WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ንቃተ ህሊና
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
እቴጌይት

ዋና ኮትኳች

Joined: 23 Sep 2007
Posts: 571

PostPosted: Wed Dec 28, 2011 2:48 am    Post subject: Reply with quote

እናመሰግንሀለ

ስለማሕበራሲ ሳይንስ እኮ በአንድ ምዕራፍ ብቻ ከበቂ በላይ በጣም ኤለመንተሪ የሆነ መልስ ሰጥቼህ ነበር :: ማህበራዊ ሳይንስ ምንድን ነው ? ምን ምን ትምህርቶችን ያካትታል ከሚለው ኤለመንተሪ ነገር ለምን አትጀምርም :: ያንን ለመረዳት እንዲያግዝህ ብዬ :-
1-የሀገርህን ቋንቋዎች የማህበራዊ ሳይንስ አካል በሆነው lingustic ጥናት ካልሆነ በምን ተአምር ይሆን የምታጠናው ብዬ ጠየኩህ !! መልስ የለም
2-የሀገርህ ገበሬ የሚያርሰውን እና ከብቶቹን የሚያሰማራበትን መልክዓ ምድርን የማህበራዊ ሳይንስ አካል በሆነው ጂዮግራፊ ካልሆነ በምን አይነት ባህላዊ መንገድ ይሆን የምታውቀው ብዬ ጠየኩህ !! መልስ የለም
3-በሀገር ውስጥ ያሉትን ማህበረሰባት በማህበረሰብ ሳይንስ ካልሆነ በምን አይነት ሜቴዶሎጂ ይሆን የምታጠናቸው ብዬም ጠየኩህ ? መልስ የለም
4-የሀገርህን እና የሕዝብህን ታሪክም የማህበራዊ ሳይንስ አካል በሆነው የታሪክ ትምህርት ካልሆነ በምን ምትሀት ነው የምታጠናው ብዬም ጠየኩህ ?? መልስ የለም
5-ሀገርህ ውስጥ የሚገኙትን አጽሞች እና ታሪካዊ ህንጻዎች የማህበራሲ ሳይንስ አካል በሆነው አርኪዮሎጂ እና አንትሮፖሎጂ ካልሆነ በምን አይነት ባህላዊ መንገድ ይሆን የምትጠናው ብዬ ጠየኩህ ? ....መልስ የለም
6-የአገርህን ኢኮኖሚ በየትኛው ሞዴል እንደምትመራ የምትወስነው የማህበርሰስብ ትምህርት አካል በሆነው የኢኮኖሚ ጥናት ላይ ተመርኩዘህ ካልሆነ በምን ይሆን የምትቀርጸው ብዬ ጠየኩህ ? መለስ የለም ወዘተ ...

እነዚህ በጣም ኤለመንተሪ ለሆኑ ጥያቄዎች መልስ ሳትሰጥ ዘለህ ከእምነተህ ጋር የሚጋጭ የሚመስሉህን ግን ከመሀበረሰባችን ነባራዊ ችግሮች ጋር ምንም ዝምድና የሌላቸውን ቁንጽል ሀሳቦችን (ቲዎሪዎችን ) መዘህ ታወጣና አጠቃላይ ማህበራዊ ሳይንስ ጥፋት ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ለመድረስ ትሄዳለህ :: እና በእንደዚህ ዓይነት መንገድ እንዴት ምክንያታዊ የሆነ ውይይት /ክርክር ማድረግ ይቻላል ::

ስለዚህ ባጭሩ ማህበራዊም ሆነ የትኛውንም የትምህርት ዘርፍን በጅምላ በመቃወም ከሚከራከር ሰው ጋር ሲርየስ የሆነ ውይይት ማድረግ ትርጉም ያለው አይመስለኝም ::

ደህና ቆይ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 811

PostPosted: Wed Dec 28, 2011 3:05 am    Post subject: Reply with quote

----

Last edited by እናመሰግንሃለ on Tue Sep 03, 2013 7:35 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እቴጌይት

ዋና ኮትኳች

Joined: 23 Sep 2007
Posts: 571

PostPosted: Wed Dec 28, 2011 3:20 am    Post subject: Reply with quote

ሠላም ፀዋር
በተመቸህ ቋንቋ ጻፍ ወንድሜ :: ቋንቋ መግባቢያ መሳሪያ ስለሆነ አያጣላንም !!

ፀዋር እንደጻፈ(ች)ው:

እኔ እስከተረዳሁሽ ድረስ systematically ሀሳብሽ ተቀባይነት እንዲያገኝ በእኔ "ክፋት " መታከክ ፈልገሽ እንጂ አንቺ ያልሽው እኔ ካልኩት የተለዬ ሆኖ አይደለም ::

የእኔን ሀሳብ በምክንያታዊ ማስረጃዎችና ምሳሌዎችን የዘረዘርኩበት ጽሁፍ ላይ አንተን ያነሳሁበት ቦታ የለም :: ሀሳብህን ለምን እንደተቃወምኩትም በዝርዝር ጽፌአለሁ ::

ፀዋር እንደጻፈ(ች)ው:

እኔ በፈሪሀ እግዚአብሄር ስም : በመገዘት ልማዶች ተንበርካኪ አደረጋችሁን ስል አንቺ Submissive ሆንን አልሽ :: For most part of it your church is responsible ስል ቁጥር አንድ ስትይ ያስቀመጥሽውን ቤተ ክርስቲያናቸውን ተጠያቂ ማድረግ ነው :: I CAN'T SEE ANY DIFFERENCE BETWEEN THESE POINTS.

ከላይ እንዳልኩህ እኔ የአንተን ጽሁፍ ሳነብ ያገኘሁት ስሜት የኦርቶዶክስ እምነትን በጅምላ የሚፈርጅ እና 'ቅዱሳኑን ' ሳይቀር ስም እየጠራ የሚያንጓጥጥ አይነት ሆኖ ነው :: ከመረዳት ችግሬ ከሆነ ይቅርታ :: እኔ ልገልጽ የሞከርኩት ግን ከሀይማኖት የተወረሱ በርካታ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ እሴቶች እንደተጠበቁ ሆኖ ... የተገዢነት ባህል ላይ ማስረጽ ላይ ግን ሀይማኖት አሳድሯል ብዬ የማስበውን ተጽእኖ ማቅረብ ነው :: እዚህ ነጥብ ላይ በመሠረቱ አንድ አይነት አቋም ከሆነ ያለን እሰየው !! (ያንተ ስድብ ተቀንሶበት ማለት ነው Laughing )

ፀዋር እንደጻፈ(ች)ው:

IT IS MORE LIKELY THAT THE NEXT TARGET WILL BE YOU Wink , I MEAN PEOPLE LIKE YOU WHO ARE OBSESSED WITH WESTERN IDEOLOGY.

የተጻፉትን በቅጡ ብታነብ በየትኛውም ቦታ ስለየትኛውም አይዲዮሎጂ አላወራሁም :: ውይይቱ በንቃተ ሕሊና ዙሪያ እና ከዛም ጋር በተያያዘ ዘመናዊ ትምህርት ንቅታ ሕሊና ላይ ስላለው ተጽዕኖ ነው :: የዘመናዊ ትምህርትን አስፈላጊነት መገንዘብ በምን አይነት የደከመ ስሌት ይሆን 'obsession with western ideology' የሚባለው ?

መልካም ቆይታ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ናፖሊዮን ዳኘ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 18 Apr 2008
Posts: 1878

PostPosted: Wed Dec 28, 2011 4:02 am    Post subject: Reply with quote

አርኪዮሎጂ ጂኦግራፊን ሜትሮሎጂን እና አንዳንዶቹን የጠቃቀስሻቸውን የትምህርት መስኮች ለፖለቲካ ትግል ከሚያስፈልግ ንቃተ ህሊና መፍጠር ጋር ያላቸው አስፈላጊ እና ጠቃሚ ተያያዥነት ምንድን ነው ?? ከይቅርታ ጋር ለስሊፐሪ ስሎፕ የምትጠቀሚበት ትንተና ራሱ ማቹሪቲ የለውም :: ኤለመንታሪነት ይታይበታል :: ስለ ኢቮሎሽን በሁለተና ደረጃ ትምህርት እንደተማርን ታውቂ ይሆን ?? ስለ ጂኦግራፊ ጥቅም ?? ስለ ታሪክ ጥቅም ...ስንጀመራቸው ከዴፍኒሽን ነው የጀመርናቸው .... እዛ ነው የመለስሽን ::

የግብረ ሰዶማውያን የመወያየት መብት ኢትዮጵያ ውስጥ መከበር አለበት ስላስባለሽ የእውቀት ምንጭ ጥቀሽልን ...ስለ ዲሞክራሲው ስለ ሊበራሊዝሙ ...ምንድን ነው ፋይዳው ? እነዚህ ሊበራል የምትያቸው ሀገሮች ህወሀትን አስታጥቀው እንደላኩብን ዛሬ ድረስ ምክር እየሰጡ እንደሆነ አታውቂም ? በሌላ በኩል ደሞ እናንተንም በጎን ይዘው ኢትዮጵያን በቀጣይነት ""ሊበራል "" ሊያደርጉ ዱብ እንቅ ይላሉ :: በፍፁም እንደናንተ ባለ ሰው እምነት የለኝም :: ዛሬ ደሞ አንዱ አዋቂ ነኝ ባይ የኢትዮጵያን አርበኝነት ሲወርፈው አየሁ ! ያገሬ የዋህ ሰው ደሞ ... አዋቂ ናቸሁ ብሎ ጆሮ ይሰጣል :: ድንች የሚለውን ክሊፕ ተመልከችው ...

ናፖሊዮን ዳኘ ::

እቴጌይት እንደጻፈ(ች)ው:
እናመሰግንሀለ

ስለማሕበራሲ ሳይንስ እኮ በአንድ ምዕራፍ ብቻ ከበቂ በላይ በጣም ኤለመንተሪ የሆነ መልስ ሰጥቼህ ነበር :: ማህበራዊ ሳይንስ ምንድን ነው ? ምን ምን ትምህርቶችን ያካትታል ከሚለው ኤለመንተሪ ነገር ለምን አትጀምርም :: ያንን ለመረዳት እንዲያግዝህ ብዬ :-
1-የሀገርህን ቋንቋዎች የማህበራዊ ሳይንስ አካል በሆነው lingustic ጥናት ካልሆነ በምን ተአምር ይሆን የምታጠናው ብዬ ጠየኩህ !! መልስ የለም
2-የሀገርህ ገበሬ የሚያርሰውን እና ከብቶቹን የሚያሰማራበትን መልክዓ ምድርን የማህበራዊ ሳይንስ አካል በሆነው ጂዮግራፊ ካልሆነ በምን አይነት ባህላዊ መንገድ ይሆን የምታውቀው ብዬ ጠየኩህ !! መልስ የለም
3-በሀገር ውስጥ ያሉትን ማህበረሰባት በማህበረሰብ ሳይንስ ካልሆነ በምን አይነት ሜቴዶሎጂ ይሆን የምታጠናቸው ብዬም ጠየኩህ ? መልስ የለም
4-የሀገርህን እና የሕዝብህን ታሪክም የማህበራዊ ሳይንስ አካል በሆነው የታሪክ ትምህርት ካልሆነ በምን ምትሀት ነው የምታጠናው ብዬም ጠየኩህ ?? መልስ የለም
5-ሀገርህ ውስጥ የሚገኙትን አጽሞች እና ታሪካዊ ህንጻዎች የማህበራሲ ሳይንስ አካል በሆነው አርኪዮሎጂ እና አንትሮፖሎጂ ካልሆነ በምን አይነት ባህላዊ መንገድ ይሆን የምትጠናው ብዬ ጠየኩህ ? ....መልስ የለም
6-የአገርህን ኢኮኖሚ በየትኛው ሞዴል እንደምትመራ የምትወስነው የማህበርሰስብ ትምህርት አካል በሆነው የኢኮኖሚ ጥናት ላይ ተመርኩዘህ ካልሆነ በምን ይሆን የምትቀርጸው ብዬ ጠየኩህ ? መለስ የለም ወዘተ ...

እነዚህ በጣም ኤለመንተሪ ለሆኑ ጥያቄዎች መልስ ሳትሰጥ ዘለህ ከእምነተህ ጋር የሚጋጭ የሚመስሉህን ግን ከመሀበረሰባችን ነባራዊ ችግሮች ጋር ምንም ዝምድና የሌላቸውን ቁንጽል ሀሳቦችን (ቲዎሪዎችን ) መዘህ ታወጣና አጠቃላይ ማህበራዊ ሳይንስ ጥፋት ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ለመድረስ ትሄዳለህ :: እና በእንደዚህ ዓይነት መንገድ እንዴት ምክንያታዊ የሆነ ውይይት /ክርክር ማድረግ ይቻላል ::

ስለዚህ ባጭሩ ማህበራዊም ሆነ የትኛውንም የትምህርት ዘርፍን በጅምላ በመቃወም ከሚከራከር ሰው ጋር ሲርየስ የሆነ ውይይት ማድረግ ትርጉም ያለው አይመስለኝም ::

ደህና ቆይ

_________________
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እቴጌይት

ዋና ኮትኳች

Joined: 23 Sep 2007
Posts: 571

PostPosted: Wed Dec 28, 2011 4:08 am    Post subject: Reply with quote

እናመሰግንሃለ� እንደጻፈ(ች)ው:

ከላይ የዘረዘርሻቸውን ጉዳዮችና ዘርፎች በሙሉ በምዕራባውያን መንገድ አጠናናቸው : ይኸው ገደል ገባን !

ውይ አሁንስ አሳዘንከኝ ከምር !! የምትመልሰው ስታጣ በቃ ይሄው ሆነ ?? ገደል የገባነው መልካ ምድራችንን በጂዮግራፊ ስላጠናን ወይም በቋንቋ ጥናት ቋንቋዎቻችንን ስለተረዳን ወይም በታሪክ ትምህርት ታሪካችንን ስለመረመርን ወይም በአርኪዮሎጂ ቅርሳችንን ቆፍረን ስላወጣን ነው ብለህ ታስባለህ ?? አረ ትንሽ ጭንቅላትህን ተጠቀመው ወንድሜ !!

ሊያስቆጭህ ይገባ የነበረው የሀጋርችንን ታሪክ ብዙ የታሪክ ምሁራን እና ተመራማሪዎች አፍርተን እኛው ራሳችን ሳንመረመር መቅረታችን ነበር ::..ያገራችንን ቅርስ ብዙ አርኪዮሎጂስትና አንትሮፖሎጊስቶች እኛው አፍርተን ቆፍረን ሳናወጣ ..የሀገራችንን ቶፖግራፊ እኛ ሳናጠና ሌላው እየመጣ ማድረጉ ነበር !! ይቅርታ አድርግልኝ እና የተምታታበት የድንቁርና ናሽናልዚም ማለት ያንተ ነው !!

ብዙ ወጣት ጭንቅላቱ የደነዘዘው ወይም ብሄራዊ ስሜቱ የመከነው ...ምንነቱን እንኳን አንድ ቀን ሰምቶት የማያውቀውን ከላይ ሳይገባህ በቁንጽል የዘረዘርከውን ቲዎሪ ስለተማረ ነው ስትል ስለ 'ኮዝ እና ኢፌክት ' ትንሽ እንድታነብ ከመምከር ውጭ የምጨምረው የለኝም !!

ደህና ቆይ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ናፖሊዮን ዳኘ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 18 Apr 2008
Posts: 1878

PostPosted: Wed Dec 28, 2011 4:46 am    Post subject: Reply with quote

አልገባሺም ብየ ከማስበው ነገር ውስጥ አንደኛ ሂስቶሪካ ኮንቲኒዮቲ ነው :: የምዕራቡ ዓለም ዲሞክራት እና ሊበራል ነኝ ይል በነበረበት ሰአት በዮናይትድ ኔሽን አማካይነት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌ ባወጣበት (1948) የአፍሪካ ሀገሮች በነዚፍ የሰብአዊ መብት አሳውጀናል በሚሉ ""ዲሞክራሲያዊ "" ሀገሮች የአገዛዝ ቀንበር ስር ይማቅቁ ነበር :: በአሜሪካ ስለነበረው የቀለም ልዮነት በማውገዝም ሆነ በመኮነን አንድ ሀረግ በድንጋጌው ላይ አልነበረም :: እንዲህ ያለ ረገጣ እና ዘረፋ በአፍሪካ እና በሌላውም ዓለም በነበረበት ሰዐት ( ከእኛ በስተቀር ) ከነዚሁ ከሚዘርፉ ሀይሎች ጋር ሊያሰለጥኑን የመጡ ናቸው በማለት አብረው የሚሰሩ እና የጥቅም ትስስር የነበራቸውም አፍሪካውያን ነበሩ ---ባንዳ የምንላቸው ማለት ነው :: ኢትዮጵያ ውስጥ ያንን ሊያደርጉ የሚችሉበት አጋጣሚ እና ሁኔታ ስላልነበረ እንደ ህወሀት ያሉ ባንዳዎችን ፈጥረው የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ እያደረጉ እዚህ አደረሱአቸው :: ዛሬ ለህወሀት ዕድሜ መራዘም ዘርፈ ብዙ ምክር እና በእርዳታም ስም የትየለሌ ገንዘለ ለህወሀት የሚሰጡት እነኚሁ ሀይሎች ናቸው ::

በሌላ በኩል ደሞ ሁሉ ሁኖ ህወሀት ሌጂትሜሲ ሊኖረው ያልቻለ ድረጂት ሆኖ ስላገኙ ለማንኛውም በሊበራል ስም የያዙት ቡድን አለ :: ይሄ የሆነው ሂስቶሪካል ኮንቲኒቲ ስላለ ነው :: ዓላማቸው ባንድ ትውልድ ላይ የሚያልቅ ስላልሆነ ነው :: የቅኝ ግዛቱ ዘመን ንቃተ ህሊና ደሞ ለዚህ ከቅኝ አገዛዝ በኍላ እንኳን ለሁለተኛ ጊዜ ተቀይሮ 'በግሎባላይዜሽን ' እያራመዱ ስላለው የረቀቀ የማይሞት የዘረፋ ጥሜት ብቁ አልሆነም :: ዛሬ እንደበፊቱ በአንድ ሀገር ላይ የራሳቸውን አስተዳደር ሰይመው በራሳቸው ወታደር እና ፖሊስ ሀይል እያስጠበቁ አይደለም የሚሰሩት :: ባንድ በኩል ዲስቴብላይዝ የሚያደርግ የፓለቲካ ሁኔታ ይፈጥራሉ :: ከዚህ ሂደት የሚመረተው ስደተኛ ደሞ በሌበር ሰፕላይነት ብቻ ሳይሆን አስተዳደራቸውን (በሀገራቸው ) ""ዳይቨሲፋይድ የሆነ የወክ ፎርስ ""- በተለይ በፕብሊክ ሰርቪሱ በመፍጠር ተጠባባቂ የግሎባላይዜሽን ማራመጃ የሆነ ሀይል እያፈሩ ነው :: ይሄ ሳይገባችሁ ቀርቶ አይመስለኝም እኔ እንደሚገባኝ ... ንቃተ ህሊና ይመስለኛል :: ንቃት እና ህሊና ሲጠፉ አድርባይነት እና ጥቅም ማሳደድ ቤቱን ይሰራል :: ለነገሩ በአንድ በኩል ሲታይ የኢትዮጵያው ወጣት በማደንዘዙ ረገድ ዲያስፖራው የራሱ የሆነ ተጽዕኖ አለው ::

እንደሚገባኝ በዚህ ጉዳይ ላይ እናመሰግንሀለን ካንቺ ጋር ውይይት ማድረግ ያለበት አይመስለኝም :: አንቺም ስለ አርኪዮሎጂ እያወራሽ ቀጥይ ...(ሌሎቹን ያልተያያዘ ርዕስ ሲጽፉ ስትናገሪ አይቼሽ ነበር ) ...

ሌላ ይሄ ጭፍን ብሄራዊነት የምትሉትን ነገር ይቆይላችሁ :: ለነገሩ ከጭፍን ጥቅም አሳዳጂነት ጭፍን ብሄርተኝነት በስንት ጣዕሙ !

ናፖሊዮን ዳኘ ::

Quote:
ሊያስቆጭህ ይገባ የነበረው የሀጋርችንን ታሪክ ብዙ የታሪክ ምሁራን እና ተመራማሪዎች አፍርተን እኛው ራሳችን ሳንመረመር መቅረታችን ነበር ::..ያገራችንን ቅርስ ብዙ አርኪዮሎጂስትና አንትሮፖሎጊስቶች እኛው አፍርተን ቆፍረን ሳናወጣ ..የሀገራችንን ቶፖግራፊ እኛ ሳናጠና ሌላው እየመጣ ማድረጉ ነበር !! ይቅርታ አድርግልኝ እና የተምታታበት የድንቁርና ናሽናልዚም ማለት ያንተ ነው !!

_________________
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
menzewu

ኮትኳች

Joined: 25 Dec 2009
Posts: 368

PostPosted: Wed Dec 28, 2011 4:51 am    Post subject: Reply with quote

እቴጌይት እንዲያው ልፊ ብሎሽ ነው እንጂ እውቀት የሞላውና የሚያስብ ጭንቅላት እዚህ አታገኝም . በመረጃ የተደገፈ ውይይት ሳይሆን በስሜት የሚነዳ አታካራ ነው ዋርካን የሞላው . ታሊባንና ሙላዎች ያሉት እኮ አፍጋኒስታንና ኢራን ብቻ አዪደለም . የኛም ታሊባኖችና ሙላዎች አሉ . እረ አያቶላዎችም አናጣ !!! ራቂያቸው .... አትከራከሪያቸው . የእውቀት ድንክየነታቸው ሲጋለጥባቸውና ማጣፊያው ሲያጥራቸው ምላስ ጎራዴ ይመዛሉ . ዘመናዊ ትምህርት መጥፎ ነው ለሚል ሰው ድንቁርናን ሞክረው ከማለት በቀር ምን ይባላል ?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 811

PostPosted: Wed Dec 28, 2011 5:08 am    Post subject: Reply with quote

----

Last edited by እናመሰግንሃለ on Tue Sep 03, 2013 7:36 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እቴጌይት

ዋና ኮትኳች

Joined: 23 Sep 2007
Posts: 571

PostPosted: Wed Dec 28, 2011 5:26 am    Post subject: Reply with quote

ናፖሊዮን ዳኘ እንደጻፈ(ች)ው:

አርኪዮሎጂ ጂኦግራፊን ሜትሮሎጂን እና አንዳንዶቹን የጠቃቀስሻቸውን የትምህርት መስኮች ለፖለቲካ ትግል ከሚያስፈልግ ንቃተ ህሊና መፍጠር ጋር ያላቸው አስፈላጊ እና ጠቃሚ ተያያዥነት ምንድን ነው ??

እነዚህ ነጥቦች እንዴት እንደተነሱ በቅጡ ሳታነብ ነው እንዴ ጥያቄ የምታነሳው ?? ሀሳቡን ደግፈዋለሁ የምትለው እናመሰግንሀለ መጀመሪያ በጅምላ ዘመናዊ ትምህርት ለንቅተ ሕሊና ጠንቅ ነው ሲል ..በትምህርት ስለሚገኘው ቴክኖሎጂ ጥቅም ሲነገረው ..አይ እኔ ያልኩት "ማህበራዊ ሳይንስ ' ነው ብሎ ሲንሸራተት .....ማህበራዊ ሳይንስ ምን ምንን እንደሚያካትት እና እንዴት ጠቃሚ እንደሆነ የእርሱን ደረጃ በሚመጥን መንገድ ለማስረዳት ነው እነዚህ የማህበራሲ ሳይንስ የትምህርት ዘርፎች የተዘረዘሩት :: ገባህ ??

ሁለተኛ ደግሞ እነዚህን ማህበራዊ ሳይንስ የተማሩ የሀገርህ ባለሙያዎች ሲኖርህ ነው ታሪክህን ራስህ የምትመርምረውና ሀገርህን የምታጠናው ... ቅርስህን የምታወጣው ... መልካ ምድርህን የምታውቀው ... ለገበሬህ ተስማሚ የሆነ ግብርና የምትተልመው ....ቋንቋህን የምታጠናው ...ወዘተ ...በሀገር ደረጃ እነዚህን መተግበር ለራስህ እድገት እራስህ ባለቤት እንድትሆን ..ታሪክህን ምድርህን ህዝብህን ቋንቋህን አየርህን እንድታውቅ ያደርግሀል :: ታዲያ ንቃተ ሕሊና ማዳበር ማለት ይሄና የመሳስሉት እንጂ "ንቃተ ሕሊና ' የሚል ትምህርት አየር ላይ ለብቻው እንዲሰጥ ነው እንዴ የምትጠብቀው ?? እንደ እነ / መስፍን ያለ የጂዮግራፊ ባለሙያ ሙያውን ተንተርሶ የሀገሩን ቶፖግራፊ ሲያጠና እና አንድ ነጭ መጥቶ ሲያጠና አንድ ነው ልትለኝ አትችልም :: አንድ ፈረንጅ ስለአማርኛም ሆነ ግዕዝ ሲያጠና እና ኢትዮጵያዊ የቋንቋ ባለሚያ ሲያጠና አንድ ነው ልትለኝ አትችልም :: በምትደግፈው እንዳመሰግንሀለን ስሌት ግን ገና ሲጀመር ፕሮፌሰሩ ጂዮግራፊ ወይም ቋንቋ መማርም አልነበረባቸውም :: ምክንያቱም ዘመናዊ ማህበራሲ ሳይንስ ነዋ !! ከይቅርታ ጋር ይሄንን ሀሳብ ነው ደግፈዋለሁ ስትል የነበረው እና ከዚህ የደለበ ድንቁርና እኔ አላውቅም !!

ናፖሊዮን ዳኘ እንደጻፈ(ች)ው:

ስለ ኢቮሎሽን በሁለተና ደረጃ ትምህርት እንደተማርን ታውቂ ይሆን ?? ስለ ጂኦግራፊ ጥቅም ?? ስለ ታሪክ ጥቅም ...ስንጀመራቸው ከዴፍኒሽን ነው የጀመርናቸው .... እዛ ነው የመለስሽን ::

ሀሳቡን እጋራዋለሁ የምትለው ሰውዬ እየደጋገመ የትኛውም ማህበራዊ ሳይንስ አይበጅም ማለቱን ሳታይ ነው እንዴ የሀሳቡ አጋር የሆንከው :: አንተም ራስህ ቢሆን በተለያዩ አምዶች ላይ ....በተጠናወተህ ጽንፈኛ ጸረ ምዕራባውያን ፓራኖያ የተነሳ ምክንያታዊነት የሌለው ተመሳሳይ ሀሳቦችን ማቀንቀንህን ስለማውቅ አሁንም የሰውየውን ሀሳብ ስታነብ እንዳልከው አብዛኛው ሰው by definition ጥቅሙን የሚረዳውን ጉዳይ እንኳን የሚቃወመውን ሰውዬ ለመደገፍ የተነሳኸው :: ሌላው ቢቀር ይሄንን መሰረታዊ ነጥብ መቀበልህን እንደመልካም ጅምር አየዋለሁኝ !!

ናፖሊዮን ዳኘ እንደጻፈ(ች)ው:

የግብረ ሰዶማውያን የመወያየት መብት ኢትዮጵያ ውስጥ መከበር አለበት ስላስባለሽ የእውቀት ምንጭ ጥቀሽልን ...ስለ ዲሞክራሲው ስለ ሊበራሊዝሙ ...ምንድን ነው ፋይዳው ?

ይኸውልህ እንግዲህ ! ከላይ የጠከስኩት ጸረ ምዕራባውያን ፓራኖያህ ነጥቦችን እንደ ድግስ ወጥ እየቀላቅልክ ከርዕስ ውጪ እንድትሄድ ሲያደርግህ :: እዚህ እኔ እና እናመሰግንሀለ (ባንተ እየተደገፈ ) እየተከራከርንበት ያለው ንኡሰ -ርዕስ ዘመናዊ ትምህርት በለው ወይም በሁውላ አፈግፍጎ ያስቀመጠው ማህበራዊ ሳይንስ ወይም የመጨረሻ ማፈግፈጊያው የተወሰኑ የማህበራዊ ሳይንስ ቲዎሪዎች .... ንቃተ ሕሊና ላይ አላቸው ተብሎ ክሌም ያደረገው አሉታዊ ተጽዕኖ ላይ ነው !! ታዲያ የእናንተ ድርሻ ባገራችን ኮንቴክስት ለወጣቱ ብሄራዊ ስሜት መምከንም ሆነ ንቃተ ሕሊና መኮስመን እነዚህ ቲዎሪዎች እንዴት ምክንያት እንደሚሆኑ ማስረዳት ነው !! ለምሳሌ አዲስ አበባ 12 ክፍልን ሳያልፍ ጫት እየቃመ የአሜሪካን ኑሮ የሚመኘው አብላጫው ወጣት እንደዛ የሆነው ....Wilhelm Wundt ወይም Sigmund Freud ቲዎሪ ስለተማረ እንደሆነ ይሄንን ግንኙነት እስቲ አሳዩን !! የምታወሩት ስለባህል ተጽእኖ ስለ የግሎባላይዤሽን ስለሚዲያ ኢፌክት ከሆነ ደግሞ ያንን በቅጡ መተንተን !!

ከዚህ ውጪ ግን እኔ ስለግብረ ሰዶምም ሆነ በየትኛውም ማህበራዊ ጉዳይ ላይ ያለኝ አቋም ምንነት ከክርክር ርዕሱ ጋር ዝምድና የለውም !!
ለማለት የፈለከው ለሁሉ ነገር እንደ ጥፋት ምንጭ የምታየው 'ሊብራሊዝም ' ነው ለኢትዮጵያ ወጣትን ንቃተ ሕሊና ያደከመው ለማለት ከሆነ አሁንም ስለየትኛዋ ሀገር እንደምታወራ የገባህ አልመሰለኝም :: በየተኛውም ሚዛን ቢለካ የክላሲካልም ሆነ ሶሻል ሊብራሊዝም እንጥፍጣፊ እንኳን ገና ያልገባባት ሀገር ውስጥ ....እሱን እንደ ንቃተ ህሊና ጉድለት ምክንያት ማሰብ ለእኔ ከላይ by definition ሰው ሊረዳው ይገባል ካልከው ነጥብ የማይተናነስ አለመረዳት ነው !!

ናፖሊዮን ዳኘ እንደጻፈ(ች)ው:

እነዚህ ሊበራል የምትያቸው ሀገሮች ህወሀትን አስታጥቀው እንደላኩብን ዛሬ ድረስ ምክር እየሰጡ እንደሆነ አታውቂም ?

የምዕራብ ሀገሮች ወያኔን በቀጣይነት መደገፍ የግለሰብ ነጻነትን ማዕከል ያደረገ ስርአትን ጎጂ አያደርገውም እኮ !!
በጣም ኤለመንተሪ የሆነ ምሳሌ ልጠቀምና :- የክርስትና ትምህርትን ጠቃሚነት ወይም ጎጂነት ለሕይወትህ መርጠህ የምትወስነው ክርስትናን የሚያስተምረው ቄስ በሆነ ጉዳይ ላይ በሰራው ኩነኔ ወይም ጽድቅ ላይ ተመስርተህ አይደለም :: የትምህርቱን ሞራላዊነት በራሱ መዝነህ እንጂ !! ስለዚህ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ንቃተ ሕሊናችንን ያጎድላል ብለህ ከሆነ የምትከራከረው እንዴት እንደሆነ በተጨባጭ ማስረዳት ....አንተ ይበጃል የምትለውን ስርአት ማህበር ፍሬም ወርክም ማስቀመጥ ይጠበቅብሀል !! አለበለዚያ ከፓራኖያ የተለየ ሀሳብ ነው ብዬ ለመቀበል ይከብደኛል ::

ናፖሊዮን ዳኘ እንደጻፈ(ች)ው:

በሌላ በኩል ደሞ እናንተንም በጎን ይዘው ኢትዮጵያን በቀጣይነት ""ሊበራል "" ሊያደርጉ ዱብ እንቅ ይላሉ ::

ወይ ጉድ ! ኢትዮጵያን ሊብራል ዲሞክራሲ የሚያደርጉት የሊብራል ዲሞክራሲ ፍጽም ተጽራሪ የሆነውን አብዮታዊ ብሄርተኛ መንግስትን በመደገፍ ነው ?? እንደዚህ የተዘበራረቀ ሀሳብ ይዞ ለመወያየት እኮ በጣም ያስቸግራል :: የምዕራባውያን መንግስታ ድጋፍ ከስርዓቱ ባህሪ ጋር ምንም ዝምድና እንደሌለው መረዳት አይከብድም እኮ ! ታሊባንን ሳይቀር ይደግፉ ነበር እኮ !! ታዲያ የራሳቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚወስዷቸው አቋሞች ትክክለናነት ወይም ስህተትነት በምን አይነት ስሌት ነው ሊብራል ዲሞክራሲን ለመመዘኛ መስፈርት የሚሆኑት ?? ጉንጭ ማልፋት ስለሰለችኝ ከዚህ ርዕስ ላይ ልሰናበት !!

ደህና ቆይ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እቴጌይት

ዋና ኮትኳች

Joined: 23 Sep 2007
Posts: 571

PostPosted: Wed Dec 28, 2011 5:34 am    Post subject: Reply with quote

menzewu እንደጻፈ(ች)ው:
እቴጌይት እንዲያው ልፊ ብሎሽ ነው እንጂ እውቀት የሞላውና የሚያስብ ጭንቅላት እዚህ አታገኝም . በመረጃ የተደገፈ ውይይት ሳይሆን በስሜት የሚነዳ አታካራ ነው ዋርካን የሞላው . ታሊባንና ሙላዎች ያሉት እኮ አፍጋኒስታንና ኢራን ብቻ አዪደለም . የኛም ታሊባኖችና ሙላዎች አሉ . እረ አያቶላዎችም አናጣ !!! ራቂያቸው .... አትከራከሪያቸው . የእውቀት ድንክየነታቸው ሲጋለጥባቸውና ማጣፊያው ሲያጥራቸው ምላስ ጎራዴ ይመዛሉ . ዘመናዊ ትምህርት መጥፎ ነው ለሚል ሰው ድንቁርናን ሞክረው ከማለት በቀር ምን ይባላል ?Very Happy Very Happy Very Happy ትክክል ብለሀል ወንድሜ !! ስለምክርህ አመሰግናለሁ !! መልካም የፈረንጅ አዲስ አመት ይሁንልህ !!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 811

PostPosted: Wed Dec 28, 2011 5:55 am    Post subject: Reply with quote

----

Last edited by እናመሰግንሃለ on Tue Sep 03, 2013 7:37 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
menzewu

ኮትኳች

Joined: 25 Dec 2009
Posts: 368

PostPosted: Wed Dec 28, 2011 7:20 am    Post subject: Reply with quote

አይ እንግዲህ አስኩዋላ ካልጠቀመ አብነት ትምህርት ቤት ገብቶ ቅኔ መቀጠር ወይ ዜማ ማዜም ነው . አያቴ ይሉ የነበረውም ይህንን ነው .

በተማርነው አስኩዋላ መስራት ስላልቻልን ...ወይም ስላቃተን ...ወይም የሚያሰራን ስላጣን አለያም አላሰራ ስላሉን ....መሰናክሉ በዝቶ ስለተቸገርን .....በጠቅላላው አስኩዋላውን መተግበሩ አልሆን ስላለን አስኩዋላው መጥፎ ነው ብለን ራሳችንን እናጽናና ነው የምትለው ? የችግራችን ምንጩ ከውጭ ሳይሆን ከውስጥ ነው . የኛ ጠላት እኛ ነን . እንዲህ ያደረገን ደሞ ዘመናዊ ትምህርት ሳይሆን የዚህ እጦት ነው .
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed Dec 28, 2011 7:59 am    Post subject: Reply with quote

ሻቢያው menzewu እንደጻፈ(ች)ው:
አይ እንግዲህ አስኩዋላ ካልጠቀመ አብነት ትምህርት ቤት ገብቶ ቅኔ መቀጠር ወይ ዜማ ማዜም ነው . አያቴ ይሉ የነበረውም ይህንን ነው .

በተማርነው አስኩዋላ መስራት ስላልቻልን ...ወይም ስላቃተን ...ወይም የሚያሰራን ስላጣን አለያም አላሰራ ስላሉን ....መሰናክሉ በዝቶ ስለተቸገርን .....በጠቅላላው አስኩዋላውን መተግበሩ አልሆን ስላለን አስኩዋላው መጥፎ ነው ብለን ራሳችንን እናጽናና ነው የምትለው ? የችግራችን ምንጩ ከውጭ ሳይሆን ከውስጥ ነው . የኛ ጠላት እኛ ነን . እንዲህ ያደረገን ደሞ ዘመናዊ ትምህርት ሳይሆን የዚህ እጦት ነው .

ለምን እዚያው አገርህ ሹምባሾች መንደር ድባርዋ ከበሮህን እየደለቅህ ከኢሣያስ ወፈፌው ቀጥሎ የሚያስገብርህን ሽፍታ አትጠብቅም Razz Razz Razz እኛን ኢትዮጵያውያንን አትበጥብጠን Cool Cool Cool

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Wed Dec 28, 2011 3:37 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ቤቱ

ከተነሳው ርዕሰ ጉዳይ ጋር ይገናኛልና ወንድም / ዳንኤል ክብረት በራሱ ጦማረ -ገጽ ላይ 'ኮኮነት ' በሚል የጻፈውን ቆንጆ ጽሁፍ እዚህ ላካፍላችሁ እዚህ አመጣሁት :: ሃገራዊነት የተላበሰን ንቃተ -ህሊና በመግደል ትልቅ አስተዋጽዖ የሚያደርገው ይሄው 'ኮኮነቶች ' መብዛት እንደሆነ ጽሁፉ በምሳሌ ጥሩ ይናገራል :: በተረፈ እናመሰግንሀለንና ናፖሊዮን ዳኜ የምታነሱት ሀሳብ ተስማምቶኛል :: እቴጌይት ግን ጭራሹኑ አልፈሽ ተርፈሽ የመንፈሳዊና ሞራላዊ እሴት መጋቢ የሆነችውን /ክርስቲያናችን ለተገዥነት ስሜት አስተዋጽዖ አድርጋለች ብለሽ ኮነንሻት ....ዘይግረም ! ከዚያም ቀጠልሽና ሴክዩላራይዜሽን ምዕራባዊያንን ከዚህ አላቋቸዋል ......ለኛም ሴክዩላራይዜሽን ያስፈልገናል ልትይን ነው እንግዲህ Rolling Eyes አንች ግን ሀይማኖትሽ ምንድን ነው Rolling Eyes ለሰው 'ትርጉም ያለው ህይወት ' ሲባልስ ላንች ምን ማለት ነው Question

ለማንኛውም ሊንኩና የዲያቆኑ ጽሁፍ እነሆ

http://www.danielkibret.com/2011/04/blog-post_05.html?spref=fb

ኮኮነት

ከአዲስ አበባ ወደ ሐራሬ እየተጓዝኩ ነው፡፡ ከጎኔ አንደ ደቡብ አፍሪካዊ ተቀምጧል፡፡ እርሱ ከአዲስ አበባ ወደ ሉሳካ በሐራሬ በኩል የሚጓዝ ነው፡፡ ሲያነበብበው የነበረውን መጽሔት ተዋስኩትና ማገላበጥ ጀመርኩ፡፡
አያሌ ማስታወቂያዎች ቀልብ በሚስቡ መንገድ ተደርድረዋል፡፡ መቼም ደቡብ አፍሪካውያን ማስታወቂያ መሥራት ያውቁበታል አልኩ በልቤ፡፡ ከዘጠኝ ዓመታት በፊት ኬፕታውንን ስጎበኝ ያየሁትን የቮዳፎን ካምፓኒ ማስታወቂያ አስታወሰኝ፡፡ በተራራማዋ የኬፕታውን ከተማ መሐል የቴሌፎን ካምፓኒው ቮዳፎን ‘’ this is cape town, where the clouds cover the mountains, and we cover the rest’’ ይል ነበር ማስታወቂያው፡፡ «እነሆ ኬፕታውን፣ ተራሮቿን ደመናዎች ይሸፍኗታል፤ እኛ ደግሞ ሌላውን እንሸፍናለን» እንደ ማለት፡፡
ቮዳ ፎን አዲስ አበባ ላይ ቢሆን ኖሮ የሚሰቅለውን ማስታወቂያ አስቤ ለብቻዬ ሳቅሁ፡፡ «የቴሌኮ ሙኒኬሽን አገልግሎት ለሁሉም በማዳረስ የኢትዮጵያን ሕዳሴ እናበሥራለን» ነበር የሚለው፡፡ ለምንድን ነው ? ቢሉ መፈከር እንጂ ማስታወቅ አንችልበትምና፡፡ ድሮስ ስንፈክር ስናቅራራ አይደል የኖርነው፡፡ «አስታወቁ» ብለን ዜና እንሠራለን እንጂ መቼ አስታውቀን እናውቃለን ? «ድርጅታችን ካለፈው ዓመት ይበልጥ እመርታ አሳይቷል» ብሎ መግለጫ የሰጠን ድርጅት «ባለፈው ዓመት ስንት ነበራችሁ ? ዘንድሮስ ምን ያህል ጨመራችሁ ?» ብለው ይጠይቁታል እንጂ ያላስታወቀውን «አስታወቀ» ብለው እንዴት ዜና ይሠሩለታል ? አንዳች ነገር ሳያስታውቁ «አስታወቁ» ተብሎ ዜና የሚነገርባት ሀገር ስሟ ማነው ?
ይሄንን ሁሉ እያሰብኩ ወደ መጽሔቱ ሆድ ስዘልቅ እያዘንኩ መጣሁ፡፡ የማያቸው ድርጅቶች ሁሉ የእንግ ሊዝ ወይንም የአሜሪካ እንጂ የደቡብ አፍሪካ አልመስልህ አሉ፡፡ስማቸው ሁሉ ፈረንጅ ፈረንጅ ሸተተኝ፡፡
ወደዚያ የደቡብ አፍሪካ ወዳጄ ጠጋ ብዬ «ምነው ደቡብ አፍሪካ ውስጥ አፍሪካዊ ስም የለም እንዴ ?» አልኩት እንደ መሳቅ ብዬ፡፡
«ምን ይደረግ ኮኮነቶች ናቸው እንዲህ የሚያደርጉት» አለኝ ራሱን እየነቀነቀ በቁጭት፡፡
«ኮኮነቶች ?!» አልኩ ለራሴ፡፡ እኔ ኮኮነትን የማውቀው በዘርነቱ ነው፡፡ የማወቅ ጉጉቴ ጨመረ፡፡
«ምን ማለትህ ነው ኮኮነቶች ስትል» አልኩት መጓጓቴ እንዳይታወቅብኝ ዘና ብዬ፡፡
«እኛ ውጫቸው አፍሪካዊ ሆኖ ውስጣቸው ፈረንጅ የሆኑትን ሰዎች ኮኮነት እንላቸዋለን፡፡ ኮኮነት ላዩ ጥቁር ወይንም ቡናማ ነው፡፡ ውስጡ ግን ነጭ ነው፡፡ እነዚህም ሰዎች መልካቸው ብቻ ነው አፍሪካዊ፡፡ ሌላው ነገራቸው ሁሉ ፈረንጅ ነው፡፡ የሚያስቡት እንደ ፈረንጅ፣ የሚዘፍኑት እንደ ፈረንጅ፣ የሚለብሱት እንደ ፈረንጅ፣ የሚጠሩት እንደ ፈረንጅ፣ በዓል የሚያከብሩት እንደ ፈረንጅ፣ መሆን የሚፈልጉት ፈረንጅ፣ ሁሉ ነገራቸው ፈረንጅ ነው፡፡»
«ምናልባት ዘመናዊነትን ፈልገው ከሆነስ ? መቼም ፈረንጆቹ የተሻለ ሥልጣኔ እና የአኗኗር ሥርዓት አላቸው»
«አየህ መፈርነጅ እና መዘመን ይለያያሉ፡፡ መዘመን ማለት ከማንም ካንተ ከሚበልጥ ሰው የዕድገቱን እና የሥልጣኔውን መንገድ ማወቅ እና መከተል ማለት ነው፡፡ መፈርነጅ ግን ሌላ ነው፡፡ መፈርነጅ ማለት ቢጠቅምም ባይጠቅምም፣ ቢኖርህም ባይኖርህም፣ ካንተ ጋር ቢስማማም ባይስማማም የፈረንጅ የሆነውን ሁሉ መውደድ እና መከተል ማለት ነው፡፡
«እይ እስኪ የኛ ሰዎች የወንድ ለወንድ እና የሴት ለሴት ጋብቻን እንደ መብት የሚያዩት ሥልጣኔ ነው ብለው ይመስልሃል ? ለአፍሪካስ ምን የሚፈይድላት ነገር አለ ? እነዚህ አፍሪካውያን ወገኖቻችን ይህንን ነገር የሚከተሉት መፈርነጅ ስለሚፈልጉ ብቻ ነው፡፡ አፍሪካ ውስጥ ለስም የሚሆን ነገር ጠፍቶ ነው /ቤቶቻችን፣ ምግብ ቤቶቻችን፣ መደብሮቻችን፣ ልጆቻችን፣ በፈረንጆቹ ስም የሚጠሩት ? ይህን በማድረግ ምን ዕድገት ይመጣል ? ይህንን ዘመናዊነት ትለዋለህ ? ይህኮ መፈርነጅ ነው፡፡ኮኮነትነት ነው»
ይኼኔ ወደ አገሬ በሃሳብ በረርኩ፡፡ ኒውዮርክ ካፌ፣ ዴንቨር ሬስቶራንት፣ ሲያትል ፀጉር ቤት፣ አትላንታ ጠጅ ቤት፣ ሎንደን ካፌ፣ ፓሪስ ጫት ቤት፣ ፍራንክፈርት /ቤት፣ ኦሐዮ ጫማ ቤት፣ ኦክስፎርድ ዐጸደ ሕፃናት፣ ክሊንተን ቡቲክ፣ ሎስ አንጀለስ የድለላ ሥራ፣ ዋሽንግተን ሆቴል፣ ቡሽ አሠሪና ሠራተኛ አገናኝ፣ ሆላንድ የመኪና መሸጫ፣ ቤልጅየም ሙዚቃ ቤት፣ ጣልያን ስቴሽነሪ፣ እያሉ የሰየሙት ወገኖቼ ታወሱኝ፡፡ ለካስ ኮኮነት እኛም ሀገር አለ፡፡
አሁን እነዚህ ወገኖቻችን ትንቧለል ሻሂ ቤት፣ መንዲ ምግብ ቤት፣ ገደል ግቡ ጠጅ ቤት፣ አያሌው አሠሪና ሠራተኛ አገናኝ፣ ከርክሜ ፀጉር ቤት፣ የነገዋ ኢትዮጰያ /ቤት፣ ሰላም ዐጸደ ሕፃናት፣ ዳንዲ ቦሩ /ቤት፣ ዘናጩ ቡቲክ፣ አዲስ አበባ የምግብ አዳራሽ፣ አድዋ የመኪና መሸጫ፣ ካራማራ ሙዚቃ ቤት፣ ብራና የጽሕፈት መሣርያዎች መሸጫ፣ ታማኙ የአሠሪና ሠራተኛ አገናኝ እያሉ ከሰየሙት ሰዎች ይልቅ ሠልጥነዋል ማለት ነው ? ወይስ ፈርንጀዋል ?
ኒኒ፣ ጂጂ፣ ጲጲ፣ ቲቲ፣ ኪኪ፣ ቢቢ፣ ፊፊ፣ ኤፍ፣ ዜድ፣ እየተባሉ የሚጠሩትስ እናኑ፣ ትዕግሥት፣ እጅጋየሁ፣ መገርሳ፣ ትርሐስ፣ ኦጂሎ፣ ኪሾ፣ ከሚባሉት ስሞች በላይ ዘምነዋል ማለት ነው ? አሁን የእነዚህ ሰዎች ሥራ ኢትዮጵያን እያዘመናት ነው እያፈረነጃት ? አንዳንዶችማ እነርሱ ፈርንጀው ውሻዎቻቸውንም አፈርንጀዋቸዋል፡፡
ከሐበሻ ገና የፈረንጅ ክሪስማስ ማክበር የሚቀናቸው፣ ከሐበሻ አቆጣጠር የፈረንጅ ካላንደር የሚመቻቸው፣ «እንትናዬ ድረስ»፣ «የፈጣሪ ያለህ» ከማለት ይልቅ «ኦ ማይጋድ» ሲሉ የዘመኑ የሚመስላቸው፡፡ «ኢየሱስ» ብለው ከሚጠሩ «ጂሰስ»፣ «እግዜር ይስጥልኝ» ከሚሉ « thank you´ ቢሉ የሚቀናቸው ኮኮነቶች መጡብኝ፡፡
የገና ዕለት ዳቦ የማይደፉ፣ ነገር ግን ከቀረችን 3% ዛፍ ቆርጠው የገና ዛፍ የሚሠሩ፤
«የኛ ሙሽራ ኩሪባቸው፣
በእንግሊዝ አናግሪያቸው» እያሉ የሚዘፍኑ፤ ሀገር ቤት ተቀምጠው «ልጄኮ ኦሮምኛ አይችልም፣ እንግሊዝኛ ብቻ ነው የሚናገረው» ብለው በድፍረት ሲናገሩ ኀፍረት የማይሰማቸው፤
የጋዜጣቸው ስም፣ የመጽሔታቸው ስም፣ የኤፍ ኤማቸው ስም፣ የሬድዮ ፕሮግራማቸው ስም፣ የሙዚቃ አልበማቸው ስም፣ የፊልማቸው ስም፣ የቆርቆሯቸው ስም፣ የቢራቸው ስም፣ የደብተራቸው ስም፣ የማስተ ካቸው ስም፣ የከረሚላቸው ስም፣ በፈረንጅኛ ካልሆነ የማይረኩት የኛዎቹ ኮኮነቶች ታወሱኝ፡፡
መፈርነጅ ካልሆነ በቀር አሁን በምን መለኪያ ነው «ባለ ሥልጣን» ከሚለው ይልቅ «ኤጀንሲ»፤ «የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን» ከሚለው ይልቅ «ኢትዮ ቴሌኮም» መሠልጠን የሚሆነው ? ከኢትዮጵያ ጋራዎች ኩልል ብሎ የሚወርደውን ውኃ እያሸጉ «ብራቦ»፣ «ፋንታስቲክ» «አኳ ምናምን»፣ «ሎው ላንድ ዋተር» እያሉ ውኃው ሰምቶት የማያውቀውን ስም የሚያወጡትን ኮኮነቶች አድባሯስ ምን ትላቸዋለች ?
እንጂ አሁን ማን ይሙት «ደብር» ከሚለው ይልቅ «ካቴድራል» የሚለው በምን በልጦ ነው ያለ ቦታው ድንቅር ብሎ መከራ የሚያየው፡፡ አድባራቱ ሁሉ ካቴድራል ለመባል መከራ የሚያዩት የፈረነጁ መስሏቸው እንጂ ዘመናዊነት ቢያምራቸውማ የገንዘብ አያያዛቸውን፣ የሠራተኛ አስተዳዳራቸውን፣ የንብረት አያያዛ ቸውን፣ የቅርስ አጠባባቃቸውን፣ የምእመናን አገልግሎታቸውን፣ የሰዓት አከባበራቸውን አያሻሽሉትም ነበር፡፡ አይ ኮኮነት ?
«እማዬ»፣ «አባዬ» ከሚለው ስም ይልቅ «ማዘሬ»፣ «ፋዘሬ» በምን በልጦ ነው ያገር ቋንቋ እስኪመስል ድረስ የተዋሐደን ? ኮኮነትነት ካልሆነ በቀር ?
በቀደም ቤት ልከራይ አንድ ቦታ ሄድኩላችሁ፤ ከደላሎቹ ጋር ተስማምተን ባለቤቶቹን ቀጥረን አገኘናቸው፡፡ ሰውዬው በግልጽነታቸው አመሰግናቸዋለሁ፡፡
«ይቅርታ አድርጉልኝ፣ ቤቴን ለአበሻ አላከራይም» አሉን፡፡
«ለምን» አልኳቸው ገርሞኝ፡፡
«ቤቴን በደንብ የሚይዝልኝ ፈረንጅ ነው» አሉ በድፍረት፡፡
«እንዴት መያዝ እንዳለበት የሚያስቡትን ይንገሩኝና በውላችን ውስጥ እናካትተው፤ ደግሞስ ሁሉም አበሻ በሙገባ አይዝም ሁሉም ፈረንጅ በሚገባ ይይዛል ብለው እንዴት ይደመድማሉ ? ለመሆኑ ስለ እኔ ቤት አያያዝ ምን ያውቃሉ ?» ብዬ አፋጠጥኳቸው፡፡
በመጨረሻ እንዲህ አሉኝ «ለታሪኬም ቢሆን ቤቱን ለአበሻ አከራየ ሲባልና ለፈረንጅ አከራየ ሲባል ክብሩ አንድ ዓይነት አይደለም» አሉና ኮኮነቱን ከተደበቀበት አወጡት፡፡
ምን ያድርጉ «አቶ እገሌን፣ወ / እገሊትን ተዋወቋቸው፣ ልጆቻቸው ሁሉ አሜሪካ ናቸው» ሲባልላቸው በደስታ እና በኩራት ፈገግ በሚባልባት ሀገር ቢያንስ «አቶ እገሌኮ ቤታቸውን ለፈረንጅ አከራዩት» ይባልላቸው እንጃ !!
«ሰሞኑን ጃፓኖችን አይተሃቸዋል ? የጃፓን ባለ ሥልጣናት ስለ አደጋው መግለጫ ሊሰጡ ወደ መድረክ ሲወጡ መጀመርያ ለሰንደቅ ዓላማቸው ቀጥሎ ለሌሎች ከወገባቸው ዝቅ ብለው ሰላምታ ይሰጣሉ፡፡ ያን ጊዜ መግለጫ የሚሰጡት ጃፓኖች መሆናቸውን ጆሮህ ባይሰማ እንኳን ታውቃለህ፡፡ አሁን ያንን የሚያህል የኒኩሌር ተቋም እኛ ገንብተን ቢሆን ኖሮ እንደ እነርሱ «ፉኩሺማ» እንለው ነበር ? ወይ ከአሜሪካ ወይም ከእንግሊዝ ስም እናስመጣለት ነበር እንጂ ?
ይህንን ሲናገር የበረራ አስተናጋጇ መጣችና «ምሳ ምን ልስጣችሁ ?» አለችን፡፡
«የጾም ምን አላችሁ ?» አልኳት፡፡
«ምንም የለንም» አለች፡፡
«አየር መንገዱ የኢትዮጵያ ነው፤ ዐቢይ ጾም የታወቀ ጾም ነው፤ ምናለ ሁለት ሦስት እንኳን የጾም ምግብ ቢይዙ ? አሁን ይህንን አሠራር ምን ልበለው ? ደቡብ አፍሪካዊ የተናገረኝ መጣብኝና ከአፌ መለስኩት፡፡

ሐራሬ፣ ዚምባብዌ

_________________
http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ናፖሊዮን ዳኘ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 18 Apr 2008
Posts: 1878

PostPosted: Wed Dec 28, 2011 6:45 pm    Post subject: Reply with quote

ጃፓን የደረሰችበት ደረጃ ላይ ለመድረስ ከጃፓን ህዝብ ማህበራዊ ባህላዊ እና ታሪካዊ ማንነት እና ተፈጥሮ ጋር ግንኙነት የሌለው ማህበራዊ እና ባህላዊ አስተሳሰብ ከምዕራቡ ዓለም በማጋበስ አልነበረም Idea እዚሁ መድረክ ላይ ብዙ ጊዜ ጽፌያለሁ :: ጃፓን ሴክሉዥን ፖሊሲ በመከተል ከምዕራቡ ዓለም ሳይንስን ብቻ በመውሰድ ወደ ራሷ ያየት ሀገር ናት :: የጃፓን ስኬት ሚስጥሩ ኤክሴፕሽናል አይ ኪው ወይ የተፈጥሮ ሀብት አይደለም :: ግልብነትን ገለው ያገኙትን ነገር ከማግበስበስ ተቆጠቡ :: የዛሬ አመት አካባቢ በኢንደስትሪያል ሪሌሽን ላይ አንድ አጠር ንጽጽራዊ ባህሪ ያለው ወረቀት ጽፌ ነበር :: እንደ ምዕራባውያኑ ቴንስ የሆነ ግንኙነት የላቸውም :: በስራ ቦታ ጭምር ቤተሰባዊነት ይጎላል :: አሰሪዎችም እንደዛው ነው የያዟቸው ::
በቀዳማዊ ኃይለስላሴ አልጋወራሽነት ዘመን ጀምሮ ኢትዮጵያ የጃፓንን ሞዴል በመጠቀም (ባህልን ማህበራዊ ግንኙነትን እና ማንነትን አሳልፈው ሳይሸጡ ) ሳይንሱን ብቻ በመውሰድ ኢትዮጵያን የማሳደግ እቅድ ነበረ :: በዘመን ሂደት ምዕራባውያኖቹ ጠልፈው ጣሉት ! በመጨረሻም እነ ህወሀት እና ኦነግ ተደገሱልን አሁን ደሞ የእነእቴጌ ቢጤዎች ማህበራዊ እሴታችንን እና ማንነታችንን ""አሮጌ ነው "" በማለት ለምዕራቦቹ ሊሸጡት ሊለውጡት ነው መከራ የሚያዮት ! ይቺን መናገር ከጽንፈኝነት ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም :: የሚያበሳጨኝ የእናንተ መቀየር አይደለም ! በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ መቀየር አለበት ብላችሁ የምትፈርዱት ነገር ነው የሚያበሳጨኝ !
እነ ቻይናም አሁን የደረሱበት ደረጃ የደረሱት ሊበራሊዝምን በማግበስበስ ያለ የሌለ የምዕራብ አስተሳሰብ በማግበስበስ አይደለም ! የወሰዱት የሚያስፈልጋቸውን እና ይጠቅማል ብለው ያሉትን ነው ::
ቬትናትም በምግብ ዋስትና ችግር ወጥታ በእድገት ጎዳና እየገሰገሰች ያለችው የምዕራብን አስተሳሰብ እንደወረደ አግበስብሳ አይደለም !

እናመሰግንሀለን የሰጠው ሀሳብ ያለውን ክሪቲካልነት የሚያሳይ እንጂ ትምህርት አይጠቅምም የሚል ነገር ውስጥ አልገባም ::

መጀመሪያ በህወሀት ጥቃት ፌንት ያደረገውን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ከተኛበት ይንቃ ! ያጣውን እና ያላጣውን ነገር ቀና ብሎ ትንፋሹን እየተቆጣጠረ ያስበው ! ከዚያ በኍላ ሊበራሊዝም የሚያስፈልገው ከሆነ እነቴጊትን ኮንታክት አድርጎ በአይነት እንዲያመጡለት ያደርጋል !
እኔ እየተቃወምኩ ያለሁት እዛው ፌንት ያደረገበት ላይ ሊበራሊዝም ይሻልሀል ይሄ ይሻልሀል የሚለው ነገር ነው በጣም የሚያበሳጨኝ :: ይሄንን ከጽንፈኝነት የምትቆጥሩ ካላችሁ የዘመናዊ ባንዳ የሌባ አይነ ደረቅነትን ከቁምነገር የምቆጥር አይደለሁም !

እቴጊይት ---ምዕራባውያንን እጠላለሁ ! so what?! what is the paranoia about it? የሌሎችም የዓለም አካባቢዎች እንደዚሁ ምዕራባውያንን ይጠላሉ እና ምን ይጠበስ ?? ከደረሰባቸው እና ስለ ምዕራባውያን ከሚያውቁት ነገር ተነሰተው ነው የሚጠሉት !

እሱን ትተሽ የምዕራቡ ዓለም ሊወደደ እና አስተሳሰቡን ልናግበሰብስበት የሚገባበትን ምክንያት ተናገሪ ?? ይሄንን ለመመዘን ግን በግለኝነት ላይ ተመርኩዞ አይደለም ! ማህበራዊ የሆነ ማይንድ ሴት ያስፈልጋል ::
Now, I don't respect you at all! እንደዚህ አይነት እቴጊት ኖሯትም አያውቅም ኢትዮጵያ !

ናፖሊዮን ዳኘ ::

menzewu እንደጻፈ(ች)ው:
እቴጌይት እንዲያው ልፊ ብሎሽ ነው እንጂ እውቀት የሞላውና የሚያስብ ጭንቅላት እዚህ አታገኝም . በመረጃ የተደገፈ ውይይት ሳይሆን በስሜት የሚነዳ አታካራ ነው ዋርካን የሞላው . ታሊባንና ሙላዎች ያሉት እኮ አፍጋኒስታንና ኢራን ብቻ አዪደለም . የኛም ታሊባኖችና ሙላዎች አሉ . እረ አያቶላዎችም አናጣ !!! ራቂያቸው .... አትከራከሪያቸው . የእውቀት ድንክየነታቸው ሲጋለጥባቸውና ማጣፊያው ሲያጥራቸው ምላስ ጎራዴ ይመዛሉ . ዘመናዊ ትምህርት መጥፎ ነው ለሚል ሰው ድንቁርናን ሞክረው ከማለት በቀር ምን ይባላል ?

_________________
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8  Next
Page 5 of 8

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia