WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ንቃተ ህሊና
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 811

PostPosted: Fri Dec 23, 2011 1:31 am    Post subject: Reply with quote

---

Last edited by እናመሰግንሃለ on Tue Sep 03, 2013 7:07 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ፀዋር

ዋና ኮትኳች

Joined: 16 Feb 2010
Posts: 501

PostPosted: Fri Dec 23, 2011 1:46 am    Post subject: Reply with quote

እናመሰግንሃለ� እንደጻፈ(ች)ው:
የኛ ቸርችማ ኢትዮጵያዊነትን ነው የምታስተምረው ::

WHICH ETHIOPIANET IS IT? በአጼ እከሌ ንጉሰ ነገስት ... ነገደ ይሁዳ መገዛትና ለጥ ብሎ ማደር ሰማያዊ ተግባር እንደሆነ ማስተማራችሁ ነው ኢትዮጵያዊነትን ማስተማር Question
_________________
I have great faith in fools; self-confidence my friends call it.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 811

PostPosted: Fri Dec 23, 2011 3:05 am    Post subject: Reply with quote

----

Last edited by እናመሰግንሃለ on Tue Sep 03, 2013 7:12 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እቴጌይት

ዋና ኮትኳች

Joined: 23 Sep 2007
Posts: 571

PostPosted: Fri Dec 23, 2011 4:53 am    Post subject: Reply with quote

ሠላም :-

ማናቸውም ጽንፈኛ አካሄድ ውስብስብ የሆኑ ጉዳዮችን በአንድ የጠበበ መነጽር እንድናይ ስለሚያደርግ የሚበጅ አይደለም :: ፀዋር እያንጸባረክ ያለኸው ሀሳብ ምክንያትዊ በሆነ ትንታኔ ሀይማኖት በሕዝባችን ንቃተ ሕሊና ላይ ያሳደረውን አሉታዊ ተጽዕኖ መተንተን ሳይሆን በጅምላ የሚፈረጅ ጽንፈኛ አቋም ይመስለኛል :: ኢትዮጵያዊውን ኢትዮጵያዊ የሚያሰኙና ልንጠብቃቸው የሚገባ ከሀይማኖት የተወረሱ በርካታ ጠቃሚ እሴቶች እንዳሉ በግልጽ ማየት እንችላለን :: ከመሪዎቻችን ጉድለት እና ካሉብን አሰቃቂ ችግሮች አንጻር ሕዝባችን ሌላው ቢቀር ሳይበላላ በአንጻራዊ ሰላም አብሮ እንዲኖር ካስቻሉት ዋነኛ ምክንያቶች አንዱ ከሀይማኖቱ የወረሰው ፈሪሀ እግዚአብሄር /አላህ ይመስለኛል !! በተጨማሪ እዚህ ላይ የዶግማ እና የቀኖና ውይይት ሳይሆን የተያዘው ስለ ንቃተ ሕሊና ጉዳይ ስለሆነ እየተነጋገርን ያለነው ... ሀይማኖትን አስታከህ የምታነሳቸው ነጥቦች ሀይማኖት ንቃተ ሕሊና ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ በሚዳሰስ መልኩ ቢሆን የሚበጅ ይመስለኛል :: የተቀረው ዝርዝር የሀይማኖት ውይይት ከርዕሳችን ውጪና ያለቦታው የመጣ ይመስለኛል ::

እናመሰግንሀለ እንዲሁ ለቀድሞው ትውልድ የተዛባ ፍጽምና እየሰጠህ ... ተምረንባቸው ልናሻሽላቸው የሚገባንንም በውስጡ የነበሩትን ጉልህ ጉድለቶችንም ፈጽሞ እየካድክ ....ባንጻሩ ሕዝባችንን ወደ ላቀ ንቃተ ሕሊና ለማሸጋገር ወሳኝ የሆነውን ዘመናዊ ትምህርትን እንደ ጥፋት የሚፈርጅ የፀዋር ተቃራኒ የሆነው ሌላኛው አስገራሚ ጽንፍ ላይ ትገኛለህ :: ስለ 'ማህበራዊ ሳይንስ ' ነው ያወራኹት ብለህ ያከልከው ማለዘቢያም ምንም ትርጉም የሚሰጥ አይደለም :: ከላይ እንደምስሌ የዘረዘርካቸው ሕዝባችን የሚገኝበት ዝቅጠት ምንጭ 'ማህበራዊ ሳይንስ ' ትምህርት መሆኑን የሚያስረዳ አንድ ትጉም የሚሰጥ ነጥብ እንኳን አላስቀመጥክም :: እስቲ የራስህን ምሳሌዎች እያቸውና መልስልኝ :-...
ለአንድ ኢትዮጵያዊ ሴት አረብ ሀገር ሄዶ ከፎቅ ወድቆ መሞት ማህበራዊ ሳይንስ መማሯ በምን አይነት ስሌት ይሆን ምክንያት የሚሆነው ?? ስለ ላንድ ግራብ እና ሌሎችም ጉዳዮች የዘርዘርከው እንዲሁ በምን አይነት አስገራሚ ሎጂክ ይሆን ማህበራዊ ሳይንስ ከመማር ጋር የሚገናኘው ?? ማህበራዊ ሳይንስ መማር ' national consciousness' ያጠፋል ማለት ምን ዓይነት ፌዝ ነው ??

ለመሆኑ የኢትዮጵያ ማህበረሰቦችን ቋንቋዎችን ወዘተ በማህበራዊ ሳይንስ (linguistic, sociology) ካልሆነ በምን ምትሀት ይሆን የምታጠናቸው ? (በስማ በለው ?)... በትዝታ የምታዛባውን የሀገራችንን ታሪክስ ... በማህበራዊ ሳይንስ (history) ካልሆነ በምን ይሆን የምትመረምረው ? (በትውፊት ?)..... የእነ ሉሲን አጽምስ በምን ትምህርት ይሆን (archeology, anthropology) አውጥተህና መርምረህ 'ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ ነች ! ብለህ የምትኮራው ? (በአፈ ታሪካዊ ግምት ?)... ሀገራችን የምትመራበትን ህግጋትንስ በምን ትምህርት ይሆን (law, criminology) የምትቀርጸውና የምትተገብረው ? (በሙሴ ህግ ?)... ወዘተ ....ወዘተ ...???

መልካም ቆይታ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 811

PostPosted: Fri Dec 23, 2011 5:15 am    Post subject: Reply with quote

እቴጌ

አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽና ለዚህ ጥያቄ በምትመልሽልኝ መልስ የኔና ያንቺ ልዩነት ምን ያህል የተራራቀ እንደሆነ እንመለከታለን ::

ለመሆኑ እቴጌ : ሚኒሊክ ወይም ኃይለ ሥላሴ ዘመናዊ ትምህርት በኢትዮጵያ የከፈቱበትን ምክንያት ታውቂያለሽ ? አንድ ኦፊሽያል ምክንያት ብቻ ነበረው :: Do you know what it is at all?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እቴጌይት

ዋና ኮትኳች

Joined: 23 Sep 2007
Posts: 571

PostPosted: Tue Dec 27, 2011 6:05 am    Post subject: Reply with quote

ሠላም ናፖሊዮን

ባነሳኸው ርዕስ ላይ ያለኝን ሀሳቦች ለማቅረብ ያህል ተመልሻለሁኝ :: በበኩሌ ሕዝባችን ለሚገኝበት የተገዢነት አስተሳሰብ (submissive mentality) ወሳኝ የሆኑ ምክንያቶች (factors) በሶስት ተርታ ሊመደቡ የሚችሉ ይመስለኛል :-

1) የሀይማኖት እና ከዛም የሚወለደው የባህል ተጽዕኖ

2) የደርግ ጭፍጨፋ ያስከተለው የስነልቦና ሰለባ እና ወያኔ በሰፊው የቀጠለው ማህበራዊ ውድቀት

3) የትምህርት አለመስፋፋት እና የኢኮኖሚ ዕድል ምክነት ናቸው ::

1)
ብዙውን ጊዜ ትኩረት የምንሰጠው ጉዳይ ሀይማኖት ሕብረተሰቡን የውጪ ወራሪዎችን እንዲዋጋ በማስተባበር የተጫወተውን ሚና ነው :: የውጪ ወራሪ ጠላትነት እና ጉዳት .... ለገዢውም ለተገዢውም ወገን እና .. ለሀይማኖት አመራሩም ጭምር በመሆኑ .. የአላማ አንድነት መፍጠሩ ምክንያታዊ ነው :: ባንጻሩ ግን እንደማንኛውም ሀገር ታሪክ ... የእኛም ሀገር ቀደምት ገዢ ሀይሎች ....... ሀይማኖትን እንደመሰራያ በመጠቀም ..... ሕብረተሰቡ ውስጥ የፍጹሙ ተገዢነት ባህልን በሰፊው አስርፀዋል :: የሀይማኖት ትምህርቶች .... የሰው ልጅ በድህነትና በባርነት ተገዝቶ ቢኖርም ... ከሰማይ ዋጋ እንደሚያገኝ ስለሚያስተምሩት ....ገዢዎችም በእግዚአብሄር የተሰየሙ ናቸው ተብሎ ስለሚነግረው ..... ተገዢነቱን በጸጋ ተቀብሎ ... እራሱን በበታችነት መድቦና አምኖ እንዲኖር ትልቅ ሚና ተጫውተዋል :: ይሄ በአውሮፓም የነበረ ሂደት ሲሆን ልዩነቱ አውሮፓ 'enlightenment' እና 'secularization' ሂደት ግለሰቦች በሀይማኖት የተነሳ ከሚመጣ ተገዥነትን አሜን ብሎ ከመቀበል ስሜት እንዲላቀቁና ስለራሳቸው ልበሙሉነት እንዲሰማቸው ሲያስችል እኛ ግን ከጥንታዊ ግዛትነት ወደ ዘመናዊነት ልናደርግ የሞከርናቸው ሽግግሮች በተለያዩ ውስብስብ ምክንያቶች ተጨንግፈው ቀርተዋል ::

2) በደርግ ዘመን በቀይ ሽብርና ከዛም በኋላ በተደረጉ አሰቃቂ ጭፍጨፋዎች , የኢኮኖሚ ውድቀት እና ተስፋ ቢስነት ... ባንድ ወገን የተወሰነውን ወገን ወደ ብሄርተኛነት ሲገፋው .....በዛ ዘመን እና ከዛም በኋላ የመጣውን በርካታ ወጣት ደግሞ ስነ ልቦና በመስለብ .... ከፖለቲካ ትግል እርም ብሎ ፈጽሞ እንዲርቅ እና በሀገሩ ጉዳይ ላይ የባለቤትና የሀላፊነት ስሜት እንዳይሰማው አድርጎታል :: ስለዚህ ራሱን ከዚህ የጨለመ የፖለቲካም ሆነ የኢኮኖሚ አዙሪት ለማውጣት በተገኘው አጋጣሚ አግባብነት ያለውም ይሁን የሌለው መንገድ ተጠቅሞ እንዲኖር .... አሊያም ባገኘው አጋጣሚ ወደ ምዕራብ ሀገሮች ተሰዶ የግሉን ከቻለም የቤተሰቡን ሕይወት እንዲቀይር .... ያልተሳካለትም ማህበራዊ ዝቅጠት ውስጥ ተዘፍቆ (በጫት በአልኮልን በዝሙት ) ራሱን እያደነዘዘ እንዲኖር አድርጎታል :: ይሄንን የሚያስረግጡ በርካታ ማስረጃዎችን ማየት ይቻላል ::
-ከደርግ ዘመን በፊት ለትምህርትም ይሁን በማናቸውም ምክንያት ወደ አውሮፓም ይሁን አሜሪካ ወጥተው ወደ ሀገራቸው የማይመለሱ ... ወደ ሱዳን እና ኬኒያ በእግር ወይም ወደ አረብ ሀገር የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን በጣም አነስተኛ የነበረ መሆኑ ....የጫት , የአልኮል የሴተኛ አዳሪነት ስርጭት በአንጻራዊ መልኩ አንስተኛ የነበረ መሆኑ ወዘተ ..ይሄንኑ ያመለክቱናል ::

ወያኔ ... የደርግን ጨፍጫፊነት የብሄር ካባ እና የዲሞክራሲን ቋንቋ አልብሶ በሰፊው ሲቀጥልበት ከላይ የጠቀስኳቸው የተገዢነት እና ተስፋ ቆርጦ ለማምለጥ የመሞከር አዝማሚያዎች (trends) በሰፊው ስር እየሰደዱ ቀጥለዋል :: ከላይ እንደማስረጃ የቀረቡት ጉዳዮችም በእጥፍ ድርብ እየጨመሩ ይገኛሉ ::

3) ገለልተኛ የሆነ ዘመናዊ ትምህርት ..... የአስተሳሰብ አድማስን ማስፋት ብቻ ሳይሆን ሰዎች ስለራሳቸው ያላቸውን አመለካከትን ከመገንባት እና ...በዜግነት ያላቸውን መብት ከመረዳት አንጻር ...ያለው ሚና ከፍተኛ ነው :: ትምህርት ዓይነተኛ ሙያን ለማዳበር ብቻ ሳይሆን ..... የሚጠይቅ እና የተባለውን አሜን ብቻ ብሎ የማይቀበል ጭንቅላትን (Inquistive and critical mind) ስለሚፈጥር የተገዢነት ባህልን የሚፈጥሩ ተጽዕኖዎችን ለማስወገድ ወሳኝ ሚና አለው :: (ለምሳሌ 'መሬት ላራሹ የሚለው ጥያቄ የመጣው ካልተማረው ገበሬ ሳይሆን ዩንቨርሲቲ ካለው ተማሪ ነበር ):: እርግጥ ትምህርት ሲባል የትምህርት ስርአቱ ትኩረት እና አሰጣጥ ከላይ የጠቀስኩትን አስተሳሰብ ከመቅረጽ አንጻር ወሳኝነት አለው :: (ይሔ ግን ራሱን የቻለ ሌላ ርዕስ ስለሆነ እዚህ ላይ ተወዋለሁኝ )

የኢኮኖሚ እድሎች (economic opportunities) መምከን ወጣቱ በሀገሩ ተስፋ ቢስ እንዲሆን እና ከላይ በተዘረዘሩት ዝቅጠቶች ውስጥ እንዲኖር ሲያደርጉት .... ተስፋውም የተሻለ የኢኮኖሚ እድሎች ባሉባቸው የምዕራብ ሀገሮች ላይ እንዲመሰረት ያደርጉታል :: ገዢው ወገንም የኢኮኖሚ እድሎችን አገዛዙን ከመደገፍ ወይም ሌላው ቢቀር አገዛዙን ካለመቃወም ጋር ስለሚያቆራኘው የሕብረተሰባችን የኢኮኖሚ ጥገኛነት የተገዢነት ባህልን ከማጠናከር አንጻር ትልቅ ሚና እንዳለው ማየት ይቻላል ::

ለማጠቃለል እነዚህ ከባድ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ እውነታዎች ከድንቁርና መስፋፋት እና 'በምድር ቢሰቃዩ በሰማይ ዋጋ ይገኛል ' ከሚለን የሀይማኖታችን ጭብጥ ጋር ሲደመሩ .... ሕብረተሰባችን ውስጥ ስር የሰደደ የተገዢነት ባህል እና ተዛማጅ ማህበራዊ ዝቅጠቶችን መፍጠራቸው አስገራሚ አይሆንም ::

መልካም ቆይታ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 811

PostPosted: Tue Dec 27, 2011 8:19 am    Post subject: Reply with quote

---

Last edited by እናመሰግንሃለ on Tue Sep 03, 2013 7:18 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እቴጌይት

ዋና ኮትኳች

Joined: 23 Sep 2007
Posts: 571

PostPosted: Tue Dec 27, 2011 4:30 pm    Post subject: Reply with quote

ጥያቄህን የዘለልኩበት ምክንያት ቀድመው የተመለሱ ነገሮችን መደጋገም ትርጉም ይሰጣል ብዬ ስላላሰብኩ ነው :: ሀሳብህን በሀሳብነቱ ባከብረውም በእኔ እይታ የምታመጣቸው ነጥቦች በየጊዜው የሚንሸራተቱ እና ቁንፅል እውነት ይዘው ትልቅና ጽንፈኛ ድምዳሜ ላይ የሚደርሱ ናቸው :: ለምሳሌ የዝግመተ ለውጥ (evolution) ትምህርት የማህበራዊ ሳይንስ አካል ሳይሆን መሠረታዊ የሆነ የባዮሎጂና የሕክምና ትምህርት አካል መሆኑን ስተኸዋል :: ስለቴክኖሎጂ ስታውራ ዛሬ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕጻናትን ከበርካታ በሽታዎች የሚታደጉ መድሀኒቶች (immunization vaccines) የተፈለሰፉት እና እየተፈለሰፉ ያሉት በዝግመተ ለውጥ ትምህርት ተመሥርቶ እንደሆነም ስተኸዋል (based on the evolution of the particular virus we are fighting). በዘረኛነት ከተለከፈ ሳይንቲስት ነኝ ባይ ካልሆነ በስተቀር ጥቁሮች በዝግመተ ለውጥ የተነሳ ወደ ኋላ ቀርተዋል የሚል የማህበራዊ ሳይንስ ድምዳሜም እንደሌለ ማወቅ ብዙም አያስቸግርም :: ስለአፍሪካም ሆነ ሌላው ሶስተኛ ዓለም ኋላ መቅረት በሳይንስ የተመሰረተ ትንታኔዎችን ለማግኘት በርካታ አፍሪካውያንም ሆነ አፍሪካዊ ያልሆኑ የማህበራዊ ሳይንስ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ምሁራን የጻፏቸውን ብታነብ ይልቅስ ብዙ ትርጉም ያላቸው ግንዛቤዎችን ያስጨብጥሀል ::

እንደሚምስለኝ መለየት የተሳነህ ከላይ በተደጋጋሚ እንደገለጽኩት የአንድን ትምህርት ስርዓቱ ትኩረት እና አሰጣጥ አግባብነትን አስመልክቶ የሚደረግ ተግባራዊ ሂስና እና ሲጀመር እራሱ ትምህርት የሚባለ ነገር ላይ (ማህበራዊ ሳይንስም ጭምር ) ጥያቄ ማንሳት መካከል ያለው የሰማይና የምድር ልዩነት ነው :: የማህበራዊ ሳይንስትን ምንነት እና ቲዎሪዎችም እንዴት እንደሚቀረጹም በቅጡ የተገነዝብከው አልመሰለኝም :: የሆኖ ሆኖ ግን በዚህ ጉዳይ ላይ ያለን የአስተሳሰብ ልዩነት ትልቅ ስለሆነ በዚሁ ብንዘጋው ጥሩ ይሆናል ::

መልካም ቆይታ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ፀዋር

ዋና ኮትኳች

Joined: 16 Feb 2010
Posts: 501

PostPosted: Tue Dec 27, 2011 6:12 pm    Post subject: Reply with quote

WAIT A MINUTE?! WHY YOU CONDEMNED ME AS AN EXTRIMIST? I CAN'T SEE ANY DIFFERENCE BETWEEN MY POINT AND YOURS EXCEPT THAT YOU PARAPHRASE MY CRITICS AND ADD UP SOME OTHER FACTORS. CAN YOU TELL ME PLS?

እቴጌይት እንደጻፈ(ች)ው:
ሠላም ናፖሊዮን

ባነሳኸው ርዕስ ላይ ያለኝን ሀሳቦች ለማቅረብ ያህል ተመልሻለሁኝ :: በበኩሌ ሕዝባችን ለሚገኝበት የተገዢነት አስተሳሰብ (submissive mentality) ወሳኝ የሆኑ ምክንያቶች (factors) በሶስት ተርታ ሊመደቡ የሚችሉ ይመስለኛል :-

1) የሀይማኖት እና ከዛም የሚወለደው የባህል ተጽዕኖ

2) የደርግ ጭፍጨፋ ያስከተለው የስነልቦና ሰለባ እና ወያኔ በሰፊው የቀጠለው ማህበራዊ ውድቀት

3) የትምህርት አለመስፋፋት እና የኢኮኖሚ ዕድል ምክነት ናቸው ::

1)
ብዙውን ጊዜ ትኩረት የምንሰጠው ጉዳይ ሀይማኖት ሕብረተሰቡን የውጪ ወራሪዎችን እንዲዋጋ በማስተባበር የተጫወተውን ሚና ነው :: የውጪ ወራሪ ጠላትነት እና ጉዳት .... ለገዢውም ለተገዢውም ወገን እና .. ለሀይማኖት አመራሩም ጭምር በመሆኑ .. የአላማ አንድነት መፍጠሩ ምክንያታዊ ነው :: ባንጻሩ ግን እንደማንኛውም ሀገር ታሪክ ... የእኛም ሀገር ቀደምት ገዢ ሀይሎች ....... ሀይማኖትን እንደመሰራያ በመጠቀም ..... ሕብረተሰቡ ውስጥ የፍጹሙ ተገዢነት ባህልን በሰፊው አስርፀዋል :: የሀይማኖት ትምህርቶች .... የሰው ልጅ በድህነትና በባርነት ተገዝቶ ቢኖርም ... ከሰማይ ዋጋ እንደሚያገኝ ስለሚያስተምሩት ....ገዢዎችም በእግዚአብሄር የተሰየሙ ናቸው ተብሎ ስለሚነግረው ..... ተገዢነቱን በጸጋ ተቀብሎ ... እራሱን በበታችነት መድቦና አምኖ እንዲኖር ትልቅ ሚና ተጫውተዋል :: ይሄ በአውሮፓም የነበረ ሂደት ሲሆን ልዩነቱ አውሮፓ 'enlightenment' እና 'secularization' ሂደት ግለሰቦች በሀይማኖት የተነሳ ከሚመጣ ተገዥነትን አሜን ብሎ ከመቀበል ስሜት እንዲላቀቁና ስለራሳቸው ልበሙሉነት እንዲሰማቸው ሲያስችል እኛ ግን ከጥንታዊ ግዛትነት ወደ ዘመናዊነት ልናደርግ የሞከርናቸው ሽግግሮች በተለያዩ ውስብስብ ምክንያቶች ተጨንግፈው ቀርተዋል ::

2) በደርግ ዘመን በቀይ ሽብርና ከዛም በኋላ በተደረጉ አሰቃቂ ጭፍጨፋዎች , የኢኮኖሚ ውድቀት እና ተስፋ ቢስነት ... ባንድ ወገን የተወሰነውን ወገን ወደ ብሄርተኛነት ሲገፋው .....በዛ ዘመን እና ከዛም በኋላ የመጣውን በርካታ ወጣት ደግሞ ስነ ልቦና በመስለብ .... ከፖለቲካ ትግል እርም ብሎ ፈጽሞ እንዲርቅ እና በሀገሩ ጉዳይ ላይ የባለቤትና የሀላፊነት ስሜት እንዳይሰማው አድርጎታል :: ስለዚህ ራሱን ከዚህ የጨለመ የፖለቲካም ሆነ የኢኮኖሚ አዙሪት ለማውጣት በተገኘው አጋጣሚ አግባብነት ያለውም ይሁን የሌለው መንገድ ተጠቅሞ እንዲኖር .... አሊያም ባገኘው አጋጣሚ ወደ ምዕራብ ሀገሮች ተሰዶ የግሉን ከቻለም የቤተሰቡን ሕይወት እንዲቀይር .... ያልተሳካለትም ማህበራዊ ዝቅጠት ውስጥ ተዘፍቆ (በጫት በአልኮልን በዝሙት ) ራሱን እያደነዘዘ እንዲኖር አድርጎታል :: ይሄንን የሚያስረግጡ በርካታ ማስረጃዎችን ማየት ይቻላል ::
-ከደርግ ዘመን በፊት ለትምህርትም ይሁን በማናቸውም ምክንያት ወደ አውሮፓም ይሁን አሜሪካ ወጥተው ወደ ሀገራቸው የማይመለሱ ... ወደ ሱዳን እና ኬኒያ በእግር ወይም ወደ አረብ ሀገር የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን በጣም አነስተኛ የነበረ መሆኑ ....የጫት , የአልኮል የሴተኛ አዳሪነት ስርጭት በአንጻራዊ መልኩ አንስተኛ የነበረ መሆኑ ወዘተ ..ይሄንኑ ያመለክቱናል ::

ወያኔ ... የደርግን ጨፍጫፊነት የብሄር ካባ እና የዲሞክራሲን ቋንቋ አልብሶ በሰፊው ሲቀጥልበት ከላይ የጠቀስኳቸው የተገዢነት እና ተስፋ ቆርጦ ለማምለጥ የመሞከር አዝማሚያዎች (trends) በሰፊው ስር እየሰደዱ ቀጥለዋል :: ከላይ እንደማስረጃ የቀረቡት ጉዳዮችም በእጥፍ ድርብ እየጨመሩ ይገኛሉ ::

3) ገለልተኛ የሆነ ዘመናዊ ትምህርት ..... የአስተሳሰብ አድማስን ማስፋት ብቻ ሳይሆን ሰዎች ስለራሳቸው ያላቸውን አመለካከትን ከመገንባት እና ...በዜግነት ያላቸውን መብት ከመረዳት አንጻር ...ያለው ሚና ከፍተኛ ነው :: ትምህርት ዓይነተኛ ሙያን ለማዳበር ብቻ ሳይሆን ..... የሚጠይቅ እና የተባለውን አሜን ብቻ ብሎ የማይቀበል ጭንቅላትን (Inquistive and critical mind) ስለሚፈጥር የተገዢነት ባህልን የሚፈጥሩ ተጽዕኖዎችን ለማስወገድ ወሳኝ ሚና አለው :: (ለምሳሌ 'መሬት ላራሹ የሚለው ጥያቄ የመጣው ካልተማረው ገበሬ ሳይሆን ዩንቨርሲቲ ካለው ተማሪ ነበር ):: እርግጥ ትምህርት ሲባል የትምህርት ስርአቱ ትኩረት እና አሰጣጥ ከላይ የጠቀስኩትን አስተሳሰብ ከመቅረጽ አንጻር ወሳኝነት አለው :: (ይሔ ግን ራሱን የቻለ ሌላ ርዕስ ስለሆነ እዚህ ላይ ተወዋለሁኝ )

የኢኮኖሚ እድሎች (economic opportunities) መምከን ወጣቱ በሀገሩ ተስፋ ቢስ እንዲሆን እና ከላይ በተዘረዘሩት ዝቅጠቶች ውስጥ እንዲኖር ሲያደርጉት .... ተስፋውም የተሻለ የኢኮኖሚ እድሎች ባሉባቸው የምዕራብ ሀገሮች ላይ እንዲመሰረት ያደርጉታል :: ገዢው ወገንም የኢኮኖሚ እድሎችን አገዛዙን ከመደገፍ ወይም ሌላው ቢቀር አገዛዙን ካለመቃወም ጋር ስለሚያቆራኘው የሕብረተሰባችን የኢኮኖሚ ጥገኛነት የተገዢነት ባህልን ከማጠናከር አንጻር ትልቅ ሚና እንዳለው ማየት ይቻላል ::

ለማጠቃለል እነዚህ ከባድ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ እውነታዎች ከድንቁርና መስፋፋት እና 'በምድር ቢሰቃዩ በሰማይ ዋጋ ይገኛል ' ከሚለን የሀይማኖታችን ጭብጥ ጋር ሲደመሩ .... ሕብረተሰባችን ውስጥ ስር የሰደደ የተገዢነት ባህል እና ተዛማጅ ማህበራዊ ዝቅጠቶችን መፍጠራቸው አስገራሚ አይሆንም ::

መልካም ቆይታ

_________________
I have great faith in fools; self-confidence my friends call it.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 811

PostPosted: Tue Dec 27, 2011 7:44 pm    Post subject: Reply with quote

---

Last edited by እናመሰግንሃለ on Tue Sep 03, 2013 7:20 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እቴጌይት

ዋና ኮትኳች

Joined: 23 Sep 2007
Posts: 571

PostPosted: Wed Dec 28, 2011 12:05 am    Post subject: Reply with quote

ሠላም እናመሰግንሀለ

ከላይ እንደገለጽኩልህ በዚህ ጉዳይ ላይ ያለን ግንዛቤ የተራራ እና የገደል ያህል የተራራቀ ስለሆነ ልሞግትህ አልሻም :: የተመለስኩበት ዋና ዓላማ ሌላው ቢቀር ስለ ዝግመተ ለውጥ (evolution) ትምህርት የጻፍከው ጉልህ ስህተት ...... ባለማወቅ ሌሎችንም ሊያስት ስለሚችል ስለ እዛ አንድ ሁለት ለማለት ነው :-

1) የዝግመተ ለውጥ ትምህርት በባዮሎጂ ስር የሚካተት ሲሆን የትምህርቱ መሰረት የሆኑት ነጥቦች natural selection, mutation, genetic drift እና gene flow ናቸው :: ስለዚህ ትምህርት በጣም አነስተኛ የሆነ ግንዛቤ ያለው ሰው እንኳን በባዮሎጂ ስር እንደሚካተት ለመረዳት ይችላል :: በነገራችን ላይ የትምህርቱ መስራች ዳርዊን ከኤደንብር ዩኒቨርሲቲ በሕክምና የተመረቀ Naturalist ነበር ::

2) evolution ትምህርት መከላከያ ክትባቶችን ጨመሮ በርካታ አፕሊኬሽንስ እንዳሉት ለመረዳት እንዲሁ ትንሽም ቢሆን ስለትምህርቱ ግንዛቤ ያለው ሰው አያዳግተውም :: ጥቂት ምሳሌዎችን ብንወስድ :-

- ከፖሊዮ ቫይረስ የሚመጣውን የፖሊዮ በሽታን ብናይ የበሽታው ክትባት የተሰራው የቫይረሱ የዝግመተ ለውጥ ሂደትን በመጠቀም ነው :: አልበርት ሳቢን የሚባል የሕክምና ባለሙያ ይሄን አደገኛ ቫይረስ ከሰው ሰውነት ውጪ በማሳደግ .... ቫይረሱ ከለመደው የሰው ሰውነት ውጪ አዳፕት ለማድረግ ዝግመተ ለውጥ እንዲያካሂድ በማድረግ .... በሽታ የማምጣት አቅሙን እንዲያጣ አደረገው (In evolutionary biology this process is called attenuation):: ይሄ የተዳከመ ቫይረስን ሰውን በምንወጋበት ጊዜ ሰውነታችን ጸረ ቫይረሱ አቅም ይገነባል (we become immuned):: በርካታ ክትባቶች በተመሳሳይ evolutionary biology በመጠቀም ነው የሚሰሩት ::

በዘመናችን በክፍተኛ ሁኔታ እያደገ ያለው እና ተስፋ የተጣለበት ባዮቴክኖሎጂ እና የመድሀኒቶች አሰራር በከፍተኛ ደረጃ በቴስት ቱብ ውስጥ ዝግመተለውጥን በመፍጠር ወይም በማገድ ላይ የተመሰረተ ሂደትን ይጠቀማል :: የአንድ መድሀኒትን ለመፍጠር ብቻ ሳይሆን የሚሰራበትን እድሜ ለማራዘምም (through preventing the evolution of resistance etc) የዝግመተ ለውጥ ሳይንስ ወሳኝ ነው ::
-በግብርና ላይ እንዲሁ የተፈጠሩ በርካታ እድገቶች በዝግመተ ለውጥ ትምህርት ላይ የተመሰረቱ ናቸው (ለምሳሌ የእንስሳት ድቀላ እና የሰብል መረጣ ዘዴዎች ወዘተ ).

ስለዚህ ነው የምንቃወመውን ነገር መጀመሪያ በቅጡ ብናውቅ በቁንጽል ሀሳቦች ላይ ተነስተን ጽንፈኛ ድምዳሜ እንዳንደርስ እና ሀሳባችንን ምክንያታዊ ለማድረግ ያግዘናል ብዬ የማስበው ::

መልካም ቆይታ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እቴጌይት

ዋና ኮትኳች

Joined: 23 Sep 2007
Posts: 571

PostPosted: Wed Dec 28, 2011 12:23 am    Post subject: Reply with quote

ፀዋር እንደጻፈ(ች)ው:
WAIT A MINUTE?! WHY YOU CONDEMNED ME AS AN EXTRIMIST? I CAN'T SEE ANY DIFFERENCE BETWEEN MY POINT AND YOURS EXCEPT THAT YOU PARAPHRASE MY CRITICS AND ADD UP SOME OTHER FACTORS. CAN YOU TELL ME PLS?

ሠላም ፀዋር :-
የፈረንጅ አፍ ስለምትመርጥ እስቲ በእርሱ ልመልስልህ Very Happy

The impression I got from your postings were that you were catagorically condemning Ethiopian orthodoxy and ridiculing its important figures. I cant see how that can be considered the same as my point which simply attempted to identify inhibiting influences inherited from our religious teachings that may have contributed to our culture of submissiveness.

Stay well
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ናፖሊዮን ዳኘ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 18 Apr 2008
Posts: 1878

PostPosted: Wed Dec 28, 2011 12:37 am    Post subject: Reply with quote

ዋናው ጉዳይ ተረሳ ! እስቲ ስለ ጫት እናውራ

ከዚህ በታች የምጽፈው ነገር ማንምም ለመንካት አይደለም ፕርሰናል አድርጋችሁ እንዳትወስዱት !
______________________________________________

ያለ ጫት አዮን የማይገልጥ አንድ ገጽ የማያነብ ሜታቦሊዝሙ በደንብ የማሰራ ሰው ቁጥሩ እምብዛም ነበር ያኔ ሳውቅ :: አሁን ደሞ የምንሰማው ከከፍተኛ ትምህርት ተመርቆ የወጣው አብዛኛው ወጣት እንደዛ እንደሆነ ነው የሚነገረው :: እንግዲህ ህወሀት በዘረጋው ምልመላ መሰረት አብዛኛው ሳይወድ በግዱ የህወሀትን ቢሮክራሲ ይቀላቀላል :: የቢሮክራሲው ሞተር ጫት ሆነ ማለት ነው ::

የሚቀጥለው ነጥብ የመንግስት ሰራተኞች ገቢያቸው የሚያወላዳ አይደለም :: ያውም አለ በሚባለው የኑሮ ውድነት ! ጫት ደሞ ርካሽ አይደለም ! በአንድ ቀን የሚቃመው እስከ ሰማኒያ ብር ይደርሳል ነው የሚባለው ! በሌላ በኩል በየጊዜው ጫት ይቃማል ?! ገቢውን እና ወጪውን ሂሳቡን ስንመታው ልክ አይመጣም :: ሰው ደሞ በኔጌቲቭ አይቅምም ! ወይ እንደመብራት እንደፈረቃ ሰው ተራ በተራ እየተጠራራ ይቅማል :: አለበለዚያ ደሞ ይሄን አጸያፊ ልማድ ለማድረስ ሲባል ---የህዝብ ንብረት ስርቆት ይገባል :: ሙስና ይጀመራል :: እኔ ደሞ የሀገር ፍቅር መጀመሪያ ነው የምለው (ያገር ፍቅርን በዘመኑ ባለው ትውልድ ድካም እና ጥንካሬ መለካት ስላለብን ) ...አዎ የመጀመሪያው የሀገር ፍቅር ...እኔ ጫት ለመቃም እና ማታ የቢራ ጠርሙስ ለመጨበጥ ብየ ከዚህ ከሚራብ ህዝብ ላይ ሰርቄ ጉቦ ወስጀ አልቅምም ብሎ የሚያስብ ሰው እሱ ያገር ፍቅር አለው ብየ አስባለሁ ::

ከዚህም ሻል ያለ ንቃተ ህሊና እና የሀገር ፍቅር ያለው ደሞ ለህጻናቱም ሆነ ወጣት ኢትዮጵያን መጥፎ አርአያ መሆን እንደሌለበት አምኖ ተደብቆ የሚቅምም ሰው ካለ ( መተው እንኳ ባይችል ) ከሀገር ግንባታ ለይቸ አላየውም Idea

እርድና መስሏቸው እንኳን እኛ እና ""ሀገሪቱም ጫት በሚቅሙ ሰዎች ነው የምትመራው "" በሚል ደሞ ለጫት ኤክስኪዮዝ መፍጠር ብቻ ሳይሆን መቃምን የሚያበረታቱ ድንዝዞች አሉ ::

ለነገሩ ሰው ጫት ባይቅም ማታ ባልኮኒ ላይ ጉብ ብሎ መለኪያ ባይጨብጥ ... ምንም ማለት አይደለም ! ለእንደዚህ አይነት ነገር ብሎ ጉቦ እና ስርቆት ቅሌት ውስጥ ሲገባ ግን ያኔ ባርነትን ጀመረው ! ከዚያ በኍላ ደሞ ስራ ለሰጠው ስርዐት ባሪያ ይሆናል :: ስርአቱ ሱሱም ነውና ! በነገራችን ላይ ባስተዋልኩት እና በታዘብኩት መጠን በውጭ ሀገር ያሉ በተለይ በዮኒቨርስቲ አካባቢ የሚፈጠሩ ""ኮኔክሽኖች "" እና የፓርቲ ካውካስም አካባቢ ሲጠነሰስ በመላ በዘዴ እና በኮኬይንም ጭምር ነው :: በእንደዛ አይነት ሰርክል ውስጥ ዊድ እና ኮኬይንም ይጨሳል - ይጠጣል ...ከዛ በዛው በኮኔክሽን አማካይነት ደህና ስራ ማግኘት ይቻላ ...ጭሰቱም በዚያው ይቀጥላል ...ያው እንደዛ ላሉት ተላላዎች የውጭ ነገር ሁሉ ጭስ ነው ....ከዚያ በኍላ አንድ ዘመን ተኝተን ...ምናምን የሚባል ቅዠት ይመጣል :: ውጭ ሀግር ያሉት የራሳቸው ሀሳብ ነው :: የሚያሳስበው የሀገራችን ጉዳይ ነው ::

አንድ ጊዜ ፕሮፌሰር መርዕድ ወልደ አረጋይ አዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ ያሉትን ላካፍል እና ለዛሬ ይብቃኝ :: ለነገሩ ከዚህ በፊት እንደስፃፍኩት አስታውሳለውሁ :: በጣም ስለምወደው ለማስታወስ ነው :: አንዴ በፎቶ ኮፒ አባዝተው ኬኔዲ ያስቀመጡት ኮርስ ሪዲንግ የተወሰነው ኮፒ የተወሰነው ገጹ ተገንጥሎ ተወስዶ ነበረ :: በጣም ተናደው ፊታቸው እየተንቀጠቀጠ ክላስ ገቡ ::

""ይሄ ዮኒቨርሲቲ ደሀ እንደሆነ ታውቃላችሁ :: ደሀ የሆነው ደሞ ሀገሪቱም ደሀ ስለሆነች ነው :: መጽሀፍ ፎቶ ኮፒ ተደርጎ የተቀመጠበት ምክንያት ባለችን ሪሶርስ ተሳስባችሁ እንድትጠቀሙ ነው :: እንደውነቱ ከሆነ ሀገር ትቀይራላችሁ ተብሎ የምትታሰቡ ናችሁ :: እናንተ ግን ዛሬ ላይብራሪ ውስጥ ተባዝቶ የተቀመጠ ንባብ ከሰረቃችሁ ነገ ደሞ ትምህርት ጨርሳችሁ የመንግስት ቦታ ሲሰጣችሁ ሌላ ነገር ትሰርቃላችሁ :: እነዚህም (ወደ አራት ኪሎ አቅጣጫ በእጃቸው እያሳዮ ) [ወያኔዎቹን ነው ] እንደናተው ተማሪ ነበሩ !""

ናፖሊዮን ዳኘ ::
_________________
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ፀዋር

ዋና ኮትኳች

Joined: 16 Feb 2010
Posts: 501

PostPosted: Wed Dec 28, 2011 12:57 am    Post subject: Reply with quote

ሠላም

አንቺም አማርኛ ከፈለግሽ ይሁን :: ኪይቦርዱን ስላለመድኩት ጊዜ ስለሚፈጅብኝ እንጂ ሌላ ምንም ምክንያት የለኝም ::

እኔ እስከተረዳሁሽ ድረስ systematically ሀሳብሽ ተቀባይነት እንዲያገኝ በእኔ "ክፋት " መታከክ ፈልገሽ እንጂ አንቺ ያልሽው እኔ ካልኩት የተለዬ ሆኖ አይደለም :: እኔ በኢንግሊሽ ያወራሁትን አንቺ በአማርኛ እኔ በአማርኛ ያወራሁትን አንቺ በኢንግሊሽ ማድረግሽ ብቻ ነው ያየሁት ልዩነት :: እኔ በፈሪሀ እግዚአብሄር ስም : በመገዘት ልማዶች ተንበርካኪ አደረጋችሁን ስል አንቺ Submissive ሆንን አልሽ :: For most part of it your church is responsible ስል ቁጥር አንድ ስትይ ያስቀመጥሽውን ቤተ ክርስቲያናቸውን ተጠያቂ ማድረግ ነው :: I CAN'T SEE ANY DIFFERENCE BETWEEN THESE POINTS. ANY WAY, THIS IS NOT A BIG ISSUE RIGHT NOW. AS YOU MIGHT BE AWARE OF, THIS WEEK I'M ON A MISSION FOCUSING AT ONE POINT IN A TIME. IT IS MORE LIKELY THAT THE NEXT TARGET WILL BE YOU Wink , I MEAN PEOPLE LIKE YOU WHO ARE OBSESSED WITH WESTERN IDEOLOGY. AND I BELIEVE, DESPITE THE CHALLENGES WE FACED TODAY, THE FUTURE WON'T BE LIKE THE PAST. AT LEAST WE WON'T LET IT BE. YOU KNOW WHAT I MEAN BY THAT, RIGHT?

እቴጌይት እንደጻፈ(ች)ው:
ፀዋር እንደጻፈ(ች)ው:
WAIT A MINUTE?! WHY YOU CONDEMNED ME AS AN EXTRIMIST? I CAN'T SEE ANY DIFFERENCE BETWEEN MY POINT AND YOURS EXCEPT THAT YOU PARAPHRASE MY CRITICS AND ADD UP SOME OTHER FACTORS. CAN YOU TELL ME PLS?

ሠላም ፀዋር :-
የፈረንጅ አፍ ስለምትመርጥ እስቲ በእርሱ ልመልስልህ Very Happy

The impression I got from your postings were that you were catagorically condemning Ethiopian orthodoxy and ridiculing its important figures. I cant see how that can be considered the same as my point which simply attempted to identify inhibiting influences inherited from our religious teachings that may have contributed to our culture of submissiveness.

Stay well

_________________
I have great faith in fools; self-confidence my friends call it.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 811

PostPosted: Wed Dec 28, 2011 1:04 am    Post subject: Reply with quote

----

Last edited by እናመሰግንሃለ on Tue Sep 03, 2013 7:23 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8  Next
Page 4 of 8

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia