WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች !!!
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 357, 358, 359 ... 381, 382, 383  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General

View previous topic :: View next topic  
Author Message
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Sat Mar 10, 2012 3:48 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችንም !!!

ወንድሜ ባለሱቅ !! በመጀመሪያ ወንድማችን ሞፊቲ በመመለሱ እንኳን ደስ ያለን ልልህ እወዳለሁ :: ስለአስተያየትህ ደግሞ ምን ልበልህ ...ባጭሩ ሞቅ ብሎኛል :: አንተ ባትሰማኝ ለነገሩ እኔም አልጽፍም ነበር :: የቀረውን ደግሞ አጫውታችኌለሁ ::

ኦዶ ሻኪሶ ኪያ ባጋ ናጌያን ኑፍ ቱርታን :: ጋላቶም ዋን ስማቴፍ !!! ወንድሜ ያሰማኸን ዜና በጣም አሳዛኝ ነው :: የምገርመው ሾፌሩም : ደላላውም እንደዚያ ዐይነቱ ጉዞ እንዴት አስጊ መሆኑን እንዳልተረዱት ነው :: ያንን ሁሉ ርቀት በኮንቴይነር ታፍኖ ያን በረሀ ማቋረጡ የማይቻል መሆኑን መቼም ሳያዉቁት ቀርተው አይደለም :: ተሳፋሪዎቹ ምናልባትም የተለመደና አደጋ የሌለው መስሏቸውም ይሆን ይሆናል :: ለማንኛውም / ነብሳቸውን ይማር ከማለት ውጭ ምን ማለት እንችላለን :: / ብቻ አገራችንን ያስባት ::
ካገር ቤት ከተመለስኩ ወር አይሞላኝም :: ታዲያ በጣም የገረመኝ ምንም የገቢ ምንጭ ወይም ጧሪ የሌላቸው የከተማው የዕድሜ ባለጸጋዎች በዚህ ምኑም በማይቀመስ ውድ ግዜ ከማንም ዕኩል ተኝተው የሚቀጥለውን ቀን ማየት መቻላቸው ነበር :: ምን በልተው እንደሚኖሩ / ብቻ ነው የሚያውቀው :: በጉብዝናቸውና በጉልምስናቸው ወቅት ተከብረው በኖሩባት ከተማ አሁን ዕድሜያቸው ገፍቶ ጉልበታቸው ዝሎ ዐቅም ባጡበት ግዜ ደግሞ ጨርቅ አንጥፈው መለመንን እንደ ነውር ቆጥረው ክብራቸውን ጠብቀው ለመሞት ከበራቸው ቁጭ ብለው ዐይናቸውን ወደ ፈጣሪያቸው በማንሳት መጨረሻቸውን የሚጠባበቁ ስንት አሉ መሰላችሁ ወንድሞቼ :: እስቲ "" ሽማግሌዬ ልሞትብኝ ነው : ለሶስት ቀን ምንም አልቀመሰም "" ያሉኝን : ከረሀቡ የተነሳ ለመተንፈስ እንኳ የሚታገሉትን አሮጊት ምን ላደርግላቸው እችላለሁ ? የነበረኝን የምችለውን ብሰጣቸው ከሁለትን ሶስት ቀን በላይ አያቆያቸውም :: ድሮ እንኳን ባዶ ቡና ጠጥተው የምግብ ስሜታቸውን ዘግተው መዋል ይችላሉ :: አሁን ማነው ቡና ኪሎ 100 ብር በገባበት ወቅት : ስኳር ኮንትሮባንድ በሆነበት ወቅት ቡና የምጠጣው ? ኦዶ ሻኪሶ ኪያ ያገር ቤቱንማ ሁኔታ ባናስታውስ ይሻላል :: በተለይ እንኳን የሰው ልጅ የእንስሳትን ህይወትን ክቡርነትን በዉጭው አለም እያየን በተቃራኒው ደግሞ የህዝባችንን ህይወት ኢምንትነት ስናይ ; ምነው እግዜሩም ያዳላል እንዴ ሊያስብለን ነው :: ወደዚያ እንኳ ሳንገባ እርሱ የፈጠራትን ነብስ እርሱ ራሱ መልሶ እስኪወስዳት መከራን መቋቋም የሚያስችላቸውን ብርታትን እንዲሰጣቸው እሱኑ ከመማጸን ውጭ መቼም ከባለስልጣኖቻችን እንደ ቀልድ የባህሪይ ለውጥ አንጠብቅም :: አምላክ ይርዳቸው !!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Sat Mar 10, 2012 8:45 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ::
.
ውድ ባለሱቅ = እንደምን አለህልኝ ? እነ አደቆርሳንም ወደዚህ እንድስባቸው ያግባባኧኝን አልተቀበልኩትም ::ከወዳጆቼ ልታጣላኝ
ነው ወይ ? እኔ እኮ እነሱ ሳያዩ ሹልክ ብዬ መጥቼ ለመሄድ እንጂ እዚህ መግባቴን ቢያዩማ በቃ የኔ ነገር ! አከተመ ማለት ነው ::
አሁንም ሁሉም ሲተኛኙ አድፍጬ ነው የመጣሁት ::ዋርካ እኮ ከነሱ ሁሉ ቂም ያላት ነው የሚመስለው :: አሁን ቢመጡ
ብልግና አይጀመርም ብላችሁ ነው ? አንፈራራማ ምርር ነው ያለው !!

ጎሲቲ ስለሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ የሰጠኧው ማስረጃ ክልብ የሚያስደንቅህና ገራገርነትህንም የሚያሳይ ነው ::
እነንም ሁሌም የሚጨንቀኝ ይሄው የወገኔ መኮራመትስ አይደል ?
ግጥምህ ግጥምጥም ነው ያለብኝ ::ትንሽ ክራር ቢጤ ብትይዝበትማ ሁሉቃን ሁሉ ባትበልጠው ነው ?
ለነገሩ ይቺን የግጥም ቤት መሰንቀር ከማን እንደለመድክ ለኔ አይነገርም ::

<< ካና እሲኒ ዺዬሴ
ተስፋዬ በሪሶዻ !>>

ይቺን ስም ስታይ ፈገግ እንደምትል ማወቄን አትጠራጠር ::
ዪመኙን ጉዳይ ብዙም አታሳድረው ::ገና የትየለሌ ፍቅረኛዎችህን
ወሬ በረድፍ ስላስያዝክል ግዜ ከመሻማት አንጻር ማለቴ ነው ::

ውድ ተድላ አየህ ገዳም መሆኔን ? እነ ወደዚህ ቤት ስመጣ ባዶ እጄን አይደለም ::የመጀመርያውን ወርቅ ገንዘቤ ዲባባ
ይዤ ከች አልኩልህ ::ለቀሩት ፍቅር ለሆኑት Iትዮጵያ አትሌቶች መልካሙን እድል እመኝላቸዋለሁ ::እኔም የሳምንቱን
መጨረሻ እንድቦርቅ ያብቃኝ ብዬ መለመኔም አይቀርም ::

ኦዶ ሻኪሶ ስለ አስዛኙ ታሪክ ዜናውን እንደሰማሁ ነበር የተከፋሁት ::ከሞቱ ውስጥ አንዱን ማወቅህም ህመምህን
እንደሚያብሰው አምናለሁ ::
ማልጎዳኒ ????
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Mar 12, 2012 6:17 pm    Post subject: Reply with quote

ማሻሻያ ተደርጎበታል !!

Last edited by Gosa on Fri Jul 20, 2012 5:38 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Mon Mar 12, 2012 9:56 pm    Post subject: Reply with quote

አሀሀሀሀ ..........ሞትኩኝ ...ሞትኩኝ በሳቅ ፍርስ ልል እኮ ነው ?
ወይኔ አይፋ ምን ዋጋ አለው አዲስ ላይ ሆነሽ ጉድሽን አልሰማሽ .........
አንተ ጉደኛ ገና ኧረ ገና ብዙ ታሪክ ሰብሳቢ ነህ ? ምን ላውራ ምን ልናገር ......
ህይወት ....አስተማሪ .....ጎሳ ...... ዋው ዋው ዋው ዋው በስመአብ በደንብ በደንብ በደንብ አስታወስኩአት ..........አቤት ስም አቀያየር ስታውቅበት
እኔ እኮ ያኔ አንተ ስትሽኮረመም ለኡሞ ወንድምህ ለመቼ ነው እርዳው አንተው ግባበት ብዬ መክሬው ነበር ::
ያንተ ነገር ስለማይሆንለት ካንተም ከሱም አምልጣ ዛሬ የሙያ አጋሯን አግብታ የሶስት (የአራት ልጆች )እናት ሆናለች ::
እርግጥ እድሜ እንደማትገናኙ እኔም መሰክራለሁ ::ህይወት ህይወት ህይወት ...አይፋ መታ ነግሬአት ብቻ !?
ኧረ እንደውም ዛሬውኑ ወደ አዲስ አበባ ስልክ መታለሁ ::ለነገሩ መምጫዋ ደርሷል ::
በናትህ ወደ ስራ ለመሄድ እየቸኮልኩ ነው
ከይመኙሻል ዘለህ ጽጌ ገባህ አይደል ?አንተ እኮ መጨረሻ ላይ ቶሎ ወደ ቦሬ ባትመለስ ኖሮ አልጋህን ሁሉ ልትሸጥ ምንም አልቀረህ ነበር ?
ወይ ቄስ ? አንተን ብሎ ቄስ ?
ግዴለም እመጣብሀለው ..አሁን ስለቸኮልኩ ነው ::

ለማንኛውም ወቤ ጃሎ ሴት ልጅ ዱቅ አድርጉአልና እንኳን ደስ አለህ በለው ::

ቸር እንሰንብት !!!
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1053
Location: ethiopia

PostPosted: Wed Mar 14, 2012 10:56 am    Post subject: Reply with quote

እየተመላለስን ነው
ጎሳን ፍለጋ

አንተ ሞፍቲ ግን ... ለካስ እንዲህ ያለህ "ጨዋ " ልጅ ነበርክ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ጎሳ ባይኖር አዳሜ ማንነትሽ እንደተደበቀ ይቀር ነበር
አይፋን እኮ አየኃት ባይገርማቹ
ቀጫጫ ነገር ትመስላለች ደሞ .... ምላሷ ግን ... አያድርስ ነው
ጥናት ላይ ከቸከለች ደሞ ... እጥብ ነው ,.....
አጣቢ ይሏት ነበር ካምፓስ

ግን ደስ ስትልልልልል ... የሴት ጓደኛ የላትም ነው ያላቹኝ ..... ስንት ነገር አስታወሳቹኝ አቦ

ወድጃቹዋለሁ ግን ሁላቹንም
ትጣፍጣላቹ .... ከምር

እስኪ ቀጥልልን አቦ "ቄስ " ጎሳ ... ደንበኛው አይደለህም እንዴ

እየጠበቅን ነው
በርታ

ሞፍቲን ግን አትስማው ... ረባሽ ነው

ውይ ረስቼ .. ለውቤ ጃሎ እንኳን ደስ ያለህ በሉልኝ
ጋዜጣ ላይ አየሁት ልበል ... ወይስ በህልሜ ነው
ረሳሁት
ለማንኛውም እንኳን እኛ ላይ ደረስክ ብለናል ...
በርትተህ ደሞ .... ሁለተኛውን ... በጊዜ .. ዱቅ
በተከታታይ ሲሆን .. ወጪ ይቀንሳልና
ፍቅርም ይበዛል
አይደለም አይፋ !
እሷ ናት ይህንን ነገር በደንብ ምታውቀው
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ሰላም ሁኑ
እንጠብቃቹዋለን
በፍቅር
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Wed Mar 14, 2012 4:16 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችንም !!!

ሞፊቲ !!!!!!!!!!!
ኧረ ግልጽ አታርገው ጉዳዩን ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ ::እኔ ስንቱን ጉድህን እንደደበቅኩልህ እያወቅክ አንተ የህይወትን ትክክለኛ ስም ልትጠራ እኮ ምንም አልቀረህም :: ስንቱን ጉድ ደብቄልሀለሁ መሰለህ አንተ እንኳ የማታስታውሳቸውን :: ንገረኝ ካልከኝ ግን ላስታውስህ እሞክራለሁ :; እነኝያ የኦክስፋሙ ኮብራዎኝ አንደበት ኖሯቸው ቢናገሩ ..... ብቻ አንተ ፍቀድልኝ :: ...ምን ትዝ እንዳለኝ ታውቃለህ : ያበደው ሾፌራችሁ !
ነገሩ እንዲህ ነው ሞፊቲ ላላጫወታችሁ ...
የነ ሞፊቲ ሾፌር ነው አሉ ትልቅ የጭነት መኪና ያሽከረክራል ወደ ጅቡቲ መስመር :: ጭነት ሊያመጣ ወደ ጅቡቲ ሲሄድ ደንገጎ ላይ ቀሽት የድሬዳዋ ልጅ ይጭናል :: ልጁም መልከመልካም ነገር ነበር መሰለኝ ሁለቱም ይፈላለጉና በሚቀጥለው ግዜ ለመገናኘት አድራሾቻቸውን ከተለዋወጡ በኌላ ልጁ ሀሳቡን ይቀይርና ድሬዳዋ አብሯት ለማደር ያግባባትና አብረው ያድራሉ :: ያው አለማቸውን እያዩ አድረው ልጁ እንቅልፉን ጨርሶ ጧት ሲነቅ አጠገቡ አልነበረችም :: ገንዘብና ጅቡቲ መግቢያ ወረቀት የነበረበት የኪስ ቦርሳውና ቀበቶው የለም : ይዛበት ሄዳለች :: የግድ ወረቀቱን ማግኘት ስለነበረበት በነገረችዉ አድራሻ አተያይቆ አባቷ ቤት ይደርሳል :: ትክክለኛ ቤቷ መሆኑን ካረጋገጠ በኌላ ቤት መኖር አለመኖሯን ብጠይቅ ቤተሰቦቿ በመገረም ዬት እንዳገኛት ይጠይቁታል :: ከዚያም ለይቷት እንዲያወጣ ፎቶግራፎችን ቀላቅለው ሲሰጡት ልጁ ትክክለኛ ፎቷን ያወጣላቸዋል :: ዝርዝር ጉዳዩን ሲነግራቸው ሰዎቹ ለቅሶ ይጀምራሉ :: በሁኔታው ግራ የተጋባው ሾፌር ለምን እንደሚያለቅሱ ሲጠይቃቸው ልጅቷ ከአምስት አመት በፊት እንደሞተች ይነግሩታል :: ልጁ ፊልም መሆኑን ተጠራጥሮ ወዲያው ፖሊስ ጣቢያ ሄዶ ፖሊስ ይዞ ይመጣል :: ፖሊሶች በሁኔታው ግራ ተጋብተው የተቀበረችበትን መቃብር እንዲያሳዩአቸው ቤተሰቦቿን ይጠይቃሉ :: ቤተሰቦቿ ልጁንና ፖሊሶቹን ወደ መቃብሩ ስወስዷቸው የልጅቷ ሀውልት እስከነፎቶግራፏ ቁጭ ብሎላቸዋል :: ሀውልቱ ላይ ደግሞ የልጁ ቦርሳና ቀበቶ ምንም ሳንቲም ሳይጎልበት ተቀምጧል :: ታዲያ ወዲያው ልጁ ዐዕምሮውን ስቶ አበደ ::

ደግሞ ዞረህ ኡሞን "በላት " ትለው ነበር እንዴ ? ለዚህ ነዋ ለሁለት ሕይወት ሆቴል አንድ ወር ሙሉ .....ጥንታዊ የጋርዮሽ ስርዓተማህበርን እኮ እኛ የደረስንበት አልመሰለኝም ነበር ሞፊቱካ ::
እውነቱን ለመናገር አንተ / ባትኖር ኖሮ እኔ ትክክለኛ ቄስ እሆን ነበር :: አበላሸኸኝ :: አይፋ ትልቅ መካሪ በሆነችበት ዘመን እንኳ አንተ ...ብቻ ልተው አሁን :: አይፋን ግን ሰላም በልልኝ :: ወቤ ጃሎን እንኳን ደስ አለህ ብዬዋለሁ : አሁንም በድጋሚ :: በጣም ነበር ደስ ያለኝ መለእክቱን ሳነበው ::

ባለሱቅ !!!!! ሞፊቲማ የድሮ አይፋን ተክቶልናል : አደገኛ ረባሽ ሆኗል :: ታሪካችንማ ይቀጥላል :: ዛሬ ግን ሞፊቲን ልሰድበው ነበር ; ግን ያን የአ / ውለታውን እያሰብኩ መጨከን አቃተኝ :: አንተም አትጥፋ እንጂ : ብቅ በል እንደልማድህ የሆነ ነገር ይዘህ :: እኔ ብቻዬን ሳወራ የሚደብራቸውና የሚሰላቹ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ገልብጤ

ውሃ አጠጪ

Joined: 26 Jun 2010
Posts: 1334

PostPosted: Wed Mar 14, 2012 4:44 pm    Post subject: Reply with quote

Quote:
የነ ሞፊቲ ሾፌር ነው አሉ ትልቅ የጭነት መኪና ያሽከረክራል ወደ ጅቡቲ መስመር :: ጭነት ሊያመጣ ወደ ጅቡቲ ሲሄድ ደንገጎ ላይ ቀሽት የድሬዳዋ ልጅ ይጭናል :: ልጁም መልከመልካም ነገር ነበር መሰለኝ ሁለቱም ይፈላለጉና በሚቀጥለው ግዜ ለመገናኘት አድራሾቻቸውን ከተለዋወጡ በኌላ ልጁ ሀሳቡን ይቀይርና ድሬዳዋ አብሯት ለማደር ያግባባትና አብረው ያድራሉ :: ያው አለማቸውን እያዩ አድረው ልጁ እንቅልፉን ጨርሶ ጧት ሲነቅ አጠገቡ አልነበረችም :: ገንዘብና ጅቡቲ መግቢያ ወረቀት የነበረበት የኪስ ቦርሳውና ቀበቶው የለም : ይዛበት ሄዳለች :: የግድ ወረቀቱን ማግኘት ስለነበረበት በነገረችዉ አድራሻ አተያይቆ አባቷ ቤት ይደርሳል :: ትክክለኛ ቤቷ መሆኑን ካረጋገጠ በኌላ ቤት መኖር አለመኖሯን ብጠይቅ ቤተሰቦቿ በመገረም ዬት እንዳገኛት ይጠይቁታል :: ከዚያም ለይቷት እንዲያወጣ ፎቶግራፎችን ቀላቅለው ሲሰጡት ልጁ ትክክለኛ ፎቷን ያወጣላቸዋል :: ዝርዝር ጉዳዩን ሲነግራቸው ሰዎቹ ለቅሶ ይጀምራሉ :: በሁኔታው ግራ የተጋባው ሾፌር ለምን እንደሚያለቅሱ ሲጠይቃቸው ልጅቷ ከአምስት አመት በፊት እንደሞተች ይነግሩታል :: ልጁ ፊልም መሆኑን ተጠራጥሮ ወዲያው ፖሊስ ጣቢያ ሄዶ ፖሊስ ይዞ ይመጣል :: ፖሊሶች በሁኔታው ግራ ተጋብተው የተቀበረችበትን መቃብር እንዲያሳዩአቸው ቤተሰቦቿን ይጠይቃሉ :: ቤተሰቦቿ ልጁንና ፖሊሶቹን ወደ መቃብሩ ስወስዷቸው የልጅቷ ሀውልት እስከነፎቶግራፏ ቁጭ ብሎላቸዋል :: ሀውልቱ ላይ ደግሞ የልጁ ቦርሳና ቀበቶ ምንም ሳንቲም ሳይጎልበት ተቀምጧል :: ታዲያ ወዲያው ልጁ ዐዕምሮውን ስቶ አበደ ::

አልገቢቶ ልጁ ያደረው ከሰላቢ መንፈስ ጋር ነው ?

ይቅርታ ለቤቱ ይህንን ቤት ሁሌ ስለማነበውና ስለምወደው ነው የሻማ ሳልከፍል የገባሁት
_________________
SEX IS NOT THE ANSWIER, SEX IS THE QUESTION '* YES* IS THE ANSWIER
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1053
Location: ethiopia

PostPosted: Fri Mar 16, 2012 9:27 am    Post subject: Reply with quote

አንተ ጎሳ
Quote:
ሀውልቱ ላይ ደግሞ የልጁ ቦርሳና ቀበቶ ምንም ሳንቲም ሳይጎልበት ተቀምጧል ::

ባይገርምህ ይህንን ታሪክ ሚስጢር ነው ብሎ አንድ ጓደኛዬ በጣም በጣም ልጅ እያለሁ ነው የነገረኝ
ሞፍቲ ያኔ ቁምጣ አድርጎ ያባቱ ማሳ እሸት በቆሎ ለመሸልቀቅ ገጠር በእግሩ ይመላለስ ነበር
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
የመስሪያ ቤታችን ሹፌር ደረሰበት ብሎ የነገረህ ታሪክን አምነት ከተቀበልክ
ወይ እውነተኛ ቄስ ነበርክ ... ወይም .... ያሁኑ እኔን ሆነሀል
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ለማንኛውም በናፍቆት በምጠብቀው ታሪክህ ውስጥ ያስገባሀት መርፌ ተመችታኛለች
ጠቅ ነው ያደረገችኝ ....
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ይቀጥላል ብለህ ያቆምከውን ታሪክ አስቀጥለው .... ሲንጠለጠል ጥሩ አይደለም ... የተፈጠሩት ሰዎች አልባሌ ቦታ ላይ አስቁመሀቸው ... እንዳይደክሙብህ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
እኔም እመጣለሁ በአዲስ ኢነርጂ
የሞፍቲን ጉድ ግን ብዙ መስማት እፈልግ ነበር ....
ጨማምረህ በልልኝ አቦ
እመለሳለሁ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Fri Mar 16, 2012 5:28 pm    Post subject: Reply with quote

ማሻሻያ ተደርጎበታል !!

Last edited by Gosa on Fri Jul 20, 2012 5:42 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ኦዶ ሻኪሶ

አዲስ

Joined: 22 Sep 2006
Posts: 37
Location: adolla lagadembi

PostPosted: Fri Mar 16, 2012 6:24 pm    Post subject: Reply with quote

የታደለች አገር ናት የተወለድንባት እንዴት እንዴት ያሉ ልጆች ተፈጥረዋል ኮራሁባቹህ በችሎታችሁ ::
ጎሳ እስካሁን የታባህ ቆይተህ ነው አሁን ጥዋት ማታ ወደኮምፒተር ምታሮጠን am very proud of you Guys . ዋርካን ወደድሮ ለዛው መለስከው :
እኔም ማስታወስ ችላለሁ ይገርማችሁአል አልረሳም ግን መፃፍ አልችልም ከማለት ጠላለሁ ብል ይሻላል እናንተጋ ሁሉም combined ነው ::
ጕደኞቼ ባለቤቴም በሁላቹም ችሎታ ስለሚደነቁ ሲያወሩ ኩራት ይሰማኛል ::
አውራዎቹ ራስብሩ አደቆርሳ አንፈራራ እንዲመለሱ አድርጉ ዋርካ ላይ ሚጻፈው ትልቅ ዲል አይደለም ማለቴ እኛ ምናገባን ? ማንን ነው ምናኮርፈው ?
ሞፍቲኮ ሰው ሲተኛ ሹልክ ማለት ይቅርብህ አላልኩም ቅቅቅቅቅቅ ገደልከኝ :
አንዳንዴ በለቅሶ ቤትና በቀበሌ እየተመካኜ አብሮ ማደር ምናምን ታስታውሳለህ ?
ተጨማሪ ዜና እንደሰማሁት ኮንቴነር ውስጥ ከሞቱት ::
በጉዞ ላይ እያሉ ትንፋሽ እያጡ ሲመጡ ኮንቴነሩን ቢደበድቡ ቢጮሁ ማንም አይሰማቸውም :
ሹፌርና ረዳት ሙዚቃ እየሰሙ በምርቃና በረሀውን ይነዱታል ::
ከተሳፋሪ አንዱ ሞባይሉን አውጥቶ አዲሳባ ላለው ደላላ ደወለለትና እረ እያለቅን ነው ብሎ ነገረው
የዚህን ግዜ ደላላው ለሹፌሩ ደውሎ ምንድነው ልጆቹ እያለቅን ለው ይላሉ አቁምና እያቸው አለው :
ሹፌሩ መኪናውን አቁሞ ኮንቴነሩን ሲከፍት ኦልሬዲ 11 ልጆች ሞተዋል ::
ጎሳ ያልከው ልክ ነው ግን አይን እያየ ወደሞት ከመሄድ ሌላ መንገድ መፈለግ ጥሩ ይመስለኛል ::
አለዛም ወይ ማረስ ወይ ድንጋይ መፍለጥ ይሻላል እንጂ ዋና የማይችለው ከውሀው ጀርባ ያለውን አይቶ ባህር ሊሻገር ቢገባ የማ ጥፋት ነው ? እኔ አይታየኝም ::
ከጃንሆይ ዘመን ጀምሮ ምንም ጥሩ ኑሮ ባገራችን ኖሮ አያቅም :: ወደፊትም ይብሳል እንጂ የሚሻል ነው ብይ አላስብም ::
_________________
May God bless Adolla
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Fri Mar 16, 2012 8:06 pm    Post subject: Reply with quote

ተመለስኩ አሁንም ::

ኦዶ ሻኪሶ ኪያ ጃኬት : ምናምኑን አውልቄ ጥዬ በካኒቴራ ብቻ ነኝ : በጣም ሞቆኝ :: ገብቶኛል አንተማ ጧትና ማታ እዚህ ኮምፒውተሩ ስር ተጎልቼ እንድውል ልታረገኝ ነው አይደል ? ቅቅቅቅቅ :: ለመልካም አስተያየትህ ሳናመሰግንህ ብናልፍ ደግሞ ድሮም መጻፍ ስለማትወድ ሁለተኛ ጣቶችህን አትቀስርም ወደ ኪቦርዱ ብለን ፈራን :: አቀሳሰርህ ደግሞ አሪፍ መሆንህን ስለሚመሰክርልህ በናትህ እንዲሁ ብቅ በልልን ወንድማችን :: ለሚያደንቁን ቤተሰቦችህም ምስጋናችንን ባታቀርብልን እራሳቸው ይታዘቡሀል ስለሚያነቡት ::
የሁላችንም ጸሎት እኮ እነኝያ አንጋፋ ጸሀፊያን እነ ራስ ብሩ : አንፈራራ እና አዶቆርሳ በሆነ ተዐምር እንዲመለሱልን ነው :: ትንሽ ግዜ እንጠብቃቸውና ካልመጡ ፊርማ አሰባስበን ወደአዲሱ ቤት ሄደን እንዲመልሱልን እንጠይቃቸዋለን ወርቃማ አባሎቻችንን ::መች እንዲሁ "ኼደዋል " ብለን እንተዋቸዋለን !!እንኳን ለነሱ ለኤርትራም ተስፋ አልቆረጥንም እስካሁን ::
ስለ ባለፈው አስራ አንዱ ልጆች የሰጠኽን ተጨማሪ ማብራሪ ደግሞ ይበልጥ ነክቶኛል :: ባጭሩ ዘግናኝ ነው ከማለት ዉጭ ምንም አልናገር :: ሞት እያየኽው ሲመጣብህ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Sat Mar 17, 2012 7:52 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ::

Quote:
ሞፊቲ !!!!!!!!!!!
ኧረ ግልጽ አታርገው ጉዳዩን ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ ::እኔ ስንቱን ጉድህን እንደደበቅኩልህ እያወቅክ አንተ የህይወትን ትክክለኛ ስም ልትጠራ እኮ ምንም አልቀረህም :: ስንቱን ጉድ ደብቄልሀለሁ መሰለህ አንተ እንኳ የማታስታውሳቸውን :: ንገረኝ ካልከኝ ግን ላስታውስህ እሞክራለሁ :; እነኝያ የኦክስፋሙ ኮብራዎኝ አንደበት ኖሯቸው ቢናገሩ ..... ብቻ አንተ ፍቀድልኝ

አንተ ጉደኛ .. ስለ ሀረር እና ኦክስፋም ድሮ ድሮ በዚህ ፔጅ አውርተን ጨርሰናል ::ምንም የቀረ ነገር የለም ::
በሹፌሩ አሳበህ እኔን ልትሸነቁጥ ሙከራ ስታደርግ ባለሱቅ ደርሶ ባያስቆምህ ኖሮ የልጅቱ <ኤኬራ > ሞፊቲም ላይ ደርሷል ማለትህ አይቀርም ነበር ::

መቼም ስለህይወት ታሪክ ከዚህ የበለጠ እንደማታወራ አምናለሁ ::ገፋ ካልክ የኔ ምላሽ ግልጥ ነው ::
እኔ እንደውም ጎሳ ክሊኒክ ስለነበረችዋና መልኳን ብቻ ለማየት ከቦሬ እየመጣን ስለምንፈዝባት የሸገር ልጅ
ታነሳለህ ብዬ ነበር ?አቤት ውበት ቁንጅና ...አረማመድ ድምፅ ,,ፈገግታ ... አቃቃም ....አለባበስ .....ኡፍ ,...ያኔ አንቺ
ከህይወት በቡቂ ወተት ሴሮ ስትጨብሺ እኛ የአዱ ገነቷ ልጅ ዱቅ ብለን እጣኑን አጫጭሰን ከራማውን እየተለማመን ልቧ ለማን አድልቶ ይሆን እያልን በመልጋኖ ጫት እንመረቅን ነበር ::

Quote:
ሞፍቲኮ ሰው ሲተኛ ሹልክ ማለት ይቅርብህ አላልኩም ቅቅቅቅቅቅ ገደልከኝ

አንዳንዴ በለቅሶ ቤትና በቀበሌ እየተመካኜ አብሮ ማደር ምናምን ታስታውሳለህ ?

ኦዶ = በጣም ነው ያሳከኝ :: እውነት ለመናገር ሰው ሲተኛ ሹልክ ማለት ከልጅነት የለመደብኝ ነገር ነው ::
ያንን ነገር እንኳ መጀምርያ ንንንንንንን ያደረኩት እኛ ቤት ጠጅ ከምትሸጥ ልጅ ሰው ሲተኛ ተሸብልዬ ነው ::
በዛው ለምዶብኝ እሄው አንተ እንዳየኧኝ ሆኜ ቀርቼልሀለው ::

Quote:
ወደማውቀው ጥሩ ምግብ ቤት ወሰድኳት :; እፊቴ ቁጭ ብላ ሳያት ከባለፈው ይበልጥ አምራ ታየችኝ :: ድሮ ቀይ ሴት ብቻ ነበር በቁንጅና የምትስበኝ :: ዛሬ ደግሞ እንደ ግድግዳ ሰዕል ብሩሽና ቀለም ያልነካኳትን ንጹህ የጠይም ቆንጆ አየሁ :: ዐይናፋርነቷ ደግሞ በጣም ተመቸኝ : አቤት ስወዳቸው የሚያፍሩትን : ስለማይጨቃጨቁ ብዙ አያስጨንቁም ::ወይ ጎሳ ? የቄሶቹ ገንዘብ እያለ ምን ችግር አለ ብለህ ነው ? ለኛስ ትተርፍ አልነበር ? ግን ወደማውቀው ጥሩ
ምግብ ቤት ስትል ከት ብዬ ነው የሳኩት ...ሞፊቲ ይነቃብኛል ብለህ ነው ? ኢታሊ ሆቴል ወስድኳት ለምን አትልም ?
መቼም ከዛ እንደማታልፍ አውቃለሁ ;; መከረኛ የከርከሮ
ይሁን የቀበሮ አሮስቶ ....ልዩ ወይን .....ልዩ የምግብ ጠረቤዛ
..ሻማ ....ለስላሳ ሙዚቃ ....በጣም የተመቸ ሰፊ መኝታ ........
አጭርም ረዥምም .....መሄድ የሚቻልበት ...ጸጥታው የጸጥታውን ምክር ቤት የመሰለ .....በቃ ! ከዛ አታልፍም ከኢታሊ !!!ሁሉንም እዛው ነው አዛ ያረከው አንተ ሌባ !
ደግሞ ቀይና ብጫ እያልክ ከለር መምረጥ ጀመርክ አይደል ? ባለሱቅ እንዳያነብህ ...ስማ ሱቂቲ ..አንድም ቀን
ከለርና መልክ አይቶ ወይም ለይቶ አያውቅም ....,በቃ ! ዳሌ ካለ የባለሱቅ ቦላሌ ቁልፉ ተበጥሶ ግንዱ ሲደንስ ነው የሚታየው ::

ዋው በጣም መሽቷል ለካ ? እኩለሊት ሆኖብኛል ;;አደራችሁን ወደዚህ መምጣቴን ወደዛናው ቤት እንዳትነግሩብኝ ::

ቸር እንሰንብት !!!!!
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Sat Mar 17, 2012 8:49 am    Post subject: Reply with quote

ሞፊቲ

"" ...መቼም ስለህይወት ታሪክ ከዚህ የበለጠ እንደማታወራ አምናለሁ ::ገፋ ካልክ የኔ ምላሽ ግልጥ ነው ::
እኔ እንደውም ጎሳ ክሊኒክ ስለነበረችዋና መልኳን ብቻ ለማየት ከቦሬ እየመጣን ስለምንፈዝባት የሸገር ልጅ
ታነሳለህ ብዬ ነበር ?አቤት ውበት ቁንጅና ...አረማመድ ድምፅ ,,ፈገግታ ... አቃቃም ....አለባበስ .....ኡፍ ,...ያኔ አንቺ
ከህይወት በቡቂ ወተት ሴሮ ስትጨብሺ እኛ የአዱ ገነቷ ልጅ ዱቅ ብለን እጣኑን አጫጭሰን ከራማውን እየተለማመን ልቧ ለማን አድልቶ ይሆን እያልን በመልጋኖ ጫት እንመረቅን ነበር ::""

ቅቅቅቅቅቅቅቅ
ያኔ እኮ በጣም ታሳዝኑን ነበር :: አንዲት ምስኪን ኤኬራ ከነገሌ መጥታ የአዱ ገነት ልጅ ነኝ ብላ ስትጫወትባችሁ አንጀታችንን ትበሉን ነበር :: ከምታጬሰውና ከምትለምነው ከራማ እንኳ ትንሽ መጠርጠር አልቻላችሁም :: አሷን ልጅ እኮ ኡሞ ሻኪሶ ወስዷት ሁለቱ ጓደኞችህን "" የጠራ ምላስ ያለው ይውሰዳት "" ብሏቸው መጨረሻ ላይ እነርሱን አባልታ ተሸበለለችባቸው እነርሱ እዚያ ሲሟዘዙባት :: ልጅቷ መቼም ረቂቅ ስለነበረች አትጨበጥም :: ምናልባት አንተንም ሀረር መንገድ በግልጽ ሳታገኝህ እንዳልቀረች አምናለሁ ::

"" ...ወይ ጎሳ ? የቄሶቹ ገንዘብ እያለ ምን ችግር አለ ብለህ ነው ? ለኛስ ትተርፍ አልነበር ? ግን ወደማውቀው ጥሩ
ምግብ ቤት ስትል ከት ብዬ ነው የሳኩት ...ሞፊቲ ይነቃብኛል ብለህ ነው ? ኢታሊ ሆቴል ወስድኳት ለምን አትልም ?
መቼም ከዛ እንደማታልፍ አውቃለሁ ;; መከረኛ የከርከሮ
ይሁን የቀበሮ አሮስቶ ....ልዩ ወይን .....ልዩ የምግብ ጠረቤዛ
..ሻማ ....ለስላሳ ሙዚቃ ....በጣም የተመቸ ሰፊ መኝታ ........
አጭርም ረዥምም .....መሄድ የሚቻልበት ...ጸጥታው የጸጥታውን ምክር ቤት የመሰለ .....በቃ ! ከዛ አታልፍም ከኢታሊ !!!ሁሉንም እዛው ነው አዛ ያረከው አንተ ሌባ !""

ሞፊቲ እሱንስ ቢሆን አንተ አልነበርክ ያሳየኸኝ ? "" አጭርም ልዥምም "" ቅቅቅቅቅ ያኔ እኮ በጣም አጭር ትወድ ነበር :: እንዴት እንደሚመችህ ግርም ይለኝ ነበር ታዲያ :: የሱንም ቤት ትዝታ አንድ ቀን አስታውስሀለሁ : አንተ መቼም ሳትረሳው አትቀርም ከብዛታቸው የተነሳ :: ደግሞ "" የቄስን ለቄስ "" እያልክ መች እንድከፍል ታረገኛለህና ነው ልናንተም የምተርፈው .::

"" ደግሞ ቀይና ብጫ እያልክ ከለር መምረጥ ጀመርክ አይደል ? ባለሱቅ እንዳያነብህ ...ስማ ሱቂቲ ..አንድም ቀን
ከለርና መልክ አይቶ ወይም ለይቶ አያውቅም ....,በቃ ! ዳሌ ካለ የባለሱቅ ቦላሌ ቁልፉ ተበጥሶ ግንዱ ሲደንስ ነው የሚታየው ::""

ባለሱቅማ የተሻለውን ነው የመረጠው : የሚያዝ : የሚጨበጥ ነው ዳሌ :: ያንተ እኮ ሞፊቲ ኪያ ይህ ነው አይባልም :: ምናልባት ድምጽ ይሆን ? ብዙዎቹ ደግሞ የወንድ ይሁን የሴት ለመለየት ያስቸግራል :: ዋናው ነገር ግን አወዳደቅህን በስተመጨረሻ አሳመረልህ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Sat Mar 17, 2012 4:25 pm    Post subject: Reply with quote

ማሻሻያ ተደርጎበታል !!

Last edited by Gosa on Fri Jul 20, 2012 5:54 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Mar 19, 2012 11:57 am    Post subject: Reply with quote

ማሻሻያ ተደርጎበታል !!

Last edited by Gosa on Fri Jul 20, 2012 5:57 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 357, 358, 359 ... 381, 382, 383  Next
Page 358 of 383

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia