WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ኦርቶዶክስ ቄስ ወደ ኢስላም ተቀየረ
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 20, 21, 22, 23, 24, 25  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ወልድያ

ኮትኳች

Joined: 24 May 2010
Posts: 492

PostPosted: Mon Apr 23, 2012 2:06 pm    Post subject: Reply with quote

...
9/11 ጥቃትም ከኢስላም ጋር አገንኝተኽ ስትጠቅሰው አያለው በመጅመርያ ድርጊቱ እንደድርጊት እጅግ የሚወገዝ ተግባር ነው የአሜሪካ ህዝብ የኢስላም ጠላት አይደለም

ሆኖም ደግሞ ይህንንም ቢሆን የተፈጸመው በእስራኤልና በአሜሪካ በተቀነባበረ ሴራ ነው ::

9/11 conspirecy የሚል ፈልገህ በደንብ አንብብ እውነቱን ተረዳ አንድ ወገን የሚመግብህን ታሪክ ብቻ አትቀበል ይህንን እንክዋን አልቃይዳ አሉ የተባሉ ድርጅቶች አንድ ላይ ቢያብሩ ሊፈጽምሙት አይችሉም አንድ የመንገደኛ አውሮፕላን ስለገጨው አንድ ህንጻ በሰከንዶች ውስጥ አመድ አይሆንም ! ኣስቀድሞ ዲሞሊሽ ለማድረግ የተቀበሩ ፈንጂዎች ነበሩ ከሁለቱ WTC ህንጻዎች ሌላ bulidind 7 ወይንም WTC 7 በመባል የሚታወቀው ህንጻም ምንም ነገር ሳይነካው (ማለትም በአውሮፕላን ሳይመታ እንደ ወንድሞቹ በሰከንዶች ውስጥ ወደዶግ አመድነት ተቀይርዋል ! ይህንን ህንጻስ ማን መታው ምን አፈረሰው ? ቀላል ነው እንደወንድሞቹ በፈንጂ ተሞልቶ ነበር ! 4000 በላይ wtc ውስጥ የሚሰሩ አይሁዳውያን በዛን ቀን ወደስራ አልመጡም :: ፔንታጎንም የተመታው በሚሳይል እንጂ እንደተባለው በአውሮፕላን አልነበረም ምንም አይነት የአውሮፕላን ስባሪ አካል አልተገኘም በአደጋው ቦታ ላይ ከዛም በላይ የተመታው ለእድሳት ተዘግቶ ከነበረው ሰክሽን ላይ ነው ብዙ ሚስጥሮች አሉ ፈልገህ አንብባቸው !

9/11 ኢንጅነር ጆርጅ ቡሽ ነው :: አንተ ግን አሁንም ካነበብክ በህዋላ በራስህ መወሰን ትችላለህ እኔ ግን ልነግርህ የምችለው ኢስላም ፍጹም የሚያወግዘው ስራ መሆኑን ነው

ሌላ ስለማይኖሪቲ ክርስትያኖች ያልከው ነው በነብዩ ሞሀመድ ዘመን በመዲና ማይኖኒቲ ክርስትያኖች አይሁዶች እንዲሁም ጣኦት አምላኪዎችም ነበሩ

የነብዩ መመርያ ማይኖሪቲዎችን በተመለከተ ይህ ነው "ማይኖሪቲዎችን የረበሸ እኔን ረብሽዋል እኔን የረበሸ ደግሞ አላህን ረብሽዋል ብለዋል "
ሙሉ መብታቸው የተከበረ ነበረ አሁንም በግብጽም ሆነ በሌላ ቦታ የሀይማኖት ግጭት እና አለመረጋጋት እንዲፈጠር የሚሰሩ የውጪ ሀይል ድጋፍ ያላቸው ይኖራሉ ኢራቅ ውስጥም የሀይማኖቶች ብጥብጥ የፈጠረው አሜሪካ ነው !

ከሁሉም ብጥብጦች ጀርባ የአሜሪካና የእስራኤል እጅ አለበት !

እኛ እንደፕሪሲፕል ግን የክርስትያን የእምነት ቦታዎች መከበር እንዳለባቸው ነው የምናምነው ነው የነብዩ መመርያ አሁንም ግን የግለሰቦችን ድርጊት ከሀይማኖቱ ጋር መያያዝ የለበትም ይህንን ካጋጨን ግን ፑቲን በቼችኒያ ጎዝኒ ላይ ላወረደው ቦንብ አሜሪካ ከነአጋሮችዋ አፍጋኒስታን ላይ ለምትፈጽመው ግድያ ለኢራቃውያን ሰቆቃ ክርስትና ተጠያቂ ሊሆን ነው ማለት ነው

እርግጥ ነው አግባብ ያልሆነ ስራ የሚሰሩ ሙስሊሞች ይኖራሉ ይወገዛል ግን ያንን ለማድረግ የገፋፋቸው ነገር የዜና ሽፋን አይሰጠውም provoke የሚያደርጋቸው ነገር አይገለጽም ሄድ ላይን የሚሆነው አላህ ወአክበር ብለው ሙስሊሞች ተነሱ የሚለው ነው ከዛ በፊት ግን የተሸፈነ ሌላ ዘና ይኖራል ስለዚህ በአለም አይን ቶለረንስ የለላቸው መስለው የሚታዩት ሙስሊሞች ናቸው እርግጥ ሙስሊሞችን በተለያየ መንገድ ፕሮቮክ ሊደረጉ ስለሚሞከር ይህንን አውቀው ይህን አውቀው መታገስ ማጋለጥ እንጂ ተደርድረው አላህ ወአክበር ብለው ወደቫዮለንስ የሚሄዱትን እኔም አወግዛቸዋለው የፕሮቮከሮች ወጥመድ ውስጥ በቀላሉ ገቡ ማለት ነው

ለምሳሌ የደንማርክ ጋዜጣ ካርቶን ሲስል የሚፈልገው የነዚህ አይነት ስሜታዊ ሙስሊሞችን ነው ቤት እንዲያቃጥሉ እንዲረብሹ ... ወዘተ ይህ ግን ከእውቀት ማነስ የሚመነጭ ሪአክሽን እንጂ ኢስላማዊ መንገድ አይደለም ...
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወልድያ

ኮትኳች

Joined: 24 May 2010
Posts: 492

PostPosted: Tue Apr 24, 2012 9:40 am    Post subject: Reply with quote

ስለህጻናት ግድያ ላነሳሁልህ ጥያቄም የመለስክልኝ መልስ አለ እርግጥ ነው በተፈጥራዊ አደጋዎች ህጻናትም እንደሌሎች ይጠፋሉ በወረርሽኝ በድርቅ ግዜም ህጻናት ይሞታሉ አምላክ ወደዚህ ,ድር እንዳመጣቸው እሱ ለሚፈልገው ምክንያት መልሶ ወስድዋቸዋል ሀጥያት የለላቸው ሆነውም ይቀሰቀሳሉ ብለን እናምናለን

ይህንን ግን ህጻናትን በሰይፍ ከመቅላት ጋር ታያይዘዋለህ አንተ በስፍራው ብትሆን ዛረ የተወለደ አለ የአንድ ወር ልጅ አለ የአንድ አመት ልጅ አለ የአአራት የአምስት አመት ሴት ህጻናት አሉ እነዚህ ላይ ሰይፍህን ለማንሳት እጅህ ይታዘዝልህ ነበር ? ትክክል ነው የምትል ከሆነ አልፌ አልከራከርህም ይህንንን ያነሳሁት ግን አንተ ዘመቻ የሚል ቃል ስላለ ብቻ ኢስላምን ጦረኛ አድርገህ ለመሳል የምትሞክረውን እንድትመረምረው ብቻ ነው ከዚህ የከፉ ጦረኛ ታሪኮች አሉ ...ቀላል ገለጻ ሊሰጥባቸው የማይችል !

ኢስላም (ሙሀመድ ) የፖለቲካ ስልጣን ፈልጎ ....የሚልም አገላለጽ አለህ
አንድ ታሪክ ልንገርህ

ነብዩ ሞሀመድ በመጀመርያው የኢስላም ወቅት ሙስሊሞች ቁጥራቸው በጣት የሚቆጠር ምናልባትም 40 ያልበለጠ በነበረበት ወቅት ሞሀመድን ገድለው መገላገል ይፈልጉ ነበር ግን ሞሀመድ ከጠንካራ ጎሳ ስለነበሩ ከጎሳው ሊደርስባቸው የሚችለውን ብቀላ ይፈሩ ነበር በተለይም የሞሀመድን አሳዳጊ አጎት አቡ ጣሊብን በማክበር ከድርጊታቸው ይቆጠቡ ነበር ሆኖም አንድ መደራደርያ ይዘው ወደ አቡ ጣሊብና ውደሞሀመድ መጡ
የቁረይሾች ኦፈር ይህ ነበር
"ሙሀመድ ሆይ ንግስና የምትፈልግ ከሆነ ንጉሳችን እናድርግህ
ገንዘብ ከፈለግክ ሰብስበን ከሁላችን በላይ ሀብታም እናድርግህ
ሚስት ከፈለግክ ከሁሉም ቆንጆዋን እንዳርልህ

ጥያቅያቸው ደግሞ አንድ ብቻ ነበር

"ይህን የጀመርከውን ነገር አቁምልን "

የነብዩ መልስ ምን ነበር
"ጸሀይን በቀኝ እጄ ጨረቃን በግራ እጄ ብታስጨብጡኝ ሞት እስካልወሰደኝ ድረስ አላቆመውም የሚል ነበር

ነብዩ ይህ መደራደርያ የቀረበላቸው እሳቸውና ተከታዮቻቸው በሚሳደዱበትና በደካማ ሁኔታ ላይ ባሉበት ወቅት ነው አንድ ሰው መቸም ከዚህ በላይ አለማዊ ነገር አይፈልግም መልሳቸው ግን ፈጽሞ የሚል ነበር

መሪነቱን ግን ዘግይቶ አግኝተውታል ሆኖም የመሪ አንዋኗር ኖረዋል ወይ ? ቤታቸው በጣም ጠባብ ነበር የሚተኙት ሰሌን ላይ ነበር አንድ ቀን ከበሉ አንድ ቀን ይራቡ ነበር አንድ እንግዳ ሰው ከመጣ ከተራው ሰው ፈጽሞ አይለያቸውም ነበር ሞሀመድ የሚባለው የቱ ነው ይል ነበር ?

የሞሀመድን የህይወት ታሪክ አንብብ የስከትና የተቀባይነታቸውን ሚስጥር ታገኛለህ አንተ እንዳሰብከው ስልጣን ቢፈልጉ ምንም ሳይደክሙ ውሰዱ ተብለው ነበር

ከዚህ በተጨማሪ ያነሳኸው ነገር ለመጥቀስ

ዛሬ ባብዛኛው ኢስላም የአለም ስጋት እየሆነ መምጣቱ ሙስሊሞች ባይቀበሉትም የማይታበል ሀቅ ነው ::

እርግጥ መስፋፋቱን ኢስራኤል እንደ ስጋት ልትወስደው ትችላለች ለዚህም ነው በሚድያም በጦር ሀይልም እየተዋጋችው ያለችው እንደባይተዋር ሁሉም የሚወጋውና የሚረባረብበት እምነት ኢስላም ነው ስጋት የሚባል ነገር ካለ ከዚህ ሁሉ ዘመቻ ጋር እንጠፋለን የሚል ስጋት ሊኖራቸው የሚገባው ሙስሊሞች ናቸው ሆኖም እኛ ጠባቂ ስላለው ይጠፋል ብለን አንሰጋም ሙስሊሞችን ለመፍጀት ወይንም ኢስላምን አዳክሞ የሙዝየም ሀይማኖት ለማድረግ ይህ ሰእል መፈጠር አለበት አንተም ማመን ከምትፈልገው ነገር ጋር ብሬይን ዋሺንጉ ሲደመር የምትፈልገውን ማመን ትችላለህ ..

Arrow
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወልድያ

ኮትኳች

Joined: 24 May 2010
Posts: 492

PostPosted: Tue Apr 24, 2012 1:05 pm    Post subject: Reply with quote

ሌላው ይህ ነው
Quote:
የክርስትናው እምነት ተከታይ አገሮች ውስጥ ስለ እስልምና በሰፊው ብትናገር እምነትህን ለሌሎች ብታሳውቅና እምነታቸውን ለማስለወጥ ጥረት ብታደርግ ወይም እምነትህን ከክርስትና ወደ እስልምና ብትለውጥ ማንም ምንም አይልህም :: እዲያውም ባለፈው ሳምንት ጀርመን አገር በጣም ብዙ ከተሞች ውስጥ ባንድ ቀን ሙስሊሞች በሰፊው ቁርአንን ለሰው ሲያድሉና ኢስላምን ሲያስተዋውቁ እንደነበር በዜና ተዘግቧል ::

የምእራባውያን አገሮች የሚያደርጉት ነገር ሁሉ ትክክል ነው ባልልም በዚህ ጉዳይ ላይ የሚያደርጉት ነገር ሲታይ ግን የክርስትናው እምነትና መጽሀፍ ቅዱስ ያሳደረው ተጽእኖ እንደሆነ ግልጽ ነው ::

ጀርመንን እንዴት የክርስትያን አገር ምሳሌ እንዳደረግከው ገርሞኛል በአብዛኛው አውሮፓ ኤቲየስት ናቸው ክርስትያን ባክ ግራውንድ ስላላቸው ለፎርማሊቲ ለሰርግና ለቀብር /ክርስትያን ይሄዳሉ እንጂ ያማሩትን የጸሎት ቤቶቻቸውን ለጸሎት የሚጎበኛቸው እምዛም የለም ስለዚህ እምነት አላቸው ልትል አስቸጋሪ ነው እምነታቸው ገንዘብና ይህ አለም ነው they wanna make the most of it የክርስትናው እምነት እና መጽሀፍ ቅዱስ ተጸኖ እንዳደረጉባቸውም ታምናለህ ነገር ግን እነዚሁ ህዝቦች ሁለት የአለም ጦርነቶችን አንስተው ህልቆ መሳፍርት ህዝብ ያስጨረሱ ናቸው እዚህ ላይ ክርስትና ምን አይነት ተጸኖ አሳረፈ ትላለህህ ? ሂትለር መጽሀፍ ቅዱስን ያነበበ ይመስላሀል እነዚሁ አገራት ፈረንሳይ ጀርመንና እንግሊዝ ለመቶዎች አመታት የሙስሊም አገራትን በቅኝ ገዝተዋል እመነታቸውን ያለገደብ የሚሰብኩበት እድል ነበራቸው ሰብከውማል አገርን በጦር ሀይል መያዝ እንጂ እምነትን ማስቀየር የሚችል ብቃት አልነበራቸውም እንጂ አሁንም ማቴርያላዊ ስኬት ቢኖራቸውም መንፈሳዊ ባዶነት አለባቸው አንድ በጎ ነገር ግን አላቸው open minded ናቸው ማንኛውንም ነገር ለማወቅ አእምርዋቸውን ቀድመው ዝግ አያደርጉም ስለዚህ ቁርአንንም ለማንበብ ኢስላምንም ቡዲዝምንም ለማወቅ አይፈሩም ካሳመናቸው ይቀበሉታል ካላመኑበትም ይተዉታል ይህ ግን ከክፍት አእምሮዋቸውና ከነጻ አስተዳደጋቸው የሚመነጭ እንጂ አንተ እንዳልከው የመጽሀፍ ቅዱስ ተጽእኖ አይመስለኝም ነው ካልክም እንደት እንደሆነ አስረዳኝ

ብዙ ሊበራል ማጆሪቲ ሙስሊም አገራት ውስጥም መጽሀፍ ቅዱስ የማደልም ሆነ ክርስትናን የማስተማር ችግር የለም ሳኡዲ አረብያ ግን የኢስላም ቅዱሳን ቦታዎች የመካና የመዲና አገር ነው ህዝብዋም 100% ሙስሊም ነው በህግ ደረጃም ሌላ ሀይማኖት መስበክ ክልክል ነው ቫቲካንም የካቶሊክ ምልክት ስለሆነ እዛ መስጊድ መስራት አይፈቀድም

ስለዚህ ጉዳይ ቁርአንና መጽሀፍ ቅዱስ ምን እንደሚሉ ማየት እንችላለን

Arrow
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወልድያ

ኮትኳች

Joined: 24 May 2010
Posts: 492

PostPosted: Wed Apr 25, 2012 8:15 am    Post subject: Reply with quote

በመጨረሻም ይህንን ብለሀል

Quote:
ወልድያ መጽሀፉን ማን ጻፈው ማን ዋናው እውነተኛነቱ ላይ ነው :: የመጽሀፍ ቅዱስን እውነተኛነት ከተለያየ አቅጣጫ አስርድቼሀለሁ ::

ቁርአንም ሆነ ሀዲስ የአምላክ ቃል አይደሉም :: ነው የምትል ከሆነ ሊሆን የሚችልበትን አሳማኝ ነጥብ አቅርብልኝ ::
ቁርአን የአምላክ ቃል ሊሆን እንደማይችል እኔ ላሳይህ እችላለሁ ::

በመጀመርያ መጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ የአምላክ ቃል እንዳለበት አምናለው ሆኖም ብዙ የተቀየጠ ነገር እንዳለ ነው የማምነው
አንተ ማንም ይጻፈው ማንም ብለሀል እኔ ግን ቅድምያ ነገር በአንድ መጽሀፍ ለማመን መጀመርያ ጸሀፊውን ማወቅ ግድ ይመስለኛል ለኔ ! ጸሀፊው ታውቆ ክሬደብሊቲው ሳይመረመር በደፈናው ለመቀበል አስቸጋሪ ነው እውነተኛነቱንም አስረድቼሀለው ብለኸኛል እስቲ ለምሳሌ ይሆኑ ዘንድ ከታች ያሉትን አስረዳኝ ይበልጥ ይገባኝ ዘንድ

ለምሳሌ አንድ ነገር ላሳይህ (የሰው ቋንቋን አምላክ ለምን እንዳደበላለቀ )

ኦሪት ዘፍጥረት 11 ላይ
Quote:

1 ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች።

2 ከምሥራቅም ተነሥተው በሄዱ ጊዜ በሰናዖር ምድር አንድ ሜዳ አገኙ፤ በዚያም ተቀመጡ።

3 እርስ በርሳቸውም። ኑ፥ ጡብ እንሥራ፥ በእሳትም እንተኵሰው ተባባሉ። ጡቡም እንደ ድንጋይ ሆነላቸው፤ የምድርም ዝፋት እንደ ጭቃ ሆነችላቸው።

4 እንዲህም። ለእኛ ከተማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ ሳንበተንም ስማችንን እናስጠራው አሉ።

5 እግዚአብሔርም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ።

6 እግዚአብሔርም አለ። እነሆ፥ እነርሱ አንድ ወገን ናቸው፥ ለሁሉም አንድ ቋንቋ አላቸው፤ ይህንም ለማድረግ ጀመሩ፤ አሁንም ያሰቡትን ሁሉ ለመሥራት አይከለከሉም።

7 ኑ፥ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።

8 እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ ከተማይቱንም መሥራት ተዉ።

ይህ እንግዲህ በዛን ወቅት ህዝብን ያሳምን ይሆናል ነገር ግን ከአሁኑ የዩኒቨርስ እውቀታችን እና የግንባታ ጥበባችን ጋር አዛምደህ እየው ጡብ ተደራርቦ አይደለም መሬትን የሚያክሉ ብዙ ቢልየን መሬቶች ቢኖሩ እና ቢደራረቡ እንክዋን ሰማይ ላይ አይደርሱም ይህች ምድር ከጠቅላላ ዩኒቨርሱ ጋር ስታያት ያብዋራ ብናኝ ብታክል ነው ከዚች ያብዋራ ብናኝ ላይ ምን ያህል ጭቃ ተሰብስቦና ጡብ ተሰርቶበት ነው ሰማይ የሚደርሰው ?
ለላው አሁን ያለውን የግንባታ ጥበብ እይ የቅዋንቅዋ ችግር የለም የመጠቀ ቴክኖሎጂ አለ ከጭቃ መጠፍጠፍ የበለጠ :: ከዚህ ሁሉ ቴክኖሎጂ ጋር እና የጋራ መግባብያ ከማዳበራችን ጋር የተገነባው ትልቁ የሚባልው የዱባዩ ህንጻ ቁመት አንድ ኪሎሜትር አልደረሰም በርጃጅም ህንጻዎች በተገጠገጠው በኒውዮርክ ከተማ ላይ በአይሮፕላን ከፍ ብለህ ብታልፍ አንድ ፎቅ አይታይህም ከምድር ላይ ትልልቅ ይመስሉህ የነበሩት ህንጻዎች ምን ያህል ሚጢጢ እንደሆኑ ሰማይ ላይ ሳትደርስ ትንሽ ከፍ በማለትህ ብቻ ይረዳሀል ሌላም የኦክሲጅን ችግር አለ ከፍ እያልክ በሄድክ ቁጥር ኦክሲጅን እያጠረ ይሄድና በመጨረሻም ይጠፋል ሰማይ ሳንደርስም እዚሁ አይውሮፕላን በሚበርበት ከፍታ ላይ ያለው የአትሞስፌር ቅዝቃዜ -100 ይሆናል በተአምር እዛ ድረስ እንክዋን ግምብ ቢሰሩ በኦክሲጅን ማጣትና በቅዝቃዜ ደርቀው ወደጅላቲነት ከተቀየሩ በህዋላ ይፈረካከሱ ነበር ታድያ በምን ሂሳብ አምላክ ጭቃ ጠፍጥፈው ሰማይ ላይ ይደርሳሉ ብሎ ይሰጋና የሰውን ቋንቋ ያበጣብጣል ?

የሰው ቋንቋ ባይበጣበጥ ሰማይ ላይ የሚደርስ ከተማ ሊሰራ ይችል ነበር ብለህ ትገምታለህ ስማዩን ተወው ኤቨረስት ተራራ ላይ የሚደርስ ግንብ መስራት ይችሉ ነበር ?

ሌላም አፈጣጠር ላይ ከሳይንስ ጋር የሚጋጭ ነገር አለ

ኦሪት ዘፍጥረት መጀመርያ አፈጣጠር ላይ

አምላክ በመጀመርያ ብርሀንና ጨለማን ፈጠረ ሌሊትም ሆነ ቀንም ሆነ ይላል

ወደታች ወረድ ብሎ በአራተኛው ቀን የብርሀን ምንጭ የሆኑትን ለቀንና ሌሊት መፈጠር ምክንያት የሚሆኑትን ጸሀይና ጨረቃን ከዋክብትንም በአራተኛው ቀን ፈጠራቸው ይላል

ታድያ የብርሀን ምንጮች ሳይፈጠሩ ብርሀንና ጨለማ ከየት መጡ ?

ጠለቅ ብለን ከገባን ብዙ የሚጠየቅ ነገር አለ

ቁርአን የአምላክ ቃል አይደለም የሚል ድምዳሜ አለህ እኔ ደግሞ እያንዳንድዋ ቃል የአላህ (ሱወ ) ቃል ነው የሚል እምነት አለኝ

አንተ እንዳታምን ያደረጉህ ምክንያቶች ስላሉ ልታቀርባቸው እና እኔ ለምን እንዳመንኩበት ልነግርህ እችላለው ይህ ማለት ከነገርኩህ በህዋላም ግድ ታምንበታለህ ማለት አይደለም ከዛ በህዋላም ላታምንበት ትችላለህ የሁሉም መብት ነው ነገር ግን ቢያንስ እኔ ለምን እንዳመንኩበት በመጠኑ ትረዳለህ ማለት ነው
የኔም ጥያቄ በተመሳሳዩ እኔ ያላመንኩበትን አንተ በምን መልኩ እንዳመንክበት ለመረዳት ብቻ ነው ሊያሳምነኝም ላያሳምነኝም ይችላል ነግር ግን ያመንክበትን ምክንያት ካንተ እረዳለው ከዛ ያለፈ ክርክር ውስጥ ለመግባት አይደለም

ከሰላምታ ጋር
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አሉ -ኡላ

ኮትኳች

Joined: 21 Apr 2004
Posts: 194
Location: ethiopia

PostPosted: Sun Apr 29, 2012 9:28 pm    Post subject: Reply with quote

ወልድያ እንደጻፈ(ች)ው:
...
9/11 ጥቃትም ከኢስላም ጋር አገንኝተኽ ስትጠቅሰው አያለው በመጅመርያ ድርጊቱ እንደድርጊት እጅግ የሚወገዝ ተግባር ነው የአሜሪካ ህዝብ የኢስላም ጠላት አይደለም

ሆኖም ደግሞ ይህንንም ቢሆን የተፈጸመው በእስራኤልና በአሜሪካ በተቀነባበረ ሴራ ነው ::

9/11 conspirecy የሚል ፈልገህ በደንብ አንብብ እውነቱን ተረዳ አንድ ወገን የሚመግብህን ታሪክ ብቻ አትቀበል ይህንን እንክዋን አልቃይዳ አሉ የተባሉ ድርጅቶች አንድ ላይ ቢያብሩ ሊፈጽምሙት አይችሉም አንድ የመንገደኛ አውሮፕላን ስለገጨው አንድ ህንጻ በሰከንዶች ውስጥ አመድ አይሆንም ! ኣስቀድሞ ዲሞሊሽ ለማድረግ የተቀበሩ ፈንጂዎች ነበሩ ከሁለቱ WTC ህንጻዎች ሌላ bulidind 7 ወይንም WTC 7 በመባል የሚታወቀው ህንጻም ምንም ነገር ሳይነካው (ማለትም በአውሮፕላን ሳይመታ እንደ ወንድሞቹ በሰከንዶች ውስጥ ወደዶግ አመድነት ተቀይርዋል ! ይህንን ህንጻስ ማን መታው ምን አፈረሰው ? ቀላል ነው እንደወንድሞቹ በፈንጂ ተሞልቶ ነበር ! 4000 በላይ wtc ውስጥ የሚሰሩ አይሁዳውያን በዛን ቀን ወደስራ አልመጡም :: ፔንታጎንም የተመታው በሚሳይል እንጂ እንደተባለው በአውሮፕላን አልነበረም ምንም አይነት የአውሮፕላን ስባሪ አካል አልተገኘም በአደጋው ቦታ ላይ ከዛም በላይ የተመታው ለእድሳት ተዘግቶ ከነበረው ሰክሽን ላይ ነው ብዙ ሚስጥሮች አሉ ፈልገህ አንብባቸው !

9/11 ኢንጅነር ጆርጅ ቡሽ ነው :: አንተ ግን አሁንም ካነበብክ በህዋላ በራስህ መወሰን ትችላለህ እኔ ግን ልነግርህ የምችለው ኢስላም ፍጹም የሚያወግዘው ስራ መሆኑን ነው

ሌላ ስለማይኖሪቲ ክርስትያኖች ያልከው ነው በነብዩ ሞሀመድ ዘመን በመዲና ማይኖኒቲ ክርስትያኖች አይሁዶች እንዲሁም ጣኦት አምላኪዎችም ነበሩ

የነብዩ መመርያ ማይኖሪቲዎችን በተመለከተ ይህ ነው "ማይኖሪቲዎችን የረበሸ እኔን ረብሽዋል እኔን የረበሸ ደግሞ አላህን ረብሽዋል ብለዋል "
ሙሉ መብታቸው የተከበረ ነበረ አሁንም በግብጽም ሆነ በሌላ ቦታ የሀይማኖት ግጭት እና አለመረጋጋት እንዲፈጠር የሚሰሩ የውጪ ሀይል ድጋፍ ያላቸው ይኖራሉ ኢራቅ ውስጥም የሀይማኖቶች ብጥብጥ የፈጠረው አሜሪካ ነው !

ከሁሉም ብጥብጦች ጀርባ የአሜሪካና የእስራኤል እጅ አለበት !

እኛ እንደፕሪሲፕል ግን የክርስትያን የእምነት ቦታዎች መከበር እንዳለባቸው ነው የምናምነው ነው የነብዩ መመርያ አሁንም ግን የግለሰቦችን ድርጊት ከሀይማኖቱ ጋር መያያዝ የለበትም ይህንን ካጋጨን ግን ፑቲን በቼችኒያ ጎዝኒ ላይ ላወረደው ቦንብ አሜሪካ ከነአጋሮችዋ አፍጋኒስታን ላይ ለምትፈጽመው ግድያ ለኢራቃውያን ሰቆቃ ክርስትና ተጠያቂ ሊሆን ነው ማለት ነው

እርግጥ ነው አግባብ ያልሆነ ስራ የሚሰሩ ሙስሊሞች ይኖራሉ ይወገዛል ግን ያንን ለማድረግ የገፋፋቸው ነገር የዜና ሽፋን አይሰጠውም provoke የሚያደርጋቸው ነገር አይገለጽም ሄድ ላይን የሚሆነው አላህ ወአክበር ብለው ሙስሊሞች ተነሱ የሚለው ነው ከዛ በፊት ግን የተሸፈነ ሌላ ዘና ይኖራል ስለዚህ በአለም አይን ቶለረንስ የለላቸው መስለው የሚታዩት ሙስሊሞች ናቸው እርግጥ ሙስሊሞችን በተለያየ መንገድ ፕሮቮክ ሊደረጉ ስለሚሞከር ይህንን አውቀው ይህን አውቀው መታገስ ማጋለጥ እንጂ ተደርድረው አላህ ወአክበር ብለው ወደቫዮለንስ የሚሄዱትን እኔም አወግዛቸዋለው የፕሮቮከሮች ወጥመድ ውስጥ በቀላሉ ገቡ ማለት ነው

ለምሳሌ የደንማርክ ጋዜጣ ካርቶን ሲስል የሚፈልገው የነዚህ አይነት ስሜታዊ ሙስሊሞችን ነው ቤት እንዲያቃጥሉ እንዲረብሹ ... ወዘተ ይህ ግን ከእውቀት ማነስ የሚመነጭ ሪአክሽን እንጂ ኢስላማዊ መንገድ አይደለም ...ሰላም ሰላም ወልድያ እንደምንድነህ ?
ጊዜህን መስዋእት አድርገህ ይህን ሁሉ መጻፍህን አደንቃለሁ ::

በርግጥ ሚድያ የሚለው ሁሉ እውነት ይሆናል ማለት አይደለም ::
ነገር ግን የሚታመንና የማይታመን ነገር አለ ::
ስለ 9/11 ጉዳይ እንዲያው የጠቅላላው የኢስላም ሀይማኖት እጅ አለበት አይባል :: ነገር ግን አንተ ስለጠቀስከው ነገር ሊታመን የሚችል እንደሆነና እንዳልሆነ እስቲ አንተም አስበው ::
መጀመሪያ ያንን ማስተባበያ ማን ነው የጻፈው ?
ከሁሉም ወገን ነጻ የሆነ ገለልተኛ ሆኖ የፈንጂ ቀባሪዎችን ሚስጥር ያወቅ የነበረ ወገን ነው ?
ከሆነ እንዴት ቀድሞ አላሳወቅም ? ወይም አላጋለጠም ?

ሌላው : ባለሙያው ባልሆንም እኔ እስከሚገባኝ ድረስ
አንድን ህንጻ ለማፍረስ ዳይናሚት ያስፈልጋል :: ያንን ደግሞ ባለሙያ የሆነ ሰው ግንቡ ውስጥ እየቦረቦረ እርስ በርስ በኬብል የተያያዙ ዳይናሚቶችን ይቀብራል :: ባለሙያው ከሩቅ ሆኖ ሲያፈነዳው መፈንዳት መፍረስ የሚጀምረው ከመሰረቱ ሆኖ ወደላይ ድረስ ይወጣል :: ልብ በል ከስር ነው መፍረስ የሚጀምረው :: እንግዲህ ዳይናሚት ከተቀበረ በምን አምር ነው ሲቀበር ሰው ሳያየው የሚቀረው ?????
በዚያ ላይ ህንጻው መፍረስ የጀመረው ልክ አውሮፕላኑ ከመታው ቦታ ከላይ እንጂ ከስር አይደለም ::

ደግሞስ ጥቃቅን ምክንያቶችን እየፈለጉ ባለስልጣኖችን የሚከሱና ከስልጣን ለማውረድ የሚሞክሩ ተቃዋሚዎችና የሰባዊ መብት ተሙዋጋቾች በሞሉባት አሜሪካ ይህ ነገር ከታወቀ ቡሀላ እንዴት ነው እነቡሽ ከተጠያቂነት ያመለጡት ??
የሌላ አገር ዜጋ የሆኑና እንደ ሽብርተኛ የሚቆጠሩ እስረኞችን አሰቃዩ ተብሎ ሲወነጀሉ የገዛ ወገናቸውን የፈጁ ባለስልጣኖች እንዴት ነው የማይጠየቁትና የማይጋለጡት ??
በተጨማሪ ያፈነዱት ግለሰቦች ሙስሊሞችና እንዲሆም ድርጊቱን በአላህ ስም ያደረጉ በመሆናቸው እንዴት ብሎ ነው የነቡሽ መጠቀሚያ የሆኑት ??

ሌላም ለላም ነገሮች ይኖራሉ ግን አንተ የምትለውን ለማመን ከባድ ይመስለኛል

ቁም ነገሩ ግን ሳይሆን ዋናው አንድ ሀይማኖት ጥሩ ሰዎችን ማፍራት ይገባዋል ፕሮቮክ ሲደረግም ታጋሽ የሆኑ ሰዎችን ማፍራት ይገባዋል ክፉን በክፉ ሳይሆን ክፉን በመልካም ማሸነፍ ማለት ነው ::
ይህንን እውነተኛ ክርስትናን በተመለከተ የምናገረው ስላለኝ እዚያ ውስጥ አብራራዋለሁ ::

ሙስሊሞች ግን የዚህ አይነት ባህሪ አያሳዩም :: የጠቀስከው የዴንማርኩ የካርቶን ሰእል ያስከተለው ጥፋት ትልቅ ነበር :: እኔ ያለሁበት ከተማ ውስጥ ያሉ ሙስሊሞች በማስ ብለው በመውጣት በንብረትና በሰው ላይ ታላቅ ጉዳት ነው ያደረሱት :: ኢራን ውስጥ ፓኪስታን ውስጥ ያሉ ሙስሊሞች ያደረጉትን የተቃውሞ ሰልፍና በኤምባሲ ላይ ያደረሱትን ጉዳት በዜና አይቼዋለሁ ::

ብቻ የነገርከኝን አንተም በቀላሉ እንዴት ልታምን እንደቻልክ አላውቅም ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አሉ -ኡላ

ኮትኳች

Joined: 21 Apr 2004
Posts: 194
Location: ethiopia

PostPosted: Sun Apr 29, 2012 10:20 pm    Post subject: Reply with quote

ወልድያ እንደጻፈ(ች)ው:
አሉ -ኡላ እንደጻፈ(ች)ው:
ወልድያ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም አሉ ኡላ

እናም ለመግለጽ እንደሞከርኩት የኢስላም ዶከመንት አጠባበቅ በጣም ጥሩ ነበር የቁርአን አንቀጾች ሲወርዱ ይር ቦታ እንደሆነ በምን ምክንያት የቁርአን ትእዛዝ ወይንም መልእክት እንደመጣ ጠቅላላ ዝርዝሩ በሀዲስ ላይ ተዘግብዋል ደጋግሜ ላብራራልህ እንደሞከርኩት ቁርአን ቀጥተኛ ቃል ስለሆነ ማብራርያው አብሮ አብሮ እንዲካተት አልተደረገም ይህ የሚገኘው በሀዲስ ነው ከመጽሀፍ ቅዱስ የሚለየውም በዚህ ነው መጽሀፍ ቅዱስ ባብዛኛው በትረካ መልክ የቀረበ አጻጻፍ ስልት አለው ይህ ታድያ የቀጥተኛ ንግግር አይነት ባህሪ የለውም ጸሀፊዎቹም በጣም የተለያዩ ከአንዳንዶቹ በቀርም የማይታወቁ ናቸው

ሌላው ጥያቄህ

Quote:

እንደምሳሌ ለመውሰድ ያህል ይህንን መልስልኝ :-
አምላክ መሀሪ እንደሆነና አዛኝ እንደሆነ ቁርአን ይገልጻል :: በእርግጥ አላህ መሀሪና አዛኝ መሆኑን በምን ታረጋግጣለህ ? መሀሪነቱን ያሳየበትን አጋጣሚ እስቲ ንገረኝ :: ምን ያህል እንደሚያዝንና በሰዎች በደልም ሆነ መልካም ስራ የሚሰማውን ስሜት እስቲ ንገረኝ ::
ማወቅ አያስፈልግም እንደማትል አምናለሁ ::

ብዙ ግዜ የኢትይዮጵያ ጋዜጠኞች አንድ ታዋቂ ግለሰብ ቃለመጠይቅ ሲያደርጉ መጨረሻ ላይ የሚጠይቅዋት ጥያቄ አለች በጣም ያዘንክበት ወይንም በጣም የተደሰትክበት ..አጋጣሚ ካለ ገጠመኝህን ንገረን ምናምን የምትል አይነት በኔ ግምት አንድ ሰው ኢትይጵያዊ ጋዜጠኛ ሊያናግረው ከቀጠረው አንድ ገጠምኝ አዘጋጅቶ ከሌለውም ፈጥሮ መጠበቅ አለበት Smile ይህቺ ጥያቄ መጨረሻ ላይ ስለማትቀርለት

አምላክ ግን ገጠመኞቹን መግለጽ ያለበት ይመስልሀል ? እከሌ ተርቦ አበላሁት እንዳይል ለሁሉም የሚያበላው እሱ ነው ታርዞ አለበስኩት እንዳይል ለሁላችን አልባሻችን ነው ባህሪውን ግን ገልጾልናል በተደጋጋሚ አዛኝ ነኝ ብልዋል ስለዚህ የአዛኝነቱን ባህሪ እናምናለን ሩህሩህ ነኝም ብልዋልና የርህራሄ ባህሪውን እናምናለን ለጋስ ነኝ ብልዋል የለጋስነት ባህሪውን እናምናለን እንዲሁ ብዙ ባህርያቱን ገልጾልናል በገለጻቸው ባህርያቱ ሁሉ እናምናለን የለገሰበትን ያዘነበትን ... ገጠመኞች እንዲነግረን አንጠይቅም አንድ ሰው ከእለታት አንድ ቀን የሚያደርገው ውይንም የሚያጋጥመውን ነገር እንደገጠመኝ ሊያወራው ይችላል አምላክ ግን የሁል ግዜ ባህሪውን ገጠመኝ ሊያደርገው አይችልም

ሌላውና ምናልባትም ለጥያቄዬ እንደመልስ ያስቀመጥከው ነገር ይህ ነው
Quote:

ባሁኑ ጊዜ በጣም አጥባቂ ሙስሊሞች እየበዙ መሄዳቸው የማይታበል ሀቅ ነው :: እየጠበቀ ሲመጣ ደግሞ እየከረረ ይሄዳል ::

ባጭሩ ሀይማኖቱን አጥባቂ አክራሪ ነው ማለት ነው አባባልህ ኢስላም አሁን ካለው የክርስትና እምነት ጋር ይለያል የአሁኑ ክርስትና ትኩረት የሚሰጠው በክርስቶስ መስዋእትነት ላይ ነው ክርስቶስ ሀጥያታችንን ተሸክሞልናል በመሰቀሉም ከሀይማኖታዊ ህግጋትም ነጻ አድርጎናል የሚል እምነት አለው ስለዚህ አንድ ክርስትያን የሚጠበቅበት ይህን መስዋአት ማመን ብቻ እንጂ ህግጋትን መተግበር አይደለም ማለት ነው ስለዚህ የመጠብቅና የሚላላ ነገር በክርስትና የለም ማለት ነው ወይንም እንዲወገድ ተደርግዋል ማለት ነው ጳውሎስ "' እየሱስ ስለኛ እርግማን ሆኖ ከህግ እርግማን ነጻ አደረገን ብሏል ስለዚህ ሀይማኖቱ ጥሩ ነጻነትን ያጎናጽፋል ከላይ በተወያየነው መሰረት ከሆነም እምነት ባይኖረው እንክዋን የሚጠብቀው ዘላለማዊ ሞት ነው ይህም እምብዛም አያስጨንቅም

ሆኖም ጥያቄው እውን እየሱስ ይህን ሁሉ ነጻነት አጎናጽፍዋል ወይ ነው ?

ተመልሸ እመልሰዋለው

ወልድያ በእርግጥ ሁሉም ሙስሊሞች አክራሪ ነውጠኞች ናቸው ብዬ አላምንም ሁሉም አይደሉም :: አንተ ራስህ ሽብርተኝነትን እንደምትቃወም አምናለሁ ::
ግን እኔ ለማለት የፈለኩት አንተ የሙስሊም አክራሪነት እንደሌለና በሙስሊሞች የሚደረጉትም እልቂቶች ሁሉ ራስን ከመከላከል አንጻር የተወሰዱ ናቸው የሚል አመለካከት እንዳለህ ስለተረዳሁ አመለካከትህ ትክክል እንዳልሆነ ለማሳየት ብቻ ነው ::

ሌላው ክርስትናው የሚያተኩረው በኢየሱእ መስዋእትነት ላይ ብቻ በመሆኑ ነጻነት አጎናጽፏቸዋል ብለህ የጀመርከው አባባል ከመጀመሪያውም ክርስትናን እንዳልተረዳኸው ያሳያል ::
የክርስቶስ መስዋእት አንተ እንዳሰብከው ክርስቲያኖችን የፈለጉትን እንዲያደርጉ ልቅ የሆነ ነጻነትን አልሰጠም ::
ከመጀመሪያውም አባባልህንና አረዳድህን እንድታስተካክለው ብዬ ነው ::

ሰላም አሉ ኡላ

ጀምሬ እያቅዋረጥኩኝ አስቸገርኩ አይደል Smile

እነ እርግጥ ነው መጽሀፍ ቅዱስ ብዙ ሞራላዊ ትምህርቶች እንዲሁም ደንቦችና ግዴታዎች እንዳሉት አውቃለው
አትስረቅ አትዋሽ አታመንዝር ...ይላል ሴት ልጅ አካልዋን እና ራስዋን መሸፈን እንዳለባት ያዛል ወንድ ልጅ ማመንዘር ሳይሆን ወደሴት ልጅ አይቶ በልቡ እንዳይመኛት ጭምር ያዛል መመኘቱን እራሱ እንደምንዝርና ይቆጥረዋል አሳማ መብላትን አጥብቆ ያወግዛል የአስካሪ መጠጥን ጉዳት ይዘረዝራል ወንድ ልጅ መገረዝ እንዳለበት ያዛል እነዚህ እኔ ከማቃቸው ህግጋት ጥቂቶቹ ናቸው
አለዚህ አንድ የመጽሀፍ ቅዱስ አማኝ እነዚህን ሊተገብር ግድ ይለዋል ላይሰርቅ ላይዋሽ ነው ላያመነዝር ነው በልቡም መጥፎ ምኞትን ላይመኝ ነው ሴትዋ ምኞትን እንዳትዘራ ተሸፍና መሄድ ሊኖርባት ነው ወንዱም ምኞቱን ለመከላከል እይታውን ሊሰብር ግድ ሊሆንበት ነው አሳማ መብላትን ሊተው ነው ወደአስካሪ መጠጥና ወደ ቁማር ላይሄድ ነው ወንድ ልጅ ግድ መገረዙ ግድ ሊሆንበት ነው አንድ / አንዲት መልካም ክርስትያን እነዚህን ህግጋት ሊፈጽሙ አለባቸው እነዚህን በመፈጸሙ መጽሀፍ ቅዱሳዊ ትእዛዛትን አከበረ ወይንም አጠበቀ ሊባል ይችላል ህግጋት የመጡት እንዲተገበሩና እንዲጠበቁ ነውና እነዚህ ህግጋት ለማህበረሰቡ መልካም ዜጋን ከመፍጠር ሌላ መጥፎ ጎን የላቸውም
ሆኖም እነዚህ ህግጋት የማይመችዋቸው አሉ መልቲ ቢልየን ዳለር የሚያንቀሳቅሱት የመጠጥ እና የሲጋራ ኢንዱስትሪዎች የፋሽን ኢንዱስትሪዎች የቁማር ኢንዱስትሪዎች የዝሙት ኢንደስትሪዎች ይህ ሀይማኖታዊ ዝንባሌ አያስደስታቸውም ስለዚህ በማንኛውም መልኩ ይህን ሀይማኖተኝነት መዋጋት አለባቸው

ይህንን ገጽ ሳላይ ከመሀል ጀመርኩኝ
አሁን ነው ድንገት ያየሁት ::

ህግጋትን ማክበር አይደለም አክራሪነት ማለት :: ነገር ግን ለግጋግቱ ያለው አመለካከትና አከባበር ላይ ነው ::
እንደምሳሌ ለመውሰድ የተለያዩ ሙስሊሞች በሴቶች አሸፋፈንና በሴቶች አያያዝ ላይ የተለያየ ህግን ሲተገብሩ ይታያል :: ታሊባኖች ሴቶችን መማር ይከለክላሉ በቢሮ መስራትን ይከለክላሉ ከላይ እስከ ታች ከነፊታቸው ጭምር መሸፋፈን አለባቸው :: ሙዚቃም ሆነ ፊልም መስማትም ማየትም ክልክል ነው ወዘተ .
ሌሎች ሙስሊሞች ደግሞ ሴትች ጸጉራቸውን ብቻ ይሸፍናሉ ይማራሉ ቢሮ ውስጥም መስራት ይችላሉ በርግጥ የተወሰኑ ገደቦች ቢኖሩባቸውም ማለት ነው :: የነዚህ ላላ ይላል ሙዚቃና ፊልምም የሚፈቀድባቸው የሙስሊም አገሮችና ህዝቦች አሉ ::

ቁርአን አንድ ህጉም አንድ ከሆነ የሚጠብቀውና የሚላላው ከምንድነው ትላለህ ??

Quote:
እስቲ አንተን ልጠይቅህ ደግሞ

አንድ ክርስትያን የአሳማ ስጋ መብላት ይችላል ወይ ?

አንዲት ሴት ፀጉርዋን መሸፈን አለባት ወይ ?

ወንድ መገረዝ አለበት ወይ ?

ወዘተ ...ለሎችንም ህግጋት ጨምሮ ሊፈጸሙ ግድ ነው ወይንስ በአሁኑ ግዜ ከዘመናዊው አንዋንዋር ጋር ስለማይሄዱ ግድ ላይሆኑ ይችላሉ ሊላሉ ወይንም ሊሰረዙ ይችላሉ ? በጠቅላላው ጥሩ ክርስትያን የምንለው ምንን የሚፈጽም ነው ? እየሱስ ህግጋቱን አላልትዋል ወይንስ አጥብቅዋል ?

አንድ አንቀጽ ላሳይ
ማትዮስ 5: 27
Quote:

7 አታመንዝር እንደ ተባለ ሰምታችኋል።

28 እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል።

29 ቀኝ ዓይንህም ብታሰናክልህ አውጥተህ ከአንተ ጣላት፤ ሙሉ ሰውነትህ በገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከአካላትህ አንድ ቢጠፋ ይሻልሃልና።

30 ቀኝ እጅህም ብታሰናክልህ ቆርጠህ ከአንተ ጣላት፤ ሙሉ ሰውነትህ በገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከአካላትህ አንድ ቢጠፋ ይሻላልና።

እንግዲህ እየሱስ ሰላም በሱ ላይ ይሁን እንክዋን አካላዊ ዝሙትን ከሱ ቀድሞ ወደዛ ሊመራን የሚችለውን አእምሯዊ ዝሙትን መከልከል እንደፈለገ ታያለህ ስለዚህ ይህንን መከላከል የሚፈልጉ መልካም ክርስትያኖች ካሉ አጥባቂ ብሎም አክራሪ ተብለው ስም ሊወጣላቸው ይገባልን ?

ይይህንን ጥያቄ ማለትም ስለ ህጎችና ትእዛዞች ለመረዳት ቀደም ብለህ ማወቅ የሚኖርብህ ነገሮች አሉ ::
አንተ የጠቀስካቸውን ጨምሮ በርካታ ህጎች በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ የሙሴ ህጎች ተብለው የሚታወቁ የነበሩ ናቸው :: ማለት ሙሴ የሰጣቸው ማለት ሳይሆን በሙሴ አማካኝነት ስለተሰጠ ነው ::
እናም በተለይ የሴት ጸጉር መሸፈን
የአሳማ ስጋ መብላት
የመገረዝን ህግጋት ክርስቲያኖች መጠበቅ አለባቸው ወይም የለባቸውም ለማለት የህጉን ምንነትና ለምን አላማ እንደተሰጠ ለማን እንደተሰጠ ማወቅ ያስፈልጋል ::
ይህ ሰፋ ያለ ራሱ የቻለ ትምህርት ስለሆነ ከፈለክ ወደፊት በሰፊው ላስረዳህ እችላለሁ አሁን በቀላሉ ብመልሰው መሰረቱን ስለማታውቅ ብዙ ጥያቄዎች ሊያስነሳብህ ይችላል ::

Quote:
ሌላው ስለሽብርተኝነት ያልከው ነው ይህንን ደጋግሜ ገልጨዋለው እርግጥ ነው ኢስላምን ለፖለቲካዊ ወይንም ሌላ የግል አጀንዳቸው መጠቀምያ የሚያደርጉ አሉ በኢስላም ስምም ኢስላማዊ ያልሆነ ድርጊት የሚፈጽሙ አሉ አጥብቀን እናወግዛቸዋለን እነዚህ ግን በቁጥር በጣም አናሳ የሆኑ ናቸው ከነሱ እጅግ የከፋ ስራ ክርስትያን ነን በሚሉና በክርስትና ስም ተፈጽምዋል
የክሩሴደሮችን ታሪክ ማንበብ ትችላለህ የደም ጎርፍ እንደፈጥሩ ! ያን ታሪክ አሁንም እንደሚኮሩበት ደግሞ በቅርጫት ኳስ ክለብ ስያምያቸው ብቻ ማወቅ ትችላለህ የቅርቡን ይቦስንያ ሙስሊሞች ታሪክም አንብብ በክርስትያን ሰርቦችና በክርስትና ስም የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈጸምባቸው ነበር አሜሪካ ለሁለት ሚልየን ኢራቃውያን አብዛኞቹ ህጻናትና ሰቶች ሞት ተጠያቂ ናቸው ኖርወያዊው አንድረስ በህሪንግ በክርስትና ስም የፈጸመውን ዘግናኝ ድርጊት ...እነዚህ ሁሉ በክርስትያኖች አብዛኖቹም በክርስትና ስም የተፈጸሙ ናቸው የአልቃይዳም ሆነ የማንም ድርጊት ከዚህ ጋር አይወዳደርም ታድያ ምንም እንክዋን በክርስትያኖች እና በክርስትና ስም ቢፈጸም ድርጊቱን የክርስትያን ሽብር ክርስትያን አሸባሪዎች ብሎ የገለጸ የለም እኛም በዛ መልኩ ልንገልጸው አልፈለግንም አንፈልግምም ድርጊቱንና ሀይማኖቱን ነጣጠለን ስለምንመለከት ....

Arrow
[/quote]

ወልድያ
በእርግጥ ጠቅላላው ሙስሊም ሽብርተኛ ነው ማለት አይደለም :: ነገር ግን ጥቂት ያይደሉ ሙስሊሞች በሽብር ተግባር ሲሰማሩ ሌሎች ደግሞ በሀሳብ በስሜት ወዘተ ይደግፉዋቸዋል ማለት እነሱም ተባባሪዎች ናቸው ማለት ነው :: እናም ይህ ሲሆን ከሀይማኖቱ የመሪዎች ክፍል ሀሰተኛ ሙስሊሞች እንደሆኑ እና ድርጊቱም የቁርአን እንዳልሆነ ምንም አይነት ትምህርትም ሆነ ማስተባበያ አይሰጥም የሚሰደረገው ነገር ልክ 9/11 ያፈነዱት ሙስሊሞች ሳይሆኑ እነቡሽ ናቸው የሚል ጥፋቱን ወደ ሌላ የማላከክ ተግባር ይፈጸማል :: ይህ ደግሞ ዋናዎቹንም የድርጊቱ ተባባሪ ያደርጋቸዋል ::

ስለክሩሴድና ሌሎችም በክርስትናው ስም የተደረጉትን እልቂቶች ገና ከመጀመሪያው የመጽሀፍ ቅዱስን አቁዋም የገለጽኩልህ የመስለኛል ካልዘነጋኸው ::

ክርስቲያን ነኝ ያለ በሙሉ ክርስቲያን አይደለም :: ሀሰተኛ ክርስቲያኖች እንዳሉ ለዚህም በስራቸው በአምላክ ዘንድ ተጠያቂ እንደሚሆኑ ነግሬሀለሁ ላለመድገም ነው ::
ክሩሴድስ ብቻ ሳይሆን ለላም ሌላም ብዙ ጥፋቶች ያደረሱበት ሁኔታም አለ :: እናም ጥፋታቸውን መጽሀፍ ቅዱስ አይሸሽግም እኔም ያደረሱትን በደል ለማስተባበልም ሆነ በሌላው ለማላከክ አልሞክርም :: ይህንን በተመለከተ እውነተኛ ክርስትናን በተመለከተ የምጽፈው ስላለ በዚያ ውስጥ እንደገና አነሳዋለሁ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አሉ -ኡላ

ኮትኳች

Joined: 21 Apr 2004
Posts: 194
Location: ethiopia

PostPosted: Sun Apr 29, 2012 10:35 pm    Post subject: Reply with quote

ወልድያ እንደጻፈ(ች)ው:
ስለህጻናት ግድያ ላነሳሁልህ ጥያቄም የመለስክልኝ መልስ አለ እርግጥ ነው በተፈጥራዊ አደጋዎች ህጻናትም እንደሌሎች ይጠፋሉ በወረርሽኝ በድርቅ ግዜም ህጻናት ይሞታሉ አምላክ ወደዚህ ,ድር እንዳመጣቸው እሱ ለሚፈልገው ምክንያት መልሶ ወስድዋቸዋል ሀጥያት የለላቸው ሆነውም ይቀሰቀሳሉ ብለን እናምናለን

ይህንን ግን ህጻናትን በሰይፍ ከመቅላት ጋር ታያይዘዋለህ አንተ በስፍራው ብትሆን ዛረ የተወለደ አለ የአንድ ወር ልጅ አለ የአንድ አመት ልጅ አለ የአአራት የአምስት አመት ሴት ህጻናት አሉ እነዚህ ላይ ሰይፍህን ለማንሳት እጅህ ይታዘዝልህ ነበር ? ትክክል ነው የምትል ከሆነ አልፌ አልከራከርህም ይህንንን ያነሳሁት ግን አንተ ዘመቻ የሚል ቃል ስላለ ብቻ ኢስላምን ጦረኛ አድርገህ ለመሳል የምትሞክረውን እንድትመረምረው ብቻ ነው ከዚህ የከፉ ጦረኛ ታሪኮች አሉ ...ቀላል ገለጻ ሊሰጥባቸው የማይችል !

ኢስላም (ሙሀመድ ) የፖለቲካ ስልጣን ፈልጎ ....የሚልም አገላለጽ አለህ
አንድ ታሪክ ልንገርህ

ነብዩ ሞሀመድ በመጀመርያው የኢስላም ወቅት ሙስሊሞች ቁጥራቸው በጣት የሚቆጠር ምናልባትም 40 ያልበለጠ በነበረበት ወቅት ሞሀመድን ገድለው መገላገል ይፈልጉ ነበር ግን ሞሀመድ ከጠንካራ ጎሳ ስለነበሩ ከጎሳው ሊደርስባቸው የሚችለውን ብቀላ ይፈሩ ነበር በተለይም የሞሀመድን አሳዳጊ አጎት አቡ ጣሊብን በማክበር ከድርጊታቸው ይቆጠቡ ነበር ሆኖም አንድ መደራደርያ ይዘው ወደ አቡ ጣሊብና ውደሞሀመድ መጡ
የቁረይሾች ኦፈር ይህ ነበር
"ሙሀመድ ሆይ ንግስና የምትፈልግ ከሆነ ንጉሳችን እናድርግህ
ገንዘብ ከፈለግክ ሰብስበን ከሁላችን በላይ ሀብታም እናድርግህ
ሚስት ከፈለግክ ከሁሉም ቆንጆዋን እንዳርልህ

ጥያቅያቸው ደግሞ አንድ ብቻ ነበር

"ይህን የጀመርከውን ነገር አቁምልን "

የነብዩ መልስ ምን ነበር
"ጸሀይን በቀኝ እጄ ጨረቃን በግራ እጄ ብታስጨብጡኝ ሞት እስካልወሰደኝ ድረስ አላቆመውም የሚል ነበር

ነብዩ ይህ መደራደርያ የቀረበላቸው እሳቸውና ተከታዮቻቸው በሚሳደዱበትና በደካማ ሁኔታ ላይ ባሉበት ወቅት ነው አንድ ሰው መቸም ከዚህ በላይ አለማዊ ነገር አይፈልግም መልሳቸው ግን ፈጽሞ የሚል ነበር

መሪነቱን ግን ዘግይቶ አግኝተውታል ሆኖም የመሪ አንዋኗር ኖረዋል ወይ ? ቤታቸው በጣም ጠባብ ነበር የሚተኙት ሰሌን ላይ ነበር አንድ ቀን ከበሉ አንድ ቀን ይራቡ ነበር አንድ እንግዳ ሰው ከመጣ ከተራው ሰው ፈጽሞ አይለያቸውም ነበር ሞሀመድ የሚባለው የቱ ነው ይል ነበር ?

የሞሀመድን የህይወት ታሪክ አንብብ የስከትና የተቀባይነታቸውን ሚስጥር ታገኛለህ አንተ እንዳሰብከው ስልጣን ቢፈልጉ ምንም ሳይደክሙ ውሰዱ ተብለው ነበር

ከዚህ በተጨማሪ ያነሳኸው ነገር ለመጥቀስ

ዛሬ ባብዛኛው ኢስላም የአለም ስጋት እየሆነ መምጣቱ ሙስሊሞች ባይቀበሉትም የማይታበል ሀቅ ነው ::

እርግጥ መስፋፋቱን ኢስራኤል እንደ ስጋት ልትወስደው ትችላለች ለዚህም ነው በሚድያም በጦር ሀይልም እየተዋጋችው ያለችው እንደባይተዋር ሁሉም የሚወጋውና የሚረባረብበት እምነት ኢስላም ነው ስጋት የሚባል ነገር ካለ ከዚህ ሁሉ ዘመቻ ጋር እንጠፋለን የሚል ስጋት ሊኖራቸው የሚገባው ሙስሊሞች ናቸው ሆኖም እኛ ጠባቂ ስላለው ይጠፋል ብለን አንሰጋም ሙስሊሞችን ለመፍጀት ወይንም ኢስላምን አዳክሞ የሙዝየም ሀይማኖት ለማድረግ ይህ ሰእል መፈጠር አለበት አንተም ማመን ከምትፈልገው ነገር ጋር ብሬይን ዋሺንጉ ሲደመር የምትፈልገውን ማመን ትችላለህ ..

Arrow

ሙሀመድ ስልጣንን ይዟል :: የያዘበት መንገድ ራሱ በመረጠው መንገድ ሊሆን ይችላል ዋናው ነገር የሀይማኖቱ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካውም መሪ እንደነበር ማወቁ ነው :: ይህንን በተመለከተም የምናገረው ይኖረኛል ::

ስለ አኑዋኑዋሩ ግን ድሀ ነበር ማለት ነው ??

ነቢዩ ብዙ ሚስቶች እንደነበሩት ይታወቃል ምን ያበላቸው ነበር ??

ቁራን ላይ አሁን በችኮላ ቦታው ጠፋኝ እንጂ ያነበብኩትን ሀሳቡን ልግለጸው አንተ ታውቀዋለህ ::

ነቢዩጋ ለምግብ በተጠራችሁ ጊዜ ከበላችሁ ቡሀላ ውጡ ብዙ አትቆዩ ነቢዩን አታስቸግሩት (በቀጥታ የተጻፈውን አልጻፍኩት ይሆናል ሀሳቡ ግን እንደዚህ ነው ሰሞኑን አይቼ ልጽፈው እችላለሁ እስከዛ አንተ አስተካክለው )
እንግዲህ ሌላ ሰው የሚጋብዘው ከየት ያመጣውን ነው እርሱ ከተራበ ማለት ነው ??

አንተ እንደዛ ስላልክ ነው እንጂ ገንዘብ ኖሮት ምግብ ተርፎት ቢበላና ቢጠጣ አልጋ ላይ ቢተኛ ነውር ሆኖ አይደለም ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አሉ -ኡላ

ኮትኳች

Joined: 21 Apr 2004
Posts: 194
Location: ethiopia

PostPosted: Sun Apr 29, 2012 10:59 pm    Post subject: Reply with quote

ወልድያ እንደጻፈ(ች)ው:
ሌላው ይህ ነው
Quote:
የክርስትናው እምነት ተከታይ አገሮች ውስጥ ስለ እስልምና በሰፊው ብትናገር እምነትህን ለሌሎች ብታሳውቅና እምነታቸውን ለማስለወጥ ጥረት ብታደርግ ወይም እምነትህን ከክርስትና ወደ እስልምና ብትለውጥ ማንም ምንም አይልህም :: እዲያውም ባለፈው ሳምንት ጀርመን አገር በጣም ብዙ ከተሞች ውስጥ ባንድ ቀን ሙስሊሞች በሰፊው ቁርአንን ለሰው ሲያድሉና ኢስላምን ሲያስተዋውቁ እንደነበር በዜና ተዘግቧል ::

የምእራባውያን አገሮች የሚያደርጉት ነገር ሁሉ ትክክል ነው ባልልም በዚህ ጉዳይ ላይ የሚያደርጉት ነገር ሲታይ ግን የክርስትናው እምነትና መጽሀፍ ቅዱስ ያሳደረው ተጽእኖ እንደሆነ ግልጽ ነው ::

ጀርመንን እንዴት የክርስትያን አገር ምሳሌ እንዳደረግከው ገርሞኛል በአብዛኛው አውሮፓ ኤቲየስት ናቸው ክርስትያን ባክ ግራውንድ ስላላቸው ለፎርማሊቲ ለሰርግና ለቀብር /ክርስትያን ይሄዳሉ እንጂ ያማሩትን የጸሎት ቤቶቻቸውን ለጸሎት የሚጎበኛቸው እምዛም የለም ስለዚህ እምነት አላቸው ልትል አስቸጋሪ ነው እምነታቸው ገንዘብና ይህ አለም ነው they wanna make the most of it የክርስትናው እምነት እና መጽሀፍ ቅዱስ ተጸኖ እንዳደረጉባቸውም ታምናለህ ነገር ግን እነዚሁ ህዝቦች ሁለት የአለም ጦርነቶችን አንስተው ህልቆ መሳፍርት ህዝብ ያስጨረሱ ናቸው እዚህ ላይ ክርስትና ምን አይነት ተጸኖ አሳረፈ ትላለህህ ? ሂትለር መጽሀፍ ቅዱስን ያነበበ ይመስላሀል እነዚሁ አገራት ፈረንሳይ ጀርመንና እንግሊዝ ለመቶዎች አመታት የሙስሊም አገራትን በቅኝ ገዝተዋል እመነታቸውን ያለገደብ የሚሰብኩበት እድል ነበራቸው ሰብከውማል አገርን በጦር ሀይል መያዝ እንጂ እምነትን ማስቀየር የሚችል ብቃት አልነበራቸውም እንጂ አሁንም ማቴርያላዊ ስኬት ቢኖራቸውም መንፈሳዊ ባዶነት አለባቸው አንድ በጎ ነገር ግን አላቸው open minded ናቸው ማንኛውንም ነገር ለማወቅ አእምርዋቸውን ቀድመው ዝግ አያደርጉም ስለዚህ ቁርአንንም ለማንበብ ኢስላምንም ቡዲዝምንም ለማወቅ አይፈሩም ካሳመናቸው ይቀበሉታል ካላመኑበትም ይተዉታል ይህ ግን ከክፍት አእምሮዋቸውና ከነጻ አስተዳደጋቸው የሚመነጭ እንጂ አንተ እንዳልከው የመጽሀፍ ቅዱስ ተጽእኖ አይመስለኝም ነው ካልክም እንደት እንደሆነ አስረዳኝ

ብዙ ሊበራል ማጆሪቲ ሙስሊም አገራት ውስጥም መጽሀፍ ቅዱስ የማደልም ሆነ ክርስትናን የማስተማር ችግር የለም ሳኡዲ አረብያ ግን የኢስላም ቅዱሳን ቦታዎች የመካና የመዲና አገር ነው ህዝብዋም 100% ሙስሊም ነው በህግ ደረጃም ሌላ ሀይማኖት መስበክ ክልክል ነው ቫቲካንም የካቶሊክ ምልክት ስለሆነ እዛ መስጊድ መስራት አይፈቀድም

ስለዚህ ጉዳይ ቁርአንና መጽሀፍ ቅዱስ ምን እንደሚሉ ማየት እንችላለን

Arrowወልድያ አባባሌን ወዴት ወዴት ነው የቀየርከው ? Laughing Laughing

እኔ ጀርመን አገር በሙሉ የክርስቲያን አገር ነው አላልኩም :: የሚያደርጉትም በሙሉ ትክክል ነው ብዬም አልደመደምኩም :: እንዲያውም ካቶሊኮችና ፕሮቴስታንት አማኞች የሚበዙበት አገር ነው :: እነዚህንም በተመለከተ አቁዋሜን ከመጀመሪያውም አሳውቄሀለሁ ::
ነገር ግን ለማለት የፈለኩት መጽሀፍ ቅዱሱንም በትክክል ባይከተሉትም ሙስሊሞች ያንን ሲያደርጉ በማስ በመውጣት ተቃውሞና ጥፋት አላስከተሉም ሙስሊም አገር ቢሆን ግን ተቃራኒው ነበር የሚሆነው :: በሙስሊም አገሮች መጽሀፍ ቅዱስን ለሙስሊሞች ማደል ቀርቶ ስለክርስትና መስበክ መሞከሩም ከባድ ችግር ያስነሳል ለማለት እንጂ ያውሮፓ ህዝቦች በሙሉ ትክክለኛ ክርስቲያኖች ናቸው ማለቴ አይደለም :: ይህን ተረዳ ::
ነገር ግን አውሮፓ በሙሉ አቴይስት ነው ብለህ ደምድመህ ከሆነ ስህተት ነው ::

ብቻ ይህ ባጋጣሚ የተነሳ ሁኔታ ነው እንጂ ምናልባትም መሰረታዊ ነገር ላይሆን ይችላል ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አሉ -ኡላ

ኮትኳች

Joined: 21 Apr 2004
Posts: 194
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Apr 30, 2012 12:02 am    Post subject: Reply with quote

ወልድያ እንደጻፈ(ች)ው:
በመጨረሻም ይህንን ብለሀል

Quote:
ወልድያ መጽሀፉን ማን ጻፈው ማን ዋናው እውነተኛነቱ ላይ ነው :: የመጽሀፍ ቅዱስን እውነተኛነት ከተለያየ አቅጣጫ አስርድቼሀለሁ ::

ቁርአንም ሆነ ሀዲስ የአምላክ ቃል አይደሉም :: ነው የምትል ከሆነ ሊሆን የሚችልበትን አሳማኝ ነጥብ አቅርብልኝ ::
ቁርአን የአምላክ ቃል ሊሆን እንደማይችል እኔ ላሳይህ እችላለሁ ::

በመጀመርያ መጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ የአምላክ ቃል እንዳለበት አምናለው ሆኖም ብዙ የተቀየጠ ነገር እንዳለ ነው የማምነው
አንተ ማንም ይጻፈው ማንም ብለሀል እኔ ግን ቅድምያ ነገር በአንድ መጽሀፍ ለማመን መጀመርያ ጸሀፊውን ማወቅ ግድ ይመስለኛል ለኔ ! ጸሀፊው ታውቆ ክሬደብሊቲው ሳይመረመር በደፈናው ለመቀበል አስቸጋሪ ነው እውነተኛነቱንም አስረድቼሀለው ብለኸኛል እስቲ ለምሳሌ ይሆኑ ዘንድ ከታች ያሉትን አስረዳኝ ይበልጥ ይገባኝ ዘንድ

ለምሳሌ አንድ ነገር ላሳይህ (የሰው ቋንቋን አምላክ ለምን እንዳደበላለቀ )

ኦሪት ዘፍጥረት 11 ላይ
Quote:

1 ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች።

2 ከምሥራቅም ተነሥተው በሄዱ ጊዜ በሰናዖር ምድር አንድ ሜዳ አገኙ፤ በዚያም ተቀመጡ።

3 እርስ በርሳቸውም። ኑ፥ ጡብ እንሥራ፥ በእሳትም እንተኵሰው ተባባሉ። ጡቡም እንደ ድንጋይ ሆነላቸው፤ የምድርም ዝፋት እንደ ጭቃ ሆነችላቸው።

4 እንዲህም። ለእኛ ከተማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ ሳንበተንም ስማችንን እናስጠራው አሉ።

5 እግዚአብሔርም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ።

6 እግዚአብሔርም አለ። እነሆ፥ እነርሱ አንድ ወገን ናቸው፥ ለሁሉም አንድ ቋንቋ አላቸው፤ ይህንም ለማድረግ ጀመሩ፤ አሁንም ያሰቡትን ሁሉ ለመሥራት አይከለከሉም።

7 ኑ፥ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።

8 እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ ከተማይቱንም መሥራት ተዉ።

ይህ እንግዲህ በዛን ወቅት ህዝብን ያሳምን ይሆናል ነገር ግን ከአሁኑ የዩኒቨርስ እውቀታችን እና የግንባታ ጥበባችን ጋር አዛምደህ እየው ጡብ ተደራርቦ አይደለም መሬትን የሚያክሉ ብዙ ቢልየን መሬቶች ቢኖሩ እና ቢደራረቡ እንክዋን ሰማይ ላይ አይደርሱም ይህች ምድር ከጠቅላላ ዩኒቨርሱ ጋር ስታያት ያብዋራ ብናኝ ብታክል ነው ከዚች ያብዋራ ብናኝ ላይ ምን ያህል ጭቃ ተሰብስቦና ጡብ ተሰርቶበት ነው ሰማይ የሚደርሰው ?
ለላው አሁን ያለውን የግንባታ ጥበብ እይ የቅዋንቅዋ ችግር የለም የመጠቀ ቴክኖሎጂ አለ ከጭቃ መጠፍጠፍ የበለጠ :: ከዚህ ሁሉ ቴክኖሎጂ ጋር እና የጋራ መግባብያ ከማዳበራችን ጋር የተገነባው ትልቁ የሚባልው የዱባዩ ህንጻ ቁመት አንድ ኪሎሜትር አልደረሰም በርጃጅም ህንጻዎች በተገጠገጠው በኒውዮርክ ከተማ ላይ በአይሮፕላን ከፍ ብለህ ብታልፍ አንድ ፎቅ አይታይህም ከምድር ላይ ትልልቅ ይመስሉህ የነበሩት ህንጻዎች ምን ያህል ሚጢጢ እንደሆኑ ሰማይ ላይ ሳትደርስ ትንሽ ከፍ በማለትህ ብቻ ይረዳሀል ሌላም የኦክሲጅን ችግር አለ ከፍ እያልክ በሄድክ ቁጥር ኦክሲጅን እያጠረ ይሄድና በመጨረሻም ይጠፋል ሰማይ ሳንደርስም እዚሁ አይውሮፕላን በሚበርበት ከፍታ ላይ ያለው የአትሞስፌር ቅዝቃዜ -100 ይሆናል በተአምር እዛ ድረስ እንክዋን ግምብ ቢሰሩ በኦክሲጅን ማጣትና በቅዝቃዜ ደርቀው ወደጅላቲነት ከተቀየሩ በህዋላ ይፈረካከሱ ነበር ታድያ በምን ሂሳብ አምላክ ጭቃ ጠፍጥፈው ሰማይ ላይ ይደርሳሉ ብሎ ይሰጋና የሰውን ቋንቋ ያበጣብጣል ?

የሰው ቋንቋ ባይበጣበጥ ሰማይ ላይ የሚደርስ ከተማ ሊሰራ ይችል ነበር ብለህ ትገምታለህ ስማዩን ተወው ኤቨረስት ተራራ ላይ የሚደርስ ግንብ መስራት ይችሉ ነበር
?

እኔ የጠየኩህን ሳትመልስልኝ ወደለላ ታስቀይሳለህ አደል Laughing
ቁርአን የአምላክ ቃል ለመሆኑ ምንድነው ማረጋገጫው ????

ያንተን ለመመለስ ያህል
በጣም የሚገርም አረዳድ ነው የተረዳኸው ::
እስከዛሬ በዚሀ አይነት አረዳድ ተረድቶ የተነሳ ጥያቄ ትዝ አይለኝም :: ከመመለሴ በፊት ግን ይህ አመለካከት የራስህ ግንዛቤ ነው ወይስ የጠቅላላው ሙስሊም በሙሉ ? ማለትም የኢስላም ሀይማኖት አመለካከት ?? ይህችን መልስልኝ ለማወቅ ያህል ነው ::

ለማንኛውም በቁዋንቁዋህ ሰማይ የምትለው ምንን ነው ?
ወፎች በሰማይ ላይ ይበራሉ
አውሮፕላን በሰማይ ላይ ይበራል
የሚሉትን አነጋገሮች ጥያቄ አስነስተህባቸው ታውቃለ ??
ከአይናችን እይታ ውጪ አልፈው የማያውቁትን ነገሮች እንዴት በሰማይ ይበራሉ ይባላል ? ብለህ የመጠየቅ ያህል ነው ጥያቄህ ::

ስለ ሰማይ ጠቀስ ፎቆችስ (skyscraper) ጠይቀህ ታውቃለህ ? ሰማይ ጠቀስ ህንጻ ለመባል ስንት ፎቆች ያስፈልጉታል ? ስንት ሜትር እርዝመት ሊኖረው ይገባል ? ለዚያውስ የቱ ረጅም ህንጻ ነው ሰማይ የደረሰው ብለህ የጠየከኝ ያህል ነው የተሰማኝ ::
ከምድር ከፍ ያለውን በአካባቢያችን ካሉት ነገሮች ሁሉ ከፍ ያለውን ሁሉ ሰማይ የነካ ወይም ሰማይ የደረስ የሚል የቁዋንቁዋ አጠቃቀም እንጂ አንተ እንዳሰብከው የተለየ ትርጉም የለውም ::

በመጀመሪያ ደረጃ በዘፍጥረት ላይ እስከ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንስራ የሚለውን ቃል የተናገሩት ሰዎቹ ናቸው :: ግንብ ተሰርቶ ዛሬ ድረስ ቢቆይ ኖሮ ሰማይ ጠቀስ ቀርቶ ረጅም ህንጻ ላይሰኝ ይችላል ነገር ግን በወቅቱ ካለው የህንጻ አሰራር አንጻር እና ከተሰሩት ህንጻዎች አንጻር ሲታይ ምናልባት እነሱ ሊሰሩት ያሰቡት ግንብ ረጂም ስለሚሆን ሰማይ ጠቀስ እንደሚባለው አባባል ለነሱ ሰማይ የደረሰ ግንብ ነው :::: ርዝመቱን ለማመልከት እንጂ ጠፈርን አቁዋርጦ ሰማይ ቤት ለመግባት እንዳልሆነ ምንም ጥርጥር የለውም ::

ድሮ ልጆች ሆነን ኩዋስ ሲጠለዝ ሰማይ አደረሳት እንል ነበር አባባላችን ስህተት ነበር ማለት ነው Laughing Laughing

እናም ይህ አተረጉዋጎም ፈጽሞ ምክንያታዊ አይደለም ::Quote:
ሌላም አፈጣጠር ላይ ከሳይንስ ጋር የሚጋጭ ነገር አለ

ኦሪት ዘፍጥረት መጀመርያ አፈጣጠር ላይ

አምላክ በመጀመርያ ብርሀንና ጨለማን ፈጠረ ሌሊትም ሆነ ቀንም ሆነ ይላል

ወደታች ወረድ ብሎ በአራተኛው ቀን የብርሀን ምንጭ የሆኑትን ለቀንና ሌሊት መፈጠር ምክንያት የሚሆኑትን ጸሀይና ጨረቃን ከዋክብትንም በአራተኛው ቀን ፈጠራቸው ይላል

ታድያ የብርሀን ምንጮች ሳይፈጠሩ ብርሀንና ጨለማ ከየት መጡ ?

ጠለቅ ብለን ከገባን ብዙ የሚጠየቅ ነገር አለ

አሁንም እስቲ ረጋ ብለህ እያሰብክበት አንብበው :: አምላክ መጀመሪያ መፍጠር ሲጀምር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ ይላል ይህ ማለት የሰማይ አካላትን (ጸሀይን ጨምሮ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ከዋክብትንና ጨረቃዎችን ) እና ምድርን ፈጠረ ማለት ነው በዚህ ውስጥ ምን የስራ ክፍፍል የለም ::

ከዚያ ቡሀላ ቁጥር 14 ላይ
እግዚአብሄር አለ ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሀናትን በሰማይ ይሁኑ ለምልክቶች ለዘመኖች ለእለታት ለአመታት ይሁኑ በምድርም ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር ብርሀናት ይሁኑ እንዲሁም ሆነ [b]እግዚአብሄርም ሁለት ታላላቅ ብርሀናት አደረገ ትልቁ ብርሀን በቀን ትንሹም ብርሀን በለሊት እንዲሰለጥኑ ... [/b]

ልብ በል እዚህ ላይ ሰማንና ምድርን ፈጠረ የተባለው ገና ከመጀመሪያው ነው አሁን ግን የሚያደርጉትን ተግባራት እየመደበላቸው ነው :: እንጂ እየፈጠረ አይደለም አስቀድሞ ተፈጥረዋል :: በደንብ ረጋ ብለህ በማስተዋል አንብበው ::

ይህም በቂ የሆነ ምክንያት አይደለም ::

ለመሆኑ ፍጥረትን በተመለከተ ቁርአን ምን ይላል ??

ማወቅ ስለማያስፈልገን አልተጻፈም ትል ይሆናል ::
Quote:
ቁርአን የአምላክ ቃል አይደለም የሚል ድምዳሜ አለህ እኔ ደግሞ እያንዳንድዋ ቃል የአላህ (ሱወ ) ቃል ነው የሚል እምነት አለኝ

አንተ እንዳታምን ያደረጉህ ምክንያቶች ስላሉ ልታቀርባቸው እና እኔ ለምን እንዳመንኩበት ልነግርህ እችላለው ይህ ማለት ከነገርኩህ በህዋላም ግድ ታምንበታለህ ማለት አይደለም ከዛ በህዋላም ላታምንበት ትችላለህ የሁሉም መብት ነው ነገር ግን ቢያንስ እኔ ለምን እንዳመንኩበት በመጠኑ ትረዳለህ ማለት ነው
የኔም ጥያቄ በተመሳሳዩ እኔ ያላመንኩበትን አንተ በምን መልኩ እንዳመንክበት ለመረዳት ብቻ ነው ሊያሳምነኝም ላያሳምነኝም ይችላል ነግር ግን ያመንክበትን ምክንያት ካንተ እረዳለው ከዛ ያለፈ ክርክር ውስጥ ለመግባት አይደለም

ከሰላምታ ጋርወልድያ እስቲ አንተ ቁርአን የአምላክ ቃል ነው ሊያሰኝ የሚችለውን አሳማኝ ማስረጃ አቅርብልኝና ልየው ::
ከዚያ ቡሀላ እኔ ለምን የአምላክ ቃል ሊሆን እንደማይችል ልነግር እችላለሁ ::

ከሰላምታ ጋር

ሰላም ሁን ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወልድያ

ኮትኳች

Joined: 24 May 2010
Posts: 492

PostPosted: Mon Apr 30, 2012 7:48 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም አሉ ኡላ

አጽኖት ያልሰጠሀቸው ጥያቄዎቼ አሉ

-አንድ ክርስትያን የመጽሀፍ ቅዱስን ህግጋት መከተል አለበት ወይንስ ባይከተልም ችግር የለም ?

-ስለ 9/11 ስናወራ በዛን የፈረሱት ፎቆች 3 ናቸው አንደኛው በዜና እንዲናፈስ ስላልተደረገ እና ስለታፈነ ሰው ልብ አይለውም ይህ ህንጻ WTC 7 ይባላል ህንጻው ሲፈርስ እዚህ ማየት ትችላለህ ይህን ህንጻ ምን አፈረሰው ?

-አንድ ጽሁፍ ጸሀፊው እንክዋን ሳይታወቅ እንዴት ከአምላክ ጋር እናቆራኘዋለን ?

ሌላው ይህ ነው
Quote:

ያንተን ለመመለስ ያህል
በጣም የሚገርም አረዳድ ነው የተረዳኸው ::
እስከዛሬ በዚሀ አይነት አረዳድ ተረድቶ የተነሳ ጥያቄ ትዝ አይለኝም :: ከመመለሴ በፊት ግን ይህ አመለካከት የራስህ ግንዛቤ ነው ወይስ የጠቅላላው ሙስሊም በሙሉ ? ማለትም የኢስላም ሀይማኖት አመለካከት ?? ይህችን መልስልኝ ለማወቅ ያህል ነው ::

ለማንኛውም በቁዋንቁዋህ ሰማይ የምትለው ምንን ነው ?
ወፎች በሰማይ ላይ ይበራሉ
አውሮፕላን በሰማይ ላይ ይበራል
የሚሉትን አነጋገሮች ጥያቄ አስነስተህባቸው ታውቃለ ??
ከአይናችን እይታ ውጪ አልፈው የማያውቁትን ነገሮች እንዴት በሰማይ ይበራሉ ይባላል ? ብለህ የመጠየቅ ያህል ነው ጥያቄህ ::

ስለ ሰማይ ጠቀስ ፎቆችስ (skyscraper) ጠይቀህ ታውቃለህ ? ሰማይ ጠቀስ ህንጻ ለመባል ስንት ፎቆች ያስፈልጉታል ? ስንት ሜትር እርዝመት ሊኖረው ይገባል ? ለዚያውስ የቱ ረጅም ህንጻ ነው ሰማይ የደረሰው ብለህ የጠየከኝ ያህል ነው የተሰማኝ ::
ከምድር ከፍ ያለውን በአካባቢያችን ካሉት ነገሮች ሁሉ ከፍ ያለውን ሁሉ ሰማይ የነካ ወይም ሰማይ የደረስ የሚል የቁዋንቁዋ አጠቃቀም እንጂ አንተ እንዳሰብከው የተለየ ትርጉም የለውም ::

በመጀመሪያ ደረጃ በዘፍጥረት ላይ እስከ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንስራ የሚለውን ቃል የተናገሩት ሰዎቹ ናቸው :: ግንብ ተሰርቶ ዛሬ ድረስ ቢቆይ ኖሮ ሰማይ ጠቀስ ቀርቶ ረጅም ህንጻ ላይሰኝ ይችላል ነገር ግን በወቅቱ ካለው የህንጻ አሰራር አንጻር እና ከተሰሩት ህንጻዎች አንጻር ሲታይ ምናልባት እነሱ ሊሰሩት ያሰቡት ግንብ ረጂም ስለሚሆን ሰማይ ጠቀስ እንደሚባለው አባባል ለነሱ ሰማይ የደረሰ ግንብ ነው :::: ርዝመቱን ለማመልከት እንጂ ጠፈርን አቁዋርጦ ሰማይ ቤት ለመግባት እንዳልሆነ ምንም ጥርጥር የለውም ::

ድሮ ልጆች ሆነን ኩዋስ ሲጠለዝ ሰማይ አደረሳት እንል ነበር አባባላችን ስህተት ነበር ማለት ነው

እናም ይህ አተረጉዋጎም ፈጽሞ ምክንያታዊ አይደለም ::የመጽሀፍ ቅዱሱ አገላለጽ ካንተ ጋር ፈጽሞ ይለያል ወፎች እና አውሮፕላኖች በሰማይ ላይ ይበራሉ ይባላል እንጂ ሰማይ ድረስ ይበራሉ ተብሎ አይታወቅም ክዋስንም ወደሰማይ ጠለዝኩት እንጂ ሰማይ ድረስ ጠለዝኩት አይባልም ጫፉ ሰማይ ላይ ደረሰ የተባለ ፎቅም አልሰማንም ሰማይ ጠቀስ ማለትም ወደሰማይ የተቅጣጩ ማለት እንጂ ሰማይ የደረሰ ማለት አይደለም እርግጥ ባለ ሶስት ወይንም ሁለት ፎቁ በድሉ ህንጻም በጊዘው ሰማይ ጠቀስ ፎቅ ይባል ነበር ሰዎችም ቀና ብለው ሲያዩት እንዳያዞራቸው ጋደም ብለው ነበር የሚያዩት ? Laughing ሆኖም እነዛ ሰዎችም ሰማይ ላይ ደረሰ አላሉም መጻህፍ ቅዱስ የሚለው ግን ጫፉ ወደሰማይ የሚደርስ ነው ስለዚህ ይህ አገላለጽ ጫፉ ፊዚካሊ ሰማይን የሚነካ ማለት ነው

ባንተ አገእላለጽ እንሂድና እግዛብህእር የሰውን ቋንቋ ያለያየበት ምክንያት ትንሽ ከምድር ከፍ ያለ ግምብ እንዳይሰራ ነው ብለን ብንወስድ ደግሞ ይህው ቻይናውያን ረጅሙን የቻይና ግንብ ሰርተዋል ግብጻውያን ፒራሚዶችን ሰርተዋል አክሱማውያን ረጃጅም ሀውልቶች ሰርተዋል ታድያ አምላክ የሰዎችን ቋንቋ በማዛባት ያሰበውን ግብ መትትዋል ትላለህ ? ሰዎች ተባብረው ግንብን መገንባታቸውን አምላክ እንዴት እንደ አደጋ ተመለከተው ? ኢስራኤል ኢራን ኑዩክለር ቦምብ መስራትዋን እንደስጋት ብትመለከተው አይገርምም አምላክ ግን የሰዎችን ስብስብና ግንባታ እንደአደጋ ቆጥሮ አለመግባባት እንዲፈጠር ያደረገው ይደርሱብኛል ብሎ ሰግቶ ነው ? ካልሆነ የአምላክ ስጋት ምን ነበር ? ማይንድ አምላክ ይሰጋል ብየ እኔ አላምንም የመጽሀፍ ቅዱስ አገላለጽ ግን አምላክ እንደሰጋ ስለሚያሳይ ነው ::

ወፍ በሰማይ ላይ ይበራል ብለን ከምናልፈው ግልጽ አድርገነው እንለፍና ወደለላው እንሂድ እስኪ

ቁርአን 49: 13 እንዲህ ይላል

እናንተ ሰዎች ሆይ እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናቹህ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናቹህ አላህ ዘንድ በላጫቹህ በጣም አላህን ፈሪያቹህ ነው አላህ ግልጽን አዋቂ ውስጥንም አዋቂ ነው ይላል

ለለሎቹ ጥያቄዎች እመለሳለው

ከሰላምታ ጋር
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
anbissa

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 27 Jan 2009
Posts: 63
Location: australia

PostPosted: Thu May 03, 2012 3:29 pm    Post subject: KEEP UNITY Reply with quote

I LOVED BOTH COMMENT OR VIEWS OF RELIGIONS,I DON'T BELIVE ABOUT RIGHT OR WRONG AS FAITH IS PERSONAL RELATIONSHIP. IT IS ALSO VERY HARD TO UNDERSTAND FOR THOSE HAVE DEPEND ONLY ON PHSICAL WORD OR THE LAW.
AS PROPHETS WROTE THROUGH MANIFESTION TO DAY THE BELEIVERS WHEN THEY READ AND MEDITATE ON THE WORD WE SEE OR FEEL THE THE FREE MOVENT OF THE SPRITOF GOD AROUND US .AS I SAID IT IS FREE CHOICE AND IT IS PERSONAL.
YOU SHOULD USE THIS ENERGY TO BRING FOR UNITING BOTH SIDES OF RELIGION TO FIGHT FOR EQUALITY AND BETTER WORK TO GETHER OUR COMMON ENEMY. NO BODY CHANGES NOBODY BUT WE CAN CHANGE OUR COUNTRY FROM POVERTY TO PROSPERITY IF WE WORK TOGETHR
GOD BLESS YOU ALL
_________________
n/a
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Yahoo Messenger Report post
አሉ -ኡላ

ኮትኳች

Joined: 21 Apr 2004
Posts: 194
Location: ethiopia

PostPosted: Sat May 05, 2012 11:00 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ወልድያወልድያ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም አሉ ኡላ

አጽኖት ያልሰጠሀቸው ጥያቄዎቼ አሉ

-አንድ ክርስትያን የመጽሀፍ ቅዱስን ህግጋት መከተል አለበት ወይንስ ባይከተልም ችግር የለም ?

አንድ ክርስቲያን የመጽሀፍ ቅዱስ ክርስቲያናዊ ህጎችንና መመሪያዎችን መከተሉና መጠበቁ የግድ ነው ::Quote:
-ስለ 9/11 ስናወራ በዛን የፈረሱት ፎቆች 3 ናቸው አንደኛው በዜና እንዲናፈስ ስላልተደረገ እና ስለታፈነ ሰው ልብ አይለውም ይህ ህንጻ WTC 7 ይባላል ህንጻው ሲፈርስ እዚህ ማየት ትችላለህ ይህን ህንጻ ምን አፈረሰው ?

የፈረሰበት ምክንያት ምን ይሁን ምን ያንን ለመርማሪዎች መተው ነው :: መቼም አንተ እንዳወከው ሁሉ ሌላውም የአሜሪካ ህዝብ በተለይም ለህግና ለእውነት እንዲሁም ለሰብአዊ መብት ተቆርቁዋሪ የሆነ ሁሉ ሳያውቀው ይቀራል ማለት ሊታመን የማይቻል ነገር ነው እናም ይህ ጉዳይ ባጋጣሚ እንደምሳሌ ተነሳ እንጂ የመፍረሱ ጉዳይ ዋነኛው የመነጋገሪያ ርእሳችን ሆኖ አይደለም ::
እናም ለህንጻዎቹ መፍረስና ለሰዎቹ ማለቅ ምክንያት የሆኑትን አውሮፕላኖች የጠለፉትና ከህንጻው ጋር ያጋጩት ሙስሊሞች አይደሉም ካልክም ምንም ማለት አልችልም መብትህ ነው

[quote]-አንድ ጽሁፍ ጸሀፊው እንክዋን ሳይታወቅ እንዴት ከአምላክ ጋር እናቆራኘዋለን ?

Quote:
ሌላው ይህ ነው
Quote:

ያንተን ለመመለስ ያህል
በጣም የሚገርም አረዳድ ነው የተረዳኸው ::
እስከዛሬ በዚሀ አይነት አረዳድ ተረድቶ የተነሳ ጥያቄ ትዝ አይለኝም :: ከመመለሴ በፊት ግን ይህ አመለካከት የራስህ ግንዛቤ ነው ወይስ የጠቅላላው ሙስሊም በሙሉ ? ማለትም የኢስላም ሀይማኖት አመለካከት ?? ይህችን መልስልኝ ለማወቅ ያህል ነው ::

ለማንኛውም በቁዋንቁዋህ ሰማይ የምትለው ምንን ነው ?
ወፎች በሰማይ ላይ ይበራሉ
አውሮፕላን በሰማይ ላይ ይበራል
የሚሉትን አነጋገሮች ጥያቄ አስነስተህባቸው ታውቃለ ??
ከአይናችን እይታ ውጪ አልፈው የማያውቁትን ነገሮች እንዴት በሰማይ ይበራሉ ይባላል ? ብለህ የመጠየቅ ያህል ነው ጥያቄህ ::

ስለ ሰማይ ጠቀስ ፎቆችስ (skyscraper) ጠይቀህ ታውቃለህ ? ሰማይ ጠቀስ ህንጻ ለመባል ስንት ፎቆች ያስፈልጉታል ? ስንት ሜትር እርዝመት ሊኖረው ይገባል ? ለዚያውስ የቱ ረጅም ህንጻ ነው ሰማይ የደረሰው ብለህ የጠየከኝ ያህል ነው የተሰማኝ ::
ከምድር ከፍ ያለውን በአካባቢያችን ካሉት ነገሮች ሁሉ ከፍ ያለውን ሁሉ ሰማይ የነካ ወይም ሰማይ የደረስ የሚል የቁዋንቁዋ አጠቃቀም እንጂ አንተ እንዳሰብከው የተለየ ትርጉም የለውም ::

በመጀመሪያ ደረጃ በዘፍጥረት ላይ እስከ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንስራ የሚለውን ቃል የተናገሩት ሰዎቹ ናቸው :: ግንብ ተሰርቶ ዛሬ ድረስ ቢቆይ ኖሮ ሰማይ ጠቀስ ቀርቶ ረጅም ህንጻ ላይሰኝ ይችላል ነገር ግን በወቅቱ ካለው የህንጻ አሰራር አንጻር እና ከተሰሩት ህንጻዎች አንጻር ሲታይ ምናልባት እነሱ ሊሰሩት ያሰቡት ግንብ ረጂም ስለሚሆን ሰማይ ጠቀስ እንደሚባለው አባባል ለነሱ ሰማይ የደረሰ ግንብ ነው :::: ርዝመቱን ለማመልከት እንጂ ጠፈርን አቁዋርጦ ሰማይ ቤት ለመግባት እንዳልሆነ ምንም ጥርጥር የለውም ::

ድሮ ልጆች ሆነን ኩዋስ ሲጠለዝ ሰማይ አደረሳት እንል ነበር አባባላችን ስህተት ነበር ማለት ነው

እናም ይህ አተረጉዋጎም ፈጽሞ ምክንያታዊ አይደለም ::የመጽሀፍ ቅዱሱ አገላለጽ ካንተ ጋር ፈጽሞ ይለያል ወፎች እና አውሮፕላኖች በሰማይ ላይ ይበራሉ ይባላል እንጂ ሰማይ ድረስ ይበራሉ ተብሎ አይታወቅም ክዋስንም ወደሰማይ ጠለዝኩት እንጂ ሰማይ ድረስ ጠለዝኩት አይባልም ጫፉ ሰማይ ላይ ደረሰ የተባለ ፎቅም አልሰማንም ሰማይ ጠቀስ ማለትም ወደሰማይ የተቅጣጩ ማለት እንጂ ሰማይ የደረሰ ማለት አይደለም እርግጥ ባለ ሶስት ወይንም ሁለት ፎቁ በድሉ ህንጻም በጊዘው ሰማይ ጠቀስ ፎቅ ይባል ነበር ሰዎችም ቀና ብለው ሲያዩት እንዳያዞራቸው ጋደም ብለው ነበር የሚያዩት ? Laughing ሆኖም እነዛ ሰዎችም ሰማይ ላይ ደረሰ አላሉም መጻህፍ ቅዱስ የሚለው ግን ጫፉ ወደሰማይ የሚደርስ ነው ስለዚህ ይህ አገላለጽ ጫፉ ፊዚካሊ ሰማይን የሚነካ ማለት ነው

ባንተ አገእላለጽ እንሂድና እግዛብህእር የሰውን ቋንቋ ያለያየበት ምክንያት ትንሽ ከምድር ከፍ ያለ ግምብ እንዳይሰራ ነው ብለን ብንወስድ ደግሞ ይህው ቻይናውያን ረጅሙን የቻይና ግንብ ሰርተዋል ግብጻውያን ፒራሚዶችን ሰርተዋል አክሱማውያን ረጃጅም ሀውልቶች ሰርተዋል ታድያ አምላክ የሰዎችን ቋንቋ በማዛባት ያሰበውን ግብ መትትዋል ትላለህ ? ሰዎች ተባብረው ግንብን መገንባታቸውን አምላክ እንዴት እንደ አደጋ ተመለከተው ? ኢስራኤል ኢራን ኑዩክለር ቦምብ መስራትዋን እንደስጋት ብትመለከተው አይገርምም አምላክ ግን የሰዎችን ስብስብና ግንባታ እንደአደጋ ቆጥሮ አለመግባባት እንዲፈጠር ያደረገው ይደርሱብኛል ብሎ ሰግቶ ነው ? ካልሆነ የአምላክ ስጋት ምን ነበር ? ማይንድ አምላክ ይሰጋል ብየ እኔ አላምንም የመጽሀፍ ቅዱስ አገላለጽ ግን አምላክ እንደሰጋ ስለሚያሳይ ነው ::

ወፍ በሰማይ ላይ ይበራል ብለን ከምናልፈው ግልጽ አድርገነው እንለፍና ወደለላው እንሂድ እስኪ

ወልድያ
ኢስላም መጽሀፍ ቅዱስ ተበርዟል ብሎ እንዲያምን ያደረገው ይህና ይህን የመሳሰለው አባባል ነው ማለታችሁ 'ጣም የሚገርምና ምን ያህል ከእውነታው ያራቃችሁ እንደሆነ ያሳያል :: ይህ ያለምክንያት አይደለም ::
ከቁርአን አጻጻፍ የተነሳ እንደሆነ አምናለሁ :: ይህንን ያልኩበትንም ምክንያት ከነማስረጃው እመለስበታለሁ

ለማንኛውም :-
ጨረቃ ላይ ለመረማመድ ጨረቃ ላይ መድረስ ያስፈልጋል
ማርስ ላይ የተሽከረከረችው ሮቦት መጀመሪያ ማርስ ላይ መድረስ ነበረባት
ወፏ ሰማይ ላይ ለመብረር መጀመሪያ ሰማይ ላይ መድረስ ያስፈልጋታል
አውሮፕላኑም በሰማይ ላይ ለመብረር መጀመሪያ ሰማይ ላይ መድረስ ያስፈልገዋል

ችግሩ አንተ ሰማይ የምትለው ምን እንደሆነ ያለማወቅህ ይመስለኛል ::
ሳይንስ እንደሚለው ዩኒቨርስ መጨረሻ የለውም :: እናም ሰማይ ያለው የት ነው ??

ሰማይ የሚጀምረው ከየት ነው ? ከከዋክብት ወይም ከጋላክሲዎች ወዲያ ? ከጸሀይ ከጨረቃ ወዲያ ?

ወይስ ከዩኒቨርስ ውጪ ? ሌላ ቦታ ?

ጨረቃ ሰማይ ላይ ነች ወይስ አይደለችም ?
ጸሀይ ሰማይ ላይ ነች ወይስ አይደለችም ?
ከዋክብትስ ሰማይ ላይ ናቸው ወይስ አይደሉም ?

ለነዚህ የምትመልስልኝ ምንድነው ?

ውሀ ማለትም ዝናብ ከየት ነው የሚመጣው ??

እስቲ ቁርአን ሰማይ የሚለውን ቃል የተጠቀመበትን እንይ :

27: 60
ወይም ሰማያትንና ምድርን የፈጠረና ከሰማይም ለናንተ ውሀን ያወረደው

16: 65
አላህም ከሰማይ ውሀን አወረደ

39: 21
አላህ ከሰማይ ውሀን እንዳወረደና በምድር ውስጥ ምንጮች አድርጎ እንዳስገባ

ከየት ሰማይ ነው ይህ ውሀ ወይም ዝናብ የሚዘንበው ?
ባይናችን ከምናየው ከደመና ውስጥ ነው ወይስ ጨረቃን ጸሀይን ከዋክብትን ሁሉ ህዋን ሁሉ አልፎ ከሚገኘው ሰማይ ?

በደንብ በግልጽ የተቀመጠውን ላሳይህ

45: 41
አላህ በሰማያትና በምድር ያለ ሁሉ በራሪዎችም ክንፎቻቸውን (በአየር ላይ ) ያንሳፈፉ ሆነው ለእርሱ የሚያጠሩ ...

በአየር ላይ ሆነው - የሚለው ቃል በኦሪጅናሉ ውስጥ የለም የኢስላም ምሁራን ናቸው ትርጉሙን ለማስረዳት የጨመሩበት ::

ይህንን ላለማመን ስትል የቁርአኑን አባባል ለማብራራት እንደምትሞክር አምናለሁ :: ነገር ግን ግልጽ ስለሆነ ምንም ማብራራት አያሻህም የሚለው ይገባኛል ::
ውሀውንም ከደመና ማለቱ እንደሆነ በሰማይ ያሉ በራሪዎች የሚለውም ባየር ላይ ያሉ መሆናቸውን ስለተረዳሁ የቁርአኑን አባባል ምንም ማብራራት አያስፈልግህም ::

የመጽሀፍ ቅዱሱን አባባል ለማስረዳት ያህል ሰዎቹ ገና በቅርቡ በመላው አለም ላይ ከደረሰው የጥፋት ውሀ ከተረፉት ሰዎች በመብዛት ላይ ያሉ ሰዎች ናቸው
ሊሰሩበት የተነሱበትን አላማ እይ
በምድር ላይ ሳይበታተኑ ስማቸውን ለማስጠራት ዝናቸውን ለማቆየት ለራሳቸው ክብር ሲሉ ለስማቸው መጠሪያ ሲሉ እንደሆነ ልብ በል ::
አንተ እንዳልከው ወደ ሰማይ ደርሰው አምላክን ስልጣን ለመጋራት አይደለም :: ስጋት የሚለውን ቃል አንተ ነህ የጨመርክበት ::
ይህ ነበር እንጂ አላማቸው አንተ ያሰብከው ሰማይ ላይ ለመድረስ አልነበረም
ጭቃ ጠፍጥፈው ጠፈርን አቁዋርጠው መዝለቅ እንኩዋንስ ያሁኑንዘመን ሰው ቀርቶ ያን ጊዜ የነበሩትን ሰዎች አያሳምንም ::

የሰዎቹ ያንን ግንብ መስራት ቡሀላ ላይ ለሚወለዱትና ለሚበዙት ሰዎች ላይ ተጽእኖ ይኖረዋል
ግንብ ቢሰራ ኖሮ ምናልባት ልክ ባሁኑ ጊዜ ባንዳንድ ሀይማኖትና አገሮች እንደሚደረገው ማለትን እገሌ የተከለው ድንጋይ እገሌ የሰራው ግንብ እየተባለ ሰዎች የአምልኮ ማእከል ያደርጉትና ገና ከጅምሩ ላይ የነበረውን የሰው ዘር በሀሰት አምልኮ ይበክሉታል በሚል ምክንያት ሊሆን ይችላል አምላክ ያን ግንብ እንዲቆም ያደረገው :: ነውም :: ቦታ ባብኤል እንደተባለ አስብ ቡሀላም ባቢሎን የነበረችበት ቦታ ነው :: ባቢሎን ለሀሰተኛ አምልኮ ማእከል የነበረችና በወቅቱ የነበረውን አለም በሀት ትምህርት የበከለች እንደነበረች መጽሀፍ ቅዱስም ታሪክም ያስረዳሉ ::
ስለዚህ የወደፊቱን ሁኔታ አይቶ እንጂ አንተ እንዳሰብከው አምላክ የሚሰጋበት ነገር ፈጽሞ የለውም :: ሁሉን ማድረግ የሚችል አምላክ ነውና ::

Quote:
ቁርአን 49: 13 እንዲህ ይላል

እናንተ ሰዎች ሆይ እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናቹህ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናቹህ አላህ ዘንድ በላጫቹህ በጣም አላህን ፈሪያቹህ ነው አላህ ግልጽን አዋቂ ውስጥንም አዋቂ ነው ይላል

ለለሎቹ ጥያቄዎች እመለሳለው

ከሰላምታ ጋር

ይህን የቁርአን ጥቅስ ከምን ጋር አገናኝተህ እንደጠቀስከው አላውቅም የማይገናኝ ሀሳብ ቢሆንም በዚህ ጥቅስ ዙሪያ የምለውም አለኝ

አንተ ከላይ ከጠቀስከው ጥቅስ ሌላ ስለሰው ፍጥረት ቁርአን የሚለውን እይ

3: 59
የኢሳ ምሳሌ እንደ አዳም ብጤ ነው ከአፈር ፈጠረው

80: 18
ከፍትወት ጠብታ ፈጠርው

መጀመሪያ የፍትወቱ ጠብታ ከየት መጣ ? Laughing

55: 14
ሰውን እንደ ሸክላ ከሚቅጨለጨል ደረቅ ጭቃ ፈጠረው

ደረቅና ጭቃ ተቃራኒ ናቸው

15: 27
ሰውን ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከሚገማ ጥቁር ጭቃ በርግጥ ፈጠርነው

በጣም የሚገርም አባባል ነው

እውነተኛው አምላክ ቅዱስና ንጹህ ነው :: ግማት በርሱ አካባቢ ሊኖር አይችልም
ግማት የመጥፎ ነገር ውጤት እንጂ ጥሩ ነገር አይደለም ::

39: 6 ላይ የተሰጠ የግርጌ ማስታወሻ

ከፍትወት ጠብታ ከዚያም ከረጋ ደም ከዚያም ከቁራጭ ስጋ ለጥቆ ሙሉ ሰው ያደርጋችሁዋል

ይህ አባባል ያን ጊዜ የነበሩትን ሰዎች ያሳምን ይሆናል ::
በየትኛው የሳይንስ ትምህርት ነው የስንተኛ ክፍል የባዮሎጂ ትምህርት ነው ሰው ከረጋ ደም የሚፈጠረው ?
የትኛው ሳይንስ ነው ከቁራጭ ስጋ ሰው እንደተፈጠረ የሚያሳየው ??

የፍትወት ጠብታስ ጠብ ስላለ ሰውይሆናል ?? ፈጽሞ ከተፈጥሮም ከሳይንስም ጋር የሚጋጭ አባባል ነው :

ባጠቃላይ ግን ሰውን አንዴ ከፍትወት ጠብታ አንዴ ካፈር አንዴ ከገማ ጭቃ ተፈጠረ እያለ ያልሆነ ትምህርትን የያዘ መሆኑን ማየት ይቻላል ::

ብዙ ማለት ይቻልል እንዲያው ስለጀመርከው ነው ::
ምን ያህል ከሳይንሱ የወጣ መሆኑን ላሳይህ ነው ::

አመሰግናለሁ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወልድያ

ኮትኳች

Joined: 24 May 2010
Posts: 492

PostPosted: Mon May 07, 2012 9:16 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም አሉ ኡላ

ያነሳሀቸው ነገሮች ላይ አንዳንድ ነገር ልበል
Quote:

አንድ ክርስቲያን የመጽሀፍ ቅዱስ ክርስቲያናዊ ህጎችንና መመሪያዎችን መከተሉና መጠበቁ የግድ ነው ::

መልካም ነገር ነው ስለዚህ አንድ መልካም ክርስትያን አሳማ መብላት የለበትም መገረዝ አለበት ተቃራኒ ጾታን በምኞታዊ አይን ማየት የለበትም ..እንዲሁም አንዲት መልካም ከርስትያን አካላትዋን መሸፈን አለባት ... ማለት ነውን ?

ሌላው እንዲሁ ለራሴ ጠቅላላ ግንዛቤ ፈልጌው ነው በክርስትና አራጣ (የወለድ ብድር ) እንዴት ይታያል
Quote:

የፈረሰበት ምክንያት ምን ይሁን ምን ያንን ለመርማሪዎች መተው ነው :: መቼም አንተ እንዳወከው ሁሉ ሌላውም የአሜሪካ ህዝብ በተለይም ለህግና ለእውነት እንዲሁም ለሰብአዊ መብት ተቆርቁዋሪ የሆነ ሁሉ ሳያውቀው ይቀራል ማለት ሊታመን የማይቻል ነገር ነው እናም ይህ ጉዳይ ባጋጣሚ እንደምሳሌ ተነሳ እንጂ የመፍረሱ ጉዳይ ዋነኛው የመነጋገሪያ ርእሳችን ሆኖ አይደለም ::

አስፈላጊ አይደለም ካልክ መልካም ነው ታድያ ሙስሊሞችን ከድርጊቱ ጋር ማቆራኘትህን ተወው ማን እንደፈጸመው ግዜ በራሱ የሚያወጣው ነገር ስለሆነ CNN አና BBC ዘገባ ላይ ብቻ ተመስርተህ ጃጅመንታል መሆኑ ይቁም !
Quote:

አንድ ጽሁፍ ጸሀፊው እንክዋን ሳይታወቅ እንዴት ከአምላክ ጋር እናቆራኘዋለን ?

ይህ ጥያቄ ሳይመለስ ታልፍዋል
Quote:

የሰዎቹ ያንን ግንብ መስራት ቡሀላ ላይ ለሚወለዱትና ለሚበዙት ሰዎች ላይ ተጽእኖ ይኖረዋል
ግንብ ቢሰራ ኖሮ ምናልባት ልክ ባሁኑ ጊዜ ባንዳንድ ሀይማኖትና አገሮች እንደሚደረገው ማለትን እገሌ የተከለው ድንጋይ እገሌ የሰራው ግንብ እየተባለ ሰዎች የአምልኮ ማእከል ያደርጉትና ገና ከጅምሩ ላይ የነበረውን የሰው ዘር በሀሰት አምልኮ ይበክሉታል በሚል ምክንያት ሊሆን ይችላል አምላክ ያን ግንብ እንዲቆም ያደረገው :: ነውም :: ቦታ ባብኤል እንደተባለ አስብ ቡሀላም ባቢሎን የነበረችበት ቦታ ነው :: ባቢሎን ለሀሰተኛ አምልኮ ማእከል የነበረችና በወቅቱ የነበረውን አለም በሀት ትምህርት የበከለች እንደነበረች መጽሀፍ ቅዱስም ታሪክም ያስረዳሉ ::
ስለዚህ የወደፊቱን ሁኔታ አይቶ እንጂ አንተ እንዳሰብከው አምላክ የሚሰጋበት ነገር ፈጽሞ የለውም :: ሁሉን ማድረግ የሚችል አምላክ ነውና ::

እንግዲህ ከገለጻህ እንደተረዳሁት ሰማይ የተባለው ከፍ ያለ ቦታ ወፎች በሰማይ ይበራሉ ዝናብ ከሰማይ ይወርዳል በሚባልበት ስመት እንጂ ፊዚካላዊ ሰማይ (የዩኒቨርስ ጣራ ላይ ) የሚደርስ አይደለም ጥሩ እንደምላሽ ተቀብዬው ግንዛቤዬን አስተካክያለው

ታድያ ይህ መገንባቱ ምን ችግር አለው ላልኩህ ሰዎች የአምልኮ ተግባራት መፈጸምያ እንዳያደርጉት ነው ነው ምላሽህ እንደዛ የሚል ድምዳሜ ላይ ሊያደርስ የሚችል ቀጥተኛ አገላለጽ ግን አላየሁበትም በመጽሀፍ ቅዱሱ ላይ :: በመጽሀፍ ቅዱሱ መሰረት ሰዎቹ ያሰቡትን ግንባታ እንዳያሳኩ አንዱ ያንዱን ነገር እንዳይሰማው እናድርግ የሚል የሚል የአምላክ ውሳነ እንጂ ቢያደርጉ ምን ችግር ያስከትላል የሚለውን ወይንም ግንባታውን አምላክ ያልፈለገበትን መሰረታዊ ምክንያት አንተ ባልከው መንገድ የተገለጸ ነገር የለም ሆኖ የመጽሀፍ ቅዱስ ምሁራን አስተያየት ሊሆን ስለሚችል በዛው ተቀብዬው አልፋለው

Quote:
Quote:
Quote:
ቁርአን 49: 13 እንዲህ ይላል

እናንተ ሰዎች ሆይ እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናቹህ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናቹህ አላህ ዘንድ በላጫቹህ በጣም አላህን ፈሪያቹህ ነው አላህ ግልጽን አዋቂ ውስጥንም አዋቂ ነው ይላልለለሎቹ ጥያቄዎች እመለሳለው

ከሰላምታ ጋር

ይህን የቁርአን ጥቅስ ከምን ጋር አገናኝተህ እንደጠቀስከው አላውቅም የማይገናኝ ሀሳብ ቢሆንም በዚህ ጥቅስ ዙሪያ የምለውም አለኝ

እኔ ይህን አንቀጽ ያመጣሁትበቁርአን የሰዎች በጎሳና በነገድ መከፈል የተለየ ምክንያት እንዳለው ለማሳየት ብቻ ነው

ከዚህ ጋር ተያይዞ ስላነሳህልኝ እና የቁርአን ግድፈት ስለመሰለህ የሰው አፈጥጣጠር ተመልሸ እገልጻለው

Arrow
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወልድያ

ኮትኳች

Joined: 24 May 2010
Posts: 492

PostPosted: Wed May 09, 2012 8:49 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም አሉ ኡላ

ስለ አፈጣጠር ትንሽ ልበልህ

ቁርአን ላይ የተጠቀሰው የመጀመርያው ኦርጅናል አፈጣጠር (የአዳም አፈጣጠርና ) ሁለተኛው የመራባት አፈጣጠር (የአዳም ዘሮች አፈጣጠር ) ነው ስለዚህ ሰውን ከአፈር ከጭቃ ከውሀ ከሸክላ ፈጠርን ሲል የመጀመርያውን ኦርጅናል አፈጣጠር ሲሆን ሰውን ከፍትወት ጠብታ ከርጋ ደም ወዘተ ተብሎ የተገለጸው ሁለተኛው የመራባት አፈጣጠር ነው ሁለቱን ነጣጥዬ ላሳይህ

የመጀመርያ አፈጣጠር

ቁርአን በተለያየ ቦታ ከአፈር ከውሀ ከጭቃ ከሚቅጨለጨል ሸክላ ፈጠርነው ይላል

ይህንን ብዙ ግዜ እንደ ግጭት ያነሱታል

አንድ ምሳሌ ልስጥህ ኬክ ለመስራት ዱቄት ስኳር እንቁላል ወተት ተጠቀምክ
ይህንን ኬክ የተሰራው በዱቄት ነው ብትል ስህተት አለው ?
ይህ ኬክ በእንቁላል ነው የተሰራው ብትልስ ?
ይህ ከክ በወተት ተሰራ ልትልስ አትችልም ?
በስኳር የተሰራ ከክ ነው ሊባልስ አይችልም ?

ቁራን 30:20 ላይ ሰውን ከአፈር ሰራነው ይላል

የሰው ልጅ አካል ውስጥ የሚገኙ 16 ሳብስታንሶች ኦክሲጅንና ማንጋነዝን ጨምሮ በላይኛው ምድር አፈር ውስጥ የሚገኙ መሆናቸው እንዲሁም አፈር ለሰው ልጅ ህይወት ያለውን ወሳኝ ሚና ስትረዳ ይህንን መቀበል አያዳግትም ለላ መረጃ ለምሳለ ፎቅን ስናፈርስ የምንከተለው ሂደት የግንባታውን ተቃራኒ ነው ሰውም ከምተ በህዋላ እንደት እንደሚደርቅ እንደሚበሰብስ በመጨረሻም ወደአፈርነት እንደሚቀየር ስንመለከት ከምን እንደተገኘ ልንረዳ እንችላለን አፈር ለሰው ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ነገር ህልውና አስፈልጊ ነው

ቁራን 21:30 ህያውን ነገር ሁሉ ከውሀ ፈጠርን ይላል

ሳይንስ አሁን ስላደገ በሴላችን ውስጥ የሚገኘው ዋናው ሰብስታንስ ሳይቶፕላዝም (cytoplasm ) 80 % ውሀ እንደሆነ ታውቅዋል አብዛኛው ፍጥረትም 50-90% በውሀ የተሞላ እንደሆነና ማንኛውም ህይወት ያለው ነገር ውሀ እንደሚያስፈልገው አሁን ታውቅዋል ሳይንቲስቶች ሌላ ጠፈር ላይ ህይወት እንደሚገኝ ለመገመት መጀመርያ የሚፈልጉት ውሀ ሊገኝ መቻሉን ነው 1400 አመት በፊት በአንድ ውሀ እንደልብ በማይገኝበት ቦታ የነበረ ሰው ህይወት ሁሉ የተፈጠረው ከውሀ ነው መገመት ይችላል ?

አፈርና ውሀ የህይወት ምንጭ ናቸው !

አሁን ጥያቄህ የሚሆነው አንድ ግዜ ከአፈር ሌላ ግዜ ከውሀ ከጭቃ እንዲሁም ከሚቅጨለጨል ሸክላ ፈጠርነው ያለው ለምንድነው

አፈር ላይ ውሀ ስትጨምር ጭቃ ይሆናል ጭቃው እንዲደርቅ ከተውከው የሚቅጨለጨል ሸክላ አይነት ይሆናል ከላይ በኬኩ ምሳሌ እንደነገርኩህ የተለያዩ ኢንግሪድያንቶቹ እና ስቴጆቹ ነው የተጠቀሱት የሚጋጭ ነገር የለም ሰውን ከወርቅና ከብር ሰራን አላለም ሰው የተሰራበትን ኢንግሪድየንት ብቻ ነው የገለጸው

በመጨረሻ እስትንፋሱን ነፋበት ህያው ሰው ሆነ

እንዲህም ብለሀል
Quote:
15: 27
ሰውን ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከሚገማ ጥቁር ጭቃ በርግጥ ፈጠርነው

በጣም የሚገርም አባባል ነው

እውነተኛው አምላክ ቅዱስና ንጹህ ነው :: ግማት በርሱ አካባቢ ሊኖር አይችልም
ግማት የመጥፎ ነገር ውጤት እንጂ ጥሩ ነገር አይደለም ::

ምኑ ገረመህ ጭቃና አፈርስ አምላክ ፊት ሊቅረቡ ይገባ ነበር ሰውን ከአልማዝና ከሉል ለምን አልሰራውም ? ሰው ከሞተ እንዴት ወደጥንብነት እንደሚቀየር ታውቃለህ ለምን ወደግም የሚቀየር ነገር ፈጠረ ? ይህ የሰው ልጅ መኩራት እንደማይገባው ብቻ ያሳይሀል ከአፈር ከውሀ ከዛም ከሚገማ ጭቃ ተፈጠረ ሲሞት ፕሮሰሱ ሪቨርስ ያደርጋል ወደሚገማ ነገር ይቀየራል ውስጡ ያለው ውሀ አልቁ ይደርቃል ወደአፈርነት ይቀየራል

ይህ ኦርጅናል አፈጣጠር ነው ከዛ ቀጥሎ ግን ሰውን ከአፈርና ውሀ እየተደባለቀ አልተፈጠረም በመራባት ስለተፈጠረው አፈጣጠርም ቁርአን ይገልጻል ይህን የአዳም ዝርያ አፈጣጠር ከአዳም አፈጣጠር የተለየ ነው እና ልታደባልቀው አይገባም ስለዚህኛው ደግሞ እመለሳለው

Arrow
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወልድያ

ኮትኳች

Joined: 24 May 2010
Posts: 492

PostPosted: Sat May 12, 2012 9:37 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም አሉ ኡላ
ከግዘው አንጻር ቃለን ለመጠበቅ አጠር አድርጌ ልመልስ

የአዳም ዝርያን አፈጣጠር ሲገልጽ ቁርአን ከፍትወት ጠብታ ከተስፈንጣሪ ውሀ ከረጋ ደም ...ፈጠርን ይላል

የረጋ ደም የሚለውን ላብራራው የረጋ ደም የሚለው ቃል ዓለቅ ከሚለው የአረብኛ ቃል ነው ተርግዋሚዎች የተረጎሙት

ይህ ትርግዋሜ ብቻ ልክ አይደለም

ዐለቅ አንድ ነገር ላይ ጥብቅ ብሎ ተንጠልጣይ ነገር ማለትም ነው

እንዲሁም ዓለቅት ብለን የምንጠራው የውሀ ውስጥ ደምን መጣጭ ትል በአረብኛው ዐለቅ ተብሎ ይጠራል

The Arabic word used by the Qur'an which has generally been translated as "a clot of blood", is "`alaq" . The meaning of this word is given by "Qaamoos al-Muheet" as:

Blood in its normal state or blood which is extremely red or which has hardened or congealed, a piece thereof;

every thing that sticks; clay that sticks to hands; unchanging enmity or love; Zu `alaq is the name of a hill of Banu Asad, where they defeated Rabi`ah ibn Maalik;

An insect of water that sucks blood; that portion of a tree that is within the reach of animals.

የወንድ ዘር ከሴት እንቁላል ጋር ተገናንቶ ካኮረተ በህዋላ በፋሎፒያን ትዩብ አልፎ ማህጸን ውስጥ ከዋኘ በህዋላ የማህጸን ግድግዳ ላይ ተጣብቆ ይንጠለጠላል መልኩም በሚያስገርም መልኩ ከውሀ ውስት አለቅት ጋር ተመሳሳይ ነው ደም የመምጠጥ ባህሪውም ከዐለቅት ጋር ፍጹም ተመሳሳይ ነው ስለዚህ የቁራን አገላለጽ ተንጠልጣይና ተጣባቂ የሆነ ዐለቅት መሳይ ፍጥረት ተፈጠረ ማለት ነው ይህን ቃል ቁርአን መጠቀሙ ሳይንቲስቶችንም አስገርምዋል ምክንያቱም በባህሪም በመልክም ተመሳሳይ በመሆናቸው , ቁርአን በትርጉም ብቻ የሚገኝ ቢሆን ከረጋ ደም የሚለውን እንደስህተትር ከመውሰድ ለላ አማራጭ አልነበረም ቁርአን ግን በኦርጅናል መልኩም የሚገኝ ስለሆነ በትርግዋሜ ስህተት የመሰለውን ነገር ከኦርጅናል ጋር በማስተያየት ምላሽ ሊያገኝ ይችላል በተረፈ ሌላው የኢምቢርዮሎጂ እድገት ላይ ቁርአን ላይ ያለው ገለጻ ከሳይንስ ጋር ግጥም ነው ::

ከሰላምታ ጋር
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 20, 21, 22, 23, 24, 25  Next
Page 21 of 25

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia