WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ኢዴፓ የአፍሪካ ሊበራሎችን ስብሰባ ሊያስተናግድ ነው
Goto page 1, 2, 3  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ቀደምት

ዋና ኮትኳች

Joined: 20 Feb 2006
Posts: 654

PostPosted: Sun Apr 29, 2012 1:30 pm    Post subject: ኢዴፓ የአፍሪካ ሊበራሎችን ስብሰባ ሊያስተናግድ ነው Reply with quote

የአፍሪካ ሊበራሎች ስብሰባ በመዲናችን :
http://ethiofact.com/index.php/ethiopian-news/ethiopian-news/3347-ethiopian-democratic-party-edp-to-host-international-meeting-in-addis-ababa

Idea
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
በይሉል

ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Sep 2004
Posts: 1115
Location: Beylul-60km North of Assab.

PostPosted: Sun Apr 29, 2012 10:22 pm    Post subject: Re: ኢዴፓ የአፍሪካ ሊበራሎችን ስብሰባ ሊያስተናግድ ነው Reply with quote

ቀደምት እንደጻፈ(ች)ው:
የአፍሪካ ሊበራሎች ስብሰባ በመዲናችን :
http://ethiofact.com/index.php/ethiopian-news/ethiopian-news/3347-ethiopian-democratic-party-edp-to-host-international-meeting-in-addis-ababa

Idea

ሰላም ቀደምት

በአሁኒቱ ኢትዮጵያ ኢዴፓ ምን አይነት ተጨባጭ ስራ መስራት ይችላል .
ቀላጤ እያወጡ ይህን ብለን ነበር ---ያንን ብለን ነበር ከማለት ዉጪ ኢዴፓ የወያኔ አሻንጉሊት ከምሆን ያለፈ ሚና አይኖረዉም .
ህወሀትን ዲሞክራት አታስመስሉ !!!!
በህወሀት አገዛዝ ከዘርህ ዉጪ ምንም አይነት ምክንያታዊነት የለም !!!

ኢዴፓ ሀገራዊ ትግሉን እየገደለው ነው .!!

ኢዴፓ ከቅንጂት በሁዋላ ምንም የሚጫወተው ሮል አልነበረም .

ኢዴፓ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም እራሳቸዉን በጉባኤ በትነው ትግሉን ለራሱ ለህዝቡ ይትዉለት !!

የህዝቡን ትግል በምክንያታዊነት እና በሊበራልነት አታውገርግሩት !!

የኢዴፓን አድራሻ ማግኘት ስላልቻልኩ እንጂ ባገኝ ይህንን ሀሳቤን በዝርዝር ጽፌ ለልደቱ ባእጁ እንዲደርስ ማድረግ ፍላጎት አለኝ .

አሁን ኢዴፓ እያደረገ ያለው የአሻንጉሊት ሚና እየተጫወቱ ህወሀትን ለሌላ 20 አመት እያመቻቹት ነው .

እና እንዲህ አይነቱን ቀልድ አቁማቺሁ ትግሉን ለባለቤቱ ተዉለት .

በይሉል ...የህዝቡን ትግል ማንም መተካት አይችልም -ብሎ የሚያምነው
_________________
*The hardest thing about any political campain is how to win without proving that you are unworthy of winning!! E.stevenson

*Even if you win the rat race,you are still a rat!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዲጎኔ

ዋና አለቃ

Joined: 19 Aug 2005
Posts: 4216
Location: united states

PostPosted: Mon Apr 30, 2012 8:29 am    Post subject: Re: ኢዴፓ የአፍሪካ ሊበራሎችን ስብሰባ ሊያስተናግድ ነው Reply with quote

በይሉል እንደጻፈ(ች)ው:
ቀደምት እንደጻፈ(ች)ው:
የአፍሪካ ሊበራሎች ስብሰባ በመዲናችን :
http://ethiofact.com/index.php/ethiopian-news/ethiopian-news/3347-ethiopian-democratic-party-edp-to-host-international-meeting-in-addis-ababa

Idea

ሰላም ቀደምት

በአሁኒቱ ኢትዮጵያ ኢዴፓ ምን አይነት ተጨባጭ ስራ መስራት ይችላል .
ቀላጤ እያወጡ ይህን ብለን ነበር ---ያንን ብለን ነበር ከማለት ዉጪ ኢዴፓ የወያኔ አሻንጉሊት ከምሆን ያለፈ ሚና አይኖረዉም .
ህወሀትን ዲሞክራት አታስመስሉ !!!!
በህወሀት አገዛዝ ከዘርህ ዉጪ ምንም አይነት ምክንያታዊነት የለም !!!

ኢዴፓ ሀገራዊ ትግሉን እየገደለው ነው .!!

ኢዴፓ ከቅንጂት በሁዋላ ምንም የሚጫወተው ሮል አልነበረም .

ኢዴፓ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም እራሳቸዉን በጉባኤ በትነው ትግሉን ለራሱ ለህዝቡ ይትዉለት !!

የህዝቡን ትግል በምክንያታዊነት እና በሊበራልነት አታውገርግሩት !!

የኢዴፓን አድራሻ ማግኘት ስላልቻልኩ እንጂ ባገኝ ይህንን ሀሳቤን በዝርዝር ጽፌ ለልደቱ ባእጁ እንዲደርስ ማድረግ ፍላጎት አለኝ .

አሁን ኢዴፓ እያደረገ ያለው የአሻንጉሊት ሚና እየተጫወቱ ህወሀትን ለሌላ 20 አመት እያመቻቹት ነው .

እና እንዲህ አይነቱን ቀልድ አቁማቺሁ ትግሉን ለባለቤቱ ተዉለት .

በይሉል ...የህዝቡን ትግል ማንም መተካት አይችልም -ብሎ የሚያምነው
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቀደምት

ዋና ኮትኳች

Joined: 20 Feb 2006
Posts: 654

PostPosted: Mon Apr 30, 2012 6:12 pm    Post subject: የአፍሪካ ሊበራል ኔትወርክ ስብሰባ በአአ Reply with quote

ሰላም በይሉል
አባባልህ ብዙም ግልጽ አይደለም :: ምንም የፓርቲ ፖለቲካ ትግል አያስፈልግም ነው የምትለው ? ''ትግሉን ለሕዝቡ ተውለት '' ስትል ምን ማለትህ ነው ? ሕዝብ የሚታገለው በድርጅት አማካኝነት አይደለም እንዴ ? ያለ ድርጅቶች ሕዝቡ በምን መልክ ነው የፖለቲካ ትግል የሚያደርገው ? ወደ ጥንታዊ ሕብረተሰብ ሁኔታ እንመለስ ካላልክ በስተቀር በዘመናችን ድርጅቶች በአንድ አገር የፖለቲካ እንቅስቃሴ ላይ የሚኖራቸውን ሚና ለመሰረዝ የሚያስነሳ ነገር በጣም የሚገርም ነው ::

በእኔ እምነት በሐገራችን ብዙ አይነት አስተሳሰቦች ስላሉ እነዚህን አስተሳሰቦችና ፍላጎቶች በማሰባሰብና ቅርጽ በመስጠት ሕዝቡን የሚያስተባብሩና በመሽጨረሻም አብዛኛው ሕዝብ የሚደግፋቸውን አስተሳሰቦች የያዘው ድርጅት የአገር አመራር ቦታውን እንዲይዝ ለማድረግ በግድ የፖለቲካ ድርጅቶች ያስፈልጋሉ :: ስለሆነም ኢዴፓ በዚህ መልክ አገራዊ ራዕዩን ለማሳከት ተደራጅተው ከሚንቀሳቀሱት ፓርቲዎች ውስጥ አንዱ ነው :: በዚህ መሠረት ሰዎች ለሚፈልጉት ድርጅት ድጋፋቸውን የመስጠት መብት አላቸው :: አንተም የምትፈልገውን ድርጅት ወስነህ ድጋፍህን መስጠት ትችላለህ እንጂ ይኸኛው ድርጅት ይወገድልኝ ለማለት የምትችል አይመስለኝም ::

ኢዴፓ ግልጽ ፕሮግራም አውጥቶ በአደባባይ የሚሰራ ድርጅት ስለሆነ ትችት /አስተያየት ወይም ድጋፍ /ተቃውሞ ካለህ ለፓርቲው ካልሆነም ሥርዓት ባለው መልክ በሚዲያ ለማቅረብ ትችላለህ :: በኔ አስተሳሰብ በብዙ ችግሮችም ውስጥ ሆነው የፓርቲው ሰዎች የተሻለ የፖለቲካ ሥርዓት ለመገንባት የሚያደርጉት ጥረት ሊደነቅ የሚገባው ነው :: ፓርቲው በሀገሪቱ አይን -ገላጭ የሆኑ መሪ አስተሳሰቦች ጀማሪ ስለሆነ እየተጫወተ ያለው ሚና ድጋፍ የሚያሰጠው ነው እንጂ እንዲጠፋ የሚመኙት አይደለም :: የኢዴፓን ታሪክና የሚመራበትን አስተሳሰቦች በሚገባ ለመረዳት ሞክር :: የድርጅቱ ድረ -ገጽ በጣም ብዙ ያስተምራል :: ለምሣሌ ከላይ ያመጣሁልህን ዜና ተመልከት :: ድርጅቱ በሐገራችን ሚደረገውን የሊበራል አስተሳሰብ ትግል ዓለም -አቀፍ ገጽታ እንዲያገኝ አንድ ርምጃ በመራመድ ላይ ነው ::

Idea
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ከስደተኛው

ኮትኳች

Joined: 25 Sep 2006
Posts: 258
Location: zxcvb

PostPosted: Mon Apr 30, 2012 8:32 pm    Post subject: Reply with quote

እንደነ መድረክ አይነቶቹ ተቃዋሚዎች በአደባባይና በአዳራሽ ውስጥ አይደለም በቢሯቸው ውስጥ ስብሰባ የማድረግ ፈቃድ እየተከለከሉና ከህዝብ ጋር እንዳይገናኙ እየታገዱ ባለበት ወቅት ኢዴፓ እንዲህ አይነት ስብሰባ እንዲያዘጋጅ ፈቃድ ሊሰጠው ቻለ ? . ይህ ስብሰባስ ወያኔን በሌላው አለም ዴሞክራት ነው ለማሰኘት ከመንደርደር ውጭ እየተገፋ ላለውና ኢዴፓ ቆሜለታለሁ ለሚለው ለምስኪኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ምን የሚፈይደው ነገር ይኖራል ? በርግጥ እነልደቱ ከዚህ ዝግጅት የሚያገኙት ዳጎስ ያለ ገንዘብ እንዳለ ከማንም የተሰወረ አይደለም።
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቀደምት

ዋና ኮትኳች

Joined: 20 Feb 2006
Posts: 654

PostPosted: Mon Apr 30, 2012 8:49 pm    Post subject: Reply with quote

ስደተኛ :- ኢዴፓ አሁን ለአሉባልታ ጊዜ የለውም :: የሚችለውን መስራት ብቻ ነው የሚፈልገው :: አንተ በሚያዝናናህ ፍልስፍና መዳከር ትችላለህ :: ስለጉዳዩ ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለግህ ደግሞ ከአገርቤት ጋዜጦች ለማግኘት ትችላለህ :: ለምሣሌ ይኸንን ተመልከተው :
http://www.ethiopianreporter.com/news/293-news/6153-2012-04-28-10-30-01.html
Idea

ከስደተኛው እንደጻፈ(ች)ው:
እንደነ መድረክ አይነቶቹ ተቃዋሚዎች በአደባባይና በአዳራሽ ውስጥ አይደለም በቢሯቸው ውስጥ ስብሰባ የማድረግ ፈቃድ እየተከለከሉና ከህዝብ ጋር እንዳይገናኙ እየታገዱ ባለበት ወቅት ኢዴፓ እንዲህ አይነት ስብሰባ እንዲያዘጋጅ ፈቃድ ሊሰጠው ቻለ ? . ይህ ስብሰባስ ወያኔን በሌላው አለም ዴሞክራት ነው ለማሰኘት ከመንደርደር ውጭ እየተገፋ ላለውና ኢዴፓ ቆሜለታለሁ ለሚለው ለምስኪኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ምን የሚፈይደው ነገር ይኖራል ? በርግጥ እነልደቱ ከዚህ ዝግጅት የሚያገኙት ዳጎስ ያለ ገንዘብ እንዳለ ከማንም የተሰወረ አይደለም።
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አስትውል

ኮትኳች

Joined: 20 Mar 2004
Posts: 266

PostPosted: Tue May 01, 2012 2:23 am    Post subject: Reply with quote

Quote:
ኢዴፓ ግልጽ ፕሮግራም አውጥቶ በአደባባይ የሚሰራ ድርጅት ስለሆነ ትችት /አስተያየት ወይም ድጋፍ /ተቃውሞ ካለህ ለፓርቲው ካልሆነም ሥርዓት ባለው መልክ በሚዲያ ለማቅረብ ትችላለህ :: በኔ አስተሳሰብ በብዙ ችግሮችም ውስጥ ሆነው የፓርቲው ሰዎች የተሻለ የፖለቲካ ሥርዓት ለመገንባት የሚያደርጉት ጥረት ሊደነቅ የሚገባው ነው :: ፓርቲው በሀገሪቱ አይን -ገላጭ የሆኑ መሪ አስተሳሰቦች ጀማሪ ስለሆነ እየተጫወተ ያለው ሚና ድጋፍ የሚያሰጠው ነው እንጂ እንዲጠፋ የሚመኙት አይደለምየሚገባው ይገባውል እንዲገባው የማይፈለግ ደግሞ ባለህበት እርገጥን ይቀጥላል ለማንኛውም መልሱ በጣም አመርቂ መልስ ነው
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
በይሉል

ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Sep 2004
Posts: 1115
Location: Beylul-60km North of Assab.

PostPosted: Tue May 01, 2012 2:35 am    Post subject: Re: የአፍሪካ ሊበራል ኔትወርክ ስብሰባ በአአ Reply with quote

ቀደምት እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም በይሉል

አባባልህ ብዙም ግልጽ አይደለም :: ምንም የፓርቲ ፖለቲካ ትግል አያስፈልግም ነው የምትለው ? ''ትግሉን ለሕዝቡ ተውለት '' ስትል ምን ማለትህ ነው ? ሕዝብ የሚታገለው በድርጅት አማካኝነት አይደለም እንዴ ? ያለ ድርጅቶች ሕዝቡ በምን መልክ ነው የፖለቲካ ትግል የሚያደርገው ? ወደ ጥንታዊ ሕብረተሰብ ሁኔታ እንመለስ ካላልክ በስተቀር በዘመናችን ድርጅቶች በአንድ አገር የፖለቲካ እንቅስቃሴ ላይ የሚኖራቸውን ሚና ለመሰረዝ የሚያስነሳ ነገር በጣም የሚገርም ነው ::

በእኔ እምነት በሐገራችን ብዙ አይነት አስተሳሰቦች ስላሉ እነዚህን አስተሳሰቦችና ፍላጎቶች በማሰባሰብና ቅርጽ በመስጠት ሕዝቡን የሚያስተባብሩና በመሽጨረሻም አብዛኛው ሕዝብ የሚደግፋቸውን አስተሳሰቦች የያዘው ድርጅት የአገር አመራር ቦታውን እንዲይዝ ለማድረግ በግድ የፖለቲካ ድርጅቶች ያስፈልጋሉ :: ስለሆነም ኢዴፓ በዚህ መልክ አገራዊ ራዕዩን ለማሳከት ተደራጅተው ከሚንቀሳቀሱት ፓርቲዎች ውስጥ አንዱ ነው :: በዚህ መሠረት ሰዎች ለሚፈልጉት ድርጅት ድጋፋቸውን የመስጠት መብት አላቸው :: አንተም የምትፈልገውን ድርጅት ወስነህ ድጋፍህን መስጠት ትችላለህ እንጂ ይኸኛው ድርጅት ይወገድልኝ ለማለት የምትችል አይመስለኝም ::

ኢዴፓ ግልጽ ፕሮግራም አውጥቶ በአደባባይ የሚሰራ ድርጅት ስለሆነ ትችት /አስተያየት ወይም ድጋፍ /ተቃውሞ ካለህ ለፓርቲው ካልሆነም ሥርዓት ባለው መልክ በሚዲያ ለማቅረብ ትችላለህ :: በኔ አስተሳሰብ በብዙ ችግሮችም ውስጥ ሆነው የፓርቲው ሰዎች የተሻለ የፖለቲካ ሥርዓት ለመገንባት የሚያደርጉት ጥረት ሊደነቅ የሚገባው ነው :: ፓርቲው በሀገሪቱ አይን -ገላጭ የሆኑ መሪ አስተሳሰቦች ጀማሪ ስለሆነ እየተጫወተ ያለው ሚና ድጋፍ የሚያሰጠው ነው እንጂ እንዲጠፋ የሚመኙት አይደለም :: የኢዴፓን ታሪክና የሚመራበትን አስተሳሰቦች በሚገባ ለመረዳት ሞክር :: የድርጅቱ ድረ -ገጽ በጣም ብዙ ያስተምራል :: ለምሣሌ ከላይ ያመጣሁልህን ዜና ተመልከት :: ድርጅቱ በሐገራችን ሚደረገውን የሊበራል አስተሳሰብ ትግል ዓለም -አቀፍ ገጽታ እንዲያገኝ አንድ ርምጃ በመራመድ ላይ ነው ::

Idea

ስማ ቀደምት !!!
ከላይ መልስ የሚመስሉ ማዘናጊያ ሀሳቦቺህን አንበብኩዋቸው .....እዉነት እልሀለሁ ኢዴፓ እዉነተኛ የህዝብ አክብሮት ካለው ራሱን በፈቃደኝነት ወደ ሲቪክ ማህበርነት መልወጥ ካልሆነም በጉባኤ ማፍረስ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚጠብቀው ታላቅ ጉዳይ መሆኑን ልነግርህ እወዳለሁ . ምናልባት የአቁዋም መግለጫዉን አሳየኝ በማለት ልትጠይቀኝ እና ልታፋጥጠኝ ትቺላለህ .
ይሄ ህዝብ እኮ በልዩ ልዩ መልክ ልወያኔም ሆነ ለእናንተ በሚገባ ገልጾላቺሁዋል .አይን እና ጆሮ ግን እንዳላቺሁ እኛም እናንተም እናዉቃለን .ግን አልሰማቺሁበትም ...አላያቺሁበትም !!!!

ምክንያት በለለበት ምክንያታዊ እንሁን !!
ጨካኝ /ዘረኛ አምባገነን ባለበት ሊበራል እንሁን !!!!

ይታይሀል ምን ያህል እንደዘቅጠ ---ኢዴፓ !!!

ከላይ መሰረታዊ የሚመስሉ ጥቂት ነጥቦችን አንስተህ መልስ ያልሰጠሁት ኢዴፓ 60% የድርጂቱ አባላት በወያኔ የተሰገሰጉ ሰላዮች ስለሆኑ ምን ይፈይዳል ብየ ነው ይምደክመው ?

አሁን እኮ ኢዴፓ ዉስጥ ምናልባት ጥቂት አገርወዳዶች ሊኖሩ ይችላሉ ብየ ባምንም ህልዉናቸው በየቀኑ አደጋ ላይ ስለሆነ ድርጂቱን አፍርሰው ወይ ሰላማዊ ዜጋ ወይ ደግሞ በቦሌ /ደወሌ
በጊዜ ጥጋቸዉን መያዝ አለባቸው ብየ አምናለሁ .አሁን ህወሀት እናንተን የሙጥኝ ይዞ አንዴ በሊበራልነት ሌላ ጊዜ በምክንያታዊነት እስክስታ እንድትወርዱ የሚፈቅድላቺሁ ያለምክንያት አይደለም !! ይቺን ምክንያት ነው በሚገባ ፈልፍላቺሁ ማወቅ የሚገባቺሁ እንጂ ዘረኝነትን በምክንያታዊነት እንዋጋለን በማለት እራስቺሁንም ሌላዉንም አታጃጂሉ !!!! 20 አመታቺሁ !!!

እዉነቱን ልንገርህ ከአንድ ኢዴፓ ይልቅ 1000 የህወሀት ድርጂት ስልጣን ላይ ቢቀመጡ ይሻለኛል .
የእናንተ መኖር የአገዛዙን ጨካኝነት እና አውሬነት
ስለሚደብቀው እና የአለም ሊብራሎቺን ለአሸሼ ገዳሜ ጠራን በማለት ስለምታደናግሩን የእናንተ አለመኖር ለህዝባቺን ፍትህ እና እርትእ መምጣት ታላቅ ዋስትና እየሆነ ነው .......ስለዚህ አደባባዩን ለራሱ ለህዝቡ ልቀቁለት .......

ይህ አስተያየቴ መድረክ ተብየዉን አስቂኝ ስብስብ ይመለከታል !!!ብትፈልጉ አንድ ላይ ተዋህዳቺሁ እንደሜጫና ቱለማ አይነት ሲቪክ ማህበር መስርቱና
ምርጫ በመጣ ቁጥር በሌለ ዲሞክራሲ ስነምግባር እያላቹሁ አትጎናበሱ !!!!

እዉነት እልሀለሁ .....;በህዝቡ ትግል ላይ ቀዝቃዛ ዉሀ እየቸለሳቺሁበት ነው !!!!
በህዝቡ ሀቀኛ ትግል ላይ ደንቃራ ሆናቺሁበታል !!!
በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ሊበራል አመለካከት ልታሰፍኑ መሞከራቺሁም ገና ጮርቃ መሆናቺሁን ነው የሚያረጋግጠው .....

ሰወች በጎሳ ማንነታቸው ----በፖለቲካ አስተሳሰባቸው
መረገጥ ብቻ ሳይሆን ደብዛቸው በሚጠፋባት የአሁኒቱ ኢትዮጵያ ሊበራልነት አድርባይነት እና አፋሽ አጎንባሺነት ብቻ ነው .የህዝቡን የልብ ትርታ ጠንቃቺሁ አታውቁትም .....አላወቃቺሁትም .....

በእንዲህ አይነት የገማ የገለማ ጨቁዋኝ መንግስት ስር ሊበራል ነን ብሎ መጻደቅ እና መፍጨርጨር
ኢዴፓን ልብ የለለው ወኔቢስ ስብስብ መሆኑን ነው በይፋ የሚያረጋግጠው ......

እና ወንድሜ ሆይ !!!
ጥረታቺሁን እና ድካማቺሁን እውቅና እንድንሰጥ እና በታሪክ ዉስጥም የሚገባቺሁን ስፍራ እንድትይዙ ከፈለጋቺሁ ይቺን የቁጩ ሊበራልነት እና ምክንያታዊነት ቁጭ አድርጉና ትግሉን መበረዝ -መከለሱን አቁሙ !!!!!

ከሰላምታ ጋር .
_________________
*The hardest thing about any political campain is how to win without proving that you are unworthy of winning!! E.stevenson

*Even if you win the rat race,you are still a rat!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ናፖሊዮን ዳኘ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 18 Apr 2008
Posts: 1878

PostPosted: Tue May 01, 2012 3:11 am    Post subject: Re: የአፍሪካ ሊበራል ኔትወርክ ስብሰባ በአአ Reply with quote

Idea Idea ኢዴፓ ገብቶሀል ::

ሕዝቡ አይንህን ለአፈር ቢለውም ህወሀት እና የምዕራቡ ዓለም ድጋፍ ያለው ድርጂት ነው :: ለይቶላቸው ባንዳነትን አዘምነው በዚያ መልክ የሚንቀሳቀሱ ናቸው Idea

በኢትዮጵያም ከኢትዮጵያ ውጪም ያለውን ኢትዮጵያን በምክንያታዊነት ስም በሰላሳ ብር አሳልፎ ሊሸጥ ሌት ከቀን ለውጪው ሰው የሚሰራውን ሰው ቁጥር ባየሁ ቁጥር --- እነዚያ የሚመጣው ትውልድ ውል ያለው እና ክብር የሚያውቅ መስሏቸው ለሀገራችን ነጻነት የተራቡ የተጠሙ እና ህይወታቸውን አሳልፈው የሰጡትን ብርቅ የኢትዮጵያ ልጆች እያሰብኩ ከልብ አዝናለሁ ::

አሁን የተያዘው እኮ ባንዳነትን ራሺናላይዝ ማድረግ ነው Idea በማይገባ ፍልስፍና ልባችንን ማውለቅ ! ከህወሀት እኩል አብዮት ሊፋፋምባቸው የሚገባ ሀይሎች ናቸው በኢዴፓ ዙሪያ የተሰበሰቡት ---የአፈ ጮሌ ባንዳ መዐት ?? መለስን ለምንድን ነው የምንጠላው ?? በህወሀት ጥላ ከሚያራምደው የባንዳነት እና የዘረኝነት ተልዕኮ ውጪ ምን የሚያጣላን ነገር አለ ??

ናፖሊዮን ዳኘ ::

ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቀደምት

ዋና ኮትኳች

Joined: 20 Feb 2006
Posts: 654

PostPosted: Tue May 01, 2012 1:29 pm    Post subject: Re: የአፍሪካ ሊበራል ኔትወርክ ስብሰባ በአአ Reply with quote

ወይ ናፖሊዎን ! Very Happy ልክህ የማታውቅ ቂል ነገር ነህ :: እዚህ ብዙ ጊዜ የምትለቀልቀውን አይቻለሁ :: ከዘረኛ አስተሳሰብህ ጋር ለወያኔ የምትቀርበው አንተ እንጂ ኢዴፓን የመሰለ የጠራ አመለካከት ያለው ድርጅት ሊሆን አይችልም ::
Idea
ናፖሊዮን ዳኘ እንደጻፈ(ች)ው:

PostPosted: Tue May 01, 2012 10:32 pm    Post subject: Reply with quote

Quote:
እዉነት እልሀለሁ ኢዴፓ እዉነተኛ የህዝብ አክብሮት ካለው ራሱን በፈቃደኝነት ወደ ሲቪክ ማህበርነት መልወጥ ካልሆነም በጉባኤ ማፍረስ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚጠብቀው ታላቅ ጉዳይ መሆኑን ልነግርህ እወዳለሁ

በይሉል አንድ የፖለቲካ ድርጂት እንዴት ወደ ሲቪክ ማህበርነት እንደሚቀይር በዚች አለም ስምቸም አይቸም አላቅም እስኪ ምሳሌ ጥቀስና አስደርዳኝ ሌላው ህዝቡ የሚጠብቀው ነው ስትል ለዚሁ ከህዝቡ ያገኘህው መረጃ ምንድነው ? እኔ ባልኝ መረጃ ሌላው ይቅር ኢዴፓ የለም በተባለብት 2002 እንኳ ምን ያህል የሕዝብ ደጋፍ ያለው መሆኑን ከታች በምታገኘው ክሊፕ ግንዛቤ መውስድ ትችላለህ ምንም ያህል ይጎምጥጥህ ይህን መርጃ አዳምጥ ትምህርት ታገኛለህ
http://ethiopiandemocraticparty-edp.org/index.php/audiovideo/47-video/284-video-clips-showing-edps-election-campaign-2010
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ደጉ የት ገባ

ኮትኳች

Joined: 22 Feb 2006
Posts: 427
Location: usa

PostPosted: Tue May 01, 2012 10:51 pm    Post subject: Reply with quote

በይሉል ወንድሜ ምነው ምን ነካህ ???
ትግሉን ለሕዝቡ ተውለት ስትል ኢዴፓውያን የሕዝቡ አካል አይደሉም ማለትህ ይሆን ???
ኢትዮጵያዊነትን ሰጭ እና ከልካይ አንተ ሆንክ እኮ !!!
ታሪክ እራሱን የደግማል ይሉሀል ይቺ ናት :: አጼ ሐይለስ ላሴ የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር 500 ነው ያሉትን !!! መሌም እኛ የወርቅ ዘሮች ነን ያለውን :: ሌሎቻችንን የጭርቅ ዘር ማለቱም አልነበር ?? አንተም እኮ .... ይቅር ወንድሜ ::
ናፖሊዮንማ አብዮት ማካሄድ ምናምን ይላል :: የሱ ደሞ በፍጹም የሚያስደምም ነው :: አሁንም ምኞቱ ባሀሳብ ከሱ የሚለዩትን በአብዮታዊ እርምጃ ድራሻቸውን ማጥፋት ነው :: ታዲያ ከወያኔ በምንድነው የምትሻለው ወንድሜ ??? ወያኔዎችም እኮ ስሙን ይቀይሩት እንጂ ህዝብ የሚፈጁትና የሚያፋጁት በዚሁ ፍልስፍና መስሎኝ ::
በተረፈ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላማዊ ትግል አያስፈልግም ማለት አዲስ አይደለም :: 97 ምርጫ ወቅትም የምርጫ ክርክር ሲጀመር ስለ ኤን ነበር ርእሱ ያኔ ቅንጅት ገና አልነበረም :: ውጭ ያለው ተቃዋሚ ሁሉ በምርጫ መወዳደር ወያኔን ዲሞክራት ከማስመሰል የዘለለ ውጤት የለውም እነ ኢዴፓም የወያኔ አጫፋሪዎች ናቸው እያሉ በየደረገጹና ፓልቶኮ ያዙኝ ልቀቁኝ እንዳላሉ አፍታም ሳይፈጅባቸው አክፍሮባት ሰርተው በሁዋላ ለምርጫው ገንዘብ አሰባሳቢም የነበሩት እነርሱው መነበራቸው የትናንት ትዝታችን ነው ::
በዚህ አጋጣሚ ከሰላማዊ ትግል ውጭ ያለው መንገድ ነው ለድል የሚያበቃው የምትሉትንም እኔ በግሌ እስኪ በፈጠራችሁ የቤት ስራችሁን በደንብ ስሩና ይህንን ጭራቅ መንግስት ገላግሉን እላለሁ !!!!! ተቃውሞዬ እንደኛ ያላሰበ ሁሉ ጠላት ነው ስትሉ ብቻ ነው ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
በይሉል

ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Sep 2004
Posts: 1115
Location: Beylul-60km North of Assab.

PostPosted: Wed May 02, 2012 12:27 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም አስትዉል

ቅድመ -ቅንጂት እና ድህረ ቅንጂት እዚህ መድረክ ላይ ስንወያይ የነበረዉን ችግር እስታዉሳለሁ .በተለይ አንተ ታደርጋቸው የነብሩትን ክርክሮች በጥቂቱም ቢሆን አስታዉሳለሁ . እንዲያዉም አንድ ወቅት "እኔ አስትዉል "" እንጂ ""አስተዉል "" አይደለሁም በማለት ያቀርበከው ክርክር አይረሳኝም .

እኔ ጸረ -ኢዴፓ አይደለሁም . ለራሱና ለድርጂቱ በማሰብ እንዲሁም ላገር አቀፉ ትግል የሚበጀዉን በማሰብ ነው ራሱን በጉባኤ ያፍርስ ወይም ወይም ወደ ሲቪክነት ይለዉጥ ያልኩት .ምክንያቶቼ አገር በቀል እና መሰረታዊ ስለሆኑ ደግመህ አንባቸው በረጋ መንፈስ .

አስትውል እንደጻፈ(ች)ው:
....አንድ የፖለቲካ ድርጂት ...

ኢዴፓ የፖለቲካ ድርጂት አይደለም !!!!!መስፈርቱን አያሙዋላም .!!!!እንኩዋን ኢዴፓ ሌሎቹ እነ መኢአድ እና መድረክ ምናምን የሚባሉት የፓርቲ ድርጂቶች አይደሉም .ይህን ካልኩ ይበቃኛል .የፓርቲ መስፈርቶች ምንድን ናቸው የሚለዉን ሪሰርች አድርግና አንብብ .

Quote:
አንድ የፖለቲካ ድርጅት እንዴት ወደ ሲቪክ ማህበርነት እንደሚቀይር በዚች አለም ስምቸም አይቸም አላቅም እስኪ ምሳሌ ጥቀስና አስደርዳኝ

ምንም ቺግር የለዉም ...ፈቃደኝነቱ ካለ !!!!!የሀገሪቱን ትንሳኤ የምንፈልግ ከሆነ ትግሉን በሚያኮላሽ አደረጃጀትም ሆነ መዋቅር ተጠምደን እንቅፋት መሆኑን ማቆም ከፈልግን -በዚህም ህዝባቺንን የድሉ እና የስልጣኑ ባለቤት ለማድረግ ከወሰንን እንኩዋን ሲቪክነት ሌላም መፍጠር ይቻላል .ዋናው ግን ፓርቲ ነን እያሉ በሌለ የመድበለ -ፓርቲ ስርአት ዉስጥ እምቡር እምቡር ማለቱን እናቁም እና ህዝቡ እራሱ ወያኔን ይታገላቸው ነው የኔ ጥያቄ !!!

Quote:
ሌላው ህዝቡ የሚጠብቀው ነው ስትል ለዚሁ ከህዝቡ ያገኘህው መረጃ ምንድነው ?

ይህም አንዱ ኢዴፓ ፓርቲ አለመሆኑን በትክክል ያረጋግጥልናል !!! አንድ ድርጂት የህዝቡን የልብ ትርታና ስሜት መገንዘብ ካልቻለ ማፍያ እንጂ ፓርቲ አይደለም .
""ሳንፈልጋቸው ሀያ አመታቸው "" እያሉ አደባባዩን ያጥለቀለቁት ኢትዮጵያን አይዶል መሆኑ ነው ?
ከህዝብ የመነጠላቺሁ ታላቁ ማረጋገጫ የአለም ሊበራሎች ጉባኤ እንዲካሄድ መወሰናቺሁ እና ወያኔን ቁንጂና ሳሎን ዉስጥ ለማኖር መጣደፋቺሁ ነው .ህዝቡን በዘሩ ምክንያት የሚያጎሳቁል ስርአትን በሊበራሊዝም እንታገለዋለን የምትሉት አባዜ የፖለቲካ ጮርቃነታቺሁን ነው በይበልጥ ያረጋገጠልን !!!እየሱስ ክርስቶስ እንኩዋን አይቀበለዉም !!!!

Quote:
እኔ ባልኝ መረጃ ሌላው ይቅር ኢዴፓ የለም በተባለብት 2002 እንኳ ምን ያህል የሕዝብ ደጋፍ ያለው መሆኑን ከታች በምታገኘው ክሊፕ ግንዛቤ መውስድ ትችላለህ ምንም ያህል ይጎምጥጥህ ይህን መርጃ አዳምጥ ትምህርት ታገኛለህ
http://ethiopiandemocraticparty-edp.org/index.php/audiovideo/47-video/284-video-clips-showing-edps-election-campaign-2010

መኖርማ ይኖራል አለ ....ልደቱስ በየክርክሩ ገብቶ እየተናገር አይደለም እንዴ ?
ዋናው ጥያቄየ የህዝቡን ትግል አኮላሻቺሁት ? ደግሞ ህዝቡ ይሞክረው ? ከፊት ለፊቱ ሆናቺሁ አትሞዳሞዱ ?
ህዝቡ አምርሮ እየታገል ባለበት ባሁን ሰአት ሰልፋቺሁን ከህዝቡ ጎን በማድረግ የስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን አበራቱት እንጂ ወያኔ ጫማ ስር እየተንደፋደፋቺሁ አታዋርዱን ነው የምለው !!!!

የህወሀት ፖሊትቢሮ አባላት በር ዘግተው ዉስኪ እየተጎነጩ ሲሳለቁ የሚውሉት በእናንተ እኮ ነው ?
ይሄ እንዴት አይከሰትላቺሁም ?

ለማንኛዉም በዚህ በእናንተ ስብስብ ዉስጥ ጥቂት ሀገርወዳዶች ይኖራሉ ብየ እገምታለሁ .አሁን የማዝነው ለነሱ ነው .ዙርያቸዉን የተከበቡት በነማን እንደሆነ በቅጡ የሚያውቁ አይመስለኝም !!!

ውሎ አድሮ የምንሰማው ብዙ ነገር ያለ ይመስለኛል .

ከሰላምታ ጋር .
_________________
*The hardest thing about any political campain is how to win without proving that you are unworthy of winning!! E.stevenson

*Even if you win the rat race,you are still a rat!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ደጉ የት ገባ

ኮትኳች

Joined: 22 Feb 2006
Posts: 427
Location: usa

PostPosted: Wed May 02, 2012 1:01 am    Post subject: Reply with quote

በይሉሌ እኔ ባለኝ የውስጥ መረጃ ወያኔ በተለይ የሱ ቅምጥ የሆነው የአማራ ድርጅት ነኝ ባዩ በሰለማዊ ትግል ወያኔን መለወጥ ይቻላል ከሚሉትና በሀገር ውስጥ ከሚንቀሳቀሱት ተቃዋሚዎች ሁሉ በተለይ ኢዴፓን ነው የሚፈሩትና እግር በግር የሚከታተሉት ሌሎቹ ሁሉ በነሱ እምነት ለስልጣን የተሰባሰቡና እርስ በርሳቸው ተባልተው የሚያልቁ ናቸው (ይህንን በሂደት ሁላችንም እያየነው ያለው ጉዳይ ይመስለኛል ) ::
በተቃዋሚነት ስም በትጥቅ ትግል እናምናለን የሚሉትም ደመኛ ጠላታቸው ኢዴፓ ነው :: ምክንያቱ ምን እንደሆነ ታውቃለህ ????

ወያኔም ኢዴፓ ምን አይነት የተጠናና ግብታዊ ያልሆነ ለነሱ የማጨናበሪያ የዲምክራሲ ትግል የሚመጥን መልስ እንዳለው በደንብ ስለሚያውቅ ነው :: ( በቅንጅት ዘመን ቅንጅትን ቅንጅት ካስባሉት ፓርቲዎች ውስጥ አንዱ ብቻ ሳይሆን ዋናው ፓርቲ ኢዴፓ መሆኑን አትዘንጋ በዛ ላይ ቅንጅት የሚፎክርባቸው የመታገያ ዶክሜንቶች ሁሉ ከየትም የመጡ ሳይሆኑ ከኢዴፓ ጭንቅላት ውስጥ የፈለቁ ሀብቶች ነበሩ ::
እንደ መስከረም ዝናብ ድንገት በትግሉ ሜዳ ላይ የፈሰሰው የዶክተርና ፕሮፌሰር መአት ሰብስቤያለሁ ባዩ ቀስተ ደመና ሳይቀር ይዞት የመጣው የስልሳዎቹን የጠልፎ መጣል ለሀገር የማይበጅ ተንኮል እንጂ አንድም የመታገያ ዶሴ አልነበረም ::
ስለዚህ ወያኔም የኢዴፓን ጥንካሬ በውል ስለሚያውቅ ለኢዴፓ ተኝቶ አያውቅም ለወደፊቱም አይተኛለትም --- ፍጹም የባህሪ ልዩነት አላቸውና !!!
በመሳሪያ ሀይል ወያኔን እጥላለሁ ባዮቹም የህዝብን ቀልብ ሊስብ የሚችልና እኛ ልናሰልፈው የምንችለውን ሀይል ይጋፋብናል ብለው ስለሚያምኑ ከኢዴፓ ውልደት ጀምሮ ደመኛ ጠላታቸው አርገው ነው የሚያዩት ::
ግን ግን በእርግጠኝነት የምነግርህ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ የኢዴፓ ሀሳብ በስተመጨሻ አሸናፊ እንደሚሆን ነው አትጠራጠር !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ናፖሊዮን ዳኘ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 18 Apr 2008
Posts: 1878

PostPosted: Wed May 02, 2012 1:16 am    Post subject: Reply with quote

እኔ እኮ የማይገባኝ ነገር እንዴት ነው ባንዳነትን ከሀሳብ ልዮነት ጋር የምታገኛኙት ???

ለኢትዮጵያ ጥፋት እየደገሰላት ያለው ዘራፊው የህወሀት ቡድን እኮ ከባንዳነት አስተሳሰብ የበቀለ ድርጂት ነው ?? ድሮ ያለ ይሉኝታውን ተትቶ እንደዕባብ ተቅውትቅጠው ቢያንስ መርዛቸውን ተፍተው መርዝ መርጨት የማይችል እባብ ሆነብ ቢሆን ኖሮ እኮ ትግራይ ውስጥ የነበረውን የአርበኛ ቤተሰብ ጭምር '"በዘር ጭቆና "" አይዲዮሎጂ አያማልሉትም ነበር ::

ኢዴፓ የያዘው በዘር ላይ ያልተደራጀ ከመሆኑ በስተቀር በባንዳነት አንጻር ከህወህት ብዙ የሚለይ አይደለም :: በሊበራሊዝም ኢትዮጵያን ምዕራባዊ ማድረግ ይቻል እደሆነ ነው እንጅ (ያማኙ ህዝብ ልብ ተፈቶ ምዕራባዊ ከሆነ ) ማህበራዊነቱን መገንባት እና ኢትዮጵያን በሚያስቀድም መርህ ላይ የተመሰረተ አስተዳደር ዜጋም ሆነ ስርዐት መፍጠር አይቻልም ::

እስቲ ኢዴፓ በሊበራሊዝም እንደ ህወሀት በኢንቬስትመንት ስም ኢትዮጵያን ለውጭ ሀይሎች ከመክፈት ውጭ እና እነሱን እየተለማመጠ አድርግ የሚሉትን ከሚያደርግ በስተቀር ምን ሊፈይድ ይችላል ?? የተበባሸው የኢትዮጵያ ማህበራዊ ግንኙነት እና የዘቀጠው የሞራል ቫሊዮስ እንዴት ነው በሊበራሊዝም የሚስተካከለው ?? የችግሩ ምንጭ ምን ሆነና ነው ??

ናፖሊዮን ዳኘ ::

ደጉ የት ገባ እንደጻፈ(ች)ው:
በይሉል ወንድሜ ምነው ምን ነካህ ???
ትግሉን ለሕዝቡ ተውለት ስትል ኢዴፓውያን የሕዝቡ አካል አይደሉም ማለትህ ይሆን ???
ኢትዮጵያዊነትን ሰጭ እና ከልካይ አንተ ሆንክ እኮ !!!
ታሪክ እራሱን የደግማል ይሉሀል ይቺ ናት :: አጼ ሐይለስ ላሴ የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር 500 ነው ያሉትን !!! መሌም እኛ የወርቅ ዘሮች ነን ያለውን :: ሌሎቻችንን የጭርቅ ዘር ማለቱም አልነበር ?? አንተም እኮ .... ይቅር ወንድሜ ::
ናፖሊዮንማ አብዮት ማካሄድ ምናምን ይላል :: የሱ ደሞ በፍጹም የሚያስደምም ነው :: አሁንም ምኞቱ ባሀሳብ ከሱ የሚለዩትን በአብዮታዊ እርምጃ ድራሻቸውን ማጥፋት ነው :: ታዲያ ከወያኔ በምንድነው የምትሻለው ወንድሜ ??? ወያኔዎችም እኮ ስሙን ይቀይሩት እንጂ ህዝብ የሚፈጁትና የሚያፋጁት በዚሁ ፍልስፍና መስሎኝ ::
በተረፈ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላማዊ ትግል አያስፈልግም ማለት አዲስ አይደለም :: 97 ምርጫ ወቅትም የምርጫ ክርክር ሲጀመር ስለ ኤን ነበር ርእሱ ያኔ ቅንጅት ገና አልነበረም :: ውጭ ያለው ተቃዋሚ ሁሉ በምርጫ መወዳደር ወያኔን ዲሞክራት ከማስመሰል የዘለለ ውጤት የለውም እነ ኢዴፓም የወያኔ አጫፋሪዎች ናቸው እያሉ በየደረገጹና ፓልቶኮ ያዙኝ ልቀቁኝ እንዳላሉ አፍታም ሳይፈጅባቸው አክፍሮባት ሰርተው በሁዋላ ለምርጫው ገንዘብ አሰባሳቢም የነበሩት እነርሱው መነበራቸው የትናንት ትዝታችን ነው ::
በዚህ አጋጣሚ ከሰላማዊ ትግል ውጭ ያለው መንገድ ነው ለድል የሚያበቃው የምትሉትንም እኔ በግሌ እስኪ በፈጠራችሁ የቤት ስራችሁን በደንብ ስሩና ይህንን ጭራቅ መንግስት ገላግሉን እላለሁ !!!!! ተቃውሞዬ እንደኛ ያላሰበ ሁሉ ጠላት ነው ስትሉ ብቻ ነው ::

_________________
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Goto page 1, 2, 3  Next
Page 1 of 3

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia