WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የአሳዛኙ ዜና ኅዘን -የንፋስ ስልክ ትዝታ
Goto page Previous  1, 2, 3  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
መላጣ

ዋና ኮትኳች

Joined: 27 Feb 2004
Posts: 567

PostPosted: Tue Feb 07, 2012 11:29 am    Post subject: Reply with quote

ካታንጋ ወደ 2ኛው ዓመት እንደተሸጋገርን በጣም ቁጡና ኃይለኛ የአማርኛ አስተማሪ ነበሩ :: እኝህ ሰው የቀኝ እግራቸው ከጉልበታቸው ጀምሮ የተቆረጠ ሲሆን የሚሄዱት በመቋሚያ ድጋፍ ነበር :: ታዲያ መምህሩ ከውጭ ሲመጡ የመቋሚያቸው ጩኸት ከሩቁ ስለሚል አንድ ተማሪ ትንፍሽ አይልም :: ክፍሉን ከፈት ሲያደርጉም ሁሉም ከመቀመጫው ይነሳል :: ከዚያም ቆም ብለው ተመልክተው ልጆች እንደምን አደራችሁ ወይም ዋላችሁ በማለት ተቀመጡ ይላሉ :: ተቀመጡ ሳይሉ የተቀመጠ ጉድ ፈላበት በዚያ በመቋሚያቸው ነርተው ነርተው ግንባርን የስሙኒ ኳስ በማሳከል ከጥቅም ውጭ የሚያደርጉ ርህራሄ የማያውቁ ጨካኝ ሰው ነበሩ :: በዚህም ነበር ተማሪው በሳቸው ስለማይደሰት "ቆሪጥ " ብሎ ስም የሰጣቸው ::

አንድ ቀን ምን ሆነ መብራቱ የተባለ ከፈሱ የተጣላ ተማሪ እሳቸው እንደገቡ ቁጭ በሉ ሳይሉ ይቀመጣል :: ለካስ አይተውት ኖሮ በቁጣ ወደኔ ብለው መቋሚያቸውን አንስተው ሊፈነክቱት ሲሉ ዘሎ እንቅ ሲያደርጋቸው መቋሚያቸው ሲፈነጠር ተማሪው በሳቅ ይፈነዳል :: ከዚያም ትግሉ ይቀጥላል ግን እንደምንም ብለው በሁለት እጃቸው ሰብሰብ አርገው በዚያ በተቆረጠው እግራቸው ሆዱን ሲደባልቁት እማዬ እያለ እንዴት ከክፍል እሮጦ እንደወጣ አይረሳኝም :: ከረፍት በኃላ አግኝተን ስንጠይቀው በጣም አሞኝ አስታወከኝ ግን በጣም ያሳዘነኝ ምቱ ሳይሆን የበላሁዋት ፓስቲ በመውጣቱዋ ነው ብሎ አሳቀን :: መብራቱ ልመንህ የቄራ ልጅ ሲሆን አባቱ ኮረኔል ነበሩ አሁን የት እንዳለ ማወቅ አልቻልኩም ::

ካታንጋ እያለን ግብረገብ እርሻና ባልትና ትምህርት የምንከታተለው ጥላ ፎቅ እየሄድን ነበር :: ትኩ የርሻ አስተማሪያችን ግብረገብ እሟሆይ ባልትና ደግሞ ወሪጌታ ነበሩ :: መምህር ትኩ ሲያሰሩ ጠንካራ መኅንዲስ ይመስሉ ነበር :: በስብስቴ የርሻ መንደር መደቡን በሥርዓቱ ያልያዘ ተማሪ ይገረፋል ጥሩ ማርክም አያገኝም :: በዚህም መደባችን የተዋጣለት በብዛት ሽንኩርትና ጎመን የሚቆረጥበት ደስታን የሚሰጥ የርሻ ይዞታችን ነበር :: መምህር ትኩ እንደተነገረው የወደደና ያበደ አንድ ነው እንደሚባለው ሁሉ የመጠጥ ቤት ባለቤቷን በማፍቀር በቅናት መልክ በተነሳሳ ሁኔታ አጥፍተው መጥፋታቸው ግልጽ ሆነ ::

እማሆይ የሰው ፍቅር እንዲኖረንና በግዚአብሔር እንድንተማመን ዘውትር ጠዋት ጠዋት ስንነሳ በስመዓብ ወልድን እንድንደግም ያስተማሩን እናት ነበሩ :: መሪጌታም ቢሆን ሥጋጃ እንድንሰፋ የተለያዩ አንዳንድ የጅ ጥበብ ነገሮችን እንድናውቅ መንገድ የከፈቱ አባት ናቸው ::

ስብስቴ ነጋሢ ውስጥ ገባ ብሎ መደዳ የመማሪያ ክፍሎች ይሰራሉ :: በዚህን ወቅት ካታንጋ 1 እስከ 5 መሆኑ ቀርቶ እስከ አራተኛ ብቻ በመሆኑ 5 ክፍሎች ወደ ስብስቴ ወደ ተሰራው አዲሱ ክፍል ይሸጋገራሉ :: እንግዲህ በዚህ ወቅት ነው መምህር በላይነህን ልናውቀው የቻልነው ::

መምህር በላይነህ . ..ይቀጥላል !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቆንጂት 08

ዋና ኮትኳች

Joined: 19 Dec 2007
Posts: 735

PostPosted: Wed Feb 08, 2012 8:27 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ወለላየ ባቀረብከው የንፋስልክ ትዝታ አመሰግንሀለሁ እብዳልከው እሞሀይ የማስታውሳቸው በታቸው ከቤቴ ፊትልትፊት አቶ ሀይለስላሴ ጊበ ስለነበር ባዛ ነው ሲገቡ ወደቤታቸው የማስታውሰው በዛ ሰአት ያስተምሩ ጡረታ ላይ ይሁኑ ትዝ አይለኝም አቶ በላይ ግን ትዝ አይሉኝም ቲቸር አባት ነህን የማስታውሳቸው ጥዋት ባንዲራ ሰር ስንሰለፍ ከፊትለፊት ቆመው አባታችንሆይ ሲሉ አሁን በሀሳቤ አያቸዋለሁ ሮማን /ጻዲቅ የምትባል አስተማሪ ነበረች የክፍላችን ሀላፊ ሌላው ቲቸር አንበርብር የጂኦግርፊው አስተማሪ ካሳሁን እኛ ተማሪዎች ጋላክሲ ብለን ስም ያወጣንለትና ጀርጀራ (መንግስቴ )ሚስተርጎት ትዝ ይሉኛል ..የኢትዮጵያ አስተማሪዎቻችን ልክ እንደአባት ሀላፊነት ወስደው ጀኔራል ኖውሌጅ እንድናውቅ ያስተማሩን ባለውለታችን ናቸው አሁን ብወጭው አለም ስመለከተው አስተማሪነት ቢዝነስ መሆኑ የሚገርመኝ ነገር ነው አስተማሪዎቼ የሰቱን
ትምህርት የሂወት መመሪያ የዘለለም ቅርስ በመሆኑ ላሉትም ለለሉትም ውድ አስተማሪዎቻችን ከልብ የመነጨ ምስጋና አቀርባልቸዋለሁ በዉጭው አለም ከባዱን ኑሮ በከፍተኛ ሞራል እንዳሸንፍው እረድቶኛል እንደዛይነት በውቀትና በወላጀነት ለተማሪዎቻቸው ሀላፊነት ወስደው ያስተምሩ የነብሩ ሰዎች እዚህ ፕሮፈሰር ከሚባሉት እንኩዋን በጀኔራል ኖውሌጅ ይበልጡ ነበር ብል ተረት አደለም ....
ሀይስኩል ኮምፕረንሲፍ ባልፍንበት ጊዘ አንድ ስፖርት አስተማሪ ቲቸር ስምዎት ማነው ከየጽ ሀገር መጡ ብለው ተማሪዎች ቢጠይቁዋቸው የማእጣሁት ከጫንጮ ነው ሲሉ ተማሪዎች ከት ብለው ከሳቁ በሁዋላ ቅጽል ስማቸውን ጭንጮ ተብሎ ቀረ ....የሚያስታውሳቸው አለ ?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወለላዬ

ዋና ኮትኳች

Joined: 26 Jan 2005
Posts: 519
Location: united states

PostPosted: Wed Feb 08, 2012 5:05 pm    Post subject: Reply with quote

ዝናዬ በሚል ስም የኢሜል የላከልኝ የንፋስ ስልክ ልጅ ነው ዝናዬ አመሰግናለሁ ዝናዬ ከታች ያሰፈራቸው መወያያ አርስቶችም ለመነጋገሪያ ስለሚረዱ እንወያይባቸው አንዳንድ ፊደላት ኮፒ ሲደርግ ስለተለወጡ እያስተከሉ ያንብብቧቸው

ሰሊም ወለላዬ የአሳዛኙ ዜና ኅዘን በሚሌ ርዕስ የጻፍከውን አንብቤ የበኩላን ለማለት ዳዳኝ፤ ስለ ትቸር በሊይነህ ሳስብ የሚታየኝ ያሌተበጠረ ፀጉሩ፤ ጠቆር ያሇ የፊቱ ገጽታ፤ ደፍረስ ያለት ዏይኖቹ፤ ፈርጠም ያሇ ትከሻው፤ ሰፋፊ እጆቹ፤ ሲራመዴ ጎምሇሌ ጎምሇሌ ሲሌ
የሚያስፈራ አንበሳ ቢመስሌም በውስጡ አምቆ የያዘው የሃገርና የወገን ፍቅር የሚያሳብቅበት ዯፋር፤ ትሑትና ቆራጥ ሰው መሆኑን ነበር :: ከማስተማር ይሌቅ ጥፊ እንዯሚቀናቸው ላሊው የእርሻ አስተማሪያችን ትቸር ትኩ ጋሼ በሊይነህ በጥፊ ቢማታ ኖሮ ስንቶቻችን ዛሬ ዯንቆሮዎች በሆንን ነበር :: ትቸር በሊይነህ ግን ዯንቆሮ ሳይሆን ብሩህ አይምሮ ያሊቸው ተማሪዎች ሇማፍራት ይጥር የነበረ፤ መጀመሪያ የጆግራፊ ከዚያም ወዯ እርሻ መምህርነት በት / ቤታችን ዱረክተር አቶ ተመስገን ቀነኒ የተመዯበ ቢሆንም የተማሪዎችን ሌብና አይምሮ ከመማረክ ያገዯው አሌነበረም :: በመርዕዴ አዝማች ስብስቴ ነጋሲ /ቤት፤ በካታንጋም ሆነ በጥሊ ፎቅ፤ ከዚያም በንፋስ ስሌክ አጠቃሊይ ሁሇተኛ ዯረጃ ትምህርታቸውን ከተከታተለ ተማሪዎች አንደ ነኝ :: ከአንዯኛ ዯረጃ እስከ ዩኒቨርስቲ በተማሪነት ያሳሇፍኳቸው ዘመናት የሌጅነትና የወጣትነት ትዝታዎቼ ሲሆኑ፤ በአንዯኛ ዯረጃ፤ በሁሇተኛ ዯረጃ እና በዩኒቨርስቲ በአስተማሪነት፤ ያሳሇፍኳቸው ዘመናት ዯግሞ የጎሌማሳነትና የመጀመሪያው ክፍሌ የሙለ ሰውነት ትዝታዎቼ ናቸው :: ታዱያ ዛሬ ካንተ ጋር በጋራ ትምሕርት ስሇቀሰምንባት የስብስቴ ነጋሲ /ቤት የበኩላን ሇመጨንቆር ነው ብዕሬን ከወረቀት ያዋዯዯኩት :: የመጀመሪያ ፍቅር፤ የመጀመሪያ ዴሌ፤ የመጀመሪያ ሽንፈትና የመጀመሪያ /ቤት በማንኛውም የሰው ሌጅ አይምሮ ውስጥ አቧራ በላሇበት ክፍሌ በጥንቃቄ ስሇተቀመጡ አይዝጉም :: እንዯ እንቁ ያብረቀርቃለ፤ ሲነገሩ ወዝ አሊቸው እጅ እጅ አይለም፤ ጆሮ አይሰቀጥቱም፤ ጉሮሮ አይቧጥጡም፤ እንዯዘመኑ ፖሇቲካ እየትዝሇገሇጉ አሌዋጥም አይለም እናም ከሰው ሌጅ ሕሉና በቀሊለ አይፋቁም :: የስብስቴ ነጋሲን ሁሇት የመማሪያ ሕንፃዎች በርግጥ ማን ካታንጋና ጥሊ ፎቅ እንዲሇቸው ባናውቅም ስማቸውን ከየትና እንዳት እንዲገኙት መገመት ይቻሊሌ :: በቀዲማዊ /ሥሊሴ ስታዱየም (በዘመኑ የተሇምድ አጠራሩ ካምቦልጆ ) ካታንጋ፤ ጥሊ ፎቅ፤ ሰሜን በርና ዯቡብ በር የሚባለ ቦታዎች አለ :: ካታንጋ የፍሌ ውሃን ከጀርባው፤ የሰሜን በሩን በስተቀኝ፤ የዯቡብ በሩን በስተግራ አዴርጎ ክፊሇፊቱ ሜዲው ሊይ ያለትን ተጨዋቾች እየተመሇከተ ከኳስ ሜዲው ባሻገር ጥሊ ፎቅን ይገሊምጣሌ :: ካታንጋ የስታዱየሙን ሙቀት የሚያግሇው ክፍሌ ሲሆን ብዙውን ጊዜ ሕዝባዊ ብሶቶች፤ ዘፈን፤ መዝሙሮች አሌፎ አሌፎም ግርግርና የቡዴን ዴብዴቦች ይዯረጉበታሌ፤ የካታንጋ የሙቀት መጠን አሌፎ አሌፎ ወዯ ዯቡብ በርና ሰሜን በር ጎራ ሲሌ ኳስ ሜዲው ሙቀቱ ጨምሮ የሚነዴበት ጊዜም ነበር (የዛሬውን ባሊውቅም ):: የጥሊ ፎቅ ዯግሞ በተቃራኒው በካታንጋ ትይዩ ያሇው ሲሆን፤ ብዙውን ጊዜ ሹማምንት፤ ባሇስሌጣናት፤ እንግድች፤ የቡዴን መሪዎችና መሰልቻቸው መታዯሚያ ሲሆን ብዙውን ጊዜ ከካታንጋ ጋር አይጣጣሙም፤ ሇነሱ የሚዯረገው ጥበቃም ከካታንጋው ሇየት ያሇ ነው :: ታዴያ ይህ የስታዱየም (የካምቦልጆ ) አጠራር ወዯ ስብስቴ ነጋሲ /ቤት ይመጣና፤ ወዯ ዯብረዘይት ከሚወስዯው መንገዴ በስተግራ ትንሽ እሌፍ ብል ዮዎሴፍ / ክርስቲያን አጠገብ ያሇው ካታንጋ ሲባሌ፤ ከአንዴ የአስተማሪዎች ክፍሌ በስተቀር የቀረው በሙለ 1 አስከ 5 ክፍሌ የመማሪያ ክፍልች በመሆናቸውና የአስተዲዯር ክፍለ በአጠገቡ ስሊሌነበር እንዯ እራስ ገዝ ቢጤ በመሆኑ አንፃራዊ ነፃነት ነበረው :: የከፋ ነገር ቢያጋጥመን እንኳን ሰኔ ሠሊሳ ጠብቀኝ ! ከመባባሌ አናሌፍም ነበር፤ ሰኔ ሠሊሳም ሲዯርስ ሁለም ቂም ተረስቶ ውጤታችንን ተቀብሇን « ትምርት ቤቴ፤ ትምርት ቤቴ» የሚሇውን መዝሙር ከዘመርን በኋሊ መስከረም 18 እንገናኝ ተባብሇን በናፍቆት እንሇያያሇን :: 2
ትንሽ ወዯሊይ ከፍ ብል ከመንገደ በስተቀኝ የሼሌ ቤዚን ማዯያ አጠገብ ያሇው ዯግሞ ጥሊ ፎቅ ተብል ሲጠራ የዱሬክተሩ ቢሮ፤ ጽሕፈት ቤቱ፤ የመምህራን ክፍሌ እና ግምጃ ቤት ቢጤን አክል 6 እስከ 8 ያለ የመማሪያ ክፍልች ያለበት ሲሆን የአስተዲዯር ክፍለ ስሊሇበት እንዯ ክብር ተቆጥሮ ጥሊ ፎቅ ሲባሌ፤ በነፃነቱ በኩሌ ሇተማሪዎቹም ሆነ ሇአስተማሪዎቹ እንዯ ካታንጋው አይዯሊም :: እንግዱህ በዚህ ምክንያት ይመስሇኛሌ ካታንጋና ጥሊ ፎቅ የተባሇው :: ከዚህ የተሇየ ምክንያት አሇው የምትለ የትምህርት ቤት ጓዯኞቻችን ካሊችሁ ብቅ በለና እንማማር :: ካሊችሁ ማሇቴ እንዯ ካሱ አቦዬ፤ አስማረ ግረፌ የመሳሰለ ጓዯኞቼን በማጣቴ ሲሆን፤ እንዯ ጌታቸው ማሞ (በወያኔ የክርስትና ስሙ አጠራር ታምራት ሊይኔ ) የመሰለትን የስብስቴ ነጋሲ /ቤት በማፍራቷ የናት ሆዴ ዝንጉርጉር መሆኑንም ተረዲሁ :: (እንዯመሰሇኝ ስሇ ትቸር በሊይነህ ሇተስፋዬ ገብረአብ የነገረው ጌታቸው ማሞ ሳይሆን አይቀርም ) ዛሬ የትቸር በሊይነህና መሰሌ መምህራን ዯም ይጮሃሌ፤ ሇፍትህ፤ ሇእኩሌነት፤ ሇዱሞክራሲና ሇብሌጽግና መሬት ሊራሹ ሲለ የወዯቁ የትምህርት ቤት ጓዯኞቻችን ነብስ፤ መሬት ሇዴንበር ዘሇሌ ከበርቴ ሲቸበቸብ፤ ዜጋ ዕትብቱ ከተቀበረበት ቀዬ ሲነቀሌ፤ እያዩ በኢትዮጵያ ሰማይ ሊይ ቁሌቁሌ አዘቅዝቀው ያነባለ………… የከተሜው የባሇቤትነት ንብረትም ተነጥቆ የወያኔ የአከራይ ተከራይ እንዱሆን ታውጇሌ ! በሳሙና ታጥቦ ቱር ያሇች ነጭ ዴህነት ይሎችኋሌ ይቺ ናት !! ”ሌጆች በርትታችሁ ተማሩ ! ሇዚች ሇወዯቀችና ሇተጎሳቆሇች ሀገር ተስፋዋ እናንተ ናችሁ ! ይሇን ነበር። አዎ ይሇን ነበር ! ታዱያ እሱ እንዲሇው ሆነን ተገኘን ???! ሇመሆኑ :
- የስብስቴ ነጋሲ / ቤት የማስተማር መማር ምን ይመስሌ ነበር ?
- የማስተማር ዜዳውና ውጤቱ፤
- ስነ ምግባር፤ የአገርና የባንዱራ ፍቅር፤
- ጤናማ የትምህርትና የእስፖርት ውዴዴሮች፤
- ተማሪውና የዩኒፎርም ሌብስ፤
- በነገው ሰው የሬዱዮ የሳይንስና የታሪክ የት / ቤቶች ውዴዴር የስብስቴ ቦታ፤
- የፍቅር ዯብዲቤና ጣጣው፤
- የመጀመሪያው የሠሊማዊ ሰሌፍ አዴማችንና የፈጥኖ ዯራሽ ወታዯር፤
- ዓመታዊ የውጤት ሽሌማትና ጎበዝ ተማሪዎች፤
- ሇመሆኑ ሇምን ንፋስ ስሌክ ተባሇ ?
- የንፋስ ስሌክ አጠቃሊይ 2 ዯረጃ /ቤት ከመሠራቱ በፊት የስብስቴ ነጋሲ ተማሪዎች ወዯ 2 ዯረጃ ሲዯርሱ የት ይመዯቡ ነበር ?
- የንፋስ ስሌክ አጠቃሊይ 2 ዯረጃ /ቤት በምን ያህሌ ተሠራ ?
- የትናንቱና የዛሬው፤ የንፋስ ስሌክ አጠቃሊይ 2 ዯረጃ /ቤት ተማሪዎች በአጉሌቶ መነጥር ሲታይ፤ ምን ይመስሊሌ ?
- በአገር ግንባታ ወይም ማፍረስ፤ የስብስቴ ነጋሲ፤ከዚያም፤ የንፋስ ስሌክ አጠቃሊይ 2 ዯረጃ /ቤት ተማሪዎች ዴርሻ…… . ወዘተ ቀጣይ ወጎች ሆነው በሁሊችንም ተሳትፎ ቢቀርቡስ ?………… ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
feredewnetu

ኮትኳች

Joined: 24 Sep 2009
Posts: 202

PostPosted: Thu Feb 09, 2012 1:16 am    Post subject: Reply with quote

ወለላዬ አንደገና ላመስግንህ አወዳለሁ የዝናዬን ድርስት ስላካፈልከን :: ስሞኑን ሌላ የሚያሳዝነው ነገር ታላቁ መሪ ጃንሆይ ለአፍሪካ የአበርከቱት ድርሻ ጉልህ ሆነ አያለ መታስቢያ አንዲደርግላቸው በላመድረጉ ሲሆን ግን ምን ይደረጋል ራስ ያቀለሉት አይደል የሚባለው :: የገዛ ራሳቸውን ቤተ መንግስት ለደሀ ልጅ መማሪያ የስጡ ንጉስ ስንቱ ተውርቶ በዚህ ርእስ ሳይሆን በሌላ አርስት ክፍተን መወያየት አንችላለን :: ጃንሆይ ታልቅ መሪ ነበሩ ::
ጋሽ በላይ በጣም ደግ ርሁርህ ስው ነበር ለዚህም ነው ኮሚንስቶች አጥምደው ለዚህ የዳረጉት :; አስማረ ግረፌ ጎበዝ ተማሪ ነበር :: ከካሱ ጋራ ከአንደኛ አስከ ዩኒበርስቲ አብረን ተምረናል ጥይት ነበረ ንፈሱን ይማረውና ብርሀኑ ነጋ ጌታቸው ማሞ ንጉሰ አለሙ አንድ ዶርም ውስጥ 6 ኪሎ ንበሩ ካሱ አንደተገድለች ከንጉሰ በስተቀር ሁሉም ጠፉ :: አዚህ ላይ ብርህኑ ነጋ መጽህፉ ላይ የተስፋዬ ደበሳይ ሹፌር ነበርኩ ያለው አሱ ሳይሆን ገስጥ /ማርያም በቀይ ሽብር የተገደለ ነው :: ገና ብዙ ታሪክ ይወጣል : ኢትዮጵያዊነት ማለት ለመሆኑ ምን ድነው ? ...... ይቀጥላል
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
መላጣ

ዋና ኮትኳች

Joined: 27 Feb 2004
Posts: 567

PostPosted: Thu Feb 09, 2012 5:18 pm    Post subject: Reply with quote

መምህር በላይነህ ተወዳጅነት ካላቸው አስተማሪዎቻችን ውስጥ የመጀመሪያው ነው ብል አልሳሳትም :: ምክንያቱም በሚሰጠን 15 ደቂቃ የረፍት ጊዜ ውስጥ አብዛኛውን ጊዜ የሚያሳልፈው ከተማሪዎች ጋር ተደባልቆ ነው :: በዚህም ከተማሪው ጋር በብዛት በመቀራረቡ የተነሳ ትቸር ብለን ሳይሆን የምንጠራው "ጋሽ በላይ " በማለት ነው ::

ጋሽ በላይ እንደተገለጸው ላለባበሱ የማይጨነቅ ከመሆኑም በላይ ፀጉሩ ከሚዶ ጋር ትውውቅነት ያለው አይመስልም ነበር :: ግን በውስጡ ያከማቸው ብሶት እንዳለ ሰውነቱና ፊቱ ይገልጹ ነበር :: ምንም እንኳ ብዙ ማለት ባይፈልግም በነበረው ያስተዳደር ሁኔታ ደስተኛ ባለመሆኑ ይመስላል ሰውነቱ የተጎሳቆለ መስሎ ብዙ ሳቅ የማይታይበት ::

ጋሽ በላይ ሲጋራ አጫሽ እንደመሆኑ መጠን አንዴ ያቀጣጠላትን ሲጋራ በሁለት ጊዜ ስቦ ፍሊተሯ ላይ የሚያደርስ ስለነበረ አብዛኛው ተማሪ በሁኔታው በጣም እንገረም ነበር :: እኛም ታዲያ እንደሱ ሙከራ አድርገን ስንቶች ይሆን የተለከፍን ?

ጋሽ በላይ ደግ ከመሆኑም በላይ ለተማሪው ያስባል :: ጥሩ ዜጎች እንድንሆን አውቀን ለሌላው እንድናሳውቅ ይመክራል :: ቶሎ አይበሳጭም ስህተት እንዳናደርግ ይመክራል ካንዴም ሁለቴ ይገስጻል :: ይህን ካለፈ ግን በኩርኩም ያቀምሳል ጭንቅላት በቀለበት ከተገኘ ኳስ አከለ ማለት ነው ::

ስብስቴን አጠናቀን ከወጣን በኃላ እድገት ጨመረ ዓመታት ለውጥን ወለዱ ብዙ ነገሮች መሆን ሲገባቸው እንዳልሆኑ ሆኑ :: ለአገር ለወገን የሚጠቅሙ አባት እናቶች ወንድም እህቶችን የበላ ዘመን ስለተተካ የምንወደው የምናፈቅረው ጋሽ በላይም የዚህ ሰለባ ሆነ ::

እንዴት ለሚለው ተጨባጭ መረጃ ባይኖርም :- ይቀጥላል !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
መላጣ

ዋና ኮትኳች

Joined: 27 Feb 2004
Posts: 567

PostPosted: Wed Feb 15, 2012 3:56 pm    Post subject: Reply with quote

ወጥቶ በሰላም መመለስ ብርቅ በነበረበት በዚያ 17 የሰው በላ ሥርዓት ዘመን ያልተነካ ማን አለ :: ወጣት ሽማግሌ አሮጊት ኮረዳ በቀይ ሽብር የተጨፈጨፉበት : አስከሬን በዱር ገደል ጫካና መንገድ ላይ የተወረወረበት አስከፊው ጊዜ የሚረሳ አይደለም ::

እከሌን ገደሉት እንጂ በምን ምክንያት ገደሉት የተባለው ቃል ጥያቄ በማይቀርብበት ሁኔታ የታጠቀ ዘበኛ ሁሉ ፈራጅ ሆኖ የስንቱን ዜጋ ህይወት ቀጠፈ ::

በዚያን ወቅት ዜጎች በጅምላ ለሊቱ ላይ ጫካ እየተወሰዱ እንደሚረሸኑና እድል ያጋጠመውም ከሩምታው ተርፎ በጭለማ ጫካውን አቆራርጦ ህይወቱን ያተረፈ እንዳለም ይነገር ነበር :: ጋሽ በላይም በዚህ አጋጣሚ ለሊቱ ላይ ወደ ጎፋ ገብርኤል እልም ያለ ጫካ ውስጥ ወታደሮች ይዘዋቸው በመምጣት ከመኪና አውርደው ነብስ ያውጣህ እሩጥና አምልጥ በማለት በትነዋቸው የያዙትን መሳሪያ ጥይት አልተኮስክም እንዳይባሉ ይመስላል ወደሰማይ እያንጣጡት ከጨረሱ በኃላ ወደመጡበት የተመለሱት ::

ጋሽ በላይም በዚህ አጋጣሚ እድል ቀንቶት ለሊቱ ላይ ጫካውን አቆራርጦ አባ ሳሙኤል ወደሚባለው ሥፍራ በማምራት ቀደም ሲል የሚያውቃቸው ሰዎች ወይም ዘመዶች ሳይሆኑ አይቀርም ገበሬ ማኅበር ማለት ነው ይቀላቀላል :: ያለውን ሁኔታ በመጠኑም ቢሆን ያስጠለሉት ሰዎች የሚያውቁ ይመስላል ለብዙ ጊዜ ያስቀምጡታል :: ጊዜው እየጨበረ በሄደ ቁጥር ጉርጉምታ በመሰማቱ ሰዎቹ ይፈራሉ እሱም ሰዎቹን ላለማስበላት አስቦ ሳይሆን አይቀርም እንደ ባህታዊ ለብሶ ወደ አቃቂ ለመግባት ሲል ዱከም አካባቢ አግኝተው በላይ መሆኑን በማረጋገጥ ገደሉትን የሰማነው ::

ጋሽ በላይም ሆነ የተቀሩት ያለፍርድ ያለ ዳኝነት ህይወታቸው በከንቱ ያለፈውን ሁሉ እናስባለን :: ነብሳችሁ ፀጋን ትውረስ ---አሜን ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ኡቹሩ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 23 Oct 2011
Posts: 96

PostPosted: Sun Feb 19, 2012 2:45 pm    Post subject: Reply with quote

መላጣ እንደጻፈ(ች)ው:
ወጥቶ በሰላም መመለስ ብርቅ በነበረበት በዚያ 17 የሰው በላ ሥርዓት ዘመን ያልተነካ ማን አለ :: ወጣት ሽማግሌ አሮጊት ኮረዳ በቀይ ሽብር የተጨፈጨፉበት : አስከሬን በዱር ገደል ጫካና መንገድ ላይ የተወረወረበት አስከፊው ጊዜ የሚረሳ አይደለም ::

እከሌን ገደሉት እንጂ በምን ምክንያት ገደሉት የተባለው ቃል ጥያቄ በማይቀርብበት ሁኔታ የታጠቀ ዘበኛ ሁሉ ፈራጅ ሆኖ የስንቱን ዜጋ ህይወት ቀጠፈ ::

በዚያን ወቅት ዜጎች በጅምላ ለሊቱ ላይ ጫካ እየተወሰዱ እንደሚረሸኑና እድል ያጋጠመውም ከሩምታው ተርፎ በጭለማ ጫካውን አቆራርጦ ህይወቱን ያተረፈ እንዳለም ይነገር ነበር :: ጋሽ በላይም በዚህ አጋጣሚ ለሊቱ ላይ ወደ ጎፋ ገብርኤል እልም ያለ ጫካ ውስጥ ወታደሮች ይዘዋቸው በመምጣት ከመኪና አውርደው ነብስ ያውጣህ እሩጥና አምልጥ በማለት በትነዋቸው የያዙትን መሳሪያ ጥይት አልተኮስክም እንዳይባሉ ይመስላል ወደሰማይ እያንጣጡት ከጨረሱ በኃላ ወደመጡበት የተመለሱት ::

ጋሽ በላይም በዚህ አጋጣሚ እድል ቀንቶት ለሊቱ ላይ ጫካውን አቆራርጦ አባ ሳሙኤል ወደሚባለው ሥፍራ በማምራት ቀደም ሲል የሚያውቃቸው ሰዎች ወይም ዘመዶች ሳይሆኑ አይቀርም ገበሬ ማኅበር ማለት ነው ይቀላቀላል :: ያለውን ሁኔታ በመጠኑም ቢሆን ያስጠለሉት ሰዎች የሚያውቁ ይመስላል ለብዙ ጊዜ ያስቀምጡታል :: ጊዜው እየጨበረ በሄደ ቁጥር ጉርጉምታ በመሰማቱ ሰዎቹ ይፈራሉ እሱም ሰዎቹን ላለማስበላት አስቦ ሳይሆን አይቀርም እንደ ባህታዊ ለብሶ ወደ አቃቂ ለመግባት ሲል ዱከም አካባቢ አግኝተው በላይ መሆኑን በማረጋገጥ ገደሉትን የሰማነው ::

ጋሽ በላይም ሆነ የተቀሩት ያለፍርድ ያለ ዳኝነት ህይወታቸው በከንቱ ያለፈውን ሁሉ እናስባለን :: ነብሳችሁ ፀጋን ትውረስ ---አሜን ::አሀ እድሜ ተገብ የኢሀአፓ አባላት ናቹህሳ ለካ

ኢትዮጵያ ትቅደም
ኡቹሩ ከግራዚያኒ መንደር ቀበሌ 54
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዲጎኔ

ዋና አለቃ

Joined: 19 Aug 2005
Posts: 4206
Location: united states

PostPosted: Sun Feb 19, 2012 8:04 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችን ይሁን
በኢትዮጲያ ህዝቦች የአርነት ታሪክ ትውልድ የፈጸምው ድንቅ ተጋድሎ ማንም በጎ ህሊና ያለው የሚረዳው ነው ::ምንም እንኩዋን የአመራር ችግርና ጀብደኝነት ድንቃራ ቢሆኑም በኢህአፓ ጥሪ ትግሉን ተቀላቅለው የደርግ ግድያና ድለላ ሳይበግራቸው የደከሙ የተገረፉና የታረዱት ሁሌም ሊታሰቡ የሚገባ ናቸው ::በስደት ያለው ለሁለት የተከፈለ ድርጅት ይህን ድንቅ ገድል ለምን እንደማይዘግብ ለመጭ ትውልድ እንደማይጽፉ አይገባኝም ::ይህ ያነበቡ ለአመራሮቹ ሹክ እንዲሉ በዚህ አጋጣሚ አስስባለሁ ::
ጋሽ በላይ ከዛ ትውልድ እንቁዎች 1 ሲሆን ታሪኩን ሰምቻለሁ እዚያው ትምህረት ቤት የነበሩ መምህራን በከርቸሌ በሰንበል ታስረው
መከራ የተቀበሉ የደርግ እስረኞች ከአንደኛ ደረጃ እስከ 2 ደረጃ ድረስ የትምህርት እድል እንዲያገኙ አብቅተዋል ::
በሌሎች 2 ደረጃ ትምህርት ቤቶች የነበሩ ለህዝባችን ድንቅ ከሰሩ መምህራንና ተማሪዎች መካከል የሽመልስ ሀብቴው ዶር አበራ ገይድ ፓስተር ኢንስቲቱትን ያሳደጉ ከተማሪዎቹ የምኒሊክና የአስፋውሰውን እጅግ ብሩህ ተማሪዎች /ገብርኤል አድሀኖምና የፍሉሀዎቹ ግርማ አሰግድና ዘርሁን በለጋነት ያላቸውን ለኢሀፓ ሰጥተው ህይወታቸው የከፈሉ ለዘላለም ይታወሳሉ ::
ዲጎኔ ሞረቴው በክርስቶስ ከዛ ትውልድ እልቂት የተረፈው
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወለላዬ

ዋና ኮትኳች

Joined: 26 Jan 2005
Posts: 519
Location: united states

PostPosted: Sun Feb 19, 2012 11:24 pm    Post subject: Reply with quote

በውስጥ መጻጻፊያ የተላከልኝ
To: ወለላዬ
Posted: Sun Feb 19, 2012 9:49 pm
Subject: Re: ሰላም ለአንተ ይሁን ወለላዬ Quote message
ይድረስ ለሀገር ልጅ ወለላዬ ;

ያንን የወገን አጥር የነበረውን መምህር ከዘመናት ቆይታ አስታውሰህ አመጣህልን :: ደስ ብሎን ተካፈልንህ :: ዛሬም ጥቂት ብል አትገፈትረኝም ብዬ ወንድማችን መላጣው ባለው ላይ ትንሽ ሀሳቡን ፈርጅ ለማስያዝ ላግዘው ብቅ አልኩ ::

በመጀመሪያ መላጣው ከትዝታው ኮሮጆው ያለውን በማካፈሉ ደስ ተሰኝቻለሁና ምስጋናዬ እነሆ ይድረሰው ::

መምህር በላይ ለሞት በተጠራበት ጊዜ እንደወትሮው ሁሉ የተረጋጋ እና ሁሌም ቆጥቦ የሚያሳየን ትንሽዋ ፈገግታው ፊቱ ላይ ነበረች :: ድንጋጤ አይታይበትም :: ለነገሩ በአዘቦቱ የእስር ቆይታችን አንዴ አንዱ እስረኛ መምህር በላይ የአዲስ አበባ ልጅ ይመስለው ስለነበር መምህር የት ሰፈር ነው ያደከው ሲለው አርበኛው ሀይለ ማርያም ማሞ ካደገበት ያለውን አስታውሳለሁ :: 1958 ወይም 1959 . . ከትምህርት ቤቱ ማትሪክ ካለፉት 3 ምርጥ ተማሪዎች አንዱ እንደነበርና (ምናልባት ደብረ ብርሀን ሊሆን ይችላል ) በውጤቱም የአለም ማያ ዩንቨርስቲ ኮሌጅ የተቀላቀለውም እስከ ሶስተኛ አመት ድረስ አጠናቆ የተማረም ነበር .:: አራተኛ አመቱን ያላጠናቀቀበት ምክንያት የጠመመበት ኮርስ ይኑር ወይ በችግር ምክንያት አላስታውም ::

ወደ መላጣው መሰረታዊ አስተያየት ልመለስና : ከመጀመርያው የሞት ግድያ አመላለጥ በትክክል ከመምህር በላይ ከራሱ አንደበት የሰማሁትንና የማስታውሰውን እነሆ ::

በወቅቱ እስረኞች ስማቸው ለሞት ሲጠራ ገና ከበሩ መፈክር እያሰሙ ለኢትዮጵያ ህዝብ የዲሞክራሲ መብት ማግኘት አንድ ቀን ግድ እንደሚል እያሳሰቡ ወታደራዊው የጁንታ መንግስትና ግብረ አበሮቹን እያወገዙ ነው የሚወጡት :: ከበር ላይ ለመረሽን የተመደቡ የመንግስቱ ሀይለ ማርያም ገዳይ ጋንጎች በጠረባ እየተቀበሉ እስረኞቹ ከመሬት ተዘርረው ሲወድቁ እዚያው የወደቁበት ላይ እጃቸውን የሁዋሊት የፊጥኝ በገመድ አስረው ልክ እንደ ጤፍ ኩንታል ሁለት ጁንታዎች አንዱ የእስረኛውን እግሮች ሌላው ጁንታ የእስረኛውን ኮሌታ በመያዝ የወታደራዊ ማክ መኪና ላይ ይወረወራሉ :: በሆነ አጋጣሚ ያን ቀን የማን እንደሆነ የማላስታውሰው እስረኛ የታሰረበት ገመድ ላልቶ ኖሮ አንድ እጁን አሾልኮ ከታሰረበት ገመድ ያወጣል ከዚያም ሁለት እጆቹ ነጻ ሆኑ :: የወታደራዊው ማክ ከሁዋላው ገዳይ ጦር ሰራዊቶችን በጫነና BR በጠመደ ጂፕ ታጅቦ ወደ ግድያ ወረዳው እየሄደ ነው ቀኑም እየመሸ ነበርና እጁን ከገመዱ እስር ነጻ ያወጣ እስረኛ የሌላውን እስረኛ ገመድ ፈታ :: እንዲያ እየተባለ እንዱ የሌላውን እስር ሲፈታ የወታደራዊው ማክ ከአዲስ አበባ የከተማ ክልል ወጥቶ ነበር :: የማኩን ሸራ (የጦር ሰራዊት መኪናዎች የሚሸፈኑበት ሸራ ለማለት ነው ) ወደ ላይ ሰብሰብ በማድረግ ልክ ማኩ መታጠፊያ ከርቭ ላይ ሲደርስና ሲታጠፍ ከሁዋላ የሚከተለው የጂፕ መኪና መብራት አያገኘውም :: ያን ጊዜ አንድ ወይም ሁለት እስረኞች ይዘሉና ወደጢሻው ይንከባለላሉ :: ከእይታ ለመሰወር :: እንደ መምህር በላይ አባባል (ለሁለተኛ ጊዜ ታስሮ ሲመጣ የነገረንን ከማስታውሰው ) እሱ የዘለለው ብዙ እስረኞች ከዘለሉ ብሁዋላ ነበር :: በእለቱ ሊታረዱ የወጡት አስረኞች ቁጥር አሁንም በትክክል እንደማስታውሰው 41 ነበር ::

መምህር በላይ የዘለለው የኢህአፓ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል የነበረውንና የአዲስ አበባ ብርጭቆ ፋብሪካ (ጉለሌ ) ስራ አስኪያጅ ከነበረው ኢንጅነር ኡስማን እንዲሁም ናዝሬት ወወክማ የሚል ሸርት ከለበሰ ጋር ትንሽ መንገድ አብረን ሮጠን መልካም እድል ተባብለን የራሳችን አቅጣጫዎች መርጠን መሮጣችን ቀጠልን አለን : ናዝሬት ወወክማ የሚል ሸርት ይለብስ የነበረው የሁዋላ እሸት የተባለው የክፍላችን እስረኛ ለመለየት ለማንኛችንም አልከበደም ::

መምህር በላይ ከአንደበቱ እንደተናገረው : እነሱ በሌላ አቅጣጫ ሲሮጡ እሱ ግን በማታ የማክ መኪናውን የመብራት ፋና እያየ በጢሻው እየተሽሎከለከ ይከተላቸው ነበር :: አንዴም ልክ እስሮኞች ከርቭ ላይ ሲዘሉ ይከተል የነበረው ጂፕ መብራት ከርቩን ጨርሶ ሲዞር መብራት ላይ ገቡ ::ጁንታዎቹ ወርደው እነዛን አርደው እዛው ጥለዋቸው ጉዞ ሲቀጥሉ ሁሉ ተከትሎ አይቷል :: በመጨረሻም የቀሩትን (ያልዘለሉትን ወይም ሊዘሉ ያልቻሉትን ) ከተዘጋጀው መታረጃ ቄራ ደርሰው ከማኩ አስወርደው ሲደረድሩዋቸው ከዚያም በጥይት እሩምታ ሲደበድቡዋቸው መምህር በላይ ከጢሻው ውስጥ ከቅርብ እርቀት ሲከታተል እንደነበርና በመጨረሻም የገዳዮች ቡድን መሪ የተረሸኑትን እያንዳንዱን ሟች እስረኛ በአንዳንድ የማጣርያ ጥይት ግንባር ግንባራቸውን ዳግም በጥይት ሲመታ እንዳስተውለ ከራሱ ከመምህር በላይ የሰማሁት እማኝነት ቃሌ ነው ::

ከዚያስ : ከዚያማ ያችኑ ብጫ ጥለት ነጠላውን ካንገቱ ላይ ጣል እንዳደረገ አንድ ወደ ሚያውቀው ሰው እንደተጠጋና ከዚያም ለመተዳደርያው ቆፍጣና መምህር የዘበኝነት ስራ አግኝቶ እየሰራ ዳግም ጸረ ደርግ ትግሉን ቀጠለ :: የሁለተኛ ዙር አያያዙን በመጀምሪያው ገፅ ላይ ገልጬዋለሁና መድገሙ አይታየኝም ::

ይህንን መጻፍ ያስፈለገኝ ወንድሜ መላጣ ሲጽፍ ወታደሮቹ አምልጡ እንዳላቸውና የገደሉ ለማስመሰል ጥይት ወደ ሰማይ እየተኮሱ ....................... በማለቱ ከመምህር በላይ ከራሱ ክሟቹ አንደበት የሰማሁትን ለንጽጽር ማቅረቤ እንጂ ወንድሜ መላጣ ያቀረበውን መቃወሜ አይደለም ::

ጉዳዩ በዚህ አላበቃም :: ከብዙ ሳምንታት በሁዋላ ዳግም መምህር በላይ ሲታሰር : የሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ምርመራ ሀላፊ የነበረው አረመኔው የአምሳ አለቃ ተሾመ ሁለት አይኖቹ ፈጠጡ :: መምህር በላይን እበራችን ድረስ መጥቶ አንተን እኮ እንድትመታ ለቡድኑ ፈርሜ ስጥቼህ ነበር አለው :: የመምህር በላይ መልስ ምን ቢሆን ጥሩ ነበር ትላላችሁ ???? እሱ ግን የመለሰው "" እኔ እንጃ "" እርምጃ እንዲወሰድብህ ለመውጣትህ ነው እኔ እንጃ የምትለኝ ?? አለ ሀምሳ አለቃው !!!! አይ በላይሻ አሁንም ደግሞ አዎ ሲለው በቁጣ እየተንተከተከ ተመለሰ :: ምን ያድርገው :: መምህር በላይን እንኩዋን ቁጣ እና ግልምጫ ስድስት ሰአት የፈጀ ቶርች እንኩዋን የሚመልሰው አልባሌ ሰው እንዳልሆነ ራሱ ሀምሳ አለቃ ተሾመ ያውቃል :: ደግሞ ዝም እንዳይባል ሰውየው መምህር በላይ ነው :: ካንድ ብርጌድ ጦር በላይ የሚያስፈራ በጭንቅላቱ እውቀትም ሆነ በወኔው :: ግራዝያኒ መንግስቱ ሀይለማርያምን ለሽንት እንኩዋን አላስወጣ ያለ :: በአንድ አሮጌ ታክሲ ሆኖ ፋሺስት መንግስቱ ሀይለማርያምን ማታ ከደርግ ጽህፈት ቤት ሲወጣ ከአፍሪካ አዳራሽና እስጢፋኖስ ቤት ክርስቲያን መሀል ተቀብሎ አራተኛ ክፍለ ጦር (መሹዋለኪያ ) ዘሎ ገብቶ እስኪያመልጠው ድረስ በአንድ አነስተኛ ኡዚ ጠመንጃ ያሩዋራጠ የመንግስቱ ሁለቱ ቦዲ ጋርዶች መልሶ ለመተኮስ እንኩዋን የሰከንድ ጊዜ ቢያሳጣቸው መንግስቱን ላንድሮቨር ወለሉ ላይ ጥለውት እነሱ ከላዩ ላይ ተኙ :: ሁለቱም ቦዲጋርዶች ወዲያው ሲሞቱ መንግስቱም ገና አንድ ጥይት መዋሂቱ ላይ ከማግኘቱ ላንድሮቨሯ ክፍለ ጦሩ በር ላይ ደርሳለት ኖሮ ተረፈ :: መምህር በላይም ወደመጣበት ተመለሰ :: ማን ተከትሎ :: መንግስቱን አጅበው የነበሩ ጂፖች እንኩዋን በላይን ለመከተል አልደፈሩም ::እነሱ ያሰቡት አንድ ሀያል ጦር መንግስቱን እንዳባረረ ብቻ ነበር :: እውነቱን ነው : መምህር በላይ የት ሰፈር ነው ያደከው ሲባል አርበኛው ሀይለ ማርያም ማሞ ካደገብት ያለው ::

ሌላው የወቅቱ ችግር ያን ቀን እነ መምህር በላይ ላይ እርምጃ እንዲወስዱ የተምደበው ቡድን የተሰጠኝን እስረኞች ላይ በሙሉ አብዮታዊ እርምጃ ወስጃለሁ ብሎ ነው በማግስቱሪፖርት ያደረገው :: የተለመደው አሰራራቸው ነበር :: መምህር በላይ ዳግም ሲያዝ የሶተኛ ፖሊስ ጣቢያው አረመኔው ሀምሳ አለቃ እኔ 41 እስረኞችን መምህር በላይን ጨምሬ ለቡድኑ ሰጥቻለሁ አለ :: የገዳይ ቡድኑ ደግሞ እኔ ፈርሜ የተቀበልኩትን በሙሉ ገድያለሁ : መምህር በላይን ግን አልሰጠህእኝም ነበር ብሎ መለሰ ::ጦርነት መሳርያ መማዘዝ የቀረው አይነት ሆነ በመሀላቸው :: መምህሩ ደግም የሚመልሰው አሁንም እንደገናም እኔ እንጃ ሆነ :: ያኔ ነው ልክ እንደበፊቱ መምህር በላይን መልምሎ ከጎኑ ለማሰለፍ የደርግ አባሉ ብርሀኑ ባየህ እንደገና መመላለስ የጀመረው :: ሆነም ቀረ ; መምህሩ የሚለሳለስ አይነት ሆኖ አልተገኘም :: ቀጥ ያለ ከእምነቱ ፈቀቅ ወይ ነቅነቅ የማይል ጥቅም የማያባብለው ምቾት የማያጉዋጉዋው የፕሪንሲፕል ሰው ነበርና መምህር በላይ ገብረ ማርያም ለኢትዮጵያ እንጂ ለፋሺስቱ ደርግ እንደማይጠቅም ታምኖ ዳግም ሞት ተፈረደበት :: አልባሌ ሰዎች አረዱትም :: ግራዚያኒ መንግስቱም ነጻ ወጣ አደባባይም መታየት ጀመረ :: ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ለሞት የሚሄዱ እስረኞች በሰንሰለት መታሰር ጀመሩ ::

ከምስጋና ጋር
View user's profile

Reply to message All times are GMT
Jump to:

Provided by CyberEthiopia.com , pow
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
ወለላዬ

ዋና ኮትኳች

Joined: 26 Jan 2005
Posts: 519
Location: united states

PostPosted: Sun Feb 19, 2012 11:38 pm    Post subject: Reply with quote

ዝናዬ በድጋሚ ቢኢሜል የላከልኝ

ሠላም የስብስቴ ልጆች ወለላዬ፤ ፍርድ ዕውነቱ፤ መላጣው እንዲሁም ቆንጂት እንደምን ሰነበታችሁ ?

ለአምላክ አምላክ ይስጠው እኔ ደህና ነኝ !

የጋራችን ስለሆኑት ስለ ስብስቴና ንፋስልክ አጠቃላይ / ቤቶቻችን ጥቂት ለማለት ነው ::

1969 የትምህርት መባቻ ላይ ነበር ከንፋስ ስልክ አጠቃላይ 2 ደረጃ ቤት ተማሪዎች ለጊዜው ከማስታውሳቸው መሃከል፤ አስማረ ግረፌ፤ ረዘነ ገብረስላሴ፤ ካሱ አቦዬ፤ ብርሃኑ ነጋ፤ ጌታቸው ማሞ እኔ እና ከሴቶች ደግሞ ዓለም ፀሃይ ያባቷን ስም እረሳሁት ቤቷ ከስበቴ ጀርባ ከባቡር ሃዲሩ በታች የነበር፤ 6ኪሎ ዩነቨርስቴ እንደነበርን አውቃለሁ :: አንድ ቀን እኔ ብቻዬን ከመኝታ ሕንፃ 501 ወደ መማሪያ ክፍል ስሄድ፤ ካሱ አቦዬ፤ ብርሃኑ ነጋ፤ ጌታቸው ማሞ እና ሌሎች ተገናኝተን ካሱ አቦዬ ቆም ብላ ሰላም ተባብለን ትንሽ አውርተን ተለያየን፤ ከካሱ አቦዬ ጋር 8 ክፍል አብረን ነበርን ከአስማረ ግረፌ ጋር ደግሞ በንፋስልክ አጠቃላይ 9 እና 10 ክፍል በአንድ ክፍል አብረን ተምረናል… ..የት / ቤታችንና የት / ቤት ጓደኞቻችንን ታሪክ እንደዘመኑ ሸፍጠኞች በገመድ ጠልፈን ሳንጥል አብረን እየተጋገዝን ከመሰረቱ እንድንጽፈው ያስፈልጋል ::

ስብስቴ ነጋሢ / ቤት እንደ አገራችን ኢትዮጵያ የሁሉም እናት ነበረች፤ ከቃሊቲ፤ ከዳርማር፤ ከሳሪስ፤ ከቡልቡላ፤ ከፉሪ፤ ከንፋስ ስልክ፤ ከመሿለኪያ፤ ከጨርቆስ፤ ከልደታ፤ ከድሮው አውሮፐላን ማደፊያ፤ ከሳር ቤቶች፤ ከጠባይ ማረሚያ ሰፈር፤ ከቄራ፤ ከጎፋ፤ ከጎተራ ከዘይት ቤት ..ወዘተ ቀበሌ የሚባል መጠሪያ ሳይፈጠር በፊት የምንሰባሰብባት ድንበር የለሽ የፍቅርና የእውቀት ጠበል እየቀዳን የምንጎነጭባት / ቤታችን ነበረች ::
እኔ መጀመሪያ የድሮው አውሮፕላን ማረፊያ አጠገብ ከአሸዋ ሜዳ ወዲህ ካሉት ሳር ቤቶች አጠገብ ከኮተኒ በታች ካቶ ብሩክ ሠፈር ጓደኞቼ፤ ይጥና አብሬ፤ ጌታደጉ አባ ቡላ፤ ካሳሁን፤ ከልደታ ከሚመጡት ሃይሉ (ቀጭኔ ) የቅጽል ስሙ ከታናሽ ወንድሙና ጓደኞቹ ጋር ሆነን የአትክልት ሠፈሩን አቋርጠን ቄራ ስንደርስ ደግሞ ከቄራ ልጆች መብራቱ ልመንህ፤ ጌታቸው (ቁራ ) ሱልጣን (ተምትም ) አባተ እና ሌሎች ሆነን ወደ ስብስቴ ስንተም መሃይምነትን ድል ለመንሳት የዘመተ ጦር እንመስል ነበር ::
አዎ መሃይምነትን ገና በልጅነት ድል ለማድረግ የቆረጥን ርቀት የማይገድበን ረሃብ የማይፈታን ከህዝብ አብራክ የወጣን የህዝብ ልጆች !
በትንንሽ አካሎቻችን ውስጥ ትልልቅ መንፈስና ምኞት ሰንቀን / ቤታችን እንደደረስን በሰንደቅ አላማችን መዝሙር ለአገራችን ቃል ገብተን፤ በጸሎት የውንድማማችነትና የህትማማችነት ፍቅር ልባችንን ሞልተን ነበር ትምህርት የምንጀምረው……………… ባቡሩ መጣ ! እንዳያመልጠኝ ሲያመቸኝ ብቅ እላለሁ :: እብስ !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
ሀዲስ 1

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 10 Mar 2010
Posts: 1631

PostPosted: Mon Feb 20, 2012 1:33 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ዝናዬ !
ሰላም ለሌሎቻችሁ የቤቱ ተሳታፊዎች ሁላ !

የዝናዬን ትረካ ሳነብ የሆነ ነገር ታወሰኝ :: ይሄንን የሚረሸኑ ሰዎች በማክ መታገዝና በመሀከሉም የአንዱ እጅ እነደተፈታና የሌሎቹንም ፈትቶ እንዴት ለማምለጥ እንደበቁ ጥንት በህፃንነቴ የሰማሁት ታሪክ ነው :: አንዴ አይደለም የሰማሁት ::
የሆነ ተረት ይመስለኝ ነበረ :: ግን ደግሞ ተረት እንዳይመስለኝም ታዲያ ሌላ የተፈፀመ ታሪክ እንደገና ስለሰማሁኝ የዚህን ታሪክ እውነተኝነት አምኜ ይሄንን ያህል አመት ልቀመጥ በቅቻለሁኝ ::

ወንድሜ ዝናዬ ሆይ !!!
ለረሸኑ ከተጋዙት ውስጥ አንድ ስሙ ተስፉ ልመታ የሚባል የቂርቆስ ልጅ እንደነበረ አውቃለሁኝ :: ማለት ተስፉ ልመታ ካንተም ጋራ ታስሮ ነበረ ማለት ነው :: ታውቀው ነበረ ????

አንድ ሌላ የሰማሁት ታሪክ ያልኩህ ታዲያ :--- የተስፉ አባት አቶ ልመታ በበኩር ልጃቸው ሞት በጣም ጥልቅ ሀዘን ላይ እያሉና (ተስፉ እንደተገደለ ነው መጀመሪያ ቤተሰቦቹ የተነገራቸው ) በህይወት ተስፋ ቆርጠው ባሉበት ሰዓት (አመታቶች አልፈው ) የሆኑ ሰዎች መጥተው
ልጅዎት ተስፉ አልሞተም : በህይወትም አለ ይሏቸዋል :: እሳቸውን ግን ምንም ቢሆን አላምንም ብለው ድርቅ ይላሉ :: ሰዎቹም እንግዲያውስ ካላመኑን እሱ ወዳለበት ቦታ አይንዎን ሸፍነን ወስደንዎት እናሳይዎታለን : ግን ለዚህ ፈቃደኛ ይሁኑ ይሏቸዋል :: አቶ ልመታ ግን ምንም እንኳን የልጃቸውን በህይወት መኖር ለማየት በጣም ጉጉ ቢሆኑም : እንዴት አድርገው ግን እኒህን ሰዎች ይመኗቸው ??? በዚህ አይነት የዚህ ታሪክ እውነተኛነት ሳይገለጥ ቀረ :: ግን ብዙዎች ወጣቶች የተስፉን ማምለጥ ያረጋግጡ ነበረ :: እንደውም ያለው አሲምባ እንደሆነ አስረግጠው የሚናገሩ ነበሩ ::

ውድ ወንድሜ ዝናዬ !!!
ለመሆኑ ስለተስፉ በህይወት መትረፍ (ማምለጥ ) የምታውቀው ታሪክ አለ ???
እስኪ በፈጠረህ ስለተስፉ የምታውቀውን አሳውቀኝ :: ተይዞ የታሰረው 1967 ይሁን 1968 በኢህአፓ በተዘጋጀው ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ተገኝቶ ነው :: ይህ ሰላማዊ ሰልፍ የተደረገው የሜይዴይ በዓልን በማስመለከት ነበረ :: እንደውም ሰልፉ ላይ ብዙ ልጆች ተገድለዋል :: ተስፉ በፓርቲው ውስጥም ትልቅ ቦታ እንደነበረው አውቅ ነበረ ::

ሰላም ሁን

ሀዲስወለላዬ እንደጻፈ(ች)ው:
በውስጥ መጻጻፊያ የተላከልኝ
To: ወለላዬ
Posted: Sun Feb 19, 2012 9:49 pm
Subject: Re: ሰላም ለአንተ ይሁን ወለላዬ Quote message
ይድረስ ለሀገር ልጅ ወለላዬ ;

ያንን የወገን አጥር የነበረውን መምህር ከዘመናት ቆይታ አስታውሰህ አመጣህልን :: ደስ ብሎን ተካፈልንህ :: ዛሬም ጥቂት ብል አትገፈትረኝም ብዬ ወንድማችን መላጣው ባለው ላይ ትንሽ ሀሳቡን ፈርጅ ለማስያዝ ላግዘው ብቅ አልኩ ::

በመጀመሪያ መላጣው ከትዝታው ኮሮጆው ያለውን በማካፈሉ ደስ ተሰኝቻለሁና ምስጋናዬ እነሆ ይድረሰው ::

መምህር በላይ ለሞት በተጠራበት ጊዜ እንደወትሮው ሁሉ የተረጋጋ እና ሁሌም ቆጥቦ የሚያሳየን ትንሽዋ ፈገግታው ፊቱ ላይ ነበረች :: ድንጋጤ አይታይበትም :: ለነገሩ በአዘቦቱ የእስር ቆይታችን አንዴ አንዱ እስረኛ መምህር በላይ የአዲስ አበባ ልጅ ይመስለው ስለነበር መምህር የት ሰፈር ነው ያደከው ሲለው አርበኛው ሀይለ ማርያም ማሞ ካደገበት ያለውን አስታውሳለሁ :: 1958 ወይም 1959 . . ከትምህርት ቤቱ ማትሪክ ካለፉት 3 ምርጥ ተማሪዎች አንዱ እንደነበርና (ምናልባት ደብረ ብርሀን ሊሆን ይችላል ) በውጤቱም የአለም ማያ ዩንቨርስቲ ኮሌጅ የተቀላቀለውም እስከ ሶስተኛ አመት ድረስ አጠናቆ የተማረም ነበር .:: አራተኛ አመቱን ያላጠናቀቀበት ምክንያት የጠመመበት ኮርስ ይኑር ወይ በችግር ምክንያት አላስታውም ::

ወደ መላጣው መሰረታዊ አስተያየት ልመለስና : ከመጀመርያው የሞት ግድያ አመላለጥ በትክክል ከመምህር በላይ ከራሱ አንደበት የሰማሁትንና የማስታውሰውን እነሆ ::

በወቅቱ እስረኞች ስማቸው ለሞት ሲጠራ ገና ከበሩ መፈክር እያሰሙ ለኢትዮጵያ ህዝብ የዲሞክራሲ መብት ማግኘት አንድ ቀን ግድ እንደሚል እያሳሰቡ ወታደራዊው የጁንታ መንግስትና ግብረ አበሮቹን እያወገዙ ነው የሚወጡት :: ከበር ላይ ለመረሽን የተመደቡ የመንግስቱ ሀይለ ማርያም ገዳይ ጋንጎች በጠረባ እየተቀበሉ እስረኞቹ ከመሬት ተዘርረው ሲወድቁ እዚያው የወደቁበት ላይ እጃቸውን የሁዋሊት የፊጥኝ በገመድ አስረው ልክ እንደ ጤፍ ኩንታል ሁለት ጁንታዎች አንዱ የእስረኛውን እግሮች ሌላው ጁንታ የእስረኛውን ኮሌታ በመያዝ የወታደራዊ ማክ መኪና ላይ ይወረወራሉ :: በሆነ አጋጣሚ ያን ቀን የማን እንደሆነ የማላስታውሰው እስረኛ የታሰረበት ገመድ ላልቶ ኖሮ አንድ እጁን አሾልኮ ከታሰረበት ገመድ ያወጣል ከዚያም ሁለት እጆቹ ነጻ ሆኑ :: የወታደራዊው ማክ ከሁዋላው ገዳይ ጦር ሰራዊቶችን በጫነና BR በጠመደ ጂፕ ታጅቦ ወደ ግድያ ወረዳው እየሄደ ነው ቀኑም እየመሸ ነበርና እጁን ከገመዱ እስር ነጻ ያወጣ እስረኛ የሌላውን እስረኛ ገመድ ፈታ :: እንዲያ እየተባለ እንዱ የሌላውን እስር ሲፈታ የወታደራዊው ማክ ከአዲስ አበባ የከተማ ክልል ወጥቶ ነበር :: የማኩን ሸራ (የጦር ሰራዊት መኪናዎች የሚሸፈኑበት ሸራ ለማለት ነው ) ወደ ላይ ሰብሰብ በማድረግ ልክ ማኩ መታጠፊያ ከርቭ ላይ ሲደርስና ሲታጠፍ ከሁዋላ የሚከተለው የጂፕ መኪና መብራት አያገኘውም :: ያን ጊዜ አንድ ወይም ሁለት እስረኞች ይዘሉና ወደጢሻው ይንከባለላሉ :: ከእይታ ለመሰወር :: እንደ መምህር በላይ አባባል (ለሁለተኛ ጊዜ ታስሮ ሲመጣ የነገረንን ከማስታውሰው ) እሱ የዘለለው ብዙ እስረኞች ከዘለሉ ብሁዋላ ነበር :: በእለቱ ሊታረዱ የወጡት አስረኞች ቁጥር አሁንም በትክክል እንደማስታውሰው 41 ነበር ::

መምህር በላይ የዘለለው የኢህአፓ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል የነበረውንና የአዲስ አበባ ብርጭቆ ፋብሪካ (ጉለሌ ) ስራ አስኪያጅ ከነበረው ኢንጅነር ኡስማን እንዲሁም ናዝሬት ወወክማ የሚል ሸርት ከለበሰ ጋር ትንሽ መንገድ አብረን ሮጠን መልካም እድል ተባብለን የራሳችን አቅጣጫዎች መርጠን መሮጣችን ቀጠልን አለን : ናዝሬት ወወክማ የሚል ሸርት ይለብስ የነበረው የሁዋላ እሸት የተባለው የክፍላችን እስረኛ ለመለየት ለማንኛችንም አልከበደም ::

መምህር በላይ ከአንደበቱ እንደተናገረው : እነሱ በሌላ አቅጣጫ ሲሮጡ እሱ ግን በማታ የማክ መኪናውን የመብራት ፋና እያየ በጢሻው እየተሽሎከለከ ይከተላቸው ነበር :: አንዴም ልክ እስሮኞች ከርቭ ላይ ሲዘሉ ይከተል የነበረው ጂፕ መብራት ከርቩን ጨርሶ ሲዞር መብራት ላይ ገቡ ::ጁንታዎቹ ወርደው እነዛን አርደው እዛው ጥለዋቸው ጉዞ ሲቀጥሉ ሁሉ ተከትሎ አይቷል :: በመጨረሻም የቀሩትን (ያልዘለሉትን ወይም ሊዘሉ ያልቻሉትን ) ከተዘጋጀው መታረጃ ቄራ ደርሰው ከማኩ አስወርደው ሲደረድሩዋቸው ከዚያም በጥይት እሩምታ ሲደበድቡዋቸው መምህር በላይ ከጢሻው ውስጥ ከቅርብ እርቀት ሲከታተል እንደነበርና በመጨረሻም የገዳዮች ቡድን መሪ የተረሸኑትን እያንዳንዱን ሟች እስረኛ በአንዳንድ የማጣርያ ጥይት ግንባር ግንባራቸውን ዳግም በጥይት ሲመታ እንዳስተውለ ከራሱ ከመምህር በላይ የሰማሁት እማኝነት ቃሌ ነው ::

ከዚያስ : ከዚያማ ያችኑ ብጫ ጥለት ነጠላውን ካንገቱ ላይ ጣል እንዳደረገ አንድ ወደ ሚያውቀው ሰው እንደተጠጋና ከዚያም ለመተዳደርያው ቆፍጣና መምህር የዘበኝነት ስራ አግኝቶ እየሰራ ዳግም ጸረ ደርግ ትግሉን ቀጠለ :: የሁለተኛ ዙር አያያዙን በመጀምሪያው ገፅ ላይ ገልጬዋለሁና መድገሙ አይታየኝም ::

ይህንን መጻፍ ያስፈለገኝ ወንድሜ መላጣ ሲጽፍ ወታደሮቹ አምልጡ እንዳላቸውና የገደሉ ለማስመሰል ጥይት ወደ ሰማይ እየተኮሱ ....................... በማለቱ ከመምህር በላይ ከራሱ ክሟቹ አንደበት የሰማሁትን ለንጽጽር ማቅረቤ እንጂ ወንድሜ መላጣ ያቀረበውን መቃወሜ አይደለም ::

ጉዳዩ በዚህ አላበቃም :: ከብዙ ሳምንታት በሁዋላ ዳግም መምህር በላይ ሲታሰር : የሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ምርመራ ሀላፊ የነበረው አረመኔው የአምሳ አለቃ ተሾመ ሁለት አይኖቹ ፈጠጡ :: መምህር በላይን እበራችን ድረስ መጥቶ አንተን እኮ እንድትመታ ለቡድኑ ፈርሜ ስጥቼህ ነበር አለው :: የመምህር በላይ መልስ ምን ቢሆን ጥሩ ነበር ትላላችሁ ???? እሱ ግን የመለሰው "" እኔ እንጃ "" እርምጃ እንዲወሰድብህ ለመውጣትህ ነው እኔ እንጃ የምትለኝ ?? አለ ሀምሳ አለቃው !!!! አይ በላይሻ አሁንም ደግሞ አዎ ሲለው በቁጣ እየተንተከተከ ተመለሰ :: ምን ያድርገው :: መምህር በላይን እንኩዋን ቁጣ እና ግልምጫ ስድስት ሰአት የፈጀ ቶርች እንኩዋን የሚመልሰው አልባሌ ሰው እንዳልሆነ ራሱ ሀምሳ አለቃ ተሾመ ያውቃል :: ደግሞ ዝም እንዳይባል ሰውየው መምህር በላይ ነው :: ካንድ ብርጌድ ጦር በላይ የሚያስፈራ በጭንቅላቱ እውቀትም ሆነ በወኔው :: ግራዝያኒ መንግስቱ ሀይለማርያምን ለሽንት እንኩዋን አላስወጣ ያለ :: በአንድ አሮጌ ታክሲ ሆኖ ፋሺስት መንግስቱ ሀይለማርያምን ማታ ከደርግ ጽህፈት ቤት ሲወጣ ከአፍሪካ አዳራሽና እስጢፋኖስ ቤት ክርስቲያን መሀል ተቀብሎ አራተኛ ክፍለ ጦር (መሹዋለኪያ ) ዘሎ ገብቶ እስኪያመልጠው ድረስ በአንድ አነስተኛ ኡዚ ጠመንጃ ያሩዋራጠ የመንግስቱ ሁለቱ ቦዲ ጋርዶች መልሶ ለመተኮስ እንኩዋን የሰከንድ ጊዜ ቢያሳጣቸው መንግስቱን ላንድሮቨር ወለሉ ላይ ጥለውት እነሱ ከላዩ ላይ ተኙ :: ሁለቱም ቦዲጋርዶች ወዲያው ሲሞቱ መንግስቱም ገና አንድ ጥይት መዋሂቱ ላይ ከማግኘቱ ላንድሮቨሯ ክፍለ ጦሩ በር ላይ ደርሳለት ኖሮ ተረፈ :: መምህር በላይም ወደመጣበት ተመለሰ :: ማን ተከትሎ :: መንግስቱን አጅበው የነበሩ ጂፖች እንኩዋን በላይን ለመከተል አልደፈሩም ::እነሱ ያሰቡት አንድ ሀያል ጦር መንግስቱን እንዳባረረ ብቻ ነበር :: እውነቱን ነው : መምህር በላይ የት ሰፈር ነው ያደከው ሲባል አርበኛው ሀይለ ማርያም ማሞ ካደገብት ያለው ::

ሌላው የወቅቱ ችግር ያን ቀን እነ መምህር በላይ ላይ እርምጃ እንዲወስዱ የተምደበው ቡድን የተሰጠኝን እስረኞች ላይ በሙሉ አብዮታዊ እርምጃ ወስጃለሁ ብሎ ነው በማግስቱሪፖርት ያደረገው :: የተለመደው አሰራራቸው ነበር :: መምህር በላይ ዳግም ሲያዝ የሶተኛ ፖሊስ ጣቢያው አረመኔው ሀምሳ አለቃ እኔ 41 እስረኞችን መምህር በላይን ጨምሬ ለቡድኑ ሰጥቻለሁ አለ :: የገዳይ ቡድኑ ደግሞ እኔ ፈርሜ የተቀበልኩትን በሙሉ ገድያለሁ : መምህር በላይን ግን አልሰጠህእኝም ነበር ብሎ መለሰ ::ጦርነት መሳርያ መማዘዝ የቀረው አይነት ሆነ በመሀላቸው :: መምህሩ ደግም የሚመልሰው አሁንም እንደገናም እኔ እንጃ ሆነ :: ያኔ ነው ልክ እንደበፊቱ መምህር በላይን መልምሎ ከጎኑ ለማሰለፍ የደርግ አባሉ ብርሀኑ ባየህ እንደገና መመላለስ የጀመረው :: ሆነም ቀረ ; መምህሩ የሚለሳለስ አይነት ሆኖ አልተገኘም :: ቀጥ ያለ ከእምነቱ ፈቀቅ ወይ ነቅነቅ የማይል ጥቅም የማያባብለው ምቾት የማያጉዋጉዋው የፕሪንሲፕል ሰው ነበርና መምህር በላይ ገብረ ማርያም ለኢትዮጵያ እንጂ ለፋሺስቱ ደርግ እንደማይጠቅም ታምኖ ዳግም ሞት ተፈረደበት :: አልባሌ ሰዎች አረዱትም :: ግራዚያኒ መንግስቱም ነጻ ወጣ አደባባይም መታየት ጀመረ :: ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ለሞት የሚሄዱ እስረኞች በሰንሰለት መታሰር ጀመሩ ::

ከምስጋና ጋር
View user's profile

Reply to message All times are GMT
Jump to:

Provided by CyberEthiopia.com , pow

_________________
what we learn from history is, we do not learn from history.

http://www.isil.org/resources/philosophy-of-liberty-english.swf
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
feredewnetu

ኮትኳች

Joined: 24 Sep 2009
Posts: 202

PostPosted: Mon Feb 20, 2012 2:11 am    Post subject: Reply with quote

መጣ ጬዋታው ረዘነ /ስላሴ ሙኒክ ነው ያለው አሉ ጂኒየስ ነበር 1969 ፍሬሽ ማን አልነበረም ብርሀኑ ነጋ ' ካሱ አቦዬ ' ጌታቸው ማሞ ' ንጉሴ አለሙ ' አለምጽህይ ግርማ ' ትንሳኤ አይናለም ' ዳንኤል ኣሚኔ ታደስ መላኩ አፈወርቅ ደሳለኝ አያሌው ህብቱ አኔ 250 የንፋስልክ ተማሪዎች መካከል ፍሬሽ ማን ነበርን :: ጸሎተ ነው ብርሀኑ ነጋን ጌታቸው ማሞን (ታምራት ላይኔ የወያኔ ስሙ ) መልምሎ አሲምባ የገባው "" አዎ ደሙን ያፈስስ ብለን ባንዲራችንን ስቅለን ጸሎት አርገን ነበር የአለት ትምህርታችንን የምንጀምረው "" ትግሬው አማራው ኦሮሞው ወላሞው ጉራጌው ሁሎ ኢትዮጵያዊ ነበር አንደ ዛሬው አያድርገውና ኢትዮጵያዊነት ክብር ነበር :: አንተ ትግሬ አንተ አማራ አንተ ኦሮሞ አንተ ምናምን ብሎ መካፋፈል አልነበረም ንጉሱ ከሁሎም ዘር አየተጋቡ አንዱ ካንዱ የማያንስ አኩል አንደነበር በምሳሌነት የሚጠቀሱ ነበሩ :: አቤቱ የኢትዮጵያ አምላክ ምህረቱን ስጠን !!!! ..........ያን የድንጋይ ዳቦ ዘመን መልስህ አምጣልን ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
-...-

ኮትኳች

Joined: 09 Feb 2012
Posts: 367

PostPosted: Mon Feb 20, 2012 2:14 am    Post subject: Reply with quote

ሀዲስ 1 እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ዝናዬ !
ሰላም ለሌሎቻችሁ የቤቱ ተሳታፊዎች ሁላ !

የዝናዬን ትረካ ሳነብ የሆነ ነገር ታወሰኝ :: ይሄንን የሚረሸኑ ሰዎች በማክ መታገዝና በመሀከሉም የአንዱ እጅ እነደተፈታና የሌሎቹንም ፈትቶ እንዴት ለማምለጥ እንደበቁ ጥንት በህፃንነቴ የሰማሁት ታሪክ ነው :: አንዴ አይደለም የሰማሁት ::
የሆነ ተረት ይመስለኝ ነበረ :: ግን ደግሞ ተረት እንዳይመስለኝም ታዲያ ሌላ የተፈፀመ ታሪክ እንደገና ስለሰማሁኝ የዚህን ታሪክ እውነተኝነት አምኜ ይሄንን ያህል አመት ልቀመጥ በቅቻለሁኝ ::

ወንድሜ ዝናዬ ሆይ !!!
ለረሸኑ ከተጋዙት ውስጥ አንድ ስሙ ተስፉ ልመታ የሚባል የቂርቆስ ልጅ እንደነበረ አውቃለሁኝ :: ማለት ተስፉ ልመታ ካንተም ጋራ ታስሮ ነበረ ማለት ነው :: ታውቀው ነበረ ????

አንድ ሌላ የሰማሁት ታሪክ ያልኩህ ታዲያ :--- የተስፉ አባት አቶ ልመታ በበኩር ልጃቸው ሞት በጣም ጥልቅ ሀዘን ላይ እያሉና (ተስፉ እንደተገደለ ነው መጀመሪያ ቤተሰቦቹ የተነገራቸው ) በህይወት ተስፋ ቆርጠው ባሉበት ሰዓት (አመታቶች አልፈው ) የሆኑ ሰዎች መጥተው
ልጅዎት ተስፉ አልሞተም : በህይወትም አለ ይሏቸዋል :: እሳቸውን ግን ምንም ቢሆን አላምንም ብለው ድርቅ ይላሉ :: ሰዎቹም እንግዲያውስ ካላመኑን እሱ ወዳለበት ቦታ አይንዎን ሸፍነን ወስደንዎት እናሳይዎታለን : ግን ለዚህ ፈቃደኛ ይሁኑ ይሏቸዋል :: አቶ ልመታ ግን ምንም እንኳን የልጃቸውን በህይወት መኖር ለማየት በጣም ጉጉ ቢሆኑም : እንዴት አድርገው ግን እኒህን ሰዎች ይመኗቸው ??? በዚህ አይነት የዚህ ታሪክ እውነተኛነት ሳይገለጥ ቀረ :: ግን ብዙዎች ወጣቶች የተስፉን ማምለጥ ያረጋግጡ ነበረ :: እንደውም ያለው አሲምባ እንደሆነ አስረግጠው የሚናገሩ ነበሩ ::

ውድ ወንድሜ ዝናዬ !!!
ለመሆኑ ስለተስፉ በህይወት መትረፍ (ማምለጥ ) የምታውቀው ታሪክ አለ ???
እስኪ በፈጠረህ ስለተስፉ የምታውቀውን አሳውቀኝ :: ተይዞ የታሰረው 1967(Cool የሜይዴይ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በኢህአፓ በተዘጋጀው ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ተገኝቶ ነው :: በፓርቲው ውስጥም ትልቅ ቦታ እንደነበረው ከሁኔታው ያስታውቅ ነበረ ::

ሰላም ሁን

ሀዲስ

እናንተ ሰዎች ለናንተ የመዝናኛ ንባብ ቢሆንም በዚያ ሰቆቃ ላለፍን ሰዎች አሰቃቂ ቅዠት ነው መልሳችሁ የምትቀሰቅሱብን :: ለምን አትተዉትም ያለፈው አልፏል ::

ከተስፋ ለመታና ከመምህር በላይ ጋር ልንረሸን ከወጡት አንዱ ነበርኩ :: በታምር አላመለጥንም :: ልናመልጥ የቻልነው ከረሻኞቹ አንዱ የድርጅት አባል ጓድ ስለነበር አንዱን ተረሻኝ ስለፈታውና የተፈታውም ሌሎቻችንን ስለፈታን ነው :: እኛ ያገኘነውን ዕድል ተጠቅመን ስንፈረጥጥ መምህር በላይ ግን እዛው ለመታገል ባለው ቁርጥ ውሳኔ አሻፈረኝ አልፈረጥጥም ብሎ ዳግም በደርግ እጅ ወድቆ መስዋዕትነትን ከፍሏል :: እሱ ብቻ አይደለም የተሰዋው :: የፈታን ጓድ በአንጃዎች ተጋልጦ ደርግ ይሄነው የማይባል ቶርቸር አድርሶበት እንደውሻ ተሰቃይቶ አይሞቱ አሟሟት ነው የሞተው :: እንደሱ ከፍተኛ ዋጋ የከፈለ የለም :: ከሁሉ ከሁሉ የሚዘገንነኝ የሱ ቶርቸር መደረግ ነው :: እንደሰማሁት አውጣ እየተባለ አስር የእግሩ ጣቶች በየተራ አንድ የእግሩን ጣት በአንድ ቶርች ጊዜ እየቀነጠሱ ነብሱን ሲስት ወስደው እስር ማጎሪያው እየወረወሩት በሚቀጥለው ሌላ ጣቱን እንዲህ አሰቃይተው ነው የገደሉት ::

እባካችሁ ይህንን ተዉት የተረሳ ቁስል አትቀስቅሱ ብዙ ብዙ የዚያ የቀውጢ ቀን ሰቀቀን በቀላሉ ሊያገረሽባቸው የሚችል ግለሰቦች አሉ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዲጎኔ

ዋና አለቃ

Joined: 19 Aug 2005
Posts: 4206
Location: united states

PostPosted: Mon Feb 20, 2012 3:27 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችን
ውድ ወለላዬ የዚያ ዘመን ትዝታ ፍንትው ላደረገ የዝናዬ መጣጥፍ ብዙ ምስጋና ::ይጥና አብሬ አባተ ይርዳው ግርማ ወልደአብ ለግድያ እየተጠሩ ሲሄዱ ሳርቤት /መካኒሳ የቀበሌ እሰርቤቶች አይረሳኝም የእናት አገር ጥሪ ብለው ወጣቶቹ የለበሱት ጃኬት ሳይቀር ሶማሊያ ዘማች የረዱት ሳይቆጠር ያለምህረት የረሸኑዋቸው ሀምሳአለቃውና የከተማ ልማቱ ካድሬ በርሄ አንድ አይና እንደ ናዚው ሮችማን ጨካኞች ነበሩ ::ሊገድሉ ሲመጡ የጠጡት አረቄ ይሸተናል በሌሊት ዘምሩ እያሉ በተገረፈ ቁስል ላይ እየተራመዱ ስም ይጠሩ ነበር ::ቀን መጥተው ማታ ድራማ አለ ብለው በሚቀጥለው ቀን የተገደሉ ወንድሞች ደምና አንጎል እንድናይ በሌሊት ይቀስቅሱን ነበር ::ለገደሉት ልጅ ቤተስብ ቀይሽብር በላው ተመቷል እያሉ ይስቁ ነበር ::ጌቱ ሲጠራ አዲስ ስሊፐሩን ለናቴ ስጡ ብሎ ወርውሮ ወጣ አባተ ይርዳው አላልኩሽም ብሎ በኒኬ ጠርቶኝ ነበር ::አባቱ አምጡ ተብለው ታስረው ነበር ::ይጥና ተገርፎ ከብሩክ ፈይሳ ጋር ተገለዋል ::ይጥናን የጠቆመ ደበበ የሚባል ቀበሌ ተመራጭ ራሱ ኢሀፓ የነበረ ግን አልገደሉትም ነበር ::
ከሀገር ሳልወጣ እነዚያ ገዳዮች ለመፋረድ ሰዎች ለስብሰባ ተግባረድ /ቤት ምንዋጋ አለው ብዬ ቀርቻለሁ ::አንዳንድ ገራፊዎች ተለውጠዋል ::ዋናው ነገር ያለፈው መዘከራችን ለመጨው ትውልድ ትምህርት ይሁን ! የዋርካው ስም የለሹ ወገን ትረካ ድንቅ ነው ታሪኩን ያላወቀ ለነገ አይዘጋጅም ነውና እናሳውቀው እንዘግበው ::ከፍተኛ 4 የተደረገውም እንዲሁ የሚዘገብ አለ ::እውቁ የጠረጴዛ ኩዋስ ሊቅ ግርማ ትርፌ ከክልሱ ጉዋዱ ኒኒ ጋር ሲረሸኑ የኒኒ እናት ህሊናዋን ስታ የልጇን ደም ከመሬት እየጠረገች እራሷን ትቀባ ነበር በዚያው ጠንቅ ሳትቆይ ሞታለች እረስንቱ !
የሜይ ዴይ ሰልፍ በኢሀፓ የተደረገው 1969 ነበር ::ውጋ በለው እያልን እየዘመርን የደርግ ገዳዮች እሩምታ ሲከፍቱ አመለጥን ዛሬ ሳስበው ጌታ አስመለጠኝ !!ክብር ለስሙ !!!
ያልገባኝ በነፍሰገዳዩ መንግስቱ ሀይለማርያም ላይ ግድያ የሞከረ ሱራፌል ካባ አልነበር ?/ በላይ ትክክል ድንቅ ታጋይ ነበር ያንን እርሱ ማድረጉን ግን አላውቅም ነበር ::

ወለላዬ እንደጻፈ(ች)ው:

ነበርን ከአስማረ ግረፌ ጋር ደግሞ በንፋስልክ አጠቃላይ 9 እና 10 ክፍል በአንድ ክፍል አብረን ተምረናል… ..የት / ቤታችንና የት / ቤት ጓደኞቻችንን ታሪክ እንደዘመኑ ሸፍጠኞች በገመድ ጠልፈን ሳንጥል አብረን እየተጋገዝን ከመሰረቱ እንድንጽፈው ያስፈልጋል ::
ስብስቴ ነጋሢ / ቤት እንደ አገራችን ኢትዮጵያ የሁሉም እናት ነበረች፤ ከቃሊቲ፤ ከዳርማር፤ ከሳሪስ፤ ከቡልቡላ፤ ከፉሪ፤ ከንፋስ ስልክ፤ ከመሿለኪያ፤ ከጨርቆስ፤ ከልደታ፤ ከድሮው አውሮፐላን ማደፊያ፤ ከሳር ቤቶች፤ ከጠባይ ማረሚያ ሰፈር፤ ከቄራ፤ ከጎፋ፤ ከጎተራ ከዘይት ቤት ..ወዘተ ቀበሌ የሚባል መጠሪያ ሳይፈጠር በፊት የድሮው አውሮፕላን ማረፊያ አጠገብ ከአሸዋ ሜዳ ወዲህ ካሉት ሳር ቤቶች አጠገብ ከኮተኒ በታች ካቶ ብሩክ ሠፈር ጓደኞቼ፤ ይጥና አብሬ፤ ጌታደጉ አባ ቡላ፤ ካሳሁን፤ ከልደታ ከሚመጡት ሃይሉ (ቀጭኔ ) የቅጽል ስሙ ከታናሽ ወንድሙና ጓደኞቹ ጋር ሆነን የአትክልት ሠፈሩን አቋርጠን ቄራ ስንደርስ ደግሞ ከቄራ ልጆች መብራቱ ልመንህ፤ ጌታቸው (ቁራ ) ሱልጣን (ተምትም ) አባተ እና ሌሎች ሆነን ወደ ስብስቴ ስንተም መሃይምነትን ድል ለመንሳት የዘመተ ጦር እንመስል ነበር ::
!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ውልጮ

ኮትኳች

Joined: 04 Feb 2004
Posts: 386

PostPosted: Mon Feb 20, 2012 5:48 pm    Post subject: Reply with quote

እነክፍሉ ታደስ ሲጥፋ መሰለኝ ነገር መበላሽት የጅመረው ::
መብታቸው ቢሆንም

ዲያስፖራ እንደጻፈ(ች)ው:
ታዲያ ይህን ይምስለ ጀገና ታሪክ እያለ ድርጅቱ ኢሕአፓ የብዙዎችን ጨምሮ በመጽሀፍ መልክ አላቀርቡልንም ?? የመንግስቱ መጽሀፍ ህገ ወጥ በሆነ መንገድ ማራከስ ነው የጅገናው በላይ ታሪክ መዘከር ? ወለላዬ አንተን እግዚአብሄር ይስጥህ ለኛ ትውልድ በመዘከርህ ::
ግን ግን ብዙ ታሪካቸው ተከድኖ ያለ የዛ ትውልድ ጀግኖች ገድል ማን ይንገረን ? ኢሕአፓ ምናልባት እውቅ የሆኑ ሰዎች አልቀውበት ህይወታቸውን ለማዳን የሸሹ ፈሪ አባላቶቹ ይህን ለመጽሀፍ እውቀቱ አይኗርቸው የሆን ? ድብተራው ሆነ አሲምባ ብዙ ብዙ የሚታወቁት የተቃዋሚ ተቃዋሚዎች እንጂ ካላቸው ልምድ ትግሉን አለመምራታቸው ሳስብ የነዛ ጅግኖች ትግል እና ጅግነት እንዲህ በዚህ ትውልድ ሲድበስበስ ሳይ በጣም ያስዘነኛል እረ ስለተሰዉት ትውልድ ብለን ሰጣ ገባ ተትው ኢሕአፓ ትግሉን ምሩት ሁሉንም ድርጅት አሰባብስባችሁ ታሪክ ስሩ :: እያደፈጣችሁ ብቻ የቃላት ጦርነት ይትም አያድርስም ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3  Next
Page 2 of 3

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia