WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
አቶ ስብሃት ተገደለ ወይስ ሞተ ?

Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ዉቃው

ዋና ኮትኳች

Joined: 07 Jan 2007
Posts: 970

PostPosted: Fri Mar 02, 2012 5:18 am    Post subject: አቶ ስብሃት ተገደለ ወይስ ሞተ ? Reply with quote

"ይህንን ህግ ስትጥስ የማነው ይሄ ቅሌታም ሽማግሌ ትባላለህ " አለ ስብሃት :: በጨዋታ ፕሮግራም :: ቁም ነገሩ ሪጮ የዋርካዋ ቅሌቱን ባይኗ በጆሮዋ በበረቱ ታዝባለች ::

ይህንን ጥያቄ ለመጠየቅ ያሳሰበኝ ..እንደው አቧራ አስነስቶ ...የማያባራ አተካሮ ለመፍጠር ሳይሆን ....ምናላባች አቶ ስብሃት ከሞተ በኋላ ..ሞተ ...በቃ አርጅቶ ...ወዶ ለዘመናት ያጤሰውም ሲጋራ ወይም በህግ የተፈቀደለኝ ያለው ዕጸ -ፋርስ የጉሮሮ ካንሰር አምጥቶ አሳምሞት ..መጠጡና ..ጫቱም ተጨመሮ ....እያልን ምክንያቶች ማቅረብ ይቻላል ::

ግን ደግሞ .....በጉሮሮ ካንሰር ..በቅርቡ አሜሪካዊው ..አቶ ማይክል ዳግላስ ....ከብዙ መጠጥና ማጤስ ብዛት ለዚህ በቅቻለሁ ...ብሎ በናሽናል ቴሌቪዥን ከታወጀና ..ብዙም ሳይቆይ ..አሁን ለጊዜውም ቢሆን ጤና አግኝቶ እያየነው ነው :: [ያው አሜሪካ ..ገንዘቡ ...ህክምናው ምናምን ......እንዳትሉኝ ] ጉዳዬ እሱ አየደለምና !

ሊዲንግ ማን ዘነበ ወላ [ያልተነጠቀ ማዕረጉን አክብሬ ].... ሲያብራራ [አወራሩ የመንደር ዱርዬ መስሎብኛል (ለኔ )] http://www.youtube.com/watch?v=0Ly6b53uP-M ከአቶ ስብሐት ጋር ሰለሞት ብዙ እንዳወሩ ..ደምሰው {አቶ ስብሃት የሚያሳድገው የተባለ ጸጉሩ ገባ ያለ ወጣት } ሚስ ኮል አረገልኝ ...አይ የለም ኤሴኤም ኤስ አረገልኝና ...ጋሽ ስብሐት ስሪንጁን ነቅሎ ጣለው አለኝ ...ባላ ብላ ..እያለ ያብራራል :: እናም ..ስሪንጁ [{ፊዲንግ ቲዩቡ } ወይም አይቪ ፍሉዱ ] እንደህግ ተከበረና ..እንደ ሊዲንግ ማን ዘነበ ወላ አባባል ..(እኔ ያልኩት ሆነ )

ከዛ ሊዲንግ ሲማን ዘነበ ወላ በአዲስ አድማስ ዌብ -ሳይት ይህ አለ ::
Quote:
የስብሃት የመጨረሻ ቀናት እንዴት ነበሩ ?

በሽታው የጉሮሮ ካንሰር መሆኑ ከታወቀ በኋላ ውጭ አገር ወስዶ ለማሳከም በጣም ጥረት ተደርጐ ነበር፡፡ የሬዲዮ ፕሮግራም ሁሉ ሊሰራ ታቅዶ ነበር፡፡ / ወንድሙ ተወልደም በጣም ደክሟል፡፡ ግን ሁኔታው ተስፋ አስቆራጭ መሆኑን ካወቅን በኋላ የሠላም እረፍት እንዲያገኝ ዝም ብለን መንከባከብ ጀመርን፡፡ እኔ ለመጨረሻ ጊዜ ያየሁት ሐሙስ ዕለት ነው፡፡ እሱ የሚያሳድገው ደምሰው የሚባል ልጅ አለ - ሆስፒታል ውስጥ እየጠበቀው ነበር፡፡ እሱ እንደነገረኝ ከምሽቱ 5 ሰዓት ከምናምን ላይ ምግቡን በቲዩብ ሰጠው፡፡

ያንን ወሰደ፡፡ ትንሽ ጋደም ካልኩበት ስነቃ ስብሃት ለምግብ መውሰጃ የተሰራለትን ቱቦ (ቲዩብ ) ነቃቅሎ ጣለው “ምነው ? ስለው “ከዚህ በላይ እየተሰቃየሁ መኖር አልፈልግም፡፡ በጣም የምወድህ ልጅ ነህ፤ የዛኑ ያህል እንድጠላህ እያደረከኝ ነው፡፡ ምክንያቱም መኖር አልፈልግም እያልኩህ በግድ እንድኖር እያስገደድከኝ ነው” አለኝ ብሎ ነገረኝ፡፡ ቃሉ እንደ ህግ እንዲከበርለት ፈልገናል፡፡

ሐሙስ ዕለት ተረኛው እኔ ነበርኩ፡፡ እየጠበኩት እያለ ቀን ላይ ብንን አለና በምልክት ወረቀት ስጠኝ አለኝ ሰጠሁት፡፡ በግራ እጁ “ተኛ” ብሎ ፃፈልኝ፡፡ እሺ አልኩት፡፡ በዛን ወቅት ጉሮሮው ላይ ኩርር የሚል ነገር እያስቸገረው ነበር፡፡

ለምን መሰለህ እንዲህ የሚያደርግህ ? ምግብ ስለማትወስድ ነው የሚያሰቃይህ አልኩትና ቲዩቡ ተመልሶ እንዲገባልህ ትፈልጋለህ ወይ ? አልኩት አዎ አለኝ፡፡

ከቤተሰቦቹ ጋር ሆነን ቱዩቡ እንደገና እንዲቀጠልለት ለማድረግ ስንሞክር የጉሮሮው እጢ አብጦ ቱዩቡን አላስገባ አለን፡፡ በቃ ያኔ ተስፋ ቆረጥኩ፡፡ የመጨረሻችንም ዕለት ያቺ ሆነች፡፡
http://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_content&view=article&id=1820:2012-02-25-14-43-46&catid=96:3d-computer-graphics&Itemid=503

ይሄ ኮንስፓይረሲ አይደለም :: ስብሃት ከሞተ በኍላ ..በኢትዮጵያ ናሽናል ቴሌቭዥን [ለጊዜው ናሽናል ይባልልኝ ]...አትንካው የኔን አቋም ይቀበላሉ {በኔ ትርጉም ሌት ሂም ዳይ ) ያለው ሰውዬ ..ስብሃት ትዩቡ ተቀጥሎለት ከሰቃዩ ተንፈስ እንዲል ሲሞክር ይታያል ::

መች ይህ ብቻ ? ስብሃት ... ሰባት ቤት ሽምግልንና ሞትን እንደሚፈራ ሰምተና አንበናል :: (http://www.shegerfm.com/ የስብሐት ገብረእግዚአብሄር መታሰቢያ ከደረጄ ሃይሌ ጋር part one Feb 25, 2012) አጋፋሪ እንደሻው ..ሞቱን የሚፈሩት እኮ ..እኛው ራሳችን ነኝ ..ይላል :: ስብሃት በመጨረሻው ሰዓትም ቢሆን ..ሞትን ፈልጎ እንዳልነበር ሁኔታዎች ያስረዳሉ : በኔ እምነት :: ዕድምሜ ልኩን ሞትን እፈራለሁ ያለ ..ሞት ጥርሱ አግጥጦ ሲመጣ ...?????

ለመሆኑ ..ቴሪ ሻይቮ ....በቱዩብም ሆነ በሌላ ዘለዓለም ትኑርልን ..ያሉቱ ..ይወለዷዋት ወላጆቿ ወይስ ባሏ ? አዎን ወላጆቿ ትኑር ሲሉ ባሏ በቃ አለ :: ዳኛው እስትንፋሷ በባሏ ይወሰን አለ :: በባሏም ተወሰነ :: ባሏ ግን እንኳን ሞተችለት አገባ ! http://www.cbsnews.com/8301-201_162-1227404.html ይሞታል እንዴ !

ስብሃት ሞተ ::

ዘነበ ወላስ ?

Quote:
ደስ የሚለኝ ነገር እሱ ከማለፉ በፊት አርትኦት ችዬ አሳይቼው ነው ያለፈው፡፡ አሁንም እጄ ላይ ያሉ ሥራዎች አሉ፤ እነሱንና የቀሩኝን ሃሳቦች ጨማምሬ እንዲሁም እሱን ለማዳን የተደረጉ ሙከራዎችን ጨማምሬ “ማስታወሻ”ን ከሁለትና ከሶስት ወራት በኋላ እንደገና አሳትመዋለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ይመቻችሁ :: ማስታወሻ ደግሞ ሊታተም ነው :: ገቢው ...ህም .. ለኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ይሁን ::
_________________
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
recho

ዋና አለቃ

Joined: 20 Sep 2004
Posts: 3059
Location: Earth

PostPosted: Fri Mar 02, 2012 2:51 pm    Post subject: Re: አቶ ስብሃት ተገደለ ወይስ ሞተ ? Reply with quote

ዉቃው እንደጻፈ(ች)ው:
"ይህንን ህግ ስትጥስ የማነው ይሄ ቅሌታም ሽማግሌ ትባላለህ " አለ ስብሃት :: በጨዋታ ፕሮግራም :: ቁም ነገሩ ሪጮ የዋርካዋ ቅሌቱን ባይኗ በጆሮዋ በበረቱ ታዝባለች ::
ዌል ስሜን ባታነሳ ኖሮ በስብሀት ዙሪያ ዋርካ ላይ ምንም ላለማለት ወስኜ ነበር ... ማብራራት ካለብኝ ግን ... ስብሀትም ሆነ ማንም ላይ ግላዊ የሆነ ግጭት የለኝም ሰው ሁሉ ሰዋዊ ለሆኑ ህጎች ሁሉ ይገዙም አልልም .. ብዙ ሰዎች መጥፎ ስለሆኑ ሳይሆን ስላላመኑብት የሶሳይቱውን ህግ ሳይጠብቁም ሳያከብሩም ኖረዋል ..

ስብሀት ... ደራሲ ስብሀት .. ጸሀፊ ስብሀት ... ያላችሁትን በሉት ... ለኢትዩዽያ ስነጽሁፍ እድገት አስተዋጾ አድርጎ ሊሆን ይችላል .. አድርግዋል ወይንም አላረገም ብዬ ለመናገር ግን በጥልቀት የማውቀው ነገር የለም እንደዚሁም መስፈርቱንም አላውቅም ... በይ ግን ከተባልኩ ዋርካ ላይ የማውቃቸው ጨዋ ጸሀፊያን ዋናው , ፓኑ , ዋኖስ , ወለላዬ , ውቃው ... ለኔ ብዙ ያበረክቱ ጸሀፊያን ናቸው .. እንግዲህ ሰው የሚያውቀውን ነው የሚፈርደው ... ከዛ ውጪ አቶ ስብሀት ከስሩ የሚያስከትላቸው የልጅ ልጅ የሚሆኑትን ወጣቶች ምን እያስተማራቸው እንደሆነስ ልብ ብለናል ? ልቅነት ውበት ከሆነ ይሄን እኔ አላቅም .. ልቅነት , አደንዛዥ እጽ ተገዥነት , እንደ እንሰሳ ልቅ ወሲብን ሲያስቡና በተግባርም እንዲያውሉት መመከር እናም ደግሞ እግዜሩም ህግ የሆነውን ታላቅ ስተት እንደቀልድ ምንም አይደል ብለው እንዲያልፉት ጭንቅላታቸውን መቅረጽ ታላቅ ሰው ያስብላል ? እኔ እንግዲህ ከአገር ከወጣሁ 4አመት በላይ ሆነኝ መሰል ... በዛን ጊዜ ዳታ ነው የማወራው ... ስብሀት ሲባል ራሱ ያቅለሸልሸኛል .. ጥሩ ሰው ሊሆን ይችላል ስራው ግን የዲያቢሎስ ነው .. ምን አለበት እነዛን ከስሩ የሚያስከትላቸውን ቡችላዎቹን ስነጽሁፍን ቢያስተምራቸው ሀሽሽ ማጨስ ምንም ማለት እንዳልሆነና ሴክስ ከዚችም ከዛችም ጋር እያረጉ ስለሱ እየቀለዱ መዋል ምንም አለመሆኑን ከሚያስተምር ? እንግዲህ እርፍ በሉት .. ለነ ስብሀት ተራ ዱርዬ ነው .. ሞተ ? ዌል ማን ይቀራል .. ለሚወዱት "አድናቂዎቹ " መጽናናት ይስጣቸው .. እርግጥ ታላቅ አጥፊ አጥተዋል ... ግን ስብሀት የዘራው ዘር ለስንት ጀነሬሽን ይበቃ ይሆን ... ለመሁኑ በይፋ ሀሽሽ የሚያጨስ የሚያስጨስ መንግስታዊ ፍቃድ ያለው አንድ ስው ለኢትዩዺያ ወጣት በርግጥ ችግር ፈቺ .. አስተማሪ ነበረ ብላቹ ልትከራከሩኝ ነው ? እርግጥ ወጣቱ ችግሩን በሚያጨሰው ምናምን እንዲረሳ አድርጎታል .. ለዛ ታላቅ ምስጋና ይገባዋል .. ማለት ችግር መርሳት መፍትሄ ከሆነ

ማይ ፐርሰናል ኤክሲፕሪያንስ ...እናትሽን #$ ብሎ ሲሳደብ በዛ ሽበትና እርጅናው ላይ በጣም ደንግጫለሁ !!!

በሉ ተሳደቡ , አንቁዋሹኝ , ያላችሁትን በሉ .. እንደሰው ጥሩ ሊሆን ይችላል .. ስራው እድሜው አይሄድም .. !!!

ሪቾ
_________________
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጩጉዳ

ውሃ አጠጪ

Joined: 31 Jan 2005
Posts: 1202
Location: Studio City, Wilson Republic

PostPosted: Fri Mar 02, 2012 3:13 pm    Post subject: Reply with quote

ዌል ስብሐት 76 ዐመት አዛውንት መሆኑን አንዘንጋ ጎበዝ (ለዚያውም ትክክለኛ የልደት ቀን ሪከርድ ስለማይታወቅ ዕድሜው እሱ ነው እንበለውና ) በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ሰውዬው ኑሮው ዕድሜውን ሁሉ አልኮል ቤት የኖረ መሆኑም አይረሳ Rolling Eyes ይህ ሁሉ ተጨማምሮበት የኑሮ ሁኔታና የሕክምና ኬር እምብዛም በሆነበት አገራችን ምን ይጠበቃል ? ?

ሬቾ ከሞላ ጎደል ሀሳብሽን እጋራለሁ ሰውዬው ለወጣቱ መልካም ምሣሌ አልነበረም ግን በጣም ታለንትድ የሆነ የሥነጽሑፍ እውቀት የነበረው ግለሰብ እንደነበረና ብዙዎችንም ኢንስፓየር ያረገ እኔንም ጭምር በልጅነቴ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የእሱን አምድ እያነበብኩ ትርጉሙን እያብሰለሰለኩ ነው ያደኩት ::

ሬቾ : ሞት ለማንም የማይቀር መሆኑ እርግጥ ቢሆንም ቀን እስኪደርስ ሁሉም ለቤሰሰቡና loved ones በጣም አስፈላጊ ፍጡር ነውና ሞትን የመሰለ ነገር መመኘት ጥሩ አይደለም :: ግን አንቺ ግን .... ከአገር ቤት ከወጣሁ አራት ዐመት ሆነኝ መሰለኝ ያልሽ መሰለኝ ተይ እንጂ ..... ዋርካን ጆይን ካረግሽ እንኳ ይሄው 8 ዐመት ደፈንሽ Rolling Eyes ወይስ አንዷ ከኍላ ጠፍታብሽ ነው ወይም ደግሞ አገር ቤት እንደገና ቪዚት ካረግሺበት አንስቶ ...... መሆኑ ነው ?? ባልሳሳት ዋርካ ሥራዋን በጀመረች ገና በአመቷ 2001 ተጀምራ ወዲያው ጨለመች :: አይደል እንዴ ?
_________________
መታገስንና መቻልን የመሰለ ብቀላ የለም ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
recho

ዋና አለቃ

Joined: 20 Sep 2004
Posts: 3059
Location: Earth

PostPosted: Fri Mar 02, 2012 3:35 pm    Post subject: Reply with quote

ጩጉዳ እንደጻፈ(ች)ው:

ሬቾ ከሞላ ጎደል ሀሳብሽን እጋራለሁ ሰውዬው ለወጣቱ መልካም ምሣሌ አልነበረም ግን በጣም ታለንትድ የሆነ የሥነጽሑፍ እውቀት የነበረው ግለሰብ እንደነበረና ብዙዎችንም ኢንስፓየር ያረገ እኔንም ጭምር በልጅነቴ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የእሱን አምድ እያነበብኩ ትርጉሙን እያብሰለሰለኩ ነው ያደኩት ::
ታንክስ ብሮ .. ሀሳቤን የተሙዋላ አርገህዋል .. ጥሩ ይጽፋል .. አንዳንዴ የሚናገራቸው (ጨዋዎቹን ) ንግግሮቹን ወድለታለሁ .. ፈኒም ነው .. ግን ያለውን ችሎታ እና ኤነርጂ አላስፈላጊ ነገር ላይ አባክኖታል ብዬ አምናለሁ .. እንዳልከው ለወጣቱ ጥሩ አርአያ አይደለም .. ጋሽ ስብሀትት ብለው ነው እየተከተሉት ያሉት እና ከሱም ምን ተማሩ ???? መልሱት ...

Quote:
ሬቾ : ሞት ለማንም የማይቀር መሆኑ እርግጥ ቢሆንም ቀን እስኪደርስ ሁሉም ለቤሰሰቡና loved ones በጣም አስፈላጊ ፍጡር ነውና ሞትን የመሰለ ነገር መመኘት ጥሩ አይደለም ::
ሞቱን ተመኘሁ እንዴ ? እንደዛ ያልኩ አልመሰለኝም .. ካልኩ ስተት ነው ይታረማል ... ማንም አይሙት ..ለሚወዱት ቤተሰቦቹ እና አድናቂዎቹ ቢኖርላቸው ጥሩ ነው .. ! መጽናናቱን ይስጣቸው .. !

Quote:
ግን አንቺ ግን .... ከአገር ቤት ከወጣሁ አራት ዐመት ሆነኝ መሰለኝ ያልሽ መሰለኝ ተይ እንጂ ..... ዋርካን ጆይን ካረግሽ እንኳ ይሄው 8 ዐመት ደፈንሽ Rolling Eyes ወይስ አንዷ ከኍላ ጠፍታብሽ ነው ወይም ደግሞ አገር ቤት እንደገና ቪዚት ካረግሺበት አንስቶ ...... መሆኑ ነው ?? ባልሳሳት ዋርካ ሥራዋን በጀመረች ገና በአመቷ 2001 ተጀምራ ወዲያው ጨለመች :: አይደል እንዴ ?
ቅቅ አገርቤት እያለሁ ነው ዋርካን እጠቀም የነበረው .. ከተዘጋ ቡሀላም መግባት እችል ነበር .. ከሆነ ጥያቄህ ማለት ነው .. Laughing [/quote]
_________________
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post

ኮትኳች

Joined: 17 Oct 2010
Posts: 312

PostPosted: Fri Mar 02, 2012 7:17 pm    Post subject: Reply with quote

Quote:
ዋርካ ላይ የማውቃቸው ጨዋ ጸሀፊያን ዋናው , ፓኑ , ዋኖስ , ወለላዬ , ውቃው ... ለኔ ብዙ ያበረክቱ ጸሀፊያን ናቸው

[url]ይሽምማል [/url] ሪቾ እኛስ ግን Rolling Eyes Rolling Eyes እኛ እኮ ላንመስገን ወይ ላይሰጠን ዝም ብለን እንለፋለን ..ልፋ ያለው በምን ይለፋል ነበር የተባለው ( ለሴቶች ) ቢሆንም
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
-...-

ኮትኳች

Joined: 09 Feb 2012
Posts: 367

PostPosted: Sat Mar 03, 2012 4:39 am    Post subject: Reply with quote

ምነው ብትተዉት

አንድ ሰካራም ዶፕሄድ ከኢትዮጵያውያን ባህል ጋር የማይሄድ ባለጌ ሽማግሌ ሞተና ምን ሊያጎድል ነው ? ሾተል ለቅሶ ቢቀመጥለት ይገባኛል እናንተ ግን ተዉት ይረፍበት

አፈሩን ያቅልለት
_________________
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ናፖሊዮን ዳኘ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 18 Apr 2008
Posts: 1878

PostPosted: Sat Mar 03, 2012 6:41 am    Post subject: Re: አቶ ስብሃት ተገደለ ወይስ ሞተ ? Reply with quote

አሜን እንዳትይኝ እንጂ በዚህኛው ጽሁፍሽ አፌ ቁርጥ ይበልልሽ !

ስነ -ጽሁፉንም አስተምሯቸው ቢሆን እኮ ስነ -ጽሁፉ እንዲሁ ወሲብ ነው ! ፓሪስ ሄዶ የተከተበውን ነገር ልክ በዓለም ላይ የስብሀት ተደርጎ በዚህ ትውልድ መወሰዱ ራሱ ከስብሀት የበለጠ ትውልዱን እንድታዘበው አድርጎኛል ::recho እንደጻፈ(ች)ው:
ዉቃው እንደጻፈ(ች)ው:
"ይህንን ህግ ስትጥስ የማነው ይሄ ቅሌታም ሽማግሌ ትባላለህ " አለ ስብሃት :: በጨዋታ ፕሮግራም :: ቁም ነገሩ ሪጮ የዋርካዋ ቅሌቱን ባይኗ በጆሮዋ በበረቱ ታዝባለች ::
ዌል ስሜን ባታነሳ ኖሮ በስብሀት ዙሪያ ዋርካ ላይ ምንም ላለማለት ወስኜ ነበር ... ማብራራት ካለብኝ ግን ... ስብሀትም ሆነ ማንም ላይ ግላዊ የሆነ ግጭት የለኝም ሰው ሁሉ ሰዋዊ ለሆኑ ህጎች ሁሉ ይገዙም አልልም .. ብዙ ሰዎች መጥፎ ስለሆኑ ሳይሆን ስላላመኑብት የሶሳይቱውን ህግ ሳይጠብቁም ሳያከብሩም ኖረዋል ..

ስብሀት ... ደራሲ ስብሀት .. ጸሀፊ ስብሀት ... ያላችሁትን በሉት ... ለኢትዩዽያ ስነጽሁፍ እድገት አስተዋጾ አድርጎ ሊሆን ይችላል .. አድርግዋል ወይንም አላረገም ብዬ ለመናገር ግን በጥልቀት የማውቀው ነገር የለም እንደዚሁም መስፈርቱንም አላውቅም ... በይ ግን ከተባልኩ ዋርካ ላይ የማውቃቸው ጨዋ ጸሀፊያን ዋናው , ፓኑ , ዋኖስ , ወለላዬ , ውቃው ... ለኔ ብዙ ያበረክቱ ጸሀፊያን ናቸው .. እንግዲህ ሰው የሚያውቀውን ነው የሚፈርደው ... ከዛ ውጪ አቶ ስብሀት ከስሩ የሚያስከትላቸው የልጅ ልጅ የሚሆኑትን ወጣቶች ምን እያስተማራቸው እንደሆነስ ልብ ብለናል ? ልቅነት ውበት ከሆነ ይሄን እኔ አላቅም .. ልቅነት , አደንዛዥ እጽ ተገዥነት , እንደ እንሰሳ ልቅ ወሲብን ሲያስቡና በተግባርም እንዲያውሉት መመከር እናም ደግሞ እግዜሩም ህግ የሆነውን ታላቅ ስተት እንደቀልድ ምንም አይደል ብለው እንዲያልፉት ጭንቅላታቸውን መቅረጽ ታላቅ ሰው ያስብላል ? እኔ እንግዲህ ከአገር ከወጣሁ 4አመት በላይ ሆነኝ መሰል ... በዛን ጊዜ ዳታ ነው የማወራው ... ስብሀት ሲባል ራሱ ያቅለሸልሸኛል .. ጥሩ ሰው ሊሆን ይችላል ስራው ግን የዲያቢሎስ ነው .. ምን አለበት እነዛን ከስሩ የሚያስከትላቸውን ቡችላዎቹን ስነጽሁፍን ቢያስተምራቸው ሀሽሽ ማጨስ ምንም ማለት እንዳልሆነና ሴክስ ከዚችም ከዛችም ጋር እያረጉ ስለሱ እየቀለዱ መዋል ምንም አለመሆኑን ከሚያስተምር ? እንግዲህ እርፍ በሉት .. ለነ ስብሀት ተራ ዱርዬ ነው .. ሞተ ? ዌል ማን ይቀራል .. ለሚወዱት "አድናቂዎቹ " መጽናናት ይስጣቸው .. እርግጥ ታላቅ አጥፊ አጥተዋል ... ግን ስብሀት የዘራው ዘር ለስንት ጀነሬሽን ይበቃ ይሆን ... ለመሁኑ በይፋ ሀሽሽ የሚያጨስ የሚያስጨስ መንግስታዊ ፍቃድ ያለው አንድ ስው ለኢትዩዺያ ወጣት በርግጥ ችግር ፈቺ .. አስተማሪ ነበረ ብላቹ ልትከራከሩኝ ነው ? እርግጥ ወጣቱ ችግሩን በሚያጨሰው ምናምን እንዲረሳ አድርጎታል .. ለዛ ታላቅ ምስጋና ይገባዋል .. ማለት ችግር መርሳት መፍትሄ ከሆነ

ማይ ፐርሰናል ኤክሲፕሪያንስ ...እናትሽን #$ ብሎ ሲሳደብ በዛ ሽበትና እርጅናው ላይ በጣም ደንግጫለሁ !!!

በሉ ተሳደቡ , አንቁዋሹኝ , ያላችሁትን በሉ .. እንደሰው ጥሩ ሊሆን ይችላል .. ስራው እድሜው አይሄድም .. !!!

ሪቾ

_________________
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሀሪከን 2

ዋና ኮትኳች

Joined: 31 Oct 2008
Posts: 782

PostPosted: Sat Mar 03, 2012 4:26 pm    Post subject: Reply with quote

ውቃው እንዳጭበረበረው
Quote:
ይህን ጥያቄ ለመጠየቅ ያሳሰበኝ .. እንደው አቧራ አስነስቶ የማያባራ አተካሮ ለመፍጠር ሳይሆን
Laughing Laughing ቢሳካልሽ ኖሮማ ምን አቧራ ብቻ ዝናብ ሁሉ አዘንበሽ ዋርካን እና አካባቢዋን ሁካታ በሁካታ ልታደርጊ ነበር Laughing የኛ ኮንስፓይራሲ ቲዮሪስት :lol

ጋሽ ስብሀት ሂወትን እሱ እንደፈለገው እና እንደመረጠው ኖሯት አለፈ በቃ : ውቃው እና ግብረ አበሮቹ ስም እጠቅሳለሁ .. ጌታ , ሙዝ እግር , ግን ሂወትን እነሱ እንደፈለጉት ሳይሆን ማህበረሰቡ እንደፈለገው ስለሚኖሩ በጋሽ ስብሀት ሂወት እንደሚቀኑ ግፍም ሲል እንደሚንተከተኩ ለመገመት አያዳግትም

በነገራችን ላይ መለስ ዜናዊም እንደ ጋሽ ስብሀት አይነት የኑሮ ፍልስፍና እንደሚከተል ማንበቤን አስታውሳለሁ እንደ መለስ ዜናዊ ከሆነ ምርጥ ኑሮ ማለት የፈለግከውን ተናግረህ እና አድርገህ መኖር ማለት ነው

ስለ እውነት ግን ከስብሀት እና ከመለስ ዜናዊማነው ሂወትን እንደፈለገው የኖራት ? መለስ ሲፈልግ ብድግ ብሎ ባንዲራ የሚያክል ነገር በድፍረት ጨርቅ ነው ይልሀል Laughing እንዴ ባንዲራ ጨርቅ አይደለም ብለህ ስትንጫጫ ታዲያ ብረት ነው እንዴ ብሎ መልሶ ያላግጥብሀል Laughing ውይ ውይ መለስ ምን ወሰደኝ አቦይ ስብሀት ነጋስ አሉ አይደል እንዴ Rolling Eyes Rolling Eyes ሂወትን እራሱ እንደፈለጋት መኖር ብቻ ሳይሆን እኛ ኢትዮጵያዊያን ራሳችንን እሱ እንደፈለገው እንድንኖር ያደረገን Rolling Eyes እንዳውም ሂወትን እንደ ፈለጉት ኖሮ ማለፍ ማለት እንደ ስብሀት ገብረ እግዛብሄር ሳይሆን እንደ ስብሀት ነጋ እና መለስ ዜናዊ ነው Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes

በነገራችን ላይ ስብሀት እጅግ የበዙ አድናቂወች በአሉ ግርማን ጨምሮ እንዳሉት እንጅ እንደ ሪቾ አይነት ነቃፊወች እንዳሉት አላቅም ነበር Laughing ይህ ነገር እንደሰላምታም እንደ ነቆራም ይወሰድልኝ ስል በትህትና እጠይቃለሁ
ሪቾ ስትነሳ እህምምስ ለምን ትረሳ ...... የቀድሞዋ ኮረዳ የዛሬዋ ሙሉ ሴት እህምም Laughing በዚህ በዋርካ አካባቢ ካለፍሽ ሰላም ብያለሁ Laughing
_________________
each mind is a different world
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ማካሮቭ

ኮትኳች

Joined: 07 Dec 2004
Posts: 464
Location: united states

PostPosted: Mon Mar 05, 2012 4:00 am    Post subject: Reply with quote

ስብሐት ወደ ቤቱ ሲገባ ጠብቀው የወያኔ ወታደሮች ብዙ ተኩሰውበት ቶሎ ሊሞት ባለመቻሉ በብዙ መትርየስ ደብድበው ገደሉት ይባላል :: Cool
_________________
Wisdom is better than weapons of war: but one sinner destroyeth much good.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia