WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ሲኒማ ራስ ሞት ተፈረደብት

Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ገደል

ኮትኳች

Joined: 02 Jan 2010
Posts: 487

PostPosted: Wed Dec 21, 2011 2:02 pm    Post subject: ሲኒማ ራስ ሞት ተፈረደብት Reply with quote

ያለማፍረስ ሥራ የሌላቸው የወያኔ "መሀንዲሶች " 80 አመት ግድም የቆየውንና በጣልያኖች የተገነባውን ታሪካዊውን ሲኒማ ራስ ለማፍረስ ጉብ ቂጥ እያሉ ነው :: ሲኒማ ቤቱ ጣልያኖች የሰጡት ጣሊያናዊ ስም ነበር ጣልያኖች ከለቀቁ በሁዋላ ተቀይሮ ሲኒማ ራስ ሀይሉ ተባለ በአርበኛው በራስ ሀይሉ ተክለሀይማኖት ስም :: ይህ ሲንማ ቤት በጊዜው ጣልያኖች የሰሩት ጥቁሮች እነጮቹ ሰፈር ፒያሳ አካባቢ እንዳይደርሱ ለማድረግ ነበር :: በአሁኑ ጊዜ ሲኒማ ቤቱ አርጅቶ ከሆነ ጠግኖ በታሪካዊ ሕንጻ ተመድቦ መቀመጥ ሲችል ማፍረስ ለምን አስፈለገ :: ሌላ ሲኒማ ቤት በአካባቢው መስራት ካስፈለገ ስንት ቦታ እያለ አሁን ይህን ታሪካዊ ሕንጻ ማፍረስ ምን የሚሉት ነው ? ወይ ታሪክ የምይገባቸው ወይ የአዲስ አበባን ታሪካዊ አመጣጥ ለማጥፋት ቆርጠው የተነሱ ካልሆነ በስተቀር ሌላ ምንም
ምንጭ :
http://addisfortune.com/City%20Admin%20Plan%20to%20Replace%20Ras%20Theatre.htm
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዲጎኔ

ዋና አለቃ

Joined: 19 Aug 2005
Posts: 4208
Location: united states

PostPosted: Thu Dec 22, 2011 8:36 am    Post subject: Re: ሲኒማ ራስ ሞት ተፈረደብት Reply with quote

ሰላም ለሁላችን ይሁን
ወገን ገደል ወቅታዊ ዘገባህ የሚመሰገን ቢሆንም በጣልያን የተሰራ ቤት አርጅቶ ለአካባቢው ህብረተሰብ ጥቅም የማይሰጥ ከሆነ መፍረሱና ትልቅ ህንጻ በዚያ መገንባቱ የሚወቀስ አይደለም :: ሊወቀስ ሊወገዝ የሚገባው ፈጣሪ የሰራቸው የራስ ቲያትር ባለሙያዎች ከያኒያኑ ከነይግረም ረታ ጀምሮ በሰፈነው ስርአት ብልሹ ፖለቲካና አሰራር ጠንቅ ህይወታቸው መፍረሱ ነው :: ደግሞም ለጣልያን አድረው በአጼው ይቅርታ የተደረገላቸው ራስ ሀይሉ ይህን ያህል መታሰቢያ የሚገባቸው አይደሉም ::
ቲያትር ቤቱ ከያኒያንና ሰረተኞች ለሰጡት አገልግሎት ግን መታሰቢያ ማድረጉ አስፈላጊ ይሆናል ""
ዲጎኔ ሞረቴው ልዩ ጥበቃና ክብካቤ ከሚያሻው ታሪካዊው የሀገር ፍቅር ማህበር ፒያሳ

ገደል እንደጻፈ(ች)ው:
ያለማፍረስ ሥራ የሌላቸው የወያኔ "መሀንዲሶች " 80 አመት ግድም የቆየውንና በጣልያኖች የተገነባውን ታሪካዊውን ሲኒማ ራስ ለማፍረስ ጉብ ቂጥ እያሉ ነው :: ሲኒማ ቤቱ ጣልያኖች የሰጡት ጣሊያናዊ ስም ነበር ጣልያኖች ከለቀቁ በሁዋላ ተቀይሮ ሲኒማ ራስ ሀይሉ ተባለ በአርበኛው በራስ ሀይሉ ተክለሀይማኖት ስም :: ይህ ሲንማ ቤት በጊዜው ጣልያኖች የሰሩት ጥቁሮች እነጮቹ ሰፈር ፒያሳ አካባቢ እንዳይደርሱ ለማድረግ ነበር :: በአሁኑ ጊዜ ሲኒማ ቤቱ አርጅቶ ከሆነ ጠግኖ በታሪካዊ ሕንጻ ተመድቦ መቀመጥ ሲችል ማፍረስ ለምን አስፈለገ :: ሌላ ሲኒማ ቤት በአካባቢው መስራት ካስፈለገ ስንት ቦታ እያለ አሁን ይህን ታሪካዊ ሕንጻ ማፍረስ ምን የሚሉት ነው ? ወይ ታሪክ የምይገባቸው ወይ የአዲስ አበባን ታሪካዊ አመጣጥ ለማጥፋት ቆርጠው የተነሱ ካልሆነ በስተቀር ሌላ ምንም
ምንጭ :
http://addisfortune.com/City%20Admin%20Plan%20to%20Replace%20Ras%20Theatre.htm
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ገደል

ኮትኳች

Joined: 02 Jan 2010
Posts: 487

PostPosted: Thu Dec 22, 2011 2:11 pm    Post subject: Reply with quote

ዲጎኔ .....እንኩዋን አደረሰህ :: ስለራስ ቲያትር ጉዳይ ያለን እይታ አራምባና ቆቦ ሳይሆን አልቀረም :: አዲስ አበባ ከተማ ታሪካዊ ከተማ ነች በብዙ አኩዋያ :: በኢትዮጵያውያን ተመርጣ በኢትዮጵያውያ ከመመስረቱዋ ጀምሮ በጣልያኖች የግፍ እልቂትና ሴግሪጌሽን የተካሄደባት ከተማ ነች :: ይህ ታሪኩዋ ሂደቱዋ ታድያ እንዴት ነው ለሚቀጥለው ትውልድ የሚተላለፈው ?
ሲኒማ ራስ ማርጀቱ ለመፍረሱ ምክንያት አይሆንም :: የታሪክ መዘክሮች እኮ ያርጁ ቅሪቶች ናቸው :: እኔ የሚመስለኝ ለማፍረስ የወሰኑት ወገኖች እይታ እነደአንተ ሳይሆን አልቀረም ብዬ እገምታለሁ :: ታሪክ ለማጥፋት ሆን ብለው ያደረጉት ነው ለማለት መረጃ የለኝም :: ራስ ሀይሉ ባንዳ ነበሩ አልነበሩም ቁምነገር አይደለም :: ቁምነገሩ ሕንጻው ለትውልድ የሚያስተላልፈው ግዙፍ መለክት ስላለው ተጠግኖ በመዘክርነት መያዝ ይገባዋል የሚል አመለካከት ነው ያለኝ ::
ያረጀ ሕንጻ ሁሉ ይፍረስ የሚባል ከሆነ ሮም ከተማ እንዲህ የቱሪስት መናሕርያ አትሆንም ነበር :: ኮሎሲየም ነበር የመጀመርያው ፈራሽ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia