WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home | About us | Advertise with us | Contact us
28ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ -ኢኳቶሪያል ጊኒ እና ጋቦን
Goto page Previous  1, 2, 3  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Mon Jan 30, 2012 9:14 pm    Post subject: Reply with quote

ሰኞ ጥር 21 ቀን 2004 ..

በዚህ የአፍሪቃ ዋንጫ ውድድር እንደዛሬው ግጥሚያዎች ድራማ የበዛበት አላየሁም :: በመጀመሪያው ግማሽ ኮት --ቯር እና ሱዳን በተመሣሣይ 33ኛው ደቂቃ ጎል አስቆጠሩ :- ሱዳን 17 ቁጥሩ ሙዳቲር አልጣይብ ኢብራሒም : ኮት --ቯር ደግሞ በቀድሞው የአርሴናል (አሁን የቱርኩ ጋላታሣራይ ) ተጨዋች በሆነው 21 ቁጥሩ ኢማኑኤል ኢቡዬ :: ሁለተኛው ግማሽ ሱዳን ቡርኪናፋሶን : ኮት --ቯር አንጎላን ተጭነው አጥቅተው ተጫወቱና ኮት --ቯር ቀድሞ በአንጎላ ላይ 65ኛው ደቂቃ 12 ቁጥሩ ዊልፍረድ ጉዬሚያንድ ቦኒ ግሩም ጎል አስቆጠረ :: 15 ደቂቃ በኋላ የሱዳን በረኛ በረዥሙ የለጋትን ኳስ ልማደኛው 17 ቁጥሩ ሙዳቲር በአንድ ምት የተለጋውን ኳስ ቀድሞ አገኘና የቡርኪና ፋሶን በረኛ አታልሎ ጎል አገባ :: ጨዋታው በዚህ ውጤት ይጠናቀቃል ተብሎ ሲጠበቅ ቡርኪና ፋሦ በተጨማሪው ሰዓት የመጨረሻ ደቂቃ (97ኛው ደቂቃ ) 20 ቁጥሩ በኢሣካ ኢዌድራጎ ጎል አስቆጥሮ በዜሮ ከመሸነፍ አመለጡ ::

በዚህ ውጤት መሠረት ኮት --ቯር እና ሱዳን 1 እና 2 ሆነው ለሩብ ፍጻሜ ለማለፍ ችለዋል :: በሩብ ፍጻሜ ኮት --ቯር ከአዘጋጇ አገር ኢኳቶሪያል ጊኒ : እንዲሁም ሱዳን ከዛምቢያ ይጋጠማሉ ::

እስከዚያ በነገው ዕለት በሚደረጉት የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ውድድሮች እንዝናናለን :- ነገ ማክሰኞ ጥር 22 ቀን 2004 ..
ጋቦን ከቱኒዚያ
ሞሮኮ ከኒጀር

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed Feb 01, 2012 9:59 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም የእግር ኳስ አፍቃሪዎች :-

የአፍሪቃ ዋንጫ የመጀመሪያው የዙር ውድድር ተጠናቀቀ : ከሦሥት ቀናት ዕረፍት በኋላ ቅዳሜ ጥር 26 ቀን 2004 .. የሩብ ፍፃሜው ውድድር ይጀመራል ::

የትላንቱን ጨዋታዎች አላየሁም - ምክንያት አላፊዎቹ ቡድኖች ጋቦን እና ቱኒዚያ ስለታወቁ ቀሪው የማስተካከያ ጨዋታ ለደረጃ ምደባ ብቻ ስለነበረ :: ውጤቱ የሚከተለውን ይመስላል :-

ጋቦን 1 - ቲኒዚያ 0
ሞሮኮ 1 - ኒጀር 0

የዛሬው ጨዋታዎች በሥሌት ደረጃ አራቱም ቡድኖች የማለፍ ዕድል ስለነበራቸው አጓጊ ነበር :: ጨዋታዎቹም ጥሩ የሚባሉ ነበሩ :: ጋና እና ጊኒ ከኃይል ይልቅ በአጭር የጥልፍልፍ ቅብብል የታጀበ ጨዋታ አሣይተዋል :: አብዛኛውን የጨዋታ ጊዜ ጊኒ ያጠቃ ነበር : ሆኖም ቀድሞ ጎል ያገባው ጋና 8 ቁጥሩ በኢማኑኤል አጊዬማንግ ባዱ አማካይነት 28ኛው ደቂቃ ላይ ነበር :: ከዕረፍት በፊት ጊኒ ይበልጥ ጫና ፈጥሮ በመጫወቱ በመጀመሪያው ግማሽ ጭማሪ ሰዓት ውስጥ 2ኛው ደቂቃ ጎል አስቆጥሯል :: ለጊኒ ጎሉን ያገባው 7 ቁጥሩ አብዱል ራዛጉሪ ካማራ ነበር :: ከዕረፍት መልስ ጊኒ እያጠቃ : ጋና በመልሶ ማጥቃት እያሸበረ እስከ 70ኛው ደቂቃ ጨዋታው ዘለቀ :: 70ኛው ደቂቃ የጊኒው 4 ቁጥር ማማዱ ዱዋልዴ ለሁለተኛ ጊዜ ቢጫ ካርድ የሚያሠጥ ጥፋት በመሥራቱ ከሜዳ በቀይ ተባረረ :: ከዚያ በኋላ ጨዋታው ቀዝቅዛ እና በመፈራራት ላይ ያተኮረ የመልሶ ማጥቃት ሥልት ብቻ የሚታይበት ሆኖ ሁለቱም ቡድኖች በእኩል 1 - 1 ጎል ጨዋታቸውን ጨርሠዋል ::

ሌላኛው የምድቡ ግጥሚያ የማሊ እና ቦትስዋና ጨዋታ ነበር :: ቦትስዋና በዚህ ውድድር አንድም ጨዋታ ያለማሸነፋቸውና በጊኒ 6 1 መሸነፋቸው የቆጫቸው በሚመሥል ሁኔታ ጥሩ ሲያጠቁ ይታዩ ነበር :: እስከ ዕረፍት 0 0 ሆኑና ከዕረፍት መልስ ቦትስዋና አስቀድሞ 50ኛው ደቂቃ 19 ቁጥሩ ሞጋኮሎዲ ኒጌሌ አማካይነት ለቡድኑ የመጀመሪያዋንም የመጨረሻዋንም ጎል አስቆጠረ :: ይህንን ውጤት ለመቀልበስ ማሊ ይበልጥ ተጭኖ በማጥቃቱ ሁለት ጎሎች አከታትሎ አስቆጠረ :- የመጀመሪያውን 11 ቁጥሩ ጋራ ደምበሌ 56ኛው ደቂቃ እንዲሁም ሁለተኛውን 75ኛው ደቂቃ በሠይዱ ኬይታ አማካይነት :: ስለዚህ ማሊ ቦትስዋናን 2 1 በማሸነፉ ለሩብ ፍፃሜ ማለፉን አረጋግጧል ::

በዚህ መሠረት ቅዳሜ ለሚጀመረው የሩብ ፍፃሜ ውድድሮች ያለፉት ተጋጣሚ ቡድኖችና የውድድሩ መርኃ -ግብር የሚከተለውን ይመሥላል ::

ቅዳሜ ጥር 26 ቀን 2006 ..
1 ..... ዛምቢያ ከሱዳን

2 ..... ኮት --ቯር ከኢኳቶሪያል ጊኒ

እሑድ ጥር 27 ቀን 2004 ..
3 ..... ጋቦን ከማሊ

4 ..... ጋና ከቱኒዚያ

ማን ወደ ዋንጫ ያመራ ይሆን Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጌታ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Apr 2005
Posts: 3486
Location: ዶሮ ተራ

PostPosted: Wed Feb 01, 2012 10:12 pm    Post subject: Reply with quote

ልጅ ተድላ

ጨዋታውን የመከታተል ምንም ዕድል ባይኖረኝም ያንተን ፖስቶች በጉጉት እየተከታተልኩ አነባለሁ :: ኢትዮጵያዊያን ለጋና እና ለጋና ፉትቦል ፍቅር ቢኖረንም ባንድ ወቅት አጨዋወታቸው የወደድኳቸው ጋቦኖች ዋንጫውን ቢበሉ ደስ ይለኛል ::
_________________
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed Feb 01, 2012 10:25 pm    Post subject: Reply with quote

ጌታ እንደጻፈ(ች)ው:
ልጅ ተድላ

ጨዋታውን የመከታተል ምንም ዕድል ባይኖረኝም ያንተን ፖስቶች በጉጉት እየተከታተልኩ አነባለሁ :: ኢትዮጵያዊያን ለጋና እና ለጋና ፉትቦል ፍቅር ቢኖረንም ባንድ ወቅት አጨዋወታቸው የወደድኳቸው ጋቦኖች ዋንጫውን ቢበሉ ደስ ይለኛል ::

ሰላም ጌታ :-

ጋቦን ለዋንጫ ለመድረስ የተሻለ ዕድል አለው : ምክንያቱም ጋቦን በሩብ ፍፃሜ ካሸነፈ የሚገጥመው ከዛምቢያና ሱዳን አሸናፊ ጋር ይሆናል : ከዚያ ካሸነፈ ለዋንጫ ደረሰ ማለት ነው :: በሌላ ወገን ደግሞ ጋና ቱኒዚያን ካሸነፈ የሚጋጠመው ከኮት --ቯር እና ኢኳቶሪያል ጊኒ አሸናፊ ጋር ይሆናል :: ለጋና በሁለቱም ውድድሮች ማሸነፍ ከባድ ይሆኑበታል : በተለይ ደግሞ በአሁኑ አቋማቸው ኮት --ቯርን ማሸነፍ ለማንም ቡድን ከባድ ነው :: የእግር ኳስ ውጤት ሁሌም ከመጨረሻዋ ፊሽካ በኋላ የሚታወቅ ስለሆነ አንተ እንደጠበቅኸው እንግዲህ አንደኛው አዘጋጅ አገር (ጋቦን ) ካሸነፈ በዚህ የአፍሪቃ ዋንጫ ውድድር አንድ ተጨማሪ አዲስ ዋንጫ የሚያነሣ ቡድን ይገኛል ማለት ነው :: አብረን እናያለን ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጥልቁ 1

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Jan 2004
Posts: 1560
Location: bhutan

PostPosted: Thu Feb 02, 2012 11:03 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ተድላ ሀይሉ :
እስከአሁን እንደተመለከትሁት ከሆነ እና የውድድሩም አቅጣጫ እንደሚየመለክተው ... ጋና እና አይቮሪኮስት ለዋንጫ የሚደርሱ ይመስለኛል :: በጭዋታ ስልታቸው ግን ሁሉም ቡድኖች የተመጣጣኝነት ባህርይ ይስተዋልባቸዋል ::

በተለይ ከላይ የገለጽኋቸው ሁለቱ ቡድኖች ለዋንጫ ከደረሱ ... ጋና ዋንጫውን ይበላዋል የሚል እምነት አለኝ ::

Idea
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message MSN Messenger Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sat Feb 04, 2012 11:57 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም የእግር ኳስ አፍቃሪዎች :-

ሰላም ጥልቁ :-
የጠበቅኸው የዋንጫ ጨዋታ በእርግጥ የጋና እና ኮት --ቯር መሆኑን በጥቂት ቀናት እናውቃለን :: እስከዚያው ድረስ ጨዋታችንን እንኮምኩም ::

የዛሬዎቹን ጨዋታዎች ሙሉ በሙሉ የመከታተል ዕድሉ አላጋጠመኝም :- በተለይ የዛምቢያና ሱዳንን ግጥሚያ :: የሁለተኛው ጨዋታ የመጀመሪያ ግማሽ በሥርጭት መቋረጥ ምክንያት ማዬት የቻልኩት የተወሠኑትን የመጨረሻ ደቂቃዎች ብቻ ነበር :: ሆኖም 'Replay' ድሮግባ የሣተውን የፍጹም ቅጣት ምት (ሬጎሪ ) እና 32ኛው ደቂቃ ያገባውን ጎል ዐይቻለሁ :: ሁለተኛው ግማሽ እንደተጀመረ የአዘጋጇ አገር ኢኳቶሪያል ጊኒ ተጫዋቾች በጥሩ ቅብብል የኮት --ቯሮችን የማጥቃት እንቅስቃሴ መገደብ ችለው ነበር :: ነገር ግን 65ኛው ደቂቃ በኋላ ኮት --ቯሮች ይበልጥ ተጭነው በማጥቃታቸው ሁለት አሪፍ ጎሎች አገቡና ጨዋታው 3 0 አለቀ :: ድሮግባ በዛሬው ጨዋታ 2 ጎል አግብቶ የኮከብ ግብ አግቢነቱን ሽልማት ለማግኘት ዕድሉን አሥፍቷል :: ስለ ግጥሚያዎቹ አጠር ያሉ የቪዲዮ መረጃዎች ....

ምንጮች :-
1 ..... ዛምቢያና ሲዳን (3 0)

2 ..... ኮት --ቯርና ኢኳቶሪያል ጊኒ (3 0)

እስካሁን ለሩብ ፍፃሜ ከደረሡት ቡድኖች ውስጥ ከሁለት በላይ ጎል ያስቆጠሩ ተጫዋቾች :-

1 ..... ቴቢሊ ዲዲዬር ኢቪስ ድሮግባ (ኮት --ቯር )___2 (.ጊኒ ) + 1 (ሱዳን ) = ጠቅላላ 3 ጎሎች
2 ..... ኢማኑኤል ማኩያ (ዛምቢያ )_______________1 (ሴኔጋል ) + 1 (ሊቢያ ) = ጠቅላላ 2 ጎሎች
3 ..... ክሪስቶፈር ካቶንጎ (ዛምቢያ )_______________1 (ሊቢያ ) + 1 (.ጊኒ ) + 1 (ሱዳን ) = ጠቅላላ 3 ጎሎች
4 ..... ፒዬር ኤመሪክ ኦባሚዬክ (ጋቦን )____________1 (ኒጀር ) + 1 (ሞሮኮ ) + 1 (ቱኒዚያ ) = ጠቅላላ 3 ጎሎች
5 ..... የሱፍ ምሣክኒ (ቱኒዚያ )___________________1 (ሞሮኮ ) + 1 (ኒጀር ) = ጠቅላላ 2 ጎሎች

እኒህ ናቸው ::

በዛሬው ጨዋታዎች ሁለቱም ግጥሚያዎች በእኩል 3 0 ማለቃቸው ገርሞኛል ::

ነገ ደግሞ :-

ጋቦን ከማሊ
ጋና ከቱኒዚያ

የሚያደርጓቸውን ግጥሚያዎች እናያለን :: የነገ ሰው ይበለን ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sun Feb 05, 2012 10:45 pm    Post subject: Reply with quote

እሑድ ጥር 27 ቀን 2004 ..

የአፍሪቃ ዋንጫ የድሮውን የተራዘመ ጨዋታዎች የሚያስታውሡን የዛሬው ግጥሚያዎች ናቸው :: ጋቦን እና ማሊ 120 ደቂቃ የጨዋታ ጊዜ 1 1 በመሆናቸው ወደ ፍጹም ቅጣት ምት ተሸጋገሩና ጋቦን አንዷን በመሣቱ ተሸነፈ :: በእርግጥ በጨዋታም ማሊ የበለጠ አጥቅቶ ተጫውቷል :: ጋና እና ቱኒዚያም ልክ እንደ እነ ማሊ 90ውን ደቂቃ 1 1 ውጤት ሰለጨረሱ ወደ ተጨማሪ ጊዜ ሄዱ :: በጭማሪው ሰዓት 101 ደቂቃ ላይ ጋና በተቀያሪው ሁለተኛ አምበል አንድሬይ አዩ (የአቤዲ ፔሌ ልጅ ) አማካይነት ጎል አስቆጥሮ ከመለያ ቅጣት ምት ተርፏል ::

ጋቦን 1 - ማሊ 1 (መለያ ምት ጋቦን 4 - ማሊ 5)
ጋና 2 - ቱኒዚያ 1

የቱኒዚያ ተጫዋቾች በዳኛው ንዝህላልነት እየታገዙ አያሌ አስቀያሚ ፋዎሎችን ሲሠሩ ነበር :: በተለይ በጭማሪው ሰዓት ያሣዩት ባሕርይ በጣም አስቀያሚ ነው ::

እንግዲህ ሩብ ፍጻሜው ተጠናቋል :: በመጪው ረቡዕ ጥር 30 ቀን 2004 .. የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ይደረጋሉ ::
ጋና ከዛምቢያ (ባታ - ኢኳቶሪያል ጊኒ )
ኮት --ቯር ከማሊ (ሊበርቪል -ጋቦን )

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጌታ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Apr 2005
Posts: 3486
Location: ዶሮ ተራ

PostPosted: Mon Feb 06, 2012 10:17 pm    Post subject: Reply with quote

ጋቦን በፍጹም ቅጣት ምት መሸነፉ ቅር ብሎኛል :: ነገር ግን የቀሩት አራቱም ቡድኖች ከሰሜን አፍሪካ አለመሆናቸው ጥሩ ነው :: አንድ ወቅት ግብጾች ለዓለም ዋንጫ ኳሊፋይ አድርገው 'ለአፍሪካ ሳይሆን ለመካከለኛው ምሥራቅ ክብር ነው የምንጫወተው ' ብለዋል ተብሎ በኛ ዜና ማሰራጫ ከሰማሁ ወዲህ ሰሜን አፍሪካዎች በሌሎች አቅጣጫዎች ሲሸነፉ ደስ ይለኛል ::

አሁን ግን በስተርጅና ሳስበው ምናልባት ግብጾች ያሉት 'የምንጫወተው ለአፍሪካ ክብር ብቻ ሳይሆን ለመካከለኛውም ምሥራቅ ጭምር ነው ' ይሆናል :: ወይ እኔ አዛብቼ ሰምቻለሁ ወይ ጋዜጠኛው አዛብቶ ተርጉሟል ወይም እውነት ብለዋል :: ያም ሆነ ይህ ስሜቴን አይቀይረውም :: አሁን የበረታ ይብላ :: ጋናና ኮትዲቯር ከናንተ እንደሰማሁት ተሥፋ አላቸው ::
_________________
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
ጥልቁ 1

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Jan 2004
Posts: 1560
Location: bhutan

PostPosted: Wed Feb 08, 2012 7:33 pm    Post subject: Reply with quote

ጋና ተሰናበተ የማሊን ማሸነፍ ተስፋ በማድረግ ... ቀጣዩን 30 ደቂቃ እጠባበቃለሁ ::

ጌታ ... ይቅርታ አድርግልኝና የፈለገ ቢፈጠር ... ለሰሜን አፍሪካ አገሮች እንኳንስ መደገፍ ቀርቶ ... መሳተፋቸውም ያናድደኛል :: ሊቢያ በአንድ የዐለም ዋንጫ ወቅት ; ካሜሩን እንዳያልፍ ለፈርንሳይ መልቀቋንም በታሪክ የሰማሁ ይመስለኛል :: እራሳቸውን እንደአፍሪካዊ የማይቆጥሩ ሰዎች እንዴት የአፍሪካ ዋንጫ እንደሚገባቸው አይገባይኝም ::

Idea
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message MSN Messenger Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed Feb 08, 2012 10:05 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም የእግር ኳስ አፍቃሪዎች :-

ሰላም ጌታ :-
ግብፆችም ሆነ በአጠቃላይ የሰሜን አፍሪቃ ልውጥ አረቦች አፍሪቃውያን ነን አይሉም - አረቦች ነን ነው የሚሉት :: በአፍሪቃ ዋንጫ ደግሞ አንድ ኢሣ ሃያቱ የሚሉት እንቅልፋም የካሜሩን ሰው አስቀምጠው ይኼን ያህል ዓመት የሌላውን አፍሪቃ እግር ኳስ አቀጭጨው ይኖራሉ :: እኔ ምንጊዜም ቢሆን ግብፆች ያሉበት ውድድር የማጭበርበር እንደሚሆን አጠረጥራለሁ :: ዘንድሮ ተመልከት እነርሱ ስለሌሉበት ምን ያህል አሥደሣች ጨዋታዎች እንዳየን ::

ጥልቁ :-
ምነው ጋና ተሸነፈ ብለህ ስለ ጨዋታው ምንም ሣትለን ቀረህ Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes አይዞን ዛምቢያም ቢሆን የኛው ናቸው እንዲያውም የተገፉ ተጫዋቾች ስለሆኑ ዋንጫውን እነርሱ ቢበሉት እመርጣለሁ ::

የዛሬውን የመጀመሪያ ግጥሚያ ባለማዬቴ ቅር ብሎኛል :: ሁለተኛው ግጥሚያ ግን የአፍሪቃ እግር ኳስ የደረሠበትን ደረጃ የሚያመለክት ሥለሆነ በትኩረት ተከታትዬዋለሁ :: ኮት --ቯት እያጠቃ ማሊ እየተከላከለ 90 ደቂቃው አልቋል :: በግብ ሙከራ ኮት --ቯር 10 ቢሞክር ማሊ ጎል መድረስ የሚችለው አንዴ ብቻ ነበር :: የአርሴናሉ የመሥመር ተጫዋች ጀርቪ ያሆ 44ኛው ደቂቃ ከራሱ ሜዳ የተላለፈለትን ኳስ ከግማሽ ሜዳ ጀምሮ በፍጥነት ኳሷን በመንዳት ጎል አስገብቷል :: እጅግ የሚያስገርም ፍጥነት ያለው ልጅ ነው :: የማሊ ቡድን በጨዋታ መበለጥ ብቻ ሣይሆን ጎል ሊያገቡ የሚችሉበትንም አጋጣሚዎች በተደጋጋሚ አልፈጠሩም :: እንግዲህ እሑድ የካቲት 4 ቀን 2004 .. ለዋንጫ ዛምቢያ ከኮት --ቯር ይፋለማሉ :: በዋዜማው ቅዳሜ ማሊ ከጋና ለደረጃ ይጫወታሉ ::

ቸር እንሠንብት ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed Feb 08, 2012 11:07 pm    Post subject: Reply with quote

ከአፍሪቃ ዋንጫ የታሪክ ማኅደር

የዛሬ 20 ዓመት በሴኔጋል በተደረገው 18ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ በምድብ ማጣሪያ በምድብ '' ውስጥ ዛምቢያ እና ጋና ከግብፅ ጋር ተደልድለው ነበር :: ሁለቱም ቡድኖች ግብፅን 1 0 አሸንፈዋል :: በምድባቸው የመክፈቻ ውድድር የተገናኙት ጋና እና ዛምቢያ ነበሩ :: በዚያ ጨዋታ የጋናው 10 ቁጥር አቤዲ ፔሌ ባስቆጥራት አንድ ጎል ጋና አሸንፏል ::
ምንጭ :- Uploaded by rameco89 on Jul 29, 2009. CAN 92 18th Cup of Nations, Group D - Ghana V Zambia.

በዘንድሮው 28ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ ደግሞ ዛምቢያና ጋና በግማሽ ፍፃሜ ውድድር ተገናኝተው አሸናፊው ዛምቢያ ሆኗል - በተመሣሣይ 1 0 ውጤት ::
ምንጭ :- Uploaded by TheNewHipHopSongsTv on Feb 8, 2012. Zambia VS Ghana 28th African Nations Cup 2012 Semifinals [Full highlights].

ዘንድሮ በጋና ቡድን ውስጥ ሁለት ወንድማማቾች የመስመር አጥቂዎች ሆነው ይጫወታሉ :- እነርሱም የአቤዲ ፔሌ ልጆች 'አንድሬይ አየው ' እና 'ጆርዳን አየው ' ናቸው :: አባታቸው በአፍሪቃ ዋንጫ በተደጋጋሚ የጋናን ቡድን ወክሎ ተጫውቷል : ልጆቹ የሚጫወቱበት ቡድን ዘንድሮ ዋንጫ መብላት ባይቀናውም እነርሱ ግን ቡድናቸውን ጥሩ አንቀሣቅሠዋል ::

20 ዓመት በፊት 18ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ የጥሎ -ማለፍ ዙር ዛምቢያን ከውድድር ያስወጣው ኮት --ቯር ነበር :- በጭማሪ ሰዓት በተቆጠረች አንድ ጎል :: ዘንድሮ ደግሞ ዛምቢያና ኮት --ቯር ለዋንጫ ተፋጥጠዋል :: ማን ያሸንፍ ይሆን Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes

ኮት --ቯሮች ለመጀመሪያም ለመጨረሻም ጊዜ ዋንጫ ያነሱት በዚያው 18ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ ውድድር ነበር :: በፍጻሜው ከጋና ጋር ተጋጥመው በመደበኛውም ሆነ በጭማሪው ሰዓት 0 0 በመውጣታቸው በፍጹም ቅጣት ምት አሸናፊው ተለይቷል :: ሁለቱም 12 : 12 ጊዜ ፍጽም ቅጣት ምት መትተው ጋና ሁለቱን ሲስት (አሣሬና ባፎዬ ) ኮት --ቯር አንዱን ብቻ መበሣቱ (ቲዬሂ ) 11 10 ውጤት አሸንፎ ዋንጫ በልቷል :: ከዚያ በኋላ ኮት --ቯር 6 ዓመት በፊት ግብፅ ላይ በተደረገው 25ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ ለዋንጫ ሽሚያ ከግብፅ ጋር ተጋጥመው በመለያ የፍጹም ቅጣት 4 2 ተሸንፈው ዋንጫ አጥተዋል :: ዘንድሮስ ይሣካላቸው ይሆን Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጥልቁ 1

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Jan 2004
Posts: 1560
Location: bhutan

PostPosted: Thu Feb 09, 2012 6:53 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ተድላ፡
በጋና መሸነፍ ክፉኛ እንደተናደድሁ ነኝ። ያው ዛምቢያዎችም የኛው ወንድሞች ቢሆኑምና በተለይም አንተ እንዳልኸው የተገፉ ከመሆናቸው አንጻር ብቻ ሳይሆን ያኔ በአውሮፕላን አዳጋ ላልቁባቸው ተጫዎቾች ሁሉ መታሰቢያ ዋንጫ ቢበሉ ምኞቴ ነው። የጋናው የቆጨኝ ለምን መሰለህ ? በአለም ዋንጫ ላይ በግፍ መሸነፋቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ሲሆን በተለይ ግን ጋናን በግፍ ያሸነፈው ኡራጋይ የኮፕ -አሜሪካ ዋንጫ ባለቤት ለመሆኑ ከጋና የነጠቁት የግፍ ድል አስተዋጾ አድርጓል ብየ አምናለሁ። እንደመታደለም በለው እንዳለመታደል ጭንቅላቴ ነገሮችን ያይዛል። ሱራዝ የሚሉት መጥፎ የኦራጋይ ተጫዋች (የጋናን ጎል በጁ ያስቀረ ገጦ ) ባለፈው ሁሉ የቅጣት ናዳ ሲጣልበት (ኤቭራን ለተሳደበበት ) አንጀቴ ነበር የራሰው።

እናም ጋና ለዚህ ዋንጫ ቢበቃ እጅግ ደስ ባለኝ ነበር። ሌላም ምክንያት አለኝ የዛሬ ሁለት አመት ጋና በግብጽ ሲሸነፍ በጨዋታ ግን ምን ያህል ብልጫ ያሳይ እንደነበረ ከአይኔ ላይ አለ። አቦ ጋናን የምደግፍበት ምክንያቴ መብዛቱ ዋናው የድጋፌ ምንጭ ግን ከአፍሪካ አገሮች የኛን ሰንደቅ አላማ የሚጋሩንን ሁሉ እወዳቸዋለሁ። ማኢሊዎች ለብሰው የሚገቡትን ማሊያ አየህልኝ ?! የኛ ሰንድቅ አላማ (ለዛውም አምብሻው የሌለበት ) ደረታቸው ላይ ተነጥፎ ሳየው እንዴት ደስ እንደሚለኝ።

በተረፈ የጋና እና የዛሚቢያ ጨዋታ እንደኮትዲቫር እና ማሊው አያምርም። ከአንተ ጋር የማልስማማው ግን በጨዋታ ኮትዲቫሮች በልጠዋል በሚለው ነው። ለኔ ማሊዎች ፍጹም የተልየ ብቃት አሳይተዋል። እንዴውም በዚህ ቶርናመንት ብዙም ያላየሁን አይነት ጌጣጌጥ ጨዋታ ሁሉ ያሳዩኝ እነሱ ናቸው።

ፔሌ ቀንደኛ የኮትዲቫር ደጋፊ ቢሆንም ሜዳ ላይ በማየቴ ደስ ብሎኛል…

እኔ የምለው ግን ልምንድን ነው ስታዲዮሙ እንደዚያ ባዶ የሚሆን ? ምናለበት በነጻም ቢሆን ቢሞሉት ?

Cool
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message MSN Messenger Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Thu Feb 09, 2012 10:08 pm    Post subject: Reply with quote

ጥልቁ 1 እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ተድላ፡

ሰላምነህ ወንድሜ : እኔ ባለሁብት አለሁ ::

ጥልቁ እንደጻፈ(ች)ው:
በጋና መሸነፍ ክፉኛ እንደተናደድሁ ነኝ። ያው ዛምቢያዎችም የኛው ወንድሞች ቢሆኑምና በተለይም አንተ እንዳልኸው የተገፉ ከመሆናቸው አንጻር ብቻ ሳይሆን ያኔ በአውሮፕላን አዳጋ ላልቁባቸው ተጫዎቾች ሁሉ መታሰቢያ ዋንጫ ቢበሉ ምኞቴ ነው።

ዛምቢያዎችን ከጋናዎች ለይቼ አላያቸውም :: እነርሱም የኢትዮጵያ የዘወትር ወዳጅ የሆኑት የዶክተር ኬኔት ካውንዳ አገር ዜጎች ናቸው ::

የዛምቢያን እግር ኳስ ታሪክ በደንብ ካየኸው ጥሩ ደረጃ ላይ ሲደርሱ የሚያጋጥሟቸው እንከኖች አሉ ::
# ..... 1966 .. ግብፅ ላይ በተደረገው 9ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ በፍጻሜው ጨዋታ ከያኔው ዛዬር (ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ) ጋር ተጋጥመው 2 2 ተለያዩ :: በወቅቱ በነበረው የካፍ ሕግ መሠረት ድጋሚ መጫወት ስለነበረባቸው 2 ቀናት በኋላ ባደረጉት ግጥሚያ በዛዬር 2 0 ተሸነፉ : እና ዋንጫ አጡ :: በእርግጥ ያኔ በጨዋታ ጥበብ ዛምቢያዎች ይበልጡ እንደነበረ ጋዜጣ ላይ አንብቤያለሁ ::

# ..... ለሁለተኛ ጊዜ ዛምቢያዎች ለዋንጫ የደረሡት 1986 .. ቱኒዚያ ላይ በተደረገው 19ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ ላይ ነበር :: ውድድር ለዛምቢያዎች እስከዛሬ ድረስ የመጥፎ ትዝታ ምንጭ እንደሆነ አንተም ታስታውሣለህ :: በፍጻሜው ግጥሚያ በናይጄሪያ 2 1 ተሸንፈው ዋንጫ አጡ ::

ስለዚህ ዛምቢያዎች ጥሩ ቡድን እየሠሩ ጫፍ ሲደርሱ ዋንጫ ያጣሉና ዘንድሮ እንዲሣካላቸው እመኛለሁ ::

Quote:
የጋናው የቆጨኝ ለምን መሰለህ ? በአለም ዋንጫ ላይ በግፍ መሸነፋቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ሲሆን በተለይ ግን ጋናን በግፍ ያሸነፈው ኡራጋይ የኮፕ -አሜሪካ ዋንጫ ባለቤት ለመሆኑ ከጋና የነጠቁት የግፍ ድል አስተዋጾ አድርጓል ብየ አምናለሁ። እንደመታደለም በለው እንዳለመታደል ጭንቅላቴ ነገሮችን ያይዛል። ሱራዝ የሚሉት መጥፎ የኦራጋይ ተጫዋች (የጋናን ጎል በጁ ያስቀረ ገጦ ) ባለፈው ሁሉ የቅጣት ናዳ ሲጣልበት (ኤቭራን ለተሳደበበት ) አንጀቴ ነበር የራሰው።

እናም ጋና ለዚህ ዋንጫ ቢበቃ እጅግ ደስ ባለኝ ነበር።

ባለፈው ደቡብ አፍሪቃ ላይ በተደረገው የዓለም ዋንጫ በጋና ቡድን ላይ የተሠራው ግፍ እንዳለ ሆኖ የራሣቸው አምበል አሣሞያ ጋያን ሪጎሪ መሣቱ (ትላንትም ዛምቢያ ላይ ሥቷል ) ትልቅ ዋጋ አስከፍሏቸዋል :: እንዳልኸው ጋና ላይ ብቻ ሣይሆን በዓለም ዋንጫ ውድድሮች በሁሉም የአፍሪቃ ቡድኖች ላይ ለምሣሌ :- 1974 እስፓኝ ላይ በተደረገው 12ኛው የዓለም ዋንጫ በአልጄሪያ ላይ ኦስትሪያና ጀርመን የሠሩት ሻጥር እንዲሁም 1982 .. ጣሊያን ላይ በተደረገው 14ኛው የዓለም ዋንጫ እንግሊዝ ለፍፃሜ እንዲያልፍ ተብሎ በካሜሩን ቡድን ላይ ያለ አግባብ ሁለት ፍጹም ቅጣት ምቶች ተሠጥቶ እነ ሮጀር ሚላን ያቀፈው ታላቁ የካሜሩን ቡድን ከውድድር እንዲወጣ ያደረጉበት ተንኮል : ሌላም ሌላም መጥቀስ ይቻላል ::

ጥልቁ እንደጻፈ(ች)ው:
ሌላም ምክንያት አለኝ የዛሬ ሁለት አመት ጋና በግብጽ ሲሸነፍ በጨዋታ ግን ምን ያህል ብልጫ ያሳይ እንደነበረ ከአይኔ ላይ አለ። አቦ ጋናን የምደግፍበት ምክንያቴ መብዛቱ ዋናው የድጋፌ ምንጭ ግን ከአፍሪካ አገሮች የኛን ሰንደቅ አላማ የሚጋሩንን ሁሉ እወዳቸዋለሁ። ማኢሊዎች ለብሰው የሚገቡትን ማሊያ አየህልኝ ?! የኛ ሰንድቅ አላማ (ለዛውም አምብሻው የሌለበት ) ደረታቸው ላይ ተነጥፎ ሳየው እንዴት ደስ እንደሚለኝ።

እኔም ብሆን የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማን የሚመስል የሚያውለበልቡ አገሮች ቡድኖችን እደግፋለሁ :: ማሊ ደግሞ ለአረብ ቡድኖች ጥሩ ቀጪያቸው ስለሆነ የምወደው ቡድን ነው :: 19ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ አዘጋጁን አገር ቱኒዚያን እና ግብፅን ከውድድር ያስወጣቸው ማሊ ነበር (ቱኒዚያን በማጣሪያው ውድድር 2 0 እንዲሁም ግብፅን በጥሎ ማለፉ የሩብ ፍፃሜ 1 0) ::

ጥልቁ እንደጻፈ(ች)ው:
በተረፈ የጋና እና የዛሚቢያ ጨዋታ እንደኮትዲቫር እና ማሊው አያምርም። ከአንተ ጋር የማልስማማው ግን በጨዋታ ኮትዲቫሮች በልጠዋል በሚለው ነው። ለኔ ማሊዎች ፍጹም የተልየ ብቃት አሳይተዋል። እንዴውም በዚህ ቶርናመንት ብዙም ያላየሁን አይነት ጌጣጌጥ ጨዋታ ሁሉ ያሳዩኝ እነሱ ናቸው።

አሃ የጋናና ዛምቢያ ጨዋታ ያን ያህል አይስብም ነበር ? .... እኔ ማሊን መናቄ አይደለም : እነርሱ በአመዛኙ እንደ ድሮው የጀርመን ቡድን በራቸውን ዘግተው በጥሩ የመከላከል ሥልት ይጫወቱ ስለነበረ ነው :: ከኮት --ቯር ጋር ሲነፃፀሩ ብዙ የሚታወቁ ተጫዋጮች አይኑሯቸው እንጂ ቡድኑ ማንኛውንም ቡድን ቢገጥም ቢሸነፍ እንኳን በሠፋ የጎል ልዩነት አይሸነፍም :: ጠንካራና አስተማማኝ የኋላ ተከላካዮች አሏቸው ::

Quote:
ፔሌ ቀንደኛ የኮትዲቫር ደጋፊ ቢሆንም ሜዳ ላይ በማየቴ ደስ ብሎኛል…

እኔ የምለው ግን ልምንድን ነው ስታዲዮሙ እንደዚያ ባዶ የሚሆን ? ምናለበት በነጻም ቢሆን ቢሞሉት ?

Cool

የአዘጋጆቹ አገሮቹ የሕዝብ ብዛት ሥንት ይመስልሃል ? ጋቦን 1.5 ሚሊዮን : ኢኳቶሪያል ጊኒ ደግሞ 650, 000 ... ታዲያ ተመልካቹን ከዬት ያምጡት Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes ::

በል ወንድሜ እስከ ቅዳሜና እሑድ ቸር እንሠንብት ::

አክባሪህ ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sat Feb 11, 2012 10:33 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም የእግር ኳስ አፍቃሪዎች :-

ማሊ የአፍሪቃ እግር ኳስ ተስፋ

ማሊ እና ጋና ዛሬ ለደረጃ ተጫውተው ነበር :: ማሊ በጥሩ የመከላከልና የመልሶ የማጥቃት የአጨዋወት ሥልት ጋናን 2 0 አሸንፏል :: በዚህም ማሊ በማጣሪያው ጨዋታ ጋና ያገባበትን የሁለት ጎሎች ዕዳ አወራርዷል :: ጨዋታው የዳኛ ፊሽካ የበዛበት ነበር :: ከጨዋታ ችሎታ አንፃር ውጤቱን ስገመግመው የጋናን መውረድና የማሊ ቡድን የወደፊቱ የአፍሪቃ ተስፋ እንደሆነ የሚያመለክት ነው :: ለማሊ ጎሎቹን ያገባው 9 ቁጥሩ ቼክ ቲዴኒ ዲያባቴ 23 እና 80 ደቂቃዎች ነበር ::

የጨዋታውን ትዕይንት ለመከታተል :-

ምንጮች :-
የመጀመሪያው ግማሽ :- CAN 2012:Ghana vs Mali 3rd place part 1 .

ሁለተኛው ግማሽ :- Can 2012: Ghana vs Mali 3rd place part 2.

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sun Feb 12, 2012 11:28 pm    Post subject: Reply with quote

ዛምቢያ አዲሱ የአፍሪቃ ዋንጫ ሻምፒዮና ::

እንኳን ደስ ያላችሁ Exclamation Exclamation Exclamation Exclamation Exclamation Exclamation Exclamation Exclamation Exclamation Exclamation Exclamation Exclamation Exclamation Exclamation Exclamation Exclamation Exclamation Exclamation Exclamation Exclamation Exclamation Exclamation Exclamation Exclamation Exclamation

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3  Next
Page 2 of 3

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia