ ታውቃላቹ ?" ብላ ስትጠይቀኝ በስሜት እንዴ ! የማራቶን የ 10 ሺህ እና የ 5ሺ ሬከርድ ባለቤቶች ; ያበበ ቢቂላ የኃይሌ ገብረስላሴ አገር እያልኩ ደነፋሁና ድንፋታዬን በማስረጃ ላስረግጥ ጉግል ሳደርግ ማራቶኑ ካንድ ቀን በፊት እንደተወሰደ ተረዳሁ :: ቢሆንም ቅሉ ላለፉት ብዙ ዓመታት በኛ እጅ እንደነበር ማሳየት ችያለሁ :: በቅርቡ አንዱ አንበሳ መልሶ እጃችን እንደሚያስገባ አልጠራጠርም :: አይዞን ::
ሠላም ጌታ እንዴት ነህ ?
የዘንድሮውን የኢትዮጵያ ሯጮች ውጤት 'ተከድኖ ይብሠል :' ማለቱ ይቀልላል :: እንዲያው ለእኛ ለኢትዮጵያውያን የሩጫ ውድድር ማለት 'አንድ ዐይን ያለው በአፈር አይጫወትም :' እንደሚባለው ሆኖብን ነው እንጂ በኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ስፖርት አዝማሚያ በጣም አስጊ ሁኔታ ላይ ነው :: የእኔ ፍርሃት በዘንድሮው የሎንዶን ኦሎምፒክ ያለ ምንም ሜዳሊያ እንዳንቀር ነው :: ብቻ እንደ ምኞትህ በጎ በጎውን ያሠማን ::
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4451 Location: ኢትዮጵያ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4451 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Sun Nov 06, 2011 11:37 pm Post subject:
እሑድ ጥቅምት 26 ቀን 2004 ዓ .ም .
42ኛው የኒው ዮርክ ከተማ የማራቶን ውድድር ::
በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ ፍሬሕይወት ዳዶ በወንዶች ምድብ ደግሞ አምና በቦስተን ማራቶን የዓለም ፈጣኑን ሰዓት ያስመዘገበው ጆፍሬይ ሙታይ አሸናፊዎች ሆነዋል :: ለፍሬሕይወት ይህ የኒው ዮርክ ድሏ በታላቅ የማራቶን ውድድር የመጀመሪያዋ ነው : የግሉአንም ሬኮርድ በ 1 ደቂቃ ያህል አሻሽላለች :: ጆፍሬይ በዚሁ የኒው ዮርክ ማራቶን ውድድር ከ 10 ዓመታት በፊት በኢትዮጵያዊው ተስፋዬ ጅፋር ተይዞ የነበረውን የሥፍራውን ሬኮርድ በ 2 ደቂቃ ከ 37 ሴኮንድ ያህል አሻሽሎታል ::
ምንጭ :- The New York City Marathon - Top Women's Finishers, Sun Nov 6, 2011.
ደረጃ ___ ስም _____________ ሰዓት ___
1ኛ ..... ፍሬሕይወት ዳዶ ________ 02:23:15
2ኛ ..... ብዙነሽ ዳባ ____________ 02:23:19
11ኛ ... ምሥክር መኮንን ደምሴ ____ 02:31:40
13ኛ ... ወርቅነሽ ኪዳኔ _________ 02:33:08
15ኛ ... ሠርካለም ቢሠጥ አብርሃ __ 02:33:22
17ኛ ... አዚዛ አልዩ ___________ 02:38:32
ምንጭ :- The New York City Marathon - Top Men's Finishers, Sun Nov 6, 2011.
ደረጃ ___ ስም _____________ ሰዓት ___
1ኛ ..... ጆፍሬይ ሙታይ (ኬንያ ) ____ 02:05:05
2ኛ ..... ኢማኑኤል ሙታይ (ኬንያ ) __ 02:06:28
3ኛ ..... ፀጋዬ ከበደ (ኢትዮጵያ ) ____ 02:07:14
4ኛ ..... ገብረእግአብሔር ገብረማርያም (ኢትዮጵያ ) _02:07:59
9ኛ ..... ሕዝቅያስ ሲሣይ (ኢትዮጵያ ) ____ 02:11:04
14ኛ .... ተክሉ ተፈራ ደነቀ (ኢትዮጵያ ) ___ 02:16:20
16ኛ ... ተስፋዬ አሰፋ ዱቤ (ኢትዮጵያ ) ___ 02:19:24
18ኛ ... ባዶ ወርቁ መርደሣ (ኢትዮጵያ ) ___ 02:20:22
19ኛ ... ፈቃዱ ለማ (ኢትዮጵያ ) ___ 02:20:41
ውጤታቸውና ደረጃቸው ይህንን ይመስላል ::
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ጌታ Joined: 17 Apr 2005 Posts: 3225 Location: ዶሮ ተራ
Posted: Mon Nov 07, 2011 3:08 pm Post subject:
ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው : እሑድ ጥቅምት 26 ቀን 2004 ዓ .ም .
42ኛው የኒው ዮርክ ከተማ የማራቶን ውድድር ::
በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ ፍሬሕይወት ዳዶ በወንዶች ምድብ ደግሞ አምና በቦስተን ማራቶን የዓለም ፈጣኑን ሰዓት ያስመዘገበው ጆፍሬይ ሙታይ አሸናፊዎች ሆነዋል :: ለፍሬሕይወት ይህ የኒው ዮርክ ድሏ በታላቅ የማራቶን ውድድር የመጀመሪያዋ ነው : የግሉአንም ሬኮርድ በ 1 ደቂቃ ያህል አሻሽላለች :: ጆፍሬይ በዚሁ የኒው ዮርክ ማራቶን ውድድር ከ 10 ዓመታት በፊት በኢትዮጵያዊው ተስፋዬ ጅፋር ተይዞ የነበረውን የሥፍራውን ሬኮርድ በ 2 ደቂቃ ከ 37 ሴኮንድ ያህል አሻሽሎታል ::
ምንጭ :- The New York City Marathon - Top Women's Finishers, Sun Nov 6, 2011.
ደረጃ ___ ስም _____________ ሰዓት ___
1ኛ ..... ፍሬሕይወት ዳዶ ________ 02:23:15
2ኛ ..... ብዙነሽ ዳባ ____________ 02:23:19
11ኛ ... ምሥክር መኮንን ደምሴ ____ 02:31:40
13ኛ ... ወርቅነሽ ኪዳኔ _________ 02:33:08
15ኛ ... ሠርካለም ቢሠጥ አብርሃ __ 02:33:22
17ኛ ... አዚዛ አልዩ ___________ 02:38:32
ምንጭ :- The New York City Marathon - Top Men's Finishers, Sun Nov 6, 2011.
ደረጃ ___ ስም _____________ ሰዓት ___
1ኛ ..... ጆፍሬይ ሙታይ (ኬንያ ) ____ 02:05:05
2ኛ ..... ኢማኑኤል ሙታይ (ኬንያ ) __ 02:06:28
3ኛ ..... ፀጋዬ ከበደ (ኢትዮጵያ ) ____ 02:07:14
4ኛ ..... ገብረእግአብሔር ገብረማርያም (ኢትዮጵያ ) _02:07:59
9ኛ ..... ሕዝቅያስ ሲሣይ (ኢትዮጵያ ) ____ 02:11:04
14ኛ .... ተክሉ ተፈራ ደነቀ (ኢትዮጵያ ) ___ 02:16:20
16ኛ ... ተስፋዬ አሰፋ ዱቤ (ኢትዮጵያ ) ___ 02:19:24
18ኛ ... ባዶ ወርቁ መርደሣ (ኢትዮጵያ ) ___ 02:20:22
19ኛ ... ፈቃዱ ለማ (ኢትዮጵያ ) ___ 02:20:41
ውጤታቸውና ደረጃቸው ይህንን ይመስላል ::
ተድላ
ሰላም ተድላ
ትናንት ይህን ማራቶን ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ ተከታትዬው ነበር :: አጀማመሩ ላይ ከሴቶቹ ይልቅ ወንዶቹ ላይ የተሻለ ተሥፋ ታይቶኝ ነበር :: በሴቶቹ ኬንያዊቷ ሜሪ ኪታኒ ቀደም ብላ ፈትለክ ብላ በመውጣት 3 ማይል አካባቢ እስኪቀራት ድረስ ባለድልነቷን እርግጠኛ ሆና ነበር :: መጨረሻ ላይ ጉልበቷን አሟጣ ስታንቀላፋ የኛ አናብስት ተረጋግተው ወርቅና ብሩን ተረከቧት :: በወንዶቹ ሕዝቅያስ ሲሳይ , ገብሬ ገ /ማርያም እና ጸጋዬ ከበደ ጥሩ ፉክክር ቢያደርጉም ጄፍሪ ሙታይ ከሌላ ዓለም የመጣ ፍጡር ወይም ማሽን እንጂ እንደኛ ሰው አይመስል ስለነበር ምንም ማድረግ አልተቻለም :: አዎ ኬንያዎቹ በርትተዋል :: ይህን ክብር ለመመለስ ብዙ መስራት ይጠበቅብናል :: ሌላው ስለ አሸናፊው ሙታይ ያቀረቡት የሚያስደስት ነገር አሸንፎ ባገኘው ገንዘብ ቤት ገዝቶ ወደ 60 የሚሆኑ አትሌቶችን አሰባስቦ እንደሚረዳ አሳይተው ነበር :: ሲሰለጥኑም እንዲሁ በኅብረት ነው :: ኃይሌ ከብዙ ዓመታት በፊት እንደዚህ ዓይነት ነገር አስቦ እንደነበር ሰምቻለሁ የት እንደደረሰ ባላውቅም :: ምንአልባትም ኃሳቡን ከሱ ይሆናል የወሰደው ::
ለማንኛውም ባጠቃላይ ያገኘነው ውጤት የሚያኮራ ነው :: _________________ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4451 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Mon Nov 07, 2011 11:53 pm Post subject:
ጌታ እንደጻፈ(ች)ው : ሰላም ተድላ
ትናንት ይህን ማራቶን ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ ተከታትዬው ነበር :: አጀማመሩ ላይ ከሴቶቹ ይልቅ ወንዶቹ ላይ የተሻለ ተሥፋ ታይቶኝ ነበር :: በሴቶቹ ኬንያዊቷ ሜሪ ኪታኒ ቀደም ብላ ፈትለክ ብላ በመውጣት 3 ማይል አካባቢ እስኪቀራት ድረስ ባለድልነቷን እርግጠኛ ሆና ነበር :: መጨረሻ ላይ ጉልበቷን አሟጣ ስታንቀላፋ የኛ አናብስት ተረጋግተው ወርቅና ብሩን ተረከቧት :: በወንዶቹ ሕዝቅያስ ሲሳይ , ገብሬ ገ /ማርያም እና ጸጋዬ ከበደ ጥሩ ፉክክር ቢያደርጉም ጄፍሪ ሙታይ ከሌላ ዓለም የመጣ ፍጡር ወይም ማሽን እንጂ እንደኛ ሰው አይመስል ስለነበር ምንም ማድረግ አልተቻለም ::
ሰላም ሰላም ጌታ :-
ሴቶቹ የማራቶን ሯጮቻችን ተስፋ አላቸው :: እንዲያውም አንተ ይህንን ውድድር ተከታትለህ አንድ ጠቃሚ ቁምነገር ጠቁመኸናል :- የእኛ ሴት ሯጮች ጉልበታቸውን አስቀደመው አሟጠው ሣይጨርሱ ወደ መጨረሻ ላይ ያሣዩትን ጥንካሬ :: አየህ ከቀድሞው የተለየ ሥልጠና አግኝተዋል : ያለበለዚያም እነርሱው በልምድ ድክመታቸውን አግኝተውታል ማለት ነው :: እስካሁን ድረስ እንደሚታየው ኢትዮጵያውያት የማራቶን ሯጮች እስከ ግማሹ ድረስ ይመሩና ከዚያ ወገቤን ይሉ ነበር :: ወንዶቹ ግን ከፀጋዬ በስተቀር ያን ያህል ታዋቂ የማራቶን ሯጮች አይደሉም :: ገብረእግዚአብሔር ይህ ሦሥተኛው ወይም እንደዚያ የማራቶን ውድድር ነው :: ምናልባት ገብረእግዚአብሔር ወደፊት በማራቶን ሩጫ እያሻሻለ ይሄድ ይሆናል ::
Quote: አዎ ኬንያዎቹ በርትተዋል :: ይህን ክብር ለመመለስ ብዙ መስራት ይጠበቅብናል ::
ኬንያዎች መበርታታቸውን እያዩ የእኛ አገር የአትሌቲክስ ስፖርት ባለሥልጣኖች ይበልጥ አፍራሽ ተግባር ላይ ናቸው :: ይህ ድርጊት ደግሞ የማንኛውንም ኢትዮጵያዊ ልብ የሚያደማ እና የሚያስጨንቅ ነው :: እንዲያው እንደ ሁልጊዜው አትሌቶቹ በራሣቸው ጥረት በኦሎምፒክ ውጤት ለማምጣት ቢጣጣሩ እንዳይባል እንኳን እነርሱም ብር ባለበት ልባቸው እስኪጠፋ መሮጥ እንጂ ለሜዳሊያ ብዙም የሚጨነቁ ሆነው አልተገኙም :: እንደ እኔ እንደ እኔ በመጪው የሎንዶን ኦሎምፒክ ያለ ሜዳሊያ እንዳንቀር እሠጋለሁ ::
Quote: ሌላው ስለ አሸናፊው ሙታይ ያቀረቡት የሚያስደስት ነገር አሸንፎ ባገኘው ገንዘብ ቤት ገዝቶ ወደ 60 የሚሆኑ አትሌቶችን አሰባስቦ እንደሚረዳ አሳይተው ነበር :: ሲሰለጥኑም እንዲሁ በኅብረት ነው :: ኃይሌ ከብዙ ዓመታት በፊት እንደዚህ ዓይነት ነገር አስቦ እንደነበር ሰምቻለሁ የት እንደደረሰ ባላውቅም :: ምንአልባትም ኃሳቡን ከሱ ይሆናል የወሰደው ::
ለማንኛውም ባጠቃላይ ያገኘነው ውጤት የሚያኮራ ነው ::
ኃይሌ ገብረሥላሤ በወያኔ እቅፍ ሙሉ በሙሉ ከገባ በኋላ ምኅዋሩን የሣተ መንኮራኩር ሆኗል :: እንኳን እንደ ድሮው አትሌቶችን ሠብስቦ ሊረዳ ይቅርና በየውድድሩ እንኳን ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አብረውት እንዳይወዳደሩ እስከማድረግ ደርሷል :: ኃይሌ ገብረሥላሤ ለእኔ በአትሌትነቱ ሞቷል : ያለው ገንዘብ የሚያሣድድ ደላላ ኃይሌ ነው :: ይህንን የምለው ኃይሌ ራሱን ከጉልላት አውርዶ አለት ላይ በመፈጥፈጡ እያዘንኩ ነው ::
አክባሪህ ::
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ወርቅነች Joined: 03 Oct 2010 Posts: 564
Posted: Tue Nov 08, 2011 8:24 am Post subject:
ከንቲባ . እንደጻፈ(ች)ው : ምን አይነት ልክስክስ ሠይጣን ነው በናታቹ
አንተ ውሻ ይሄ ያንተ ቦታ አይደለም የአንበሶች ቤት ነው ስትባል አትሰማም እንዴ ?
ውሻ ድሮስ ከመጮህ ሌላ ምናባቱ ያውቃል አይ ውሾ ወርቅነች !
ቅቅቅቅ ...ግማታሙ ከንቲባ በናትህ ቤት አሁን አንተ መሳደብህ ነው ...ፈላሻዋ ቆንጂት ቂጧን ባወዛወዘች ቁጥር እንደ ውሻ ተከትሎ ቂጥ ቂጥዋን የሚያሸተው አንተ ና ፈዛዛው መሆናችሁን እንዴት ረሳሀው ቄሶችንና ፈላሻዎቹን ከዚህ ቤት ድምጥማጣቸውን እንዳጠፋሁት ሁሉ አንተንም ከዚህ ቤት ዘረማንዘርህን አጠፋለሁ .. አንት ግማታም ወሰላት ከንቲባ ....
ጀሚላ ከቸርችል ጎዳና
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4451 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Mon Nov 21, 2011 11:12 pm Post subject:
ሰኞ ኅዳር 11 ቀን 2004 ዓ .ም .
የቡላኝ -ቢላንኩር (ፈረንሣይ ) ግማሽ ማራቶን ውድድር ::
ትላንት እሑድ ኅዳር 10 ቀን 2004 ዓ .ም . በቡላኝ -ቢላንኩር በተደረገው የግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶችም ሆነ በወንዶች ምድቦች ኢትዮጵያውያን ሯጮች አሸናፊዎች ሆነዋል :: በሴቶች ምድብ አሸናፊ የሆነችው ጎቲቶም ሓፍቱ ተሰማ ስትሆን የወንዶቹ ምድብ አሸናፊ ደግሞ እጅጉ ስንታየሁ መርጋ ነው :: በሴቶቹ ምድብ ኬንያዊቷ ሉሲ ማቻሪያ ጣልቃ ገብታ ሦሥተኛ ከመሆኗ በስተቀር ከ 1ኛ እስከ 5ኛ ያሉት ደረጃዎች በሙሉ የተያዙት በኢትዮጵያውያት አትሌቶች ነው :: ዝርዝር ውጤቶቹ የሚከተለውን ይመስላሉ ::
Wየሴቶች ምድብ
1ኛ ..... ጎቲቶም ሓፍቱ ተሰማ _____ 1 ሰዓት 10 ደቂቃ 57 ሴኮንድ
2ኛ ..... አድህና ፀሐይ ደሣለኝ _____ 1 ሰዓት 11 ደቂቃ 9 ሴኮንድ
3ኛ ..... ሉሲ ማቻሪያ (ኬንያ ) ______ 1 ሰዓት 11 ደቂቃ 16 ሴኮንድ
4ኛ ..... እህተ ገብረየስ __________ 1 ሰዓት 11 ደቂቃ 47 ሴኮንድ
5ኛ ..... አመለወርቅ ፈቃዱ ቦሾ ____ 1 ሰዓት 12 ደቂቃ 35 ሴኮንድ
የወንዶች ምድብ
1ኛ ..... እጅጉ ስንታየሁ መርጋ ____ 1 ሰዓት 1 ደቂቃ 38 ሴኮንድ
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ወርቅነች Joined: 03 Oct 2010 Posts: 564
Posted: Fri Nov 25, 2011 8:17 am Post subject:
ፈዛዛው ... ግማታሙ ከንቲባ አር ጠራጊው የት ጠፋ ...መርካቶ ገብተን ልንጎበኝ የሸንቱ ሸታ ሰውን አላሰኬድ አለ ... ምነው ብለን ብንጠይቅ አሁን ከንቲባው መጥቶ ይመጠዋል አሉን ...ምነው አይሰለቸለውም እንዴ ይህን መምጥጥ ...ሁሌ በአር ና በሸንት ውስጥ ነው የምናየው ....ምነው ደረጃ አትሰጡትም ብለን ብንጠይቅ ..የሴተኛ አዳሪ አጋፋሪ ሆኗል አሉን ..መልካም ደረጃ ነው ያገኘው ትለሀለች ጀሚላ ከቸርችል ጎዳና
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4451 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Sun Nov 27, 2011 11:12 pm Post subject:
እሑድ ኅዳር 18 ቀን 2004 ዓ .ም .
የ 28ኛው የፍሎሬንስ (ጣሊያን ) ማራቶን ውድድር
በዚህ በየዓመቱ በሚደረግ የማራቶን ውድድር በሴቶችም ሆነ በወንዶች ምድቦች ኢትዮጵያውያን አሸናፊዎች ሆነዋል :: በወንዶች ምድብ ብርሃኑ በቀለ በርጋ በ 2 ሰዓት 9 ደቂቃ 52 ሴኮንድ ቀዳሚ ሲሆን የሴቶቹ ምድብ አሸናፊ አይሻ ጂጂ ደግሞ በ 2 ሰዓት 31 ደቂቃ 36 ሴኮንድ ውድድሩን አጠናቃለች :: ዝርዝር ውጤቶቹ የሚከተለውን ይመሥላሉ ::
ምንጭ :- Diego Sampaolo (IAAF), Sunday, 27 November 2011. Bekele and Gigi lead Ethiopian sweep in Florence.
የወንዶች ምድብ
1ኛ ..... ብርሃኑ በቀለ በርጋ ___ 2 ሰዓት 9 ደቂቃ 52 ሴኮንድ
2ኛ ..... ኃይሉ ገላ ሠይፉ ___ 2 ሰዓት 10 ደቂቃ 17 ሴኮንድ
4ኛ ..... ዘምባባ የማኑ ______ 2 ሰዓት 14 ደቂቃ 3 ሴኮንድ
የሴቶች ምድብ
1ኛ ..... አይሻ ጂጂ ____________ 2 ሰዓት 31 ደቂቃ 36 ሴኮንድ
4ኛ ..... ትዕግሥት ማሙዬ ገበየሁ ___ 2 ሰዓት 36 ደቂቃ 49 ሴኮንድ