WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
በቴዲ አፍሮ 'ጥቁር ሰው ' የተዛቡ የታሪክ እውነቶች
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ


 
View previous topic :: View next topic  
Author Message
ጥልቁ 1

ዋና ውሃ አጠጪ


Joined: 27 Jan 2004
Posts: 1560
Location: bhutan

PostPosted: Tue Apr 24, 2012 7:06 am    Post subject: Reply with quote

ክፍል አንድ

ቀጥሎ የምጽፈው ከልቤ የሚወጣ ቃል ሲሆን መቸም ሲፈጥረኝ የምጽፈው እራሴን ለማጽዳት እንጅ ሌላውን ለመስበክ ባለመሆኑ እንጅ ይህን ሃሳቤን “አማራ” ከሚለው ይልቅ “ኢትዮጵያዊያን ጸጉር ሰንጣቂዎችን” ሁሉ እንዲነካካ በሌላ መልኩ ጽፌ በየድህረ -ገጹ ብለቀው እመርጥ ነበር። ግን እኔ ይህን የምጽፈው ለዋርካ ታዳሚና ለህሊናየ ነው። እኔ እራሴ በአራቱም አቅጣጫ ዘሬ ቢቆጠር የአማርኛ ተናጋሪ ከሆኑ ቤተሰቦች የተወልድሁ ስልሆነ “አማራ” የሚለው መታወቂያ ፈጽሞ እንደማይወክለኝ ብቀበልም ለዚህ ጽሁፍ ግን እንደ ማሳጠሪያ ስለሚጠቅመኝ እና አንዳንዶች የአምርኛ ተናጋሪዎችም “አማራ” የሚለውን ቃል እንደ መለያ የማይቀበሉበት ምክንያት እያደር ሲገባኝ በእውነት ኢትዮጵያዊነታቸውን ስለሚያሳንስባቸው ሳይሆን ሌላውን ለመናቅ የሚጠቀሙበት በመሆኑ “አማራ” የሚለውን ቃል እየተጠቀምሁ እንደነ የተሞናሞነው ያለውንና ሌሎችንም እነካካበታለሁ። ዞር ብየ የዋርካ ቆይታየንም ስቃኘው ምንም እንኳ የውስጤን ህመም ሲያስትጋስልኝ ቢኖርም እነአብራራው በመሰላቸት እነወርቅሰው በሞት እነ እንድሪያስ በሆድ ከዋርካ መንፈሳቸው ሲሸሽ ‘እኔን ምን ጎለተኝ ? የሚለውና 8 አመታት የዋርካ ቆይታ በኋላ እራሴንም የመቆጠቢያ አቅጣጫየን በዚህ አምድ አስተካክላለሁ።

በዚህ አጋጣሚ የፈረንጁ ዴቪዲ ጽሁፍ ቀጥሎ ለማቀርበው መጣጥፍ ምንም አይነት ግፊት የለውም ::

ወደ ነጥቤ !

‘የአማርኛ ተናጋሪ አካባቢ ተወላጅ ጥሩ ታማኝ አገር ጠባቂ ወታደርነት እንጅ ጥሩ የአገር መሪ ሊወጣው አይችልም።’

የዚህ ሃሳብ መነሻየ ብዙ ጊዜ ስታዘበው የኖርሁት የኢትዮጵያ ፖለቲካ እና የአማራውን ስነ -ልቦና በማስተዋል ሲሆን ዛሬ ግን ይህን ጽሁፍ ለማስፈር የገፋፋኝ በቴዲ አፍሮ ላይ የሚወረወረው የቃላት ድንጋይ የመጽሃፍ ቅዱሱ ዲያቆኑ -እስጢፋኖስን ያለጥፋቱ ወግሮ የገደለው የሰይጣናዊ ተግባር ስላስታወሰኝ ነው። እጅግ የሚገርመው ታዲያ ይህ በቴዲ ላይ የሚወረወረው ድንጋይ የኢትዮጵያዊነት ጠላት ከሆነው ወያኔ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት ካባ ውስጥ ከሚዘናፈለው አማራ መሆኑ ነው። ለመሆኑ ግን እንደዚህ ያለው ጸረ -ኢትዮጵያዊነት አካሄድ በቴዲ ላይ የተጀመረ ነው ? አይደለም። በምሳሌ እንመልከት።

ምሳሌ 1
ከአንድ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ -ጥበብ ተመራቂ ወዳጀ ጋር ሰሞኑን ያወጋነውን ሰሞንኛ ወሬ እንመልከት። የታላቁ ክቡር ሎሬት አፈወርቅ ተክሌን ሞት ተከትሎ አንድ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ -ጥበብ ሌክቸረር በኢቲቪ ላይ ቀርበው ስለሎሬት አፈወርቅ ተክሌ እጅግ ሞቅ ደመቅ ያለ ክብር እና ሞገስ እኔም ይህ አርቲስት ወዳጀም (እርሰዎም ) በኮምፒዩተራችን ተመልክተናል። ይህን ምስል ግን ባየንበት ወቅት እኔን ደስ ሲለኝ ወዳጀን ግን ከፍቶታል። ለምን ቢባል ለካስ እኝህን አስተያየት ሰጭ በተማሪነት ዘመኑ ያቃቸዋል። ይህን አስተያየት የሚሰጡት መምህሩ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎቻቸውን የሚሏቸው “ሎሬት አፈወርቅ ማለት ነገረ ስራቸው ሁሉ የባዕዳን የሆነና ለአገራቸው የስነ -ጥበብ እድገትም ይህ ነው የሚባል አስተዋጽዖ የሌላቸው” አድርገው ነው ተማሪዎቻቸውን ሲያንጹ የኖሩት። ታዲያ ግን የአርቲስቱን ሞት ተከትሎ እንዲህ ያለ የህሊናቸውን -መሬት የለቀቀ አስተያየት በሚዲያ ላይ ለመስጠት እርሳቸውን ባይዘገንናቸውም ይህን ወዳጀን ግን ክፉኛ ቀፍፎታል። የሎሬት አፈወርቅ ከብር ከምድር አልፎ ጨረቃ ላይ መሰቀሉ ምድር ላይ በክፋት ለሚንፏቀቀው አስተማሪ የማይደረስ ቢሆንበትም በተማሪነት የሚያንጻቸውን ታዳጊ አርቲስቶች ሁሉ ግን ምን ያህል ሲበክል እንደኖረ ልብ ይሏል። ዛሬ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ከኢትዮጵያ የሚዘርፉትን ንብረት ወደ ውጭ በሚያሸሹበት ዘመን ሎሬት አፈወርቅ ግን የጥበብ ንብረታቸውን በሙሉ ለኢትዮጵያ ህዝብ አውርሰው ማለፋቸውንም ሲሰማ ቀድሞ በሎሬት ላይ የነበረውን አመለካከት እያሰበ ይህ ወዳጀን እራሱን እንዲጠይቅ አስገድዶት አልፏል። ግን አማራው መምህር ሌላውን አማራ ታላቅ ባለክብር በማሳነስ ክብር ለመቀዳጀት ሞከረ።

ምሳሌ 2
እስኪ “ኢትዮጵያዊ” ነኝ እያለ በሚንጠባረረው አማራ ዙሪያ ሌላ የክፋት ምሳሌ ልጥቀስ። ኬኒያ ውስጥ አሉ አሉ ነው ታዲያ ግን “እውነት ነኝ” ያለ “አሉ” ነው። ምክንያቱም በብዙ ማስረጃ የተረጋገጠ ነው። ኬኒያ ውስጥ በስደት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሁለት አንጃ አላቸው። አንደኛው “ኦሮሞ” ነኝ ባይ ሲሆን ሌላው ደግሞ “ኢትዮጵያዊ ነኝ” ባይ ነው። ይህን የማነሳው ታዲያ ለእኛው ነው እንጅ ይህ ሃሳብ የሚያጠነጥነው በሶማሌዎችና በኢትዮጵያውያን መካከል ነው። እናም ኬኒያ በስደት ሆነው የሚማቅቁ ወገኖቻችን በተለያየ ሰው አስተዋጽዖ ወደተለያዩ የአለማችን ክፍሎች የስፖንሰር እድል ሲያገኙ ኬዛቸውን ከማበላሸት እስከ ፓስፖርታቸውን እና ጠቅላላ ዶክመንታቸውን መስረቅ “የክፉ ኢትዮጵያውያን ነን ባዮች” አይነተኛ መለያቸው ሲሆን ሶማሌዎች ግን እንኳንስ አንዱ አንዱን ሊመቀኝ ቀርቶ አንዱ ለሌላው በመደጋገፍ ፕሮሰሱን እንደሚያሳምር ያስተዋለች አንዲት ካናዳዊት የቪዛ ኦፊሰር የሚከተለውን ተናገረች። “እስርቤት ውስጥ አስቀምጦ ጠባቂ ዘበኛ የሚያስፈልጋቸው ሶማሌዎች እንጅ ኢትዮጵያውያን አይደሉም። ምክንያቱም ኢትዮጵያውያን እርስ በእርስ ይጠባበቃሉ።”

ምሳሌ 3 ላስቀድምና ወደ ጠቅላላው የአማራ የፖለቲካ ፍልስፍና ላምራ።
በደርግ ጊዜ ለበርካታ አመታት እስር ቤት የማቀቁት ብጹዕ አቡነ መልከ ጸዲቅ በአንድ ወቅት ተከታዩን ሃሳብ በቃለ ምልልስ ሲናገሩ ሰማሁ። “እስር ቤት ውስጥ ያለን ሰዎች ያው ኖሯችን እዚያው መሆኑን በመረዳት የስራ ክፍፍል አደረግን። ከስራው ዝርዝር በጥቂቱ፦ ስንቅ ተቀባይ ቤት ጠራጊ እቃ አጣቢ ይህን ደግሞ ተከታትሎ አስፈጻሚ በሚል የስራ ክፍፍል ተካሄደ። ሆኖም ግን በዚህ የስራ ክፍፍል ውስጥም የስልጣን ፉክክር መጀመሩን የተመለከቱ አንድ አባት “እኛስ ተፈትተን ብንወጣም ስለማንጠቅም እዚሁ እንደታሰርን ብንቀር ነው የሚሻለን” አሉ።

ይህ ሁሉ የክፋት ምንጩ ምንድን ነው ? ፈጽሞ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ቀርቶ ሰው የመሆን መንፈስ ከውስጣችን አለመኖሩን ልብ ይሏል። ለዚህ አይነተኛው ምሳሌ ደግሞ የአማራ -ፖለቲካዊ ስነልቦና የተመስረተበት ጉድፍ ነው። ለመሆኑ ጠቅላላውን የአማራን ፖለቲካዊ ስነልቦና እንዴት መገመት እንችላለን ? መልሱን በተከታዩ የአማራው -ፖለቲከኛ ጥቅሶቹ ውስጥ እናገኛለን፦

“ዘራችን ኢትዮጵያዊነት ነው”
“ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር”
“አንድ ኢትዪጵያ ወይም ሞት”
“ኢትዮጵያ በዘር አትከፋፈልም”
“ኤርትራ ወደ እናት አገሯ ኢትዮጵያ መመለስ አለባት”
“ከወያኔ ጋር በሚደረግ ትግል ሻቢያን ማመን አይገባንም”
“የጎሳ ፖለቲካ ከሚከተሉ ተቃዋሚዎች ጋር ምንም አይነት ድርድር አያስፈልግም”
“ኢትዮጵያን ከወያኔ ነጻ ለማድረግ በሚደረገው ትግል ከአሜሪካ ከእንግሊዝ ከህንድ ከቻይና …” በአጠቃላይ ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ ምንም አይነት እገዛ መጠበቅ የለብንም”

እነዚህን ጥቅሶች ፉርሽ ወደሚያደርገው ገለጻየ ከመሄዴ በፊት ሰሞኑን በውቀቱ ስዩም አጼ ቴወድሮስን የወረፈበትን ጽሁፉን ላስቀምጥ። “እውነት ለመናገር አጼ ቴወድሮስ በዘመናቸው ከነበሩ ወደረኞቻቸው ጋር ሲመዘኑ እጅግ ኋላ ቀር ነበሩ።” ይላል በውቀቱ ስዩም። እንግዲህ ልብ እንበል “ኢትዮጵያዊ” ነኝ ከሚለው ውጭ ከማናቸውም አይነት ክፍል ድጋፍን ይጸየፉና እንደገና ደግሞ ዞር ብሎ “እንሥሳት ሁሉ እኩል ናቸው አሳማ ግን የበለጠ እንሥሳ ነው” በሚለው መስፈርት ደግሞ ዞር ብሎ “ኢትዮጵያዊ ነኝ” የሚለውን ክፍል ደግሞ ኢትዮጵያዊነቱን ለማሳነስ ይሞክራል። እዚች ላይ እንድ የማረፊያ ፌርማታ ልስራ። ቴዲ አፍሮ ሰሞኑን እየተባለ ያለው የአድዋን ድል ስታነሳ ቃላት አዛንፈሃል እንዲያም ሲል ግጥምህ ሲመዘን ኢትዮጵያዊነትን የማጉላት ሃቅም ያንሰዋል። ስለዚህ ኢትዮጵያዊነት ያንስሃል። ይህ ነው የአማራው የፖለቲካ ስልጣኔ ደረጃ። የሁለቱን ቴወድሮሶች ህይወት ልብ ይሏል።

ለዚህ ነው አማራው አገር ነጻ አውጭ እና ጠባቂ እንጅ መሪ መሆን የማይችልበት ሃቅ። እውነት የመሪነት ብቃት ያለው ፖለቲከኛ ባዶ ህሊናውን በሙሉ አፉ ለመሸፈን “ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” ከሚል ይልቅ ኢትዮጵያዊነቱን ከጸነሰለት የቋራው ቴወድሮስና ኢትዮጵያዊነትን የሚያወድሰውን ቴዲ አፍሮን በቃላት ሊሰቅለው የሚሞክር።


ትዝ ይለኛል በአማካኝ 8 አመታት በፊት እዚሁ ዋርካ ላይ “የኛ ፖለቲካ” በሚል አርዕስት ግጥም ዓቅርቤ ነበር። የግጥሜ ምንጩ ኢዴፓ እና መኢአድ አንድ ለመሆን ሲደራደሩ ቆይተው ድርድሩም ፈርሶ ልደቱና ሃይሉ በሚዲያ ሲዘራጠጡ ድርድሩ ያልሰመረበት አይነተኛ ‘አስቂኝ’ ምክንያት ከፓርቲዎች ውህደት በኋላ በሚኖረው የስልጣን ክፍፍል እና ከውህደቱ በኋላ የፓርቲው ስም ማን ይባል በሚለው አለመግባባት ነው። ልብ በሉ እነዚህ ፓርቲዎች ከላይ ያሉትን ጥቅሶች የሚያቀነቅኑ ሲሆን ለፓርቲ ስም መጠሪያነት ሁለቱም የሚያመነዥኩት “ኢትዮጵያ” የሚል ቃል ካለበት ምን ያጣላ ነበር ? ባልና ሚስትስ በፍቅር ከተዋሃዱ በኋላ ቤቱን ማን ያስተዳድረው የሚለው ፍቅር ወይስ ስልጣን ? ይህ ነው የአማራው ፖለቲካዊ ስነ -ልቦና።

እስኪ በተቃራኒ ደግሞ የትግራይ -ወያኔዎችን እንመልከት። አንድ አላማ ይዘው ተነሱ ቆይተው ግን ሁለት አላማ አደረጉት። የመጀመሪያው የማያወላውለው አላማቸው “ትግሬነትን” ከኢትዮጵያዊነት መንፈስ ፈልቅቆ ማውጣት ነበር። ለአላማ ጽናታቸው አስተዋጽዖ አደረገ። ቆይቶም ይህ አላማቸው ወደ ድል ሲያስጠጋቸው “የኢትዮጵያዊነትን መንፈስን በአለበት ትተን ትግራይን ብቻ ብንገነጥል መንፈስ መልሶ ያሸንፈናል ስለዚህ ኢትዮጵያዊነትን ከውስጡ ገብተን የማጥፋት ስራችንን ካልፈጸምን ትግራይን ብቻ መገንጠል ትርጉም የለውም” በሚለው አመኑ። ዛሬ ይህ አላማቸውን በብቃትና በአንድነት እያሳኩ ይገኛሉ። አቶ ዳኛቸው ይህን የቴዲን አልበም አሳምረው በገለጹበት መጣጥፋቸው “ቴወድሮስ ሲያዜም ኢትዮጵያ ትከበራለች” አሉን። በመጣጥፋቸውም ውስጥ ከቴዲ አልበም በፊት በኢትዮጵያዊነት ላይ የሚነፍሰውን የወርደት እና ተስፋ -ማጣት አይነት በቁጥር ተነተኑት። ከእሳቸው በላይ ግን ቴዲ አፍሮ ስለአልበሙ በሰጠው ቃለ -ምልልስ ማርቲን ሉተር ኪንግን ጠቅሶ እጅግ ምጡቅ የሆነ ነገር ነገርን። “ተስፋ የምናደርገው ነገር ስለሌለን እራሳችን ተስፋ ሰርተን ወደ ተስፋው እናምራ” አለን። ለዚህም ወያኔን የወረፉበትን የታላቁን ሎሬት ጸጋዬ ስነ -ግጥም ተጠቀመ። ለአማራው ፖለቲከኛ ግን ይህም አይጠቅመውም። ምክንያቱም ለአማራው -ፖለቲከኛ ትልቁ ውድድሩ የኢትዮጵያዊነት ተስፋን የመፍጠር ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት ከቴዲ በልጦ መገኘት ነው።

ለመሆኑ የአማራው -ፖለቲከኛ ከትግራይ -ወያኔዎች ምን መማር ይገባዋል Question

ክፍል ሁለቱን ወረድ ብለው ያንብቡ Arrow


Idea Idea Idea Idea Idea Idea


Last edited by ጥልቁ1 on Tue Apr 24, 2012 8:50 am; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message MSN Messenger Report post
ጥልቁ 1

ዋና ውሃ አጠጪ


Joined: 27 Jan 2004
Posts: 1560
Location: bhutan

PostPosted: Tue Apr 24, 2012 7:36 am    Post subject: Reply with quote

ክፍል ሁለት እና የመጨረሻው


ለመሆኑ የአማራው -ፖለቲከኛ ከትግራይ -ወያኔዎች ምን መማር ይገባዋል Question

ከላይ እንደገለጽሁት የመጀመሪያው የወያኔዎች የማያወላውለው አላማቸው “ትግሬነትን” ከኢትዮጵያዊነት መንፈስ ፈልቅቆ ማውጣት ነበር። ዛሬ ደግሞ የአማራው ፖለቲከኛ ማንነቱን ከኢትዮጵያዊነት መንፈስ ፈልቅቆ ሊመለከተው ይገባል። “ዘሬ ኢትዮጵያዊ ነው” ሲልም ምን ማለቱ እንደሆነ እራሱን ይጠይቅ። ምክንያቱም ኢትዮጵያዊነት የጋራ ዘር ግን የግል ነው። ስለዚህ በሌላው ላይ ሊጭነው የሚሞከረው ኢትዮጵያዊነት ምን አይነት ኢትዮጵያዊነት ነው ? እራሱን ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር የማያስማማ ኢትዮጵያዊነት ? ኢትዮጵያዊነት ማለት ግዙፍ የሆነ ሃሳብ ነው። እኔን ተመስሎ “ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” እያለ እኔን ግን “በኢትዮጵያዊነት እበልጥሃለሁ” የሚለኝ በሰይጣናዊ ቅናት ከሆነ እሱ እራሱ እንኳንስ ኢትዮጵያዊ ገና አማራ አልሆነም ማለት ነው። ስለዚህ መጀምሪያ የራሱን ህሊና ያጽዳ። ከሌላው አማራ ጋር ከተፎካከረ ፉክክሩ መንፈሳዊ እንጅ ሰይጣናዊ ክርክር መሆን አይገባውም። ቴዲ አፍሮ ኢትዮጵያዊነቱን ካጎላለት ከዚህ የበለጠ ሌላ ምን መፎካከርን ያመጣል ?! እኔ እራሴ በቴዲ በመንፈሳዊ መልኩ እቀናለሁ። የምቀናው ግን በሚበላው በሚጠጣው በሚያቅፋት ሴት በሚያጅበው አድናቂው ሳይሆን ‘ምነው የሱን ያህል ስለኢትዮጵያ የመሰማት እድል ቢኖረኝ’ ብየ ነው። ግን ደግሞ ቅናቴን የሚያስታግስልኝ ለካስ እሱም የኔ ነው።

ሌላው የአማራው ፖለቲከኛ ያልተገነዘበው ትልቁ ሃቅ የፖለቲካ ብቃት እንደሌለው ነው። ልብ እንበል ልደታ ፍርድ ቤት በጠበቃነት ተቀጥሮ አማርኛ ቃላትን ሲያሽኮረምሙ መዋልና የሚሰነዘርን -ኢትዮጵያዊ -ግዙፍ -ሃሳብ ሁሉ በቃላት ደረጃ አውርዶ መዘራጠጥ ፖለቲከኛነት መሆን ማለት አይደለም። 10 ሆኖ በኮሚቴነት የሚያገለግለውን የፖለቲካ ድርጅት በቃላት እንካ ስላንትያ ዘነጣጥሎ መከፋፈል አይደለም ፖለቲከኛነት ማለት። “ወያኔ አላንቀሳቅሰኝ አለ” ሲሉ ሰነባብቶ በምርጫ ሰሞን ዱብዱብ ማለት አይደለም ፖለቲከኛነት። ከውስጥ በሚፍተለተል ያልጸዳ የማንነት ቆሻሻ እየተበጣጠሱ ወያኔ በመሃከላችን ገብቶ ከፋፈለን ማለት አይደለም ፖለቲከኛነት። ወያኔማ ስልጣኑን ለማስከበር ከመከፋፈል እስከ መግደል ቢጨክን አላማው ነው። ትልቁ ጥያቄ መሆን ያለበት የአማራው -ፖለቲከኛ ልዩነቱን አቻችሎ በአለፉት 20 አመታት ውስጥ ይህ ነው የሚባል ፖለቲካዊ ተቋም አለው ወይ ነው። የለውም። በዚያን ሰሞን አንዱ ተነስቶ የኦነጉን መሪ ሲጠይቅ “እውነት ለኢትዮጵያ መታገል ከጀመራችሁ “ኦነግ” የሚለውን ስም ለምን አትተውትም ? አላቸው። ተጠያቂው ተለሳልሰው ፖለቲካዊ መልስ ሰጡ። መልሱ ግን መሆን የነበረበት ‘ኢትዮጵያ በሚለው ስም የተደራጁት መዝለቅ ያልቻሉትን ረዥም የአንድነት ጎዳና ግን የተራመደ ኦነግ ብቻ ነው’ ነበር የሚያረካኝ።

አማራው -ፖለቲከኛ የፖለቲካ መሪነት ብቃት ቀርቶ ህዝብን የማነሳሳት ሃቅም እንኳ እንደሌለው እየታየ ያለው
አይነተኛ ምሳሌ በታማኝ በየነ ነው። በአሁኑ ሰአት በዳያስፖራ -ፖለቲካ ውስጥ ትልቁ ጨውና ስኳር ሆኖ ያለው ታማኝ በየነ ነው። ታማኝ ግን አርቲስት ኢትዮጵያዊ እንጅ ፖለቲከኛ አይደለም። ፖለቲከኞች በሚጠሩት ስብሰባ ላይ ከሚገኘው ይልቅ ህዝብ እጥፍ ድርብ ሆኖ የሚታየው ታማኝ ባለበት ስብሰባ ነው። እሱም ይህን ስለሚገነዘብ ንግግሩን የሚከፍት “የመሳደቢያ እንጅ የአርቲስትነት ጃኬቴን አለበስሁም” ብሎ ነው። ይህ የታማኝ ነገር የሚያሳየን አንድ ሃቅ አለ። ኢትዮጵያውያን የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪዎች ላይ ያላቸው ተስፋ ተሟጥጦ መጣሉን ነው። ያማ ባይሆን ከኪነጥበብ ከተለየ አመታት ያለፈውን አርቲስት ሁሉም በኮምፒዩተሩ አማካኝነት ማግኘት ከሚችለው የተለየ መረጃ ታማኝ ምን ኖሮት ነው ልስማው ብሎ የሚሄድ ?!

መረሳት የሌለበት ታዲያ የታማኝም ጉዞ የመከራ ነበር። ታማኝም የቴዲ አፍሮ አይነት የቃላት ድንጋይ የተወረወረበት ከወያኔ አይደለም። ወያኔማ የቃልና የፕሮፕጋንዳ ሃቅሙ ለፈረንጅ እንጅ ለኛ አይሰራም። ትልቁ ትችት ይሰነዘርበት የነበረው ከአማራው -ፖለቲከኛ ነው። (ትዝ ይለኛል ከፕ / ኤፍሬም ይስሃቅ ጋር አሜሪካ ውስጥ በመገናኘቱ ብቻ “በነጻነት -ለኢትዮጵያ” ሬዲዮና በሌሎችም የአማራው -ፖለቲከኞች “ወያኔ” የሚል ታርጋ ተሰጥቶት የከፋ ትችት ሲደርስበት አስታውሳለሁ።
ስለዚህ አማራው የፖለቲካ መሪነቱ ቀርቶ የሚወዳት እና “የኔ” የሚላት “ኢትዮጵያን” አስጠብቆ የመኖር የወታደርነት እድል ለማግኘት እንኳ በመጀመሪያ ታግሎ የሚያታግለው ፖለቲከኛ ሳይሆን አርቲስት ወይም መሰል አገር ወዳድ ያስፈልገዋል። እንጅ ለፖለቲካ ስልጣን ለመታገል የተለየ የፖለቲካ ስነ -ልቦናዊ ግንዛቤ ያስፈልገዋል። ልብ እንበል ስነ -ልቦናችንን በአንድ ሌሊት ልናንጸው አንችልም። የመተባበር የመከባበር በትንሽነት -ውስጥ -ትልቅነት -እንዳለ መኖርን የማወቅ የትህትና የታጋዥነት የታጋሽነት ስነ -ልቦናን በመጀመሪያ ፈልጎ ማግኘት የሚገባው ከሌላ ሳይሆን ከራሱ እና እሱን መሰል ከሆነው “ኢትዮጵያዊ ነኝ” ከሚለው ነው መሆን ያለበት።

ፌርማታ ሁለት፡
አጼ ምኒሊክን የሚወርፍ መጸሃፍ ከወጣ እስከበርካታ ወራቶች ድረስ አንድም የማስተካከያ ሃሳብ ያላቀረበ እብን አጼ ምኒሊክን ለዘከረ ኢትዮጵያዊ ወገኑ የውረፋ ስጦታ ያበርክትለታል። ይህ ነው የአማራ -ፖለቲከኛ ማለት።

ለመሆኑ ውስጡን መፈተሽ ስል ምን ማለቴ ነው ?... በታሪክ ቀመስ ምሳሌ ልቀጥል…

አንድ የማይካድ ሃቅ ቢኖር ኢትዮጵያዊ ማንነት በኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ላይ የታነጸ መዝገብ ነው። በአገሪቱ የተፈራረቁት ነገስታትም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት የተቀቡ ነገስታት ነበሩ። እነኝህ ነገስታቶችም ወደ አማራነት እንደሚያደሉ የማይካድ ሃቅ ነው። ታዲያ አገሪቱን ሲገዙ እና ሲገዘግዙ የኖሩት በመጸሃፍ ቅዱስ ጥቅስ ሲሆን መጽሃፉን ለማያነቡት አማኒያን የሚጠቅስላቸው ግን ተገዥነትን አሜን ብሎ ስለመቀበል ብቻ ነበር። ያማ ባይሆን አፍሪካ -አሜሪካውያንን ነጻ ያወጣ መጸሃፍ ቅዱስ ኢትዮጵያውያንን ነጻ ማውጣት ባልተሳነው። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ አገዛዝን የሚቃወም የመጸሃፍ ቅዱስ አስተማሪ ብቅ ብሎ የማያወቀውም ለመጽሃፉ በቀረበ ቁጥር ለአገዛዙ የበለጠ ስለሚቀርብ ነበር። ታዲያ ክርስቲያን ወገኑን ረግጦ የገዛው ነግስታት ሁሉ ዘግይተውም ቢሆን ከአፄ ዩሃንስ በስተቀር እስልምና በአገሪቱ እንዲንሰራፋ ለመፍቀድ ግን ደንታ አልነበረው። (ሙስሊም ከሆኑም ተረራግተው ያንብቡኝ )
ታዲያ ለሌላው ክርስቲያን ተገዥው የማይፈቅደውን አንድ አምላክ የማምለክ ነጻነት ለሙስሊሙ ግን ቁራንን በነጻ የመማር ነጻነት ሰጠው። አንዳንዴ ሳስበው ስጋን እያስገዙ መንፈሳቸውን ለአንድ ፈጣሪ ሰጥተው ከኖሩት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን እና ስጋውንም መንፈሳዊ ህይወቱም ከመጸሀፍ ቅዱስ ውጭ ሆኖ ከኖረው ክርስቲያን የበለጠ ተበዳዩ ማን እንደሆነ እራሴን ያጠያይቀኛል። የዚህ ጽሁፍ አላማ ግን እምነትን በምሳሌ ተጠቅሞ የአማራውን ፖለቲከኛ ለመጎንተል ስለሆነ ልቀጥል። እናም ፣የአማራው ፖለቲከኛ ከላይ “አንድ ኢትዮጵያ” ከሚለው በተቃርኖ ልቦናው ለሌላ እምነትና ሌላው ዜጋ ምን ያህል እንደሚከፈት የማስተውልበት ድክመቱ ደግሞ ይገርመኛል። ለምሳሌ ቴዲ አፍሮን ኢትዮጵያዊነቱ ያልተሟላ አድርጎ የሚሟገተው የአማራ -ፖለቲከኛ አሊ ቢራ “ኢትዮጵያ” ብሎ እንደገና ቢዘፍን ከከማል ገልቹ እኩል እንደሚዘምርለት እርግጠኛ ነኝ። ስለዚህ በመጀመሪያ ደረጃ ያለውን አጥብቆ ሳይዝ ሌላ ሊጨብጥ ቢሞክር ተራ ተግባር ነው። የሰሞኑን የፈረንሳይ ምርጫም ይህን ያሳያል። ሳርኮዚ የመጀመሪያውን ዙር ምርጫ በሶሻሊስቱ በተሸነፈ በማግስቱ የድጋፍ ተማጽኖውን እያደረገ ያለው ፍጹም የፖለቲካ አቅጣጫው ከሱ የራቀውን የቀኝ ክንፍ ፓርቲ ነው። አማራው ግን አማራን ንቆ ነው ኦሮሞና ደቡብ -ምስራቁን ለመጠቀም የሚሞክር።

በመጨረሻም፡
አማራው ኢትዮጵያን እያጠፋት ከአለው ወያኔ አፍ የማስጣል ሞራላዊም ሆነ የቁርጠኝኘት ሃቅም አለው። ነገር ግን እርስ እርሱ መከባበርና እሱነቱን ከግለሰብ እስከ ማህበረሰባዊ ቅርጹ በቅጥ ሊፈትሽ ይገባዋል። (1)ድሮ በጥንት ዘመን አንድ ሰው ከሌላው ጋር የደም እዳ ቢኖርበት እና ለመግደል የሚፈልገው ባላንጣው ባልተዘጋጀበት ወቅት ቢይዘው ሱሪውን አውልቆ ቁጭ ካለ ባላንጣው አይገድለውም ነበር። (2)የትኛውም አውሬ -የሆነ -ውሻ ሊነክስህ ሲያሯሩጥህ ቁጭ ካልህ እጅ የሰጠህ ያህል ቆጥሮ ሳይነክስህ ጥሎህ ይመለሳል። (3)በሰለጠነው የጦርነት አለም ደግሞ አንድ ወታደር ነጭ መሃረብ አውጥቶ እያወለበለበ እጁን ከሰጠ አይተኮስበትም። ታዲያ የአማራ -ፖለቲከኞች ሆይ እንናንተ ልትነግሱባት የምትመኟትን ኢትዮጵያን ከሚያወድሳት እና እናንተ የምትወዱትን ሰንደቅ አላማ በእጁ ከፍ አድርጎ ለያዘው አርቲስት እና ለሌላውም መሰል ኢትዮጵያዊ በሁለት በኩል የተሳለውን የቃላት ጎራዴያችሁን አታንሱ። ምክንያቱም በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራን ልባም ወጣት በቃላት ጎራዴ ስታጭዱት ሌላውም ሰው በእናንተ ጉድፍ ውስጥ ኢትዮጵያዊነትን ይጸየፍና 21 አመታት በኋላም እንዲህ ጠና ያለ ድርጅት ሳይኖር እንዳለ ሁሉ ኢትዮጱያም አይናችሁ ስር እየጠፋች ትቀጥላለች። የመጸሃፉ ቃል “ጠላትህን ውደድ ሲል ወዳጅህን ግን ጥላ” ማለት አይደለምና የኢትዮጵያዊነት ፍቅር ሰባኪው ቴዲ ላይ ጥላቻችሁን ተውት።
የጥላቻ ቀስታችሁ ማረፍ ያለበት የትግራይ -ወያኔ ላይ ብቻ እና ብቻ ነው Exclamation Exclamation Exclamation

በቴዲ ዜማ እንሰነባበት፦

“ቀስተ ዳመና ነው የለበስሁት ጥበብ የያዝሁት አርማ
አልጠላም ወድጀ የነፍሴ ላይ ፋኖስ እንዳይ ጨልማ።”


ጥልቁ -ብሄረ ኢትዮጵያ
ብሄር ማለት አገር ነው።Idea Idea Idea Idea Idea Idea Idea Idea Idea Idea Idea Idea Idea Idea
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message MSN Messenger Report post
Ibn Khaldun

ኮትኳች


Joined: 15 Dec 2009
Posts: 203

PostPosted: Tue Apr 24, 2012 12:59 pm    Post subject: Reply with quote

Quote:
ጥልቁ 1
ስምን መልአክ ያወጣዋል Exclamation
_________________
IF YOU CAN'T SAY ANYTHING NICE - SHUT UP!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እንድሪያስ

አለቃ


Joined: 19 Mar 2004
Posts: 2130
Location: *****

PostPosted: Tue Apr 24, 2012 1:30 pm    Post subject: Reply with quote

Ibn Khaldun እንደጻፈ(ች)ው:
Quote:
ጥልቁ 1
ስምን መልአክ ያወጣዋል Exclamation


ወገኔ ኢብን ካልዱን ...... ከልብህ ከሆነ የጻፈውን አላነበብከውም ማለት ነው :: ሽሙጥ ከሆነ ደግሞ ዋርካ ውስጥ አስተዋይና አመዛዛኝ ከሆኑ ታዳሚዎች አንዱ ነህ ማለት ነው ?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች


Joined: 01 Jun 2009
Posts: 811

PostPosted: Tue Apr 24, 2012 3:39 pm    Post subject: Reply with quote

-----

Last edited by እናመሰግንሃለ on Tue Sep 03, 2013 9:57 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዲጎኔ

ዋና አለቃ


Joined: 19 Aug 2005
Posts: 4208
Location: united states

PostPosted: Tue Apr 24, 2012 4:09 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችን ይሁን
አፌ ቁርጥ ይበል እናመሰግናለን በል እንግዲህ ይህን ወንጌል የክርስቶስ ብቸኛው ተስፋችን ከሆነ በተግባር እዚሁ ዋርካ ልይ ጀምረውና ሀዲያ ላይ እአስት እንዲወርድ የጀመርከውን ሱባኤ ትተህ ንስሀ ግባ ትክክለናውን የክርስቶስ ወንጌል ከዮሀንስ ወንገል ጀምረን ከፈለግህ አብረን እናጥና ::
ስለብሄሮችና ዘርና ኢትዮጲዊነት ከተነሳ ባለፈው / ብርሀኑ አበጋዝ የስነህዝብ ሊቅ በአሜሪካ ድምጽ ባደረጉት የስነህዝብ ብዙሀኑ ኢትዮጵያ ነዋሪ ህዝብ ከሁለትና ሶስት በላይ ብሄሮችድብልቅ መሆኑ የተናገሩት ይሰመርበት ::ትክክለና ወንጌል ከተሰበከ ግን ይህ ሁሉ መባላት ወልመካ ሳፊ መባባሉ ይጠፋል ::
ዲጎኔ ሞረቴ ኩሽቲክ ሴሜቲክ ናይሎቲክ ድብልቁ ኢትዮጲያዊ አንዱንም ዘሩን ሊሰድቡበት የማይፈቅደው


እናመሰግንሃለ� እንደጻፈ(ች)ው:

እኔ ግን ወንጌሉን በደንብ እንዲያነብቡ ከመጋበዝ ውጭ ምንም ልለው የምችለው የለኝም ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች


Joined: 01 Jun 2009
Posts: 811

PostPosted: Tue Apr 24, 2012 4:18 pm    Post subject: Reply with quote

--------

Last edited by እናመሰግንሃለ on Tue Sep 03, 2013 9:59 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ናፖሊዮን ዳኘ

ዋና ውሃ አጠጪ


Joined: 18 Apr 2008
Posts: 1878

PostPosted: Tue Apr 24, 2012 6:13 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ጥልቁ

ያስነበብክን ጽሁፍ ግሩም ነው :: ወቅታዊነትም አለው ---ከቴድሮስ ካሳሁንም ጉዳይ ባለፈ ::

አንዳንዶቹ ያነሳኻቸው ጉዳዮች ታሪካዊ ማመሳከር እና ጥናት የሚጠይቁ ሆነው እንደ ጭብጥ ያነሳኸው ጉዳይ ግን የሚያስማማ ብቻ ሳይሆን ራሴንም ጭምር የፈተሽኩበት ነው ::


ቴዲሮስ ካሳሁንን በሚመለክት የሙዚቃ ስራው አይተች አይነካ የሚል እምነት የለኝም :: ሊነካ ይችላል :: ነገር ግን የሙዚቃ ስራውን በሙዚቃዊ አስተሳሰብ እና እውቀት ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት :: እንደሚገባኝ ደሞ አብዛኛው የኔ ቢጤ የሙዚቃውን ቅላፄ እና መልዕክት ከማጣጣም ውጪ በሙዚቃው አንጻር ይሄ ጎድሎታል የሚለው ነገር አይኖርም :: መቼም ፌስ ቡክ የማያሳየው ነገር የለም - መጽሀፍ ሊያጥብ የደረሰው አንድ ያዲስ ነገር ባልደረባ የቴድሮስን ስራ በፖለቲካ ቲዮሪ እና ፍልስፍና በሚመስል አቀራረብ ጭምር ሊመዝነው ሲንደፋደፍ አያይቻለሁ :: እሱን ተከትሎ የሚያዳንቅ አና ወጥ የሚረግጥም አልጠፋም :: በነገራችን ላይ የሌላ የሙዚቃ ሰው ስራ ቴድሮስ ካሳሁን ስራ ባነጋገረበት መጠን እና እንዳላነጋገረ ሳስተውል ሳይገርመኝ ሁሉ አልቀረም :: በበኩሌ ስማቸውን እንኳን የማላውቃቸው ለእኔ አዲስ የሚመስሉ ነገር ግን ከቴድሮስ እኩል በሙዚቃ ዓለም የቆዮ እንዳሉ ተረድቻለሁ :: እርግጥ ነው ከቴድሮስ ስራዎች ጋር ያቀራረበኝ በዘፈኑ የሚያስተጋባቸው መልዕክቶች ናቸው ::

የሆነ ሆኖ በዚህ ባዲሱ አልበም ቴድሮስ ካሳሁን እንደበፊቱ የአድማጩን ቀልብ ገዝቷል :: የዘፈነው ደሞ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ ሌት ከቀን ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንጂ ለፈላስፎችም ለጸጉር ሰንጣቂዎችም ለፖለቲካል ቲዎሪስቶችም አይደለም :: ህወሀት የተከለውን የጎሳ ፖለቲካ አስከፊነት እና ህዝቡ ከዚህ የጎሳ ፖለቲካ ጋር ያለውን ጥላቻ ስለተረዳ በማይናገረው የኦሮምኛ ቋንቋ እስከመዘመር ድረስ ደርሷል :: ያስመሰግነዋ Exclamation

ላለመዋሸት በግሌ ቴዎድሮስን የተቃወምኩበት አገባብ ---ከትግሬ ጋር ተጋባ የሚባል ነገርን ሰምቼ ነው :: ይሄ ደሞ ለቴድሮስ ሳይሆን ለህወሀት እና ለደጋፊዎቻቸው ካለኝ ጥላቻ የመነጨ ነው :: በተጨማሪም ደሞ ቴድሮስ እንደሚያንጸባርቀው ጥልቅ ኢትዮጵያዊነት እና ጨዋነት ይቺኑ ትግሬ ነች የምትባል ልጂ ልክ ፊልም ይሰራ ይመስል ሜዲያ በተገኘበት ባደባባይ እየሳመ ፎቶ መነሳቱ ከሱ ስብዕና ጋር ስለማይሄድ እና ኢትዮጵያም ውስጥ መለመድ የሌለበት ጉዳይ ነው ብየ ስለማምን ወቅሼዋለሁ :: አሁንም አቁዋሜ ያው ነው ::


በተረፈው ወደ ሌላኛው መሰረታዊ ትንተናህ ስመጣ ---ከአማራነት ጋር በተያያዘ የሰጠኸው አስተያየት ትክክል ነው :: ለነገሩ እኔ አማራ ምናምን እያሉ ማውራት ብዙ አይመቸኝም :: አለወደውምም :: በጎሳ አንፃር ከአንድ በላይ ከሆኑ ኢትዮጵያውያን የተገኘሁ በመሆኔ ብቻ ሳይሆን እንደ እምነት እምነቴ ኢትዮጵያዊነት እምነቴ ነው ብየ ስለማምን ነው ::

ምንም እንኳን አማራ እየተባለ የሚጠራው የህበረተሰብ ክልፍ በኢትዮጵያዊነት አንጻር ብዙ መከራ ቢከፍልም አማራነት ኢትዮጵያዊነት ነው ብየ በፍፁም አላምነም :: እንደዛ ከሆነ እነ ሎሬት ፀጋየ ገብረ መድህን እነ ራስ ደታ ዳምጠው እነ ሲሳይ አጌና እነ ማን ልበልህ አበበ አረጋይ ኢትዮጵያዊ ላይሆኑ ነው :: እንደ ቲዎሪም አማራነት ኢትዮጵያዊነት ነው የሚለው አያስኬድም :: በተለያየ ጊዜ ለመደራጀት የተደረጉ ጥረቶች ---አንተ የጠቀስካቸውን ጨምሮ ---ቢደረጉም ርባና ያላቸው ሳይሆኑ እዚህ ደርሰዋል :: በፖለቲካ አንፃር አለመግባባቶች እና መከፋፈሎች የትም ቦታ በየትኛውም ዘመን ያለ ነገር ቢሆንም አንድ ርባና ያለው ነገር ሳይሰሩ ግን በማይረባ የፖለቲካ ሀይል ሲቀጠቀጡ መኖር ደካማነትብ ብቻ አይደለም የሚያሳየው Idea

ትልቁ ነጥብ የቁርጠኝነት እና የወኔ ችግር እንዳለ ነው የሚያመላክተው Idea Idea Idea ደፋር እና ጭስ መውጪያ አያጣም እንደሚባለው የቆረጠው ሰው አደረጃጀቱን ያሳምራል ! በትንሽ በትልቁ አይናቆርም ! አማራ እየተባለ የሚጠራው ሰው መደራጀት አልቻለም :: ስድስት ኪሎ እያለሁ በባዶ መሬት ሳይደራጁ ""እኔ የጎነደሩ ልጂ "" እያሉ የሚኮፈሱ እና የኢትዮጵያ ነባራዊ የፖለቲካ ሁኔታ ያልገባቸው የማየቴን ያህን ከሚያወሩት እና ከሚናገሩት ነገር ግን ዓላማ እና ቁርጠኝነት ያነገበ ሀሳብ እና ስለ መደራጀት ሲያወሩ አልሰማም ነበር :: ወያኔ አዲህ አድርጎ ወያኔ እንዲህ ሰርቶ ከማለት ውጪ ::

አሁን ሀገር ቤት ያሉ አንዳንድ ወጣቶችም ደሞ ለመደራጀት ጥሩ ጂምር ይዘው ሳለ አደረጃጀታቸውን እንደምንም ብለው ""ዓለማቀፋዊ "" ይዘት ያለው ለማድረግ እና ""ፕሮግረሲቭ "" ነው የሚሉት ሀሳት በግልብነት የሚያራግቡ ከሚመስሉ በስተቀር ኢትዮጵያዊነትን እንደ አክራሪነት እና እንደ ""ናሺናሊስትነት "" እና ያንን ደሞ እንደ ችግር የሚያዮ እና በዚሁ ህሳብ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ የሚሞክሩ እያየን ነው ::

የአሜሪካ ፕሮግረሲቮች እኮ ምንም እንኳን ስለ ""ግሎባል ሲቲዝን "' አሜሪካዊ ላልሆነው ቢሰብኩም ከልባቸው ግን አሜሪካውያን ናቸው :: "" our founding fathers'" "In God we Trust" this is unAmerican ሲሉ የሚደመጡ ናቸው :: "ምክንያታዊነት ዘመን "" የሚባለውን ዘመን ያባቱት የፈረንሳይ ፈላስፋዎች እኮ ከፈረንሳይነት እና ከፈረንሳያዊ ብሄራዊ ስሜት ጋር ጠብ አልነበራቸውም Idea ዛሬም ቢሆን የፈረንሳይ ማህበረስብ በየትኛውም አለም ካለው ህብረተሰብ የፖለቲካ ግንዛቤ አለው እየተባለ በብሄርተኝነት አንስፃር ግን ፍስቱም ፈረንሳያዊ ነው :: ከሳርኮዚም ጋር ያለው አንደኛው ጠብ ( አንዴ አንገቱን ይዘው ጎትትው ሊደፉት እስከ መድረስ ) የሚያራምደው አስተሳሰብ ፈረንሳዊ አይደለም :: ፈረንሳይን ይጎዳል ከሚል ነው :: እንግሊዞቹም በራሳቸው መንገድ ብሄርተኞች ናቸው :: ካናዳውያኑም እንደዚያው ...

ይሄኛውን ነጥብ ያነሳሁበት ምክንያት ላለመደራጀታችን አንድ ምክንያት የሆነው እና ቅጥ ባጣ ምክንያታዊነት ምክንያት ለኢትዮጵያዊነት የምንስጠው ግምት እና ዋጋ እያነሰም በመምጣቱ ነው :: በዛ ላይ እንደቴዎድሮስ አይነት ለብዙ ኢትዮጵያውያን የሚገባ የሚዳሰስ የሚጨበጥ ሀሳብ ከማስተጋባት ይልቅ ግራ የሚያጋባ የዓለማቀፋዊነት ሀሳብ የሚራግብ ሰው የፖለቲካ መድረኮችን እና ከበስከጀርባም በመሆን ሀሳብ ላይ ተጽዕኖ በማሳደር ስለ ተጠመደ ---ወጣቱ በቁርጠኝነት የሚሰባሰብበት እና የሚደራጂበት ጠንካራ እና ከኢትዮጵያዊነት ጋር ፅኑ ትስስር ያለው ሀሳብ ስለማይራመድ ይመስለኛል ::

ከዚያ ውጪ ግን አማራ ነኝ እያለ ለህወሀት የትሮጃን ፈረስ ሆኖ የሚያስጨፈጭፍም ድርጂት አለ ::

ህወሀት ከምንም ነገር በላይ የሚያውቀው ቢኖር ኢትዮጵያዊ ነን አማራ ነን የሚለው ሀይል ቁርጠኝነት እንደሌለው ያውቃል :: በአስተሳሰብም ነፈዝነት ቢጤም አለው ብሎ የገመተም ይመስላል :: ለዚያም ነው የውጪ የሚያደነዝዝ ባህል ኢምፖርት በማድረጉም በኩል ከወጣቱ ጋር ተስማምቶ አደንዛዥ ሀሳቦችን በማስፋፋቱ ረገድ ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተ ያለው ::

ንቃተ ህሊና ሲዳብር ቁርጠኝነት ይመጣል :: ከዚያ መደራጀት ይከተላል :: ከዚያ በኍላ ያለው ነገር ቁልቁለት ነው :: የሚከብድ ነገር የለውም ::

ናፖሊዮን ዳኘ ::
_________________
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዞብል 2

አለቃ


Joined: 30 Jan 2004
Posts: 2031

PostPosted: Tue Apr 24, 2012 6:15 pm    Post subject: Reply with quote

ስማ ጌታው Razz ስምንት ዓመት ሙሉ ያረገዝከውን ለኢትዮጵያ ያለህን ጥላቻ ዛሬ አማራ በሚል ስም ተገላገልከው Evil or Very Mad

ዞብል ከአራዳ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ስራ ፈት

ጀማሪ ኮትኳች


Joined: 17 Jan 2005
Posts: 59

PostPosted: Tue Apr 24, 2012 6:39 pm    Post subject: Reply with quote

ብዙ ሰዎች ሲጽፉ ወይም ሲናገሩ ልብ ብላችው ተመልከቱ ""አቤት አጻጻፉ , የሱ ንግግር እኮ መሬት ጠብ አትልም "" እንዲባሉ እንጂ , የሚጽፉት ነገር ፍሬ አለው ወይም የለውም ግድ አይሰጣቸውም :: ሰላሳ ገልጽ ጽፎ አንባቢን ከማሰልቸት እጥር ምጥን አድርጎ ሀሳብን መግለጽ ትልቅ ችሎቻ ነው :: ይሄ ትዝብቴ ለዋርካ ብቻ አይደለም አብዛኛው የኢትዮጵያ ዌብ ሳይቶች ዜናንና አንዳንድ ነገሮችን ሲጽፉ የሚጠቀሙበት ወርድ ያስቀኛል :: በጣም ረጅም ከባድ ወርድ ጽፈው አንባቢውን ግራ ያጋባሉ ባጭሩ ቀለል ባለ እንግሊዝኛ መጻፍ ትልቅ ችሎቻ እንደሆ ይዘነጉታል ::

በዚህ ዘመን አብዛኛው ውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ግዜ እንደ አቶ ተሰማ ቁምጣ ያጠረው ነው :: የሱን አራት አምስት ገልጽ ማንበቡ ሳይሆን ግዜውን ሰውቶ አራትና አምስት ግልጽ ተነቦ ቁምነገር የሌለው የቃላት ክምችት ከሆነ በአንባቢው ግዜ መጫወት ይመስለኛል ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ


Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5049

PostPosted: Tue Apr 24, 2012 6:48 pm    Post subject: Reply with quote

Quote:
Code:
ላለመዋሸት በግሌ ቴዎድሮስን የተቃወምኩበት አገባብ ---ከትግሬ ጋር ተጋባ የሚባል ነገርን ሰምቼ ነው ::   አሁንም አቁዋሜ ያው ነው ::


የኛ ፕሮጊሪሰቪ ቲንከር ..ግሎባል ሲትዝን ...ዩኒፊኬሺኒስት ....የእምዬ ኢትዮጵያ የበኩር ልጅ ...ወዘ .....ስለማነትህ ካንተ በላይ ማንም ምስክርነት መስጠት አይቻለውም :: እኔ አልሰድብህም ..አልቃወምህምም ....አደብ ይዥ አንባብቢያን ማን መሆንህን እንዲያውቁ ግን አደርጋለሁ :: አይዞኝ !!Quote:
Code:
ስማ ጌታው   ስምንት ዓመት ሙሉ ያረገዝከውን ለኢትዮጵያ ያለህን ጥላቻ ዛሬ አማራ በሚል ስም ተገላገልከው  
 

ዞብል ከአራዳ


ቀደም ባለው አንድ መጻፅፌ ውስጥ ሰውየው የሻቢያ የቤት ወታደር መሆኑን ተናግሬ ነበር :: ሰሚ ግን አልነበረኝም :: ይሀው ስሶት ቀን አምጦ በሳልስቱ የሚተናነቀውን ነገር አስታወከው :: አውች !! Very Happy

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች


Joined: 01 Jun 2009
Posts: 811

PostPosted: Tue Apr 24, 2012 6:53 pm    Post subject: Reply with quote

-----

Last edited by እናመሰግንሃለ on Tue Sep 03, 2013 10:00 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ገልብጤ

ውሃ አጠጪ


Joined: 26 Jun 2010
Posts: 1334

PostPosted: Tue Apr 24, 2012 7:00 pm    Post subject: Reply with quote

Quote:
ላለመዋሸት በግሌ ቴዎድሮስን የተቃወምኩበት አገባብ ---ከትግሬ ጋር ተጋባ የሚባል ነገርን ሰምቼ ነው :: ይሄ ደሞ ለቴድሮስ ሳይሆን ለህወሀት እና ለደጋፊዎቻቸው ካለኝ ጥላቻ የመነጨ ነው :: በተጨማሪም ደሞ ቴድሮስ እንደሚያንጸባርቀው ጥልቅ ኢትዮጵያዊነት እና ጨዋነት ይቺኑ ትግሬ ነች የምትባል ልጂ ልክ ፊልም ይሰራ ይመስል ሜዲያ በተገኘበት ባደባባይ እየሳመ ፎቶ መነሳቱ ከሱ ስብዕና ጋር ስለማይሄድ እና ኢትዮጵያም ውስጥ መለመድ የሌለበት ጉዳይ ነው ብየ ስለማምን ወቅሼዋለሁ :: አሁንም አቁዋሜ ያው ነው ::ስማ ናፖሊዋን ዘረኛ ዘረ ቢስ ታዲያ አንተ ነህ የምዬ ኢትዮጵያ ልጅ Question ወያኔን ዘረኛ እያልክ እዚህ ታደርቀናለህ አንተ ከሱ በምን ተሻልክ ታዲያ Question ወይ ነዶ የኛ ተቃዋሚ የኛ የወደፊቱ አገር ገዥ ምን ተሻለክ ታዲያ .. እውነትም ደደብ የሚልህ ወዶ አይደለም
_________________
SEX IS NOT THE ANSWIER, SEX IS THE QUESTION '* YES* IS THE ANSWIER
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ


Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Tue Apr 24, 2012 8:02 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ወገን

ይህንን ቤት ምክንያት አድርጎ ወንድሜ ጥልቁ (በወፍ በረር እንዳነበብሁት ) በተለይም ከአማራ (አማርኛ ተናጋሪ ) ማህበራዊ ፖለቲካዊ ስነ ልቦና ጋር የተያያዘ የራሱን አስተያየት አስቀምጧል :: እኔ ወንድሜ ጥልቁን የምጋራው የምለይበትን ሀሳብም ቀስ ብየ እገልጻለሁ :: ነገር ግን በጥልቁ ጥልቅ ጽህፈት ውስጥ ካነበብሁት በመነሳት ለጊዜው አንድ ነገር ማለትን ወደድሁ :: ምናልባት አንባቢያን ከተረዳችሁኝ እኔ ቴዎድሮስ ካሳሁንን (ቴዲን ) የተቸሁት ከኢትዮጵያዊነቱ ወይም ስለ ኢትዮጵያ በድምጹ (በሙዚቃው ) ሊያስተላፈው ከፈለገው መልዕክት አንጻር አይደለም :: እኔ እሱን እያወዳደርኩትና እየተቸሁትም ያለሁት በተለይም ከግጥሞቹ ብስለት እደግመዋለሁ ከግጥሞቹ ብስለት ወይም ጥልቀትና ከተሰጠው አጉል መደነቅ በሉት መሞገስ አንጻር ነው ....ይህንንም ለመግለጽ ነበር በኪናዊ ጥልቀቷ ከማይወዳደራት እጂጋየሁ ሽባባው (ጂጂ ) ጋር ያወዳደርኩት Exclamation እንጂ አርዕስተ ጉዳይ በማንሳት ጉዳይ አይደለም :: ጂጂም ቴዲም ስለ ኢትዮጵያ ገጣሚዎች አንጎራጓሪዎች ናቸው :: ከርዕሰ ጉዳያቸው አንጻር ቢመሳሰሉም ከግጥም ጥልቀታቸው አንጻር ግን በፍጹም የማይወዳደሩ ናቸው ነው ያልኩት :: እንጂ የቴዲን ኢትዮጵያዊነት መጠራጠሬም አይደለም :: ጥልቁ ባነሳህው አማራ ዙሪያ ግን የራሴ የምለው ይኖረኛል እመለሳለሁ ::ልጅ ሞንሟናው
_________________
http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሓየት 11

ዋና አለቃ


Joined: 06 Apr 2008
Posts: 2792
Location: ላን'ሊይ

PostPosted: Tue Apr 24, 2012 8:07 pm    Post subject: Reply with quote

ጥንቅሹ Laughing

ዋርካ ከመምጣቴ በፊት እኮ ነው ... ታታሪ ተማሪ በነበርኩበት ዘመን ... ከፕሮፌሰሬ ጋር አንድ ወረቀት እየሰራሁ ... ነበር :: ... መቼም እንደምታውቀው ... ድፍረት አለች :: ... ያባ መላ ልጆች ሲፈጥረን ... እጅ መስጠት አንወድም አይደል ... ሌሎች ያልደፈሩትን ... ግብዳ ርዕስ መርጬ ... ፕሮፌሰሬን አሜዝ ለማድረግ አሰብኩ :: ... ወደፊት እንጀራ ቢወጣልኝ ብዬ ማለት ነው :: ... ሰውዬው አኳሀኔ ሳያስደንቀው አልቀረም :: ... ድፍረቴ ምናምኔ ማለት :: ... ታድያልህ ... ነገሩን ጀመርኩት :: ... ጀመርኩትና ስጽፈው ... ስንደረደር ለጉድ ነበር ... ግብዳ ግብዳ ሀሳቦችን እያነሳሁ አምቢሼስ ሆኜያለሁ ... የሰዎችን ሀሳብ ስከልስም እንዲሁ ... ከአቅሜ በላይ የሆኑ ከበድ ከበድ የሚሉ ቃላት ነበር የማነሳው ... እየቀጣጠልኩ ቀጠልኩ :: ... ቀጠልኩና ትንሽ እንደተጓዝኩ የጀመርኩትን ድራፍት እንዲያይልኝ ጠየቅኩት :: ... ቅሌቴ Laughing Laughing ... ወንድሜ ሰውዬው ... መንደርደሪያውን ተመስጦ ሲያነብ ቆየና ወደ ዋናው ሀሳብ ሲገባ ... ፊቱን እያየሁት እንዴት እንደለዋወጠው ... አትጠይቀኝ :: ... ትንሽ ገፋ አድርጎ ሲሄድማ በተለይ ... ትዕግስቱን ጨረሰና ... ምንድነው ይሄ ... ሲል አይደነፋብኝም :: ... ያባ መላ ልጅ ... ኩክ ላደርግ የሄድኩትኝ ... ባንዴ በርን አደረገኛ Laughing ... ምንድነው ይሄ ... በኢንግሊዝኛ ነው Very Happy ... "ሻሎ ... ዋይ ዶንችዩ ዲፕ ...&... አድሬስ ዋን ቲንግ አት ታይም " ... አይለኝም :: ... ወንድሜ ... እኔ ድሀ ነኝ ... ኢንግሊዝኛ አላርፍም ... እያልኩ በውስጤ ... ዲፕ ምናምን ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ ሳይገባኝ ወደቤቴ ሄድኩኝ :: ... ሄጄም ሳልጨምር ሳልቀንስ ... ያንኑ ያንቧረቀበትን ድራፍት ... ሳብሚት አደረኩ :: ... ውጤቱን አትጠይቀኝ ... ገና ወደፊት ልጆቼም ... ይጨሱበታል Laughing

እናልህ ጥልቅሻ ... ከስድስት አመታት ብኋላ ... ፕሮፌሰር .... ዲፕ ... ሲለኝ ምን ማለቱ እንደሆነ የገባኝ ዛሬ ባንተ ጽሁፍ ነው Laughing Laughing ... ስንት ... ስትንደረደር ... ያዙኝ ልቀቁኝ ስትል ሰንብተህ ... ያንንም ያንንም ... ነካክተህ ... ግን ደግሞ አንድ ወጥ የሆነ ምንም አይነት ... ዒላማም ይሁን ይዘት ሳይኖረው ... ስንት ቃላት በከንቱ ፈጀህ :: ...

ሲጀመር ለምን "አማራ " Question አንዳንድ ያነሳሀቸው ከግለሰብ ጋር የተያያዙ ችግሮች ... አማራ የምትለውን ማህበረሰብ እንዴት ነው የሚወክሉት Question ... ሲጀመር የቴዲንም ሆነ የታማኝን ስም የማጥፋት ስራ ... ማን እንደጀመረው ... ታውቅና ነው ... "አማራን " የምትወርፈው Question ... እንደምታስታውሰው ... እስከ ቅርብ ጊዜ ሳስብህ ... አክራሪ ኢትዮጵያዊነትን ... በየዋሆች ላይ ለማስረጽ የተጎለትክ ... ጉልት ትመስለኝ ነበር :: ... ተሳስቼያለሁ Question .... ታስታውሳለህ አይደል እኔና አንተ ለመጀመሪያ ጊዜ ... በዋርካ ሀይለቃል የተሞላበት ውይይት ስናደርግ ያልኩህን Question "ውሀ ውስጥ የሚያልበው ትውልድ "... እያልክ እንደዛሬ አፍህን ስታሾል ... ያልኩህ ... "ስከታተልህ ነበር ... የማንም ስራ አይጥምህም ... የግንቦት 7 አይጥምህም ... የግለሰቦች እንቅስቃሴ አይጥምህም ... የሌሎች ተቃዋሚዎች እንቅስቃሴም አይጥምህም ... ዛሬ ደግሞ ትውልድን ትሳደባለህ " ... ስልህ አስታወስከኝ Question ... ሁሉንም ለማውገዝ የተጎለትክ ሰው ነበረክ :: ... በሂደት ግን ... ያንተን ባህሪ እኔ ላይ ለጠፍክና ... ተቃዋሚን ለማሳቀቅ ነው እዚህ ያለሀው አልከኝ ... Laughing Laughing ... ቀጠልክና ደግሞ ... በርካታ ደደብ ዋርካዊያንን ... በአክራሪ ኢትዮጵያዊነት ... ለማጥመቅ በቃህ :: ... አክራሪ ኢትዮጵያዊነት ... ማለት ... "ኢትዮጵያ ከትግራይ ውጪ "... ማለት ሲሆን ... ከእኛ በላይ ኢትዮጵያዊ ላሳር ... የሚሉ ደደብ ሰዎችን ለመፍጠር የተነዛ ስራ ነበር :: ... ዛሬ .. እንደሞንሟናው አይነቱን ...ጅል ሰው ... አሳስተህ በጠበልህ ካጠመቅከው ብኍላ ... ተመልሰህ እንዲህ ልታዋክበው ማለት ነው Laughing Laughing

እስኪ ያኔ ሻሎ ሲለኝ ፕሮፌሰሬ ዛሬ የገባኝ እንዴት እንደሆነ በአንድ ምሳሌ እላሳይህ ...

Quote:
አንድ የማይካድ ሃቅ ቢኖር ኢትዮጵያዊ ማንነት በኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ላይ የታነጸ መዝገብ ነው። በአገሪቱ የተፈራረቁት ነገስታትም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት የተቀቡ ነገስታት ነበሩ። እነኝህ ነገስታቶችም ወደ አማራነት እንደሚያደሉ የማይካድ ሃቅ ነው። (HOW?? Rolling Eyes )ታዲያ አገሪቱን ሲገዙ እና ሲገዘግዙ የኖሩት በመጸሃፍ ቅዱስ ጥቅስ ሲሆን መጽሃፉን ለማያነቡት አማኒያን የሚጠቅስላቸው ግን ተገዥነትን አሜን ብሎ ስለመቀበል ብቻ ነበር። (HOW IS THIS RELATED TO AFRO-AMERICAN STORY? Laughing ) ያማ ባይሆን አፍሪካ -አሜሪካውያንን ነጻ ያወጣ መጸሃፍ ቅዱስ ኢትዮጵያውያንን ነጻ ማውጣት ባልተሳነው። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ አገዛዝን የሚቃወም የመጸሃፍ ቅዱስ አስተማሪ ብቅ ብሎ የማያወቀውም (ARE YOU SURE?? Laughing ) ለመጽሃፉ በቀረበ ቁጥር ለአገዛዙ የበለጠ ስለሚቀርብ ነበር። ታዲያ ክርስቲያን ወገኑን ረግጦ የገዛው ነግስታት ሁሉ ዘግይተውም ቢሆን ከአፄ ዩሃንስ በስተቀር እስልምና በአገሪቱ እንዲንሰራፋ ለመፍቀድ ግን ደንታ አልነበረው። (ሙስሊም ከሆኑም ተረራግተው ያንብቡኝ ) (WHAT IS THE POINT HERE? Question )
ታዲያ ለሌላው ክርስቲያን ተገዥው የማይፈቅደውን አንድ አምላክ የማምለክ ነጻነት ለሙስሊሙ ግን ቁራንን በነጻ የመማር ነጻነት ሰጠው። አንዳንዴ ሳስበው ስጋን እያስገዙ መንፈሳቸውን ለአንድ ፈጣሪ ሰጥተው ከኖሩት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን እና ስጋውንም መንፈሳዊ ህይወቱም ከመጸሀፍ ቅዱስ ውጭ ሆኖ ከኖረው ክርስቲያን የበለጠ ተበዳዩ ማን እንደሆነ እራሴን ያጠያይቀኛል [ (AGAIN, WHAT IS THE POINT HERE Question Question Question Question Question ... ) የዚህ ጽሁፍ አላማ ግን እምነትን በምሳሌ ተጠቅሞ የአማራውን ፖለቲከኛ ለመጎንተል ስለሆነ ልቀጥል። እናም ፣የአማራው ፖለቲከኛ ከላይ “አንድ ኢትዮጵያ” ከሚለው በተቃርኖ ልቦናው ለሌላ እምነትና ሌላው ዜጋ ምን ያህል እንደሚከፈት የማስተውልበት ድክመቱ ደግሞ ይገርመኛል። ለምሳሌ ቴዲ አፍሮን ኢትዮጵያዊነቱ ያልተሟላ አድርጎ የሚሟገተው የአማራ -ፖለቲከኛ አሊ ቢራ “ኢትዮጵያ” ብሎ እንደገና ቢዘፍን ከከማል ገልቹ እኩል እንደሚዘምርለት እርግጠኛ ነኝ። ስለዚህ በመጀመሪያ ደረጃ ያለውን አጥብቆ ሳይዝ ሌላ ሊጨብጥ ቢሞክር ተራ ተግባር ነው። የሰሞኑን የፈረንሳይ ምርጫም ይህን ያሳያል (TEW BAKIH Laughing ) ሳርኮዚ የመጀመሪያውን ዙር ምርጫ በሶሻሊስቱ በተሸነፈ በማግስቱ የድጋፍ ተማጽኖውን እያደረገ ያለው ፍጹም የፖለቲካ አቅጣጫው ከሱ የራቀውን የቀኝ ክንፍ ፓርቲ ነው። አማራው ግን አማራን ንቆ ነው ኦሮሞና ደቡብ -ምስራቁን ለመጠቀም የሚሞክር። (TELL US HOW?)


ስቱን ረገጥከው :: ስንቱን ቦጫጨከው :: ስንቱን እርስ በእርሱ አባላሀው ::

1. ለአማራ ያደላ ነበር ትላለህ ... ደግሞም ገዘገዘው ትላለህ
2. ክርስትያኑ ፕሪቭሌጅድ ነበረ ለማለት በሚመስል መልኩ ...
ክርስትያኑ የሚያምንበት መጽሀፉ እየተገለጠለት ይገዛ ነበር ስትል ... ሌላው የሚጠቀስለት ግን መገዛቱን አሜን ብሎ እንዲቀበል ነበር ... ትልና ... ወረድ ብለህ ደግሞ ... ክርስቲያኑን በዝብዘው ... ሙስሊሙን ሀይማኖቱን እንዲያስፋፋ አደረጉት ... የሚል አይነት አቤቱታም ታቀርባለህ ... ምን እንበልህ ታድያ Question ... እንደምሳሌ የጠቀስከው ይህ ተራ አንቶ ፈንቶ ... ከጽሁፉ አላማ ጋር (አላማ ካለው ማለት ነው Laughing ) ምንድነው የሚያገናኘው Question

3. ይሄ ሁላ ዝባዝንኬ የአማራው ፖለቲከኛ ከምትለው ጋር ምንድን የሚያገናኘው ... ከዛሬው የቴዲ ጉዳይስ ምንድነው የሚያገናኘው ? ............. መልሱን እኔ ልንገርህ ... ምንም ...

4. ስሞትልህ ... የፈረንሳዩን ምርጫ ... ምን አመጣው ከዚህ Question ...

ለማንኛውም ጥንቅሹ ... አሁንም የሚያጨበጭቡ አይጠፉምና ... ግፋበት Wink Laughing

እኔ ግን አልደብቅህም ... ትዝብቴን ባጭሩ ነው የምንገርህ ... በሁለት ክፍል ያቀረብከውን ጠቅላላ ሀሳብ ይቅርና ... በአንድ አንቀጽ ላይ ያቀረብካቸውን ሀሳቦች ማያያዝ አቅቶኛል ... ሲፈጥረኝ ደደብ ሆኜ ሊሆን ይችላል Laughing ... which is 99.96% unlikely Laughing ... ነገር ግን ማያያዝ አልቻልኩም :: ... አንዲት የተረዳኋት ነገር ብትኖር ... አማራ ላይ ማነጣጠርህና ... ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ሳይል መጀመሪያ ራሱንን "አማራን " እንዲሆን ነው ... ስትንደረደር ደግሞ ... አማራ ማነው የሚለውን ጥያቄ ... ጋርቤጅ ከተህዋል Laughing

ይልቅ ኤሎና የምትባለውን ሰው አስታወስከኝ ... ቀና በል አማራ ... ብላ የጻፈችው ሴት ማለት ነው ... "ጠረኗን " እዚህ ዋርካ የማውቀው ይመስለኛል Wink ...:: ምን አለች ኤሎና ... በክፍል አንድ ቅርሻቷ ማለት ነው ... አማራን በአማራነቱ እንዲደራጅ ... እንደጉድ በስሜት ከለቀለቀች ብኋላ .... በሁለተኛው ቅርሻቷ ... ከአንባቢዎች ለቀረበላት ... በዘር መደራጀት ምን ይጠቅማል ... ለሚል ጥያቄ ... መልስ ስትሰጥ ... ትንፋሽ አጠራት :: ... ትንፋሽ አጥሮት የተናገረችውንም አስታውሳለሁ ... በአማራነት ከተደራጀ ብኍላ ራሱ ህዝቡ ወይም አመራሩ ነው ... በዘር መደራጀት ይበጀናል ወይስ በአንድነት የሚለውን ጥያቄ የሚመልሰው ... ነበር ያለችው Laughing Laughing እንዳንተ የምትጽፈውን የምታውቅ አይመስለኝም ... እና ባጭሩ ... እንዲህ አይነት ከብቶች ... እንዲህውም አሳሳቾችና ... እስስቶችም አላችሁ ለማለት ነው ::

ሓየት
አንድ ላገሩ
_________________
An eye for an eye, and the whole world would be blind. (KGK)
>>>>>>>>> ገዛ ሓየት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5  Next
Page 3 of 5

 
Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum


Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia