View previous topic :: View next topic
Author
Message
ስርርር Joined: 05 Mar 2010 Posts: 731
Posted: Wed Jan 04, 2012 8:41 pm Post subject: ከዚያኛው መንደር
ከህሊናው ጋር የጦፈ ክርክር ይዞ ወዴት እንደሚግዋዝ እንክዋን ሳያውቀው እግሩ ወደመራው ይግዋዛል :: መንገደኛ ሁሉ ""ደህና ዋልክ ልጅ አስራት ?".ይሉና መልስ ሲያጡ ...."አልሰማኝም መሰል ?...አላወቀኝም ይሆን ?...እያሉና የጎሪጥ እያዩት ያልፋሉ :: ከመንደሩ የሚያስወጣውን ቁልቁለት እንደኤሊ ተጉዞ ከቸረሰ በህዋላ ....ትረተሩን ተከትሎ ወደጥሻው ገባ :: በጢሻው ውስጥ አቖርጦ እጁን በኪሱ እንዳደረገ ከሩቅ በአማሩ አጸዶች የተከበበውን ቤ /ክርስቲያን አስተዋለና ..... "ትንሽ ቀናትን ጠብቂኝ ፍቅሬ ....ፍቅሬ እስከመቃብር ነውና እከተልሻለሁ ::" አለ ድምፁን አሰምቶ ::
እንደምንም አዝግሞ ከቤተክርስቲያኑ ደረሰ :: ገና ከቅጥር ግቢው ሲዘልቁ ለአፍንጫ እጅጉን የሚስማማው መአዛ "ኑ ግቡ !" እያለ የሚያስተናግድ ይመስላል :: ቁመታቸው 50 ና 60 ሜትር የሚሆኑ ረጃጅም "የሀበሻ ፅድ , የወይራ , የዝግባና የዋንዛ ዛፎች ለዚያች ቦታ ምዳራዊ ገነትነትን አጎናፅፈዋታል :: አልፎ አልፎ "እውድ !" የሚያደርገው የዋንዛው አበባ ሽታ ከእጣን ጢስ ሽታ ጋር ተዋህዶ በደስታ ሲቃ ያስቃትታል ::
ወይ ተፈጥሮ እያለ ወድቆ ተሳለመ ....."ሰላም እለኪ ቤ /ክርስቲያን ቅድስት አምሳለ እየሩሳሌም ሰማያዊት , ማህደረ መለኮት " እያለ ሶስት ግዜ ሰእግዶ ተነሳ እና አረፍ አለ :: ወዲያው ትዝታ በትዝታ ፈረስ ተጭና እንደገና ብቅ አለች !
"አስራትዬ የኔ ጌታ ...በምን አቅሜ ልቻለው ....የጫኑብኝ ድንጋይ እኮ ትልቅ ነው " ስትለው ተሰማው ::ሳያስበው ....ድምፁን ከስፍ አድርጎ ማልቀስ ጀመረ ::
"አይዞህ ልጄ ! ....እመቤታችን ጠሎትህን ትስማህ !" አሉ አንዲት እማሆይ ከወደ ቀኝ በኩል ......ሌላዋ ደግሞ "አይ መልክ ...አይ ቁመና ....አሁን ይህን የመሰለ ጠንበለል እንዲህ ሆኖ ይቅር ?..
እጁን በኪሱ እንዳደረገ ...በቤ /ክርስቲያኑ የግዋሮ በር አድርጎ ወደመቃብር ግቢ ዘለቀ ::...ወደሙታን መንደር :: እንባው በአይኑ ረብቦ አቆርዝዟል :: የትዝታን መቃብር ፍለጋ ! የሚስቱን ....የግራጎኑን ማረፊያ ፍለጋ .....ባዛነ ::
የመቃብር ግቢው ...ትልቅ መንደር ይመስላል :: እዚህም እዚያም ሀውልቱ ተደርድሯል :: ሙታንም በቕንቕቸው ያወራሉ ::....እዚህ ግቢ ውስጥ ያለው መንፈስ ትንሽ ያስጨንቃል ::
አስራት በየሃውልቶች ላይ የተፃፉትን ፅሁፎች እያነበበ ...የትዝታን መፈለጉን ተያያዘው ::
አንዳንዱ ጽሁፍ እንዲህ ይላል ....."ሩጫዬን ጨርሻለሁ ...የክብር አክሊል ይጠብቀኛል " ሌላው ደግሞ ...."ደግ ሰው ስራው ህያው ነው " ....ጀግና ነበርኩ !
አንዳንዱ ደግሞ ግጥም ይመስላል
ለምሳሌ
እዚህች ቦታ ላይ ነጭ እርግብ አርፋለች ....
ቀስ ብለው ይለፉ ትደነግጣለች "
ሌላው ደግሞ .....አቶ እገሌ በ 19-- ተወልደው ...አረፉ :: ይህንን መታሰቢያ ቤተሰቦቻቸው አሰሩላቸው ......""
አስራት ..."እንደው ከዚያኛው መንደር እውን ሙታን ተግባብተው ያወሩ ይሆን ? እኛስ የመቃብር ላይ ፅሁፎችን አሰባስበን ስርአትና ደንብ ሰርተንላቸው ከስነፅሁፍ ተርታ መመደብ እንችል ይሆን ?....." ከጨቅጫቃው ህሊናው ጋር ክርክር ሊጦፍ ሲል .....የትዝታን አየው :: ና የኔ ጌታ እዚህ ነኝ ....የሚል ድምፅ የሰማ መሰለው ::...........
ተፈፀመ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ስርርር Joined: 05 Mar 2010 Posts: 731
Posted: Fri Jan 13, 2012 8:43 pm Post subject:
አሜኬላ !!! ለዋርካ እድምተኞች
ሰለሞን ከኢትዮ ወደአሜሪካ ከመጣ 3 ዓመታትን አስቆጥሯል :: ሀገር ቤት በተክሊል ያገባት ሚስቱን እና በአይኑ ያላየውን ልጁን (እሱ እዚህ ሀገር ከመጣ በ 6ኛ ወር የተወለደ ልጁን ) እናቱን እና አባቱን ሁልግዜ ይናፍቃል :: በተስፋም ይኖራል :: አሁን የሚሰራውን ስራ ከመጀመሩ በፊት ያልሰራው የስራ አይነት የለም :: ይሄን የሴኩሪቲ ስራ ከጀመረ አንድ 6 ወር ሆኖታል :: በአንድ ትልቅ የመብራት ሀይል ካምፓኒ ውስጥ የመግቢያ በሩ ላይ ካለው ትልቅ ጠረጴዛ ላይ ተጎልቶ ለአላፊ አግዳሚው ሲፈግግ ነው የሚውለው :: ያውም ጉንጩን እስቲያምመው ድረስ ::
ሰሞኑን ግን አንዲት ሐበሻ አይቶ ዘፈኑ ሁሉ .....
"አስተውዬ አይቼ ...አመልማሎ ገላ
አፍርስ አፍርስ አለኝ ያን ሁሉ መሃላ " ሆኗል :: የተክሊሉን መሀላ መሆኑ ነው :: ይቺ ጠጋ ጠጋ ...እቃ ለማንሳት ነው ! ብለው የለ አበው ::
እንዲሁ እንደቀነዘረብኝ ከምኖር እሲት ላስታግሰው ብሎ ወስኗልና ልጅትን ለቀም አድርጎ ያዛት :: በጣም ደንግጣ ኖሮ "ሊቭሚ አሎን ...." ብላ በያዘችው ቦርሳ ............
ለማንኛውም ለመጀመሪያ ግዜ መሆኑ ነው :: የሌላ ግላ ሊያቅፍ ነው :: በ 3 አመት ውስጥ :: ይህንን ለዋርካውያን ንገርልኝ ስላለኝ ነው ወደዚህ ማምጣቴ !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ፀዋር Joined: 16 Feb 2010 Posts: 481
Posted: Fri Jan 13, 2012 9:59 pm Post subject:
ስርርር ጭሱ አሪፍ ስቶሪ ነው . Much better than (አምላክህ ) Yohhanis Kema's Story
Greetings to you, Okelo & Wagaye Kefyalew
ስርርር እንደጻፈ(ች)ው : አሜኬላ !!! ለዋርካ እድምተኞች
ሰለሞን ከኢትዮ ወደአሜሪካ ከመጣ 3 ዓመታትን አስቆጥሯል :: ሀገር ቤት በተክሊል ያገባት ሚስቱን እና በአይኑ ያላየውን ልጁን (እሱ እዚህ ሀገር ከመጣ በ 6ኛ ወር የተወለደ ልጁን ) እናቱን እና አባቱን ሁልግዜ ይናፍቃል :: በተስፋም ይኖራል :: አሁን የሚሰራውን ስራ ከመጀመሩ በፊት ያልሰራው የስራ አይነት የለም :: ይሄን የሴኩሪቲ ስራ ከጀመረ አንድ 6 ወር ሆኖታል :: በአንድ ትልቅ የመብራት ሀይል ካምፓኒ ውስጥ የመግቢያ በሩ ላይ ካለው ትልቅ ጠረጴዛ ላይ ተጎልቶ ለአላፊ አግዳሚው ሲፈግግ ነው የሚውለው :: ያውም ጉንጩን እስቲያምመው ድረስ ::
ሰሞኑን ግን አንዲት ሐበሻ አይቶ ዘፈኑ ሁሉ .....
"አስተውዬ አይቼ ...አመልማሎ ገላ
አፍርስ አፍርስ አለኝ ያን ሁሉ መሃላ " ሆኗል :: የተክሊሉን መሀላ መሆኑ ነው :: ይቺ ጠጋ ጠጋ ...እቃ ለማንሳት ነው ! ብለው የለ አበው ::
እንዲሁ እንደቀነዘረብኝ ከምኖር እሲት ላስታግሰው ብሎ ወስኗልና ልጅትን ለቀም አድርጎ ያዛት :: በጣም ደንግጣ ኖሮ "ሊቭሚ አሎን ...." ብላ በያዘችው ቦርሳ ............
ለማንኛውም ለመጀመሪያ ግዜ መሆኑ ነው :: የሌላ ግላ ሊያቅፍ ነው :: በ 3 አመት ውስጥ :: ይህንን ለዋርካውያን ንገርልኝ ስላለኝ ነው ወደዚህ ማምጣቴ !
_________________ I have great faith in fools; self-confidence my friends call it.