View previous topic :: View next topic
Author
Message
ጋንች . Joined: 16 Dec 2011 Posts: 80
Posted: Sun Mar 18, 2012 2:30 am Post subject: የኢትዮጵያ ወታደሮች በባድሜ በኩል ድጋሚ ጥቃት ሰነዘሩ
የኢትዮጵያ ወታደሮች በባድሜ በኩል ድጋሚ ጥቃት ሰነዘሩ
Ethiopia Zare (ቅዳሜ መጋቢት 9 ቀን 2004 ዓ .ም . March 17, 2012)፦
የኤርትራ መንግስት ኢትዮጵያ ድንበሬን ጥሳ ለፈጸመችበት ጥቃት ጠንካራ እርምጃ ሊወሰድባት ይገባል በማለት ለጸጥታው ምክር ቤት ክስ ባቀረበች በማግስቱ የኢትዮጵያ ወታደሮች ዛሬ አዲስ ጥቃት መሰንዘራቸውን ሮይተርስ ዘገበ።
ጥቃቱ የተፈጸመው ዛሬ መጋቢት 9 ቀን ጠዋት ሲሆን ያስከተለው ጉዳት ልክ ግን አልተብራራም። አንድ የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ለሮይተርስ እንደገለጹት ከሆነ የዛሬው የኢትዮጵያ ወታደሮች ጥቃት የተፈጸመው በሰሜናዊ ክፍል በባድሜ አቅራቢያ ሲሆን ወታደሮቹ ተልእኳቸውን በተሳካ ሁኔታ ፈጽመዋል ብለዋል።
ባለፈው ሀሙስ በኤርትራ ደቡባዊ ምስራቅ አቅጣጫ 16-18 ኪሎ ሜትር ዘልቄ ገብቼ በሶስት ወታደራዊ ጣቢያዎች ላይ ጥቃት በማድረስ የኤርትራ ተላላኪዎችን ማሰልጠኛ፣ ማቀጃና መዘጋጃ ቦታዎችን አውድሜያለሁ ሲል የኢትዮጵያ መንግስት በይፋ መግለጹ ሲታወስ ያሁኑ ጥቃት ግን በተለይ ማን ላይ ያነጣተጠረ እንደነበር ባለስልጣኑ አላብራሩም።
ከ 2 ቀናት በፊት የተወሰደውን እርምጃ የኤርትራ መንግስት በጽኑ አውግዞ “ኢትዮጵያ ይህንን መሰል ድፍረት ልትፈጽምብኝ የቻለችው አሜሪካንን ድጋፍ በመመካቷ ነው።” ሲል መወንጀሉ ይታወሳል።
የተለያዩ የኤርትራ ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ጦር ባለፈው ሀሙስ እርምጃ ለመውሰድ የወሰነው በሀገር ውስጥ በየአቅጣጫው በተነሳበት ውስጣዊ ተቃውሞ ምክንያት የህዝቡን ስሜት አቅጣጫ ለማስቀየር ነው ከማለታቸውም በላይ ያለፈውን ጦርነት ተከትሎ ለኤርትራ የተፈረደላትን ባድሜ ላለማስረከብ ማዘናጊያ አዲስ ምእራፍ ለመፍጠር ነው ሲሉም መኮነናቸው አይዘነጋም።
የዛሬውን አዲሱን ጥቃት በተመለከተ ለጋዜጠኞች የገለጹት በስም ያልተጠቀሱ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ለወታደራዊ እርምጃው ዝርዝር ሁኔታ ከሰዓታት በሗላ መግለጫ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ደብረብርሀን 33 Joined: 17 Aug 2011 Posts: 252
Posted: Sun Mar 18, 2012 3:28 am Post subject: Re: የኢትዮጵያ ወታደሮች በባድሜ በኩል ድጋሚ ጥቃት ሰነዘሩ
"" የኢትዮጵያ ወታደሮች "" የሚለውን በ "" ወያኔ ወታደሮች "" ይስተካከል ልክ እንደ ሮይተርና ቢቢሲ እነዚህም የኢትዮጵያ ድኅረ -ገጾች ይህን ሥም ሲሰጡ በጣም ያናዳሉ በዚህ በኩል ኢልያስ ክፍሌ ይበልጣቸዋል . " የወያኔ ወታደር "ና እንዲሁም " የወያኔ መንግሥት " ብሎ ነው የሚጠራቸው ሰውን በትክክለኛ ስሙ መጥራት በጣም ደስ ያስብላል :ወያኔ እና ኢትዮጵያ የሰማይና መሬት ያክል ይለያያሉ
ጋንች . እንደጻፈ(ች)ው : የኢትዮጵያ ወታደሮች በባድሜ በኩል ድጋሚ ጥቃት ሰነዘሩ