WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ያባቱልጅ ዌልካም ባክ ብለናል ..እስኪ ስለ ሽገር ለቀቅ ለቀቅ

Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

View previous topic :: View next topic  
Author Message

ኮትኳች

Joined: 17 Oct 2010
Posts: 312

PostPosted: Fri Feb 10, 2012 12:17 am    Post subject: ያባቱልጅ ዌልካም ባክ ብለናል ..እስኪ ስለ ሽገር ለቀቅ ለቀቅ Reply with quote

Code:
ክቡርነቶ

ባታየኝ ነው እንጂ ኖር ባያለሁ ....አስታዋሽ አያሳጥኝ ....አንተ ሰላም ነህ በቅድሚያ ? ቀየው , ጎረቤቱ , ከብቱ ሰላም ውሎ ይገባል ? በማስቀደም ዋርካ ቤታችን እንዴት ናት ...ሁሉ ሰላም .....ተመስገን በሉ (ይቺ ቃል ኢትዮ የተማርኩዋት ናት ...

ይሄ የወንድማችን ጉዳይ ትንሽ ሁላችንንም ረብሾ ወደዛ እሮጥኩ እንጂ ዝም ለማለት አስቤ አይደልም .....በዚህ አጋጣሚ ለሙዝ ትልቅ ምስጋና አቀርባለሁ .....እንዴት ነህ , በርታ ቃላቶችህ አስደምመውኛል ....ቀናት አጥረው ያሰብነውን ባናሳካም ይሄ ጅማሪ እንጂ መጨረሻው አይደለም ::

ሎሚ ለሚወረውሩት ባለተራዎች ሎሚ ስናቀብል ትንሽ ጊዜ አጥፍተናል ....ለምን ይዋሻል ??? ቅቅቅቅ

አታምነኝ የጥምቀት ሰሞን ሎሚ በጣም ተወዶ ነበር ቅቅቅቅ አግኝተህም ልትጨምቅ ስትታገል ቀድሞ ጠብ የሚለው ያንተ ላብ ነው በጣም ከመድረቁ የተነሳ ....እና እንደዚህ የደረቀ ሎሚ አንዲት ልጅ ላይ ብትወረውር ግፍ አይሆነም ???? ሁሉም ነገር ኢትዮፕያ ላይ money talks ነው .....አሁንም የኢትዮፕያ እድገት የት ሊደርስ ነው በሚያስብል ጨምሩዋል .....ከልጅ እሰክ አዋቂ ይሰራል , ይፍጨረጨራል .... ደሞ እድገትን , ልምድን ....እያሰተማረ ካለው ላይ እየጨመረ እየተጉዋዘ ነው :: ለዛ ምስክር መሆን እችላለሁ ::
ነዋሪው ከአምናው ካቻማናው ዘንድሮ አይኑ more የተከፈተበት ጊዜ ነው ....5 ሳንቲም 10 ለማደረግ ሲሮጥ ይውላል ....መንግስት አውቆ ያደረገውም ይመስለግኛል የኑሮ ውድነቱን ለማሸነፍ ቀዳዳ ፈለጎ ይሰራል , ይሮጣል ....በተኬደበት ወሬው ስራ ስራ ነው ....

የሰው ቤት እንዳላቆረፍድ እስቲ አንድ ክፍል ቤት ሰራልኝ ? እና እዛ እናወራ ....ፎቶዎችም አሉ

የሎሚዋ ነገር ፈገግ አድርጋኛለች ...ቅቅቅ አንተ አልወርወርኩም ለማለት ነው ..እስኪ ይሁን
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
ያባቱልጅ

ኮትኳች

Joined: 31 Oct 2006
Posts: 347

PostPosted: Fri Feb 10, 2012 9:04 pm    Post subject: Reply with quote

ቅቅቅቅቅ ምስጋናዪ ከፍ ያለ ነው ኮርማው

እንግዲህ አለምነህ ዋሴን ልታደርገኝ ነው Laughing Laughing Laughing በል ጀምር ማንኛውንም ጥያቄ ልናስተናግድ ዝግጁ መሆናችንን ስንገልጽ ደስታ ይሰማናል :: ከየት ይጀምር ለእናንተ ትተናል ....

ውዲቱዋ my queen ኢትዪፕያ ግን ሁላችሁንም ናፍቂያለሁ ብላለች ....ከሄዳችሁ ለቆያቹ , በቅርቡም ለሄዳቹ , እስከዛሪም እግር ላልጣላቹ በደፈናው ብዙ አምልጡዋችሁዋል ግን አረፈድም ብላችሁዋለች ....

ከተማውን እያነቃነቀ ካለው ሀይሌ ሩትስ አንድ ዘፈን ልጋብዝ እና እንቀዳለን .....በነገራችን ላይ ይህ ሙሉ ዘፈኑ እጅግ ተውዶለታል ....ምርጥ ስራም ነው ባይ ነኝ ....ቴዲ አፍሮ አጅቦታል .....ሰዉም ዘፈን መራጭ , ለጥሩ ሙዚቃ ብቻ ትኩረት የሰጠ ይመስላል ....እነ እትና ጉዳቸው ቅቅቅቅ ለነገሩ እንሱም ሙሉ አልበም አያስቡትም .....

http://www.youtube.com/watch?v=4laafiRDV-4

መልካም ሰንበት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
መንፈሳዊው .

መንገደኛ

Joined: 11 Feb 2012
Posts: 3

PostPosted: Sat Feb 11, 2012 6:02 am    Post subject: Reply with quote

ስማ ሰልማ 1 ኮርማው .እንደምነክ ባባጃሌው ? እኔ ይውልሽ አንዳንዴ ስጋ አንዳንዴ በመንፈስ ከናንተ እዚችው ዋርካ ላይ ክስቶ እያልኩ ብሰነብትም አሁን ግን በጥንቱ ስሜ ከች ብዬለት ያደባባይ ሚስጥር ሆኜልሻለው ::

አባ አገርቤት አትሂድና ደርሶ የመጣ ሰው እየጠበክ በርበሬ ቀፍል ::
ወደቁምነገሩ ምሉ እንበልና አባ እኔ የዛሬ አመት ሄጄልሽ ያየዋቸው ችኮች እስካሁን ባስታወስኳቸው ቁጥር ሚድል ክላሴን ( ማለቴ አለ አይደል ላጀስትራዬን ) ላልታሰበ ደም ግፊት ይዳርጉታል ስልክ ...
እናም ያባቱልጅ ...የደረሰበትን እና ያደረሰውን እስኪነግረን በኔ ትዝታዎች ትቆዝማለክ ::

እኔ ከሁሉም መጀመርያ የገረመኝ ሲገነባ ሳለ አገር ስለቅ እንደዛ አጀብ እያልኩለት የወጣሁት አዲሱን ተርሚናል ......ገና ከፕሌን ወጥተን አዳራሽ ውስጥ ስገባ ድንግዝግዝ ብሎብኝ ምናምን የሻማ ምሽት መስሎኝ "ብርቱካን ሚደቅሳ ስቲል አልተፈታችም ? " ምናምን ብዬ ጠይቄልሽ ከስተምስ ዊንዶ ውስት ያለችዋ ባድግ ዳያጎናል ግልምጫ አሞላቀቀችኝና አርፌ ወደዝምዱዎቼ ልቀላቀል ሻንጣ ፍለጋዬን አደራራሁት ...እልሻለው

ለክፉም ለደጉም መንፌው ነኝ የድሮው
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሀሚሮዝ

አዲስ

Joined: 17 Mar 2010
Posts: 40
Location: Milano

PostPosted: Sat Feb 11, 2012 10:34 am    Post subject: Reply with quote

ምንድን ነው ዝምታው ትንሽየ የዋርካ ደንበኞችን ልብ ያንጠለጠለ አልመሰላችሁም ? ጭውቴው ይጀመር እንጅ ...በነገራችን ላይ እንኩዋን በደህና መጣሕ ዉድ የዋርካ ደንበኛችን የአባቱ ልጅ ..
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post

ኮትኳች

Joined: 17 Oct 2010
Posts: 312

PostPosted: Sat Feb 11, 2012 8:55 pm    Post subject: Reply with quote

ያባቱልጅ እንደጻፈ(ች)ው:
ቅቅቅቅቅ ምስጋናዪ ከፍ ያለ ነው ኮርማው

እንግዲህ አለምነህ ዋሴን ልታደርገኝ ነው Laughing Laughing Laughing በል ጀምር ማንኛውንም ጥያቄ ልናስተናግድ ዝግጁ መሆናችንን ስንገልጽ ደስታ ይሰማናል :: ከየት ይጀምር ለእናንተ ትተናል ....

ውዲቱዋ my queen ኢትዪፕያ ግን ሁላችሁንም ናፍቂያለሁ ብላለች ....ከሄዳችሁ ለቆያቹ , በቅርቡም ለሄዳቹ , እስከዛሪም እግር ላልጣላቹ በደፈናው ብዙ አምልጡዋችሁዋል ግን አረፈድም ብላችሁዋለች ....

ከተማውን እያነቃነቀ ካለው ሀይሌ ሩትስ አንድ ዘፈን ልጋብዝ እና እንቀዳለን .....በነገራችን ላይ ይህ ሙሉ ዘፈኑ እጅግ ተውዶለታል ....ምርጥ ስራም ነው ባይ ነኝ ....ቴዲ አፍሮ አጅቦታል .....ሰዉም ዘፈን መራጭ , ለጥሩ ሙዚቃ ብቻ ትኩረት የሰጠ ይመስላል ....እነ እትና ጉዳቸው ቅቅቅቅ ለነገሩ እንሱም ሙሉ አልበም አያስቡትም .....

http://www.youtube.com/watch?v=4laafiRDV-4

መልካም ሰንበት

ምስጋናውን ተቀብለናል
ከየት ይጀመር ላልከው እግርህ አዲስን ከረገጠበት ጀምሮ አይሻልም ..
መቼም አሳዳጅ ነገር ነሽና ያባቱ ልጅ ..ባገራችን እሙሙ ስንት እንደጋባ በስላው ብእርሽ እንደምታስነብቢን በኔና በዋርካ እሙሙ በጠረረባቸው ስም ባክብሮት እንጠይቃለን
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post

ኮትኳች

Joined: 17 Oct 2010
Posts: 312

PostPosted: Sat Feb 11, 2012 9:13 pm    Post subject: Reply with quote

መንፈሳዊው . እንደጻፈ(ች)ው:
ስማ ሰልማ 1 ኮርማው .እንደምነክ ባባጃሌው ? እኔ ይውልሽ አንዳንዴ ስጋ አንዳንዴ በመንፈስ ከናንተ እዚችው ዋርካ ላይ ክስቶ እያልኩ ብሰነብትም አሁን ግን በጥንቱ ስሜ ከች ብዬለት ያደባባይ ሚስጥር ሆኜልሻለው ::

አባ አገርቤት አትሂድና ደርሶ የመጣ ሰው እየጠበክ በርበሬ ቀፍል ::
ወደቁምነገሩ ምሉ እንበልና አባ እኔ የዛሬ አመት ሄጄልሽ ያየዋቸው ችኮች እስካሁን ባስታወስኳቸው ቁጥር ሚድል ክላሴን ( ማለቴ አለ አይደል ላጀስትራዬን ) ላልታሰበ ደም ግፊት ይዳርጉታል ስልክ ...
እናም ያባቱልጅ ...የደረሰበትን እና ያደረሰውን እስኪነግረን በኔ ትዝታዎች ትቆዝማለክ ::

እኔ ከሁሉም መጀመርያ የገረመኝ ሲገነባ ሳለ አገር ስለቅ እንደዛ አጀብ እያልኩለት የወጣሁት አዲሱን ተርሚናል ......ገና ከፕሌን ወጥተን አዳራሽ ውስጥ ስገባ ድንግዝግዝ ብሎብኝ ምናምን የሻማ ምሽት መስሎኝ "ብርቱካን ሚደቅሳ ስቲል አልተፈታችም ? " ምናምን ብዬ ጠይቄልሽ ከስተምስ ዊንዶ ውስት ያለችዋ ባድግ ዳያጎናል ግልምጫ አሞላቀቀችኝና አርፌ ወደዝምዱዎቼ ልቀላቀል ሻንጣ ፍለጋዬን አደራራሁት ...እልሻለው

ለክፉም ለደጉም መንፌው ነኝ የድሮው

መንፌክስ የጥንቱ የጥዋቱ
ባለ ላጀስትራ ምልክቱ
ቅቅቅቅ ..በርበሬ ቀፍል አልሽኝ ..ይሁና
አዎ ልክ ነክ ያባቱ ልጅ የደረሰበትን እስኪነግረን ባንተ እንቆዝም ..ኤክስፓየድር ያደረገ ቢሆንም Rolling Eyes ግን ግን
አመት ሙሉ ይህን ሁሉ ቀደዳ እንደ ቆምጨው በመሀረብ ቋጥረህ Rolling Eyes Rolling Eyes ዛሬ ምን አሰተነፈሰክ በል ባባጀሌው ይዤካለው
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
ያባቱልጅ

ኮትኳች

Joined: 31 Oct 2006
Posts: 347

PostPosted: Sat Feb 11, 2012 10:53 pm    Post subject: Reply with quote

....ይቅርታ ስለዘገየሁ ....ምን ከኢትዪ መል s እኮ አብዛኛው ያለችውን ትርፍ ጊዜ የሚጠፋው ኢትዪ በመደውል ነው ... Laughing Laughing

....ያው ኢትዮፕያ በወርም ሂዱ በአመታችሁ ሁሌ እንደ ስሙዋ አዲስ ናት . ቦሌ ስታፎች ቀልጣፋ ሆነዋል ...ጋሪ ከሚገፉት ጀምሮ ከውጭ ስለመጣህ ዶላር /ፓውንዲቱዋን አምጣ ብለው አያጨናንቁም ....የታባቱ ደሞ መጣ ነገር ነው ....ይሄን ነገር ሰፈርም ሆነ ታክሲ ውስጥ አሰተውያለሁ ...ማንም ደንታ የለውም ....እንደድሮ ለከሌ ይሄን ሳልይዝ ብሎ መጨነቅ ፋራነት ነው ....የያዝክለትን ልጅ ላታገኘው / ትችላለህ ....ድንገት ጊዜ አግኝቶ / አግኝተሀው / ያመጣሀውን ስትሰጠው የታወቀ ብራንድ ካልሆነ በጣም ተሸወድክ ማለት ነው ቅቅቅ አለመውሰዱ ይመከራል ....አለዛ ሽቶ እና መነጽር የመሳሰሉት ነገሮች ተቀባይነት አላቸው ....ይዘሀው ተመለስ የተባለ ፍሪንድ አቃለሁ Laughing Laughing Laughing ከአዛውንቶች በቀር በብዛት ዲዛይነር ለባሽ ነው ....ኦሪጅናሊትነቱዋ ቢያጠያይቅም .

አንዴ ከሰሀት በሁዋላ ምሳ ሰሀት አለፈ በሁዋላ አብሮኝ ከተጉዋዝ ጀለሴ ጋር ምሳ ልንበላ አንድ ሆቴል ስንገባ ያየናቸው ወደ 10 የሚጠጉ ሴቶች አስደምመውናል ....ቀርቦ ላላያቸው 20-25 እድሜ ክልል ውስጥ ነው የሚመድባቸው .... ያላለዙት የመጠጥ እና የምግብ አይነት የለም , ወርያቸው ከእነሱ የሚጠብቅም አይደል ...አለባበሳቸው አሳዝኖናል ....እንደ ግሩፕ ነገር እንደሆኑ በጨዋታቸው ተረድተናል ....እድሚያቸው 50 በላይ እንደሚሆን አልተጠራጠርንም .....ብቻ ለማለት የፈለኩት ቅጥ ያጣ ዘመናዊነት ከተማዋ ላይ እንደፋሽን ተይዙዋል ....ሰዉ ከራሱ ጋር ተራርቁዋል Crying or Very sad Crying or Very sad

አዲስ አበባ ላይ ከምን ጊዜም በላይ ፎቅ በዝቱዋል ....ቴሌ ለሞባይል ኮኔክሽን ችግር ከተማው ውስጥ የፎቅ መብዛት ነው እስኪል ድረስ ቅቅቅቅ ተመስገን ነው !!!
ሙዝ ታርመኛለህ ከተሳሳትኩ .....ይትም ሂዱ የትም በየ 100 ሜትር አንድ ፎቅ አለ ....ድሮ ድሮ ቦሌ ነበር አሁን ጨርቆስን ብትጠይቁት ....ፎቅ ብርቅ ነው እንዴ ? ይላችሁዋል

የአሁን ሀብታም አንድ ፎቅ ሊኖረው ህግ ያስገድደዋል Wink

አዲሱን የአፍሪካ ህብረት ህንጻ ተታኮ ጋሽ አላሙዲን ጉደኛ ፎቅ እየገነቡ ነው ....ሸራተን ቁጥር 2 ነው እየተባለም ይወራል ....ውበቱ ለጉድ ነው ....አጀማመሩ ከአሁኑ ሸራተን ይበልጣል ....ወደ አዲሱ አፍሪካ ህብረት በቀጥታ የሚያገናኝ ውስጥ ለውስጥ መንገድም አለው ተብሉዋል ....እንደሳቸው ያወቀበት የለም

እስቲ እመለሳለሁ ....የሚወራ ብዙ አለ 'my queen Ethiopia'
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ያባቱልጅ

ኮትኳች

Joined: 31 Oct 2006
Posts: 347

PostPosted: Mon Feb 13, 2012 9:36 pm    Post subject: Reply with quote

.....ከትውልዱ ማነው ያስተዋለው " የሚለው ማስታወቂያ ብዙ ታክሲዎች ላይ ይነበባል :: ብዙዎችንም ያነጋግራል

....በቅናት የቀላ ፊት በቫዝሊን አይወዛም ' የምትለዋ ደሞ አይዙዎች ላይ ትበዛለች ::

አዲሱ መነጋገሪያ ደሞ የአዲስ አበባ ባቡር ፕሮጀክት ነው :: ከሀያትች cmc ተነሰቶ በመስቀል አደባባይ አንዱ ወደ ቃሊቲ ሲያቀና አንደኛው ወደ ጦርሀይሎች ይጉዋዛል ...ጅምሩ እጅግ ደስ ይላል እዛው እያለሁ ስራው ከሀያት ጊቢ ተጀምሩዋል ....ውጭው አለም ትራም ወይም ኦቨር ግራውንድ የምንለው አይነት ወድ 30 ስቶፕ አለው ....

ሌላው ደሞ ከመሰቀል አደባባይ እስከ ቦሌ ያለው አስፋልት በሁለቱም ሳይድ የማስፋቱ ፕሮጀክት ነው ....በነገራችን ላይ አንድ ነገር በመንግስት ተጀምሮ ማለቅ የተለመደ ነገር ሆኑዋል ይሄም የቦሌ መነገዱን የማሰፋት ስራ ብዙዎችን አነጋግሮ የነበረ ቢሆንም ባለፈው ወር ጀምረውታል .... ሁሉ ፎቅ እንዴት ሊሆን ነው የሁሉም ጥያቄ ነበር ግን ጅማሪውን ሳየው ምሳሌ በደንበል ፎቅ እና በዋናው አስፓልት ያለውን እግረኛ መንገድ ያጣቡታል ..... z other ልክ እንደዚሁ

ከፒያሳ በእሪ በከነቱ እሰከ መገናኛ የተሰራው አዲስ መነገድ , የድሮውን አስመራ መንገድ (ሃይሌ መንገድ ) ያለውን መጨናነቅ ከእጥፍ በላይ ቀንሶታል ....ከፒያሳ መገናኛ 20 ደቂቃ በላይ አይፈጅም

ዜብራ ክሮሲግ በየቦታው ቢኖርም አሁንም ለተሻጋሪው ቅድሚያ አለምስጠት አለ ....አንዱ ታክሲ ሹፌር አንዱዋ ጉብል ቀስስስ እያለች ስትሻገር አይቶ ....ለምን አትነቀሽውም ? ያላት አስቃኛለች
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post

ኮትኳች

Joined: 17 Oct 2010
Posts: 312

PostPosted: Tue Feb 14, 2012 4:49 pm    Post subject: Reply with quote

ቀጽል ..ቀጽል ..የፋዙካ ልጅ ..እያነበብንክ ነው ....
እንዴት ነው የእሙሙ ነገር ስንት ገባ ግን ...አይ ውቃው ...ውቃውም ዝም ብሏል Rolling Eyes
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
ያባቱልጅ

ኮትኳች

Joined: 31 Oct 2006
Posts: 347

PostPosted: Wed Feb 15, 2012 9:34 pm    Post subject: Reply with quote

እንደጻፈ(ች)ው:
ቀጽል ..ቀጽል ..የፋዙካ ልጅ ..እያነበብንክ ነው ....
እንዴት ነው የእሙሙ ነገር ስንት ገባ ግን ...አይ ውቃው ...ውቃውም ዝም ብሏል Rolling Eyes

እንግዲህ በደረስኝ መረጃ መሰረት እሙሙ ዋጋው ከፍ ብሉዋል እርምህን አውጣ .....አብሮኝ የተጉዋዘ ጉዋዴ አንዱዋ አክሲዪን ግዛልኝ ብላው መከራውን ሲያይ አስተውለናል Laughing Laughing Laughing አክሲዎኑ በሺዎች ሊቆጠር ይችላል ቅቅቅቅ ደፈር ብለው ደምበል ላይ ሱቅ ከፍተህልኝ ትሄዳለህ አይደል ሲሉህ አደነግጥም ??? እና አጠያየቃቸው ጫን ያለ ነው .....በነገራችን ላይ ድሮ ድሮ ሴቱ ይበዛ ነበር አግባኝ እና አውጣኝ ጥያቄ ዘንድሮ ወንዶቹ ጨምረው ተገኝተዋል .....ከአሜሪካ የመጣችውን የአክስቴን ልጅ የጠበሰው ልጅ ግን መቼም አረሳውም ....ወይኔ ፍጥነቱ ነው ያልኩት ....ቤተሰቦቹዋን ሲያውቅ ሳምንት አልፈጀበትም Laughing Laughing ቤተሰቦቹን እና ፍሪንዶቹን ሲያስተዋውቃት እሱዋ አግብቼ ነው አሜሪካ ይምሄደው ሲል በቢዝነስ ያጋባት ነው የሚመስለው Laughing Laughing
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ያባቱልጅ

ኮትኳች

Joined: 31 Oct 2006
Posts: 347

PostPosted: Wed Feb 15, 2012 10:00 pm    Post subject: Reply with quote

......የሀይሌ ሩት እና የግርማ ተፈራ ዘፈኖች ለጉድ ይሰማሉ . ግርማ ተፈራ ከለንደን ወደ ሸገር ከከተመ ትንሽ ቆየ .... ሰዉ ሙሉ ዘፈኖቹን ወዶለታል :: አሁን ከሳምንታት በፊት ከማዲንጎ ጋር ጋላክሲ የሚባል ክለብ ቦሌ መድሀኒያለም ጋር የራሱን ከመክፈቱ በፊት የተለያየ ቦታ ይጫወት ነበር :: ወንዳታ ግርምሽ ብያለሁ ....

ሌላው እጅግ ያስደመመኝ እና ትልቅ ለውጥ ያየሁበት ጣይቱ ሆቴል ነው :: እነ ሄኖክ እና እውቅ የሙዚቃ ተጫዋቾች እጅግ ለዛ ያለው , ኩዋኩዋታ ያልበዛበት አስደሳች አርት የሚያሳዩበት ቦታ ሁኑዋል .....ለምሽት ላይፍ ወደ ቦሌ ብቻ የሚሮጥ ያን ቤት ያላየ ነው ....ኩኩም አልፎ አልፎ ትጫወታለች ....50 ብር መግቢያ ያስከፍላሉ እጅግ ሲያንስ ነው .....ከዛው ሳንረቅ Think out side Bole የሚል ሀሳብ ይዞ 4 ኪሎ , ሚኒልክ /ቤት ፊት ለፊት የተከፈተው ደሞ ጆሊ ባር ነው .....ዌስተርን አይነት ይዘት ያለው ቦሌ አካባቢ ካሉት የማይሻል ነው ::

ወደ ቦሌ ስንመለስ ፍለርት የሚባል ክለብ አለ .....ከጀርመን ቢር ጋርደን ፊትለፊት አዲስ እና ሰፋ ያለ ባር /ክለብ ከፍተዋል ....ቤቱ እጅግ ዘመናዊ , ሰፊ , AC በሚገባ የሚሰራ ሲሆን ዲጄው አማርኛ ዘፈኖች ጣል ጣል ማድረጉ አስደስቶናል .....አንድ ቀን ምሽት ግን ዲሲ የገባሁ እስኪመስለኝ የዲሲ ልጆች ሞልተው ነበር ......ይመቻቹ ብዙ ተጫውተናል Wink Wink Wink
ፍለርት አንድ ቦትል ዊስኪ እስከ 1,000 ብር ይሸጣል ሌላ ቦታ ከዛ በላይ ነው ኮምፔር ሲደረግ ፍለርት ርካሽ ነው

አዴክት ከሚያደርግ ቤት አንዱ ደሞ ወሎ ሰፈር መዞሪያ ጋር ያለው በሙሉ ባንድ አማርኛ የሚጫውቱበት 'መሳፍንት ቤት ' የሚባለው ነው :: ከቤቱ መጥበብ ጋር ቤቱ ባይመችም የሚቀርቡት ዘፈኖች ከየትኛው ከተማዋ ውስጥ ካሉ ክለቦች የተሻለ ነው ....ግርማም እዛ ይጫወታል ::

መጣሁ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ሀሚሮዝ

አዲስ

Joined: 17 Mar 2010
Posts: 40
Location: Milano

PostPosted: Sat Feb 18, 2012 11:32 am    Post subject: Reply with quote

በጣም ይመቻል በቶሎ ተከሰት እና ጭውቴዉን አድራልን የፋዙካ ልጅ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ያባቱልጅ

ኮትኳች

Joined: 31 Oct 2006
Posts: 347

PostPosted: Sun Feb 19, 2012 10:48 pm    Post subject: Reply with quote

ሀሚሮዝ እንደጻፈ(ች)ው:
በጣም ይመቻል በቶሎ ተከሰት እና ጭውቴዉን አድራልን የፋዙካ ልጅ

የወንዜ ልጅ አለሁ ....ጥያቄ ካለ እንስተናግዳለን

ዛሬ ስለቤት መስራት ኦር መግዛት ለምን አንቀድም ?! መሬት በጣም ተወዱዋል , አዲሱ ህግ ደሞ ተገበያተኛውን ቀጥ አድርጎታል በተዘዋዋሪ ግን እራሱ እየሸበሸበው ይገኛል ....ሊዝ !!! ማጆሪቲ የአዲስ አበባ ህዝብ በጭፍን ነው የሚጉዋዘው ..... በተወሰነ ደረጃ ሊዙ የተሻለ ይመስለኛል ;; ጨረታ በየጊዜ በሁሉም ክፍለከተማ ይወጣል ....ይሄ ሊዝ እንደጨረታ ነው መንግስት ይሄ መሪት በካሬ 100 ብር ያወጣል ብሎ ሲያወጣ እስከ 1,000 ብር ሊደርስ ይችላል ...ምሳሌ የቦሌ /ከተማ አሰራር አስደስቶኛል ....በቅድሚያ ሙሉ ኢንፎ ይነግሩሀል , ቦታው ድረስ ወስደው ያሳዩሀል ቪው ታይም ይሉታል እና ቦታውን ከወደድከው ዋጋህን ቆልለህ ታስገባለህ ማለት ነው ..... 2 ወር ኦር ከዛ በላይ የሄደ ይሄን ነገር ያሳካል ባይ ነኝ .....

ከግለሰብ ላይ ከተገዛ ገዥው ለሻጭም , ለመንገስትም ይከፍላል ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia