WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ንቃተ ህሊና
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 805

PostPosted: Fri Dec 23, 2011 1:31 am    Post subject: Reply with quote

ፀዋር እንደጻፈ(ች)ው:
INNOCENT PEOPLE

ቡሽን መሰልከኝ ! ኢራቅ ገብቶ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢራቃውያንን የገደለው የሳዳም መንግሥት ብዙ Innocent people በዲሞክራሲ እጦት ከሚያንገላታቸው አንባገነባዊ መንግሥት ሊያድናቸው ነበር ::

Quote:
BELIEVE ME, I HAVE MY DOUBLE-EDGED SWORD TOO

አንዱ የአገርህን ክርስቲያኖች የምታርድበት ነው :: በዛኛው በኩል ያለው ስለት ራስህን በራስህ አርደህ አጥፍቶ ጥፋ የምትፈጽምበት ነው ? Laughing

Quote:
አናመስግንሃለ ? YOU ARE FUNNY Laughing የሞተ ነጭ ብቻ አይደለም የምናመልከው : በተቅማጥ የሞተ ኢትዮጵያዊም እናመልካለን ማለትህ ነው አይደለ

በተቅማጥ የሞተ ኢትዮጵያዊማ እንዳውም ይሻላል :: መስቀል ላይ ራቁቱን ደም ለብሶ አጥንቱ ገጥጦ የተሰቀለውን ክርስቶስን እያመለክን አይደል ?

Quote:
አድርባይ ተንበርካኪ ህዝብ ያደረጉት :

ያንተ ቢጤ የአገራቸውን ሃይማኖት የሚጠሉ እምነት የለሽ ወፈፌዎች ናቸው ::

Quote:
TAKE ONE MORE POINT PLS, በአገራችን በራሳችን እንዳንኮራ ያደረገንም ያንተ ቸርች ነው ::

አንተ ከቸርቹ ውጪ ነህ :: ታድያ ኩራትህ ለምን ጠፋብህ ?

Quote:
እንደ ኢትዮጵያዊ ከመኖር ይልቅ እንደ አይሁዳዊ መሆንን : እንደ እስራኤላዊ መሆንን ለሁለት ምእተአመታት ገደማ ሲያስተምር የነበረው ቸርችህ ነው ::

አንተ አይሁዳዊነት ከኢትዮጵያዊነት የሚበልጥ ይመስልህ ነበር እንዴ ? እንዴት ተሸወድክ ?! እኛኮ "ፈላሻ " ብለን ንቀናቸው ነበር የተቀመጥነው - ለሁለት ብቻ ሳይሆን ለብዙ ምዕተ አመታት ?! ከእስራኤል የመጡ አይሁዶችም እስራኤላዊነታቸውን እስራኤል አስቀምጠው ኢትዮጵያዊነታቸውን ተቀብለው ነው የመጡት ::

ማን ለማን ተንበረከከ ??

አሁን እስራኤል ሄደው ስለተንበረከኩት ከሀዲ ፈላሻዎችስ ምን ትላለህ ? እነርሱም ልክ እንዳንተ ከቸርች ውጪ ናቸው :: የኛ ቸርችማ ኢትዮጵያዊነትን ነው የምታስተምረው ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ፀዋር

ኮትኳች

Joined: 16 Feb 2010
Posts: 481

PostPosted: Fri Dec 23, 2011 1:46 am    Post subject: Reply with quote

እናመሰግንሃለ� እንደጻፈ(ች)ው:
የኛ ቸርችማ ኢትዮጵያዊነትን ነው የምታስተምረው ::

WHICH ETHIOPIANET IS IT? በአጼ እከሌ ንጉሰ ነገስት ... ነገደ ይሁዳ መገዛትና ለጥ ብሎ ማደር ሰማያዊ ተግባር እንደሆነ ማስተማራችሁ ነው ኢትዮጵያዊነትን ማስተማር Question
_________________
I have great faith in fools; self-confidence my friends call it.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 805

PostPosted: Fri Dec 23, 2011 3:05 am    Post subject: Reply with quote

ፀዋር እንደጻፈ(ች)ው:
እናመሰግንሃለ� እንደጻፈ(ች)ው:
የኛ ቸርችማ ኢትዮጵያዊነትን ነው የምታስተምረው ::

WHICH ETHIOPIANET IS IT? በአጼ እከሌ ንጉሰ ነገስት ... ነገደ ይሁዳ መገዛትና ለጥ ብሎ ማደር ሰማያዊ ተግባር እንደሆነ ማስተማራችሁ ነው ኢትዮጵያዊነትን ማስተማር Question

በሚገባ !

አንተ ለገብጋባ ነጫጭባ ኒዮሊበራል ጄኖሳይዳል ፔዶፋይል ግብረሶዶማውያን ሳታኒስት ባንከርስ እየተገዛህ አይደል ? የቱ ይሻላል ? ለአገርህ ሰው መገዛት ወይስ በሰይጣን ስም ለነገሠብህ ባዕድ ?

ኢትዮጵያን አማራ አይገዛትም : ኦሮሞው ይናደዳል :... ኦሮሞው አይገዛትም : ትግሬው ይናደዳል :... ትግሬው አይገዛትም : ጉራጌው ይናደዳል : .....ጉራጌው አይገዛትም : አደሬው ይናደዳል : ......አደሬው አይገዛትም : ሶማሌው ይናደዳል :....... ሶማሌው አይገዛትም ኤርትራዊው ይናደዳል ...... ይህ ሁሉ በአንድ ንጉሥ ሥር መገዛት "መረገጥ " መስሎ ተሰማው :: "ታድያ ገዢ ከፈለግህ እኔ ለምን አልረግጥህም " ብላ እነሆ አሜሪካ ረግጣ እየገዛችው ነው !!

ፀዋር ሆይ : ትውልዱ አንተን ይመስላል :: የፈለገውም ያገኘውም አንተ የምትፈልገውንና የምትሟገትለትን ነው - በባዕድ መገዛት !!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እቴጌይት

ዋና ኮትኳች

Joined: 23 Sep 2007
Posts: 547

PostPosted: Fri Dec 23, 2011 4:53 am    Post subject: Reply with quote

ሠላም :-

ማናቸውም ጽንፈኛ አካሄድ ውስብስብ የሆኑ ጉዳዮችን በአንድ የጠበበ መነጽር እንድናይ ስለሚያደርግ የሚበጅ አይደለም :: ፀዋር እያንጸባረክ ያለኸው ሀሳብ ምክንያትዊ በሆነ ትንታኔ ሀይማኖት በሕዝባችን ንቃተ ሕሊና ላይ ያሳደረውን አሉታዊ ተጽዕኖ መተንተን ሳይሆን በጅምላ የሚፈረጅ ጽንፈኛ አቋም ይመስለኛል :: ኢትዮጵያዊውን ኢትዮጵያዊ የሚያሰኙና ልንጠብቃቸው የሚገባ ከሀይማኖት የተወረሱ በርካታ ጠቃሚ እሴቶች እንዳሉ በግልጽ ማየት እንችላለን :: ከመሪዎቻችን ጉድለት እና ካሉብን አሰቃቂ ችግሮች አንጻር ሕዝባችን ሌላው ቢቀር ሳይበላላ በአንጻራዊ ሰላም አብሮ እንዲኖር ካስቻሉት ዋነኛ ምክንያቶች አንዱ ከሀይማኖቱ የወረሰው ፈሪሀ እግዚአብሄር /አላህ ይመስለኛል !! በተጨማሪ እዚህ ላይ የዶግማ እና የቀኖና ውይይት ሳይሆን የተያዘው ስለ ንቃተ ሕሊና ጉዳይ ስለሆነ እየተነጋገርን ያለነው ... ሀይማኖትን አስታከህ የምታነሳቸው ነጥቦች ሀይማኖት ንቃተ ሕሊና ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ በሚዳሰስ መልኩ ቢሆን የሚበጅ ይመስለኛል :: የተቀረው ዝርዝር የሀይማኖት ውይይት ከርዕሳችን ውጪና ያለቦታው የመጣ ይመስለኛል ::

እናመሰግንሀለ እንዲሁ ለቀድሞው ትውልድ የተዛባ ፍጽምና እየሰጠህ ... ተምረንባቸው ልናሻሽላቸው የሚገባንንም በውስጡ የነበሩትን ጉልህ ጉድለቶችንም ፈጽሞ እየካድክ ....ባንጻሩ ሕዝባችንን ወደ ላቀ ንቃተ ሕሊና ለማሸጋገር ወሳኝ የሆነውን ዘመናዊ ትምህርትን እንደ ጥፋት የሚፈርጅ የፀዋር ተቃራኒ የሆነው ሌላኛው አስገራሚ ጽንፍ ላይ ትገኛለህ :: ስለ 'ማህበራዊ ሳይንስ ' ነው ያወራኹት ብለህ ያከልከው ማለዘቢያም ምንም ትርጉም የሚሰጥ አይደለም :: ከላይ እንደምስሌ የዘረዘርካቸው ሕዝባችን የሚገኝበት ዝቅጠት ምንጭ 'ማህበራዊ ሳይንስ ' ትምህርት መሆኑን የሚያስረዳ አንድ ትጉም የሚሰጥ ነጥብ እንኳን አላስቀመጥክም :: እስቲ የራስህን ምሳሌዎች እያቸውና መልስልኝ :-...
ለአንድ ኢትዮጵያዊ ሴት አረብ ሀገር ሄዶ ከፎቅ ወድቆ መሞት ማህበራዊ ሳይንስ መማሯ በምን አይነት ስሌት ይሆን ምክንያት የሚሆነው ?? ስለ ላንድ ግራብ እና ሌሎችም ጉዳዮች የዘርዘርከው እንዲሁ በምን አይነት አስገራሚ ሎጂክ ይሆን ማህበራዊ ሳይንስ ከመማር ጋር የሚገናኘው ?? ማህበራዊ ሳይንስ መማር ' national consciousness' ያጠፋል ማለት ምን ዓይነት ፌዝ ነው ??

ለመሆኑ የኢትዮጵያ ማህበረሰቦችን ቋንቋዎችን ወዘተ በማህበራዊ ሳይንስ (linguistic, sociology) ካልሆነ በምን ምትሀት ይሆን የምታጠናቸው ? (በስማ በለው ?)... በትዝታ የምታዛባውን የሀገራችንን ታሪክስ ... በማህበራዊ ሳይንስ (history) ካልሆነ በምን ይሆን የምትመረምረው ? (በትውፊት ?)..... የእነ ሉሲን አጽምስ በምን ትምህርት ይሆን (archeology, anthropology) አውጥተህና መርምረህ 'ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ ነች ! ብለህ የምትኮራው ? (በአፈ ታሪካዊ ግምት ?)... ሀገራችን የምትመራበትን ህግጋትንስ በምን ትምህርት ይሆን (law, criminology) የምትቀርጸውና የምትተገብረው ? (በሙሴ ህግ ?)... ወዘተ ....ወዘተ ...???

መልካም ቆይታ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 805

PostPosted: Fri Dec 23, 2011 5:15 am    Post subject: Reply with quote

እቴጌ

አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽና ለዚህ ጥያቄ በምትመልሽልኝ መልስ የኔና ያንቺ ልዩነት ምን ያህል የተራራቀ እንደሆነ እንመለከታለን ::

ለመሆኑ እቴጌ : ሚኒሊክ ወይም ኃይለ ሥላሴ ዘመናዊ ትምህርት በኢትዮጵያ የከፈቱበትን ምክንያት ታውቂያለሽ ? አንድ ኦፊሽያል ምክንያት ብቻ ነበረው :: Do you know what it is at all?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እቴጌይት

ዋና ኮትኳች

Joined: 23 Sep 2007
Posts: 547

PostPosted: Tue Dec 27, 2011 6:05 am    Post subject: Reply with quote

ሠላም ናፖሊዮን

ባነሳኸው ርዕስ ላይ ያለኝን ሀሳቦች ለማቅረብ ያህል ተመልሻለሁኝ :: በበኩሌ ሕዝባችን ለሚገኝበት የተገዢነት አስተሳሰብ (submissive mentality) ወሳኝ የሆኑ ምክንያቶች (factors) በሶስት ተርታ ሊመደቡ የሚችሉ ይመስለኛል :-

1) የሀይማኖት እና ከዛም የሚወለደው የባህል ተጽዕኖ

2) የደርግ ጭፍጨፋ ያስከተለው የስነልቦና ሰለባ እና ወያኔ በሰፊው የቀጠለው ማህበራዊ ውድቀት

3) የትምህርት አለመስፋፋት እና የኢኮኖሚ ዕድል ምክነት ናቸው ::

1)
ብዙውን ጊዜ ትኩረት የምንሰጠው ጉዳይ ሀይማኖት ሕብረተሰቡን የውጪ ወራሪዎችን እንዲዋጋ በማስተባበር የተጫወተውን ሚና ነው :: የውጪ ወራሪ ጠላትነት እና ጉዳት .... ለገዢውም ለተገዢውም ወገን እና .. ለሀይማኖት አመራሩም ጭምር በመሆኑ .. የአላማ አንድነት መፍጠሩ ምክንያታዊ ነው :: ባንጻሩ ግን እንደማንኛውም ሀገር ታሪክ ... የእኛም ሀገር ቀደምት ገዢ ሀይሎች ....... ሀይማኖትን እንደመሰራያ በመጠቀም ..... ሕብረተሰቡ ውስጥ የፍጹሙ ተገዢነት ባህልን በሰፊው አስርፀዋል :: የሀይማኖት ትምህርቶች .... የሰው ልጅ በድህነትና በባርነት ተገዝቶ ቢኖርም ... ከሰማይ ዋጋ እንደሚያገኝ ስለሚያስተምሩት ....ገዢዎችም በእግዚአብሄር የተሰየሙ ናቸው ተብሎ ስለሚነግረው ..... ተገዢነቱን በጸጋ ተቀብሎ ... እራሱን በበታችነት መድቦና አምኖ እንዲኖር ትልቅ ሚና ተጫውተዋል :: ይሄ በአውሮፓም የነበረ ሂደት ሲሆን ልዩነቱ አውሮፓ 'enlightenment' እና 'secularization' ሂደት ግለሰቦች በሀይማኖት የተነሳ ከሚመጣ ተገዥነትን አሜን ብሎ ከመቀበል ስሜት እንዲላቀቁና ስለራሳቸው ልበሙሉነት እንዲሰማቸው ሲያስችል እኛ ግን ከጥንታዊ ግዛትነት ወደ ዘመናዊነት ልናደርግ የሞከርናቸው ሽግግሮች በተለያዩ ውስብስብ ምክንያቶች ተጨንግፈው ቀርተዋል ::

2) በደርግ ዘመን በቀይ ሽብርና ከዛም በኋላ በተደረጉ አሰቃቂ ጭፍጨፋዎች , የኢኮኖሚ ውድቀት እና ተስፋ ቢስነት ... ባንድ ወገን የተወሰነውን ወገን ወደ ብሄርተኛነት ሲገፋው .....በዛ ዘመን እና ከዛም በኋላ የመጣውን በርካታ ወጣት ደግሞ ስነ ልቦና በመስለብ .... ከፖለቲካ ትግል እርም ብሎ ፈጽሞ እንዲርቅ እና በሀገሩ ጉዳይ ላይ የባለቤትና የሀላፊነት ስሜት እንዳይሰማው አድርጎታል :: ስለዚህ ራሱን ከዚህ የጨለመ የፖለቲካም ሆነ የኢኮኖሚ አዙሪት ለማውጣት በተገኘው አጋጣሚ አግባብነት ያለውም ይሁን የሌለው መንገድ ተጠቅሞ እንዲኖር .... አሊያም ባገኘው አጋጣሚ ወደ ምዕራብ ሀገሮች ተሰዶ የግሉን ከቻለም የቤተሰቡን ሕይወት እንዲቀይር .... ያልተሳካለትም ማህበራዊ ዝቅጠት ውስጥ ተዘፍቆ (በጫት በአልኮልን በዝሙት ) ራሱን እያደነዘዘ እንዲኖር አድርጎታል :: ይሄንን የሚያስረግጡ በርካታ ማስረጃዎችን ማየት ይቻላል ::
-ከደርግ ዘመን በፊት ለትምህርትም ይሁን በማናቸውም ምክንያት ወደ አውሮፓም ይሁን አሜሪካ ወጥተው ወደ ሀገራቸው የማይመለሱ ... ወደ ሱዳን እና ኬኒያ በእግር ወይም ወደ አረብ ሀገር የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን በጣም አነስተኛ የነበረ መሆኑ ....የጫት , የአልኮል የሴተኛ አዳሪነት ስርጭት በአንጻራዊ መልኩ አንስተኛ የነበረ መሆኑ ወዘተ ..ይሄንኑ ያመለክቱናል ::

ወያኔ ... የደርግን ጨፍጫፊነት የብሄር ካባ እና የዲሞክራሲን ቋንቋ አልብሶ በሰፊው ሲቀጥልበት ከላይ የጠቀስኳቸው የተገዢነት እና ተስፋ ቆርጦ ለማምለጥ የመሞከር አዝማሚያዎች (trends) በሰፊው ስር እየሰደዱ ቀጥለዋል :: ከላይ እንደማስረጃ የቀረቡት ጉዳዮችም በእጥፍ ድርብ እየጨመሩ ይገኛሉ ::

3) ገለልተኛ የሆነ ዘመናዊ ትምህርት ..... የአስተሳሰብ አድማስን ማስፋት ብቻ ሳይሆን ሰዎች ስለራሳቸው ያላቸውን አመለካከትን ከመገንባት እና ...በዜግነት ያላቸውን መብት ከመረዳት አንጻር ...ያለው ሚና ከፍተኛ ነው :: ትምህርት ዓይነተኛ ሙያን ለማዳበር ብቻ ሳይሆን ..... የሚጠይቅ እና የተባለውን አሜን ብቻ ብሎ የማይቀበል ጭንቅላትን (Inquistive and critical mind) ስለሚፈጥር የተገዢነት ባህልን የሚፈጥሩ ተጽዕኖዎችን ለማስወገድ ወሳኝ ሚና አለው :: (ለምሳሌ 'መሬት ላራሹ የሚለው ጥያቄ የመጣው ካልተማረው ገበሬ ሳይሆን ዩንቨርሲቲ ካለው ተማሪ ነበር ):: እርግጥ ትምህርት ሲባል የትምህርት ስርአቱ ትኩረት እና አሰጣጥ ከላይ የጠቀስኩትን አስተሳሰብ ከመቅረጽ አንጻር ወሳኝነት አለው :: (ይሔ ግን ራሱን የቻለ ሌላ ርዕስ ስለሆነ እዚህ ላይ ተወዋለሁኝ )

የኢኮኖሚ እድሎች (economic opportunities) መምከን ወጣቱ በሀገሩ ተስፋ ቢስ እንዲሆን እና ከላይ በተዘረዘሩት ዝቅጠቶች ውስጥ እንዲኖር ሲያደርጉት .... ተስፋውም የተሻለ የኢኮኖሚ እድሎች ባሉባቸው የምዕራብ ሀገሮች ላይ እንዲመሰረት ያደርጉታል :: ገዢው ወገንም የኢኮኖሚ እድሎችን አገዛዙን ከመደገፍ ወይም ሌላው ቢቀር አገዛዙን ካለመቃወም ጋር ስለሚያቆራኘው የሕብረተሰባችን የኢኮኖሚ ጥገኛነት የተገዢነት ባህልን ከማጠናከር አንጻር ትልቅ ሚና እንዳለው ማየት ይቻላል ::

ለማጠቃለል እነዚህ ከባድ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ እውነታዎች ከድንቁርና መስፋፋት እና 'በምድር ቢሰቃዩ በሰማይ ዋጋ ይገኛል ' ከሚለን የሀይማኖታችን ጭብጥ ጋር ሲደመሩ .... ሕብረተሰባችን ውስጥ ስር የሰደደ የተገዢነት ባህል እና ተዛማጅ ማህበራዊ ዝቅጠቶችን መፍጠራቸው አስገራሚ አይሆንም ::

መልካም ቆይታ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 805

PostPosted: Tue Dec 27, 2011 8:19 am    Post subject: Reply with quote

እናመሰግንሃለ� እንደጻፈ(ች)ው:
እቴጌ

አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽና ለዚህ ጥያቄ በምትመልሽልኝ መልስ የኔና ያንቺ ልዩነት ምን ያህል የተራራቀ እንደሆነ እንመለከታለን ::

ለመሆኑ እቴጌ : ሚኒሊክ ወይም ኃይለ ሥላሴ ዘመናዊ ትምህርት በኢትዮጵያ የከፈቱበትን ምክንያት ታውቂያለሽ ? አንድ ኦፊሽያል ምክንያት ብቻ ነበረው :: Do you know what it is at all?

እቴጌ ይህን ጥያቄዬን የዘለልሽበት ምክንያቱ ምን እንደሆነ ግልጽ አይደለም :: ልመልሰውና ልሂድ ::

ዘመናዊ ትምህርት በኢትዮጵያ የተጀመረበት ምክንያት ቋንቋን ለማጥናት አይደለም : ሰው ከዝንጀሮ እንዴት እንደመጣና ጥቁሮች በዝግመተኛ ኢቮሉሽን እንዴት ወደኍላ እንደቀሩ ማስረጃ ለመሰብሰብ አይደለም : ወይም በብሔር : በጎጥ : ወይም በቋንቋ ህብረተሰብ እንዴት እንደሚደራጅ ለማጥናትት አልነበረም ::

ብቸኛው ምክንያት - ቴክኖሎጂ ብቻ ነበር :: የነበረው የዘመናዊ ትምህርት ዓላማ - "ቴክኖሎጂ ቢኖር : የገበሬ የሥራ ጫና ይቀልላል :: ቴክኖሎጂ ቢኖር : የሴቶች የሥራ ጫና ይቀላል :: ቴክኖሎጂ ቢኖር መንግሥትና ሕዝብ በቀላሉ በመገናኛ ዘዴዎች ይገናኛሉ :: ቴክኖሎጂ ቢኖር : የሌላውን አገር ግኝት ለማየትና ተሞክሮ ለመቅሰም ይረዳል :: በተለይ በተለይ ቴክኖሎጂ ቢኖር ማንም እንደልቡ እየመጣ ቦንብ እየጣለ ሕዝባችንን አይፈጅም : እኛም የምንተኩሰውን እንሠራለን -ከእነርሱም ጋር እንከባበራለን " የሚል ነበር :: በተለይ የመጨረሻው - ራስን ዲፌንድ ማድረግ መቻል - በጣም የተዛተበት ግብ ነበር ::

ዘመናዊ ትምህርት የተመሠረለትን ዓላማ ትቶ ያልተመሠረለትንና ያልቸገረንን ሲዘባርቅ : እነሆ የተባለው አንድ እንኳ ቴክኖሎጂ መሠረት ይዞ በኢትዮጵያ ራሱን ሳይችል : ይልቁኑ ስለቡርዧ : ስለቋንቋ : ስለጎጥ : ስለኢንፊርዮሪቲ ኮምፕሌክስ : ስለሱፒሪዮሪቲ ኮምፕሌክስ : ስለሴት መብት : ሕጻን መብት : ግብረሶዶማዊ መብት : ቡጊ ቻቻ : ፊልም : ካራቴ : ስደት ስደት ስደት : አገርን መጥላት : የኔ ባሕል ከሌላው ያንሳል የሚል ንጽጽር : ማርኮ ፖሎ : ማጅላን : ቫስኮ ዳጋማ : የምዕራባውያን ገድል : ባሕል : ዓለምን እንዴት "ዲስከቨር " እንዳደረጉ : አፍሪካ እንዴት የጨለማ አህጉር እንደነበረች : ......ገለመሌ ገለመሌ ገለመሌ ውስጥ ገባን :: የሚያሳዝነው : ገበሬው አሁንም በበሬ ያርሳል : ሚስት አሁንም ውኃ ልትቀዳ ትንከራተታለች : ሐረር አሁንም ቧንቧ ለመሥራት ከሕዝቧ መዋጮ ትለምናለች : መንግሥትም ጦርነት በተነሳ ቁጥር ከሕዝቡ ጉሮሮ ነጥቆ ለሚሊታሪ ሥልጠና ጉድ የሚያስብል ወጪ ካቅሙ በላይ ያወጣል :: የኢትዮጵያ መንግሥት የዲፌንስ በጀት ከትምህርት በጀት በጣም የላቀ ነው :: ታንኩን ሚጉን ምኑን የሚሾፍሩለትን እስራኤል አሜሪካ ራሽያ ምናምን እየወሰደ ሲያሠለጥን : ለዛም እልፍ አእላፍ ብር ሲመድብና ሲያባክን : ለጦር መሣሪያ እርዳታ ሲባልም የቀድሞውም ያሁኑም መንግሥት በተለያየ አይዲዮሎጂ ላሉ አገራት ሲያሸረግድ : አንዱን ሲቀበል ሌላውን ሲጥል - በመሃል ደም መፋሰስ ሲመጣ (ሕወሀት : ማሌሊት : ኢዲዩ : ሻቢያ : ቀይ ሽብር ነጭ ሽብር ....) ይህ ሁሉ ከጦር መሣሪያ ምንጭ ጋር የሚሄድ የየራሱ ጦስ ይዞ ሲመጣ : ይኸው አለ ! የሳይንስ ሙያተኞች በየዘርፉ ይማራሉ - ነገር ግን በተንሻፈፈ የሶሻል ሳይንስ ቲዮሪ ጦስ በሆነ ፖለቲካ ምክንያት አገር ለቅቀው ይሰደዳሉ !

ዘመናዊ ትምህርት የተባለውን ትቶ ያልተባለውን ነው በኢትዮጵያ የዘባረቀው ! ዓላማውን ስቷል ! ሕዝቡን አንድ የሚያደርግና የጋራ ሕብረተሰባዊ ራዕይ የሚያስሰንቀው ነገር ማስጨበጥ አልቻለም :: ስለሆነም Education is at the brink of collapse በሚል ድምዳሜ ላይ የኢትዮጵያ ምሑራን ይገኛሉ ::

ስለሆነም : የኢትዮጵያ ወጣት : ከዛሬ 60 ወይም 70 አመት በፊት ከነበረው ትንሽ አለማወቅ (የቴክኖሎጂ ውጤቶች ብቻ ከጎደለው ) ወደ ትልቁ የንድንቁርና ዝቅጠት (ጋጠ ወጥነት : ወኔ ቢስነት : ሕብረተሰባዊ ራዕይ ማጣት : አልችልም ባይነት : ዓላማ ቢስነት : ራስን መግዛት አለመቻል : የወንድማማችነት ፍቅር ከወገኑ ጋር ማጣት ... + በጣም ጎዶሎ የትምህርት አሰጣጥ ያመጣው ቴክኒካል ድንቁርና ) በዘመናዊው ትምህርት መንገድነት ሸርርርርርርርር ....ብሎ ገብቷል !

ዘመናዊ ትምህርት ገድሎናል ! ዓላማ የለውም : አቅጣጫ የለውም : ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ የሚያደርጋት ምን እንደሆነ ሪኮግናይዝ አያደርግም : ስለዚህ የሚጠብቀውና የሚያስተምረው ሕብረተሰባዊ ራዕይ የለም :: በመሆኑም : የማናውቃቸውን አውሮፓውያን ቲዮሪ ሸምድደን እንድናጠናና ዕድሉን ካገኘን በባሌም በቦሌም ብለን የቲዮሪዎቹን ባለቤቶች ለማገልገል ካገር እንድንወጣ መንገዱን ወለል አድርጎ ከፍቶልናል ---- ራዘር ... ከፍቶብናል !

ለዚያ ነው : ባሁን ጊዜ በትልልቅ የምዕራብ ዩኒቨርስቲዎች ኢትዮጵያውያንም ሆኑ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ምሑራንና ተማሪዎች ስለኢትዮጵያ ትምህርት አስመልክቶ የሚያጠኗቸው ጥናቶች : እጅግ በተሳከረው የኢትዮጵያ የትምህርት አካሄድ የተነሳ መጨረሻ ላይ "what is the purpose of schooling in Ethiopia in the first place?" ብለው ለመጨረስ የሚገደዱት ::

ውኃ ቢወቅጡት እንቦጭ ! ዌል ካም ባክ ሬይንስ ኦፍ ሚኒሊክ ዮሐንስ ወቴዎድሮስ ...... 150 አመት ወደኍላ !! ቅቅቅቅቅ !!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እቴጌይት

ዋና ኮትኳች

Joined: 23 Sep 2007
Posts: 547

PostPosted: Tue Dec 27, 2011 4:30 pm    Post subject: Reply with quote

ጥያቄህን የዘለልኩበት ምክንያት ቀድመው የተመለሱ ነገሮችን መደጋገም ትርጉም ይሰጣል ብዬ ስላላሰብኩ ነው :: ሀሳብህን በሀሳብነቱ ባከብረውም በእኔ እይታ የምታመጣቸው ነጥቦች በየጊዜው የሚንሸራተቱ እና ቁንፅል እውነት ይዘው ትልቅና ጽንፈኛ ድምዳሜ ላይ የሚደርሱ ናቸው :: ለምሳሌ የዝግመተ ለውጥ (evolution) ትምህርት የማህበራዊ ሳይንስ አካል ሳይሆን መሠረታዊ የሆነ የባዮሎጂና የሕክምና ትምህርት አካል መሆኑን ስተኸዋል :: ስለቴክኖሎጂ ስታውራ ዛሬ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕጻናትን ከበርካታ በሽታዎች የሚታደጉ መድሀኒቶች (immunization vaccines) የተፈለሰፉት እና እየተፈለሰፉ ያሉት በዝግመተ ለውጥ ትምህርት ተመሥርቶ እንደሆነም ስተኸዋል (based on the evolution of the particular virus we are fighting). በዘረኛነት ከተለከፈ ሳይንቲስት ነኝ ባይ ካልሆነ በስተቀር ጥቁሮች በዝግመተ ለውጥ የተነሳ ወደ ኋላ ቀርተዋል የሚል የማህበራዊ ሳይንስ ድምዳሜም እንደሌለ ማወቅ ብዙም አያስቸግርም :: ስለአፍሪካም ሆነ ሌላው ሶስተኛ ዓለም ኋላ መቅረት በሳይንስ የተመሰረተ ትንታኔዎችን ለማግኘት በርካታ አፍሪካውያንም ሆነ አፍሪካዊ ያልሆኑ የማህበራዊ ሳይንስ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ምሁራን የጻፏቸውን ብታነብ ይልቅስ ብዙ ትርጉም ያላቸው ግንዛቤዎችን ያስጨብጥሀል ::

እንደሚምስለኝ መለየት የተሳነህ ከላይ በተደጋጋሚ እንደገለጽኩት የአንድን ትምህርት ስርዓቱ ትኩረት እና አሰጣጥ አግባብነትን አስመልክቶ የሚደረግ ተግባራዊ ሂስና እና ሲጀመር እራሱ ትምህርት የሚባለ ነገር ላይ (ማህበራዊ ሳይንስም ጭምር ) ጥያቄ ማንሳት መካከል ያለው የሰማይና የምድር ልዩነት ነው :: የማህበራዊ ሳይንስትን ምንነት እና ቲዎሪዎችም እንዴት እንደሚቀረጹም በቅጡ የተገነዝብከው አልመሰለኝም :: የሆኖ ሆኖ ግን በዚህ ጉዳይ ላይ ያለን የአስተሳሰብ ልዩነት ትልቅ ስለሆነ በዚሁ ብንዘጋው ጥሩ ይሆናል ::

መልካም ቆይታ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ፀዋር

ኮትኳች

Joined: 16 Feb 2010
Posts: 481

PostPosted: Tue Dec 27, 2011 6:12 pm    Post subject: Reply with quote

WAIT A MINUTE?! WHY YOU CONDEMNED ME AS AN EXTRIMIST? I CAN'T SEE ANY DIFFERENCE BETWEEN MY POINT AND YOURS EXCEPT THAT YOU PARAPHRASE MY CRITICS AND ADD UP SOME OTHER FACTORS. CAN YOU TELL ME PLS?

እቴጌይት እንደጻፈ(ች)ው:
ሠላም ናፖሊዮን

ባነሳኸው ርዕስ ላይ ያለኝን ሀሳቦች ለማቅረብ ያህል ተመልሻለሁኝ :: በበኩሌ ሕዝባችን ለሚገኝበት የተገዢነት አስተሳሰብ (submissive mentality) ወሳኝ የሆኑ ምክንያቶች (factors) በሶስት ተርታ ሊመደቡ የሚችሉ ይመስለኛል :-

1) የሀይማኖት እና ከዛም የሚወለደው የባህል ተጽዕኖ

2) የደርግ ጭፍጨፋ ያስከተለው የስነልቦና ሰለባ እና ወያኔ በሰፊው የቀጠለው ማህበራዊ ውድቀት

3) የትምህርት አለመስፋፋት እና የኢኮኖሚ ዕድል ምክነት ናቸው ::

1)
ብዙውን ጊዜ ትኩረት የምንሰጠው ጉዳይ ሀይማኖት ሕብረተሰቡን የውጪ ወራሪዎችን እንዲዋጋ በማስተባበር የተጫወተውን ሚና ነው :: የውጪ ወራሪ ጠላትነት እና ጉዳት .... ለገዢውም ለተገዢውም ወገን እና .. ለሀይማኖት አመራሩም ጭምር በመሆኑ .. የአላማ አንድነት መፍጠሩ ምክንያታዊ ነው :: ባንጻሩ ግን እንደማንኛውም ሀገር ታሪክ ... የእኛም ሀገር ቀደምት ገዢ ሀይሎች ....... ሀይማኖትን እንደመሰራያ በመጠቀም ..... ሕብረተሰቡ ውስጥ የፍጹሙ ተገዢነት ባህልን በሰፊው አስርፀዋል :: የሀይማኖት ትምህርቶች .... የሰው ልጅ በድህነትና በባርነት ተገዝቶ ቢኖርም ... ከሰማይ ዋጋ እንደሚያገኝ ስለሚያስተምሩት ....ገዢዎችም በእግዚአብሄር የተሰየሙ ናቸው ተብሎ ስለሚነግረው ..... ተገዢነቱን በጸጋ ተቀብሎ ... እራሱን በበታችነት መድቦና አምኖ እንዲኖር ትልቅ ሚና ተጫውተዋል :: ይሄ በአውሮፓም የነበረ ሂደት ሲሆን ልዩነቱ አውሮፓ 'enlightenment' እና 'secularization' ሂደት ግለሰቦች በሀይማኖት የተነሳ ከሚመጣ ተገዥነትን አሜን ብሎ ከመቀበል ስሜት እንዲላቀቁና ስለራሳቸው ልበሙሉነት እንዲሰማቸው ሲያስችል እኛ ግን ከጥንታዊ ግዛትነት ወደ ዘመናዊነት ልናደርግ የሞከርናቸው ሽግግሮች በተለያዩ ውስብስብ ምክንያቶች ተጨንግፈው ቀርተዋል ::

2) በደርግ ዘመን በቀይ ሽብርና ከዛም በኋላ በተደረጉ አሰቃቂ ጭፍጨፋዎች , የኢኮኖሚ ውድቀት እና ተስፋ ቢስነት ... ባንድ ወገን የተወሰነውን ወገን ወደ ብሄርተኛነት ሲገፋው .....በዛ ዘመን እና ከዛም በኋላ የመጣውን በርካታ ወጣት ደግሞ ስነ ልቦና በመስለብ .... ከፖለቲካ ትግል እርም ብሎ ፈጽሞ እንዲርቅ እና በሀገሩ ጉዳይ ላይ የባለቤትና የሀላፊነት ስሜት እንዳይሰማው አድርጎታል :: ስለዚህ ራሱን ከዚህ የጨለመ የፖለቲካም ሆነ የኢኮኖሚ አዙሪት ለማውጣት በተገኘው አጋጣሚ አግባብነት ያለውም ይሁን የሌለው መንገድ ተጠቅሞ እንዲኖር .... አሊያም ባገኘው አጋጣሚ ወደ ምዕራብ ሀገሮች ተሰዶ የግሉን ከቻለም የቤተሰቡን ሕይወት እንዲቀይር .... ያልተሳካለትም ማህበራዊ ዝቅጠት ውስጥ ተዘፍቆ (በጫት በአልኮልን በዝሙት ) ራሱን እያደነዘዘ እንዲኖር አድርጎታል :: ይሄንን የሚያስረግጡ በርካታ ማስረጃዎችን ማየት ይቻላል ::
-ከደርግ ዘመን በፊት ለትምህርትም ይሁን በማናቸውም ምክንያት ወደ አውሮፓም ይሁን አሜሪካ ወጥተው ወደ ሀገራቸው የማይመለሱ ... ወደ ሱዳን እና ኬኒያ በእግር ወይም ወደ አረብ ሀገር የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን በጣም አነስተኛ የነበረ መሆኑ ....የጫት , የአልኮል የሴተኛ አዳሪነት ስርጭት በአንጻራዊ መልኩ አንስተኛ የነበረ መሆኑ ወዘተ ..ይሄንኑ ያመለክቱናል ::

ወያኔ ... የደርግን ጨፍጫፊነት የብሄር ካባ እና የዲሞክራሲን ቋንቋ አልብሶ በሰፊው ሲቀጥልበት ከላይ የጠቀስኳቸው የተገዢነት እና ተስፋ ቆርጦ ለማምለጥ የመሞከር አዝማሚያዎች (trends) በሰፊው ስር እየሰደዱ ቀጥለዋል :: ከላይ እንደማስረጃ የቀረቡት ጉዳዮችም በእጥፍ ድርብ እየጨመሩ ይገኛሉ ::

3) ገለልተኛ የሆነ ዘመናዊ ትምህርት ..... የአስተሳሰብ አድማስን ማስፋት ብቻ ሳይሆን ሰዎች ስለራሳቸው ያላቸውን አመለካከትን ከመገንባት እና ...በዜግነት ያላቸውን መብት ከመረዳት አንጻር ...ያለው ሚና ከፍተኛ ነው :: ትምህርት ዓይነተኛ ሙያን ለማዳበር ብቻ ሳይሆን ..... የሚጠይቅ እና የተባለውን አሜን ብቻ ብሎ የማይቀበል ጭንቅላትን (Inquistive and critical mind) ስለሚፈጥር የተገዢነት ባህልን የሚፈጥሩ ተጽዕኖዎችን ለማስወገድ ወሳኝ ሚና አለው :: (ለምሳሌ 'መሬት ላራሹ የሚለው ጥያቄ የመጣው ካልተማረው ገበሬ ሳይሆን ዩንቨርሲቲ ካለው ተማሪ ነበር ):: እርግጥ ትምህርት ሲባል የትምህርት ስርአቱ ትኩረት እና አሰጣጥ ከላይ የጠቀስኩትን አስተሳሰብ ከመቅረጽ አንጻር ወሳኝነት አለው :: (ይሔ ግን ራሱን የቻለ ሌላ ርዕስ ስለሆነ እዚህ ላይ ተወዋለሁኝ )

የኢኮኖሚ እድሎች (economic opportunities) መምከን ወጣቱ በሀገሩ ተስፋ ቢስ እንዲሆን እና ከላይ በተዘረዘሩት ዝቅጠቶች ውስጥ እንዲኖር ሲያደርጉት .... ተስፋውም የተሻለ የኢኮኖሚ እድሎች ባሉባቸው የምዕራብ ሀገሮች ላይ እንዲመሰረት ያደርጉታል :: ገዢው ወገንም የኢኮኖሚ እድሎችን አገዛዙን ከመደገፍ ወይም ሌላው ቢቀር አገዛዙን ካለመቃወም ጋር ስለሚያቆራኘው የሕብረተሰባችን የኢኮኖሚ ጥገኛነት የተገዢነት ባህልን ከማጠናከር አንጻር ትልቅ ሚና እንዳለው ማየት ይቻላል ::

ለማጠቃለል እነዚህ ከባድ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ እውነታዎች ከድንቁርና መስፋፋት እና 'በምድር ቢሰቃዩ በሰማይ ዋጋ ይገኛል ' ከሚለን የሀይማኖታችን ጭብጥ ጋር ሲደመሩ .... ሕብረተሰባችን ውስጥ ስር የሰደደ የተገዢነት ባህል እና ተዛማጅ ማህበራዊ ዝቅጠቶችን መፍጠራቸው አስገራሚ አይሆንም ::

መልካም ቆይታ

_________________
I have great faith in fools; self-confidence my friends call it.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 805

PostPosted: Tue Dec 27, 2011 7:44 pm    Post subject: Reply with quote

እቴጌይት እንደጻፈ(ች)ው:
ለምሳሌ የዝግመተ ለውጥ (evolution) ትምህርት የማህበራዊ ሳይንስ አካል ሳይሆን መሠረታዊ የሆነ የባዮሎጂና የሕክምና ትምህርት አካል መሆኑን ስተኸዋል :: ስለቴክኖሎጂ ስታውራ ዛሬ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕጻናትን ከበርካታ በሽታዎች የሚታደጉ መድሀኒቶች (immunization vaccines) የተፈለሰፉት እና እየተፈለሰፉ ያሉት በዝግመተ ለውጥ ትምህርት ተመሥርቶ እንደሆነም ስተኸዋል (based on the evolution of the particular virus we are fighting).

ይሄ ስህተት ነው እቴጌ :: የዝግመተ ለውጥ ወሬ ሕክምናን ኢንፎርም አላደረገም :: ዝግመተ ለውጥ ሶሻል ዳርዊኒዝምን ነው ያመጣው :: ሶሻል ዳርዊኒዝም ደግሞ Public education በሚባል ጠቅላላ ርዕስ ሥር ሴኩላር የትምህርት አሰጣጥን አመጣ :: ይህ በአሜሪካ Horace Mann, G. Stanley Hall, and John Dewey በተባሉ የትምህርት ቲዮሪስቶች አማካኝነት ሥር ያዘ :: ቀጥሎም ወደሌላው ዓለም ሞዴሉን ማስፋፋት ጀመረ :: የአውሮፓ ትምህርት አሰጣጥም በዛው ምስያ ራሱን ሞልድ አደረገ :: የበለጠ ለማወቅ ከፈለግሽ ቱብ ግቢና ጎልጉዪ :: እንዳው ለዘመናዊ ትምህርት ጥብቅና መቆም ከሆነ አላማሽ ዝም ብለሽ ተዪው ::

ኢቮሉሽን ቲዮሪ መድኃኒት አላስፈለሰፈንም እቴጌ :: ከየት እንዳመጣሽው በጣም የሚያስቅ ነው :: የድረጎች እና የንጥረ ነገሮች ጥናት ነው መድኃኒትን የሰጠን :: ኢቮሉሽን ተመሥርቶ ያላለቀና አከራካሪ ዘርፍ ነው ::

የሆነ ሆኖ : ዘመናዊ ትምህርት በኢትዮጵያ አሰጣጡ ብቻ ሳይሆን : በማኅበራዊ ሳንሶች ዘርፍ እስከ ድረስ ገዳይ መርዝ የሆነ ንቃተ ሕሊናን የሚያፈዝዝ ብቻ ሳይሆን ነፍስን የሚገድልና መንፈስን የሚያደነዝዝ : ነጻ ምርጫንም የሚሠብር አካሄድ ነው ::

ብሬን ዋሺንግ

ብሬን ዋሺንግ

ብሬን ዋሺንግ

የትምህርት ቲዮሪ ፈልሳፊዎች ተብለው በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ባሁን ጊዜ ተማሪዎች የሚማሯቸው ቲዮሪስቶች የሚከተሉት ናቸው :-

    Arrow Wilhelm Wundt- የሕጻኑን ፍሪ ዊል በኮንዲሽኒንግ አማካኝነት እንዴት መስበር ይቻላል ብሎ ያጠና የነበረ ጀርመናዊ ዕብድ ! በዚህ መሠረት በክላስ ሩም ውስጥ በመምህሩና በተማሪዎች መሀል ሊኖር የሚገባውን ነገር ሌይ አውት ለማድረግ የሚሆን የሜንታል ኮሎናይዜሽን መንገድ ጠነሰሰ :: በርሱ ስም በአሜሪካ የትምህርት ላቦራቶሪዎች ተቋቋሙ - እስካሁን ቲዮሪው ተቀባይነት አለው :: ስለርሱ አካሄድ የበለጠ መረዳት ከፈለግሽ Charlotte Iserbyt በዪና ቱብ ገብተሽ ጎልጉዪ :: አሜሪካኖቹ ሕጻናት ልጆቻቸውን ከራሳቸው ኢንተረስት ውጪ ሌላ ነገር የማያዩ በማኅበራዊ ንቃተ ሕሊና ረገድ ደነዞችና emotionally shallow ሰፋ ያለ ራዕይ የሌላቸው ሊያደርጓቸው የቻሉበትና ጉዳቱን ግን አሁን አሁን ብቻ የተገነዘቡበትን ሂደት ሴትዮዋ ትተርክልሻለች :: አሜሪካም ልጆቿን ትመስላለች :: አፍሪካም አውስትራሊያም ማርስም ሄዳ ስለራሷ ነው የምታወራው ! የሆነ ቦታ ላይ ይህ አካሄዷ ሊያስቆማት እንደሚችል የምታውቅ አትመስልም !

    Arrow John Dewey- አንድን ሕጻን ከቤተሰቦቹ የሚሰጠውን ወይም ከማኅበረሰቡ የወረሰውን ኖርም "እንዲመረምርና ኤክስፒርየንስ እንዲያደርገው " በሚል ከላይ ከላይ ጥሩ በሆነ ሰበብ ማኅበረሰባዊ ቫልዩዎችን ወደኋላ ተመልሶ "መጠየቅን " "መጠርጠርን " እና ከስክራች ጀምሮ የራሱን ቫልዩ መመሥረትን "Constructivism" በሚል ቲዮሪ ስም ያስተማረ : Intergenerational value transference እንዳይኖርም ልጅን ከቀደሙት አባቶቹ እናቶቹ ዓላማ እና ውርስ ጋር የሚያቆራርጥ - በተለይ በተለይ የዚህን አካሄድ ሊሚቴሽንና ጥቅም የሚያውቁና ከራሳቸው እሴት ጋር (እንደ እንግሊዞቹ ) ባላንስ አድርገው መጠቀም የሚችሉ ያደጉ አገራት ሳይሆኑ : ሁሉን እንደወረደ የሚቀበሉ ያላደጉ አገራት የማኅበረሰብ እሴታቸውና ማንነታቸው ብትንትኑ ወጥቶ ቴክኖሎጂያዊ ምርምራቸው ግን ወዴትም እንዳይሄድ ሆኖባቸው ይገኛል :: በኛ ላይና በልጆቻችን ላይ ከሚደርሰው Generation gap የበለጠ የነጭ ማስረጃ ከፈለግን C.A.Bowers የተባለው ጸሐፊ The false promises of Constructivist Theories of Learning በሚል ስለሦስተኛው ዓለም አገራት ቀውስ የጻፈውን መመልከት ነው :: Collectivist ማኅበራዊ እሴት Individualist ስግብግብነትና ግሪድ ለመተካቱ ይህ አካሄድ በጣም ሚና ተጫውቷል ::

    Arrow Sigmund Freud and Carl Jung- Unconscious mind እንዴት በትምህርትና በሚድያ ማኒፑሌት ማድረግ እንደሚቻል ያጠኑ የነበሩ አስማተኞች ! (Literally- አስማተኞች !! Sorcery ሥራዬ ብለው ያጠኑ ነበረ ):: የፍሮይድ ቤተሰቦች በጠቅላላ በአድቨርታይዝመንት ቢዝነስ ውስጥ ገብተው የማስታወቂያ ድርጅቶች ኢምፓየር በአሜሪካ መመሥረት ችለዋል :: ሴክስ : ድረግ : ቫዮለንስ : ማቴሪያሊዝም : ሰርቫይቫል ኢንስቲንክት : ዴዝ ኢንስቲንክስ ....በመጠቀም የሰውን እንሰሳዊ ዝንባሌ (id) በመኮርኮር እንዴት የፈለግከውን ኣይነት ምርትና አገልግሎት እንደምትሸጥለት በማድረግ በኩል እነዚህ ሰዎች ኤክስፐርት ናቸው ! ትምህርት ቤቶችም የነርሱን ቲዮሪ በተለያየ መንገድ ይጠቀማሉ - ማለት ልጁን በፈለጉት አቅጣጫ ኮንዲሽን ማድረግ ይችላሉ :: ንቃተ ሕሊና በትምህርት ፖሊሲ ቀራጩ እጅ ይገባል ማለት ነው ! ልጁ የሚተርፈው ብቸኛ ነገር ቢኖር - ለደመነፍሳዊ ስሜቱ ባርያ በመሆን የራሱን ሰርቫይቫልና የበላይነት ለማረጋገጥ ሳይታክት በአእምሮም በአካልም መታገል እንዳለበት የሚያስታውስ በጭንቅላቱ ውስጥ ጠልቆ የተቀበረ ደወል ብቻ ነው :: ሰላም የለውም ! ሊኖረውም አይችልም ! ስለዚህ ለወገኑ : ለአላማው : ለእሴቱ መሞት አይችልም :: ከደመነፍሳዊ ግፊቱ በላይ ቫልዩ የለውም ::

    በነገራችን ላይ ማርክሲዝምና ፍሮይዲዝም የተለያየ ደረጃ ላይ ያሉ አንድ የፍልስፍና ቤተሰብ ናቸው ::

ይሄ ነው የመምህራን ሥልጠና ካሪኩለም :: እነዚህ እንግዲህ ከብዙ በጥቂቱ ናቸው :: እኔ ከላይ እንደጻፍኩት በእውነተኛ ጎኑ ገጥጦ ሳይሆን : በማር በተለወሰ መልኩ በመልካም ቃላት ታጅቦ የነዚህ ሰዎች ታሪክ : ቲዮሪ : እና አፕሊኬሽን ነው የኢትዮጵያ የመምህራን ሥልጠና ተቆአማት ለተማሪዎቻቸው የሚያስተምሩት ::

አንድ እንኳ ኒዩክሌር እንዴት እንደሚሠራ ወይም ዩራኒየም እንዴት እንደሚወጣ ሲክሬት ሬሲፒውን ሊያስተምረን የሚችል ሳይንስ የለም :: ያለው ይሄው ራስን በራስ የማፍረስ አጥፍተህ ጥፋ ፕሮፓጋንዳ ነው !

እቴጌ : በይ ሁለተኛ ለዘመናዊ ትምህርት ጥብቅና ስትቆሚ : ባለፊልዶቹና ሰለባዎቹ እንዳይሰሙሽ !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እቴጌይት

ዋና ኮትኳች

Joined: 23 Sep 2007
Posts: 547

PostPosted: Wed Dec 28, 2011 12:05 am    Post subject: Reply with quote

ሠላም እናመሰግንሀለ

ከላይ እንደገለጽኩልህ በዚህ ጉዳይ ላይ ያለን ግንዛቤ የተራራ እና የገደል ያህል የተራራቀ ስለሆነ ልሞግትህ አልሻም :: የተመለስኩበት ዋና ዓላማ ሌላው ቢቀር ስለ ዝግመተ ለውጥ (evolution) ትምህርት የጻፍከው ጉልህ ስህተት ...... ባለማወቅ ሌሎችንም ሊያስት ስለሚችል ስለ እዛ አንድ ሁለት ለማለት ነው :-

1) የዝግመተ ለውጥ ትምህርት በባዮሎጂ ስር የሚካተት ሲሆን የትምህርቱ መሰረት የሆኑት ነጥቦች natural selection, mutation, genetic drift እና gene flow ናቸው :: ስለዚህ ትምህርት በጣም አነስተኛ የሆነ ግንዛቤ ያለው ሰው እንኳን በባዮሎጂ ስር እንደሚካተት ለመረዳት ይችላል :: በነገራችን ላይ የትምህርቱ መስራች ዳርዊን ከኤደንብር ዩኒቨርሲቲ በሕክምና የተመረቀ Naturalist ነበር ::

2) evolution ትምህርት መከላከያ ክትባቶችን ጨመሮ በርካታ አፕሊኬሽንስ እንዳሉት ለመረዳት እንዲሁ ትንሽም ቢሆን ስለትምህርቱ ግንዛቤ ያለው ሰው አያዳግተውም :: ጥቂት ምሳሌዎችን ብንወስድ :-

- ከፖሊዮ ቫይረስ የሚመጣውን የፖሊዮ በሽታን ብናይ የበሽታው ክትባት የተሰራው የቫይረሱ የዝግመተ ለውጥ ሂደትን በመጠቀም ነው :: አልበርት ሳቢን የሚባል የሕክምና ባለሙያ ይሄን አደገኛ ቫይረስ ከሰው ሰውነት ውጪ በማሳደግ .... ቫይረሱ ከለመደው የሰው ሰውነት ውጪ አዳፕት ለማድረግ ዝግመተ ለውጥ እንዲያካሂድ በማድረግ .... በሽታ የማምጣት አቅሙን እንዲያጣ አደረገው (In evolutionary biology this process is called attenuation):: ይሄ የተዳከመ ቫይረስን ሰውን በምንወጋበት ጊዜ ሰውነታችን ጸረ ቫይረሱ አቅም ይገነባል (we become immuned):: በርካታ ክትባቶች በተመሳሳይ evolutionary biology በመጠቀም ነው የሚሰሩት ::

በዘመናችን በክፍተኛ ሁኔታ እያደገ ያለው እና ተስፋ የተጣለበት ባዮቴክኖሎጂ እና የመድሀኒቶች አሰራር በከፍተኛ ደረጃ በቴስት ቱብ ውስጥ ዝግመተለውጥን በመፍጠር ወይም በማገድ ላይ የተመሰረተ ሂደትን ይጠቀማል :: የአንድ መድሀኒትን ለመፍጠር ብቻ ሳይሆን የሚሰራበትን እድሜ ለማራዘምም (through preventing the evolution of resistance etc) የዝግመተ ለውጥ ሳይንስ ወሳኝ ነው ::
-በግብርና ላይ እንዲሁ የተፈጠሩ በርካታ እድገቶች በዝግመተ ለውጥ ትምህርት ላይ የተመሰረቱ ናቸው (ለምሳሌ የእንስሳት ድቀላ እና የሰብል መረጣ ዘዴዎች ወዘተ ).

ስለዚህ ነው የምንቃወመውን ነገር መጀመሪያ በቅጡ ብናውቅ በቁንጽል ሀሳቦች ላይ ተነስተን ጽንፈኛ ድምዳሜ እንዳንደርስ እና ሀሳባችንን ምክንያታዊ ለማድረግ ያግዘናል ብዬ የማስበው ::

መልካም ቆይታ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እቴጌይት

ዋና ኮትኳች

Joined: 23 Sep 2007
Posts: 547

PostPosted: Wed Dec 28, 2011 12:23 am    Post subject: Reply with quote

ፀዋር እንደጻፈ(ች)ው:
WAIT A MINUTE?! WHY YOU CONDEMNED ME AS AN EXTRIMIST? I CAN'T SEE ANY DIFFERENCE BETWEEN MY POINT AND YOURS EXCEPT THAT YOU PARAPHRASE MY CRITICS AND ADD UP SOME OTHER FACTORS. CAN YOU TELL ME PLS?

ሠላም ፀዋር :-
የፈረንጅ አፍ ስለምትመርጥ እስቲ በእርሱ ልመልስልህ Very Happy

The impression I got from your postings were that you were catagorically condemning Ethiopian orthodoxy and ridiculing its important figures. I cant see how that can be considered the same as my point which simply attempted to identify inhibiting influences inherited from our religious teachings that may have contributed to our culture of submissiveness.

Stay well
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ናፖሊዮን ዳኘ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 18 Apr 2008
Posts: 1874

PostPosted: Wed Dec 28, 2011 12:37 am    Post subject: Reply with quote

ዋናው ጉዳይ ተረሳ ! እስቲ ስለ ጫት እናውራ

ከዚህ በታች የምጽፈው ነገር ማንምም ለመንካት አይደለም ፕርሰናል አድርጋችሁ እንዳትወስዱት !
______________________________________________

ያለ ጫት አዮን የማይገልጥ አንድ ገጽ የማያነብ ሜታቦሊዝሙ በደንብ የማሰራ ሰው ቁጥሩ እምብዛም ነበር ያኔ ሳውቅ :: አሁን ደሞ የምንሰማው ከከፍተኛ ትምህርት ተመርቆ የወጣው አብዛኛው ወጣት እንደዛ እንደሆነ ነው የሚነገረው :: እንግዲህ ህወሀት በዘረጋው ምልመላ መሰረት አብዛኛው ሳይወድ በግዱ የህወሀትን ቢሮክራሲ ይቀላቀላል :: የቢሮክራሲው ሞተር ጫት ሆነ ማለት ነው ::

የሚቀጥለው ነጥብ የመንግስት ሰራተኞች ገቢያቸው የሚያወላዳ አይደለም :: ያውም አለ በሚባለው የኑሮ ውድነት ! ጫት ደሞ ርካሽ አይደለም ! በአንድ ቀን የሚቃመው እስከ ሰማኒያ ብር ይደርሳል ነው የሚባለው ! በሌላ በኩል በየጊዜው ጫት ይቃማል ?! ገቢውን እና ወጪውን ሂሳቡን ስንመታው ልክ አይመጣም :: ሰው ደሞ በኔጌቲቭ አይቅምም ! ወይ እንደመብራት እንደፈረቃ ሰው ተራ በተራ እየተጠራራ ይቅማል :: አለበለዚያ ደሞ ይሄን አጸያፊ ልማድ ለማድረስ ሲባል ---የህዝብ ንብረት ስርቆት ይገባል :: ሙስና ይጀመራል :: እኔ ደሞ የሀገር ፍቅር መጀመሪያ ነው የምለው (ያገር ፍቅርን በዘመኑ ባለው ትውልድ ድካም እና ጥንካሬ መለካት ስላለብን ) ...አዎ የመጀመሪያው የሀገር ፍቅር ...እኔ ጫት ለመቃም እና ማታ የቢራ ጠርሙስ ለመጨበጥ ብየ ከዚህ ከሚራብ ህዝብ ላይ ሰርቄ ጉቦ ወስጀ አልቅምም ብሎ የሚያስብ ሰው እሱ ያገር ፍቅር አለው ብየ አስባለሁ ::

ከዚህም ሻል ያለ ንቃተ ህሊና እና የሀገር ፍቅር ያለው ደሞ ለህጻናቱም ሆነ ወጣት ኢትዮጵያን መጥፎ አርአያ መሆን እንደሌለበት አምኖ ተደብቆ የሚቅምም ሰው ካለ ( መተው እንኳ ባይችል ) ከሀገር ግንባታ ለይቸ አላየውም Idea

እርድና መስሏቸው እንኳን እኛ እና ""ሀገሪቱም ጫት በሚቅሙ ሰዎች ነው የምትመራው "" በሚል ደሞ ለጫት ኤክስኪዮዝ መፍጠር ብቻ ሳይሆን መቃምን የሚያበረታቱ ድንዝዞች አሉ ::

ለነገሩ ሰው ጫት ባይቅም ማታ ባልኮኒ ላይ ጉብ ብሎ መለኪያ ባይጨብጥ ... ምንም ማለት አይደለም ! ለእንደዚህ አይነት ነገር ብሎ ጉቦ እና ስርቆት ቅሌት ውስጥ ሲገባ ግን ያኔ ባርነትን ጀመረው ! ከዚያ በኍላ ደሞ ስራ ለሰጠው ስርዐት ባሪያ ይሆናል :: ስርአቱ ሱሱም ነውና ! በነገራችን ላይ ባስተዋልኩት እና በታዘብኩት መጠን በውጭ ሀገር ያሉ በተለይ በዮኒቨርስቲ አካባቢ የሚፈጠሩ ""ኮኔክሽኖች "" እና የፓርቲ ካውካስም አካባቢ ሲጠነሰስ በመላ በዘዴ እና በኮኬይንም ጭምር ነው :: በእንደዛ አይነት ሰርክል ውስጥ ዊድ እና ኮኬይንም ይጨሳል - ይጠጣል ...ከዛ በዛው በኮኔክሽን አማካይነት ደህና ስራ ማግኘት ይቻላ ...ጭሰቱም በዚያው ይቀጥላል ...ያው እንደዛ ላሉት ተላላዎች የውጭ ነገር ሁሉ ጭስ ነው ....ከዚያ በኍላ አንድ ዘመን ተኝተን ...ምናምን የሚባል ቅዠት ይመጣል :: ውጭ ሀግር ያሉት የራሳቸው ሀሳብ ነው :: የሚያሳስበው የሀገራችን ጉዳይ ነው ::

አንድ ጊዜ ፕሮፌሰር መርዕድ ወልደ አረጋይ አዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ ያሉትን ላካፍል እና ለዛሬ ይብቃኝ :: ለነገሩ ከዚህ በፊት እንደስፃፍኩት አስታውሳለውሁ :: በጣም ስለምወደው ለማስታወስ ነው :: አንዴ በፎቶ ኮፒ አባዝተው ኬኔዲ ያስቀመጡት ኮርስ ሪዲንግ የተወሰነው ኮፒ የተወሰነው ገጹ ተገንጥሎ ተወስዶ ነበረ :: በጣም ተናደው ፊታቸው እየተንቀጠቀጠ ክላስ ገቡ ::

""ይሄ ዮኒቨርሲቲ ደሀ እንደሆነ ታውቃላችሁ :: ደሀ የሆነው ደሞ ሀገሪቱም ደሀ ስለሆነች ነው :: መጽሀፍ ፎቶ ኮፒ ተደርጎ የተቀመጠበት ምክንያት ባለችን ሪሶርስ ተሳስባችሁ እንድትጠቀሙ ነው :: እንደውነቱ ከሆነ ሀገር ትቀይራላችሁ ተብሎ የምትታሰቡ ናችሁ :: እናንተ ግን ዛሬ ላይብራሪ ውስጥ ተባዝቶ የተቀመጠ ንባብ ከሰረቃችሁ ነገ ደሞ ትምህርት ጨርሳችሁ የመንግስት ቦታ ሲሰጣችሁ ሌላ ነገር ትሰርቃላችሁ :: እነዚህም (ወደ አራት ኪሎ አቅጣጫ በእጃቸው እያሳዮ ) [ወያኔዎቹን ነው ] እንደናተው ተማሪ ነበሩ !""

ናፖሊዮን ዳኘ ::
_________________
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ፀዋር

ኮትኳች

Joined: 16 Feb 2010
Posts: 481

PostPosted: Wed Dec 28, 2011 12:57 am    Post subject: Reply with quote

ሠላም

አንቺም አማርኛ ከፈለግሽ ይሁን :: ኪይቦርዱን ስላለመድኩት ጊዜ ስለሚፈጅብኝ እንጂ ሌላ ምንም ምክንያት የለኝም ::

እኔ እስከተረዳሁሽ ድረስ systematically ሀሳብሽ ተቀባይነት እንዲያገኝ በእኔ "ክፋት " መታከክ ፈልገሽ እንጂ አንቺ ያልሽው እኔ ካልኩት የተለዬ ሆኖ አይደለም :: እኔ በኢንግሊሽ ያወራሁትን አንቺ በአማርኛ እኔ በአማርኛ ያወራሁትን አንቺ በኢንግሊሽ ማድረግሽ ብቻ ነው ያየሁት ልዩነት :: እኔ በፈሪሀ እግዚአብሄር ስም : በመገዘት ልማዶች ተንበርካኪ አደረጋችሁን ስል አንቺ Submissive ሆንን አልሽ :: For most part of it your church is responsible ስል ቁጥር አንድ ስትይ ያስቀመጥሽውን ቤተ ክርስቲያናቸውን ተጠያቂ ማድረግ ነው :: I CAN'T SEE ANY DIFFERENCE BETWEEN THESE POINTS. ANY WAY, THIS IS NOT A BIG ISSUE RIGHT NOW. AS YOU MIGHT BE AWARE OF, THIS WEEK I'M ON A MISSION FOCUSING AT ONE POINT IN A TIME. IT IS MORE LIKELY THAT THE NEXT TARGET WILL BE YOU Wink , I MEAN PEOPLE LIKE YOU WHO ARE OBSESSED WITH WESTERN IDEOLOGY. AND I BELIEVE, DESPITE THE CHALLENGES WE FACED TODAY, THE FUTURE WON'T BE LIKE THE PAST. AT LEAST WE WON'T LET IT BE. YOU KNOW WHAT I MEAN BY THAT, RIGHT?

እቴጌይት እንደጻፈ(ች)ው:
ፀዋር እንደጻፈ(ች)ው:
WAIT A MINUTE?! WHY YOU CONDEMNED ME AS AN EXTRIMIST? I CAN'T SEE ANY DIFFERENCE BETWEEN MY POINT AND YOURS EXCEPT THAT YOU PARAPHRASE MY CRITICS AND ADD UP SOME OTHER FACTORS. CAN YOU TELL ME PLS?

ሠላም ፀዋር :-
የፈረንጅ አፍ ስለምትመርጥ እስቲ በእርሱ ልመልስልህ Very Happy

The impression I got from your postings were that you were catagorically condemning Ethiopian orthodoxy and ridiculing its important figures. I cant see how that can be considered the same as my point which simply attempted to identify inhibiting influences inherited from our religious teachings that may have contributed to our culture of submissiveness.

Stay well

_________________
I have great faith in fools; self-confidence my friends call it.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 805

PostPosted: Wed Dec 28, 2011 1:04 am    Post subject: Reply with quote

በነገርሽ ላይ እቴጌ :

ቁርጥ አእምሮሽ ሰዎቹን ይመስላል ! ነጮች በአንድ ነገር ተከራካሪያቸውን ማሳመን የማይችሉ መሆኑን ሲገነዘቡ : ኮምፕሊትሊ የማያሸንፉበትን አስፔክት እርግፍ አድርገው ይተዉትና : 1% ብትሆንም በነርሱ ሳይድ ልትሆን ትችላለች ብለው ያሰቧትን ርዕሰ ጉዳይ መዝዘው ይጫወቷታል :: እኔ ስለማኅበራዊ ሳይንስ ነበር በአብዛኛው ያወራሁት :: በጣም ረጅም ጽሑፎችን የተነተንኩት በነርሱ ላይ ነው :: የቤቱ ርዕስ ንቃተ -ሕሊናም በማኅበራዊው ሳይንስ ላይ ያተኮረ ነው :: አንቺ ኢቮሉሽንን ወይም ክትባትን ይዘሽ አቧራ ታጨሻለሽ :: ከላይ ስለተነተንኳቸው የማኅበራዊ ሳይንስ ጉዳዮች የምትዪው ይኖርሻል ወይስ ዝም ብለሽ አልሸነፍ ባይነት ነው ?

ባንቺ ርዕስ እንኳ እስቲ እንሂድና እንየው :-

ሰው ከዝንጀሮ መጣንና መድኃኒት አሠራርን እንደምንም አገናኝተሽ በጂን ዲዛይንና በዘር ማዳቀል በኩል አድርገሽ መልካም ነገር እንደሆነ ልታስረጂን ሞከርሽ ... Genetic modification እና vaccination በራሳቸው ባሁን ጊዜ ከጥቅማቸው ጉዳታቸው እንደሚያመዝን ራሳቸው ሳይንቲስቶቹ የሚናገሩት ነገር ነው :: ቫክሲኔሽንና ኦቲዝምን እስቲ አንብቢ ወይዘሮ እቴጌ ? ስለቲቢ ክትባትና የአፍሪካ ሰዎች ወደምዕራብ ሲመጡ በቫይረሱ መከላከያ ሳይሆን መመረዝ ይዘው እንደሚመጡ ስለሚታወቅ እንዴት ወዲያውኑ የቲቪ ሰስፔክት እንደሚሆኑና ድጋሜ ክትባት መከተብ እንዳለባቸው እስቲ ዞር ዞር በይና ጠያይቂ - ዝም ብለሽ ደህና ነገር ይመስል ከማዳነቅ ?

ስለሰብል መረጣና ድቀላ ገለመሌ : ባለሙያዎቹ

-እነ ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር
- እነ ዶክተር መላኩ ወረደ
- የሕንዷ vandana shiva

ሌሎችም ብዙ አንቱ የተባሉ የዘርፉ ባለሙያዎች ምን እንደሚሉ እስቲ ስሚ ? እንደመልካም ነገር ከምትቆጥሪው ካንቺ ጋር አይስማሙም :: ምናልባት "ነጭ ያመጣው ሃሳብ ስለሆነ ብቻ ዝም ብለሽ አታዳንቂ " ይሉሽ ይሆናል :: ቫንዳና ሺቫ የአያቶች ኮሌጅ በሚል ስም ትራዲሽናል ኮሌጅ ከፍታ አዌርነስ ለመፍጠር በአገሯ እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች :: እነመላኩ ወረደ ኦርጋኒክ ሲድ አክሽን ሊድ የተባለ ድርጅት በኢትዮጵያ መሥርተው ከገበሬው ጋር እየሠሩ በጂን ሞዲፋይድ ያልሆነ እሕል ዘር ለኢትዮጵያ ለማስቀረትና በሂደት የተዳቀለ ምርት የሚባል ነገር ከአገር ለማስወጣት ደፋ ቀና ይላሉ ::

___________

ግን : እኔ ሲጀመር ጀምሮ እያወራሁ የነበረው በተለይ በተለይ ስለማኅበራዊ ሳይንስ ዘርፎች ነበረ :: ስለዚያ የምትዪው ነገር ያለሽ አይመስለኝም :: ባሕል : ማንነት : አእምሮ : ራስን ማወቅ : ኅብረተሰባዊ ግንኙነት : ርዕዮተ ዐለም : ...እነዚህ ናቸው በሞደርን ኤጁኬሽን ምክንያት መርዝ ሲሆኑብን የኖሩት ነገሮች ::

የምዕራባውያን ትምህርት በማኅበረሰብና በባሕል ረገድ ምን ጥቅም ሰጠን ? እስቲ ዘርዝሪ ?!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8  Next
Page 4 of 8

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia