WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ንቃተ ህሊና
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ናፖሊዮን ዳኘ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 18 Apr 2008
Posts: 1878

PostPosted: Sat Mar 10, 2012 11:42 pm    Post subject: Reply with quote

ባለፉት ሶስት ቀናት ""ኮኒ 2012"" http://youtu.be/Y4MnpzG5Sqc የሚል ትንሽ ረቀቅ ለማለት የሚሞክር የፕሮፓጋንዳ ስራ ተሰርቶ በመላው ዓለም ተሰራጭቷል :: ሶስት ቀን በማይሆን ጊዜ ውስጥ 67 ሚሊየን አንደ መቶ ሺህ ሰው በላይ ክሊፑን አይቷል :: እንዲሁ ቁጥሩ በርካታ የሆነም ሰው ቪዲዮውን አምኖ ተቀብሏል ::

መጀመሪያ ነገር የአሜሪካ ኢንተለጄንስ እና የኡጋንዳ መንግስት ኮኒ የት እንዳለ ሎኬት በማድረግ ኮኒን መያዝ አቃታቸው (ራሱን እስካላጠፋ ድረስ ) ብሎ ማመን የግንዛቤ ጉድለትን ብቻ የሚያመላክት ይመስለኛል ::

ከሁሉ የከፋው ችግር ግን የፕሮፓጋንዳውን ረቂቅነት ተረድቶ ነገሩን ትንሽ በማጤን ፋንታ --- በፌስ ቡክ በፍጥነት ሼር በማድረግ ኮኒን ለመኮነን ሩጫ ይህ ነው የማይባል ጥድፊያ ተስተዋለ ::

በነገሩ የተበሳጨ የሚመስል ግለሰብ ፕሮፓጋንዳውን ቻሌንጂ የሚያድረግ ሌላ ክሊፕ ሰርቶ ሲለጥፍ (ማርች Cool
http://youtu.be/9LyYaZkC1Tg ቲዮብ ራሱ ለማንሳት ሞክሮ ነበር :: እስካሁን ያየው ሰው ሶስት ሺህ እንኳን አይሆንም ::

ያኛው ክሊፕ ግን ቲዮብ ዋና ፔጂ ላይ ፊት ለፊት ነው ፖስት የተደረገው :: በዛ ላይ አሉ የሚባሉ የምዕራብ ዓለም ሜዲያዎች ነገሩን እንዴት እንደተቀባበሉት እጂግ በጣም የሚገርም ነው :: ለዚህ ትውልድ ደሞ የእውቀት ምንጩ እኒሁ ሜዲያዎች ናቸው :: እንደወረደ ይቀበላላ የሚያየውን የሚሰማውን :: አመንክዮ ውሀ በላው ::

አበሻ እንኳን በተፈጥሮ ቆቅ ነበረ ! ይሄኛውን ጄነሬሽን ግን በእውነት ምን እንደነካው ግራ የሚያጋባ ነው :: ለነገሩ እንኳንስ እንዲህ ትንሽ ረቀቅ ለማለት የሚሞክር ፕሮፓጋንዳ ይቅር እና በህወሀት አቅም የሚሰራውን ፕሮፓጋንዳ አምኖ ተቀብሎ ህወሀት "" የልማር አርበኛ ነው "" ብሎ የሚያስብ ትውልድ ተፈጥሯል ::

የሚያስቀው ነገር ኢትዮጵያን የበለጠ ደሀ ያደረጉአት (በዝርፊያ ) ባለ ስልጣኖች ለወጣቱ ችግራችን ""ድህነት ነው "" እያሉ ንግግር ሲያሰሙ የሚያጨበጭብ ወጣት ! ንዴት እና ቁጣው ቀርቶ !

ንቃተ ህሊና !

ናፖሊዮን ዳኘ ::
_________________
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sun Mar 11, 2012 2:40 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ናፖሊዮን ዳኘ :-

ጆሴፍ ኮኔ የሚባለው በላዔሰብ እነ ሆስኒ ሙባረክ በአፍሪቃ ይከተሉ ለነበረው ጥቁር ሕዝብን እርስ በእርስ የማበጣበጥ ፖሊሲ አንዱ አስፈጻሚ ነበር :: ዛሬ ሆሲኒ ሙባረክ ለምዕራባውያን ያበረከተው ውለታ ሁሉ ተረስቶ በሆስፒታል አልጋ ላይ ሆኖ ፍርድ ቤት የሚመላለስ አሻንጉሊት ሆኗል :: ስለዚህ የላከው ሆሲኒ ሙባረክ ከሥልጣን ሲፈነገል ጆሴፍ ኮኔም አብሮ ከጨዋታው ሜዳ መወገድ ስላለበት ምዕራባውያን ተከታዩን ዕርምጃ ሲወስዱ የየአገሮቻቸውን ሕዝብ አስተያዬት ለማስቀየስ በእርሱ ላይ በቅድሚያ የካርቱን ፊልም መሥራት አለባቸው :: ያም ቢሆን ከምዕራባውያን የሚመጣው ነገር በሙሉ መጥፎ አይደለምና እኛ አፍሪቃውያን ከአንድ በላዔሰብ ብንገላገል ልንጸጽትበት አይገባም :: እንዲያውም ይህንን ፊልም የሠራው ሰው በነካ እጁ ሙሴቪኒን : ፖል ካጋሜን : አል -በሽርን : ኢሣያስን እና ለገሠን በዚህ ዘመቻው እንዲያጠቃልላቸው ማሣሠብ ይገባናል ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ናፖሊዮን ዳኘ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 18 Apr 2008
Posts: 1878

PostPosted: Sun Mar 11, 2012 5:53 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ጋሽ ተድላ

ጆሴፍ ኮኒ የጎሪላ ተዋጊ እንደመሆኑ እጁ ላይ ደም አያጣም :: በኛስ ሀገር ህወሀቶቹ ይቀናቀኗቸው የነበሩትን በተኙበት እስከመፍጀት ጀምሮ የራሳቸውን አባል ጭርም በአሰቃቂ ሁኔታ የሚያጠፉበት አሰራር አልነበራቸው ?!

ነጥቡ አንደኛ ምዕራባውያኑ በዚህ ሰዐት የዚህ አይነት ሀሳብ ይዘው የተነሱበት ምክንያት አልትሩይስቲክ አይደለም ነው :: ህጻናትን በአየር በመጨረስ ወንጀል እኮ የዘጋቢ እና ያጋላጭ ማጣት ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ምዕራባውያኑም አድርገውታል :: በኮዞቮ በኢራቅ በሊቢያ በአፍጋኒስታን ...ሌሎቹን አይነት ግድያዎስ ሳንጨምር

ሁለተኛ ነገር ደሞ በተለያዮ ጉዳዮች ላይ የሚነዙትን ፕሮፓጋንዳ አይነቶች ከማጤንም አንጻር ነው ...ወጣቱ ዝም ብሎ የፕሮፓጋንዳ አግበስባሽ ሆነ ነው ነጥቤ ::

ሁለተኛ ያስቀመጥኩት ክሊፕ ከኪኒ ባልተናነሰ ሁኔታ (እንደውም ባይበልጥ ) ራሱ ሙሴቪኒ ህጻናትን ለጦርነት ያሰለፈበት ሁኔታ እንደነበረ ነው :: የአፍሪካ የጎሪላ ተዋጊዎች በኢትዮጵያ የበቀሉትን ጨምሮ ...በዚህ ጉዳይ ላይ ተጠያቂ ናቸው ::

ሌላው በሁለተኛው ክሊፕ ማስተላለፍ የተፈለገው ነገር ነው ትልቅ ግምት ሊሰጠው ይገባል ብየ የማስበው :: በርግጠኝነት የምናገረው ነገር ምዕራባውያኑ ሀገሩን እና ህዝቡን የምር የሚወድ ሰው አይወዱም Idea የዛኑ ያህል ደሞ ዘራፊ እና ዱርየ መሪ ''ፕሮግረሲቭ ሊደር "" እያሉ ማቆላመጥ ያውቁበታል ::

ናፖሊዮን ዳኘ ::
ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ናፖሊዮን ዳኘ :-

ጆሴፍ ኮኔ የሚባለው በላዔሰብ እነ ሆስኒ ሙባረክ በአፍሪቃ ይከተሉ ለነበረው ጥቁር ሕዝብን እርስ በእርስ የማበጣበጥ ፖሊሲ አንዱ አስፈጻሚ ነበር :: ዛሬ ሆሲኒ ሙባረክ ለምዕራባውያን ያበረከተው ውለታ ሁሉ ተረስቶ በሆስፒታል አልጋ ላይ ሆኖ ፍርድ ቤት የሚመላለስ አሻንጉሊት ሆኗል :: ስለዚህ የላከው ሆሲኒ ሙባረክ ከሥልጣን ሲፈነገል ጆሴፍ ኮኔም አብሮ ከጨዋታው ሜዳ መወገድ ስላለበት ምዕራባውያን ተከታዩን ዕርምጃ ሲወስዱ የየአገሮቻቸውን ሕዝብ አስተያዬት ለማስቀየስ በእርሱ ላይ በቅድሚያ የካርቱን ፊልም መሥራት አለባቸው :: ያም ቢሆን ከምዕራባውያን የሚመጣው ነገር በሙሉ መጥፎ አይደለምና እኛ አፍሪቃውያን ከአንድ በላዔሰብ ብንገላገል ልንጸጽትበት አይገባም :: እንዲያውም ይህንን ፊልም የሠራው ሰው በነካ እጁ ሙሴቪኒን : ፖል ካጋሜን : አል -በሽርን : ኢሣያስን እና ለገሠን በዚህ ዘመቻው እንዲያጠቃልላቸው ማሣሠብ ይገባናል ::

ተድላ

_________________
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 811

PostPosted: Mon Mar 12, 2012 6:05 am    Post subject: Reply with quote

---

Last edited by እናመሰግንሃለ on Tue Sep 03, 2013 7:40 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ናፖሊዮን ዳኘ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 18 Apr 2008
Posts: 1878

PostPosted: Tue Mar 27, 2012 5:13 pm    Post subject: Reply with quote

ከሁለት የተለያዮ በጎሳ የተደራችጁ ብድን አመራሮች ጋር ስለያዙት የፖለቲካ አቋም እና ስለ ወደፊቱ የኢትዮጵያ ሁኔታ ለማውራት እድል ገጥሞኝ ነበር ::

አንደኛው የአፋር ነው ሌላኛው አክራሪ ይባሉ የነበሩ ኦነጎች ወገን የሆነ ሰው ነው :: ከኦነጉ ጋር ያደረኩት ብዙም ሳልልገረመኝ ስለሱ አላወራም ::

የአፋሩ አስተሳሰብ ፍጹም የተረጋጋ በቀል ያልተጠናወተው በሪኮንሲሌሽን መንፈስ ወደፊት (እንደአክራሪዎቹ ወደ ኍላ የሚያይ ሳይሆን ) ሲሆን ትንሽ ኦቨር አምቢሺየስም ሆኖ አገኘሁት :: ምናለ --- ማስተዋል እና ትዕግስት እንጂ ወደፊት ኤርትራም ትመጣለች :: ጂቡቲም ትመጣለች ...ደቡብ ሱዳን እና ሌሎችም ይመጣሉ አለ :: ከውይይታችን የፖለቲካ ግንዛቤ ብቻ ሳይሆን ትምህርትም ያለው ሰው በመሆኑ የሚያወራውን ያለማወቅ ችግር እንደሌለበት እና ከምን አንጻር እያወራ እንደሆነ ግምት ወሰድኩ :: እያወራ የነበረው ምዕራባውያኑ በተለይም አሜሪካውያኑ ምስራቅ አፍሪካ አካባቢ ያሉ ሀገራትን አዳክሞ አንድ ላይ በመሰብሰብ የምስራቅ አፍሪካ ""ኮንፌደሬሽን "" ለመፍጠር የነደፉትን ፕሮጀክት እንደሆነ ገባኝ :: ወዲያው ግን ሰውየውን ትቼ ከሰውየው በስከጀርባ የኢትዮጵያዊነትን ካባ ከላይ ጣል አድርገው የደህነት ስራ እና የፖለቲካ ድለላ እየሰሩ ያሉ ሰዎችን ግምት ውስጥ አስገባሁ :: እንደገባኝ እነዚህ ሀይሎች አማራጭ ናቸው :: መስራት የተፈለገውን ነገር በህውህት በኩል መስራት ካልተቻለ እና ኢትዮጵያ ውስጥ በሀሳብ ደረቻ ያለው ጸረ -ህወሀት ተቃውሞ ህውሀትን ጠራርጎ ወደ ደደቢት ወይ ወደ እንጦሮንጦስ የሚወስድ ከሆነ ...ለመጠባበቂያ ዳረጎት እና ድጎማ እየተደረገለት ውጪ ሆኖ ዱብ ዱብ የሚል ሀይል አለ :: ቦታ ለመረከብ :: በሌላ በኩል ደሞ ውጪ ያለውን ኢትዮጵያዊ በተቃዋሚነት ስም እያግባባ የፈረንጆቹን ራዕይ እንደኢትዮጵያዊ ራዕይ አድርጎ የሚሸጥ ቡድን ነው ::

ያሳዘነኝ ታዲያ ይህንን እኩይ ስራ ለመስራት ንጹህ ኢትዮጵያውያንን ጭምር መሰብሰባቸው ነው :: ለምን ቢባል ንጹህ ኢትዮጵያዊ የሚባለው ( እነሱ ናሺናሊስት እና ጂንጎይስት ናሺናሊስት ይሉታል ) በመድረክ ላይ መስህብነት አለው :: ከበስከጀርባ ሆነው የሚያጋፍሩት ግን ተልዕኳቸው ሌላ ነው :: አፋር ያልኩት ፓለቲካኛ ለኔ ንፁህ ኢትዮጵያዊ ነበር ...ባያዋክቡት እና ባያሳክሩት :: እንደ ታማኝ በየነ ያለው የዋህ እና ቅን ኢትዮጵያዊ የሚያደርገውንም ነገር የሚያደርገው ካለው ንጹህ የሀገር ፍቅር በመነሳት ነው ... ነገር ግን ከበስከጀርባ ሆነው ሌላ ስራ እየሰሩ ፓለቲካዊ ሂደቱን በሌላ መልኩ ለሌላ ወገን የሚዘግቡ አሉ ::

ይሄንን ጉዳይ ለምን ዛሬ አነሳሁት ???

የህወሀትን ቡድን በሆዳምነት እና በዘረፋ እየከስስን በውጪ ደሞ በተቃዋሚነት ስም በሀገሩ ላይ የሚሰልል እና የፖለቲካ ድለላ የሚሰራ የሚመስል ብድን ያለ ስለመሰለኝ ነው ( i could be wrong but i am not a political naive) :: እና ምን ይጠበስ ???

ኢትዮጵያ ውስጥ ይነስም ይብዛ በሀሳብም በገቢርም ስለኢትዮጵያ ደፋ ቀና እያለ ያለ ቡድን ስላለ በውጭ በኢትዮጵያ ስም እየተንቀሳቀሰ ያለውን ቡድን ብዙ ግምት እንዳይሰጥ እና እምነት እንዳይጥልበትም ለማስታወስ ነው በድጋሚ :: ከሚቀበሉት ፈንድ እየቀነሱ የተወሰነ ነገር የወረውራሉ ማለት የፖለቲካ እሳቤያቸው መነሻ እና መድረሻ ኢትዮጵያ ናት ማለት አይደለም :: በሀገር ቤት ያሉም ፓርቲዎች ይሄንን ነገር በጥቆማ ደረጃ ይዘው ከውጪ የሚመጣን ተጽዕኖ ( በኢትዮጵያውያን በኩል ) ለመቀነስ በሳል የሆነ አካሄድ መሄድ እንዳለባቸው ለማስታወስ ነው :: ዘመኑ የሆዳምነት ሆኗል በሚያሳዝን ሁኔታ !

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የኢትዮጱያ ውስጥ ያሉ ወጣቶች -በገጠርም በከተማም - በያገኙት ቀዳዳ እና ቀዳዳም በመፍጥር ከነዚህ ሀይሎች ተጽዕኖ ነጻ በሆነ ሁኔታ ንጹህ ኢትዮጵያዊ የሆነ የፖለቲካ አደረጃጀት የሚፈጥሩበትን ሁኔታ መፍጠር ይቻላል ባይ ነው :: ውጪ ያለው ደሞ ኢትዮጵያዊ እነዚህን ሀይሉች ሙሉ በሙሉ አቮይድ ሳያደርግ ጠጋ በማለት ቢያስን አካሄዳቸውን እና አስተሳሰባቸውን ጭምር የሚከታተልበትን ሁኔታ መፍጠር ያለበት ይመስለኛል :: ፎር ዛት ማተር ፈረንጆቹ ጭምር የሚያደርጉትን አካሄድ ተጠግቶ ማወቅ የሚያስፈልግ ይመስለኛል ::

ናፖሊዮን ዳኘ ::
_________________
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ናፖሊዮን ዳኘ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 18 Apr 2008
Posts: 1878

PostPosted: Fri Mar 30, 2012 12:18 am    Post subject: Reply with quote

ይብዛም ይነስም እንደየ አስተሳሰብ አቅማችን በህይወት ዘመናችን የህይወትን ትርጉም መጠየቃችን አይቀርም ::
በዕለት ተዕለት አኗኗራችን ቫልዮ ስለምናደርገው ነገር የሚናገረው ነገር ይኖረዋል ::

በዚህ ዘመን የመገናኛ ዘዴው እየረቀቀ እንደመምጣቱ የሀሳብ ልውውጥ እና አንዳችን በሌላችን ላይ የሀሳብ ተጽዕኖ ለማድረስ ያለንን አቅም አና አጋጣሚ የጨመረ ቢመስለንም ቅሉ የአብዛኖቻችንን አስተሳሰብ እየቀረጸ ያለው ግን በትላልቅ ሜዲያዎች የሚስተጋባው የገዢዎች እና የቱጃሮች አሳብ ነው :: ትምህርት ቤት እያለሁ Is it idea or interest that matters in policy making? የሚለው ጥያቄ በጣም ይመስጠኝ ነበር :: የኔ መልስ ሁለቱም matter እንደሚያደርግ ጥርጥር የለምው :: ነገር ግን whose interest, whose idea? የሚለው ነበር ለኔ አወዛጋቢ መስሎ የሚሰማኝ :: የቱጃሮች አስተሳሰብ የዓለም እይታ እና የሰዎችን አስተሳሰብ እየቀየረ ለመምጣቱ እንደ ዋነኛ ማስረጃ ሊቀርብ የሚችል የሚመስለኝ ነገር ሰዎች - ለእውነት ለሰው ልጂ እና ለጋራ ጉዳዮች የሚሰጡት ትኩረት እና ዋጋ እየቀነሰ ----ከቁሳቁስ እና ከንዋይ ጋር ያላቸው ትስስር እየጨመረ መጥቷል :: ቱጃራዊ አስተሳሰብ ነው :: በዚህ አጋጣሚ የየእምነቱም ትምህርቶች ውሀ አልበላቸውም ለማለት ያስቸግራል ::

እንዲህ ባለ ስግብግብ ዓለም ግን ዛሬም ቢሆን የህይወት ትርጉምን ከዕቃ ከንብረት እና በዓለም ላይ ተድላ ተብሎ ከሚታሰበው ነገር ማግኘት እንደማይቻል ገብቷቸው ---ዓለምን ከነግሳብግሱ ተጠይፈው በገዳማት የገዳምን ህይወት እየኖሩ ያሉ አሉ :: ከግሸን እና ከላሊባላ ውጪ ገዳማትን ጎብኝቼ ባላውቅም ---ገዳማት ጸጥ ረጪ ያሉ የሰላም አውድማዎች እንደሆኑ ግን እገምታለሁ :: ስግብግብነት የለም :: ወድድር የለም :: ማስመሰል የለም :: ለባለስልጣን ማጎብደድ የለም :: የሀገርን ጥቅም አሳልፎ ለባዕድ መስጠት የለም :: ምቀኝነት የለም :: የጎሳ ፖለቲካ የለም ....:: ያለው ሲምፕሊሲቲ ነው ::

በነገራችን ላይ በሰማሁት እና ባለችኝ ትንሽ ንባብ ለማወዳደር ያልህ ምንም እንኳን የቡዲስት መነኮሳቶች እና ትምህርት ሰዎች በህይወት ዘመኛቸው ስቃይ እና ችግር የሚጋብዝባቸው ነገር የፈጠሩት ፍላጎት ነው ...እሱን ከገደሉ ሰላም ይኖራቸዋል ብለው ቢያምኑም ..የገዳም አኗኗራቸው በእኛ እምነት እንዳሉት መናንያን አይነት ጥንካሬ እና ሀርድ ሺፕ የሚኖሩ አይመስለኝም ::

እንደ ሰባኪ እንዳልመስል እንጂ ዛሬ ...በገዳም የሚኖሩ መናንያን የሚኖሩት ህይወት በዓለምኛ አነጋገር ሀርድ ሺፕ የበዛበት ሆኖ ሳለ ....መናንያኑ ግን ፕሌዥር ያገኙበታል :: ጆይ አላቸው :: የሚኖሩት ከሰማያዊ ሀሳብ ጋር ነው :: ጥንካሬ አላቸው :: የፕሌዥራቸው አንድ ምንጪ የሚመስለኝ በዓለም ካለው አንፕሌዛንት ነገር ጋር ስለሚያወዳድሩት ይመስለኛል .... እስኪ የኛን ዘመን ሰው እና ራሳችንን እናስበው ... ለንብረት ለገንዘብ እና ""ቤተር ላይፍ "" ባለን ክፍተኛ ጉጉት ምክንያት ሀገር የምሸጥ ሰዎች አለን ; እንደ ህወሀት ካለ ቡድን ጋር ተጠግተን የምንዘርፍ እና ማታ ማታ አስረሽ ምቺው የምንል አለን የሀገርን ፖለቲካ እና ጥቅም ለውጭ ሀይሎች በስራ እድል እና በዶላር የምንሸጥ አለን ... ቤቱ ይቁጠረው
..."ለቤተር ላይፍ " ሲባል በሌላው ላይ መረማመድ ...በሀገር ላይ መረማመድ

እንዲሀ አይነቱን ዓለም በእውነት መጠየፍ እና ራስን ከዚህ መሰወር ጀግንነትን ብቻ ሳይሆን የመንፈስ ልዕልናን ይጠይቃል ... እንደ ጠቢቡ ሰለሞን ጠቢብ መሆንን ይጠይቃል ... የህይወትን እና የነገሮችን ትርጉም ማወቅ ...:: አውሊያ አላማው ጥሩ ሙስሊም እንጂ ጥሩ ሆዳም ማውጣት አይደለም ብሎ ማሰብ የመንፈስ ልዕልና ይጠይቃል

ህወሀት ታዲያ ራሳቸውን ከዓለም ለይተው በገዳም የሚኖሩ ሰዎች ሀሳብ ከራሱ የዘራፊነት እና የአዘራፊነት ባህሪ በመነሳት ለወደፊት አንዳንድ የመንፈስ ልዕልና ያላቸው ዜጎች እንደሚወጡበት ታየው ... ሁለቱም ደሞ እሳት እና ጭድ ናቸው :: ስለዚህ ዓለሙን ወስዶ እዚያው ሊጥድባቸው ፈለገ ...ለምን ቢባል የመንፈስ ልዕልና ያለው ዜጋ '' ለእድገት እና ትራንስፎርሜሽን "" አይሆንም :: ስራዊትን ክብሮምን ሓያትን ስልኪን መሆን ያስፈልጋል ""ትራንስፎርሜሽን "" ወይ በጥቅም ወይ በጎጥ የምናምን ""ትራንስፎርሜሽን "" ...

ሌላው ዋልድባ ያልገባው ኢትዮጵያዊ ወጣት ዋልድባ የገቡትን እና የመነኑትን የሩብ ሩብ ያህል የዐለም ከንቱነት ቢገው እና ቁርጠኛ አቋም ላይ ቢደርስ እንኳን ዋልድባን እና መጅሊስን ቀርቶ ባጪር ጊዜ ኢትዮጵያን ማዳን ይቻል ነበር !

ናፖሊዮን ዳኘ ::
_________________
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ናፖሊዮን ዳኘ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 18 Apr 2008
Posts: 1878

PostPosted: Sat Oct 13, 2012 9:00 pm    Post subject: የአበሻ ፈረንጆች ታሪክ Reply with quote

ሰሞኑን 'Thanks giving' በአል ጋር ተያይዞ እንድ ጓደኛየ ስለቤተሰቦቹ ( እዚህ ውጪ ያሉ ናቸው ) በስልክ አጫወተኝ ::

እይ እዳየ ?! እለኝ ምን ሆንክ አልኩት ?! ከአጎቱ ጋር ከደቂታዎች በፊት በስልክ የተለዋወጠውን ነገር አስታውሶ ነው ::

ለካስ "Thanks Giving" በዓል ደግሰው ጠርተውት ነበር እና ልጁ ደሞ እንኳንም ስራ ኖሮት ባይኖረውም የሚሄድ አይመስለኝም :: እና ጥሪው ጋር አልሄደም :: እሱ የሚለው ለራሳችን የእንቁጣጣሽ በዓል መች ጠሩኝ እና ነው ለፈረንጂ በዓል እንዲህ ተካብዶ የምጠራው ባይ ነው :: የእጎትየውም ወቀሳ አልበቃውም ከሌላም ቦታ እንዲሁ በስልክ ደረሰኝ እለ ::
______________________
በዚያው አያይዤ ውጭ ሀገር ያሉ የአበሻ ፈረንጆች ሲገርሙህ በእኛ ዕድሜ ካሉ ካዲስ እበባ ፌስ ቡክ የሚያጠቀሙ ልጆችን ፎቶ አልበም ብታይ እንዴት ይገርምህ ነበር አልኩት ::

ከፈረንጂ ጋር ሻይ ቡና እያሉ ፎቶ ተነስቶ መለጠፍ የምሁርነት መታወቂያ እስኪመስል ድረስ ፌስ ቡክ ላይ እንዲህ እይነት ነገር ማየት የተለመደ ሆኗል አልኩት :: በመስተንግዶም ስም ለፈረንጆች ኢትዮጵያ ላይ የዘር መድሎ የመሰለ ነገር እየተደረገ ነው :: ፈንረጂ አይሰለፍም ; በካፍቴሪያዎች እና መሰል አገልግሎቶች ቅድሚያ የሚሰጥበት አግባቡ ምንድን ነው ?? በነገራችን ላይ እንዲህ አይነት ነገር የነገሰው በህወሀት አስተዳደር ዘመን እንደሆነ ልብ ይሏል !

ይሄን ሳነሳለት እንዲሁ ተረተረው .... እኔም ካዲስ አበባ ከቀበሌ 10 ፌስቡክ የሚጠቀሙ ልጆች እንዲህ ያለ ነገር ስሊጥፉ እይቼ ገርሞኛል አለኝ :: ቦሌ እና ሌላው ሌላው ከፈረንጂ ጋር የሚነሳውን ቢለጥፍ እሺ እለ "ቀበሌ አስር ምን ጨመረበት " እይነት ነገር ... እና ብዙ ተወራ

ነገሩ በጣም ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው :: ኢትዮጵያ ውስጥ ህጻናቶች በገዛ ሀገራቸው የዘር መድሎ አስተሳሰብ እያዮ እንዲያድጉ እያስፈልግም :: የቱሪዝም ኢንደስትሪውን ለማስፋፋት በባርነት የተበረዘ ማህበራዊ አስተሳሰብ መፍጠር ወንጀል ነው ---- ድንቄም ታላቅ መሪ :: የማንም ልክስክስ ባንዳ ልጂ ባንድነትን እንደ ማዕረግ ኖሮ ኖሮ ...

ናፖሊዮን ዳኘ ::
_________________
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሀዲስ 1

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 10 Mar 2010
Posts: 1631

PostPosted: Mon Oct 15, 2012 12:20 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም !!!

የሚስብ አፃፃፍ ነው ::
አፃፃፍህ ብቻ ሳይሆን ያለህ ርዕዮተ አለም በጣም ያስገርመኛል :: እውን እንደምትለው በጣም ወጣት ትሆን ይሆን ??? ... ለምን መሰለህ እንዲህ አይነት ጥያቄ ያቀረብኩልህ ? ....... ብዙዎች (ትላልቆች ) ተቃዋሚ ነን እያሉ የማይገባቸው ነገር አለ -- አንተ ግን ስለዛ ጥሩ ግንዛቤ አለህ :: ተቃዋሚ ነን ብለን የማንም መሳሪያ ልንሆን ?????
የድሮዋንና የጥንቷን ኢትዮጵያ ከመመስረት ባሻገር ምን አይነት ኢትዮጵያን ነው መመስረት ያለብን ብለን ራሳችንን መጠየቅ አለብን :: ድሮ እኮ ! ውስብስብ ያለች ኢትዮጵያ አልነበረችንም የነበረችን .... ግን ምስጋና ይግባቸውና Laughing ወያኔዎች መጥተው በተንኮላዊና በተለያየ ሰይጣናዊ ትዝታ እንድንቀዝፍ አደረጉን ::

ከኮምፒዩተሬ ፊት ተቀምጬ ይሄንን ነገር መፃፍ የለብኝም ነበረ : ሀገሬ ገብቼ ድንግል መሬቷን መንድዬ እርሻ የማያውቀውን : መንግስት ሊደርስለት ያልቻለውን ገበሬ ሰለእርሻ ባለበት ደርሼ ማስተማር ነበረብኝ .....
እንዴት አድርጎ ጥሩ አይነት ውሀ መጠጣት እንዳለበት ለወገኔ ለማስተማር ሀገሬ መግባት ነበረብኝ ግን እስካሁን በዚያም በዚያም እያልኩኝ የራሴን ጊዜንም ሆነ ወገኔ ከኔ የሚጠብቀውን ጊዜ እያጠፋሁት ነው ያለሁት ...

ወገኔ በቀላል ሁኔታ ቀላል የኑሮ ማቲማቲክስ መስራት እንዲችል ለማድረግ ባጠገቡ መገኘት ሲገባኝ : በረባውም ባልረባውም ምክንያት እየፈጠርኩኝ እሱን ሳይሆን ያዘናጋሁት ራሴ ለራሴ የራስ ምታት ሆኛለሁኝ : የሰው ሀገርም ቁራኛ ሆኛለሁኝ ::
ትንሽ በመማሬ - የኛ ማህበረሰብ (ሀገር አሳቢው ) : እየከፋፈለን ላለውና ለሰው ልጅ በጎ ( Laughing Laughing Laughing ) ለሆነው - የአለም ማህረሰብ ጥልፍልፍና አጥፊ ፕላን ወገናችን በአፀፋው መመለስ የሚገባውን ትልቅ ሪፕላይ እንዲሁም ማድረግ የሚገባውን ነገር እውን ለማድረግ እስካሁንም አልተዘጋጀሁም ::

እመለስ ይሆናል

ሀዲስናፖሊዮን ዳኘ እንደጻፈ(ች)ው:
ይብዛም ይነስም እንደየ አስተሳሰብ አቅማችን በህይወት ዘመናችን የህይወትን ትርጉም መጠየቃችን አይቀርም ::
በዕለት ተዕለት አኗኗራችን ቫልዮ ስለምናደርገው ነገር የሚናገረው ነገር ይኖረዋል ::

በዚህ ዘመን የመገናኛ ዘዴው እየረቀቀ እንደመምጣቱ የሀሳብ ልውውጥ እና አንዳችን በሌላችን ላይ የሀሳብ ተጽዕኖ ለማድረስ ያለንን አቅም አና አጋጣሚ የጨመረ ቢመስለንም ቅሉ የአብዛኖቻችንን አስተሳሰብ እየቀረጸ ያለው ግን በትላልቅ ሜዲያዎች የሚስተጋባው የገዢዎች እና የቱጃሮች አሳብ ነው :: ትምህርት ቤት እያለሁ Is it idea or interest that matters in policy making? የሚለው ጥያቄ በጣም ይመስጠኝ ነበር :: የኔ መልስ ሁለቱም matter እንደሚያደርግ ጥርጥር የለምው :: ነገር ግን whose interest, whose idea? የሚለው ነበር ለኔ አወዛጋቢ መስሎ የሚሰማኝ :: የቱጃሮች አስተሳሰብ የዓለም እይታ እና የሰዎችን አስተሳሰብ እየቀየረ ለመምጣቱ እንደ ዋነኛ ማስረጃ ሊቀርብ የሚችል የሚመስለኝ ነገር ሰዎች - ለእውነት ለሰው ልጂ እና ለጋራ ጉዳዮች የሚሰጡት ትኩረት እና ዋጋ እየቀነሰ ----ከቁሳቁስ እና ከንዋይ ጋር ያላቸው ትስስር እየጨመረ መጥቷል :: ቱጃራዊ አስተሳሰብ ነው :: በዚህ አጋጣሚ የየእምነቱም ትምህርቶች ውሀ አልበላቸውም ለማለት ያስቸግራል ::

እንዲህ ባለ ስግብግብ ዓለም ግን ዛሬም ቢሆን የህይወት ትርጉምን ከዕቃ ከንብረት እና በዓለም ላይ ተድላ ተብሎ ከሚታሰበው ነገር ማግኘት እንደማይቻል ገብቷቸው ---ዓለምን ከነግሳብግሱ ተጠይፈው በገዳማት የገዳምን ህይወት እየኖሩ ያሉ አሉ :: ከግሸን እና ከላሊባላ ውጪ ገዳማትን ጎብኝቼ ባላውቅም ---ገዳማት ጸጥ ረጪ ያሉ የሰላም አውድማዎች እንደሆኑ ግን እገምታለሁ :: ስግብግብነት የለም :: ወድድር የለም :: ማስመሰል የለም :: ለባለስልጣን ማጎብደድ የለም :: የሀገርን ጥቅም አሳልፎ ለባዕድ መስጠት የለም :: ምቀኝነት የለም :: የጎሳ ፖለቲካ የለም ....:: ያለው ሲምፕሊሲቲ ነው ::

በነገራችን ላይ በሰማሁት እና ባለችኝ ትንሽ ንባብ ለማወዳደር ያልህ ምንም እንኳን የቡዲስት መነኮሳቶች እና ትምህርት ሰዎች በህይወት ዘመኛቸው ስቃይ እና ችግር የሚጋብዝባቸው ነገር የፈጠሩት ፍላጎት ነው ...እሱን ከገደሉ ሰላም ይኖራቸዋል ብለው ቢያምኑም ..የገዳም አኗኗራቸው በእኛ እምነት እንዳሉት መናንያን አይነት ጥንካሬ እና ሀርድ ሺፕ የሚኖሩ አይመስለኝም ::

እንደ ሰባኪ እንዳልመስል እንጂ ዛሬ ...በገዳም የሚኖሩ መናንያን የሚኖሩት ህይወት በዓለምኛ አነጋገር ሀርድ ሺፕ የበዛበት ሆኖ ሳለ ....መናንያኑ ግን ፕሌዥር ያገኙበታል :: ጆይ አላቸው :: የሚኖሩት ከሰማያዊ ሀሳብ ጋር ነው :: ጥንካሬ አላቸው :: የፕሌዥራቸው አንድ ምንጪ የሚመስለኝ በዓለም ካለው አንፕሌዛንት ነገር ጋር ስለሚያወዳድሩት ይመስለኛል .... እስኪ የኛን ዘመን ሰው እና ራሳችንን እናስበው ... ለንብረት ለገንዘብ እና ""ቤተር ላይፍ "" ባለን ክፍተኛ ጉጉት ምክንያት ሀገር የምሸጥ ሰዎች አለን ; እንደ ህወሀት ካለ ቡድን ጋር ተጠግተን የምንዘርፍ እና ማታ ማታ አስረሽ ምቺው የምንል አለን የሀገርን ፖለቲካ እና ጥቅም ለውጭ ሀይሎች በስራ እድል እና በዶላር የምንሸጥ አለን ... ቤቱ ይቁጠረው
..."ለቤተር ላይፍ " ሲባል በሌላው ላይ መረማመድ ...በሀገር ላይ መረማመድ

እንዲሀ አይነቱን ዓለም በእውነት መጠየፍ እና ራስን ከዚህ መሰወር ጀግንነትን ብቻ ሳይሆን የመንፈስ ልዕልናን ይጠይቃል ... እንደ ጠቢቡ ሰለሞን ጠቢብ መሆንን ይጠይቃል ... የህይወትን እና የነገሮችን ትርጉም ማወቅ ...:: አውሊያ አላማው ጥሩ ሙስሊም እንጂ ጥሩ ሆዳም ማውጣት አይደለም ብሎ ማሰብ የመንፈስ ልዕልና ይጠይቃል

ህወሀት ታዲያ ራሳቸውን ከዓለም ለይተው በገዳም የሚኖሩ ሰዎች ሀሳብ ከራሱ የዘራፊነት እና የአዘራፊነት ባህሪ በመነሳት ለወደፊት አንዳንድ የመንፈስ ልዕልና ያላቸው ዜጎች እንደሚወጡበት ታየው ... ሁለቱም ደሞ እሳት እና ጭድ ናቸው :: ስለዚህ ዓለሙን ወስዶ እዚያው ሊጥድባቸው ፈለገ ...ለምን ቢባል የመንፈስ ልዕልና ያለው ዜጋ '' ለእድገት እና ትራንስፎርሜሽን "" አይሆንም :: ስራዊትን ክብሮምን ሓያትን ስልኪን መሆን ያስፈልጋል ""ትራንስፎርሜሽን "" ወይ በጥቅም ወይ በጎጥ የምናምን ""ትራንስፎርሜሽን "" ...

ሌላው ዋልድባ ያልገባው ኢትዮጵያዊ ወጣት ዋልድባ የገቡትን እና የመነኑትን የሩብ ሩብ ያህል የዐለም ከንቱነት ቢገው እና ቁርጠኛ አቋም ላይ ቢደርስ እንኳን ዋልድባን እና መጅሊስን ቀርቶ ባጪር ጊዜ ኢትዮጵያን ማዳን ይቻል ነበር !

ናፖሊዮን ዳኘ ::

_________________
what we learn from history is, we do not learn from history.

http://www.isil.org/resources/philosophy-of-liberty-english.swf
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዳግማዊ ዋለልኝ

ዋና አለቃ

Joined: 20 Oct 2010
Posts: 2952

PostPosted: Mon Oct 15, 2012 2:13 am    Post subject: Reply with quote

ዋርካ ላይ ሁለት ከብቶች ሲነጋገሩ እንደማንበብ የሚያስቀኝ ነገር የለም ......በተለይ ደደብሊዮና ሀዲስ 1 Laughing Laughing Laughing

በመጀመሪያ ደደብሊዮን ከሚፅፋቸው ቅዠቶች አንዱን ብቻ ለጊዜው እንዝናናበት

ናፖሊዮን ዳኘ እንደጻፈ(ች)ው:
በመስተንግዶም ስም ለፈረንጆች ኢትዮጵያ ላይ የዘር መድሎ የመሰለ ነገር እየተደረገ ነው :: ፈንረጂ አይሰለፍም ; በካፍቴሪያዎች እና መሰል አገልግሎቶች ቅድሚያ የሚሰጥበት አግባቡ ምንድን ነው ??

ኢትዮጵያ ውስጥ የትኛው ካፊቴሪያ ለፈረንጅ ቅድሚያ አገልግሎት እንደሚሰጥ ንገረኝና አብረን ሰልፍ ወጥተን እናዘጋው Wink Laughing Laughing Laughing Laughing ስትቃዥ ያደርከውን እዚህ እያመጣህ ትዘላብዳለህ ቅቅቅቅቅቅቅ

አሁን ደግሞ ወደሁለተኛው ዘገምተኛ ..ሀዲስ እንመለስ Laughing

ሀዲስ 1 እንደጻፈ(ች)ው:
ከኮምፒዩተሬ ፊት ተቀምጬ ይሄንን ነገር መፃፍ የለብኝም ነበረ : ሀገሬ ገብቼ ድንግል መሬቷን መንድዬ እርሻ የማያውቀውን : መንግስት ሊደርስለት ያልቻለውን ገበሬ ሰለእርሻ ባለበት ደርሼ ማስተማር ነበረብኝ .....

Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing

እሺ የግብርና ኤክስቴንሽን ባለሙያው ......ተቀድመሀል እኮ Laughing Laughing Laughing ለሁሉም የኢትዮጵያ ገበሬ በየቀበሌው ስለተሻሻሉና ዘመናዊ የግብርና ሂደቶች ትምህርት የሚሰጡ የግብርና ባለሙያዎች አሉ Wink ደግሞስ ለብቻዬ ላዳርስ ብትልስ ስንቱ ጋር ልትሄድ ነው Laughing ስለግብርና ማስተማር ብቅ እያሉ ዋርካ ላይ መፃፍ መሰለህ እንዴ Question Laughing Laughing Laughing Laughing

ሀዲስ 1 እንደጻፈ(ች)ው:
እንዴት አድርጎ ጥሩ አይነት ውሀ መጠጣት እንዳለበት ለወገኔ ለማስተማር ሀገሬ መግባት ነበረብኝ ግን እስካሁን በዚያም በዚያም እያልኩኝ የራሴን ጊዜንም ሆነ ወገኔ ከኔ የሚጠብቀውን ጊዜ እያጠፋሁት ነው ያለሁት ...

ኧረ በለው Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing

የኢትዮጵያ ህዝብ እኮ እንዴት አድርጎ ጥሩ ውሀ መጠጣት እንዳለበት እንዳንተ አይነት ከብት ነጋሪ አያስፈልገውም Laughing Laughing Laughing ......የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈልገው ንፅሁ የመጠጥ ውሀን የሚያቀርብለት ልማታዊ መንግስት ነው ...ገባህ ዘገምተኛው Question Laughing Laughing

ሀዲስ 1 እንደጻፈ(ች)ው:
ትንሽ በመማሬ

Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing

ገና ብዙ መማር ይቀርሀል Wink
_________________
“Meles Zenawi's passion was in abolishing poverty" Former Prime Minister of United Kingdom Gordon Brown
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8
Page 8 of 8

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia